24 May 2023
Channel «ኪዳን ዘኢየኡስ» created
Channel photo changed
ኪ
13:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቶሳዊነት

ክርስቶሳዊነት
ማለት ክርስቶስን መምሰል ነው የዓለም ብርሃን የሆነ እርሱን በሰውናታችን ሁሉ ላይ ተቀብሎ እንደ እንቁ ማብረቅረቅ ነው። ይህን ታላቅ ጸጋ እንዴት መግለጽ ይቻላል ሰው እንዴት አምላኩን ሊመስል ይችላል? የምንችለውስ በኛ አቅም አይደለም በእርሱ በእራሱ ላይ ተደግፈን ነው እንጂ ፣ ይገርማል በክርስቶስ ላይ ተደግፎ ወደ ክርስቶሳዊነት መውጣት። እኛማ ምን አቅም አለን ከምድራዊ አዳም ተወልደን በስጋችን ሟቿች ሆነን ፣ ነፍሳችንም ኃጢአትን የምትናፍቅ በኃጢአት ሞት ውስጥ ተከባ ያለች ናት ፣ መልካሙን ከመስራት ይልቅ ሁል ጊዜ ኃጢአትን እንመኛለን ፣ በኃጢአታችንም ምክንያት የሞት ባሮች ሆነናል። ሕይወታችንም በጨለማ ተከቦ የሌሊት አውሬ እንዳይውጠን ፈርተናል። ነገር ግን በዚ ሁሉ ጨለማ ውስጥ እንደ ንጋት ኮከብ የሚያበራልን ብርሃን አለ እርሱም የጠፉ ልጆቹን ሊፈልግ የመጣ የአማልክት አምላክ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። አሮጌው አዳማዊ ማንነታችንን ደምስሶ አዲስ ክርስቶሳዊ ማንነትን ሰራለን ፣ እኛ እንደ ተፈጠርንበት ማንነት መኖር ሲያቅነት የአማልክት አምላክ የእኛን ማንነት ይዞ መጣ ፣ አከበረው ወደ እርሱ ማንነትም አወጣው። ወደ ጨለማ ሕይወታችን ወርዶ የብርሃንን ነጸብራቅ አሳየን ፣ በብርሃናዊ ማንነቱ ወልዶ የብርሃን ልጆች እንባል ዘንድ አድሎናል። ከአዳም የተወለደ ሁሉ አዳማዊ ነው ከክርስቶስ የተወለደ ሁሉ ደግሞ ክርስቶሳዊ ነው ፣ ይህም የሆነው ባሕርያችንን ባሕርይው አድርጎ ባደሰው ሁሉ ከእርሱ እና ስለእርሱ በሆነው በክርስቶስ ነው። ከክርስቶስ ውጪ ሕይወት የለንም ፣ ከክርስቶስ ውጪ ብርሃን የለንም ፣ ከክርስቶስ ውጪ የምንመካበት ማንነት የለንም ።

ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በክርስቶሳዊ ማንነት ይኖር ዘንድ በተጠመቀ ጊዜ ክርስቶስን የመምሰል ጉዞ ጀምሯል ፣ ዘላለም የማያልቅ ረጅም ጉዞ ፣ የመለኮትን ባሕርይ በጸጋ ገንዘብ እያደረጉ ዘላለም የሚጓዙበት ጉዞ ። በዚህ ሁሉ የሚገርመው ደግሞ የጉዞው መነሻ ከክርስቶስ ጎን በፈለቀ ውሃ ጥምቀት ነው ፣ የጉዞው መንገድም ክርስቶስ ነው ፣ የጉዞው ስንቅም ክርስቶስ እንበላው እና እንጠጣው ዘንድ የሰጠን የክርስቶስ የእራሱ ስጋና ደም ነው ፣ የጉዞው አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓሶች ክርስቶስን የመሰሉ ቅዱሳን ናቸው ፣ የጉዞው መዳረሻም እራሱን ክርስቶስን መምሰል ነው ከዚህ ጉዞ ያልተሰናከለ ምነኛ ብጹእ ነው!

ክርስቶሳዊነት ማለት እሳት ነው ፣ ኃጢአታችንን ከውስጣችን አቃጥሎ የሚጨርስ እሳት ነው ፣ አዳማዊ ማንነታችንን ለብልቦ እሳት ወደ ሆነ ክርስቶዊ ማንነት የሚያቀርበን እሳት ነው ፣ በጥምቀት ክብሪት ውስጣችን ተለኩሶ ዘወትር የስጋውና ደሙ ጋዝ እየተጨመረበት የሚንበለበል ፣ አጋንንትን የሚያቃጥል እሳት ነው። በዚህ እሳት እንኑር ፣ ወደዚህ እሳት እንጠጋ ፣ ከዚህ እሳት እንሙቅ ፣ ዘወትርም የጽድቅን ስራ እየሰራን ይህን እሳት እናቀጣጥለው እንጂ የኃጢአትን ውሃ አንቸልስበት። አሜን የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
❤ 18 🥰 3 👍 1
Channel title changed to «ኪዳን ዘኢየሱስ»
ኪ
14:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ጌታ እኮ ነው " (ዮሐ 21፡7)

ይህን ቃል የተናገረው የተወደደው ሐዋርያ ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ነው። ጌታ ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ አሳ ሊያጠምዱ ወደ ጥብርያዶስ ባሕር ሄደው ነበር። ሌሊቱን ሙሉ ሲያጠምዱ ቢያድሩም ምንም አልያዙም ። በነጋ ጊዜ ግን ጌታ ወደ መርከባቸው መጣና አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው እነርሱም ጌታ መሆኑን ሳያውቁ ምንም የለንም አሉት። እርሱም መረባችሁን በቀኝ በኩል ጣሉት አላቸው ፤ እነርሱም ማን እንደሆነ ገና ባያውቁም እሺ ብለው መረባቸውን ጣሉት በጣም ብዙ አሳም ያዙ። ያን ጊዜም ፍቁረ እግዚአ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ስምዖን ጴጥሮስ ጠጋ ብሎ ጌታ እኮ ነው አለው። ከሁሉም በፊት ለእርሱ ተገለጠለትና ጌታው መሆኑን አወቀ ለ3 ዓመት ከ3 ወር ያስተማረው ጌታ ፣ ሁሉን ጥሎ የተከተለው ጌታ ፣ በፊት ለፊቱ ሲሰቀል ያየው ጌታ ፣ ሊወዱት ዘንድ ደም ግባት የለውም እስኪባልለት ድረስ መከራውን ሁሉ በአይኑ ያየው ጌታ ፣ አንጀቱ እስኪቃጠል ድረስ ያለቀሰለት ጌታ ፣ እነኋት እናትህ ብሎ ምልዕተ ጸጋ እመቤትን የሰጠው ጌታ!! አዎ ይህ ፊት ለፊቱ የቆመው ጌታ እርሱ እራሱ ነው። በክብር ስጋውን ዳግመኛ እንዳይሞት አድርጎ የተነሣው ጌታ ፣ እራሱ የተሰቀለው ኢየሱስ ነው። ነፍሱ የወደደችውን አየ ፣ ነገር ግን እርሱ ብቻውን እንዲደሰት የፈቀደስ አይደለም ለእርሱ የተገለጠውን ጌታ ስምዖን ጴጥሮስ ጀልባዋ መሬት እስክትደርስ አላስችል ብሎት ውሃ ውስጥ ገብቶ እየዋኘ ጌታ ጋር እስኪደርስ ድረስ የሚያስደስተውን መልካም ዜና ሄዶ ጌታ እኮ ነው ብሎ ነገረው። ነገር ግን እርሱስ በስምዖን ጴጥሮስ ብቻ ያበቃስ አይደለም እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እናምን ዘንድ፥ አምነንም በስሙ ሕይወት ይሆንልን ዘንድ (ዮሐ 20፡31) ለሁላችን የምስራቹን ቃል ወንጌልን "ጌታ እኮ ነው" እያለ አበሰረን እንጂ።

አዎ እርሱ ጌታ ነው በሕይወታችን እኛ ባናውቀውም ፤ እርሱን ረስተን በዓለማዊ ስራችን ብቻ ብንጠመድም ፣ ወደ እኛ መጥቶ ስራችንን የሚባርክልን ጌታ እርሱ ነው። እኛ በሕይወታችን እርሱን ረስተን ብንባዝንም በብዙ አምሳል ሲረዳን ባናውቀውም ሕይወታችንን በበረከትን የሚሞላልን ጌታ እኮ ነው። እስቲ ተስፋ የቆረጥንበትን ጊዜ እናስታውስ ለፍተን፣ ጥረን ፣ ግረን፣ ይሄስ መቼስ አይሳካልኝም ያልንበትን ጊዜ በዓይነ ልቦናችን እንሳለው ያንን ሁሉ ያሳለፈን ጌታ እኮ ነው። በመከራችን የሚያግዘን ፣ በድካማችን የሚያበረታን ፣ የማይቻለውን ሁሉ የሚያስችለን ጌታ እኮ ነው! መረቦቹ እንኳን ያለ እርሱ ቃል በአሳ የማይሞሉ ከሆነ ሕይወታችንም እርሱ ከሌለበት ጎዶሎ ነው ሁሉን የሚሞላ እርሱ ጌታ ነውና።
👍 13 🥰 4 ❤ 1
14:29
25 May 2023
ኪ
07:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዐርገ በስብሐት ፣ ወበይባቤ

በዚህ ቀን፣ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዕርገት እናስባለን ፣ ከትንሣኤው 40 ቀናት በኋላ፣ በደቀ መዛሙርቱ ፊት ወደ ሰማይ ወደ አባቱ ዘንድ ዐረገ። ሞትን በሞቱ ድል ነስቶ ፣ መፍረስና መበስበስን በትንሣኤው ካጠፋ በኋላ አሁን ደግሞ ባሕርያችንን ያከብረው ዘንድ በአባቱ ቀኝ አስቀመጠው (የተዋሐደውን ስጋ በመለኮታዊ ክብሩ አክብሮ ከአብ ጋር አስተካከለው)።

ዕርገት የክርስቶስን ምድራዊ ተልእኮ ይኸውም በጽንሰቱ የኛን ባሕርይ በመንሳት የጀመረውን ድኅነታችንን ማጠናቀቅን የሚያመለክት ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ መውረድ የሚጀምረውን አዲስ ዘመን - የቤተክርስቲያንን ዘመን ያውጃል። በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥም በክርስቶስ አንድ የሆንን ሁላችን የመጨረሻው ግባችን ወደ ዐረገው መሢሐችን መሄድ እና ከመለኮታዊ ክብሩ በጸጋ መካፈል ነው።

የድኅነታችን ራስ ክርስቶስ የሄደበትን እኛ የእርሱ አካላት ደግሞ እንደምንከተል አውቀን ዕርገቱ በሚያመጣው ተስፋ እና ዋስትና ደስ ይበለን። በዚህ ቀን እውነት በፍጹም ሐሴትን እናድርግ መድኅናችን ክርስቶስ በክብር ድኅነታችንን ፈጽሞ አርጓልና ነገር ግን ከክርስቶስ ድኅነት ለመሳተፍ እርሱ ጨርሶታል ብለን ብቻ የምንተውስ አይደለም የክርስቶስን በክብር ዳግመኛ መምጣት በመጠባበቅ በመልካም ሥራ እንጸናለን እንጂ ምክንያቱም ይህ ከእኛ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳየነው፥ እንዲሁ ይመጣልና።(ሐዋ 1፡11)
👍 5 🥰 2
07:31
❤ 1
27 May 2023
ኪ
08:08
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 2
30 May 2023
ኪ
14:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢየሱስ ❤️
👍 3 ❤ 2
1 June 2023
ኪ
05:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
ራእይ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።
⁸ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
❤ 2
3 June 2023
ኪ
12:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
"አጽናኙ የእውነት መንፈስ"

ጌታ ሐዋርያትን ተለያቸው ፣ ሁሉን ጥለው የተከተሉት ጌታ ተለያቸው! እነርሱም ዓይናቸውን ከፍ አደረጉ ወደ ሰማይም አንጋጠጡ መድኃኒታቸውን ግን ደመና ተቀበለችው። ብቸኛ ሃብታቸው ከእርሱ ውጪ ገንዘብ እንኳን እንዳይዙ ያዘዛቸው ጌታ ተለያቸው። ዓይናቸውም ለመጨረሻ ጊዜ እረኛቸውን ለማየት ወደ ሰማይ አማተረች ነፍሳቸው የወደደችው ግን ላይመለስ ሄዷል። በዚህ ጊዜ ግን አንድ የምሥራች ቃል ወደ ጆሯቸው ገባ "ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ እንዲሁ ይመጣል" የሚልን ዜና ከመላእክት ሰሙ። መድኃኒታቸው ሄዶ የሚቀርስ አይደለም ይመጣል! ስለዚህ ዳምመኛ የሚመጣው ጌታቸው ቃል የገባላቸውን "አጽናኙን የእውነት መንፈስ" በመጠባበቅ ከጌታ እናት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም በደስታ ተመለሱ።

የተስፋው ቃል የታመነ ነው በበዓለ ጰንጠቆስጤ (በዓለ ኀምሳ) ሐዋርያት በአንድ ልብ ከመድኃኒታቸው እናት ጋር በጽርሐ ጽዮን ሳሉ ከአብ የወጣው የእውነት መንፈስ በእሳት አምሳል ወረደባቸው ፤ በሰዎች ቋንቋ ሁሉም ተናገሩ ይህ ቀንም የቤተክርስቲያን ልደት ሆነ። ይህቺንም ቤተክርስቲያን የገሃነም ደጆች አይችሏትም አጽናኙ የእውነት መንፈስ በመላባቸው ሐዋርያት ላይ ተመስርታለችና አትነቃነቅም። የዚህች ቤተክርስቲያን መሠረቷም "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" የሚለው የሐዋርያው ጴጥሮስ ምሥክርነት ነው ፤ የቤተክርስቲያን ጌጧ የእግዚአብሔር ልጅ ነውና። እኒህ ሐዋርያትም በፊት ፈሪ የነበሩ በረቱ ፣ አጽናኙ የእውነት መንፈስም አፍ ሆኗቸው በሰዎች ሁሉ ፊት "እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።" ሲሉ ያለ ፍርሃት መሠከሩ ፣ የክርስቶስ ሙሽራ የምትሆን ቤተክርስቲያን ኤቅሌሲያንም በመሢሁ አማኞች ሞሏት በህዝብም ሁሉ ፊትም ደምቀው ታዩ ፤ አጽናኛቸውን ከአብ የወጣውን የእውነት መንፈስ አድርገዋልና ይኸውም ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ነው።

አሜን መድኃኒታችን ሆይ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ ስምህም ክርስቶስ የአብ መሢሁ ነው። ዓለምን በደምህ ተቤዠህ ፤ ለቅዱሳን ሐዋርያትም ከአብ የወጣውን መንፈስህን አጽናኝ አድርገህ ላክህላቸው። አቤቱ በጽርሐ ጽዮን ቤተክርስቲያንህ ለምንገኝ ለእኛም አጽናኙን የእውነት መንፈስ ላክልን በእርሱ ጸንተን ስምህን ለዓለም እንመሰክር ዘንድ። አቤቱ ሙሽራህን ቤተክርስቲያንንም ጠብቃት የእርሷንም ጥፋት አታሳየን ፤ ስለ ስምህም አጽናን።
👍 7 🥰 2
12:08
12:08
19 June 2023
ኪ
09:18
ኪዳን ዘኢየሱስ
The icon of the archangel Mikhail is set up in every church, where he is dressed in a soldier's dress as "commander of the army of the Lord". He has a spear in his hand by which he pierces Satan who appears as a dragon, as it is written in the book of Revelation: "And war broke out in heaven: Michael and his angels fought with the dragon". Michael triumphed in that war, and he cast the devil out of heaven (Apoc. 12: 7-9).

In spite of the greatness of the archangel Michael, we see his humility, as it was mentioned in the epistle of Jude: [Yet Michael the archangel, in contending with the devil when he disputed about the body of Moses, dared not bring against him a reviling accusation, but said: "The Lord rebuke you!"] (Jude 9).

BY His Holiness Abuna SHENOUDA III

Holy Archangel Michael pray for us!
ኪ
09:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
In realms unseen, where angels dwell,
There stands a warrior, mighty and bright,
Saint Michael, with his sword of flame,
Defender of truth, in God's holy name.

By teachings passed down, from ages past,
Orthodox Church Fathers, their wisdom vast,
They spoke of Michael, celestial guide,
Leading God's faithful, side by side.

With fiery zeal and strength untamed,
He battles darkness, his foe proclaimed,
From heavenly heights, he descends with might,
To shield God's children, in darkest night.

He treads on evil, with steadfast grace,
Invisible armor adorns his celestial face,
His wings unfurled, majestic and grand,
A symbol of God's protection, across the land.

Orthodox Church Fathers, in their holy creed,
Speak of Michael's role, with utmost heed,
As defender and guardian, he takes his stand,
Protecting the faithful, throughout the land.

In hymns and prayers, his name we raise,
Saint Michael, intercede for our days,
Guide us with wisdom, by ancient lore,
To honor God's truth, forevermore.
❤ 4
20 June 2023
ኪ
11:18
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ዘንድ ጠበቃ

"ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" 1ኛ ዮሐ 2፡1
(Fr. Moses Samaan; Aug 15, 2012 (Coptic Orthodox Church)
የክርስቶስ ጥብቅና ለኃጢአታችን የተደረገ የካሳ ክፍያ ነው፤ ይህም ማለት ጌታችን እኛ ኃጢአትን ባደረገን ጊዜ እራሱን የኃጢአት ካሳ አድርጎ በእኛ ፈንታ ስለእኛ የኃጢአትን ደሞዝ የከፈለ ነው። የክርስቶስ ከአብ ጋር ያለው ጥብቅና የተመሰረተው በእኛ ፈንታ የሁላችንን በደል ተሸክሞ የተሸከመው እርሱ በመሆኑ ነው (ኢሳ 53፡6) ። በዚህም ሥላጣኑ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል መካከለኛ (አስታራቂ ) ሆኖ ይቆማል። እንደ እውነቱ ከሆነ, በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል ያለ ብቸኛ መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እንደ አምላክነቱ በአብ የሚፈለገውን መለኮታዊ ፍትህ በማሟላት እና እንደ ሰውነቱ ለሰዎች ለኃጢአታቸው ማስተሰረያ በእነርሱ ምትክ በመሞት የኃጢአታቸውን ይቅርታ የሰጠ ብቸኛው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ ጠበቃና መካከለኛ ተብሏል።

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም "ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።" ይለዋል እንዲህ ማለቱ በግልጽ የክርሶቶስ ጥብቅና የኃጢአት ማስተስረያ መሆኑን ያሳያል ይሄውም "ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ" ብሎ ስለሚጀምር በኃጢአተኛው ሰው ፈንታ ካሳን በመክፈል ዳግም ከእግዚአሔር ጋር ያስታርቀዋል ይሄንንም ከጻድቁ ከኢየሱስ ውጪ ያደረገ የለም አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ባቀረበው ደሙ ዘላለም የኃጢአታችን ካሳ ክፍያ በመሆን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልናልና፣ በዚህም ባቀረበው መሥዋዕት ጠበቃችን ነው።

ይኸውም ሐሳብ ቅዱስ ጳውሎስ ጌታ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ያለው ብቸኛ መካከለኛ አድርጎ በገለጸበት ወቅት፡- “በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ ነው እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ራሱን ለሁሉ ቤዛ ሰጠ” (1ጢሞ 2፡5) እራሱን አሳልፎ የሰጠ እና ለእኛ ሲል የኃጢአትን ደሞዝ የከፈለ አስታራቂያችን ነው
ይህንን የጌታ ክርስቶስን ብቸኛ የሰው ልጅ ጠበቃ ሚና ማንም አይከራከርም። የቅዱሳን ምልጃ ከዚ ከክርስቶስ የኃጢአት ደሞዝ እና አስታራቂ ከመሆኑ ጋር አይገናኝም ፣ የቅዱሳን ምልጃ ስለእኛ በክርስቶስ ፊት የሚቀርብ ልመና ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ, Comparative Theology )

ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ራሱም የኃጢአታችን ማስተስረያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ደግሞ ነው።" (1ዮሐ.2፡1፣2) እዚህ ላይ፣ ማስተስረያው በጣም ግልጽ ነው። ይኸውም ለኃጢአተኛው የቀረበ አስታራቂነት ነው። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ፥ ይህ ኃጢአተኛ ሥርየት ያስፈልገዋል። ይህን ማስተሰረያ ያቀረበው ጻድቅ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።ስለዚህም ስለ እኛ በፈሰሰው በደሙ አስታራቂነት ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ይችላል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ብቸኛ መካከለኛ ስለመሆኑ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተነገረው ቃልም ተመሳሳይ ትርጉም ተሰጥቶታል። እንዲህ ይላል፡- “አንድ አምላክ አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ራሱን ለሁሉ ቤዛ ሰጠ” (1ጢሞ.2፡5፣6)። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን የሠዋ እና የኃጢአታችንን ዋጋ የከፈለ አዳኝ ሆኖ ለእኛ መካከለኛ ነው።
የዚህ አይነት ማስታረቅ አገልግሎት ጨርሶ የማያጠራጥር አይደለም የተሰጠውም ለክርስቶስ ብቻ ነው ፣ የቅዱሳን ምልጃ ግን ከኃጢአት ካሳ እና ከቤዛነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። የቅዱሳን ምልጃ ስለእኛ በክርስቶስ ፊት የሚቀርብ ልመና ነው።
👍 9 ❤ 3 🥰 1
11:19
🥰 1
ኪ
19:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጌታ ሆይ እወድሃለው ልልህ ፈልግና በኃጢአት የተሞላ ሕይወቴን ሳየው ግን መልሼ አንደበቴን እሰበስባለው ፣ ለኔ ስትል የከፈልክልኝን ውለታ ሳስበው ደግሞ ምድር አፍ አውጥታ ብትውጠኝ ብዬ እመኛለው ። ነፍስህን አሳልፈህ የሰጠኸኝ ጌታዬን መውደድ ካልቻልኩ ሕይወት ምን ይሰራልኛል ጌታ ሆይ ሁሌም ወደ አንተ ነው የማንጋጥጠው አሁንም ወደ አንተ ወደ ማትታክተኝ አምላኬ ዞሬ አንተን መውደድን ስጠኝ እልሃለው እንደ ሐዋርያህ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ እንደወድህ አንተ ታውቃለህ " እል ዘንድ አድለኝ ላንተ ሁሉ ይቻልሃልና ጌታ ሆይ አንተን መውደድን ስጠኝ።
❤ 9 🥰 1
25 June 2023
ኪ
19:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
#የእግዚአብሔር_በግ
#እረኛ
~~~~
በግ ሆኖ እረኛ መሆን፥ እረኛም ሆኖ በግ መሆን የሚቻለው የለም። ሰውም አምላክም ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ይቻላል እንጂ። ሥጋ ስለለበሰ፣ በግ ስለሆነ መሥዋእታችን ነው፡ አምላክ ስለሆነም እረኛችን ነው።
“...በጉ እረኛቸው ይሆናልና...”(ራእይ 7፥17)
" የጠፋውን በጉን የሚፈልግ እረኛ እርሱ ነው። ስለ ዓለሙ ሁሉ የታረደ፥ ዓለሙን ሁሉ ከኃጢአቱ ያነጻ በግ እርሱ ነው"። (ሃይ.አበው ዘኢራቅሊስ ም 49:38)
✍️ የዮሐንስ ወንጌል ማብራርያ (መ.ሐ ስቡሕ)
“በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ”። አሜን 🙏
✍️ Binyam Geć
👍 5 ❤ 2 🥰 1 🙏 1
28 June 2023
ኪ
08:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ማርያም ሆይ አንቺ የእግዚአብሔር እናት እና ንግሥታችን ነሽና ጸጋን ሁሉ በሰጠሽ በእርሱ አጠገብ ስትቆሚ እኛን ታስቢን ዘንድ ይገባሻል። ከአንቺ ስለተወለደው አምላክ ፣ መምህር እና ንጉሥ ስትዪ ትረጂን ዘንድ ወደ እኛ ነይ። ከዚህ የተነሳ “ጸጋን የተመለሽ” ተብለሻልና። ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ሆይ አስቢን ፣ ጸጋን የተመልሽ ድንግል ሆይ ከጸጋሽ ባለጠግነ ጸጋን አድዪን።" ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
❤ 9 🥰 1
08:29
O Mary, Mother of our Lord divine,
Whose graces abundant, on us shine,
Stand close to Him who bestowed all grace,
Our Queen, bearing God's love in embrace.

You, vessel chosen, with faith so pure,
Carried the King, our salvation sure,
His birth brought hope, our souls set free,
Full of grace, you're called eternally.

Mindful of us, most holy Virgin dear,
Bestow on us gifts, your graces near,
From heavenly riches, our souls imbue,
Virgin full of grace, we seek from you.

In your intercession, solace we find,
Your loving embrace, to us, inclined,
Amidst trials, your refuge we seek,
Through your prayers, our hearts find peace's peak.

Mary, Queen, ordained by divine will,
In your presence, our hopes fulfill,
Guide and protect us through life's array,
In endless praise, your name we convey.

O Mary, full of grace's embrace,
Your love and mercy, all doubts erase,
We honor you with grateful acclaim,
In heavenly realms, we sing your name.
❤ 4 🥰 2
5 July 2023
ኪ
04:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን

ቤተክርስቲያን ማለት በዚ ዓለምም ያሉ እና በሕይወተ ስጋም የተለዩ ቅዱሳን ሕብረት ናት ራሷም ሊቀ ካህናት ኤየሱስ ክርስቶስ ነው። በዚህች ሕብረታዊት በሆነችው ቤተክርስቲያን ውስጥ ብቻ ነው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ማግኘት የሚቻለው እርሱ ራስ የሆነላት ቤተክርስቲያን ውስጥ ብቻም ነው መዳን ያለው። ራሷ ክርስቶስ አንድ እንደሆነ ፣ አካሉ ቤተክርስቲያንም አንዲት ናት ሁሉን በጉያዋ ሰብስባ ከራሷ ከክርስቶስ ያገኘችውን ስጋውን ትመግበናለች ፣ ከጎኑ የፈሰሰውን ደሙንም ታጠጣናለች እራሱ ሕይወት ወደ ሆነው ክርቶስም ታደርሰናለች ። ወደዚህች ቤተክርስቲያን እንሰብሰብ እናታችን ነሽም እንበላት የንጉሡ የክርስቶስ አካሉና ሙሽራው እርሷ ናትና ፣ ሰማእቱ ቅዱስ ቆጵርያኖስ እንዳለው "ቤተክርስቲያንን እናቴ ያላለ እግዚአብሔርን አባቴ ሊል አይችልማና ።
❤ 4 👍 3 🥰 1
6 July 2023
ኪ
00:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቤተክርስቲያን ወደ ስህተት ትምህርት ልትገባ ትችላለችን?

ቤተክርስቲያን በምድር እና በሠማይ ያሉ የቅዱሳን ሕብረት ናት ሙሽራዋም እራሱ እውነት የሆነው ክርስቶስ ነው። እውነት ደግሞ መቼም ውሸት ሊሆን አይችልምና ቤተክርቲያን ወደ ስህተት ትምህርት ልትገባ አትችልም!! ቅዱስ ጳውሎስ ሳወል ይባል በነበረ ጊዜ ቤተክርስቲያንን ያሳድድ ነበር በደማስቆ መንገድም ጌታ ተገለጠለትና "ሳወል ስለምን ታሳድደኛለህ" ሲል ጠየቀው ሳወል ሲያሳድድ የነበረው ቤተክርስቲያንን ቢሆንም ክርስቶስ ግን ስለምን ታሳድደኛለህ አለው። ጌታ ቤተክርስቲያንን "እኔ" እያለ ይጠራታል አካሉ ናትና ፣ ክርስቶስ ደግሞ ሁለመናው እውነት ስለሆነ ቤተክርስቲያንም እውነት ናት ወደ ስህተት ልትገባ አትችልም።

በ3ኛው ክፍለ ዘመን ሰማእትነትን የተቀበለው ቅዱስ ቆጵርያኖስ ስለ ቤተክርስቲያን እንዲህ ይላል " የክርስቶስ ሙሽራ አመንዝራ ልትሆን አትችልም። እርሷ ያልተበላሸች እና ንጽሕት ናት። አንድ ቤት ታውቃለች በንጽሕና የአንድን ወንበር ቅድስና ትጠብቃለች። እኛን ለእግዚአብሔር [ትጠብቀናለች]። እርሱ የወለዳቸውን ልጆች ለመንግሥቱ ትሾማለች።"
ቤተክርስቲያንን የክርስቶስ ሙሽራ ያላት በመጀመርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነው ሰርጓም አንድ ጊዜ ለዘላለም የተፈጸመው በዕለተ አርብ ነው ፣ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ሙሽራዋ አንድ ነው እርቃኑን መስቀል ላይ የተሰቀላለት ኢየሱስ ነው። ስለፍጹም ፍቅሩ ወዳዋለችና መቼም ከእርሱ ፈቀቅ ልትል አትችልም ውበቱን አይታ ወደደችው እንዳንል ታየው ዘንድ ደም ግባት የለውም ፊቱ በደም ተጨማልቋል ፣ ስለሃብቱ ወደደችው እንዳንል እርሱ ቤት እንኳን የሌለው በተራራ የሚያድር ነው ነገር ግን ለእርሷ ሲል ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቷት በመስቀል ላይ አግብቷታልና አይኗ ከክርስቶስ ላይ መቼም አይነቀልም እውነቱን ክርስቶስን ይዛለችና የሲዖል ደጆች ሊቀርቧት አይችሉም።
❤ 15 👍 3 🥰 1
8 July 2023
ኪ
19:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጸጋን የተመላችዋ የሐዲስ ኪዳን ታቦት 🕊✨

ሌቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ባበሠራት ወቅት በግሪክ “Kecharitomene” ብሏት ነበር ትርጉሙም "ጸጋን የተመላሽ ሆይ" ማለት ነው። ይህ ቃል ትልቅ ትርጉምን ያዘለ ቃል ነው 🌟 በቤተ ክርስቲያን አባቶች ድርሳናት ይህ ቃል የማርያምን ከፍጥረታት ሁሉ ተለይታ በእግዚአብሔር ልዩ በሆነ መንገድ "ጸጋን" እንዳገኘች በሰፊው ተብራርቷል ።

ከምዕራቧ ሀገር ጣሊያን ቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶች አንዱ የሆነው የሚላኖው ቅዱስ አምብሮሰ ስለ ማርያም ጸጋ መመላት እንዲህ ይላል“ ለሌሎች ጸጋ በከፊል ተሰጥቷል ፣ በማርያም ላይ ግን ጸጋ ሁሉ በሙላት ፈሰሰ” ።

ከምስራቅም ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አላረፈም የልጁ ውበት እና የእናቲቱ በጸጋ መመላት ዝም ማለት አላስችል ብሎት "አንተ ብቻ እና እናትህ ከማንም በላይ ቆንጆዎች ናችሁ፣ በአንተ ላይ ነውር የለም በእናትህም ላይም እድፍ የለም ከልጆቼ በውበት ከእነዚህ ጋር የሚነጻጸር ማን ነው?" ሲል ስለንጽሕናዋ በሚያምሩ ቃላት መስክሯልል።

ምልዕልተ ጸጋ የሚለው ቃል የጸጋን ሁሉ ፍጽምና ያሳያል እንደ ማርያም ከፍጥረታት ሁሉ ይህን ጸጋ የተመላ ማነው የሰማይ ሃብታት ሁሉ በርሷ ላይ አርፈዋልና ፣ ይህም የእመቤታችንን ለስጋዌ ቃለ እግዚአብሔር የተመረጠች ታቦት እንደሆነች የሚያመለክተን ነው።

በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር አሠርቱ ቃላት የተጻፈበት ጽላት ማደርያው ታቦት ነበር በሐዲስ ኪዳን የሥግው ቃል የኢየሱስ ክርስቶስ ማደርያ እመቤታችን ስለሆነች አማናዊት ታቦት ትባላለች 🕊⚓️ እግዚአብሔር ለቃሉ ፍፁም ማደሪያን ሲገነባ ምን ያህል ተጠንቅቆ እንደሆነ እንመልከት ምልዕተ ጽጋ ድንግልን ከሁሉ ለይቶ መርጧታልና ። በሚያስደንቅ ሁኔታ በብሉይ ኪዳኑ ታቦት እና በእመቤታችን መካከል ተመሳሳይነትን እናያለን። በብሉይ ኪዳን ዳዊት ታቦቱን ባየ ጊዜ በደስታ፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?” ሲል ተናግሯል። በሐዲስ ኪዳንም ኤልሳቤጥ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?" ስትል ተመሳሳይ ሀሳብ አስተጋብታለች። 🙌

ዳዊት በበታቦቱ ፊት በደስታ እንደጨፈረ መጥምቁ ዮሐንስ በታቦቷ እመቤታችን ፊት በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ዘለለ፣ ኤልሳቤጥ ማርያምን ከሴቶች መካከል ለይታ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እምብዛም በማይታዩ እና ታቦቱ ፊት በሚባሉ ቃላት ባረከቻት እመቤታችን አማናዊት የሐዲስ ኪዳን ምልዕተ ጸጋ ታቦት ናትና።

በጥንቃቄ ከማይነቅዝ ከማይበሰብስ እንጨት እንደተሠራው ታቦት እመቤታችን ማርያም ንጽሕትና ቅድስት ናት። 🌹 እሷ እንደ ሁላችንም በኢየሱስ የዳነች ቢሆንም። ይህ መዳን ለእርሷ በተለየ ሁኔታ የተከናወነው ገና ከእናቷ ማኅጸን ሳለች ነው የእግዚአብሔር ታቦት ገና ከመሠራቱም ከንጹሕ እንጨት ነውና🌟
❤ 3 👍 3 🥰 1
ኪ
19:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
19:34
9 July 2023
ኪ
01:44
ኪዳን ዘኢየሱስ
✝️ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ስል ምን ማለቴ ነው? 🙏🏽💒

ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ስል በክርስቶስ ተመስርታ ፣ በሐዋርያት ተሰብካ በቅዱሳን አባቶች በተጠበቀችዋ አንዲቷ ሃይማኖት አምናለው እያልኩ ነው📜✨

ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ስል ከጥንታዊቷ የቤተክርስቲያን አምልኮ ሥርዓት አንዱ በሆነው እና ኅሊናን ማርኮ ከቅዱሳን መላእክት ጋር ለምስጋና በሚያገናኘው ቅዳሴ አምናለው ፣ በቅዳሴ ላይም የሚቀርበውን ከሰማይ የወረደ እንጀራ የበጉን የክርስቶስን ስጋ እና ደም እቀበላሉ እያልኩ ነው 🙌🕯

ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ስል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "እስከ ዓለም ፍጻሜ ከእናንተ ጋር ነኝ " ባለው ቃል አምናለው ፣ አካሉ እና ሙሽራው በሆነችዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን ኅብረት ውስጥ ያለው ነኝ በሰማይም ካሉ በምድርም ካሉ ክርስቲያን ወንድም እህቶቼ ጋር በክርስቶስ የተሳሰርኩ ቤተክርስቲያን ነኝ እያልኩ ነው 🌅🔥

ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ስል ጌታ ክርስቶስ "እርስ በእርሳችሁ ብትዋደዱ ደቀመዛሙርቴ መሆናችሁ ያኔ ይታወቃል" በሚለው ቃል አምናለው ፣ የክርስቶስን ትእዛዛት በመከተል ሌሎችን ለመውደድ እና ለማገልገል ተጠርቻለሁ። በዙሪያዬ ካሉ ሰዎች ጋር ባለኝ ግንኙነት የክርስቶስን ፍቅር በማንፀባረቅ የርህራሄ፣ የይቅርታ እና የትሕትና ሕይወት ለመኖር እሻለሁ እያልኩ ነው። ❤️🤝

ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ስል እምነቴ የእድሜ ልክ ጉዞ መሆኑን አምናለሁ። ከኔ በፊት ክርስቶስን የመሰሉትን ቅዱሳን አብነት እያደረኩ ክርስቶስን ወደ መምሰል ጉዞ ላይ ያለው ደካማ ባላቴና ነኝ እያልኩ ነው። 🚶‍♂️🚶‍♀️

የጌታ ክርስቶስ ፍቅር እና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን 😊

✍️ ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 21 👍 2 🥰 1
12 July 2023
ኪ
00:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
🕊✝️ ሐምሌ 5፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ✝️🕊

ዛሬ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለዓለም ለማዳረስ ሕይወታቸውን የሰጡ ሁለቱ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች እና የዓለም ብርሃናት ጴጥሮስና ጳውሎስን እናከብራለን። 🙏

የዮና ልጅ ስምዖን ትሑቱና ትምህርት እንኳን ያልተማረው የገሊላዋ ቤተሳይዳ አሳ አጥማጅ ፣ ለእምነት የፈጠነ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት ግንበኞች ቢንቁትም የማእዘን ራስ የኾነውን ዓለት ኢየሱስን በመመስከር ቤተክርስቲያን የምስመሠረትበት ዓለት (በግሪክ ጴጥሮስ) የኾነ ፣ በዚህም የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ የተቀበለ። ሕይወቱን በሙሉ ለክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያን በመስጠት የክርስቶስን ወንጌል ያለፍርሃት በሰው ሁሉ ፊት ሰበከ ከይሁዳ ተነስቶ ፣ ከዚያም በአንጾክያ አከባቢዎች ሁሉ ከሰበከ በኋላ ሮም ደረሰና በኔሮን ቄሳር እጅ ይሰቀል ዘንድ ተፈረደበት ። ሮማውያን ስቅላትን እንደ እርግማን እና ውርደት ቢያዩትም ተወዳጁ ጴጥሮስ ግን በመስቀሉ ላይ የታየው የነፍሱ ጌታ ኢየሱስ ነው ፣ከዚህም የተነሳ እኔስ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም በማለት ተዘቅዝቆ እንዲሰቅሉት ጠይቋል ፣ መጀመርያ ከክርስቶስ ጋር መሰቀልን ፈርቶ "ሰውዬውን አላውቀውም" ብሎ ቢክደውም አሁን ግን ልቡ ጸንቶ ለተሰቀለለት ኢየሱስ እርሱም ተሰቅሏል። ✝️

ቀናተኛው ሳውል (በሮማይስጥ ጳውሎስ) ከፈሪሳዊው ገማልያል ዘንድ የተማረ ታላቅ የመጻሕፍት ምሁር ለአይሁድ እምነት በጣም የሚቀና ፈሪሳዊና የቤተክርስቲያን ቀናተኛ አሳዳጅ ነበር። ሆኖም፣ ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ላይ በነበረው የኢየሱስ መለኮታዊ መገለጥ፣ ጥልቅ የሆነ ለውጥን አገኘ የተመረጠ እቃም ተባለ። በሰማያዊ ብርሃን ታውሮ የኢየሱስን ድምፅ በመስማት ሕይወቱን ለአሕዛብ ወንጌልን በመስበክ ራሱን የሰጠ የክርስቶስ ተከታይ ሆነ። እስራትና ድብደባን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችንና መከራዎችን ተቋቁሞ ዛሬም እኛን የሚያበረታታን የእምነት ውርስ እነርሱም ውድ የሆኑ መልእክቶቹን ትቶልናል። የመዳንን መልእክት ያለ ፍርሃት ለሕዝብ ሁሉ ካደረሰ በኋላ በመጨረሻም ሮም ሲደርስ በኔሮን ቄሳር ሞት ተፈረደበት እርሱ በዘር አይሁዳዊ ቢሆንም በሮሟ ጠርሴስ በመወለዱ የሮም ዜግነት ስላለው ከአሰቃቂው ስቅላት ይልቅ በፈጣኑ አንገትን በሰይፍ መቀላት ይሞት ዘንድ ተወሰነበት ስለዚህም የቤተክርስቲያን አሳዳጅ በመሆን የጀመረውን ሕይወት ለቤተክርስቲያን ተሳዳጅ በመሆን መራና በመጨረሻም እራሱን ለቤተክርቲያን በመሰዋት ፈጸመ። 🌟

የጴጥሮስና የጳውሎስ ሰማዕትነት የደቀመዝሙርነት መንገድ የመጨረሻውን መስዋዕትነት ሊጠይቅ እንደሚችል ያስታውሰናል። ሕይወታቸው የራሳቸው ሳይሆን የጠራቸው መሆኑን በመረዳት ለእምነታቸው ሲሉ ስደትንና ሞትን በፈቃዳቸው ተቀበሉ። ለክርስቶስ እና ለሙሽሪቱ ቤተክርስቲያን ያሳዩት የማይናወጥ ቁርጠኝነት ስፍር ቁጥር የሌላቸው አማኞችን ማነሳሳቱን ቀጥሏል፣ ዛሬም ቤተክርስቲያን ጴጥሮስና ጳውሎስን የመሰሉ ሰማእታትን የምታፈራ ማኅጸነ ለምለም ናትና ።🌹

የእነርሱን ሰማዕትነት ስናስብ ግን እንዲሁ ለመስማት ብቻ አይሁን ለክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያኑ ስንል ሁሉንም ነገር አሳልፈን ለመስጠት ፈቃደኞች እንሁን። መከራ ቢያጋጥመንም በእምነት ጸንተን እንድንቆም እና ወንጌልን በድፍረት እና በፍቅር እንድንሰብክ የነሱ ምሳሌነት ያበረታን። ስለ ክርስቶስ የሚፈስ ደም የእምነት ዘር ነው ዘላለም ከትውልድ እስከ ትውልድ በአማኞች ልብ ውስጥ ይለመልማልና🌱✨

የቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም የተሞላ የተባረከ በዓል ይሁንላችሁ። 🌹

✍️ ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 3 🥰 1
00:10
00:10
13 July 2023
ኪ
15:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
አነ ዘክርስቶስ

እኔ የክርስቶስ ነኝ ስል ፍጹም እኮራለው በመልኩ ፈጥሮኝ እኔ ግን በፈጠረኝ መልክ አልገኝ ስል እርሱ የኔን የወደቀ መልክ ይዞ ዳግመኛ የፈጠረኝ በደሙ የገዛኝ ጌታዬ ነው። የእርሱ የክርስቶስ ነኝ ስል በሰው ሁሉ ዘንድ ኩራት ይሰማኛል እስከ ሞት ድረስ ያፈቀረኝ ፣ ኃጢአተኝነቴን ያልተጸየፈ ፣ ሁሌ በእቅፉ የሚያኖረኝ አባቴ እኮ ነው። ስቅበዘበዝ ጠባቂ ሲያሻኝ እኔ በግ የምሆነው እርሱም እረኛ የሚሆነኝ ፣ ነፍሴ በረሃብ ስትጨነቅ ለነፍሴ ምግብ የሚሆናት ፣ ስጠማ የሕይወት ውኃን የሚያጠጣኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ምግቤ እና መጠጤ ነው። የሰውነት መአዛዬ በኃጢአት ሽታ ሲከረፋ ናርዶስ ሽቶዬ ፣ ለጨለማ ሕይወቴ ፋኖስ መብራቴ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ታዲያ እኔ ሁለመናዬ የሆነልኝ የክርቶስ ነኝ ከማለት በላይ ምን ኩራት ምንስ ትምክህት ሊኖረኝ ይችላል?🌟

ነገር ግን ከዚህ ኩራት ውስጥ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር ያወጣኛል "የሚወደኝ ቢኖር ትእዛዜን ይጠብቅ" የምትለዋ ቃል እራሴን ከፍ ካረኩበት ኩራቴ አሽቀጥሮ ይጥለኛል። እኔ የክርቶስ ነኝ ብዬ ነገር ግን በኃጢአት ውስጥ ስገኝ ጌታዬን ያሰደብኩት ይመስለኛል። አንድ ልጅ አጥፍቶ ቢገኝ "አሳዳጊ የበደለው" አይደል የሚባለው ፣ ታድያ እንዲህ በልጁ ድርጊት አሳዳጊው ከተወቀሰ እኔ በኃጢአቴ ክርቶስን ስንቴ አስወቅሼው ይሆን? ታድያ በዚህ የኃጢአት ሕይወት ውስጥ እየተመላለስኩ እንዴት ደፍሬ የክርቶስ ነኝ ልበል? ታድያ የክርስቶስ ካልሆንኩ የማነኝ? የሰይጣን መሆኔስ አይደለምን?

እባክህ ጌታ ሆይ መተላለፌን አታስብብኝ ደካማ ነኝና ታገሰኝ ፣ ዛሬም ብበድልህ አንተ ግን አሁንም ይቅር በለኝ ፣ አቤቱ ደፍሬ እኔ የክርስቶስ ነኝ የምልበትን አንደበት አድለኝ!!

✍️ ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 18 🥰 1
14 July 2023
ኪ
10:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ነአኩተከ እግዚኦ በፍቁር ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ -አቤቱ በተወደደ ልጅህ በጌታችን ኢየሱስ እናመሰግንሃለን " ቅዳሴ ሐዋርያት

በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት ውስጥ፣ አማኞች ቅድስት ሥላሴን የሚያመልኩበት አንዱ ጥልቅ መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አምልኮታቸውን ለእግዚአብሔር አብ በማቅረብ ነው። (Worshiping God the Father through Jesus Christ by the Holy Spirit) ይህ በኦርቶዶክስ አባቶች አስተምህሮ ላይ የተመሰረተ የአምልኮ አቀራረብ በመለኮታዊ አካላት መካከል ስላለው ልዩ ሚና እና ግንኙነት ጥልቅ ግንዛቤን ይሰጣል። ፡-

🌟 የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ተጽኖ ፈጣሪ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሔር አብ መቅረብ አስፈላጊ መሆኑን አስምሮበታል። ክርስቶስ በሰው ልጆች እና በአብ መካከል ያለ መካከለኛ እንደሆነ አስተምሯል ስለዚህም ጌታ ኢየሱስ ወደ አብ የሚወስድ ድልድይ ከመለኮት ጋር እንድንገናኝ የሚያደርግ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በመዋሉ፣ በመስዋዕቱ እና በትንሣኤው ወደ አብ እንድንቀርብ እና በመለኮታዊ ፍቅሩና በጸጋው እንድንሳተፍ ያስችለና "ፍኖት ሃበ አቡሁ አንቀጽ ዘመንገለ ወላዲሁ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ፟- ወደ አባቱ የሚወስድ መንገድ ወደ ወለደውም የሚያስገባ በር እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" እንዲል መጽሐፈ ሰአታት።

ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ ዋጋን ከከፈሉ አባቶች መካከል ቅዱስ አትናቴዎስ በአምልኮታችን እና በመንፈሳዊ ጉዟችን ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን ወሳኝ ሚና አጉልቶ ያሳየናል። ከክርስቶስ ጋር የተዋሐደነው በመንፈስ ቅዱስ በኩል እንደሆነና በዚህም ወደ አብ መቅረብ እንደምንችል አበክሮ ተናግሯል። መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ እኛን ለመንፈሳዊ ነገሮች እንድንነሳሳ ብርታት የሚሰጠን አምላክ እንደመሆኑ መጠን አምልኮታችንን ኃይል ይሰጥልናል በክርስቶስ በኩል ከአብ ጋር ባለን ግንኙነት መሪ በመሆን በድካማችን ሁሉ ያግዘናል።

ነአምን አበ ፈናዌ ወልደ ተፈናዌ መንፈስ ቅዱሰ ማኅየዌ - በላከ አብ እናምናለን ፣ በተላከው ወልድም እናምናለን ፣ ሕይወትን ሰጪ በሆነው መንፈስ ቅዱስም እናምናለን።

✍️ ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 11 🥰 1
10:59
10:59
19 July 2023
ኪ
18:59
ኪዳን ዘኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኃጢአተኛውን እኔን ማረኝ።
የኔ መተማመኛ ከእኔ ኃጢአተኝነት ይልቅ የበዛው የአንተ መሐሪነት ነውና ❤️
❤ 12 👍 2
22 July 2023
ኪ
23:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
የነፍሴ ጌታ ክርስቶስ ሆይ አይሁድ አንተ ንጹሕ ሆነህ ሳለህ በግፍ በመስቀል ላይ ሰቀሉህ አንተ ሁሉን ማድረግ ስትችል እነርሱን እንኳን ማጥፋት ስትችል በፍቅር ተከተልካቸው፣ ሲጎትቱህ ሲጥሉህ እንደ ሚነዳ በግ ተጎተትኽላቸው። በምስማር ቢቸነክሩህም አንተን ግን በመስቀል ላይ ያቆየህ ችንካሩ ሳይሆን ፍቅርህ ነው።

ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ አይሁድስ የሰቀሉህ አንዴ ነው እኔ ግን በኃጢአቴ ዘወትር እቸነክርሃለው በበደሌ እሰቅልሃለው አንተ ግን አላጠፋኸኝም እንደ አይሁድ ዝም ብለኸኛል ፣ አሁንም ስበድል አንተ ግን አሁንም ታኖረኛለኽ። ጌታዬ ዝምታህ ድንቅ ነው!
❤ 11
23 July 2023
ኪ
21:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ፣ አንዲት ናት ስንልም ከተለያዩ ነገድና ቋንቋ የተዋጀች አንዲት ማለታችን ነው። በዚህም የኖኅን መርከብ ትመስላለች፣ ከትልቁ ዝሆን እስከ ትንሿ ትንኝ ድረስ የያዘች እና ከጥፋት ውኃ የምትታደግ አንዲት መርከብ ናት። ቤተክርስቲያንም የተለያዩ ነገድና ቋንቋ ያላቸውን ሕዝብ ይዛ ከባሕረ ሲዖል ትታደጋለች። ይሄን ስንል ግን ቤተክርስቲያን በብሔር ማንነት ላይ የቆመችስ አይደለም ከዚያ በላይ ናት እንጂ ዳግመኛ የተወለድነው ከሚጠፋ ዘር አይደለምና(1ኛ ጴጥ 1፡23)።

ሐመረ ኖኅ ይእቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን!
👍 4 🥰 2 ❤ 1 🔥 1
24 July 2023
ኪ
00:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
"እንግዲያውስ ነፍሳችንን ሰማይ እናድርግ። ሰማይ በተፈጥሮ ብሩህ ነው; በዐውሎ ነፋስ ውስጥ እንኳ አይጠቆርምና፥ መልኩንም አይለውጥም፥ ዳመናት እየሮጡ ይጋርዱታል እንጂ። ሰማይ ላይ ፀሐይ አለ; እኛ ደግሞ ፀሐየ ጽድቅ [ክርስቶስ] አለን። እኔስ ሰማይን መሆን ይቻላል እላለሁ ኧረ ከሰማይም የተሻለ መሆን እንደሚቻል አያለው። እንዴት? የፀሃይ ጌታ ከኛ ጋር ሲኖር። ሰማይ ንጹሕና ነውር የሌለበት ነው; በዐውሎ ነፋስ ወይም በሌሊት አይለወጥም ። እኛም እንዲሁ በመከራዎችም ሆነ በ‹ዲያብሎስ ሽንገላ› ተጽዕኖ ውስጥ አንውደቅ (ኤፌ 6፡11)

ነገር ግን ያለ ነውር በንጽሕና እንቀጥል። ሰማይ ከፍ ያለ ነው ከምድርም የራቀ ነው። እኛም [ራሳችንን በተመለከተ] እንዲሁ እናድርግ። ራሳችንን ከምድር እናርቅ፣ ራሳችንንም ወደ ከፍታ ከፍ እናድርግ፣ ከምድርም እንራቅ። ሰማይ ዝናብና ከአውሎ ነፋስ ይልቅ ከፍ ያለ ነው አንዳቸውም አይደርሱበትም ፣ እኛም ከፈቀድን ይህን ደግሞ ማድረግ እንችላለን።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
❤ 2 🥰 1
25 July 2023
ኪ
17:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ

ይህን የተናገረው የተወደደው ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። በዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 6 ላይ ተዘግቦ እንደምናገኘው ጌታ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር ሲከተሉት የነበሩትን ሕዝብ በ5 እንጀራ እና በ 2 አሣ ከመገበ በኋላ የስጋቸውን ምግብ አግኝተዋልና "ይህስ ነቢይ ነው" ብለው ሊያነግሱት ፈለጉ። እርሱ ግን ከአጠገባቸው ወደ ተራራ ፈቀቅ አለ ሲመሽም ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ወደ ቅፍርናሆም ሲሄዱ ጌታ ግን በእግሩ ባሕሩ ላይ እየተራመደ ቅፍርናሆም ደረሰ። በነጋ ጊዜም ባሕር ማዶ ላይ ሲፈልጉት የነበሩት ሕዝብ አገኙትና "ጌታ ሆይ መቼ መጣህ አሉት"። ጌታ ኢየሱስ ግን እናንተ ስጋዊ ምግብን ስለመግኳችሁ ትፈልጉኛላችሁ ፣ አባቶቻችሁ ራሱ በምድረ በዳ ከሰማይ የወረደን መናን በልተው ሞቱ ፣ ለሚጠፋ መብል አትሥሩ ለማይጠፋው እንጂ ከሰማይ የወረደ የሕይወት የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ስጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በእርሱ እኖራለው እርሱም በእኔ ይኖራል ሲል ስለ ነፍስ ምግብ አስተማራቸው ፣ እነርሱ ግን ይህ ትምህርት ከበዳቸው ከደቀመዛሙርቱ ሳይቁሩ ብዙዎቹ "ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው" ሲሉ ብዙዎቹ አፈገፈጉ። ይሄን ጊዜ ጌታ 12ቱን እናንተስ ልትሔዱ ትወዳላችሁን? ሲል ጠየቀ። ያኔ ፈጣኑ ቅዱስ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ" ሲል መለሰለት።

ጌታ ሆይ እንደ ሐዋርያህ እኛም እንልሃለን ወደ ማን እንሄዳለን አንተ አባታችን ነህ አንተም እናታችን ነህ ፣ የዘላለም ሕይውት ቃል ከአፍህ ይወጣል ፣ የዘላለም ሕይወት ውኃ ከሆድህ ይፈሳል ፣ የዘላለም ሕይወት እንጀራ የሰጠኸን ስጋህ ነው እንግዲያውስ ሕይወትን ትተን ወደ ማን እንሄዳለን? ያደረክልንን ሁሉ እየረሳን አንተን ብንበድልህም ኃጢአታችን አንተ ፊት ለመቆም ባያስደፍረንም ጌታ ሆይ ካንተ ውጪ ሌላ መሄጃ መች አለንና ወደ ማን እንሄዳለን። አንተንስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱ ጋርም አብሮ ይበላል እያሉ ያሙሃል አንተ ግን በእኛ ኃጢአተኛ ልጆችህ አታፍርብንም "ኃጥአንን እንጂ ጻንቃንን ልጠራ አልመጣውም" ብለህ እነርሱን ታሳፍራቸዋልህ እንጂ። ታድያ አባት ሆይ ከአንተ ወደ ማን እንሄዳለን? በዓለም ተቅበዝብዘን ብንጠፋም ፣ በደስታችን ጊዜ ባናስብህም ፣ በኃጢአት ተዘፍቀን በዚ ዓለም ምኞት ብንወድቅም አንተ እጅህን ዘርግተህ "ልጆቼ አልተውኳችሁም ዛሬም ቢሆን እወዳችኋለው የዘላለም ሕይወት እንጀራ እኔ ጋር አለ ኑ ብሉ" ትለናለህ አምላክ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን ወደ አንተ ወደ ሕይወታችን እንጂ ከአንተ ውጪ ሁሉ ሞት ነውና።

✍️ ኪዳን ዘኢየሱስ
👍 6 ❤ 3 🥰 1
28 July 2023
ኪ
11:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
“አንዳንዶች ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ መባል መቻል አለመቻሉን ሙሉ በሙሉ ጥርጣሬ ውስጥ መግባታቸው አስገርሞኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ከሆነ እርሱን የወለደች ቅድስት ድንግል እንዴት የአምላክ እናት አትሆንም? ~ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
❤ 7 🥰 1
29 July 2023
ኪ
10:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ ሐምሌ 22 የሁለት ብፁዓን ጳጳሳት እረፍት ይታሰባል

የመጀመርያው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው ። ሐምሌ 22፣ 1928 ዓ.ም አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት በግፍ በፋሽስት ጣልያን የተገደሉበት ቀን ነው፡፡ 1921 ዓ.ም. ግብጽ ወርደው ጳጳስ በመሆን የተሾሙ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው ጵጵስናን አስከብረው ለሃገራቸውም ለቤተ ክርስቲያንም ሰማዕት ሆነዋል።

ሁለተኛው ከዛሬ 40 ዓመታት በፊት የሸዋ ክፍለ ሀገር ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ናቸው። በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ለዲያቆናት እና ካህናት ሃይማኖት ከምግባር እየመረመሩ ክህነት ይሰጡ ነበር። ብጹዕነታቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በክረምቱ መርኃ ግብር ወደ ዝዋይ እንዲመጡ በማድረግ ተምሮ ማስተማር አገልግሎት እንዲጀመር አደረጉ በዚህም ለማኅበረ ቅዱሳን ምሥረታ ታላቅ ሚናን ተጫውተዋል።ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ለዐሥራ አንድ ዓመታት በዚህ ዓይነት ከፍተኛ እና አርአያነት ያለው አገልግሎት ካበረከቱ በኋላ ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም በመኪና አደጋ አርፈዋል።

አሁን ላይ በጳጳሳት እየተሰራ ባለው ደባ ብናዝንም ግን እንዲህ ያሉትን ለዘመናችን ቅርብ የሆኑ ጳጳሳትን ስናስብ ውስጣችን በተስፋ ይለመልማል፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም የቤተ ክርስቲያን ቀኖና አይሻርም ብለው ለእምነታቸው ቆርጠው ሰማዕት የሚሆኑ ጳጳሳትን በዘመናችን ያስነሳልን ፣ የብፁዓን አባቶች አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ጎርጎርዮስ በረከታቸው ይደርብን።

✍️ ኪዳን ዘኢየሱስ
👍 2 🥰 2
10:06
31 July 2023
ኪ
18:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር -[እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እወቁ]

ስለእግዚአብሔር ማወቅና እግዚአብሔርን ማወቅ ይለያያል። ምናልባት እኛ ስለ እግዚአብሔር ብዙ ነገር ልናውቅ እንችላለን ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር የምናውቀውን በሕይወት ካልኖርነው የእግዚአብሔር እውቀት ማለትም ነገር መለኮት እንደ ማንኛውም ሳይንሳዊ እውቀት የጥናት ዘርፍ ብቻ ሆኖ ይቀራል። እግዚአብሔርን ማወቅ የጥናት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ሕይወትን ይጠይቃል ፣ ከእርሱ ከጌታችን ጋር በሕይወት መሳተፍ ስንችል እግዚአንሔርን እያወቅን እንሄዳለን። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ "እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ" (መዝ 33/34፡8) ይለናል ምናልባት ስለ እግዚአብሔር ቸርነት ብዙ ሰምተን ፣ ተምረን ሊሆን ይችላል ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር ቸርነት አወቅን እንጂ የእግዚአብሐኢርን ቸርነት አላወቅንም የእግዚአብሔርን ቸርነት የሚያውቀው በሕይወቱ እንደ ዳዊት የቀመሰው ብቻ ነው የቀመሰውም እንደ ዳዊት ኑ ቅመሱት ሲል ይጋብዛል ምክንያቱም አባታችን ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ እንዳለው "ማርን ቀምሶ ለማያውቅ የማርን ጣፋጭነት በቃላት መግለጽ እንደማይቻል እኛም ራሳችን በራሳችን ልምድ ወደ ጌታ ቸርነት ዘልቆ መግባት ካልቻልን የእግዚአብሔርን ቸርነት በማስተማር መንገድ በግልፅ መግለጽ አይቻልም።"

በዘመነ ሐዲስ ኪዳን ደግሞ የሚለየው እኛ እግዚአብሔርን ማወቅ ሲቅተን እግዚአብሔር እራሱን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ገለጠ በደሙም ታረቀን እርሱን እናውቀው ዘንድ መንገድ አድርጎ ልጁን አቀረበልን። ልጁ ኢየሱስም ከሰማይ የወረድኩ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ይለናል። ስለዚህ ኑ ሁሌ ስለእግዚአብሔር መስማት ብቻ ይብቃን እግዚአብሔርን እራሱን እናውቀው ዘንድ በእርሱ ሕይወትም እንሳተፍ ዘንድ የሕይወት እንጀራችን ክርስቶስን እንቅመሰው እውነተኛው የነገረ መለኮት ሊቅ ስለእግዚአብሔር ያወቀ ሳይሆን ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለው ነውና።

Join 👉🏽 ኪዳን ዘኢየሱስ
🥰 2 ❤ 1
2 August 2023
ኪ
22:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
አንዲት ቤተ ክርስቲያን

የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት ናት። እርሷ በመንፈስቅዱስ የምትመራና ራሷ ክርስቶስ የሆነላት አንዲት አካል ናት። እያንዷንዷ የቤተክርስቲያን ክፍሎች፣ ስህተትን ሊሰሩ በሚችሉ ሰዎች ቢመሩም፣ አሁንም እንደ አንድ የዩኒቨርሳል ቤተ ክርስትያን አባላት እርስ በርስ የተያያዙ አንድ አካላት ናቸው። እንደ አንድ የዛፍ ቅርንጫፎች፣ በግንዳቸው በክርስቶስ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ።

ምንም እንኳን ሰብዓዊ መሪዎች ስህተት ሊሠሩ ቢችሉም፣ መንፈስ ቅዱስ በጊዜ ሂደት ቤተክርስቲያንን እንደሚመራ እና እንደሚጠብቃት ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያን የመጨረሻ ኅልውና የሚረጋገጠው በመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ስለሆነ አንዳንድ ጳጳሳት ሲሳሳቱ መደንገጥ የለብንም።በታሪክ ውስጥ፣ ቤተክርስቲያኒቷ ፓትሪያሪክ የነበረውን ንስጥሮስ ምንፍቅና ትምህርቶችን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችን አጋጥሟታል። ነገር ግን፣ እስከ ዓለም ፍጻሜ በማይለያት መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሁሉንም አልፋ ዛሬ ላይ ደርሳለች። ቤተ ክርስቲያን የሰውን ልጅ ለማዳን እና ወደ ቅድስና ሊመራ በመጣው መስራችዋ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቃል፣፣ መስዋዕትነት እና መከራ ተቀድሳለችና አሁንም በቅድስናዋ ትኖራለች።

ቤተክርስቲያን ከቦታ፣ ከግዜ፣ ከሀገር እና ከቋንቋ ወሰን በላይ ስለሆነች ኩላዊት ተብላለች። ከተለያዩ አስተዳደግ እና ባህሎች የተውጣጡ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ትምህርት በመምራት ወደ መዳን ታደርሳለች። የቤተ ክርስቲያን ኩላዊነት ሁሉንም ዘር እና ቋንቋዎች እስከማለፍ ድረስ ይዘልቃል፣ ይህም በእምነት የተዋሐደ አለም አቀፋዊ አንዲት አካል መሆኗን የሚያጸና ነው።

ነገር ግን፣ አንዳንድ ጳጳሳት፣ በወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታዎች ተጽዕኖ ሥር ሆነው፣ የቤተክርቲያንን ኩላዊነት በመዘንጋት ቤተ ክርስቲያንን በዘር ለመከፋፈል ሲሞክሩ ማየት የሚያሳዝን ነው። ይህ አካሄድ ምንም ይሁን ምን ለሁሉም አማኞች የአንድነት ሃይል እንዲሆን የታሰበውን የቤተክርስቲያንን ሰማያዊ ጥሪ ይቃረናል።

እንደ ታማኝ የቤተክርስቲያኒቷ አባላት፣ እንደዚህ አይነት የመከፋፈል ዝንባሌዎችን በመቃወም ጸንቶ መቆም ያስፈልጋል። የቤተ ክርስቲያን ጥንካሬዋ ኩላዊነቷ (ሁለንተናዊነቷ) እና በመንፈስ ቅዱስ እየተመራች የሰው ልጆችን ሁሉ ያለ ዘር ልዩነት በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ማጽናት ነው የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ የሞተው ለሁሉም ነውና።

Join 👉🏽 ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 3 🥰 1
6 August 2023
ኪ
19:40
ኪዳን ዘኢየሱስ
"በብሉይ ኪዳን አንዲት ዕብራዊት ድንግል (ማርያም) ሠራዊቷን በባሕር መካከል መራች (ዘፀ. 15፡21)። በአዲስ ኪዳን የንጉሥ ሴት ልጅ (ድንግል ማርያም) የድኅነት ሰማያዊ መግቢያ (መራሂተ መንግስተ ሰማያት) ትሆን ዘንድ ተመረጠች።"ቅዱስ አምብሮስ ዘሚላን

መራሂተ መንግስተ ሰማያት የተባለች እመቤት ወደ መንግስተ ሰማያት መፍለሷን ለምናስብበት ለጾመ ፍልሰታ እንኳን በሰላም አደረሰን።
❤ 2
7 August 2023
ኪ
16:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
እመቤታችን ሆይ በሕፃንነታችን በክረምቱ እየተሽቀዳደምን ጾምሽን ጾመናል በዛ በልጅ ኅሊናችን ፍቅርሽ በልባችን አደሮ ስምሽ ከአፋችን አይለይም ነበር። ሰውነታችን ላይ ጥቁር ነጥብ ስናይ ማርያም የሳመችኝ ብለናል አባሮሽ እየተጫወትን ሲደክመን የማርያም መንገድ ስጠኝ ብለን ማምለጫችን አንቺ ነበርሽ። ምልዕተ ጸጋ እመቤት ሆይ አሁን ግን አደግንና በዓለም ውጥረት ተይዘን ማምለጫው ጠፍቶናል ማን የማርምን መንገድ ይሰጠን ይሆን? ማደጋችን በጎ ኅሊናችንን አስረስቶን እርድና እየመሰለን ከቤተ ክርስቲያንሽ ርቀን በብዙ ኃጢአት ውስጥ ተዘፍቀናል ።

እመቤታችን ሆይ በልጅነት ዕድሜያችን ስለ ጾምነው ጾም እንማጸንሻለን ልጅሽ "እንደ እነዚህ ልጆች ካልሆናችሁ መንግስተ ሰማያትን አትወርሱም" ብሏልና በዚህ ጾምሽ የልጅነት አእምሮአችንን መልሺልን በፍጹም የዋህነት አንቺና ልጅሽን እናመሰግን ዘንድ። ድንግል ሆይ አቤቱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በለመነሽ ልመና እኛም እንለምንሻለን በኃጢአት ባሕር እንዋኛለንና ከኃጢአትና ከበደል ረግረግ አውጥተሽ በልጅሽ ይቅርታ ጥልቅ ባሕር እንድንሰጥም አድርጊን።
❤ 10 🥰 1 🤣 1
ኪ
21:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅዳሴ ማርያም ❤️
❤ 11
13 August 2023
ኪ
10:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው” /መዝ.86፥1/

ነሐሴ 7 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽንሰት ነው ፣ መሠረቶቿ የተባሉ እናት እና አባቷ ብንል ቅዱሳን ሐና እና እያቄም ናቸው ፣ ወደ ኋላ አሁንም ብንሄድ እርሷ ከንጉሱ ከዳዊት ወገን እና ከካህኑ ከአሮን ወገን ናት ከቅዱሳን መሠረት የተገኝች ቅድስተ ቅዱሳን ናት። አባ ሕርያቆስም ስለ ጽንሰቷ ባማረ ቃሉ እንዲህ ይላል “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ (“ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ”) (ቅዳሴ ማርያም)

እኔም ጥቂት ከጥንቷ የቤተክርስቲያን አባቶች ስለ እመቤታችን ከተናገሩት ጋበዝኳችሁ፡

ቅዱስ ዮስጢኖስ ሰማዕት (100-165 ዓ.እ)፡- "ማርያምን እንደ ማንኛውም ሴቶች አድርገን አናከብራትም ነገር ግን እርሷ ከደናግል ሁሉ ይልቅ ቅድስትና የከበረች መሆኗን ተምረናል።"

ቅዱስ ሄሬኔዎስ ዘልዮን (130-202 ዓ.እ፡- “የሔዋን አለመታዘዝ ቋጠሮ በማርያም መታዘዝ ተፈታ ፤ ድንግልቱ ሔዋን በአለማመንዋ ያሰረችውን፣ ድንግል ማርያም በእምነቷ ፈታችው።

ሊቁ አርጌንስ (184-253 ዓ.እ.) " የፊተኛው ሰው ስም አዳም ከሆነ ዘፍጥረት ላይ እንደምናነበው "አዳምም የሚስቱን ስም ሄዋን ብሎ ጠራት" ትርጉሙም ሕይወት ማለት ነው እንግዲህ በእውነት ሕይወት የሆነ እርሱን ከተሸከመች ከድንግል ማርያም በላይ ሕይወት መባል ለማን ይገባል"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (306-373)፡- "ማርያም ሆይ አንቺ የማትጠፊ ማኅተም ነሽ ለዘላለም ንጽሕት ድንግል ሆነሽ ኖረሻልና።ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ሆይ በእናትነትሽ አምላክ የሆነውን ወልድን ወልደሽዋል በድንግልናሽም ከወለድሽ በኋላ ድንግልሽ ነሽ"

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ (376-444) " ማርያም ሆይ ሰላምታ ይገባሻል አንቺ በዓለም ሁሉ እጅግ የተከበርሽ ፍጥረት ነሽ ፣ ንጽሕት ርግብ ማርያም ሆይ ሰላምታ ይገባሻል ፣ ፀሐየ ጽድቅን የወለድሽ የማትጠፊ መብራት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል"
👍 3 🔥 1 🥰 1
16 August 2023
ኪ
22:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
22:00
ይህ የምታዩት የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (MOSHE) History module ሲሆን በገጽ 36 ላይ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ሞኖፊሳይት(Monophysite) ሲል ይገልጻታል ነገር ግን ይህ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማይመጥን ትልቅ የፍረጃ ስም ነው። Monophysite ማለት የግሪክ ቃል ሲሆን አንድ ነጠላ ባሕርይ ማለት ነው ይሄም የአውጣኪ አስተምህሮ ሲሆን በኢየሱስ ውስጥ የመለኮት ባሕርይ ብቻ ነው ያለው መለኮት ስጋን ውጦታል በኢየሱስ ውስጥ የስጋ ባሕርይ የለም ሲል አስተምሯል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና ጠቅላላ አኃት ጽብሐውያን ኦርቶዶክስ(Oriental Orthodox) አብያተ ክርስቲያናት ይህ የአውጣኪን ትምህርት አንቀበልም እኛ በክርስቶስ አንድ ባሕርይ አለ ብንልም አንድ ነጠላ ባሕርይ ግን አንልም በተዋሕዶ እና በተአቅቦ ያለ አንድ ጥምር ባሕርይ እንላለን እንጂ ይህን አስተምሮአችንን የሚገልጽ የግሪክ ቃል ሚአፊሲስ (Miaphysis) ነው Mia እንደ Mono አንድ ነጠላ ነገርን የሚገልጽ ሳይሆን በተዋሕዶ ያለ አንድነትን የሚገልጽ ነው መለኮት እና ስጋ የተዋሐዱ ቢሆንም አንዱ አንዱን ሳያጠፋው በተአቅቦ (በመጠባበቅ) በአንድ ኢየሱስ ውስጥ አሉና። Oriental Orthodoxን Monophysite ብሎ መፈረጅ የተጀመረው አሁን ሳይሆን በ451 ዓ.ም ከኬልቄዶን(Chalcedon) ጉባኤ ጀምሮ ጀምሮ ነው ካቶሊካውያን ሚሺነሪዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በጀመሩበት ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይሄን ፍረጃ በመከተል ብዙ ጽሑፎችን ጻፉ አሁን ያሉ የምእራባውያን ጸሐፊዎችም እነዚህን የሚሽነሪዎችን ጽሑፎች ምንጭ በማድረግ በሚያሳዝን ሁኔታ አሁንም ቤተ ክርስቲያንን አውጣኪያዊ እያሏት ነው። የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮሽ ምንድነው ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ከውጪ ምእራባውያን ያገኘውን ቀጥታ ገልብጧል። ስለ ነገር ሃይማኖት በመንገስት የሚወጡ ጽሑፎች ሲነበቡ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል የMoshe History Module ላይ ያለኝ ቅሬታ ይሄ ብቻ አይደለም ሌላውን በሌላ ጽሑፍ መጣበታለው።
👍 7 ❤ 4 🥰 1
18 August 2023
ኪ
22:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
መለኮታዊ ብርሃን: ደብረ ታቦር🌟

የታቦር ተራራ በደመና ተሸፈነ አከባቢውም በነጓድጎድ ድምፅ ተዋጠ ፤ የጌታ ኢየሱስ ፊትም በራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ኾነ። እነ ጴጥሮስ ደነገጡ ፣ ተርበተበቱ ይህ የሚያዩት ብርሃን እንደሚያውቁት አይነት ብርሃን አይደለም። የፀሐይን ብርሃን ያውቁታል ይህ የሚያዩት ብርሃን ግን የተጠፈረስ አይደለም መለኮታዊ ነው እንጂ ። ምንጩም ፀሐይ ሳትሆን ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፣ ለካስ ሰው ብቻ መስሎ ቢታያቸውም እርሱ የአማልክት አምላክ ነው ፣ ብርሃን ከመፈጠሩ በፊት የነበረ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው  ።  ታቦር ሆይ የጸና ተራራ ሳለህ መነሳትህ ስለምንደር ነው? እግዚአብሔር ያድርብህ ዘንድ ወዷልና (መዝ 67:16) አንተም አርሞንኤም ሆይ ብርሃኑ ደርሶሃልና በጌታህ ስም ደስ ይበልህ ( መዝ 87:12)🏔️✨

ሙሴ እና ኤልያስም ብሉይ ኪዳን የሐዲስ ኪዳን ጥላው አይደል እንዴ ብለው ሕግ እና ነቢያትን ወክለው ለአምላካቸው ይመሰክሩ ዘንድ በታቦር ተገኙ እንጂ ዝም ይሉ ዘንድ አላስቻላቸውም። ኢየሱስ ግን የሚመሰክርለት ሰው ብቻ ሳይሆን "የምወደው ልጄ ይህ ነው" ሲል የሰማይ አባቱ ነው ።

ጴጥሮስ ትእይንቱ ቢያስደምመው የክርስቶስን ያለተፈጠረ ብርሃን እያየ ሁል ጊዜ ይኖር ተመኝቶ "በዚህ ብንኾን ለእኛ መልካም ነው" ሲል ጠየቀ። ጴጥሮስ ሆይ ለአንተስ ዘላለም የክርስቶስን ብርሃን እያየህ እዛው መኖር መልካም ነበር ነገር ግን የክርስቶስ ብርሃን አምፖል ለዓለም ኹሉ ይበራ ዘንድ ከፍ ብሎ በእንጨት ላይ መሰቀል ነበረበትና በዛ መኖሩ መልካም አይደለም።

ደብረ ታቦርን ስናከብር እንደ ታሪክ እያወራነው ብቻ አይሁን ይህን ክስተት መነሻ አድርገን ከዕለት ተዕለት ሕይወታችን ጋር እናገናኘው እንጂ። በጥርጣሬ ጊዜያት፣ የክርስቶስ አንጸባራቂ ክብር ኹል ጊዜ በልባችን ያለውን መሰናክል ያስወግድልን ዘንድ ከእኛ ጋር እንዳለ እናስታውስ። ጨለማ ሲያጋጥመን፣ የእርሱ ብርሃን ወደ ርህራሄ፣ ይቅርታ እና ፍቅር ይምራን። 🌟

የክርስቶስ ብርሃን በእኛ እንዲበራ ልባችንን እና አእምሮአችንን እንለውጥ። ደቀ መዛሙርቱ ከመለኮታዊው ጋር በመገናኘታቸው ለዘላለም እንደተለወጡ፣ እኛም በፍቅሩ እንለወጥ። ✨🕊️

እንኳን ለደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ! ይህ ቀን በውስጣችን ያለውን የመለኮታዊ ብርሃን ብልጭታ ያቀጣጥል እና ዓለምን በፍቅር እና በጸጋ እንድናበራ ኃይል ይስጠን!
🥰 2 ❤ 1
22:53
21 August 2023
ኪ
03:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
🌟 ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ 🌟

ነሐሴ 15 ቀን ለግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ባለውለታ መምህር ቅዱስ ሀቢብ ጊዮርጊስ ይታሰበል።

🙏 የሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊርጊስ ጉዞ የጀመረው በዘፍጥረት መጽሐፍ እንደተገለጸው ቀዳማዊ ጨለማ በሚመስል የሃይማኖት ትምህርት እና እውቀት ውስን በሆነበት ዘመን ነው። ነገር ግን፣ “ብርሃን ይኹን” የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ብርሃንን እንዳስገኘ ኹሉ፣ የሐቢብ ጊዮርጊስ መምጣት ይህንን መለኮታዊ ድንጋጌ አንጸባርቋል—በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚፈጥር ብሩህ ሰው ነበርና።

🌞 ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ስለ ሀቢብ ጊርጊስ እንዲህ ባማረ ቃል ይናገራሉ።

"መምህራችን ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊርጊስ... ሕይወቱን የጀመረው የሃይማኖት ትምህርት እና እውቀት ከሞላ ጎደል ውስን በሆነበት ዘመን ነው... ኦሪት ዘፍጥረት እንደሚገልጸው ከዚያም እግዚአብሔር 'ብርሃን ይኹን' አለ ብርሃንም ኾነ። ብርሃኑም ሀቢብ ጊርጊስ ነበር!"

📖 —ጥበብን፣ ራስን መወሰን እና ለኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የማይናወጥ ቁርጠኝነትን ያንጸባረቀ ሕይወት። በተሐድሶ ሚሽነሪዎች ግፊቶች እና ለውጦች በታየበት ፈታኝ ዘመን፣ የኦርቶዶክስ ክርስትና አስተምህሮቶችን እና ትውፊቶችን ለመጠበቅ ጠንካራ ተሟጋች ሆኖ ብቅ አለ። ሀቢብ ጊዮርጊስ!

🌍 የሀቢብ ጉዞ የጀመረው የሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ አራተኛ ወጣት ደቀ መዝሙር ሆኖ ነው፣ ገና በ17 አመቱ፣ በመላው አገሪቱ ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ በማሰባሰብ የኮፕቲክ ቲዎሎጂ ኮሌጅ ለማቋቋም ተልእኮ ጀመረ። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በጥረቱ ሥርዓተ ትምህርቱን አስፋፍቶ፣ የግብፅ መንግሥት እውቅናን አረጋገጠ፣ በሥነ መለኮት ትምህርት ላይ የማይረሳ አሻራ ጥሏል። የእርሱን ፈለግ በተከተሉ ደቀ መዛሙርቱም ኹሉም ካህናት የሚኾኑ  ነገረ መለኮት መማር እንዳለባቸው በመደንገግ ቤተ ክህነቱ ላይ የነበረውን የእውቀት ችግር ቀርፏል በዚህም አሁን እንደ ምናያት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለደረሰችበት ልዕልና ፋና ወጊው ኾኗል ሀቢብ ጊዮርጊስ!

📚 የሰንበት ትምህርት ቤቶች ንቅናቄ📚
ወጣት አእምሮን የመቅረጽ አስፈላጊነትን በመገንዘብ ሀቢብ ገና በ24 ዓመቱ የኮፕቲክ ሰንበት ትምህርት ቤት ንቅናቄን በአቅኚነት አስጀመረ። በእሱ ጥረት፣ በመላው ግብፅ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕጻናት በቤተክርስትያን ትምህርት መማር እንዲችሉ ኾነዋል። በዚህም አዲሱ ትውልድ በሰንበት ትምህርት ቤት እምነቱን ፣ እሴቶቹን ፣ እና ባህሉን አውቆ እንዲያድግ ኾኖአል ስለዚህ ሰንበት ትምህርት ቤት ኹሌም ስሙን ያነሳል የሀቢብ ጊዮርጊስን!!

በረከቱ ይደርብን ❤️
👍 4 ❤ 1 🥰 1
03:30
❤ 2
03:30
ኪ
22:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
ተንሥእ እግዚኦ ውስተ እረፍትክ አንተ ወታቦተ መቅደስከ (አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነሥ አንተ እና የመቅደስህ ታቦት) መዝ 131:8

ብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ጥላው ነው ፣  በሐዲስ ኪዳን የሚኾነው ነገር ኹሉ በምሳሌነት ደረጃ ቢኾንም እንኳን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ይገኛል። ዛሬ ግን የእመቤታችንን ትንሣኤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለማየት አንድን የብሉይ ኪዳን ታሪክ ወስደን ከሐዲስ ኪዳን ጋር እያነጻጸርን እንመልከት። ይሄውም የእስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት መውጣትን ነው። ሙሴ እስራኤላውያንን እየመራ ከግብጽ ባርነት ማውጣት ውስጥ የክርስቶስን ዓለምን ከኃጢአት ባርነት እየመራ ማውጣት እንመለከታለን። ምክንያቱም ክርስቶስ እራሱ መጻሕፍትን ኹሉ መርምሩ እነርሱም ስለ እኔ ይናገራሉ ይለናል ኹሉም የብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ ክርስቶስን እንመለከታለን እና። ይህ ታድያ ከእመቤታችን ትንሣኤና እርገት ጋር ምን ያገናኘዋል? እስቲ አንድ በአንድ እንመልከት:

1. ሙሴ እስራኤልን እየመራ ከግብጽ ካወጣ በኋላ ለደብተራ ኦሪቱ መጀመሪያ ስራ የተባለው ቅዱስ ንዋይ የቃልኪዳኑን ታቦት ነው። (ዘጸ 25:8)

2. የቃልኪዳኑ ታቦት እግዚአብሔር አድሮበት ሕዝቡን የሚያነጋግርበት የእግዚአብሔር ማደሪያ ነበር።

3. የቃልኪዳኑ ታቦት ውስጥ 3 ነገሮች ነበሩበት እነዚህም አሠርቱ ቃላት የተጻፉበት ጽላት ፣ መናን የያዘ መሶበ ወርቅ እና ሳይተክሏት የለመለመች የአሮን በትር ናቸው።

4. ታቦቱ የተሰራው ከማይነቅዝ ከማይበሰብስ የግራር እንጨት ነበር ከዚያም በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር። (ዘጸ 25:10)

ይሄንን ብሉይ ኪዳን ውስጥ ካየን እስቲ ደግሞ ወደ ሐዲስ ኪዳን እንምጣ እስራኤልን ከግብጽ እየመራ ያወጣ ሙሴ የክርስቶስ ምሳሌ ነው። የእስራኤላውያን ከግብጽ ጸአት (መውጣት) በኋላ በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ለነበር ቃልኪዳን ታቦቱ ምልክት ነበር። እንግዲህ አሮጌው ኪዳን አልፎ ሐዲሱ ኪዳን ሲመጣ ደግሞ የሰው ልጆች በክርስቶስ መሪነት ከሲኦል መውጣት ምልክት ታቦት ያስፈልግ ነበር ይህቺም አማናዊት የሐዲስ ኪዳን ታቦት እመቤታችን ናት። እስቲ comparisonኑን አንድ በአንድ እንመልከት

1. ታቦቱ ለመቅደሱ የተሰራ የመጀመሪያ ነዋይ እንደኾነ ኹሉ እመቤታችንም ፍጥረት እንደ አዲስ ይታደስባት ዘንድ የተዘጋጀች አዲሱ ፍጥረት የተባለ ዳግማይ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘባት አዲሲቷ ሔዋን ናት።

2. ታቦቱ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ማደሪያ እንደኾነ ኹሉ እመቤታችንም የእግዚአብሔር ማደሪያ ኾናለች።

3. ታቦቱ ውስጥ አሠርቱ ቃላት እንደነበረ እመቤታችንም አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል ማደሪያ ኾናለች ፣ መናም እንደነበረ  ከሰማይ የወረደ እንጀራ የኢየሱስ ክርስቶስ ማደሪያ ናት እንዲኹም ሳይተክሏት የለመለመች የአሮን በትር እንደ ነበረባት እመቤታችንም ያለ ወንድ ዘር ክርስቶስን አስገኝታለች።

4. ታቦቱ ከማይነቅዝ ከግራር እንጨት እንደተሰራ የእመቤታችንም ስጋ እንዲሁ የማይሰብስ መኾኑ ግድ ይለዋል በንጹሕ ወርቅም እንደተበለጠ እርሷ በወርቅ ፈንታ ንጽሕናን ተጎናጽፋለች።

ይሄ comparison ለአንዳንዶች forced ሊመስላቸው ይችላል ነገር ግን ሉቃስ በወንጌሉ ምእራፍ 1 ላይ የእመቤታችንን ታቦትነት ግልጥ አድርጎ ይነገረናል ይሄም የእመቤታችን ወደ ኤልሳቤጥ ያደረገችው ጉብኝት ላይ ነው ከብሉይ ኪዳን የቃልኪዳኑ ታቦት ጉዞ ጋር ተመሳሳይነት አለውና እስቲ እንመልከት ፡

ዳዊት “ተነሥቶ ሄደ” (2ሳሙ 6፡2)
ማርያም “ተነሥታ ሄደች” (ሉቃስ 1:39)

“የእግዚአብሔርን ታቦት” ለማምጣት ወደ “ባአል-ይሁዳ” (ማለትም፣ የይሁዳ ተራራማ አገር) (2ሳሙ 6፡2)
ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት ወደ “ኮረብታማው የይሁዳ አገር” (ሉቃስ 1፡39)

ዳዊት “የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ይመጣል?” በማለት ታቦቱን ለመቀበል ብቁ እንዳልነበረው ተናግሯል። (2ሳሙ 6፡9)
ኤልሳቤጥ ማርያምን ለመቀበል ብቁ እንዳልነበረች በመግለጽ “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ይህ ስለ ምን ተሰጠኝ?” በማለት ተናግራለች። (ሉቃስ 1:43)

ታቦቱም ወደ አቢዳራ ቤት ገባ (2ሳሙ 6፡10)
ማርያም ወደ “ዘካርያስ ቤት” ገባች (ሉቃስ 1:40)

“ለሦስት ወር” (2ሳሙ 6፡11)
"ማርያም ከእርስዋ ጋር ሦስት ወር ያህል ተቀመጠች" (ሉቃስ 1:56)

"ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ዘለለ" (2ሳሙ 6:16)
ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ በኤልሳቤጥ ማኅፀን ውስጥ “ዘለለ” (ሉቃስ 1:41)

በእነዚህ ኹሉ ማስረጃዎች እመቤታችን የሐዲስ ኪዳን አማናዊት ታቦት መኾኗ ተመሠከረ። የእግዚአብሔር ታቦትም ከማይነቅዝ ከማይበሰብስ እንጨት እንደተሰራ ኹሉ የእመቤታችንም ስጋ ይበሰብስ ዘንድ ተገቢ አይደለምና ዳዊት በመዝሙሩ "አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነሥ አንተ እና የመቅደስህ ታቦት"(መዝ 131/132: 8 ) ይላል በእውነት የእመቤታችን ስጋ ሳይበሰብስ ከነፍሷ ጋር ተዋሕዶ ተነስታ ወደ ሰማይ አርጋለችና። ባለራዕዩ ዮሐንስም ከአባቱ ዳዊት ተቀብሎ የእመቤታችንን አርጋ በሰማይ መገኘት እንዲህ ይመሰክራል " በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።" (የዮሐንስ ራእይ 11:19)

በእውነት አማናዊቷ ሐዲስ ኪዳን ታቦት እመቤታችን ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ዐርጋለች። እንኳን ለእመቤታችን የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
👍 3 🥰 1
26 August 2023
ኪ
12:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት

ብሉይ ኪዳንን ስናነብ ስለ መሢሑ ብዙ ትንቢቶችን እናገኛለን የት እንደሚወለድ ፣ ወደ ግብጽ እንደሚሰደድ እንደሚሰቀል ፣ እንደሚነሳ እንደሚያርግ በአጠቃላይ ስለክርስቶስ ያልተጻፈለት ነገር የለም እርሱ የመጻሕፍት ኹሉ ራስ ነውና።

ዛሬ ግን አንድ ትንቢት ላይ ማተኮር ፈለኩ ይኸውም ዳን 9: 24-25 ነው። ዳንኤል ስለ መሢሑ ሲናገር እንዲህ ይላል "
(ትንቢተ ዳንኤል ምዕ. 9)
----------
24፤ ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።

25፤ ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች። "

እስከ ቁጥር 27 ላይ ስናነበው በግልጽ እንደሚነግረን ከኾነ ኃጢአትን ኹሉ ያስተሰርይ ዘንድ መሢሑ ይመጣል ከእርሱ መገደል በኋላም የትንቢትና የራእይ ፍጻሜ ይኾናል ቤተ መቅደሱም ይፈርሳል ከዛ በኋላም የእሕል ቁርባኑም ኾነ የእንሥሳት መሥዋዕት ያበቃል።

ታድያ ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ይሄን ኹሉ የፈጸመ ሌላ ማን አለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመጣ እና በመስቀል ላይ ከተሰቀለ በኋላ በ70 ዓ.ም የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በቄሳሩ ጥጦስ ፈረሰ መሥቃዕት እና ቁርባንም የሚቀርበው በቤተ መቅደስ ውስጥ ብቻ ስለኾነ ከዛ ጊዜ በኋላ እስካኹኑ ጊዜ ድረስ የእንስሳት መሥዋዕት ቀርቦ አያውቅም። እሥራኤል ቤተ መቅደሱን ከዛ በኋላ ለመሥራት ብዙ ጊዜ ሞክራ ነበር ነገር ግን አልቻለችም አኹን ላይ በቤተ መቅደሱ ቦታ ላይ የአል አቅሳ መስጊድ ቆሞ ይታያል ፣ ትንቢትም ኾነ ራእይ በእሥራኤልም ከዛ በኋላ አልተሰማም ኹሉም በመሢሑ መምጣት ታትሟልና።

ነገር ግን ይሄን ኹሉ የትንቢት መፈጸም አይተው አይሁድ አሁንም ኢየሱስ መሢሑ እንደኾነ አላመኑበትም አሁንም ወደ ፊት ሌላ መሢሕ ይጠብቃሉ ፣ በዚህ ግን ቀጥታ ከመጽሐፉ ቃል እና ከታሪክ ጋር ተጣሉ። አሁንም መሢሑ ወደ ፊት ይመጣል የሚሉን ከኾነ እኛማስ እንጠይቃለን "ቤተ መቅደሱ የታል?" "መሥዋዕቱስ የታል? " "ነቢያትስ አሁን አላችሁን?"  ምክንያቱም ቤተመቅደሱም ፣ መሥዋዕቱም ፣ ነቢያትም እስከ መሢሑ ድረስ ይኖራሉ መሢሑ ከመጠ በኋላ ግን ያከትማሉ እርሱ አትሟቸዋልና።

ቅዱስ አትናቴዎስ እኒህን አይሑድ ስለድካማቸው "On the incarnation of the Word (ዲያቆን ያረጋል በእንተ ተሠግዎተ ቃል ሲል ተርጉሞታል)"  በሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ሲል ይወቅሳቸዋል "ስለ ሌሎቹ ትንቢቶች ለተቋውሞዋቸው ምክንያት ሊያገኙ ይችላሉ ስለዚህ ግን ምን ይላሉ?  ዳንኤል የሚናገረው ስለ መሢሑ ክርስቶስ ብቻም አይደለም እርሱን ሰው ብቻም ሳይኾን ቅዱሰ ቅዱሳን ይለዋል እንደገናም እርሱ እስኪመጣ ድረስ ኢየሩሳሌም አትፈርስም ከእርሱ በኋላ ግን ነቢይ እና ራእይ በእስራኤል ያከትማል ይላልና። ... ቅዱሰ ቅዱሳን ክርስቶስ ከመጣ በኋላ አይደለምን ኢየሩሳሌም የፈረሰችው ነቢያትና ራእይም በኢየሩሳሌም ያከተመው"

የኢየሩሳሌም መፍረስ እና የመሥዋዕቱ ማብቃት እንዲው የአጋጣሚ ጉዳይ ብቻ አይደለም የክርስቶስን የሐዲስ ኪዳን መስዋዕትነት ሚና የሚነግረን ነው እንጂ አሁን አማናዊው መሥዋዕት ኢየሱስ መጥቶልና ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የበግ እና የጊደር ደም አላስፈለገንም በገዛ በራሱ ደም ወደ እግዚአብሔር እንቀርባለን እንጂ የቤተ መቅደሱም፣ የሕግና የነቢያት ኹሉ ማኅተም እርሱ መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና።

የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ ✝️

Join 👉🏽 ኪዳን ዘኢየሱስ
👍 3 ❤ 1 🥰 1
28 August 2023
ኪ
17:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕ. 1)
----------
7፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።

8፤ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።

9፤ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
❤ 5 🥰 1
30 August 2023
ኪ
00:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
“ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ
ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብስተ ሕይወት ለዘይበልዖ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋዐ መድኀኒት ለዘይሰትዮ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ በግዐ መድኀኒት ለዘይሠውዖ ከመ ይባርኩነ ይፈኑ አርዳኦ ለጸባኢነ ይጽብኦ ወልታሁ ነሢኦ”
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ ጣፋጭ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚበላው የሕይወት እንጀራ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠጣው የመድኃኒት ጽዋ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚሠዋው የድኅነት በግ ነው፤ ይባርኩን ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን ይላክ፤ ጋሻውን አንሥቶ የሚጣላንን ይጣላው" መቅደመ ተአምረ ኢየሱስ

ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ ! አሜን የጌታ ስም ኹሌ ጣፋጭ ነው !!

Note: ሥዕሉ አሁን መስጊድ ከኾነችው እና እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያስተማሩባት የጥንቷ ቁስጥንጥንያ የአሁኗ ኢስታንቡል ማእከል ቤተ ክርስቲያን አጊያ ሶፊያ (በግሪክ ቅዱስ ጥበብ) ቤተ ክርስቲያን ላይ የነበረ ሲኾን Christ Pantocrator ይባላል። አጊያ ሶፊያን ወደ ጥንት ቤተ ክርስቲያንነቷ ይመልስልን ዘንድ ጸልዩ!
👍 6 🥰 1
31 August 2023
ኪ
00:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቶስ ይመጣል!

ክርስቶስ ይመጣል ፣ ጌታ ይመጣል የዓለም መንግስታት ይገለበጣሉ ኃጥአን ዋይ ዋይ ይላሉ ሙታን ይነሳሉ ተራሮች ይወድቃሉ የእግዚአብሔር ልጅ በክብር ይመጣል ጌትነቱን ለዓለም ሁሉ ይገልጣል!

ዋይ ዋይ ያን ጊዜ ማን ፊቱ ይቆማል የሰማይ ሰራዊት ከበውታል ኪሩቤል በፊቱ ይሰግዳሉ ፣ ሱራፌልም ያሸበሽባሉ ኃይላት ፣ አጋእዝት ሥልጣናት ፣ አርባብ ኹሉም መለከታቸውን ይዘው በፊቱ ይቆማሉ ፣ ዋይ ያን ጊዜ የሰው ልጆች ምን ይውጣቸዋል እነሆ ጌታ መጥቷል መጽሐፍ እንደተናገረው ጌታ መጥቷል! በግርማ በክብሩ ይኸው ይታያል። የወጉትም ከሙታን ተነስተዋል የሰቀሉት ኢየሱስ በክብሩ ፊታቸው ቆሟል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈራርሷል ፣ የዓለም መንግስታት ወዳድቀዋል አላመኑበትም እርሱ ግን በግርማው ይታያል። ዋይ ዋይ ያን ጊዜ ኃጥአን ምን ይውጣቸዋል በፊቱ ይንበረከካሉ ማረን ይላሉ ይንቀጠቀጣሉ ያኔ ግን ጊዜው አልፏል አብቅቷል የምሕረት ጊዜ አብቅቷል አሁን የፍርድ ጊዜ ነው ፣ ፈራጁ በክብር ይታያል ፀሐየ ጽድቅ ፀሐይን በእጁ ይዟል እውነተኛው ዳኛ በመስቀል የፈረዱበት ፊት ቆሟል። የምድር ኃያላን ሃገራት ተርበድብደዋል ፈራጁ ፊታቸው ቆሟል ፍርሃት ምድርን ሸፍኗል የእግዚኢብሔር ልጅ መጥቷል በድብቅ ሳይኾን በግልጥ መጥቷል! ክርስቶስ መጥቷል። ብር እና ወርቅ ካሁን በኋላ አይሰራም ንጉሱ ለዘላለም ሊነግስ መጥቷል አቤት የዓለም ኃያላን ሃገራት ሃብታቸውን ምን ያድርጉት ፣ የአረብ ሃገራት ነዳጃቸው ምን ይኹን ኹሉም ሊጠፋ ነው ኢየሱስ መጥቷልና!!

ጻድቃን ግን ይደሰታሉ ማራናታ ጌታ ሆይ ቶሎ ና ያሉት ጌታቸው መጥቷል መጽሐፍ እንደ ተናገረ መጥቷል በኃጥአን ዘንድ ፍርሃት ሲሰማ በቅዱሳን ዘንድ ግን ደስታ ይሰማል "እነሆ ጌታ እነሆ ጌታ" እያሉ ይጮሃሉ ንጉሳቸው መጥቷል የጠበቁት መጥቷል ዮሐንስ ሆይ ደስ ይበልህ ማራናታ ያልክለት ጌታ መጥቷል ፣ ዳዊት ሆይ ደስ ይበልህ ንግስናን ለዘላለም ይነግስ ዘንድ ንጉሱ መጥቷል ለፍርድ መጥቷል በግራ ለቅሶ ይሰማል በቀኝ ግን ደስታ ይሰማል በላይ የመላእክት መለከት ድምጽ ይሰማል አሁን ኹሉም አብቅቷል ተፈጽሟል እነሆ ጌታ መጥቷል ፈጻሚው ጌታ መጥቷል ሁሉም ነገር ተፈጽሟል።

" እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ኹሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ኹሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።"
(የዮሐንስ ራእይ 1:7)

በዛ አስጨናቂ ሰአት በቀኙ ያቆመን ዘንድ በሃይማኖት በምግባር እንጽና ባልጠበቅነው ሰአት ይመጣልና።

Note: Inspiration from Serbian Orthodox chant about the Second Coming of Christ "Pobedna Pesma" (Song of Victory)

Join 👉🏽 ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 4 🥰 1
5 September 2023
ኪ
23:59
ኪዳን ዘኢየሱስ
በአራጆቹ ፊት ምንም ያልተናገረ የዋሕ በግ ፣ ዓለም ኹሉ በእጁ ኾኖ ኹሉን ማጥፋት ሲችል የመታረጃ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ሞቱ ሲነዱት ዝም ያለ በግ የዓለምን ኹሉ ኃጢአት ተሸክሞ ስለእኛ የቆሰለ በግ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ዛሬም በቤተመቅደስ ስጋውን የምንቆርሰው ፣ ደሙንም የምናፈሰው በላይ በሰማያት በዙፋኑ ተቀምቶ አንድ ጊዜ ባፈሰሰው ደም ኃጢአታችንን የሚያስተሰርየው አምልኮን ኹሉ የሚቀበለው የታረደው በግ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ክብር እና ምስጋና አምሎክትና ውዳሴ በላይ በሰማያት ፣ በታች በምድርም በጥልቆችም ኹሉ ለታረደው በግ ይኹን አሜን!!

" መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና ።"
(የዮሐንስ ራእይ 5:9-10)
🥰 2
9 September 2023
ኪ
10:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኖላዊነ ኄር (መልካሙ እረኛችን)

"እግዚአብሔር በደብረ ሲና በእጁ አሥር ነገር ዘራ የሚያጭደውም በታጣ ጊዜ አንድ ልጁን ቢልከው እንግዳ ነውና በዳዊት ቤት አደረ ፤ ይህንም አዝመራ 33 ዓመት ሙሉ ብቻውን አጭዶ በጨረሰ ጊዜ አባቴ አባቴ አመስግነኝ አለ ፤ ምነው ከእረኛ ቤት ተወለደ ብለን አምተነው ነበር ፤ አሁንስ እርሱ ራሱ እረኝነቱን ገለጠው ፤ ለካ የበጎች እረኛ እኔ ነኝ እያለ ከሰማይ ተሰዶ የመጣ በጎችን ሊጠብቅ ነው። " (መጽሐፈ ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ)

መልካም እረኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ምድራዊ እረኛ በጎቹን ቢጠብቅ ወይ ሊሸጣቸው ወይም አርዶ ሊበላቸው ነው ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በጎቹ እንዲበሉት እንደ በግ የታረደላቸው መልካም እረኛ ነው። እንዴት ይገርማል በግም እረኛም መኾን ፤ ለሌላ ለማንም አይቻልም ሰውም አምላክም ለኾነው ለእርሱ ግን ይቻለዋል።
🥰 2 🙏 1
11 September 2023
ኪ
22:18
ኪዳን ዘኢየሱስ
በአዲሱ ዓመት አዲስ ማንነት

" ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢኾን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ኹሉም አዲስ ሆኖአል።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17)

በክርስቶስ በኾነ ጥምቀት አሮጌው አዳማዊ ማንነታችን ተወግዶ ክርስቶሳዊ ማንነትን ለብሰን አዲስ ፍጥረት ኾነናል ፤ አዲስ ፍጥረት የኾነውም ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኖር ዘንድ ነው።

እንዲሁ አሁን አሮጌው ዘመን አልፏል እነሆም አዲሱ ዓመት መጥቷል ፤ በዚህ አዲስ ዓመትም ክርስቶሳዊ ማንነታችንን ከሚያደበዝዘው ኃጢአት ርቀን በአዲሱ ክርስቶሳዊ ማንነታችን ለመኖር ይበልጥ እንበርታ ፤ " የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:3)

መልካም አዲስ ዓመት!
👍 2 🥰 2 🙏 1
16 September 2023
ኪ
10:58
ኪዳን ዘኢየሱስ
አምላክን አውሬ የሚያደርገው የጸጋ ብቻ ትምህርት

በ16ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ተሐድሶ እቅስቃሴ ላይ ጸጋ ብቻ የሚለው አስተምህሮ ጎልቶ ይወጣ ነበር። ጸጋ ብቻ የሚለው አስተምህሮ "ሰዎች ከአዳም በወረሱት ኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔርን መምረጥ እስኪያቅታቸው ድረስ በኃጢአት ሞተዋል ስለዚህ ሰው ሊድን የሚችለው ከእግዚአብሔር በኾነ ጸጋ ብቻ እንጂ ከራሱ አይደለም ሰውማ በወረሰው ኃጢአተኝነት ምክንያት ወደ ሞት ይሄዳል እንጂ ወደ ድኅነት መድረስ አይችልም" የሚል ነበር። አስቀድሞ የመወሰን (predestination) እና የመመረጥ (election) ጽንሰ-ሀሳብ በተፈጥሮ የመነጨው ከእነዚህ ሃሳቦች ነው ምክንያቱም ሰዎች እራሳቸውን ማዳን ካልቻሉ በክርስቶስ በኩል የአማኞችን መዳን የጀመረውና ያስፈፀመው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

በተለይ John Calvin የተባለው የተሐድሶ አቀንቃኝ ከኹሉም በላይ በዚህ አስቀድሞ ውሳኔ(predestination) ትምህርት የታወቀ ነው። የCalvin አስቀድሞ ውሳኔ አስተምህሮ TULIP በሚለው ምህጻረ ቃል ይገለጻል።

T= Total Depravity ማለትም ሰዎች ከአዳም በወረሱት ኃጢአተኛ ባሕርይ ምክንያት መልካም ነገርን መምረጥ እስከማይችሉ ድረስ በኃጢአት ሞተዋል ስለዚህ ሰዎች በራሳቸው እግዚአብሔርን መምረጥ አይችሉም።

U= Unconditional Election ማለትም እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ እና አላማ ላይ በመመስረት የተወሰኑ ግለሰቦችን እንዲድኑ እና የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ ይመርጣል ። ምርጫውም በግለሰቦች አምነት ወይም መልካም ሥራ ላይ የተመሰረተ አይደለም በቃ አምላክ በራሱ ፈቃድ እንዲድኑ የሚፈልጋቸውን ሰዎች ያልምንም ቅድመ ሁኔታ(እምነትም ኾነ ስራ ባይኖራቸው) ይመርጣል።

L= Limited Atonement ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሞተው እና የኃጢአትን ክፍያ የከፈለው ለሰዎች ኹሉ ሳይኾን አስቀድሞ እንዲድኑ ለመረጣቸው ለጥቂቶቹ ብቻ ነው።

I= Irresistible Grace ማለትም እነዚህ እንዲድኑ የተመረጡት እና በመስቀል ዋጋ የተከፈለላቸው ሰዎች እግዚአብሔር ሲመርጣቸው እምቢ ማለት አይችሉም በጸጋው ኃጢአተኝነታቸውን ለውጦ እርሱን እንዲመርጡ ያደርጋቸዋልና።

P= Perseverance of the Saints ማለትም እነዚህ ለድኅነት የተመረጡት ሰዎች ድኅነታቸውን እዳያጡ ዘላለም በጸጋው ይጠብቃቸዋል ስለዚህ አንዴ የዳነ ሰው ድኅነቱን መቼም አያጣውም።

እንግዲህ ፕሮቴስታንቶች በተለይ ደግሞ ካልቪኒስቶች በጸጋው ብቻ ድኛለው ሲሉ እንዲህ ማለታቸው ነው (ነገር ግን Jacob Arminius የተባለ ሰውን አስተምህሮ ተከትለው በዚህ አስቀድሞ ውሳኔ ትምህርት ማያምኑ ፕሮቴስታንቶችም አሉ እነርሱም Arminians ይባላሉ)። ከላይ ሲታይ ደስ ይላል እኔ ምንም ከሌላው ሰው የተለየ ነገር ሳላደርግ እግዚአብሔር ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ እንድድን በጸጋው መረጠኝ ሲባል ደስ ሊያሰኝ ይችላል ነገር ግን ያልተመረጡት ሰዎችስ? ያልተመረጡት ሰዎችም እኮ የተለየ ምንም አላደረጉም ነገር ግን እግዚአብሔር ስላልመረጣቸው ምክንያት ዘላለም በእሳት ይቃጠላሉ። ምን አይነት ጨካኝ አምላክ ነው ይሄ አምላክ? ኹሉንም ሰው ማዳን እየቻለ ድኅነትም በሰዎች ላይ የማይመሰረት ከኾነ ለምን ኹሉንም ሰው አያድንም?

እስቲ በምሳሌ እንየው አንድ አባት 4 ሕፃናት ልጆች አሉት እነዚህም ልጆች መንገድ ላይ እየተሯሯጡ ሳለ መኪና ሊገጫቸው ይደርሳል አባትየውም 4ቱንም ማዳን ይችላል ነገር ግን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አባትየው 2ቱን ልጆች ብቻ ያድናል አስቡት 4ቱንም ማዳን ሲችል 2ቱን እንዲሞቱ ተዋቸው ምን አይነት አውሬ እና ጨካኝ አባት ነው። ይህ የጸጋ ብቻ ትምህትም እግዚአብሔርን እንዲህ አይነት ጨካኝ እና አውሬ ነው የሚያደርገው።

እኛ ግን እንዲህ እንላለን እግዚአብሔር ማንም ይጠፋ ዘንድ አይፈልግም የሚጠፉትም እግዚአብሔር ስላልመረጣቸው ሳይኾን እነርሱ ስላልመረጡት ነው "ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።"
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:9)
❤ 6 🥰 1
19 September 2023
ኪ
21:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ጠላት የማይደፍረው ጽኑ ቅጽራችን የደስታ መገኛ መግቢያ መውጫ በራችን ሕይወትን የሚያድል ምግባችን የመንፈስ እርካታን የሚሰጥ መጠጣችን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" ትምህርተ ኅቡዓት

የኢየሱስ ፍቅር ❤️ በልባችን ይደር።
🙏 13 🥰 1
20 September 2023
ኪ
12:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
ንግስተ ሰማይ ወምድር

እመቤታችንን የሰማይ እና የምድር ንግስት ስንላት የሚቃወሙ ሰዎች አሉ ነገር ግን የዕብራውያንን የንግስና አሰጣጥ ቢያውቁ ለመረዳት ከባድ አይኾንም ነበር።

እግዚአብሔር ንግስናን ለዳዊት እና ለዘሩ ቃል ከገባ በኋላ በክፉው ሳኦል ምትክ ዳዊት የእስራኤል ንጉስ ኾኗል ይህ ዳዊታዊ መንግስትም በልጆቹ ቀጥሏል። ነገር ግን በዚህ ዳዊታዊ መንግስት ውስጥ አንድ ክፉ ልማድ ነበር እርሱም ነገስታቱ ብዙ ሚስቶች እና እቁባቶችን ይይዙ ነበር እራሱ ንጉሱ ዳዊት እና ልጁ ሰሎሞንም ጭምር  ብዙ ሚስቶች እና እቁባቶች ነበሯቸው ስለዚህ ከነዚህ ኹሉ ሚስቶች መካከል ንግስት የምትኾነዋ ሴት አጨቃጫቂ ይኾን ነበር። ለዚህም የቀረበው መፍትሄ ነገስታቱ ብዙ ሚስቶች ቢኖራቸውም አንድ እናት ብቻ ነው ያላቸው ስለዚህ ንግስት ተብላ ምትቀመጠዋ ሴት የንጉሱ እናት ነበረች። እነዚህ እናቶችም በእብራይስጥ גְּבִירָה‎ (gəḇīrā; ገቢራህ) ይባላሉ ትርጉሙም እመቤት ወይም እናት ንግስት ማለት ነው።  ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እንይ እስቲ:

" ለንጉሡና ለንጉሥ እናት #ለእቴጌይቱ(ገቢራህ)። የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ በል። "
(ትንቢተ ኤርምያስ 13:18)

" አሳ በማምለኪያ ዐፀድ ጣዖት ስለሠራች እናቱን መዓካን #እቴጌ(ገቢራህ) እንዳትሆን ሻራት፤ ጣዖትዋንም ሰበረው፥ በቄድሮንም ፈፋ አጠገብ አቃጠለው። "
(መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 15:13)

" ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ወንድሞች ጋር ተገናኝቶ። እናንተ እነማን ናችሁ? አለ። እነርሱም። እኛ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡንና #የእቴጌይቱን(ገቢራህ) ልጆች ደኅንነት ለመጠየቅ እንወርዳለን አሉት።"
(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 10:13)

" ንጉሡም አሳ እናቱን መዓካን በማምለኪያ ዐፀድ ጣዖት ስላደረገች #ከእቴጌነትዋ አዋረዳት፤ አሳም ምስልዋን ቈርጦ ቀጠቀጠው፥ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው። "
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 15:16)

" ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እናቱም #እቴጌይቱ(ገቢራህ) ጃንደረቦቹም የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወው በኋላ ነው። "
(ትንቢተ ኤርምያስ 29:2)

እንግዲህ በዳዊት መንግስት ላይ የነገሱ ነገስታት እናቶቻቸው ገቢራህ- እናት ንግስት ተብሎ የመጠራት እና በቤተመንግስት ውስጥ ታላቅ ክብር እንዳላቸው ካየን ወደ ሐዲስ ኪዳን እንሂድ እና በዳዊት ዙፋን ለዘላለሙ ይነግሳል ስተባለው ንጉስ (ሉቃ 1:32) ክርስቶስ እናውራ። ክርስቶስ በዳዊት ዙፋን የነገሰ ምድራዊ ንጉስ ብቻ ሳይኾን የሰማይና የምድር ነጉስ ነው ለዘላለምም አይሻርም። እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም የማትሻር ገቢራህ ንግስተ ሰማይ ወምድር ናት አባቷ ዳዊት ስለእርሷ እንዲህ መስክሯልና " የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና #ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።"
(መዝሙረ ዳዊት 45:9)

"አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማያት" አባ ጽጌ ድንግል ❤️
❤ 2 🥰 1
23 September 2023
ኪ
21:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 10)
----------
34፤ በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።

35፤ ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤

"ኢየሱስ ሰላምን ለማምጣት ካልመጣ ለምን ነቢያት ኹሉ ሰላምን የምስራች አድርገው ሰበኩ? ምክንያቱም እውነተኛ ሰላም እንዲህ ስለኾነ ነው እሱም በሽታ ተቆርጦ ሲጣል ፣ ካንሰር በቀዶ ሕክምና ሲወገድ ያኔ ነው እውነተኛ ሰላም የሚማጣው። ካንሰሩ ወደሌሎች ጠናማ አካላት እንዳይሰራጭ ዶክተር መዳን የማይችለውን አካል በከባድ ቀዶ ሕክምና(radical surgery) ቆርጦ እንደሚጥል ኹሉ ሰማይ እና ምድር አንድ ይኾኑ ዘንድ ሰማያዊው ሐኪም ክርስቶስ ሰላም ይመጣ ዘንድ ለእርሱ የማይኾኑትን ኃጥአን በኃጢአታቸው ጻድቃኑን እንዳይበክሉ ቆርጦ መጣል አለበት" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፣ ድርሳን ትርጓሜ ወንጌለ ማቴዎስ (Saint John Chrysostom Homily on Gospel of Matthew)
❤ 5 🥰 1 🙏 1
24 September 2023
ኪ
23:08
ኪዳን ዘኢየሱስ
''የኔ ውድ ኢየሱስ አዳኜ፣ በልቤ ውስጥ በጥልቀት ስለተጻፈ፤ ልቤ ቢከፈት እና ቢቆራረጠ የኢየሱስ ስም በእያንዳንዱ ቁርጥራጭ ላይ ተጽፎ እንደሚገኝ እተማመናለሁ'' ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)

ኢየሱስ የልቤ ንጉስ ❤️
❤ 13 🥰 2 👍 1
26 September 2023
ኪ
09:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
We believe in One Holy catholic and Apostolic Church of Christ. Oriental Orthodoxy ❤️

ከኹሉ በላይ በኾነች በአንዲት ቅድስት ኩላዊት እና ሐዋርያዊት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ጽብሐውያን ኦርቶዶክስ ❤️
🥰 2 👍 1
09:43
09:43
09:43
3 October 2023
ኪ
08:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለቀልድ ያህል 🙌😁
🤣 14 👎 2
6 October 2023
ኪ
19:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሚሰማ ሰው እርር ይበል ማርያም አማላጅ ናት!

ኦርቶዶክሳውያን ይሄን አነጋገር ማቆም አለብን የማርያም ስም ማብሸቂያ ፣ መበሻሸቂያ አይደለም። እኛ የማርያምን ምልጃ የምናምነው ከልጇ ዘንድ ለምና ምሕረትን ታሰጠናለች ብለን ነው እንጂ ሌሎቹን ለመናደድ ፣ ለማብሸቅ አይደለም ። በእነርሱ በኩልም አዳኝ የኾነውን እና ጉልበት ኹሉ የሚሰግድለትን የኢየሱስን ስም ለማብሸቂያ ሲጠቀሙት በእኛ በኩል ደግሞ የመልስ ምት ይመስል የማርያምን ምልጃ ለማብሸቂያ አውለነዋል "አንድ ኹለት ሦስት አራት ማርያም አማላጅ ናት ፣ አምስት ስድስት ሰባት መናፍቅ የካዳት" የሚል መዝሙር እስክንዘምር ድረስ የማርያምን ምልጃ ለመበሻሸቂያ ማዋላችን ያሳዝናል ፤ የዚህ መበሻሸቅ ትርፉ የኾነውም "ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም" የሚል በቤተክርስቲያን አባቶች ዘንድ ማይታወቅ ትምህርት መፈክር እስኪኾን ድረስ ደርሷል። እኛ የወላዲተ አምላክን ምልጃ እናምናለን በምልጃዋ ወደ ልጅዋ ለምና ምሕረትን ታሰጠናለች ፣ ምሕረትን የሚሰጠን ደግሞ ደሙን ለዓለም ኹሉ ያፈሰሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የኃጢአት ስርየት ያለ ደም የለምና ።(ዕብ 9፡22) እኛ የማርያምን ምልጃም የምናምነው ልጅዋ በደሙ ድኅነትን እንዲሰጠን እንድትለምንልን እንጂ መናፍቃንን የማናደድ ስላልኾነ "የሚሰማ ሰው እርር ይበል ማርያም አማላጅ ናት!" የሚሉ መፈክሮች ከእኛ ሊርቁ ይገባል።
👍 13 ❤ 3 🥰 2
10 October 2023
ኪ
09:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በአርመን ንጉስ ድርጣድርስ ዘንድ ለሰማዕትነት የቀበለችበት ዕለት ነው። ከዚ ጋር ተያይዞ ትክክለኛውን የቅድስት አርሴማ ሦዕል መለየት አለብን ብዙ በገበያ ላይ የቅድስት አርሴማ እየተባሉ የሚሸጡት ሥዕላት የሌሎች ቅዱሳን ናቸውና።
❤ 9
09:27
09:27
09:27
12 October 2023
ኪ
08:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስራኤል ታሸንፋለች!

ከእስራኤል እና ከፍልስጥኤም ጦርነት ጋር ተያይዞ ብዙ ክርስቲያኖች ከእስራኤል ጎን ነን ሲሉ እሰማለው። ይሄንንም የሚሉበት ምክንያት በመጽሐፍ ቅዱስ ለእስራኤል ብዙ ቃል ኪዳን ስለ ተገባላቸው እና የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለተባሉ ነው። ነገር ግን አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር ከእስራኤል ዘስጋ እግዚአብሔር የራቀው መሢሑ ኢየሱስን ያልተቀበሉ ጊዜ ነው ፤ ክርስቶስን ባለመቀበላቸው ምክንያት ለእስራኤል የተገባው ቃልኪዳን ኹሉ እስራኤል ዘነፍስ ለተባልን ለክርስቲያኖች ኾኗል ፤ የምናፍቃትም ኢየሩሳሌም ምድራዊቷን ሳይኾን ሰማያዊቷን ኢየሩሳሌም ነው።

አይሁዳውያን ክርስቶስ ላይ የሚናገሩት ስድብ ቢሰማ የሚቀፍ ነው ክርሶቶስን ዲቃላ በወንጀሉ የተቀጣ ወንበዴ ሲሉት ድንግል ማርያምን ደግሞ በዝሙት ስለጸነሰችው ለመሸፈን ብላ ከመንፈስ ቅዱስ ነው የጸነስኩት ያለች ዘማዊት ናት እያሉ አሰቃቂ ስድብ ነው የሚሳደቡት ፤ ታላቅ የክርስቲያን ጠላቶችም ናቸው በኒቅያ የተሰበሰቡ 318ቱ ሊቃውንት እኮ ክርስቲያኖች ከአይሁድ ጋር ፋሲካን እንዳያከብሩ ብለው ነው ፋሲካን በየዓመቱ በተለዋዋጭ ቀን ያደረጉት፣ በሀገራችን በክርስትና ላይ ታላቅ ጥፋት ያደረሰችው ዮዲት ጉዲት ራሱ እኮ የአይሁድ ንግስት ናት። ስለዚህ አይሁዳውያንን ካሰብን እንደእነርሱ የክርስቲያን ጠላት የለምና ከእስራኤል ጎን ነን ስንል በደምብ እናስብበት እንደ ሕዝብስ ካሰብን በእስራኤልም በፍልስጤምም ዘንድ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች አሉና።

እኔስ ክርስቶስ ሰላምን በመካከላቸው እንዲያወርድ ከክርስቶስ ጎን ነኝ!

N.B. እስራኤል ታሸንፋለች ስል ያሁኗን እስራኤል ሀገር ሳይኾን አዲሲቷ እስራኤል የተባለችን የክርስቶስ ሙሽራ ቤተክርስቲያንን ነው እርሷን የገሀነም ደጆች አይችሏትምና።
🔥 8 🥰 2
15 October 2023
ኪ
10:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

" መጽሐፍ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የተሾምሽ የቃል ኪዳን ምልክት ነሽ ብሎ እንደተነገረ፣ የሰንበታት ሰንበት የብርሃን ቀን ማርያም ሆይ፤ አበባ ያላት የገነት ጻድቃን በአንቺ ይደሰታሉ፤ ኃጥአንም በአንቺ ከደይን ይወጣሉ"

እውነተኛውን የዕረፍት ቀን ካስገኘችልን ከእመቤታችን በተወለደ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ ሰንበት ይሁንልን።

ብርሃን ዕለተ ብርሃን ❤️
❤ 10 👍 1 🥰 1
16 October 2023
ኪ
22:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
ታቦት ተሽሯል!

በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ይገለጥበት ዘንድ መቅደስን ስሩልኝ ብሎ በመቅደስ ውስጥም ታቦትን (Ark) ይሰራ ዘንድ ሙሴን አዘዘው ፤ ይህም ታቦት የእግዚአብሔር ማደርያ መገለጫውም ጭምር ነበር ፤ እንዲሁም በውስጡ አሠርቱ ቃላት የተጻፉበት ጽላት ማደርያ ነበር።

ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ግን አማናዊት የሐዲስ ኪዳን ታቦት የተባለችው እና እግዚአብሔር ያደረባት እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ስለዚህም የሐዲስ ኪዳን ታቦት(Ark of the new Covenant) ትባላለች ፣ እንዲሁም እግዚአብሔር በሐዲስ ኪዳን ዳግም ስለፈጠረን በእኛ በምእመናን ልብ ውስጥ ያድራል ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይለናል " የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:16)። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር በምእመናን ልብ ውስጥ ስለሚያድር የብሉይ ኪዳኑ ታቦት አገልግሎቱ አብቅቷል። ኦርቶዶክሳውያን ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት መከራከር አቁሙ ቤተ ክርስቲያናችን የብሉይ ኪዳኑ ታቦት አገልግሎቱ ቀጥሏል ብላ አታስተምርም ፣ በብሉይ ኪዳን ታቦትም ምንም ሥርዓት አትፈጽምም አንድ የብሉይ ኪዳን ታቦት ነው ያላት እርሱም በአክሱም ጽዮን በቅርስነት ተቀምጧል እንጂ ሥርዓት አይፈጸምበትም በብሉይ ኪዳን በታቦቱ ላይ የመሥዋዕቱ ደም ይረጭ ነበር አሁን ግን እኛ የእንስሳ መሥዋዕት የለንም አማናዊ መሥዋዕታችን ኢየሱስ የእንስሳትን መሥዋዕት አስቀርቷልና።

ታድያ የብሉይ ኪዳን ታቦት ከቀረ አሁን በቤተ ክርስቲያን ታቦት አለ የምንለው ምንድነው? በአጭሩ ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ከብሉይ ኪዳኑ ጋር ስሙ ተመሳሰለ እንጂ የብሉይ ኪዳን ታቦት (Ark) የለንም እኛ ያለን አሁን መሠዊያ(Altar) ነው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "መሠዊያ አለን፥ ከእርሱም ሊበሉ ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ መብት የላቸውም።" (ወደ ዕብራውያን 13:10) መሠዊያ ስንል ምን የሚሠዋበት ነው ካላችሁ አማናዊ የሐዲስ ኪዳን መሠዋዕት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት(የሚሠዋበት) መሠዊያ ነው። ታቦት ማለት ማድርያ ማለት ስለኾነ ክርስቶስ በሥጋና ደሙ ላይ በአካል ስላለ ከብሉይ ኪዳኑ ጋር በተመሳሳይ ስም ታቦት ብለን ጠራነው እንጂ መሠዊያችን ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት ጋር በምንም አይመሳሰልም። የብሉይ ኪዳኑ ታቦት 4 ካህናት የሚሸከሙት ሳጥን ኾኖ ውስጡ አሠርቱ ቃላት የተጻፉበት ጽላት ያለበት ሲኾን ፣ የሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ግን ሳጥን ሳይኾን ሰሌዳ ነው በእርሱም ላይ የተጻፈው አሠርቱ ቃላት ሳይኾን አልፋ እና ኦሜጋ የሚለው የክርስቶስ ስምና "በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ፥" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:10) የሚለው ጥቅስ ነው።

ለማጠቃለያ ያክል በቤተክርስቲያናችን የብሉይ ኪዳን ታቦት ስለሌለን እና አገልግሎቱም አብቅቷል ብለን ስለምናምን ስለብሉይ ኪዳን ታቦት መከራከር እናቁም ይልቁንም የሐዲስ ኪዳን ታቦት ምን እንደኾነ እና ለምን እንዳስፈለገ እናስረዳ።

N.B. ርእሱ ትኩረት ለመሳብ ነው በተጨማሪም ታቦት ትሽሯል ስል የብሉይ ኪዳኑን ታቦት እያልኩ እንደኾነ ይታወቅልኝ በተጨማሪም ተሽሯል ስል አገልግልሎቱን ፈጽሞ አብቅቷል አሁን ላይ በሌላ ተተክቷል ለማለት ነው።
❤ 10 🥰 2
18 October 2023
ኪ
10:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
"እግዚአብሔር ነጸረ ኲሎ ዓለመ፡፡ ወኢረከበ ማርያም ዘከማኪ እመ፡፡ ኪያሁሰ ጽጌ ዘእምከርሥኪ ተቀስመ፡፡ ዳዊትኒ አመረኪ እንዘ ይብል ቅድመ፡፡ ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ዳግመ፡፡ እስመ ፈተወ ንጉሥ ሥነኪ አዳመ፡፡

እግዚአብሔር ኹሉንም ዓለም ተመለከተ ማርያም ሆይ! እንዳንቺ ያለች እናት ግን አላገኘም! ከማኅፀንሽ የተቀሰመ አበባ እርሱን ግን ንጉሥ ውብ ደም ግባትሽን ወዷልና! ልጄ ሆይ! ስሚ ዳግመኛም አድምጭ በማለት፤ አባትሽ ዳዊት አስቀድሞ በትንቢት አመለከተሽ፡፡" ማኅሌተ ጽጌ

እግዚአብሔር ቃሉን ዓለምን ያድን ዘንድ ወደ ሰዎች ላከው ፤ ቃልም ማደሪያውን በምድር ኹሉ ላይ ፈለገ እርሱ ዓለም የተፈጠረበት የእግዚአብሔር ቃል እና ንጉሥ ነውና ለንግሥናው የሚገባውን ንጹሕ ማደርያ ፈለገ ነገር ግን ለእርሱ የተገባ ማደርያ አስቀድሞ አባቷ ዳዊት "ንጉሥ ውበትሽን ወዷልና" ብሎ ከተናገረላት ከገሊላዊቷ ድንግል በስተቀር ሌላ አላገኘም እርሷ እራሷን ለአምላክ የተገባ ንጽሕት አድርጋ ጠብቃለችና ስለዚህም ሊቁ ኦሪገን እንዲህ ይላታል " Worthy of God Immaculate of Immaculate - ለአምላክ የተገባች ንጽሕት እምንጹሐን"።

እኛም ከአባቶቻችን ተቀብለን
Axia Axia Axia
Worthy worthy worthy
ይደልወኪ ይደልወኪ ይደልወኪ
ይገባሻል ይገባሻል ይገባሻል
እናላታለን በሚገባ የአምላክ እናት ተብላለችና!!
❤ 12 🥰 2
19 October 2023
ኪ
17:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሉሲፈራችን ክርስቶስ

ሉሲፈር (Lucifer) የሚለው ቃል የላቲን ቃል ሲኾን ትርጉሙም "Morning Star-ኮከበ ጽባሕ-የአጥቢያ ኮከብ" ማለት ነው። በዚህ ስምም ሳጥናኤል ተጠርቶበታል ከመውደቁ በፊት የሚጋርድ ኪሩብ የንጋት ኮከብ ነበርና።

"How art thou fallen from heaven, O #Lucifer, son of the morning! [how] art thou cut down to the ground, which didst weaken the nations!"
(Isaiah 14:12)

" አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!" (ትንቢተ ኢሳይያስ 14:12)

ነገር ግን ሳጥናኤል የሚጋርድ ኪሩብ ኾኖ ተፈጥሮ ሳለ ዙፋኑን ከልዑል ዙፋን በላይ ሰራለው በልዑልም እመሰላለው ባለ ጊዜ ወደቀ ወደ ጥልቁም ተጣለ አሁን ላይ ሳጥናኤል የአጥቢያ ኮከብ (Lucifer) ሳይኾን የጨለማው ንጉሥ ነው። Lucifer ሲባል በአእምሮ ላይ የሚመጣባችሁ ሳጥናኤል ከኾነ አሁንም በክብሩ የአጥቢያ ኮከብ ኾኖ አለ ብላችሁ እያሰባችሁ እንደኾነ እወቁ ለእኛ በሐዲስ ኪዳን ላለን ክርስቲያኖች ሉሲፈራችን ክርስቶስ ነው።

ሉሲፈራችን ክርስቶስ ነው ስል ከራሴ ተነስቼ ሳይኾን ከመጽሐፍ ማስረጃ ላቅርብ:

" እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።" (የዮሐንስ ራእይ 22:16)

" ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።"
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:19)

የንጋት ኮከብ የሚለውን የላቲኑ መጽሐፍ ቅዱስ Lucifer ይለዋል :

"et habemus firmiorem propheticum sermonem cui bene facitis adtendentes quasi lucernae lucenti in caliginoso loco donec dies inlucescat et #lucifer oriatur in cordibus vestris" (Epistula Petri II 1:19)

ስለዚህ የብሉይን ጨለማ ገፎ የሐዲስ ኪዳንን ብርሃን የገለጠልን ጨለማውን ያበራልን የነጋት ኮከባችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኾነ ለኔ ሉሲፈሬ ክርስቶስ ነው እላለው እናንተም ሉሲፈራችሁን ምረጡ።
❤ 10 👍 3 🥰 1 🤔 1
25 October 2023
ኪ
15:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኹል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ

አሁን ባለንበት ዘመን ከዓለማችን ላይ ደስታ ርቆ አብዛኛው ሰው በድብርት እና ሀዘን ውስጥ ይገኛል። ይሄም ለምን ኾነ ብለን ስንጠይቅ ከጌታ ስለራቅን ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ደስታን ከመንፈስ ፍሬዎች እንደ አንዱ ይጠቅሰዋል " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ #ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 5:22)

በእኛ ሰዎች ወስጥ ሦስት ነገሮች አሉ እነርሱም ሥጋ ነፍስ እና መንፈስ ናቸው። ሥጋችን ለጊዜው የሚበቃውን ምድራዊ ደስታ ብቻ ይመኛል በዚህም ለጊዜው ደስታ ይሰጠኛል ብሎ ያሰበው ነገሮች እነርሱም ምግብ ፣ መጠጥ ፣ ፍትወት እና በመሳሰሉት ነገሮች ላይ ብቻ ደስታን ይፈልጋል። እነዚህ ግን ሥጋችንን እስረኛ አድርገውት ያስቀሩታል እንጂ እውነተኛውን ደስታ አይሰጡንም ለዛም ነው ብዙ በምድር ሀብታም ኾነው ለሥጋቸው የሚያስፈልጋቸውን ኹሉ ማግኘት እየቻሉ ደስታ ግን የራቃቸው ሰዎች ያሉት። መንፈሳችን ደግሞ መንፈሳዊ ከኾነው አምላካችን ጋር ኹሌ መገናኘት ይመኛል የመንፈሳችን ደስታዋ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም መኾን ነውና። በእነዚህ ተቃራኒ በኾኑ የሥጋ እና የመንፈስ ፍላጎቶች መሃል ነፍሳችን ትጨነቃለች ኹለቱም ወደራሳቸው ይስቧታልና በዚህም ምክንያት የሥጋችንን ፍላጎቶች ኹሉ ብናሟላም እንኳን ደስታችንን ግን አናገኝም።

እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ሥጋችንን ለነፍሳችን ፣ ነፍሳችንን ለመንፈሳችን ፣ መንፈሳችንን ደግሞ ለእግዚአብሔር ተገዢ ስናደርግ ነው። ለዚህም ነው ሰው በመንፈሳዊ ሕይወቱ እየበረታ ሲመጣ ከሥጋ ፍጹምነት ተነስቶ የነፍስ ፍጹምነትን አልፎ የመንፈስ ፍጹምነት ጋር ሲደርስ የመንፈስ ፍሬዎችን እንዳለ የሚያፈራው ከነዚህም ፍሬዎች መካከል ዋነኛው #ደስታ ነው እውነተኛ ደስታ የመንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ነውና ዳዊት እንዳለው "ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለው" በማለት ብቻ ነው ደስታ ላይ ሚደረሰው።(መዝ 138/139:7) እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው ሥጋው ላይ የፈለገ ነገር ቢደርስበት እንኳን ደስታውን ሊያሳጣው አይችለም። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ እስር ቤት ውስጥ ኾኖ ሳለ " ኹልጊዜ በጌታ #ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ #ደስ ይበላችሁ።"ሲል የነበረው። (ፊል4:4) እንዲሁም ለዚህ ነው ሰማዕታት ሥጋቸው በእሳት እየተቃጠለ ፣ አንገታቸው በሰይፍ እየተሰየፈ ፣ ሰውነታቸው ለኹለት እየተሰነጠቀ እነርሱ ግን በደስታ ስለጌታቸው ሲመሰክሩ እና ሲዘምሩ የነበሩት።

ደስታን ሰጪው ክርስቶስ የመንፈሳችንን ደስታ ለኹላችን ያድለን እኛም ወደ እርሱ ቀርበን እውነተኛውን ደስታ ከጌታ ስር እናጣጥም። እኔም እላችኋለሁ ኹል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ አሁንም ደግሜ እላችኋለሁ ደስ ይበላችሁ ሦስተኛ ጊዜ እላችኋለሁ ደስ ይበላችሁ 😊
❤ 12 🥰 2
6 November 2023
ኪ
13:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
"የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።" (ኤፌ 1:3)

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዓለም አስቀድሞ ከአባቱ የተወለደ ፍጹም አምላክ ነው ፤ ከእወነተኛው አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ነው። ከአባቱ የተነገኘ ስለኾነ ልጅ ነው ልጅነቱም ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ ነው " ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት እኔ #ተወለድሁ፥ " (ምሳሌ 8:25) ጊዜ የጀመረው ከፍጥረት ጀምሮ ስለኾነ አብ ልጁን ሲወልደው በዘመን አይቀድመውም አብ መባሉ ልጅ ስላለው ነውና ያለ ልጁ የኖረበት ዘመን የለም አብ ኹሌ አባት ነው አባትም የኾነው ከጊዜ ውጪ በወለደው ልጁ ነው። ወልድን ሲወልደው ዘመን ስለማይቆጠርለት የወልድ ከአብ ልደት ኹሌ ዛሬ ነው " ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ #ዛሬ ወለድሁህ።" (መዝ2:7) በዚህ ዘላለማዊ ልደቱም ለአባቱ ብቸኛ ልጅ ነው። እንዲሁም ይህ ልጅ ዘላለማዊ ቃል ነው ፤ ቃል መባሉም ከአብ ምንጭነት መጥቶ ለራሱም ለአባቱም ቃል በመኾኑ ነው ፤ ቃል ከአባቱ ሲመነጭም የጊዜ ቅደም ተከተል የለበትም አብ ያለ ቃሉ የኖረበት ዘመን የለምና ለዚህም ዮሐንስ" በመጀመሪያው ቃል ነበረ" አለ (ዮሐ 1:1)  የእግዚአብሔር ቃል ከአባቱ የወጣ ቀዳማዊ ቃል ነውና።

ይህ የእግዚአብሔር ቃል እና ልጅ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ሞትን በሞት ይሽረው ዘንድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋና ደምን ተካፍሎ ፍጹም ሰው ኾነ። (ዕብ 2:14-15) በዚህ ልደቱም ፍጹም የሰውን ባሕርይ በመንሳቱ በኹሉ ነገር እኛን ወንድሞቹን መስሏል ከአንዲቷ ከኃጢአት በቀር " ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።" (ዕብ 4:15) በነገር ኹሉ እኛን ስለመሠለ በሥጋው ፍጡር ነውና አብ አምላኩ ተብሏል። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጌታ ፍጹም ሰው ፣ ፍጹም አምላክ መኾኑን ለማጠየቅ "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ" አለ  (ኤፌ 1:3) ፍጹም ሰው በመኾኑ አምላኩ ፤ ፍጹም አምላክ በመኾኑ ደሞ አባቱ ነውና።

ቅዱስ ጄሮም እንዲህ ይላል " ከመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው የእግዚአብሔር ቃል አባት እና ቃል ለተሐዋደው (ለነሳው) ሰው አምላክ የሚኾን አብ የተባረከ ይኹን። ይህም ማለት በቃል የተነሳው ሰው እና የነሳው የእግዚአብሔር ቃል የተለያዩ ናቸው ለማለት ሳይኾን ነገር ግን አንድ እና እራሱ የኾነ ቃል [ሰው በመኾኑ] ኹኔታው እንደ ሚፈቅደው በትሕትና በዝቅታ ስለሚነገርለት ነው"

"በኢየሱስ ክርሰቶስ በአምላክነቱ እምንመካበትን ያህል በሰውነቱም እንመካበታለን ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ የተደሰትነውን ያክል ለሳምራዊቷ ሴት ሄዶ ውሃ በመለመኑም እንመካበታለን ምክንያቱም ድህነቱ ድህነታችንን ሊያርቅልን የመጣበት ፍቅሩ ስለሆነ" 🥰
( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ  )

በእወነት ፍጹም አምላክ እና ሰው በመኾኑ መካከለኛችን የኾነ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ ይኹን!

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ እግዚአብሔር አብም የተባረከ ይኹን!

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስም የተባረከ ይኹን!
❤ 8 👍 3 🥰 1
7 November 2023
ኪ
08:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
" እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።"
(መዝሙረ ዳዊት 74:12)

"በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን።"
(የዮሐንስ ወንጌል 4:42)

"መድኃነኔ ዓለም ሆይ፤
አባት ሆይ፤ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ። በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህንም በጦር በውጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ
ትንፋሽ ላልትነፈሰ እሳት ንፋስህም ሰላም እላለሁ።" መልክአ መድኃኔዓለም

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ የዓለም ንጉሥ ኢየሱስ ሆይ መድኃኒትነትህን ለዓለም እመሠክራለሁ ታርደሃልና ስለኔ ሞተሃልና የፍቅርህን ውለታ ከፍዬ ባልጨርሰውም በኃጢአተኛው አንደበቴ ክበርልኝ እልሃለው የዓለም ንጉስ ሆይ በልቤ ላይ ንገሥ።
❤ 10 👍 2 🕊 2 🥰 1
10 November 2023
ኪ
22:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢስላም ስለ መጨረሻው ዘመን

አቡ ሁራይራ የነቢዩ ሞሃመድን ስለመጨረሻው ዘመን ንግግር እንዲህ ዘገበ፡

سُهَيْلٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُقَاتِلَ الْمُسْلِمُونَ الْيَهُودَ فَيَقْتُلُهُمُ الْمُسْلِمُونَ حَتَّى يَخْتَبِئَ الْيَهُودِيُّ مِنْ وَرَاءِ الْحَجَرِ وَالشَّجَرِ فَيَقُولُ الْحَجَرُ أَوِ الشَّجَرُ يَا مُسْلِمُ يَا عَبْدَ اللَّهِ هَذَا يَهُودِيٌّ خَلْفِي فَتَعَالَ فَاقْتُلْهُ ‏.‏ إِلاَّ الْغَرْقَدَ فَإِنَّهُ مِنْ شَجَرِ الْيَهُودِ ‏"‏ ‏.‏Sahih Muslim 2922 Book 54, Hadith 103

"ሙስሊሞች አይሁዶችን እስኪዋጉ ድረስ እና እስኪገሏቸው ድረስ የመጨረሻው ዘመን አይመጣም። ያኔ አይሁዶች በድንጋይ እና ዛፍ ጀርባ ይደበቃሉ ፣ ዛፉና ድንጋዩም ሙስሊም የአላህ ባሪያ ሆይ ከጀርባዬ አይሁድ አለ ና ግደለው ይላሉ ነገር ግን ጋርቃድ ዛፍ ይሄን አይልም ጋርቃድ የአይሁዶች ዛፍ ነውና።" ሳሂህ ሙስሊም 2922

ይህ ንግግር እንግዲህ ሙስሊሞች እንዳለ የነቢዩ ሞሃመድ እንደ ኾነ ይስማሙበታል ፣ እንዴት እይሁዶችን እንዳለ እስክትገሉ ድረስ የመጨረሻው ዘመን አይመጣም ብሎ ሞሃመድ ይናገራል ሲባሉ የሚሰጡት ማብራርያ አይሁዶች መሢሑ መምጣቱን አያምኑም አሁንም ሌላ መሢሕ ይጠብቃሉ በመጨረሻው ዘመንም ሃሰተኛው መሢሕ መሢሕ አል-ጀዳል ሚባለው ሲመጣ አይሁዶች እንዳለ ጀዳል እውነተኛ መሢሕ ይመስላቸውና ከእርሱ ጎን ይሰለፋሉ እውነተኛቹ ሙስሊሞች ግን ሃሰተኛ መሢሕ እንደኾነ ያውቃሉ ፤ ያኔ አል-መሢሕ ኢሳ ይመጣል (እንግዲህ ኢየሱስ መኾኑ ነው) ሙስሊሞችም ከኢሳ ጋር በመኾን አይሁዶችን ይዋጋሉ አብዛኞቹንም ይገላሉ አይሁዶቹ ከመሸነፋቸው የተነሳ እንዳይገሏቸው ከድንጋይ እና ዛፍ ጀርባ ይደበቃሉ ነገር ግን አላህ ድንጋዮችን እና ዛፎችን ከጀርባዬ አይሁድ አለ ና ግደለው እንዲሉ ያደርጋቸዋል ይሄንን የማይለው ግን የጋርቃድ ዛፍ ብቻ ነው እርሱ የአይሁዶች ዛፍ ነውና።

እንግዲህ አላህ እንደዚህ ሰዎችን በማስገደል የሚያምን አምላክ ነው ሊያውም መግደልን ከማበረታቱ የተነሳ ድንጋዮች እና ዛፎችን ሳይቀር ና ግደለው ብሎ እስኪያናግራቸው ድረስ ለሕይወታቸው ፈርተው የተደበቁትን ሳይቀር ያስገድላል። ደግሞ ለአይሁድ ትልቅ ጥላቻ አለበት ደጃልን እንኳን ፈልገው ቢከተሉ ፍርዳቸው በወዲያኛው ዓለም ይኾናል እንጂ እስኪያልቁ ድረስ በማስገደል ማመን ማለት እንኳን አምላክ ነው ከሚባል አካል እና ከሰው እንኳን አይጠበቅም እንግዲህ አላህ ወደ 6 ሚሊዮን የሚኾኑ አይሁድን ካስገደለው ሂትለር በምን ተለየ? ደሞ ከኹሉም በላይ የሚገርመው አላህ ኹሉንም ዛፎች እና ድንጋዮች ሲያዝ የጋርቃድ ዛፍን ማዘዝ አለመቻሉ ነው እርሱ የአይሁድ ዛፍ ነውና ይለናል አላህ ፈጣሪ አይደለም እንዴ? የጋርቃድን ዛፍስ የፈጠረው እርሱ አይደለም እንዴ? እንዴት የአይሁዶች ዛፍ ይኾናል እንግዲህ አላህ የገዛ ፍጥረቱን እንኳን ማዘዝ የማይችል አምላክ ነው።

እኛ ክርስቲያኖች ግን ሃሳዊው መሢሕ መጣ ጊዜ ለክርስቶስ ሰማዕት እንኾናለን ምክንያቱም እኛ ለእምነታችን እንሞታለን እንጂ አንገልምና! መግደልስ ከእኛ ይራቅ!
❤ 7 🥰 1
13 November 2023
ኪ
23:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዝዊንጊሊ የክርስቶስ ሥጋ ምሳሌ ብቻ እንደኾነ ሚያምን ሰው ነበር እርሱንም ለማስረዳት ይሄን የመሠለ ደካማ መከራከርያ አቅርቦ ነበር:

“ይህ ሥጋዬ ነው” “ይህ” የሚለው ቃል ኅብስቱን ማለት ሲሆን “ሥጋ” የሚለው ቃል ስለእኛ የተሞተው ሥጋ ማለት ነው። ስለዚህ "ነው" የሚለው ቃል በቀጥታ ሊወሰድ አይችልም ፣ ምክንያቱም ኅብስቱ ሥጋው አይደለምና ሊሆንም አይችልም. . . “ይህ ሥጋዬ ነው” ማለት “ኅብስቱ የሥጋዬ ምልክት ነው” ወይም “የሥጋዬ ምሳሌ ነው።'' ማለት ነው" (On the Lord’s Supper, 1526; in Bromiley, 225)
👍 4
23:48
ዝዊንግሊ በዚህ እምነቱ ግን ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጋር ተጧልቷል ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ሥጋና ደም ምልክት ብቻ ሳይኾን እውነተኛ እንደኾነ ታምን ነበርና ለምሳሌ ከ160-240 ዓ.እ የነበረው ተርቱሊያን እንዲህ ሲል ተናግሯል:

“ኢየሱስም ኅብስቱን አንሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጠ በኋላ፡-' ይህ ሥጋዬ ነው'፥ እርሱም የሥጋዬ ምልክት ነው በማለት ኅብስቱን የእርሱ ሥጋ አደረገው። ነገር ግን መጀመሪያ እውነተኛ አካል ከሌለ[ሥጋው ካልኾነ] በስተቀር ምልክት ሊኖር አይችልም። ባዶ ነገር ወይም ምትሃት ምልክት መኾን አይችልምና። በተመሳሳይም ስለ ጽዋው ሲያነሳ እና አዲስ ኪዳንን ‘በደሙ’ ሲያትም የሥጋውን እውነተኝነት ያረጋግጥልናል። አካሉ [እውነተኛ] ሥጋ ካልኾነ በስተቀር ደም ሊኖረው አይችልምና” (Against Marcion, 4.40)።

ዝዊንጊሊ በዚህ አስተምህሮው የተጣላው ከጥንታውያን አባቶችጋር ብቻ ሳይኾን አብሮት ከነበረ የተሐድሶ አቀንቃኝ ማርቲን ሉተር ጭምር ነበር። ሉተር ሥጋውን እና ደሙን ምልክት ብቻ ነው በሚሉት ተማሮ እንዲህ ብሎ ነበር:

"እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከወይኑም ጋር ይኹን የክርስቶስ ደም መኖሩ ለእኔ በቂ ነው ። ከአላጋጮች ጋር ተራ ወይን ከምጠጣ ከፖፑ ጋር ንጹሕ ደም ብጠጣ እመርጣለሁ"(Early 1520s; in Althaus, 376; LW, 37, 317)

እንግዲህ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምልክት ብቻ ነው የምትሉ ፕሮቴስታንቶች ሉተር ከእናንተ ይልቅ ትቶት የወጣውን የሮም ፖፕ ይመርጣል!

ለ memeኡ commentarry 😁
❤ 8 😁 2
23 November 2023
ኪ
10:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጾመ ነቢያት (Nativity Fast)

ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታ ልደት በፊት ያሉትን 40 ቀናት በጾም እንድናሳልፍ ታዘናለች ይሄም ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል በሲና ተራራ የጾመውን 40 ቀናት ይወክልልናል። ሙሴ አሠርቱ ቃላትን ለመቀበል 40 ቀናት እንደ ጾመ እኛም ደግሞ የአካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋዌ (Incarnation of the Logos) ለመቀበል እንዲሁ 40 ቀናትን እንጾማለን።

የአዳም መድኃኒት ፣ የነቢያት ትንቢታቸው "እጅህን ከአርያም ላክ ናና አድነን" እያሉ የለመኑት ፣ የ5500 ዓመት ተስፋቸው ፣ ለሙሴ የመጀመርያ ስሙን በየውጣ የነገረው (የውጣ ማለት Iota ከሚለው የግሪክ እና ኮፕቲች ፊደል የመጣ ነው በኮፕቲክ አሥር የሚለው ቃል በIota ፊደል ይጀምራል ፣ ኢየሱስ የሚለው ስምም በግሪክም በኮፕቲክ በIota ፊደል ይጀምራል ስለዚህ Iota , the name of salvation of our Lord የጌታ የማዳኑ ስም ተብሏል (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ) ሙሴ አሠርቱ ቃላትን እንደተቀበለ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ) ፣ የኢያሱ ስሙ ኃይል (ኢያሱ እና ኢየሱስ ማለት ትርጉሙ አንድ ሲኾን ያህዌ ያድን ማለት ነው ፣ መድኃኒት ተብሎም ይተረጎማል) ፣ የኤሊያስ መሶበ ወርቅ ውስጥ ያለ መና ፣ በዳዊት ዙፋን ለዘላለም የሚነግሥ የንግሥናው ፈጻሚ ፣ የሰሎሞን ጥበብ "ጥበብሰ መድኃኒነ ውእቱ-ጥበብስ መድኃኒታችን ነው"(ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ) የተባለለት ፣ የነቢያት ትንቢት ኹሉ ፈጻሚ ፣ አዳኙ ፣ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ሊወለድ ነውና የተስፋውን ቀን በመጠባበቅ እኛም ከነቢያት ጋር እንጾማለን።

"የበዓል ቀን ሊመጣ ነው እርሱም ከኹሉም በዓላት በላይ እጅግ የተቀደሰ እና ያማረ ነው ፣ የተቀደሱ ቀናት ኹሉ አለቃ እና እናት ብለን ብንጠራው ስህተት አይኾንም። ይሄም በዓል የክርስቶስ ልደት ቀን ነው" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ቅዳሜ ኅዳር 15 ይገባልና ለነቢያት ጾም እንኳን አደረሳችሁ ፣ የዛሬውን ቀን በብቀላ ሳይኾን በቅበላ እናሳልፍ። 😁
❤ 7 🥰 1
27 November 2023
ኪ
10:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወእምወልድ(Filioque)

✝️Filioque የሚለው የላቲን ቃል ሲኾን ትርጉሙም “ወእምወልድ-ከወልድም” ማለት ነው። ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለውም መንፈስ ቅዱስ የሰረጸው ከአብ ብቻ ሳይኾን ከወልድም ጭምር ነው በሚል አስተምህሮ ሲኾን ይሄን አስተምህሮ ለመጀመርያ ጊዜ ያስተማረው የሂፖው አውግስጢኖስ እንደኾነ ይነገራል። የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ይህን አስተምህሮ ተቀብላ አባቶች በ381 በተካሄደው በቁስጥንጥንያ ጉባኤ “ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሰረጸ እምአብ -በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱ ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሰረጸ” የሚለው ርቱዕ(Orthodox) አስተምህሮ ላይ “ዘሰረጸ እምአብ ወወልድ- ከአብ እና ከወልድ የሰረጸ” ብለው ጨምረበታል። ይህን ያደረጉበት ምክንያት በወቅቱ በስፔን አርዮሳውያን በዝተው ነበር እነርሱ ደግሞ ወልድን ዝቅ አድርገው ፍጡር ብለውት ስለነበር የስፔን ቤተክርስቲያን የወልድን ቦታ ከፍ ለማድረግ ከአብ ጋር በመኾን መንፈስ ቅዱስንም አስርጿል ብለው በጉባኤ አወጁ። ይሄን አስተምህሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በይፋ ተቀብላ አንቀጸ ሃይማኖት ላይ እስከ መጨመር ደርሳለች ይሄም ከግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር The great schism በሚባለው በ 1054 ዓ.እ ለመለያየት ዓቢይ ምክንያት ኾኗል። (እዚህ ጋር በ1054 የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተለያየችው ከ Eastern Orthodox ጋር እንጂ ከእኛ Oriental Orthodox ጋር አይደለም እኛ ቀድመን በ451 በጉባኤ ኬልቄዶን ተለይተናቸዋል )።
10:54
👉🏽ነገር ግን ይህ አስተምህሮ በምስጢረ ሥላሴ ላይ ትልቅ ተፋልሶ የሚያመጣ ነው። ይኸውም የመጀመርያው በሥላሴ ዘንድ አንድነትና ሦስትነት እንጂ ኹለትነት እና አንድነት የለም ፣ ይህም ማለት በሥላሴ ዘንድ ተለይቶ ለአንዱ የሚነገር ካለ ለኹሉም በነጠላ ነው የሚነገረው ለምሳሌ፡ አብ ልብ ነው ካልን በነጠላ ወልድ ቃል ፣ መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ እንላለን። ለኹለቱ አካላት በጋራ የሚነገር ነገር ካለ ደግሞ ለሦስቱም የጋራ ይሆናል። ለምሳሌ፡ አብና ወልድ አምላክ ናቸው ካልን ፣ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው እንላለን። ስለዚህ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻሉ ካልን፣ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻል ማለት አለብን ይሄም መንፈስ ቅዱስ እራሱን አሰረጸ ወደ ማለት ይሄድብናል በሥላሴ ዘንድ የኹለት ብቻ የኾነ የለምና ወይ ለአንዱ ብቻ ይነገራል ወይ ለሦስቱም የጋራ ይኾናል እንጂ።
ሌላ ይህ አስተምህሮ በሥላሴ አካላት ዘንድ መሽቀዳደምን ያመጣል ምክንያቱም አብ ወልድን ይወልዳል ፣ አብና ወልድ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻሉ ምንል ከኾነ መንፈስ ቅዱስ ለመስረጽ መጀመርያ ወልድ መወለድ አለበት ያስብላልና። ይህ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ያልነበረበት ጊዜ ነበር ወደ ማለት ያስኬደናል። በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ደግሞ አብ ወልድን ሲወልድ እና መንፈስ ቅዱስን ሲያሰርጽ የጊዜ መቀዳደም የለም።

✝️ሌላ ደግሞ የጌታን የራሱን አስተምህሮና የአባቶችን አስተምህሮ መካድ ነው። በዮሐ 15፡26 “ ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል” በማለት ጌታ መንፈስ ቅዱስን ከአብ የሚወጣ በማለት የሚሰርጸው ከአብ እንደኾነ መስክሯል። በተጨማሪም አባቶች በቁስጥንጥንያ የሃይማኖትን አንቀጽ ሲደነግጉ “በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱ ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሰረጸ” ነው ያሉት። ጌታም ያላስተማረውን አባቶችም ያላስተማሩትን መጨመር ደግሞ ትልቅ ቅጥፈት ነው “ ነገር ግን እኛ ብንኾን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።” እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ (ገላ 1፡8)።

👉🏽ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የአብ የኹሉ መገኛ መኾን(Monarchy of The Father) አስተምህሮ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም አብን አብ ያስባለው የኹሉ መገኛ መኾኑ ነው ወልድን ወልድ ያስባለው ደግሞ ከአብ የተገኘ በመኾኑ እንጂ ገና ለገና አርዮሳውያን ወልድን ዝቅ ስላደረጉት ተብሎ ወልድን የሌለውን ማንነት የመንፈስ ቅዱስ አስገኝነት አንሰጠውም። ጌታም አላስተማረም፣ ሐዋርያትም አላስተማሩም ፣ አባቶችም አላስተላለፉልንም።
❤ 9 🥰 1
30 November 2023
ኪ
11:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
አህያ ላይ የተቀመጠው በግ

ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ ሲነሣ እንደሚሰቃይ ፣ እንደሚሞት ያውቅ ነበር ነገር ግን ይህን እያወቀ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ተነሣ ፣ ጴጥሮስ "አይሁንብህ" እያለ ይከለክለው ጀመር ኢየሱስ ግን የመጣበትም ዓላማ በሞቱ ሊያድን ነውና "ከኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን" በማለት ገስጾ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞውን ጀመረ ወደ መታረጃው ቦታ፤ የመሥዋዕቱ በግ ወደ መሠዊያው ጉዞውን ጀመረ። ብዙ በጎች መታረጃችውን አያውቁም በሰላም እየኖሩ ካሉበት ድንገት አራጅ ይዞ ይወስዳቸዋል እንጂ ፤ ወደ አራጆቹ እራሱ ጉዞን የጀመረ በግ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን አለ?

ይህ በግም ወደ መታረጃው ሲሄድ የተጫነው በአህያ ላይ ነበር ፤ በጉ ሊታረድ በአህያ ላይ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ ፤ ንጉሡ በመስቀል ላይ ሊነግሥ በአህያ ላይ ወጣ ፤ አዳኙ ሊያድን በአህያ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ። የኢየሩሳሌም ሕዝብም "ሆሣዕና-አቤቱ አድን" ፣ "ሆሣዕና-አቤቱ አድን" እያሉ ተቀበሉት እነርሱ ባይጠይቁትም በጉ አህያ ላይ መጫኑ ሊያድን ነውና በዘምባባ ተከቦ ወደ መታረጅው ጉዞውን ቀጠለ።

አቤቱ የእግዚአብሔር በግ ሆይ እኛ ልጆችህ አሁንም ታመናልና በአህያ ላይ ተጭነህ ናልን ፣ ሆሣእና- አቤቱ አሁን አድነን።

N.B. አሁን የሆሣዕና ጊዜው ባይሆንም ስለሆሣዕና ሳስብ የገረመኝን ነገር ላጋራችሁ ብዬ ነው። ፎቶው በbing AI የተሠራ 😊
❤ 10 👍 2 🥰 2
1 December 2023
ኪ
03:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጽዮን የሐዲስ ኪዳኗ ታቦታችን

ዕግትዋ ለጽዮን፤ ጽዮንን ክበቡአት ፤ የሐዲስ ኪዳኗን ታቦት ክበቡአት ፤ በድንግልስ እንደ ብሉይ ኪዳኗ ታቦት የተሰባበረው ዳጎን ብቻ አይደለም የሞትን መውጊያ የሰባበረውን አስገኝታለችና ክበቡአት። እርሷንስ እኛ ባንከባት ራሱ "ማኅበረ ቅዱሳን የአውዱኪ-የቅዱሳን ማኅበር ይኩቡሻል" የተባለላት ናት።

ለእናታችን ለጽዮን ምስጋናን እናውጣ ፤ ለእግዚአብሔር ቃል ማደርያ ለታቦቷ እንዘምር እኛ ዝማሬ እንኳን ባይኖረን ከአባታችን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት የምስጋናን ቃል ተውሰን እንዲህ እንላታለን " በተመስጦ በዳዊት በገና ያስተማረንን ዜማ እንዘምራለን፥ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ እንበል። አንተና የመቅደስህ ታቦት። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በውስጥም በውጭም በወርቅ የተሠራች የመቅደሱን መዝገብ ኹሉ የተቀበለች ታቦት ናትና።"

አብርሂ አብርሂ  ጽዮን፤ ዕንቍ ዘጳዝዮን፤
ዘኃረየኪ ሰሎሞን፡፡

እንኳን አደረሳችሁ ❤️
❤ 6 🥰 2
3 December 2023
ኪ
10:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ ቅዳሴ ላይ የተነበበው ወንጌል


(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 8)
----------
23፤ ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት።

24፤ እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር።

25፤ ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ አስነሡት።

ብዙዎቻችን እንዲነገርልን የምንፈልገው ብርታታችን ብቻ ነው እንዴት ታላቅ እንደኾን እንጂ ድክመታችን እንዲነገርብን አንፈልግም ጌታ ግን ደክሞት አንቀላፋ ተባለለት መለኮት የሚደክም ኾኖ ሳይኾን ጌታ ፍጹም የእኛን ሥጋ ተዋሕዷልና የሥጋ ድክመት ኹሉ ለመለኮት ተነገረ ቅዱስ ቄርሎስ እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቱአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል እንዲል። ቃል የሥጋን ባሕርይ ገንዘቡ አደረገ ፣ ሥጋም የቃልን ባሕርይ ገንዘቡ አደረገ በዚህም ጌታ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ፣ ከኹለት አካል አንድ አካል (Miaphysis) በመኾኑ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው። በአምላክነቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እና ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ነው ፤ እንዲሁም በሰውነቱ ከእኛ ከሰዎች ጋር አንድ ነው። ስለዚህም ጌታ የሰውን ድክመት ኹሉ በአንጻረ ሥጋ ለመለኮት ተነገረለት።

በዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም የሰውን ባሕርይ በመያዙ ከአምላክነቴ ዝቅ እላለሁ ብሎ አላሰበም ኹሉንም ለድኅነታችን አደረገው እንጂ ይሄን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይገልጸዋል

(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ. 2)
----------
6፤ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥

7፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ።

ሐዋርያትም የመርከቢቷን መናወጥ አይተው ጌታን ቀሰቀሱት ማዕቀሉን ጸጥ ያረግላቸው ዘንድ ይህ የሚገባ ነውና ፤ እኛም አሁን በአንድ መርከብ ውስጥ ነው ያለነው ፤ መርከባችን በማዕበል እየተናወጠች ነውና ጌታ ጸጥ ያረግልን ዘንድ እንቀስቅሰው በጸሎታችን እንቀስቅሰው ፤ በምሕላችን እንቀስቅሰው ፤ በጾማችን እንቀስቅሰው ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም-አቤቱ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ እንበለው(መዝ 44:23) እርሱ በተነሣ ጊዜ ማዕበሉ ጸጥ ይላልና።

በጹዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሊቀ ጳጳስ በዛሬዋ ዕለት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በቅዳሴው ተገኝተው እንዳስተማሩት።

መልካም ዕለተ ሰንበት የጌታ ቀን ይኹንላችሁ ይህቺ ቀን ከዕለታት ኹሉ የከበረች ስለኾነች ከፍ ከፍ እናድርጋት።
❤ 4 🥰 1
6 December 2023
ኪ
11:44
ኪዳን ዘኢየሱስ
The real Santa Claus

ምእራባውያን ገናን በጣም ከSanta Claus ጋር አያይዘው ያከብሩታል ፣ Santa Claus የገና ዋዜማ በሌሊት እየተደበቀ ስጦታን ይሰጣቸዋል በማለት ለልጆች ሚነገር Legend አለ ከዚህም የተነሣ በምእራባውያን ዘንድ Santa Claus የገና ምልክት ኾኗል ፣ ሀገራችንም በምእራባውያን በሃል influenced እየኾነች ስለኾነ ይህ ነገር ወደ እኛም እየመጣ ይመስላል። ይሄንን የሚቃወሙ አንዳንድ የሀገራችን ሰዎች ደሞ ነገሩን ካለማወቅ የተነሣ Santa Claus ከባእድ አምልኮ የመጣ ነው ፣ የስካንዲቬኒያን ሰዎች የአማልክት አምልኮ ነው ፣ ገሚሶቹም ደሞ በኮካ ኮላ ማስታወቂያ ምክንያት የመጣ ነው ሲሉ ይደመጣል ነገር ግን እነዚህ ኹሉ ምንጭ የሌላቸው ወሬዎች ናቸው። ይልቅስ Santa Claus በቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ብለን ከምናከብረው አባት የተወሰደ ገጸ ባሕርይ መኾኑን ያውቃሉ?

ቅዱስ ኒቆላዎስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሀገረ ሜራ (Saint Nicholas Bishop of Myra) በ270 ዓ.እ ፤ ሜራ በምትባል ሀገር (አሁን ላይ ቱርክ ውስጥ ያለች ከተማ ስትሆን፣ Demre ትባላለች) ከሃብታም ቤተሰቦች የተወለደ ሲኾን በኋላ በዚችው ከተማ ላይ ጳጳስ እስከ መኾን ደርሷል። ቤተሰቦቹም ሃብታቸውን እንዳለ አውርሰውት ነበር ያለፉት እርሱ ግን ሕይወቱን እንዳለ ለክርስቶስ አሳልፎ የሰጠ በመኾኑ በወረሰው ሃብት ሰዎችን እንዳለ ይረዳ ነበር ነገር ግን ከንቱ ውዳሴ ስላልፈለገ እንዳይታወቅበት በሌሊት እየደበቀ የተቸገሩ ሰዎች ቤት ውስጥ ገንዘብ እየጣለላቸው ይሄድ ነበር። ሥንክሳራችን ላይ ከተመዘገበው አንድ ታሪክ ምሳሌ ይኾነናል ይሄውም አንድ ሃብታም የነበረ ሰው በጣም ከመደኽየቱ የተነሳ 4 ሴት ልጆቹን ሚያጋባበት ብር አጣና ሴተኛ አዳሪ ሊያደርጋቸው አሰበ ቅዱስ ኒቆላዎስም ይሄን አውቆ በሌሊት እየመጣ 100 ዲናር ወርቅ ቤታቸው ውስጥ ጥሎላቸው ይሄዳል፣ ለ3ቱ ልጆች እንዲህ ካደረገ በኋላ አባትዬው ይሄ ገንዘብ እየጣለልኝ የሚሄደው ሰው ማነው ብሎ በ4ተኛው ሌሊት ተደብቆ ማየት ጀመረ በዚህም ያ ሰው ቅዱስ ኒቆላዎስ መኾኑን አወቀ (ሥንስክሳር ዘታኅሣሥ 10)።

እንግዲህ ቅዱስ ኒቆላዎስ በዚህ ስጦታ በመስጠት የሚወደድ ቅዱስ አባት ነበር ፣ እንዲሁም በ325 ዓ.እ በኒቅያ ጉባኤ ከተሳተፉ 318ቱ ሊቃውንት አንዱ ነበር እንዳውም አርዮስ ምንፍቅናውን ሲናገር መስማት ተስኖት በጥፊ መቶት ነበር በዚህም እስር ቤት ገብቷል(Imagine Santa Claus slapping Arius 😁)።

ታድያ እንዲህ በቤተክርስቲያን የሚወደድ አባት እንዴት Santa Claus ወደ ሚባል legend ተቀየረ? ሜራ ምትባለዋ ከተማ የወደብ ከተማ ናት ስለዚህ ብዙ መርከቦች ይመላለሱ ነበር ፣ ለእነዚህ መርከቦች ጉዞዋቸው እንዲቃናላቸው ቅዱስ ኒቆላዎስ ይጸልይላቸው ነበር እንዳውም አንድ ጊዜ በማእበል የተመታች መርከብን መርከበኞቹ መቆጣጠር አቅቷቸው ተስፋ ሲያጡ ቅዱስ ኒቆላዎስ ተገልጦ መርከቧን እየመራ በሰላም ወደ ወደቧ አድርሷታል ፤ ከዚህ የተነሣ ቅዱስ ኒቆላዎስ በመርከበኞች ዘንድ በጣም የሚወደድ ቅዱስ አባት ነው። በ17ተኛው ክፍለ ዘመን በኔዘርላድ(Dutch) ፕሮቴታንቲዝም አይሎ ቅዱሳንን ማክበር ቢያቆሙም ቅዱስ ኒቆላዎስን እንደ ባሕል ያስቡት ነበር በተለይ መርከበኞቹ ፤ እነዚህ መርከበኞችም የቅዱስ ኒቆላዎስን (በDutch Sinterklaas ይባላል) ባሕል ወደ አሜሪካ ይዘውት ሄዱ በአሜሪካ ዘንድም ይህ legend popular እየኾነ ሄዶ Sinterklaas የሚለው በEnglish adaptation Santa Claus ኾነ።

Santa Clausን ከገና ጋር ያገናኘው ነገር ቅዱስ ኒቆላዎስ የሚከበረ በገና ወቅት አጋማሽ ላይ በእኛ ታኅሣሥ 10 ፣ በግሪጎርያን ለሚያከብሩም December 6 ነው ፣ ዳግመኛም ገና የስጦታ ወቅት ነው እና ታድያ ስጦታ በመስጠት እንደ ቅዱስ ኒቆላዎስ የሚታወቅ አባት ማን አለ?

ከዚህ የተነሣ እውነተኛው Santa Claus ቅዱስ ኒቆላዎስ ነው እንጂ ከpagan ባሕል የመጣ አይደለም!!
❤ 8 🥰 2 👍 1
8 December 2023
ኪ
09:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
Jw.org ማለት የይሖዋ ምስክሮች website ነው። ይሖዋ ምስክሮች ማለት የእኛ ዘመን አርዮሳውያን ናቸው እነርሱም እንደ አርዮስ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ ይላሉና።

ቅዱስ ኒቆላዎስ ቢያገኛቸው 😁
🤣 14 😁 1
12 December 2023
ኪ
15:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኹለቱ መቅደሶች

አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ (ለሙሴ የድንኳንን አሰራር አሳየው)
እግዚአብሔር ለታቦት ማደርያ ይኾን ዘንድ የደብተራን (የድንኳን) አሰራር በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ አሳየው። ሙሴም ድንኳኗን እግዚአብሔር ባሳየው አምሳል ሰራ ፣ እርሷም ሶስት ክፍሎች ነበሯት ፣ የውስጠኛዋ ክፍልም ቅድስተ ቅዱሳን ስትባል ታቦት የሚያድርባት ክፍል ነበረች።

ብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ጥላ እንደመኾኑ ይህ ኹሉ በሐዲስ ኪዳን ለምትነሳዋ ኹለተኛዋ መቅደስ ምሳሌ ነው ይህቺም እመቤታችን ናት ጌታ ታቦት ቢባል እርሷ ማደርያው ናትና ስለዚህም ማኅደረ መለኮት እንላታለን። አማናዊት መቅደስ (ደብተራ) እመቤታችን መኾኗን ሲመሰክር ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያሙ አንቲ ውእቱ ደብተራ እንተ ተሰመይኪ ቅድስተ ቅዱሳን ወውስቴታ ጽላተ ኪዳን (ቅድስተ ቅዱሳን የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ።) ይላታል። የብሉይ ኪዳኗ መቅደስ ለታቦት ነው መደርያ የኾነችው ፤ የሐዲስ ኪዳኗ መቅደስ እመቤታችን ግን የታቦቱ ባለቤት ጌታ አድሮባታልና ኹለተኛዋ መቅደስ ከመጀመሪያዋ በክብር ትበልጣለች።

በታኅሣሥ 3 ቀን ግን አስደናቂ ክስተት ተፈጠረ ኹለቱ መቅደሶች ተገናኙ ማኅደረ መለኮት እመቤታችን ማደርያ ፈልጋ ወደ ፊተኛዋ መቅደስ መጣች ፤ በመቅደሱ ውስጥ መቅደሷ አደረች (በዓት መቅደስ ውስተ መቅደስ)። መልአኩ ፋኑኤልም መቅደስ እመቤቱን በሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ተቀበላት።

የሐዲስ ኪዳን አማናዊቷ መቅደስ እመቤታችን ሆይ እኛም የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ መቅደሶች ነንና ለአምላክ የተገባን ኾነን እንገኝ ዘንድ ወደ ልጅሽ ለምኚልን ልጀሽ ኹሉ ይቻለዋልና።

በዓታ ለማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ ፣ እንኳን አደረሳችሁ። ❤️
❤ 8 🥰 2 👍 1
17 December 2023
ኪ
16:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
መድኃኒት የኾነ ልጁን እንሰብካለን

"ወልዶ መድኅነ ንሰብክ ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ፣ ተሰብከ በኦሪት አክሊለ ሰማዕት ሠያሜሆሙ ለካህናት ወተስፋ መነኮሳት ወልዶ መድኅነ ንሰብክ ወልዶ መድኅነ ንሰብክ

መድኃኒት የኾነ ልጁን እንሰብካለን፤ ከዓለም በፊት ያለ በኦሪት የተሰበከ የሰማዕታት አክሊል የካህናት ሿሚያቸው የመነኮሳት ተስፋቸው የኾነ መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን ፣ መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን" መዝሙር ዘስብከት

" እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:23)

መልካም ዘመነ ስብከት መድኃኒት ክርስቶስን በቃል ብቻ ሳይኾን በሕይወታችን እንስበከው ልጁ ያለው ሕይወት አለውና ❤
❤ 7 🥰 2
20 December 2023
ኪ
22:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
እያምመው አባቱን እየጠራ
አይቻለው ለሚገድሉት ሲራራ ❤️

በሕማሙ የታረቀን ጌታ ይክበር ይመስገን

ዘማሪ ዕዝራን እንኳን ወደ ቤትህ ወደ ኢየሱስ ፍቅር ተመለስክ እንበለው።

ቪዲዮው ከአኬ ገጽ የተወሰደ።
❤ 3 🥰 2
24 December 2023
ኪ
09:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ ዓለም የመጣ ብርሃን

"አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት ዘይዜንዋ ለጽዮን ቃለ ትፍሥሕት ወካዕበ ይቤ በአፈ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርዓዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳእ ዘተኀጒለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ።

ለጽዮን የደስታ ቃልን የሚያበሥራት ወልድ በምስጋና እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ተነገረ ዳግመኛ በዳዊት አንደበት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው አለ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን ለጻድቃን የሚያበራ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ነው የጠፋውን ይፈልግ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደእኛ መጣ።" መዝሙር ዘብርሃን

የተፈጠረ ሳይኾን ያልተፈጠረው ብርሃን ፣ ከብርሃን የተገኘው ብርሃን ቀዳማዊው ቃል ለዓለም ያበራ ዘንድ የመጣው የዓለም ብርሃን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1)
----------
3፤ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።

4፤ በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።

5፤ ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።

የዛሬዋ ሰንበት በቤተክርስቲያናችን ብርሃን ትባላለች እንኳን ለዕለተ ብርሃን ለጌታ ቀን አደረሳችሁ የዓለም ብርሃን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችሁ ይብራ።

" ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 13:12)
🥰 1
27 December 2023
ኪ
12:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
በእንተ ዕፀ ጌና (ስለ ገና ዛፍ)

ብዙ ጊዜ በሃገራችን ያሉ ሰዎች የገና ዛፍ ጣኦት ነው ፣ የፓጋን አስተምህሮ ነው ፣ ግኖስቲኮች ክፉው አምላክ ደጉ አምላክ ላይ በተነሳበት ጊዜ ደጉ አምላክ በጥድ ዛፍ ስር ተደበቀ ብለው ያስተምራሉ ስለዚህ የገና ዛፍ pagan ነው መጠቀም አይገባንም ሲሉ ይደመጣሉ እውነት ግን የገና ዛፍ የክርስትና መሠረት አለው?

በEastern Orthodox እንደ ቅዱስ አባት የሚታየው ኢንጊሊዛዊው ቅዱስ ቦኒፌስ (ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ የተነሣ ስለኾነ ግን በእኛ Oriental Orthodox ዘንድ ቅዱስ አይደለም) ወደ ጀርመን ሕዝቦች ለወንጌል አገልግሎት በሄደ ጊዜ ለአረማዊው ጣኦት ቶር (Thor) የተቀደሱ ተብለው የተለዩ የጥድ ዛፎችን ያገኛል እርሱ ግን እነዚህን የጥድ ዛፎች በቆረጠ ጊዜ ከሥሩ የኢየሱስን ዘላለማዊ ተፈጥሮ የሚያመለክት የማይረግፍ የጥድ ዛፍ በእርሱ ቦታ በቀለ። ከእዚህ ታሪክ ጋር አያይዘውም Eastern Orthodox እና Catholics የገናን በዓል የጥድ ዛፍ በመቁረጥ ያከብሩታል የጠፋነው ዛፍን በመብላት ነው ክርስቶስም ዛፍን በመብላት የጠፋነውን ሊያድነን ሲወለድ የዛፍ ግንድ ተብሎ ተጠርቷል "ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።" (ኢሳ 11፡1) ስለዚህ ከእሴይ የወጣው ግንድ ተወልዷልና ዕፀ ሕይወት (የሕይወት ዛፍ) የኾነ ኢየሱስን ለማክበር የጥድ ዛፍን ያስውባሉ።

በእኛ ቤተክርስቲያን በኩል ያለውን ስናይ ግን እኛ የገና ዛፍ ትውፊት የለንም የራሳችን የገና ትውፊት አለን ለምሳሌ የገና ጨዋታ ስለዚህ የእኛ ትውፊት ባልኾነ አከባበር ማክበር የለብንም ይሄ ማለት ግን የእኛ ባሕል ስላልኾነ ብቻ የሌላውን ማነወር ,ጣኦት ነው ማለት የለብንም የገና ዛፍም ቢኾን የክርስትና ትርጉም አለውና ክርስትና ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ አይደለም ዓለም አቀፋዊ እንጂ።
❤ 6 🥰 2 👍 1
31 December 2023
ኪ
09:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ ዓለም የመጠ እረኛ

"ኖላዊ ዘመጽአ ውስተ ዓለም ወልዱ ወቃሉ ለእግዚአብሔር ዘወረደ እምላዕሉ በአቅሙ ክርስቶስ እስመ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ይቤሎ አብ ለወልዱ ወልድየ ንበር በየማንየ

ወደ ዓለም የመጣው እረኛ የእግዚአብሔር ቃሉና ልጁ ነው ከላይ የወረደውም ክርስቶስ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው የሰንበት ጌታ እርሱ ነውና አብ ልጁን ልጄ በቀኜ ተቀመጥ አለው" መዝሙር ዘኖላዊ

ኖላዊነ ሔር (መልካሙ) እራኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በአባቱ ክብር በቀኙ ከእርሱ ጋር ተካክሎ ሳለ የጠፋውን በግ አዳምን ሊፈልግ የመጣ ፣ 99ኙን በሰማያት ትቶ ሲቅበዘበዝ የጠፋውን አንዱን አዳምን ሊፈልግ የመጠ እረኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ምድራዊ እረኛ በጎቹን ቢጠብቅ ወይ አርዶ ሊበላቸው ወይ ሊሸጣቸው ነው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ለበጎቹ እንደ በግ የታረደላቸው መልካም እረኛ ነው ፣ በአንድ ጊዜ አምላክም ሰውም በመኾኑ እረኛችንም በጋችንም ለኾነ ለመካከለኛችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው።

"መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ። ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ" ዮሐ 10 ፡ 15-16

የዛሬዋ ሰንበት በቤተክርስቲያናችን ኖላዊ (እረኛ) ስትባል ከጌታችን ንዑሳን በዓላት መካከል አንዷ ናት። መልካም የጌታ ቀን ዕለተ እሑድ ይኹንላችሁ።
❤ 2 🥰 1
1 January 2024
ኪ
09:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዓለ ብሥራት

በዓለ ብሥራት የጌታችን የጽንሰት በዓል በመኾኑ ከ9ኙ የጌታችን ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው። በዓለ ብሥራት መጋቢት 29 ቢኾንም ኹሌ የዓብይ ጾም ውስጥ ስለሚውል በድምቀት ለማክበር የእመቤታችንን ተአምር የጻፈው ቅዱስ ደቅስዮስ በዛሬዋ ዕለት ታኅሣሥ 22 እንዲከበር አድርጓል።

በዓለ ብሥራት በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ይሰጠዋል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳኑን ሥራ የጀመረው ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ፣ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ፍጹም ሰው ኾኖ በዓለማት የማይወሰነው አምላክ በማኅጽን ውስጥ በመወሰን ነውና።

እንዲሁም በዓለ ልደት ታኅሣሥ 29 እንደኾነ ያወቅነው በበዓለ ብሥራት ነው ያመጣነውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይኸውም እንዲህ ነው፡
መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካህኑ ዘካርያስን ስላበሠረበት ቀን ፍንጭ ይሰጠናል። ዘካርያስ የአብያ ክፍል ካህን ነበር (ሉቃ. 1፡5) የአብያ ክፍል ካህናት ከ24 የክህነት ክፍል ስምንተኛው ነው (ነህ 12፡17)። እያንዳንዱ ክፍል በዓመት ሁለት ጊዜ በቤተመቅደስ ውስጥ አንድ ሳምንት ያገለግላል።

የአብያ ካህናት ክፍል በሁለተኛው ሳምንት ቲሽሪ በተባለው የአይሁድ ወር በኹለተኛው ሳምንት ማለትም በስርየት ቀን ሳምንት ነው የሚያገለግሉት። ይሄም በእኛ የቀን አቆጣጠር መስከረም 29 (በግሪጎሪያን September 25 )ይኾናል በዚህ አገልግሎት እያለ ነበር መልአኩ ገብርኤል ያበሰረ (ሉቃስ 1፡5-24)። ይሄም የዮሐንስ መጥምቅን ጽንሰት መስከረም 29 ያደርገዋል።

መልአኩ ገብርኤልም ዘካርያስን ባበሠረ በ 6ኛው ወር ድንግል ማርያምን አበሰረ ኢየሱስም ተጸነሰ ይሄም መጋቢት 29 (በግሪጎሪያን March 25) ይኾናል (ሉቃ 1፡36)።

እንግዲህ ማርያምም ጌታን በጸነሰች በ9 ወር ከ5 ቀን ከወለደችው (የወንድ ልጅ Normal Gestational period)(ከመጋቢት 29-ታኅሣሥ 29) ፣ የጌታ ልደት ቀን ታኅሣሥ 29 (በግሪጎሪያን December 25) ይኾናል።

እንኳን ለበዓለ ብሥራት ለበዓለ ጽንሰቱ አደረሳችሁ ፣ ዓለማት የማይወስኑት እርሱ ግን ዓለማትን የሚወስን ጌታ በጠባብ ማኅጸን የተወሰነው ለእኛ ሲል ነው ፣ ጌታ ሆይ ትሕትናህ ድንቅ ነው!
👍 1 🥰 1
4 January 2024
ኪ
12:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኦርቶዶክሳውያን እና ካቶሊካውያን ለምን ገናን በኹለት ቀን ያከብራሉ? ጌታ የተወለደው ኹለት ቀን ነውን?

ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ በተለያየ ቀን አናከብርም የጌታ ልደት ለኹለታችንም መነሻው ቀን አንድ ነው እርሱም በጁሊያን ካላንደር December 25 ሲኾን ፣ የጁሊያን ካላንደር December 25 በእኛ ካላንደር ታኅሣሥ 29 ይኾናል። ይሄንንም በማስመልከት ነው ሐዋርያት በመጽሐፈ ዲድስቅልያ አንቀጽ 29 እንዲህ ያሉት "ወግበሩ በዓለ ልደት አመ እሥራ ወሐሙሱ ለታኅሣሥ ወርኅ ዘዕብራውያን ዘውእቱ አመ እሥራ ወተስኡ ለራብዕ ወርኅ ዘግብፃውያን (የልደትን በዓል በእብራውያን አቆጠጣር ታኅሣሥ 25 አድርጉ ይሄውም በግብጻውያን አራተኛው ወር በ 29 ቀን ይኾናል።)

ከዚህ የተነሣ ኹሉም ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የጌታ ልደት December 25 /ታኅሣሥ 29 መኹኑን ይስማማሉ። Even በእኛ እና በግብጽ ቤተክርስቲያን በ4 ዓመት አንዴ(በዘመነ ዮሐንስ) ልደት ወደ ታኅሣሥ 28 ሚመጣው የጁሊያን ካላንደርን December 25 እንዳይለቅ ነው።

ታድያ በእኛ ዘመን ከካቶሊካውያን ጋር የ13 ቀን ልዩነት እንዴት መጣ ብለን ስንጠይቅ ፣ ካቶሊካውያን በ16ኛው ክፍለ ዘመን በፖፕ ግሪጎሪ አነሣሽነት የጁሊያን ካላንደርን አሻሻሉት ፣ የተሻሻለውም ካላንደር ግሪጎሪያን ካላንደር ተብሎ ተጠራ። ምን አሻሻሉ ስንል ጁሊያን ካላንደር በአንድ ዓመት ውስጥ 365.25 ቀን አለ ሲል ፣ ግሪጎሪያን ግን በደምብ አጥንቻለው በማለት አንድ ዓመት 365.2425 ቀን ነው አለ ፣ ይሄ የ 0.0075 ልዩነት ያመጣል። ይሄ ልዩነት በአንድ ዓመት ውስጥ በጣም ትንሽ ከመኾኑ የተነሣ unnoticable ቢኾንም ፣ በ 2000 ዓመታት ሲጠራቀም ግን የ13 ቀናት ልዩነት አመጣ። ስለዚህ አሁን ላይ የጁሊያን ካላንደር December 25 የግሪጎሪያን January 7 ላይ ያርፋል።

የእኛ ካላንደርም ከጁሊያን ጋር በተመሳሳይ አንድ ዓመት 365.25 ቀን ነው ስለሚል ገናን በጁሊያን ካላንደር ከሚያከብሩ ኦርቶዶክስ ሃገራት ጋር በአንድ ቀን ነው የምናከብረው (ለምሳሌ የግብጽ ፣ የራሺያ፣ የዩክሬን ፣ የሰርቢያ ኦርቶዶክሳውያን) ፣ ነገር ግን የግሪጎሪያን ካላንደርን adopt ያደረጉት ኦርቶዶክሳውያን ከካቶሊክ ጋር ተመሳሳይ ቀን ያከብራሉ (ለምሳሌ የህንድ ፣ የግሪክ ፣ የቁስጥንጥንያ ፣ የአንጾኪያ)።

ስለዚህ ጥያቄውን ስናጠናቅቀው ክርስቲያኖች ገናን ኹለት ቀን አይደለም የምናከብረው ጉዳዩ አንድ ዓመት ስንት ቀን አለው የሚለው አቆጣጠር እንጂ የጌታን ልደት ከአንድ ቀን ተነሥተን ነው ምንቆጥረው እርሱም December 25/ ታኅሣሥ 29 ነው።
👍 5 ❤ 3 🙏 2 🥰 1
6 January 2024
ኪ
15:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
“ ምን ልበል! እና ይህን ልደት እንዴት ልገልጽልላችሁ? ይህ ድንቅ ነገር በግርምት ይሞላልኛልና። በዘመናት የሸመገለው ሕፃን ኾነ። በላይ በሰማያዊ ዙፋን የተቀመጠው አሁን በግርግም ተኝቷል። ማንም ሊቀርበውና ሊነካው የማይችለው፣ ረቂቅ አካል ያለው፣ አሁን በሰው እጅ ተይዟል። የኃጢአተኞችን እስራት የሰበረ አሁን በሕፃንነት እስራት ታስሯል። ነገር ግን ውርደት ክብር እንዲኾነው፣ በስም መጥፋት ክብርን እንዲለብስ፣ የቸርነቱ መጠን ደግሞ ፍጹም ውርደት እንዲኾን ወስኗል።” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ዛሬ በዳዊት ከተማ አወጣጡ ከጥንትም ድንቅ የኾነ ሕፃን ተወለደ አወጣጡ ብቻ አይደለም ስሙም ድንቅ ነው! እንኳን አደረሳችሁ ❤️
❤ 8 🥰 2
13 January 2024
ኪ
00:18
ኪዳን ዘኢየሱስ
የቃልን ቀዳማዊ አኗኗር በንሥር አይኑ አይቶ "በመጀመርያ ቃል ነበረ" በሚል ድንቅ ስብከት የጀመረልን ፣ የቃልንም አምላክነት "ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" ሲል መስክሮ ለኹላችን ድኅነት ሲል መውረዱን ሲገልጽልን "ቃልም ሥጋ ኾነ" ያለን የነጓድጓድ ልጅ ዮሐንስ ፣ ወደ ጌታ ደረት ተጠግቶ "ጌታ የሚወደው ደቀመዝሙር" የተባለው ተወዳጁ ዮሐንስ ፣ "ማራናት ጌታ ክርስቶስ ሆይ ቶሎ ና" ሲል ጌታውን የጠራው ዮሐንስ በክርስቶስ ተቀደምና ወደ እርሱ ተጠራ። ዮሐንስ ተጠራ ጌታ "ወደ እኔ ና" አለው ፣ ራእዩን ካየበት ከፍጥሞ ደሴት ተነጠቀ ፣ ንሥሩ ዮሐንስ ክንፉን እያማታ ከደመናት በላይ ወደ ጌታው ደስታ በረረ!!

ሰላም ለከ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
ሰላም ለከ ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ታዖሎጎስ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ድንግል
ሰላም ለከ ዮሐንስ ወንጌላዊ
ሰላም ለከ ዮሐንስ ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ!!

የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በረከት አማላጅነት ይደርብን ፣ እንኳን ወደ ክርስቶስ ለተነጠቀበት ቀን አደረሳችሁ ❤️
👍 6 ❤ 3 🥰 2
15 January 2024
ኪ
09:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሚጣፍጥ ስም ኢየሱስ

"ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።"(ሉቃ 2፡21)

ኢየሱስ በተወለደ በስምንተኛው ቀን በአይሁድ ሕግ መሠረት ተገረዘና ኢየሱስ የሚለው ስም ለዓለም ኹሉ ታወቀ። እንዴት ይጣፍጣል ኢየሱስ የሚለው ስም ፣ ስሙ ድንቅ ነው መድኃኒት ነው ፣ እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ከዚ ስም ውጪ ሌላ የለም ፣ ለዚህ ስም ፍጥረታ ኹሉ ይንበረከካሉ ፣ ዳዊት ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል፥ ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል አለለት ፣ ነቢያት ስለዚህ ስም ተነበዩ ፣ ሐዋርያትም በዓለም ዳርቻ አስተማሩለት ፣ አባቶችም በቤተክርስቲያን "ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ -የክብር ስሙ ይመስገን" ሲሉ ቀደሱለት።

ኢየሱስ ሆይ ስምህ ለአንደበታችን ጣፋጭ ነው ቀኑን ሙሉ ኢየሱስ ፣ ኢየሱስ ፣ ኢየኡስ ብንል አንጠግብም መድኃኒታችን ነህና ፣
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ ጣፋጭ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚበላው የሕይወት እንጀራ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠጣው የመድኃኒት ጽዋ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚሠዋው የድኅነት በግ ነው።

እንኳን አደረሳችሁ ኢየሱስ ጥዑመ ስም ❤️
❤ 12
23 January 2024
ኪ
22:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
ታቦት ጣውላ ነው

በበዓለ ጥምቀቱ በተቃዋሚዎቻችን ዘንድ በተደጋጋሚ ሲሰማ የነበረው መፈክር ታቦት ጣውላ ነው የሚል ነበር። ይሄም የታቦቱን ክብር ዝቅ ለማድረግ የስድብ ቃል መኾኑ ነው። እኛም ምንመልሰው መልስ አዎ ታቦት ጣውላ ነው ፣ መጽሐፍ ቅዱስም ወረቀት ነው ዋናው ነገር ከምን እቃ ተሠራ ሳይኾን አገልግሎቱ ምንድነው የሚለው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በmaterial ደረጃ ከተራ ወረቀት ምንም አይለይም ቅዱስ ያስባለው ግን የእግዚአብሔር ቃል ስለተጻፈበት ነው ፣ ታቦትም በmaterial ደረጃ ከተራ ጣውላ የሚለይ ምንም ነገር የለውም ቅዱስ ያስባለው ግን አልፋ እና ኦሜጋ የሚለው የክርስቶስ ስም ስለተጻፈበት እና ክቡር የኾነ የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ስለሚቀርብበት ነው።

ባያውቁ እንጂ ታቦቱን ከምንጠራበት ስሞች መካከል ቅድስት ጠረጴዛ (Holy Table) ፣ የጌታ ጠረጴዛ (The Lord's Table) ይገኙበታል። እነዚህ ስሞች የሚያሳዩት በmaterial ጠረጴዛ ነው ነገር ግን ቅዱስ ተብሎ ያስጠራው የጌታ ሥጋ እና ደም ስለሚሰዋበት ነው። ዋናው ቁም ነገር ግን የጌታን ሥጋ እና ደም ክብር ያልተረዳ ሰው የቅዱስ መሠዊያውን ክብር እንዴት ሊረዳ ይችላል? ስለዚህ ስለታቦት ከማውራታችን በፊት መጀመሪያ ስለክርስቶስ ሥጋ እና ደም አማናዊነት መግባባት ይኖርብናል።

ሌላ ደግሞ ብዙ ጊዜ ሚሰማ misconception አለ ታቦት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ብቻ ነው ያላት የሚል ነው ለዚህ ሲጀመር መልስ መስጠት አያስፈልግም ከታች በፎቶ ከግብጽ ኦርቶዶክስ ጀምሮ እስከ ካቶሊክ ድረስ ያላቸውን ታቦተ ምሥዋዕ ልክላችኋለሁ።
❤ 11 👍 2 🥰 1
ኪ
23:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
👍 4 ❤ 2 🥰 1
23:03
23:03
26 January 2024
ኪ
09:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ" (1ኛ ጢሞ 1፡15)
❤ 8 🥰 1
30 January 2024
ኪ
11:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
ማርያም እኮ ሞተች ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠራት ወደ ሕይወት ጠራት እናቴ ንግሥተ ሰማይ ወምድር ሆይ በቀኜ ተቀመጪ አላት ፣ ማርያምም በድንጋጤ አለቀሰች ሐዋርያትም ከየሃገረ ስብከታቸው ተሰባሰቡ ለእመቤታቸው አለቀሱ ፣ ነፍሷ ከሥጋዋ በተለየ ጊዜም መላእክት እና ሊቃነ መላእክትም ሊቀበሏት ወረዱ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስም የንግሥናን ልብስ አለበሳት።

ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ጻዕር ወጻማ
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ
ማርያም ሆይ በልጅሽ ቀኝ በክብር ለመቀመጥ ያለ ድካምና ያለ ጣር ከሥጋዋ ለተለየች ነፍስሽ ሰላምታ ይገባል

"Your stainless and wholly immaculate body has not been left on earth; the Queen, the Mistress, the Mother of God who has truly given birth to God has been translated to the royal palaces of heaven." John Damascene

እንኳን አደረሳችሁ ❤️
❤ 8 🥰 1
4 February 2024
ኪ
18:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? (መኃ 3፡3)

ፍቅር ይዞኛል ሊያውም ነፍሴ ከሥጋዬ ልትለይ እስኪመስለኝ ድረስ ነፍሴን የሚያከንፋት ፣ ከምድር ተለይቼ ወደ መሠወርያው ሊያደርሰኝ የሚያቃጣኝ ፍቅር ፣ ነፍሴ ወዳዋለች ኹለመናው በልቤ ላይ ነግሧል ካፈቀረኝ እስከሞትም በመስቀል ላይ እርቃኑን ከኾነልኝ ከርሱ በልቤ ላይ ቤቱን ከሠራው ንጉሥ ፍቅር ይዞኛል!! ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? እንደ በረዶ ነጭ ልብስን ለብሷል ከፀሐይ በላይ ደምቆ ይታያል በደም ያጌጠ ልብስ አለው ክብሩ ዓለማትን ሞልቷል እንደ ታረደ በግ በዙፋኑ ተቀምጧል።

አዎ እርሱ ነው ነፍሴ የወደደችው እርሱ ነው በኃጢአቴ ጠፍቼ ነበር ወደ ሞትም መንገድ ሄጄ ነበር ነፍሴ የወደደችው እርሱ ግን አገኘኝ በቆሻሻ ማንነት ኾኜ አገኘኝ እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስም ወደደኝ በውድ ዋጋ በደሙ ገዛኝ ውዴ አገኘኝ እኔም አገኘሁት በመሠዊያው ላይ አገኘሁት ከሥጋው እየቆረሰ ሲመግበኝ አገኘሁት ከሆዱም እያፈለቀ ሲያጠጣኝ አገኘሁት ነፍሴ ወደደችው ተገዛችለትም እርሱ የሰማይና የምድር ንጉሥ ነው ስሙም ከስሞች ኹሉ ከፍ ያለ ኢየሱስ ነው።

"እኔ የወዴ ነኝ ውዴም የእኔ ነው፤ በሱፉ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።" (መኃ 6፡3)
❤ 16 🥰 2 👍 1
14 February 2024
ኪ
04:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
መሢሑ የዮሴፍ ልጅ-የሕማም ሰው (Mashiach ben Yoseph-The Suffering Servant)

መሢሕ (በእብራይስጥ Mashiach- ማስያስ) ማለት የተቀባ ማለት ነው ግሪኩ ክርስቶስ ይለዋል። በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ወደፊት ከሚነሡ ከታላላቅ ሰዎች ውስጥ ዋነኛው መሢሑ ነው። በብሉይ ኪዳን ስለ መሢሑ ኹለት እርስ በእርስ የሚጋጩ የሚመስሉ ትንቢቶች ይገኛሉ ፣ የመጀመሪያዎቹ ትንቢቶች ንግሥናን ለዳዊት የሚመልስ በዙፋኑ ላይ ለዘላለም ስለሚነግሥ አሸናፊ መሢሕ ሲናገሩ [1,2]፣ ገሚሶቹ ደግሞ በገዛ ሕዝቡ የተጠላ ፣ በብዙዎች በደል ምክንያት የሚሰቃይ እና ስለሚሞት የሕማም ሰው ስለተባለ መሢሕ ይናገራሉ።[3,4]

እነዚህ ኹለት አይነት ትንቢቶች እንዴት እርስ በእርስ ሊታረቁ ይችላሉ? እንዴት ለዘላለም በዳዊት ዙፋን ይነግሣል የተባለው አሸናፊ ንጉሥ መልሶ ሊሞት ይችላል? ከሞተስ እንዴት ለዘላለም ይነግሣል? በውርደት ለዛውም በወገኖቹ ተጠልቶ የተሰቃየው የሕማም ሰው መልሶ በዳዊት ዙፋን ሕዝቡ ኹሉ ተቀብለውት ሊነግሥ ይችላል? አይሁድ እነዚህን ጥያቂዎች መመልስ ቢያቅታቸው ወደፊት የሚነሣው መሢሕ አንድ ሳይኾን ኹለት ነው አሉ። በኹሉም የታወቀው እና ንግሥናን በዳዊት ዙፋን ለዘላለም የሚነግሠው ፣ እስራኤልንም ከፍ ከፍ የሚያደርገው አሸናፊው መሢሕ፡ መሲሑ የዳዊት ልጅ (Mashiach ben-David)[5] ይባላል ፣ በሕዝቡ ዘንድም ታዋቂው እና አብዛኛው የሚጠብቀው መሢሕ ይሄን የዳዊቱን ልጅ መሢሕ ነው። ይህ መሢሕ ደግሞ አሸናፊ ንጉሥ ስለኾነ መቼም ሊሞት አይችልም። ብዙ ጊዜም አይሁዶች ከክርስቲያኖች ጋር ሲከራከሩ መሢሑ ሊሞት አይችልም ኢየሱስ ደግሞ ስለሞተ እርሱ መሢሑ ሊኾን አይችልም ብለው ነው። ነገር ግን አይሁድ በግልጽ ሊናገሩት የምይፈልጉት ብዙ ጊዜም የሚሸፋፍኑት ሌላ የሚሞት መሢሕ ታልሙድ በተባሉ መጻሕፍቶቻቸው ውስጥ አለ መሢሑ የዮሴፍ ልጅ (Mashiach ben-Yoseph)! [6]

መሢሑ የዮሴፍ ልጅ የሕማም ሰው(the suffering servant) እየተባለ በብዙ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ተገልጧል ከነዚህ ውስጥ ታዋቂው ኢሳይያስ 53 እና ዘካርያስ 9-12 ናቸው። በእነዚህ ትንቢቶች ዘገባ የሕማም ሰው የተባለው ይታይ ዘንድ ደም ግባት የለውም ፣ በወገኖቹ ዘንድ ተጠልቷል ፣ ትሑት ኾኖ በአህያ ውርጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል ፣ በሠላሳ ብር ይሸጣል ፣ ንጹሕ ምንም ኃጢአት የሌለበት ኾኖ ሳለ ግን በሕዝቡ ኃጢአት ምክንያት ይሰቃያል ፣ እንደሚታረድ በግም ሲወሰድ አፉን አይከፍትም ፣ ስለ ሕዝቡም መተላለፍ ይቆስላል ፣ ይወጋል የወጉትም ያዩታል ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም ያለቅሱለታል ፣ እግዚአብሔርም የሕዝቡን ኃጢአት በእርሱ ላይ ያደርጋል ፣ ይሞታልም መቃብሩንም በሃብታም ሰው መቃብር ያደርጉታል ፣ በእርሱ ቁስል ግን ሕዝቡ ኹሉ ይፈወሳል ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ጻድቃን ይኾናሉ። እንዲሁም እንደ ታልሙዶች ገለጻ ከኾነ ከሞተ በኋላ ኢየሩሳሌም ትሸበራለች ፣ ቤተ መቅደሱም ይፈርሳል [7] ነገር ግን በመጨረሻም መሢሑ የዳዊት ልጅ ይመጣል ፣ የዮሴፍ ልጅም ይነሣል ፣ ኢየስሩሳሌምን ይመልሳታል በምድር አሕዛብ መካከልም ታላቅ ትኾናለች የዳዊት ልጅም ንግሥናን ለዳዊት መልሶ በዙፋኑ ላይ ለዘላለም ይነግሣል።(Sounds Familiar 😊)

ይሄንን የሕማም ሰው መሢሕ ለምን የዮሴፍ ልጅ አሉት? ዮሴፍ የተባለው የኢየሱስ አሳዳጊ ፣ የማርያም እጮኛ ዮሴፍ አይደለም ነገር ግን በዘፍጥረት ታሪክ ላይ ያለው የያዕቆብ ልጅ ፣ የራሔል በኩር ልጅ ዮሴፍ እንጂ [8] ። ዮሴፍን እና የሕማሙን ሰው ምን ያመሳስላቸዋል? ዮሴፍ ሕልም በማለሙ እና በአባቱ በመወደዱ ምክንያት በወንድሞቹ ተጠልቷል ፣ የሕማሙ ሰውም በወገኖቹ ተጠልቷል። ዮሴፍ ወንድሞቹ ሊገሉት ተማክረውበታል ፣ የሕማሙን ሰውም እንዲሁ ተማክረውበታል። ዮሴፍ በወንድሞቹ ባሪያ እንዲኾን ወደ ግብጽ ተሽጧል ፣ የሕማሙ ሰውም ባሪያ (the suffering servant) ተብሎ በሠላሳ ብር ተሸጧል ። ወንድሞቹ ዮሴፍን እንደ ሞተ አድርገው ለአባቱ ለያዕቆብ ነግረውታል ፣ የሕማሙ ሰው ደግሞ ተገሏል። ዮሴፍ ንጹሕ ኾኖ ሳለ ያለጥፋቱ ለጠሉት እና ለሸጡት ለገዛ ወንድሞቹ ከረሃብ መዳን ምክንያት ኾኗል ፣ በሕማሙ ሰው ቁስልም የገዛ ያሰቃዩት ሰዎች ተፈውሰዋል። በእነዚህ ኹሉ ተመሳሳይነት ምክንያት የሕማሙን ሰው አይሁድ መሢሑ የዮሴፍ ልጅ ብለው ይጠሩታል።

አይሁዶች እንግዲህ አሁን ላይ ገና ወደፊት ከመሢሑ የዳዊት ልጅ በፊት ፣ መሢሑ የዮሴፍ ልጅ ይመጣል ብለው ይጠብቃሉ። እኛ ግን አንድም ሳያስቀር እነዚህን ትንቢቶች የፈጸመ ሰው በታሪክ ውስጥ የለም ወይ? እያልን እንጠይቃለን። ኹሉን ትንቢቶች አንድም ሳያስቀር የፈጸመ በታሪክ አንድ ሰው ብቻ አለ ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ (Yeshuah Ha’mashiach) ይባላል። ብሉይ ኪዳን ስለ ኹለት መሢሖች አይነግረንም ይህ የታልሙድ ፈጠራ ነው መሢሑ አንድ ነው ፣ አሸናፊው የዳዊት ልጅ እራሱ የሕማሙ ሰው የዮሴፍ ልጅ ነው። እንዴት? እንዴት ሞቶ ለዘላለም ይነግሣል? እንዴትስ ሞቶ ያሸንፋል? ይህ ለአይሁድ አእምሮ የማይቻል ነው። እርስ በእርሱ የሚጋጭ ቢመስልም ግን አይጋጭም ለኢየሱስ የመስቀሉ ሞት ውርደት አይደለም ነገር ግን ማሸነፊያው ነው! የነገሠው በዙፋን ላይ አይደለም በመስቀል ላይ እንጂ ፣ ንግሥናንም ለእስራኤል ዘነፍስ (ለቤተክርስቲያን) መልሷል። አዎ እራሱ ነው ፣ የሕማሙ ሰው ፣ አሸናፊው ንጉሥ ኢየሱስ ነው። አይሁድ ስሙን Yeshu (ስሙ እና መታሰቢያው ይጥፋ) ብለው ቢያበላሹትም እርሱ ግን አሸናፊ ስሙ Yeshuah (ያሕዌ መድኃኒት ነው) እየተባለ ፍጥረት ኹሉ እየተገዛለት በቤተክርስቲያን ላይ ለዘላለም ይነግሣል!! የነቢያት ትንቢት ፈጻሚ የሕማሙ ሰው ፣ መሢሑ የዮሴፍ ልጅ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና!! [9]

“እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ኹሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው። በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤ እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ (መሢሕ) መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።” ሉቃ 24፡44-48

References
1. መጻሕፈ ሳሙኤል ካልዕ 7፡12-16
2.ትንቢተ ኤርምያስ 33፡14-18
3. ትንቢተ ዘካርያስ 12፡10
4. ትንቢተ ኢሳይያስ 53፡4
5. Bavli Sukkah 52a; https://www.sefaria.org/Sukkah.52a.3?lang=bi
6. Bavli Sukkah 52b; https://www.sefaria.org/Sukkah.52b?lang=bi
7.ኢየሱስ ካረገ 37 ዓመታት በኋላ አይሁዶች በሮማውያን ላይ በማመጻቸው በሮማዊው ጥጦስ (Titus) በ70 ዓ.እ ኢየሩሳሌም ጠፍታለች፣ ቤተ መቅደሱም ድጋሚ ላይሰራ ፈርሷል አሁን በቦታው ላይ የአልአቅሳ መስጊድ ይገኛል።
8. ኦሪት ዘፍጥረት 37-50
9. ዮሴፍ እንዴት ለክርስቶስ ምሳሌ(type) እንደሚኾን በዚህ ይመልከቱ፡ https://www.bible.ca/d-bible-archeology-maps-timeline-chronology-Joseph-types-Christ-Shadows-Antitypes-similarities-comparisons-2166-1876BC.htm
👍 7 ❤ 1 🥰 1
15 February 2024
ኪ
23:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው (1ኛ ጢሞ 6፡16)

በዚህ ምድር ስንኖር ከብዙ ነገር ጋር ግኑኝነት እንጀምራለን እና እነዚህ ነገሮች ላይ ጥገኛ እንኾናለን ፣ ጥገኛ ከኾንባቸው ነገሮችም ደስታ እንዲሰጡን እንጠብቃለን ደስታ ሳይሰጡን ሲቀሩ ግን ለምንድነው ደስታን ያልሰጠኝ? እያልን መጨነቅ እንጀምራለን ለዘመናት ተለጥፈንባቸው ሕይወታችንን ስለመሰረትንባቸው ከእነርሱ ውጪ ሕይወት አይታየንም ለዘላለምም የሚቆዩ ይመስለናል። ባጣናቸው ቅጽበት ግን በጣም attached ስለኾንባቸው ሃዘናችንን መቋቋም አንችልም ከእነርሱ ውጪም ሕይወት ስላማናውቅ ካጣናቸው በኋላ ሕይወት ትርጉም ያጣብናል ቀስ በቀስም ወደ ድብርት እንገባልን። እነዚህ ነገሮች ለተለያየ ሰው የተለያዩ ናቸው፡ አንዳንድ ሰው ገንዘብ ላይ ይለጠፋል ፣ አንዳንዱ ቤተሰብ ላይ ፣ አንዳንዱ ሥራ ላይ ሌላውም እንዲሁ ያስደሰተው ነገር ላይ።

ከነዚህ ኹሉ በላይ የኾነ አንድ እውነታ ግን አለ ኹሉም ነገር ሃላፊ ነው! ገንዘብ ብንል ሃላፊ ነው ፣ ቤተሰብ ብንል ምንም ብንወዳቸው ይሞታሉ ፣ ሥራ ብንል ይጠፋል በዚህ ዓለም ላይ ዘላለማዊ ነገር የለም ኹሉም ነገር ያልፋል ስለዚህ ቅዱስ ዮሐንስ "ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ...ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ" እያለ ይመክረናል (1ኛ ዮሐ 2፡15-17)። ኹሉም ነገር ሃላፊ መኾኑን ስንረዳ ከመጠን በላይ በአንድ ነገር ላይ አንጣበቅም በዚህም ምክንያት ያ ነገር እያለ ከእርሱ ብዙም አንጠብቅም (Expectations – the real happiness killer) ፣ ካላፈም አንጎዳም መጀመሪያውኑ ሃላፊ እንደኾነ ተረድተን አልተላጠፍንበትምና (Over attachment another happiness killer)።

ከመጠን በላይ መጣበቅ ያለብን በሃላፊ ነገር ላይ ሳይኾን የማያልፍ ነገር ላይ ነው በዚህ ምድር ስንኖር ደግሞ የማያልፍ ነገር አንድ ብቻ አለ እርሱም "ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ" ያለው አልፋ እና ዖሜጋው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው (ራእ 1፡18)። ቢሞትም እንኳን ሕያው የኾነው እርሱ ብቻ ነው እርሱ ዓለምን ያሳልፋል እንጂ አያልፍምና። ቅዱስ ዳዊት ይሄን ቢረዳ "አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ኹላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል፤ አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።" እያለ ዘላለማዊ አምላኩን አመሰገነ (መዝ 101/102፡25-27)።

እውነት ነው የማያልፈው እርሱ ብቻ ነው ስለዚህ መኖር ካለብንም ለእርሱ ለማያልፈው ብቻ እንኑር ለቤተሰቤ እኖራለሁ ብንል እነርሱም ያልፋሉ ፣ ጥሩ ቤተ ሰርቼ በጥሩ ሥራ ኖራለሁ ብንል ያልፋል ኢየሱስ ግን አያልፍም! ስለዚህ በዚህ ኹሉም ነገር አላፊ በኾነው ዓለም ውስጥ እየኖርን ፣ ለማያልፈው ዘላለማዊ ለኾነው ለክርስቶስ እንኑር "እርሱ ብቻ የማይሞት ነውና" (1ኛ ጢሞ 6፡16)
❤ 4 🥰 2
17 February 2024
ኪ
11:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዜማ መሣርያ?

ከሰሞኑ ወዲህ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በአጫብር ስም እየተስፋፋ ያለውን ጭፈራ እና ዳንስ ስመለከት እንደ ጥንት አባቶቻችን ዘመን ምንም የዜማ መሳርያ ወደ አለመጠቀም ብንመለስ ብዬ አስባለሁ እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ከኹሉም የበለጠ የዜማ መሳርያ የሰው ልጅ ነውና።

"ከከንቱ ጥበባት መካከል ፡ በገና መጫወት፣ መጨፈር፣ ዋሽንት መጫወት ይገኙበታል እነዚህም ልክ ጨዋታው ሲቆም ውጤታችውም አብሮ ይጠፋል ደግሞም፣ እንደ ሐዋርያው ቃል፣ የእነዚህ ውጤቶች ጥፋት ነው።" (ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ትርጓሜ ኢሳይያስ 5፡ Basil of Caesarea Commentary on Isaiah 5 )

"በከበሮ ፋንታ ዝማሬ፣ በዘግናኝ ውዝዋዜና ዘፈን ፋንታ መዝሙር፣ ከቲያትር ማጨብጨብ ይልቅ የምስጋና አድናቆትን እንቀበል።" (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ፡ Gregory of Zanianzus Patrologia Graeca 35:709B)

"ዋሽንቱ ራሱ ክፉው የተናገረውና ሔዋንን ያሳታት የእባቡ ምሳሌ ነው። ሲጫወት ጭንቅላቱን ወደ ኋላ በመወርወር ወደ ፊት ጎንበስ ብሎ እንደ እባብ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ ዘንበል ይላል።" (ቅዱስ ኤጺፋንዮስ ዘሳላሚስ፡ Epiphanus of Salamis, Panarion XXV)

"አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር የኅብረት ዝማሬ ከገባ, የዜማ መሣሪያ አያስፈልግውም" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፡ Chrysostom, Exposition on the Psalms, 42.2-3)

እንደዚ አይነት ብዙ ጥቅሶችን ማምጣት ይቻላል በጠቅላላ የጥንቷ የቤተክርስቲያን አባቶች ምንም ኣይነት የዜማ መሣርያን ለቤተክርስቲያን አይፈቅዱም ነበር አሁን ላይ በመዝሙሮቻችን ላይ ያለውን መበላሸት ስናይ ደግሞ ልክ ነበሩ ያስብላል። የኔ ሃሳብ ወደ ጥንቱ እንመለስ ነው እናንተስ እስቲ ሃሳባችሁን ስጡበት።
👍 3
21 February 2024
ኪ
11:40
ኪዳን ዘኢየሱስ
መሠዊያው የክርስቶስ ስም እና ሥዕል ተደርጎበት በሊቀ ጳጳስ ቡራኬ በሜሮን በመንፈስ ቅዱስ ከከበረ ዘንድ የክርስቶስ ምልክት ይሆናል፤ እርሱ ወደ መስቀል ከመውጣቱ በፊት ራሱን በቅዱሳን እጆቹ ላይ አድርጎ በቁርባን ሥርዓት ሠውቷልና፤ "አንሥቶ ባረከ፤ ቆረሰ፤" እንዲል። (ማቴ. 26፥26) በዚህም ምክንያት በዑደት ጊዜ ካህናት መሠዊያን (ታቦትን) በራሳቸው ይሸከማሉ፤ የቤተ ክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ነውና። ይህ ደግሞ ጥልቅ የሆነ (mystical) የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ሥርዓት ነው፤ በተለይየ መልኩ በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ይገኛል።
***
ከዲያቆን በረከት አዝመራው ገጽ የተወሰደ።

መታሰቢያነቱ የታቦት የማውጣት ሥርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ያለ ለሚመስላቸው ይኹንልኝ
👍 2 ❤ 1 🥰 1
23 February 2024
ኪ
12:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ወሪድየ ብሔረ ሮሜ ለቤተክርስቲያን ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ" ቅዱስ ያሬድ

ወደ ሮሜ ሃገር ወርጄ ቤተክርስቲያንን አየኋት አወኳት ወደድኳት። ይህን ዜማ ያዜመው ቅዱስ ያሬድ ነው ፣ ቅዱስ ያሬድ ግን ምን ነካው? ካልጠፋ ቤተክርስቲያን የሮሜን ቤተክርስቲያን እንዴት ወደድኳት ይላል? በቅዱስ ያሬድ ዘመን እኮ Oriental Orthodox ከሮም በጉባኤ ኬልቄዶን ምክንያት ተለይታለች ምናለ ቅዱስ ያሬድ ወሪድየ ብሔረ እስክድርያ ቢል። ነገሩ ወዲህ ነው ቅዱስ ያሬድ የሮምን ቤተክርስቲያን ያነሳው ካቶሊክ ኾኖ አይደለም ነገር ግን በኹለተኛው ክፍለ ዘመን ከነበረ መጽሐፍ ምንጭ ወስዶ ነው ፣ መጽሐፈ ሄርማ ኖላዊ (The Shepherd of Hermas)።

ሄርማ ወደ ሮም የተሸጠ ባሪያ ነበር በኋላም ነጻነት ተሰጥቶት ብዙ ራእዮች ተገልጦለታል ከነዚህ ራእዮች መካከል የንስሐ ፍሬ እንዲያፈራ እና የልጆቹን ኃጢአት እንዲያስተካክል እየነገረችው ደካማ ኾና በልጆቿ ኃጢአት ረዳት የሌላት አሮጊት ሴት በሚመስል አምሳል ቤተክርስቲያን ተገልጣለታለች። ከዚያም ንስሐ ከገባ በኋላ እና ልጂቹን ከገሰጻቸው በኋላ መልኳ ከበፊቱ የተሻለ ኾኖ አሁንም ግን ነጭ ጸጉር ባላት አረጋዊት ሴት ተገለጠችለት ። በመጨረሻም የንስሐን ፍሬ ስታሳየው በወጣት እና እራሷን እንደ ክብርት ሙሽራ አድርጋ አሳይታው ቤተክርስቲያን ክብሯን ገልጣለታለች። በመጨረሻው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በእረኛ መልአክ አምሳያ ተገልጦለት ብዙ ትእዛዛትን ሰጥቶታል (ለዛም ነው መጽሐፉ ኖላዊ ፣ እረኛው የተባለው እንጂ ሄርማስ እረኛ ኾኖ አይደለም)

ይህ የሄርማ መጽሐፍ ለሐዋርያት በጣም ቅርብ ከመኾኑ የተነሳ እንደነ ቅዱስ ሄሬኔዎስ ዘልዮን የመሳሰሉ አባቶች እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ይቆጥሩት ነበር ፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የማያዩትም ታላቅ አክብሮት አላቸው። ይህ መጽሐፍ በቅዱስ ያሬድ ዘመን ወደ ግእዝ ሲተረጎም ሄርማ ያያትን ቤተክርስቲያን ወደድኳት ብሎ አዜመላት በሄርማ ዘመን የሮም ቤተክርስቲያን ገና ወደ ኑፋቄ አልገባችም እና።

ነገር ግን ሄርማ ሆይ አሁን ወደ ሮሜ ብትወርድ አይተህ የምትወዳትን ቤተክርስቲያን አታገኝም ይልቅስ በኑፋቄ የተሞላች የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ታገኛለህ እንጂ ስለዚህ ካንተ ወስደን "ወሪድየ ብሔረ ኢትዮጵያ ፣ ወሪድየ ብሔረ እስክንድርያ ፣ ወሪድየ ብሔረ አርመንያ ፣ ወሪድየ ብሔረ ሶርያ ፣ ወሪድየ ብሔረ ሕንድ" እያልን ብናዜም ቅዱስ ያሬድም ቅር ሚሰኝብን አይመስለኝም።

ለማንኛውም መጽሐፈ ሄርማ ኖላዊን ታነቡ ዘንድ ጋበዝኳችሁ ከታች በEnglish እና በግእዝ ለቅላችኋለው።
❤ 2 🥰 1
12:36
ግእዙን ለምትፈልጉ ይኸው፡
https://archive.org/details/hermaepastor0000herm/page/n11/mode/2up
🙏 3
25 February 2024
ኪ
23:59
ኪዳን ዘኢየሱስ
የማሳፍረው ልጁ

ወልዶኛል! ሊያውም በመስቀል ላይ ከጎኑ በፈሰሰ ውሃ። ዋጅቶኛል በደሙ አጥቦ የክብሩ ተካፋይ ወራሽ አድርጎኛል ለመንግስቱም መርጦኛል። ኃጢአተኛ ሳለሁ ከእርሱ ርቄ ሸሽቼ በጠፋው ጊዜ ክብሩን ትቶ ከወደኩበት ፈልጎ አግኝቶ ከነ ቁሻሻዬ ተቀብሎኛል ልጁ አድርጎኛል!

እኔ ግን አሳፍረዋለሁ በምኞቴ ተስቤ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እጨምራለሁ ስሙን ተሸክሜ በኹሉ ዘንድ አሰድበዋለሁ እርሱ ግን አልተወኝም ለካስ ጌታዬ ባሳፍረውም አያፍርብኝም ፣ የኃጢአተኞች ወዳጅ መባልን አይጠላም ይወደኛል! የማሳፍረው ልጁን ይወደኛል ልጅነቴን አልወሰደብኝም እቅፉን ዘርግቶ አባትህ ይፈልግሃል ይለኛል ኃጢአተኛውን እኔን ይወደኛል። ተቅበዝብዤ የጠፋሁትን በግ ከነ ጭቃዬ በእቅፉ ይወስደኛል ልጄ የት ጠፍተህብኝ ነው ይለኛል!!

አባቴ የጠፋሁት እንዴት እንዲህ የወደድከኝ አባት ፊት ልቁም አፈርኩህ መስቀል ላይ የከፈልክልኝ ውለታ ፊቴ እየመጣ ሕሊናዬን ወጋኝ ፣ የተዋረድክልኝን ውርደት ሳስበው መሬት ተከፍታ ብትውጠኝ ተመኘሁ ለፍቅርህ ምላሽ ባይኖረኝ ስምህን በሰው ፊት ባሰድብ ጊዜ መልሼ ፊትህ መቆም አፈርኩ እኔ አሳፋሪ ልጅ ነኝ ሞትህ አይገባኝም ፣ መስቀልህ አይገባኝም ፣ ፍቅርህ አይገባኝም ነበር። አንተ ግን ተቀበልከኝ ፣ በመቀል ላይ ባፈሰስከው ደም አጠብከኝ በደለኛውን እኔን ወደድከኝ ጌታዬ ፍቅርህ ደነቀኝ!!
❤ 3 👍 3 🥰 2
26 February 2024
ኪ
23:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
Basics of Miaphysite (ተዋሕዶ) Christology:

Miaphysis, derived from Greek, denotes "one united/composite nature," while Tewahedo, from Ge’ez, signifies "unified nature" or "being made one nature." Both terms encapsulate the essence of Miaphysite Christology.
Miaphysitism posits that in the Incarnation, the self-subsistent Hypostasis of God the Word unified with a non-self-subsistent human hypostasis, resulting in the one composite Hypostasis and Nature of God the Word Incarnate.
Hypostasis refers to individuality, distinct existence of a nature. Christ, being from two natures and two hypostases, embodies both the eternal, uncreated Nature and Hypostasis of the Word, united with the temporal, created human hypostasis.
This union yields one composite Nature and Hypostasis of the Word Incarnate, retaining all properties of Divinity and humanity without mixture or confusion.
Miaphysitism emphasizes the unity of Christ's personhood, maintaining the integrity of the Divine and human properties within the unified Hypostasis.
St. Severus of Antioch (ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ) underscores that while Christ possesses two hypostases, He exists as one composite Hypostasis from two individualized, existing natures.
The Incarnate Word is one Prosopon, the Person of God the Word in His Incarnate state, preserving the integrity of His Personhood throughout.

Significance of Miaphysite Christology:

Miaphysite Christology upholds the true hypostatic humanity of Christ without separating Him into two individual hypostases.
It emphasizes the mystery of the Incarnation, affirming Jesus Christ as both fully God and fully man without mixture or confusion.
Miaphysitism maintains the reality of Christ's unity, rejecting attempts to dissect or explain the union beyond its divine mystery.
By embracing Miaphysite Christology, Oriental Orthodoxy remains faithful to the unfathomable mystery of the Incarnation, honoring the profound unity of Divinity and humanity in Christ.

Full Article here: https://polishmiaphysite.wordpress.com/2020/06/23/basic-miaphysite-christology/
👍 6 ❤ 1
2 March 2024
ኪ
11:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
ያለ ቅዱስ ጊዮርጊስ አድዋ አይታሰብም
ሰማዕተ ኢየሱስ ቅዱስ ጊዮርጊስ በትውልድ ሮማዊ
ዘሩ ክርስቶሳዊ እንኳን አደረሳችሁ ❤️
❤ 7 🥰 2
5 March 2024
ኪ
13:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
አብ አኃዜ ኩሉ (ኹሉን የያዘ አባት)

ብዙ ጊዜ ስለክርስቶስ እናወራለን ፣ እንናገራለን ፣ እንሰብካለን እርሱ የድኅነታችን ቀንድ የሃይማኖታችን ራስ ነውና! እስቲ ደግሞ ዛሬ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ስለተባለው ኹሉን ስለያዘ አባት እግዚአብሔር አብ እንናገር።

የኹሉ አስገኚ አብ ነው ለእርሱ ግን አስገኚ የለውም ይልቅስ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ራሱ መገኛቸው ነው። አባቶቻችን ሐዋርያት በአመክንዮአቸው "እስመ አልቦ ውስተ ህላዌሁ አመክንዮ ... አላ ባሕቱ ህልው በኩሉ መዋዕል አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት። ወአልቦ ዘይክል ቀሪበ ኀቤሁ። ኢኮነ ክልዔተ ወኢሠለስተ ወኢይትዌሰክ አላ አሐዱ ውእቱ ባሕቲቱ ዘይነብር ለዓለም - ለመገኘቱ ምክንያት የለበትም በአስገኝነት ብቻውን በዘመናት ኹሉ ይኖራል እንጂ ጅማሬም የለውም ፍጻሜም የለውም ማንም ሊቀርበው አይችልም ኹለተኛም አይደለም ሦስተኛም አይደለም አይጨመርበትም ብቻውን ለዘላለም የሚኖር አንድ ነው እንጂ።" እያሉ የአብን አኗኗር እና አስገኚ የማያሻው ብቸኛ አስገኚነት ይነግሩናል።

አብ ለኹሉም ነገር መሠረት ነው ለቃሉ እና ለእስትንፋሱ መሠረት ኾኖ በእነርሱ ዓለማትን ፈጥሯል ፣ ቃሉ እና እስትንፋሱም መገኛቸው ከእርሱ ነው ነገር ግን ይህ አስገኚነት ዓለማትን እንዳስገኘበት ያለ አስገኚነት አይደለም ፣ አብ ከዓለማት በፊት ነበረና ከቃሉ እና ከአስትንፋሱ በፊት ግን አልነበረም አብ ከቃሉ እና ከእስንፋሱ ውጪ የኖረበት ጊዜ አለ ካልን ቃል የሌለው ዲዳ እና እስትንፋስ የሌለው ምውት እናደርገዋለን። የቃል ከአብ መገኘት ዘላለማዊ ልደት (Eternal Begetting) ስንለው የእስትንፋስን ከአብ መገኘት ዘላለማዊ ሥርጸት (Eternal Procession) እንለዋለን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከአብ መገኘታቸው በዘላለማዊ ጊዜ ውስጥ ነዋና ስለዚህ ነው አባቶች "ልደቱ ለወልድ ወጸአቱ ለመንፈስ ቅዱስ ዘኢይኀልቅ-የወልድ መወለድ እና የመንፈስ ቅዱስ መውጣት አያልቅም" የሚሉት በዘላለም ውስጥ ከመሠረታቸው አብ እየወጡ ይቀጥላሉና ይህ ትምህርት በቀጰዶቅያ አባቶች(Cappadocians Fathers i.e. ባስልዮስ ዘቂሳርያ(Basil of Caesarea) ፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ (Gregory of Nazianzus) ፣ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ(Gregory of Nyssa)) ዘንድ Monarchy of The Father ይባላል።

ከዚ የተነሣ የኹሉ መገኛ የኾነ አንድ አምላክ አብ አለን እንላለን አብ መሠረት ነውና የሥላሴ አንዲት ባሕርይ መገኛ የእግዚአብሔር አብ አካል ነው ፣ ከአካሉ በተገኘ ባሕርይ የተወለደው ወልድም ከአብ የተነሣ ከእውነተኛው አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ እንለዋለን ፣ መንፈስ ቅዱስም ይህንኑ ባሕርይ ተጋርቶ ከእውነተኛው አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ነው።

ዓለምን በቃልህ ፈጠረህ በእስትንፋስህ ሕይወትን የሰጠህ የኹላችን አባት እግዚአብሔር አብ ሆይ በተወዳጁ ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናመሰግንሃለን አንተን ክደን በጠፋን ጊዜ በልጅህ ወደ አንተ ሰበሰብከን ፣ በመንፈስህም አጸናኸን ከፍቅርህ የተነሣ የሚያምንበት ኹሉ ሕይወትን እንዲያገኝ አንድ ልጅህን ለኹላችን ቤዛ አድርገህ ለሞት አሳልፈህ ሰጥተኸዋልና ስለዚህም እኛ ከመላእክት ጋር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እያልን እናመሰግንሃለን የሕይወታችን ባለቤት አስገኚ የሌለህ አስገኚያችን አንተ ነህና!

ያለ እርሱ ሕይወት የለንም ያለ ልጁ መዳን የለንም ያለ መንፈሱም ጽድቅ የለንም ያለ እርሱ ኹሉ አልቦ ነው! የኹሉ አባት አብ ❤️
❤ 11 🥰 1
9 March 2024
ኪ
23:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዘወረደ (የዐብይ ጾም የመጀመርያ ሳምንት)

ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ያለው ዓለምን ኹሉ በእጁ የጠቀለለው ፣ ለዓለማት ዓለም ለእርሱ ግን ዓለም የሌለው በዘመናት የሸመገለው ዘመናትን ግን የሚያስረጀው አምላክ አኃዜ ዓለማት ፣ ገባሬ ፍጥረታት ወረደ! ከላይ ከሰማያት ከአርያም ከፍታ ወረደ! ዓለምን የያዘው ተያዘ ፣ በጊዜ የማይወሰነው ዘመን ተቆጠረለት ፣ ዓለምን የጠቀለለው በዓለም መሃል ተመላለሰ ፣ በሰማያት ያለው ዙፋኑን ሳይተው ወደ ምድር ወረደ ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በግርማው ያለውን በታች በእናቱ እቅፍ አየነው ፣ ዳሰስነው ፣ በመካከላችን 33 ዓመታትን ተመላለሰ በእርሱም ረካን ፣ በልተነውም ጠገብን አይሁድ ግን አላወቁትም ቢያውቁትስ ኖሮ የክብርን ንጉሥ ባልሰቀሉት ነበር ፣ እኛ ያወቅነው ግን ከመስቀሉ ሥር ተጠግተን የሕይወትን ውሃ ከጎኑ እንጠጣለን ከሥጋውም እየቆረስን እንበላለን ይህ ኢየሱስ ከሰማይ የወረደ ለዓለም ኹሉ ሕይወትን የሰጠ ሰማያዊ እንጀራ ነውና!!

"ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ- በቃሉ የሚያድን የኹሉ ጌታ መኾኑን ባያውቁ ከከፍታ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት" ቅዱስ ያሬድ

የአምላክን መወረድ የምናጣጥምበት ሳምነት ይኹንልን እንኳን አደረሳችሁ ❤️
❤ 5 🥰 2
11 March 2024
ኪ
12:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
በተዋሕዶ (Oriental) ኦርቶዶክስ የሚዘከረው ኬልቄዶናዊ

ዘመኑ 622 ዓ.እ ነው ቦታው የጥንቷ የምሥራቅ ሮማ ሥርወ መንግስት ወይም የበራንጥያ መንግስት ነው (Eastern Roman Empire aka Byzantine Empire) ጉባኤ ኬልቄዶን ተካሂዶ የምሥራቁ ዓለም ክርስትና ኹለት ቦታ ከተከፈለ 171 ዓመታትን አስቆጥሯል የቢዛንቲን ነገሥታት ከኬልቄዶን ጎን ከወገኑ ቆየት ብሏል። የዘመኑ ኬልቄዶናዊ ንጉሥ ስሙ ሕርቃል (Heraclius) ይባላል።

የByzantine Empire አንድ ስጋት ወሯታል ፋርሳውያን (Persians) እየተጠናከሩ ወደ byzantine እየገቡ የምሥራቁን ክፍል አብዛኛውን ተቆጣጠሩ የByzantine Empire ውድቀት የደረሰ ይመስላል ሰዉ ኹሉ Byzantine አበቃላት ፣ ታላቋ ሮማ ወደቀች ፣ ቁስጥንጥንያ አመድ ኾነች እያሉ ያወራሉ እውነትም Persianስ የሚያስፈሩ ይመስላሉ ወደ Byzantine በመግባት ኢየሩሳሌምን ተቆጣጠሩ ንግሥት ዕሌኒ ያሰራችን የመስቀል ቤተመቅደስ በማፍረስ መስቀሉን ወሰዱ።

Oriental Orthodox እና Eastern Orthodox ጥል ላይ ቢኾንም የክርስቶስ መስቀል ላይ የተነሣ ኹሉ የጋራ ጠላት ነውና Orientalኦችም ድጋፋቸውን ለንጉሡ ለሕርቃል አሰሙ ፣ Persian ምታ መስቀሉን አስመልስ የእግዚአብሔር ድል ከአንተ ጋር ይኾናል እኛም እንጾምልሃለን አሉት በሕርቃል ውስጥ ታላቁን ቆስጠንጢኖስ አይተዋልና! ቆስጠንጢኖስ በመስቀል ምልክት ድል እንዳደረገ እርሱም ስለመስቀል ቢዋጋ ድል እንደሚያደርግ አምነዋልና ፣ የቆስጥንጢኖስ ልጅ ሕርቃል ዝመት የዕሌኒን መስቀል አስመልስ Persiaን ደምስስ ኢየሩሳሌምን ነጻ አውጣ እያሉ አወደሱት።
ሕርቃልም ዘመተ ከቁስጥንጥንያ ወደ Anatolia ፣ ሄዶም የpersian ወደ ኤፍራጠስ ወንዝ access ዘጋባቸው እነርሱም ወደ ቀጰዶቅያ (Cappadocia) ሸሹ ፣ የሕርቃል ሠራዊትም ቀጰዶቅያ ላይ ቀድሞ ነበር እና በቀጰዶቅያ አይቀጡቅጣት ቀጣቸው በዚህ ጦርነትም ፋርሶች ተዳከሙ በመጨረሻም በ628 ዓ.እ ሙሉ በሙሉ ተሸንፈው Byzantiንን በሙሉ ለቀቁ ሕርቃልም የክርስቶስን መስቀል ይዞ ወደ ክብር ቦታው ወደ ኢየሩሳሌም ዕሌኒ ወዳሰራችው የትንሣኤ ቤተክርስቲያን መለሰው።

በዚህ ታሪኩም ዛሬም ድረስ ለሕርቃል የጾሙለትን ጾም በማሰብ ከጾመ ኢየሱስ አንድ ሳምንት በፊት የክርስቶስን መስቀል መመለስ በማሰብ በሕርቃል ስም እየታሰበ ይጾማል። በዚህም ምክንያት ኬልቄዶናዊ እስከ ዛሬ ድረስ በስሙ ጾም ታስቦለት ስሙ በዐቢይ ጾም ኹሉ ይዘከራል።

Note: ሕርቃል ኬልቄዶናዊ በመኾኑ በእኛ ቤተክርስቲያን ዘንድ ቅድስና የለውም።
❤ 11 👍 1 🥰 1
12 March 2024
ኪ
19:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
Platytera ton ouranon (More Spacious than the Heavens)

Universe በጣም ሰፊ ነው ፣ ሰፊ ከመኾኑ የተንሣ አሁን በደረስንበት ቴክሎሎጂ እንኳን ማየት የምንችለው የUniversን 5% ብቻ ነው (Size of the Observable universe)። ይሄ ማየት የምችለው 5% Universe ብቻ 93 Billion Light Year ይረዝማል ፣ እንግዲህ በዓለማችን ላይ ከብርሃን በላይ ፈጣን ነገር የለም በብርሃን ፍጥነት ራሱ ግን Observable Universን ለማካለል 93 Billion ዓመታትን ይፈጃል ይህ ደግሞ ጭራሽ የማይቻል ነው 93 Billion ዓመታት ኖረው ቢቻል ራሱ ገና ያላካለልነው 95 % Universe ይቀራል።

ሰማያት እንግዲህ ይሄን ያህል ቢሰፋ ራሱ ለእኛ ለውስኖቹ ዓለም ይኾነናል እንጂ በፈጣሪ ዘንድ ውስን ነው እርሱ ዓለማትን ኹሉ በእጁ ጠቅልሎ ይዟልና! (The universe, for all its vastness, remains finite. God, on the other hand, is infinite!) ለዚህ ነው የመልክአ ሥላሴ ደራሲ " ዓለማተ ዓለም ሥላሴ ዘአልብክሙ ዓለም - ሥላሴ ሆይ እናንተ ለዓለማት ዓለም ናችሁ ለእናንተ ግን ዓለም የላችሁም" ያለው።

በዚህ ሳምንት ግን አንድ ድንቅ ነገር እናስባለን ፣ ይህ በዓለማት የማይወሰነው አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በድንግል ማኅጸን ተወሰነ (God who could not be contained in his created universe chose to be contained in the tiny womb of this human being.) ስለዚህም ድንግልን Platytera ton ouranon (ከሰማያት ኹሉ የሰፋች) እንላታለን እስመ አግመረቶ ለዘኢይትገመር (የማይወሰነውን ወስናዋለችና)። እንዴት ይገርማል አባ ሕርያቆስ ቢደንቀው "ሰባት የእሳት ነበልባል መጋረጃ በሆድሽ ውስጥ እንዴት ተዘጋጀ ወዴትስ ተጋረደ ፤ ከጎንሽ በቀኝ ነውን ወይስ ከጎንሽ በግራ ታናሽ አካል ስትኾኚ ፤ የሚያንጸባርቅ ነደ እሳት የሚከበው ፤ ኪረቤል የሚሸከሙት ዙፋን በሆድሽ ውስጥ እንዴት ተዘጋጀ ወዴትስ ተተከለ ታናሽ ሙሽራ ስትኾኚ ... ከስፋት ጋር የሆድ መጥበብ እንደምን ያለ ነው" እያለ በድንግል የተሰራውን ሥራ ያደንቃል ከዓለማት የሰፋው አምላክ በማኅጸኗ ጥበት ተወስኗልና!!

ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ ማኀጸነ ድንግል ጾሮ፤ እንዘ አምላክ ውእቱ ኀደረ ወተገምረ - ሰማይ እና ምድር የማይወስኑትን የድንግል ማኅጸን ተሸከመው ፤ አምላክ ቢኾንም አደረ ተወሰነውም። ስለዚህ እኛም ኹልጊዜ Platytera ton ouranon የተባለች ድንግልን ባሰብን ጊዜ እኛን ለማዳን አምላክ ከሰማይ ወደ ምድር ያደረገውን መውረድ እናስባለን ፣ የእምነታችን ኹሉ መጀመሪያ ወረደ ፣ ተወለደ ነውና!
❤ 7 👍 1 🥰 1
14 March 2024
ኪ
16:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
Did you know that the first two countries to adopt Christianity as the official state religion are part of the Oriental Orthodoxy Communion?

They are the Armenian Apostolic Church and the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.

Oriental Orthodoxy: The One, Holy, Catholic, and Apostolic Church ❤️

ክርስትናን ብሔራዊ ሃይማኖት በማድረግ የመጀመሪያዎቹ ኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጽብሐዊ ኦርቶዶክሳውያን እንደኾኑ ያውቃሉ?

እነርሱም የአርማንያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ናቸው።

ጽብሐዊት ኦርቶዶክስ፡ አንዲት ፣ ቅድስት ፣ ኩላዊት እና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ❤️
❤ 6 🥰 1
15 March 2024
ኪ
00:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጥብቅና ተዋሕዶ (Defense of Miaphysitism)

እንደምናውቀው በ428 ዓ.እ የቁስጥንጥንያ ጳጳስ የኾነው ንስጥሮስ (Nestorius of Constantinople) ባስነሳው ክህደት ምክንያት አባቶች በ431 ዓ.እ በኤፌሶን ተሰብስበው እሱን አውግዘውታል፡ እዚህ ጉባኤ ላይ አፈ ጉባኤ የኾኑት 3 ሊቃነ ጳጳሳት ፡ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ (Cyril of Alexandria) ፣ ቅዱስ አቃቄዎስ ዘሜልጤኒ (Acacius of Meltine) እና ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘአንካራ (Thedotus of Ancrya) ናቸው። ጉባኤውም የነዚህን አባቶች አስተምህሮ ኦርቶዶክሳዊ ነው ብሎ አጽድቆ ተቀብሏል ። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ከ 20 ዓመታት በኋላ ቁስጥንጥንያ እህቶቿን አስክንድርያን እና አንጾኪያን በመተው ለሮም ወግና የነዚህን አባቶች ትምህርት ክዳ በጉባኤ ኬልቄዶን ከተዋሕዶ በኋላ ኹለት ባሕርይ የሚለውን ትምህርት ተቀበለች።

የምጸት ሳቅ የሚያስነሳብን አንድ ነገር ግን አሁንም የቁስጥንጥንያ ቤተክርስቲያን ከተዋሕዶ በኋላ ኹለት ባሕርይ እያለች ጉባኤ ኤፌሶንን እና ሦስቱን አባቶች በቅድስና እቀበላለው ትላለች ነገር ግን እነዚህ ሦስቱ አባቶች ከተዋሕዶ በኋላ በጭራሽ ኹለት ባሕርይ እንደማይባል አስተምረዋል ለአብነት ጥቂት እንመልከት።

"Wherefore, we say that the two natures were united, from which there is the one and only Son and Lord, Jesus Christ, as we accept in our thoughts; but after the union, since the distinction into two is now done away with, we believe that there is one nature of the Son. ስለዚህ እኛ ኹለቱ ባሕርያት በመዋሐዳቸው አንድ እና ብቸኛ ወልድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለ እንላለንል ፤ ከተዋሕዶ በኋላ ግን ወደ ኹለት መከፈል ስለቀረ የወልድ አንድ ባሕርይ እንዳለ እናምናለን "
St Cyril, Letter 40 to Acacius (ቅዱስ ቄርሎስ ለአቃቄዎስ በላከው መልእክቱ)

"... let everyone be forced to publicly anathematize the dogmas of Nestorius and Theodore: especially those who say two natures after the union, properly each one working. For of those who are in Germanicia I have found some experienced, indeed refusing to say two sons, but indeed not refusing to say two natures. ኹሉም በግልጥ የንስጥሮስ እና የቴዎዶሮስን ዶግማ እንዲያወግዙ ይደረጉ በተለይ ከተዋሕዶ በኋላ በራሳቸው የሚሰሩ ኹለት ባሕርያት አሉ የሚሉ። በጀርማኒካ ኹለት ልጆች ማለትን ክደው ነገር ግን ኹለት ባሕርያት ማለትን የማይክዱ አሉና። "
St Acacius of Melitene, Letter 1 to St Cyril ( ቅዱስ አቃቄዎስ ለቄርሎስ በላከው መልእክቱ)

"How did he impoverish himself on our behalf? Let those who separate the manhood from God the Word, parting him who was unit­ed by mention of natures, who say Christ is 'two things,' introducing for their defense a merely invented unity – let them tell us. እራሱን ስለእኛ እንዴት አደኸየ? በባሕርያዊ ተዋሕዶ የተዋሐደውን እርሱን ሰውነቱን ከእግዚአብሔር ቃል የሚለዩ ፣ ክርስቶስ ኹለት ነገሮች ነው የሚሉ ፣ ለጥብቅናቸውም የፈጠሩትን አንድነት የሚናገሩ እስቲ ይንገሩን"
St. Theodotus of Ancyra, Second Homily on Birth of Jesus Christ our Savior (Homily at Ephesus) (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘአንካራ ስለክርስቶስ ልደት በኤፌሶን በአስተማረው ትምህርት ላይ የተናገረው)

ታድያ እንደዚህ ዓለማአቀፍ ጉባኤ ያረጋገጠውን ፣ ጉባኤው ላይ አፈ ጉባኤ የነበሩ አባቶች በግልጥ ያስተማሩትን ትምህርት ከእነርሱ 20 ዓመት በኋላ ከሮም የተነሣው ልዮ መለወጥ ይችላልን? ጉባኤ ኬልቄዶንስ ያለውን ማጽናት ሲኖርበት እንዴት የቀድሞውን ጉባኤ ውሳኔ ይቀይራል? እንዴትስ ጉባኤ ኤፌሶንን የሚቀበል ሰው ጉባኤ ኬልቄዶንን ሊቀበል ይችላል? እኛ መቼም ኬልቄዶንን ልንቀበል አንችልም ፣ ተዋሕዶንም ኾነ ቅዱስ ቄርሎስን አንክድንም የዲዮስቆሮስ ልጆች ነን ፣ ከአባቶቻችን ከአትናቴዎስ ፣ ከቄርሎስ ፣ ከዲዮስቆሮስ ጋር ኾነን " Mia physis tou Theou Logou sesarkomene -One Nature of God the Word incarnate - ሰው በኾነ የእግዚአብሔር ቃል አንዲት ባሕርይ" እናምናለን።
👍 5 🥰 1
16 March 2024
ኪ
23:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅድስት (ኹለተኛ ሳምንት)

ሕርቃልም አለፎ ጾመ ኢየሱስ መጣ ፣ በቆሮንቶስ ምድረ በዳ 40 ቀን የጾመበት። ክርስቶስስ በባሕርይ ቅዱስ ነውና መጾም አያስፈልገውም ነበር ፤ ነገር ግን እርሱ ከልዕልና ወደ ትሕትና የወረደው እኛን ወደ ልዕልና ሊያወጣን ነውና በባሕርይው ቅዱስ የኾነ እግዚአብሔር ወልድ ይቀድሰን ዘንድ ጾምን ጾመልን ስለእኛ ተራበ በሰይጣንምተፈተነ ።

ቅድስና የባሕርይው የእግዚአብሔር ነው ፣ ከእግዚአብሔር ውጪ ቅዱስ የለም ፤ ቅድስናውን በጸጋ ያድለን ዘንድ ፍጥረትን በተቀደሰች ዕለት በዕለተ እሑድ ፈጠረ ጸጋውንም በሰው ላይ አሳየ። ሰው ግን ከእግዚአብሔር ቅድስና ይልቅ የራሱን መንገድ በመምረጡ ከቅድስና መንገድ በወደቀ ጊዜ ዓለምን ኹሉ በፍጹም ፍቅር የሚወደው ቅዱስ አምላክ ሰውን ዳግመኛ ወደ ቅድስና ይመልሰው ዘንድ በዕለተ እሑድ ተጸነሶ ወደ ዓለም ገባ ፣ ሰው በመኾኑም የቅድስናን ሕይወት እንዴት ይኖር ዘንድ አሳየው ከአባቱ ከእግዚአብሔር ለአንዲት ቅጽበት እንኳን አልተለየምና ለሰው ኹሉ ምሳሌ ኾነ። በመጨረሻው ትንሣኤያችንን ያረጋግጥልን ዘንድ በዕለተ እሑድ ትንሣኤውን በማድረግ ቅዱስ እግዚአብሔር የቅድስናውን ሙላት በእኛ ላይ አፈሰሰ።

እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ፣ የፍቅሩን ፍጻሜ ያሳየባት የጌታ ቀን ዕለተ እሑድ ቅድስት ናት ፣ የእግዚአብሔርን መንገድ የሚከተሉ ወዳጆቹ ኹሉ ቅዱሳን ናቸው። እኛም በእግዚአብሔር ቅድስና እንቀደስ ዘንድ በቅድስት የጌታ ቀን ወደ እርሱ እንሰብሰብ ከቅዱስ ሥጋውም እንቀበል ፣ በቅድሳኤውም ተገኝተን በኪሩቤል ዝማሬ ከመላእክቱ ጋር በኅብረት አምላክን በፍጹም ተመስጦ እንዲህ እያልን እናመሰግነው፡

Ἅγιος, ἅγιος, ἅγιος Κύριος Σαβαώθ πλήρης ὁ οὐρανὸς καὶ ἡ γῆ τῆς δόξης σου
Hagios, hagios, hagios Kyrios Sabaoth pleres ho ouranos kai he ge tes doxes sou
HOLY, HOLY, HOLY LORD SABAOTH, HEAVEN AND EARTH ARE FULL OF YOUR GLORY
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባኦት ፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።

የተቀደሰ የጌታ ቀን ፣ የተቀደሰ ሳምንት ይኹንላችሁ ❤️
❤ 7 🥰 1
20 March 2024
ኪ
14:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዶግማ የኾኑትን አስተምህሮዎች ስለመለየት

አንዳንድ ጊዜ ኦርቶዶክሳዊያን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን አስተምህሮዎች በሙሉ መቀበል አለባችሁ እያልን ሰውን የማሸሽ ጉዳይ አያለው ነገር ግን አንድ ማወቅ ያልብን ነገር የቤተክርስቲያን አባቶች ብለን የምንቀበላቸው የአስተምህሮ አንድነት ያላቸው በዶግማ ላይ እንጂ በሌሎች አስትምህሮዎች ላይ የተለያዩ እየታዎችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነርሱ እይታዎች የተለያዩ መኾናቸው ኦርቶዶክሳዊነታቸውን አልገደበውም በዶግማ አንድ ናቸውና።

ዶግማ የምንላቸው አስተምህሮዎች ከነገር ድኅነት ጋር የሚገናኙ አስተምህሮዎች ናቸው አንድ ሰው የመዳን እውቀት የሚያገኝባቸው አስተምህሮዎች ማለት ነው። በዚህም ምክንያት ከነገር ድኅነት ጋር ቀጥታ በመገናኘታቸው መሠረታዊ ዶግማዎች የምንላቸው አምስቱ አእማደ ምሥጢራትን ነው (ምሥጢረ ሥላሴ ፣ ሥጋዌ ፣ ጥምቀት ፣ ቁርባን ፣ ትንሣኤ ሙታን)። እንዲሁም በእነዚህ አምሥቱ አእማደ ምሥጢራት መሠረትነት የታነጹ አስተምህሮዎች፡ ነገረ ቤተክርስቲያን (Ecclesiology) ፣ ነገረ ድኅነት(Soteriology) ፣ ነገረ ክርስቶስ (Christology) እና ነገረ ቅዱሳን (Communion of the saints) እንዲሁም ሌሎች ከነገረ ድኅነት ጋር በተዘዋዋሪ ግኑኝነት ያላቸው አስተምህሮቻችን የማይለወጡ ዶግማዎች ናቸው።

ከዚ ውጪ ግን ዶግማዎች ያልኾኑ አስተምህሮዎች አሉን ከፍቅር የተነሣ እና ቤተክርስቲያን ስለምታስተምረን የምናምናቸው ለምሳሌ፡ የእመቤታችን እርገት (ሥጋዋ በምድር በስብሶ እንዳልቀረ በኹሉም ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የታመነ ነው ነገር ግን በእኛ ቤተክርስቲያን ሥጋዋ ከነፍሷ ተዋሕዶ ተነሥታ አርጋለች እንላለን፣ ሥጋዋ ከነፍሷ ሳይዋሐድ ወደ ገነት ተወሰደ በመጨረሻው ትንሣኤ ከእኛ ጋ ይነሣል ብለውም የሚያምኑ አሉ) ፣ እመቤታችን ያለ መርገም ተጸንሳለች (ልዩነት ያለው የነጻችበት ሰአት ላይ ነው በእኛ ቤተክርቲያን በጽንሰቷ ጊዜ ነው የነጻችው እንላለን ፣ በገብርኤል ብሥራት ጊዜ ነው የነጻቸው የሚሉም አሉ) ፣ ዓለም ከተፈጠረ 7500 ዓመት ነው (ፀሐይ የተፈጠረችው በ4ኛው ቀን ስለኾነ ከዛ በፊት የነበረው ጊዜ ረጅም ሊኾን ይችላል ብለው የሚያምኑ አባቶች አሉ)፣ ሰው ነፍስ እና ሥጋ ብቻ ነው (መንፈስ የተባለው እራሱ ነፍስ ነው እንጂ በሰው ውስጥ የነፍስ የሥጋ የመንፈስ trichotomy የለም ብላ ቤተክርስቲያናችን ታምናለች ሰው trichotomy ነው ብለው የሚያስተምሩ አባቶችም አሉ እኔም ወደ trichotomy አስትመህሮ አደላለው) ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር (ቅዱስ አትናቴዎስ 65 መጻሕፍትን ብቻ ይቀበል ነበር ሌሎች ደግሞ 70 ቤት የሚያድርጉ አሉ ፣ የእኛ ቤተክርስቲያን ከኹሉም ተለይታ 81 መጻሕፍት አሏት)፣ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች ፣ እንዲሁም specific የቅዱሳን ተአምራት እና ገድላት።

እነዚህን በጥቂቱ አነሳዋቸው እንጂ ሌሎችም ይኖራሉ እነዚህን ማመን ቀጥታ ከነገረ ድኅነት ጋር አይገናኝም ግን ቤተክርስቲያናችን ስለምታስተምር ግን እንቀበላለን ከዚ ውጪ ግን ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የተለየ ሊያስተምሩ ይችላሉ እንዲሁም የጥንት ቤተክርቲያን አባቶችም የተለየ ሊያስተምሩ ይችላሉ ነገር ግን ከኦርቶዶክሳዊነት አይቀንስም ወይም እኛ የተለየ ስለምናምን ኦርቶዶክሳዊነት ላይ አንጨምርም ይሄ Diversity of Local Apostolic Tradition ይባላል።
❤ 8 👍 3 🥰 1
23 March 2024
ኪ
23:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ምኩራብ (ሦስተኛ ሳምንት)

አይሁዳውያን አንድ ቤተ መቅደስ ቢኖራቸውም ፣ በሰንበት ቀን ተሰብስበው የሚጸልዩበት እና ከፈሪሳውያን ስር ቁጭ ብለው በተማሩ ረቢዎች የሚማሩበትብዙ ምኩራቦች ነበሯቸው። እነዚህ ረቢዎች ፈሪሳውያን እንደ መኾናቸው ብዙ ሕጎችን ተምረዋል ነገር ግን ውጫዊ ንጽሕና ላይ ብቻ በማተኮር ምስጣዊውን ንጽሕና ችላ ይሉ ነበር እራሳቸው ለሰው ጻድቃን ኾነው ቢታዩም በውስጣቸው ግን በሙስና የጨቀዩ ምኩራቡን የንግድ ቦታ ያደረጉ ሰዎች ናቸው።

ከእነዚህ ፈሪሳውያን ረቢዎች የተለየ አንድ ረቢ ግን ተነሣ ፤ በሥልጣን ያስተማረው ረቢ ኢየሱስ ክርስቶስ! ይህ ረቢ ከፈሪሳውያን ሥር ቁጭ ብሎ አልተማረም ፤ የማስተማርም ሥልጣን የሰጠው ረቢ የለም ነገር ግን ሥልጣኑ ሰማያዊ ነው። በሰው ፊት ጻድቅ ኾኖ መታየትን አይወድም ነገር ግን የልብ ንጽሕናን ወደደ በዚህም ምክንያት ዙሪያውን የከበቡት ባለሥልጣናት ሳይኾኑ ኃጢአተኞች ፣ ቀራጮች ፣ ዘማዎች ናቸው። የፈሪሳውያን ውጫዊ የንጽሕና ሕግ ፣ በራሳቸው የጨመሩትን አፋዊ የሽማግሌዎች ሥርዓት ጣሰ፤ በሰንበት ፈወሰ። ሲያስተምርም በሥልጣን "እኔ ግን እላችኋለሁ" እያለ እንጂ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አይልም ፤ ሥልጣኑ በንግግሩ ይታያል ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር አባቴ ነው ይላል ፣ ይህ የአባቴ ቤት ነው ያለውን ቤቱንም ከነጋዴዎች ያነጻል።

ፈሪሳውያን ገረማቸው ይሄ የሚያውቁት የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ አይደለም ፤ በፊታቸው የቆመው በምኩራባቸው በሥልጣን የሚያስተምር በንግግሩ ብዙዎችን የገዛ ታላቅ ረቢ እንጂ። ይህ አናጢ የአናጢ ልጅ ይህን ኹሉ እንዲያደርግ ሥልጣን የሰጠው ማነው? ሰንበትን የሚሽር ይህ ማነው? ምኩራቡን ከነጋዴዎች የሚያጸዳ ይህ ማነው ? እያሉ ተደነቁ እነርሱ አላወቁትም እንጂ ኃጢአተኞች ፣ ቀራጮች እና ዘማዎች የተጠቀሙበት ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው! የሰንበት ጌታዋ እርሱ ነው ፤ በነቢያት የተናገረ የረቢዎች ሥልጣን ሰጪ ከረቢዎች ኹሉ በላጭ ረቢ ሰያሜሆሙ ለካህናት የተባለ የሕይወታችን መምህር ረቢ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

"ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው) ፤ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።" ቅዱስ ያሬድ

በሕይወታችን መምህር የዓለም ኹሉ ረቢ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የተባረከ የጌታ ቀን ይኹንልን ❤️
❤ 7 👍 3 🥰 1 🙏 1
31 March 2024
ኪ
14:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
መጻጉዕ (አራተኛ ሳምንት)

የቤተሳይዳው በሽተኛ 38 ዓመታትን ሰው በማጣት ውኃው አጠገብ ቁጭ ያለውን በሽተኛ ፣ ሰው ኹሉ የረሳውን በሽተኛ ጌታ ግን አስታወሰው "ልትድን ትወዳለህን" እያለ ብሶቱን የሚቀሰቅስ ንግግር እየተናገረ ሰማያዊው ሐኪም መጣ ፤ ይህ መጻጉም የ38 ዓመት ብሶት አለበትና "ሰው የለኝም" አለ ፤ በሃገራችን ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው የሚባል አባባል አለ ለዚህ መጻጉዕ ግን መድኃኒቱ ከሰው ዘንድ አልተገኘለትም ይልቅስ ሰው ኹሉ የረሳውን ሰው እግዚአብሔር ሰው ኾኖ መጥቶ ሰው ባጣ ጊዜ ሰው ኾነለት! ከሰውም ውኃ ውስጥ ጨምሮ የሚፈውስ ሳይኾን "አልጋህን ተሸክመህ ሂድ" በሚለው ቃሉ ብቻ የሚፈውስ ሰው ኾነለት።

ጌታ ሆይ መጽጉዕ እኔ ነኝ ፤ በሽተኛው እኔ ነኝ በቤተሳይዳ ሳይኾን በበደለ ተኛቻለው በኃጢአት አልጋዬ ተኝቻለው ፤ በበደሌ ታስሬ ተተብትቤያለው ጌታዬ ሰው የለኝም! አምላኬ ከኃጢአት የሚፈታኝ ሰው የለኝም አንተ ብቻ አዳኝ መድኃኒት ነህና ከአንተ ውጪ ሰው የለኝም ። የነፍሴ ሐኪም ኢየሱስ ሆይ ሰውነቴ በኃጢአት ፍላጎት ታስራለች የሰንበት ጌታዋ ሆይ ና ፍታኝ ከአንተ በስተቀር ሰው ማን አለኝ? ከአብ ዘንድ ተልከህ የመጣኸው ኃጢአተኞችን ከእስራታቸው ልትፈታ ነውና ጌታ ሆይ መጻጉዕ እኔ ነኝ እኔን ፍታኝ።

"አምላኩሰ ለአዳም ለዕረፍት ሰንበተ ሠርዐ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ ወይቤሎሙ ኢየሱስ አነኒ እገብር አንትሙኒ እመኑ ለግብርየ ወይቤሎሙ አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልድ ዋሕድ ወይቤሎሙ ብውሕ ሊተ እኅድግ ኃጢአተ በዲበ ምድር እስብክ ግእዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ።

የአዳም ፈጣሪ ለዕረፍት ሰንበትን ሠራ አይሁድ ይህንን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ ብለው ጠየቁት ኢየሱስም እኔ እሠራለሁ እናንተም ሥራዬን እመኑ የሰንበት ጌታ እኔ ነኝ አላቸው የሰንበት ጌታዋ ወልድ ዋህድ ነው አላቸው በምድር ላይ ኃጢአትን እተው/ይቅር እል ዘንድ ሥልጣን አለኝ ነጻነትን እሰብክ ዘንድ የዕውራንን ዓይን አበራ ዘንድ አባቴ ላከኝ አላቸው።" ቅዱስ ያሬድ

አጠገባችን ላሉት ወንድሞች እህቶች የምናደርገው ኹሉ ለጌታ እንደምናደርግ ነውና ሰው ላጡት ወገኖቻችን ሰው እንኹንላቸው መልካም የጌታ ቀን ይኹንልን።
❤ 6 👍 2 🥰 1
5 April 2024
ኪ
09:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
የፋሲካው በግ

እሥራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበትን ቀን "የማለፍ ቀን" (ፋሲካ_passover) እያሉ ያከብሩ ዘንድ ታዘዋል ይኸውም በዓመቱ በመጀመሪያው ወር ፣ በወሩ በ15 ኛው ቀን ሲኾን በአይሁድ ካላንደር Nisan 15 ይኾናል። በአይሁድአቆጣጠር ቀን ሚለወጠው ፀሐይ ስጠልቅ ስለኾነ Nisan 15 የሚገባው ፣ በNisan 14 ከምሽቱ 12 ጀምሮ ነው። ፋሲካው የሚበላው በNisan 15 ቢኾንም በአይሁድ ዘንድ በበዓል ሥራ አይፈቀድምና የፋሲካው በግ መታረድ የሚጀምረው በNisan 14 ከቀኑ 6 ሰአት ጀምሮ ነው ስለዚህም Nisan 14 የዝግጅት ቀን ይባላል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እሥራኤላውያን በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ በመገኘት የፋሲካውን በግ ይዘው በካህናቱ ያሳርዳሉና ቤተ መቅደሱ Nisan 14 ፣ ከ6 ሰአት ጀምሮ በበግ ደም ይሞላል።

Nisan 14ን እና የቤተ መቅደሱን ደም ስናስብ የይስሐቅን መያዝ (The Akedah) ታሪክ እናስባለን። መጽሐፈ ኩፋሌ ምእራፍ 14 እንደሚነግረን ከኾነ እግዚአብሔር አብርሃምን ልጅህን ሰዋልኝ ብሎ የነገረው በዓመቱ በመጀመሪያው ወር ፣ በወሩ በ12ኛው ቀን ነው ይኸውም Nisan 12 ማለት ነው። ከዛ በኋላ አብርሃም ይስሐቅን ወደ መታረጃው ተራራ ሲስወደው 3 ቀን ወስዶበታል ይሄም የይስሐቅን መታረጃ ቀን Nisan 14 ያደርገዋል። ነገር ግን በዛ ተራራ ላይ እግዚአብሔር በዕፀ ሳቤቅ በግ አዘጋጅቶ ነበርና ለይስሐቅ ቤዛ ኾኖት በጉ ታርዶ ይስሐቅ ነጻ ወጥቷል። ይህ ተራራም የሞሪያ ተራራ ሲባል በኋላ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ያሰራበትና የፋሲካው በግ የሚታረድበት እራሱ ይህ ተራራ ነው። በዚህም ምክንያት እሥራኤላውያን የይስሐቅን መያዝ ታሪክ ከፋሲካው በግ ጋር ያያይዙታል በአብርሃም ልጁን ሳይሳሳ እስከ ሞት ድረስ መስጠት እና በይስሐቅ ፍጹም ለአባቱ ታዛዥ ኾኖ ለሞት መቅረብ ምሳሌ ኾኖ የፋሲካው በግ ደም ከኃጢአት ያነጻናል ብለው ያምናሉ።

የፋሲካው በግ ግን የሰውን ልጅ ፍጹም ከዘለዓለም ሞት ማዳን አልቻለም በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የበግ ደም ፈሷል እሥራኤል ግን ከኃጢአቱ አልተመለሰም ፣ የገነት ደጆችም አልተከፈቱም። ነገር ግን በ33 ዓ.ም የፋሲካ ዝግጅት በዓል ቀን ታሪክ ተለወጠ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የፋሲካ በግ ታረደ ፣ ይህን የፋሲካ በግም ቤዛ አድርጎ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር አባቱ በፍጹም ፍቅር ፈቅዷል ፣ የፋሲካው በግም ለአባቱ እስከ ሞት ድረስ በመታዘዝ የይስሐቅን ቤዛ Akedah ፈጽሟል! ይህ የፋሲካው በግ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል የፋሲካው በግ በሚታረድበት ቀን Nisan 14 ከቀኑ 6 ሰአት ላይ እርሱ በመስቀል ላይ ውሏልና ከአሁን በኋላ በየዓመቱ በግ ማረዱ አላስፈለገም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ለዘለዓለም ታርዷልና! ክብርና ምስጋና ለይስሐቅ ቤዛ ለፋሲካችን በግ ክርስቶስ ይኹን!

ክርስቶስ በተሰቀለበት በ33 ዓ.ም Nisan 14 የዋለው በእኛ አቆጠጠር መጋቢት 27 ነው (በጁሊያን ካላንደር April 3 ነው የሚሉም አሉ) እንኳን አደረሳችሁ "ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና"(1ኛ ቆሮ 5፡7)
❤ 5 🥰 1
6 April 2024
ኪ
22:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
ደብረ ዘይት (አምስተኛ ሳምንት)

ክርስቶስ ይመጣል ፣ ጌታ ይመጣል የዓለም መንግስታት ይገለበጣሉ ኃጥአን ዋይ ዋይ ይላሉ ሙታን ይነሳሉ ተራሮች ይወድቃሉ የእግዚአብሔር ልጅ በክብር ይመጣል ጌትነቱን ለዓለም ሁሉ ይገልጣል!

ዋይ ዋይ ያን ጊዜ ማን ፊቱ ይቆማል የሰማይ ሰራዊት ከበውታል ኪሩቤል በፊቱ ይሰግዳሉ ፣ ሱራፌልም ያሸበሽባሉ ኃይላት ፣ አጋእዝት ሥልጣናት ፣ አርባብ ኹሉም መለከታቸውን ይዘው በፊቱ ይቆማሉ ፣ ዋይ ያን ጊዜ የሰው ልጆች ምን ይውጣቸዋል እነሆ ጌታ መጥቷል መጽሐፍ እንደተናገረው ጌታ መጥቷል! በግርማ በክብሩ ይኸው ይታያል። የወጉትም ከሙታን ተነስተዋል የሰቀሉት ኢየሱስ በክብሩ ፊታቸው ቆሟል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈራርሷል ፣ የዓለም መንግስታት ወዳድቀዋል አላመኑበትም እርሱ ግን በግርማው ይታያል። ዋይ ዋይ ያን ጊዜ ኃጥአን ምን ይውጣቸዋል በፊቱ ይንበረከካሉ ማረን ይላሉ ይንቀጠቀጣሉ ያኔ ግን ጊዜው አልፏል አብቅቷል የምሕረት ጊዜ አብቅቷል አሁን የፍርድ ጊዜ ነው ፣ ፈራጁ በክብር ይታያል ፀሐየ ጽድቅ ፀሐይን በእጁ ይዟል እውነተኛው ዳኛ በመስቀል የፈረዱበት ፊት ቆሟል። የምድር ኃያላን ሃገራት ተርበድብደዋል ፈራጁ ፊታቸው ቆሟል ፍርሃት ምድርን ሸፍኗል የእግዚኢብሔር ልጅ መጥቷል በድብቅ ሳይኾን በግልጥ መጥቷል! ክርስቶስ መጥቷል። ብር እና ወርቅ ካሁን በኋላ አይሰራም ንጉሱ ለዘላለም ሊነግስ መጥቷል አቤት የዓለም ኃያላን ሃገራት ሃብታቸውን ምን ያድርጉት ፣ የአረብ ሃገራት ነዳጃቸው ምን ይኹን ኹሉም ሊጠፋ ነው ኢየሱስ መጥቷልና!!

ጻድቃን ግን ይደሰታሉ ማራናታ ጌታ ሆይ ቶሎ ና ያሉት ጌታቸው መጥቷል መጽሐፍ እንደ ተናገረ መጥቷል በኃጥአን ዘንድ ፍርሃት ሲሰማ በቅዱሳን ዘንድ ግን ደስታ ይሰማል "እነሆ ጌታ እነሆ ጌታ" እያሉ ይጮሃሉ ንጉሳቸው መጥቷል የጠበቁት መጥቷል ዮሐንስ ሆይ ደስ ይበልህ ማራናታ ያልክለት ጌታ መጥቷል ፣ ዳዊት ሆይ ደስ ይበልህ ንግስናን ለዘላለም ይነግስ ዘንድ ንጉሱ መጥቷል ለፍርድ መጥቷል በግራ ለቅሶ ይሰማል በቀኝ ግን ደስታ ይሰማል በላይ የመላእክት መለከት ድምጽ ይሰማል አሁን ኹሉም አብቅቷል ተፈጽሟል እነሆ ጌታ መጥቷል ፈጻሚው ጌታ መጥቷል ሁሉም ነገር ተፈጽሟል።

" እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ኹሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ኹሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።"
(የዮሐንስ ራእይ 1:7)

በዛ አስጨናቂ ሰአት በቀኙ ያቆመን ዘንድ በሃይማኖት በምግባር እንጽና ባልጠበቅነው ሰአት ይመጣልና።

Note: Inspiration from Serbian Orthodox chant about the Second Coming of Christ "Pobedna Pesma" (Song of Victory) ለደብረ ዘይት በድጋሚ የተለጠፈ መልካም የጌታ ቀን ይኹንልን የምንጠብቀው መሢሐችን ይመጣልና ማራናታ ጌታ ሆይ ቶሎ ና!
❤ 5 👍 1 🥰 1
7 April 2024
ኪ
16:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነየ አመቱ ለእግዚአ ኩሉ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ (እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ)

ገብርኤል ፊቱ ያበራል የክንፉ ድምጽ አጽናፋት ድረስ ይሰማል በልቡ ደስታን ተሞልቷል ከአርያም ከመኖሪያው ከራማ ወረደ ክንፉን እያማታ ወረደ ፣ ወደ አንዲት 15 ዓመት ድንግል ታናሽ ብላቴና ዘንድ ወረደ ፣ ወደ ተናቀች ከተማ "ከእርሷ መልካም ሰው ይወጣልን" ወደ ተባለችዋ ናዝሬት ወረደ ወደ ገሊላዋ ታናሽ እመቤት ዘንድ የዓለምን የመዳን ዜና ይዞ ወረደ።

ጸጋን የተመላሽ ሆይ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ! ሲል ከዚ በፊት ለሰው ያልተባለ ሰላምታን አቀረበላት ድንግሊቱ ግን ተደነቀች እንዲህ አይነት ሰላምታ ሰምታ አታውቅም "እንደምን ያለ ሰላምታ ነው" ስትል በልቧ አሰበች። ገብርኤል ግን ያሰበችውን ገልጦለታልና ማርያም ሆይ ጸጋን የተመላሽ ስላልኩሽ ደነቀሽን እንግዲያውስ ከዚ በላይ የሚያስደንቅ ነገርን ልንገርሽ ትጸንሻለሽ የእግዚአብሔርንም ልጅ ትወልጂያለሽ ሲል ታላቅ ዜናን አወረደባት። ይህ እንዴት ይኾናል? ድንግሊቱ አልቻለችም ፣ ይህ እንዴት ይኾናል? እኔኮ ወንድ አላውቅም እንዴት ይኾናል? እያለች አመላለሰች። ገብርኤልም መች በቀላሉ ተስፋ ይቆርጣል ማርያም ሆይ ይሄ ይገርምሻልን ኤልሳቤጥስ በእርጅናዋ ጸንሳ የለምን ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር ምን አለ? ሲል መርታት የማትችለውን መከራከርያ አነሳባት ፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር ምን አለ? ድንግሊቱ ተረታች አልቻለችም በዚህ ጊዜ ፈቃድዋን ለጌታዋ አሳልፋ ሰጠች "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ስትል ድኅነት የሚከናወንባት ምርጥ እቃ ትኾን ዘንድ እራስዋን በትሕትና አቀረበች "እንደ ቃልህ ይደረግልኝ" ባለችበትም ቅጽበት አካላዊ ቃል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በማኅጸኗ አደረ የኹላችንም ድኅነት በዚያች ቅጽበት ተጀመረ ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ኾነ።

ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም! እናት እና ገረድ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ እራሽን ባሪያ አድርገሽ በጌታ ፊት ባቀረብሽ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ እናት ኾነሻልና! ስለዚህም እግዚአብሔር አብ ዘመንሽ ዘመኔ ኾነ ይልሻል በባሕርይ የወለደው ልጁ ካንቺ የሰውን ባሕርይ ነስቶአልና። ሔዋን አምላክነትን ሽታ የሰይጣን ባሪያ ኾነች አንቺ ግን ባርያነትን ሽተሽ የአምላክ እናት ኾንሽ ፣ አካላዊ ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ካንቺ ባሕርይ በነሳው ሥጋ ዘመዳችን ኾነ ወንድሞቼ ብሎም ጠራን ስለዚህም ዘመዳችን የኾነው ባንቺ ሥጋ ነውና ትምክህተ ዘመድነ የባሕርያችን መመኪያ እንልሻለን ሌላ ማመስገኛ ቃል ቢያጥረን ከአብሣሪ መልአክሽ ቅዱስ ገብሬል ተውሰን ተፈሥሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ ቡርክት አንቲ እም አምንስት _ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ እያልን ዘወትር እናመሰግንሻለን።

መልካም በዓለ ብሥራት ፣ መልካም በዓለ ጽንሰት ጌታ የሰውን ኹሉ ድኅነት ሊፈጽም ከኹላችን እመቤት እና ንግሥት ከምትኾን ከድንግል ማርያም ፍጹም ሥጋን የነሣው በመጋቢት 29 ነው ፣ ጥንተ ዕለተ ትንሣኤውም ዛሬ ነው ከኹሉም በላይ የተቀደሰ ዕለተ ሰንበት የጌታ ቀን ይኹንላችሁ ❤️
❤ 6 👍 1 🥰 1
14 April 2024
ኪ
18:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
ገብር ኄር (ስድስተኛ ሳምንት)

ለኹላችን መክሊት አለን "ጸጋ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ኹላችን በመንፈስ በመወለዳችን ክርስቲያኖች የኾንን የአንዱን የክርስቶስን ሥጋ እና ደም በመካፈላችን በመንፈስ ቅዱስ የኾነ የእግዚአብሔር ጸጋ በኹላችን አለ ፣ ይህ ጸጋም የመንፈስን ፍሬ እንድናፈራ የተሰጠን ጸጋ ነው " ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም" (ኤፌ 2፡8) እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ የመዳንን ጸጋ ኹላችን ተቀብለናል በዚህ ጸጋም መልካም ሥራን ኹሉ እንሠራለን "እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን" ስለዚህ በዚህ ጸጋ መልካም ፍሬን እያፈራን በመንፈስ ፍሬዎች እያደግን በጸጋው የምንድን መልካም አገልጋዮች እንኾን ዘንድ ይገባናል። (ኤፌ 2፡ 10)

ነገር ግን በጸጋው መልካም ፍሬን ያላፈራ ይልቅስ ጸጋውን በምድር የቀበረ አገልጋይስ? ወደ ጨለማው ይጣላል በዛም ለቅሶ እና ጥርስ ማፋጨት ይኾናል የተሰጠውም ጸጋ ከእርሱ ይነጠቅና በተሰጠው ጸጋ እጥፍ ፍሬ ላፋራው ይሰጣል ላለው ይጨመርለታልና በጸጋ ላይም ጸጋ ይሰጠዋል። ስለዚህ በተሰጠው ጸጋ መልካም ፍሬን የሚያፈራ እጥፍ የሚያተርፍ ፣ ጌታውንም የሚያስደስት መልካም አገልጋይ ማነው? ይህ በጌታ ዘንድ የተወደደ መንግስቱን የሚወርስ አገልጋይ ማነው? በጸጋ ላይ ጸጋ የሚጨመርለት የመንፈስን ፍሬ የሚያፈራ ይህ መልካም አገልጋይ ማነው? ኹላችን ታማኝ አገልጋዮች እንኾን ዘንድ ጸጋችንን የምንቀብር ሳይኾን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እየተባበርን መልካሙን ፍሬ ኹሉ እንድናፈራ እርሱ የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይርዳን " የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ ባንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።"(ሮሜ 8 ፡4)

"መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኲሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባዕ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ

ጌታው በበጎ ሥራ የሚያገኘውና ባለው ገንዘቡ ሁሉ ላይ የሚሾመው ቸርና ታማኝ አገልጋይ ማነው? ዳግመኛ እግዚአብሔር እንዲህ አለው በጥቂቱ የታመንህ አንተ ቸር አገልጋይ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።" ቅዱስ ያሬድ
🥰 1
23 April 2024
ኪ
10:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሰው ልጅ ፈጣሪም ፍጡርም ነው!

እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረው በልጁ ነው "በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ" የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ አረፍተ ነገር ላይ ሰማይ እና ምድር የተፈጠሩበት መጀመሪያ እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው ፤ ከአባቱ ጋር የዘመናት አስጀማሪ ዘመናትን የሚያስረጅ በሉየ መዋዕል (Ancient of days) እርሱ ነውና! ስለዚህ ነው በኒቅያ የተሰበሰቡት 318ቱ አባቶች "የእግዚአብሔር ልጅ ያልነበረበት ዘመን ነበረ" ለሚለው የአርዮስ ኑፋቄ መልስ ሲሰጡ "τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων-ከዘመናት በፊት ከአብ የተወለደ" ያሉት ሲወልደው ዘመን የለውምና ወልድ ያልበነበረበት ዘመን የለም ፤ በዘመናት የማይገደብ ዘላለማዊ የኾነው አምላክ ብቻ በመኾኑ " Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ, γεννηθέντα οὐ ποιηθέντα- ከእውነተኛው አምላክ የኾነ እውነተኛ አምላክ ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ" እንለዋለን ስለዚህም ጌታ በመለኮቱ ከአብ ጋር Homo-ousios -አንድ ባሕርይ ነው። ስለዚህ ጌታ በዚህ መለኮታዊ ባሕርይው ፈጣሪ እንጂ በጭራሽ ፍጡር አይደለም ፍጡር ከፈጠሪው ጋር አንድ ባሕርይ ሊኖረው አይችልምና።

የእግዚአብሔር ልጅ ከዘመናት በፊት በነበረው ልደት ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ እንደኾነ ኹሉ በዘመኑ ፍጽሜ ከሰማያት በመውረድ ከሴት በኾነ ልደቱ ደግሞ ከሰው ልጆች ጋር Homo-ousios-አንድ ባሕርይ ነው (ገላ 4፡4)። ከሰማያት ሲወርድም ከእኛው ወገን ከኾነች ምድራዊት ከምትኾን ከቅድስት ድንግል ሥጋን ነሣ እንጂ ከሰማይ ሥጋን ይዞ አልወረደም "καὶ σαρκωθέντα ἐκ Πνεύματος Ἁγίου καὶ Μαρίας τῆς παρθένου - በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ኾነ" እንጂስለዚህ በዚህ ልደቱም ከኃጢአት በስተቀር የእኛ የኾነውን ኹሉ ተጋራ፤ የእግዚአብሔር ልጅም የሰው ልጅ ኾነ ፤ ከቅድስት ድንግል ሥጋን ፈጥሮ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሕደ ስለዚህም በዚህ ልደቱ ከእኛ ጋር ፍጡር ይባል ዘንድ ተገባው።

እኛም ከአባቶቻችን ተቀብለን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኹለት ልደት አለው እንላለን ፤ የመጀመሪያው ልደት ከዘመናት በፊት ነው ፣ ኹለተኛው ግን በዘመኑ ፍጻሜ ነው ፤ በመጀመሪያው ልደት ከዓለማት በፊት ተወለደ እንጂ አልተፈጠረም ፣ በኹለተኛው ግን ተወልዷልም ተፈጠሯልም ፤ በመጀመሪያው ልደቱ ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ ነው ፣ በኹለተኛው ግን ከእኛ ጋር አንድ ባሕርይ ነው ፤ በመጀመሪያው ልደቱ ፈጣሪ ነው ፤ በኹለተኛው ግን ፍጡር ነው። ስለዚህም የሰው ልጅ ፈጣሪም ፍጡርም ነው እንላለን, ነዋ ሃይማኖተ አበው ርትዕት! የአባቶች የቀናች (Orthodox) ሃይማኖታቸው ይህቺ ናት! አባቶች ካጸኑት ሌላ መሠረት የሚመሰርት የአባቶች ውግዘት ይወድቅበታል።

እኛ ግን አባታችን ቅዱስ ቄርሎስ እንደተናገረው እንዲህ እያልን እናምናለን " የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አማላክ እንዲሁም ሥጋ እና ነፍስ ያለው ፍጹም ሰው ነው። በመለኮቱ ከዘመናት በፊት ከአብ የተወለደ ሲኾን ፤ እራሱ በዘመኑ ፍጽሜ ስለ እኛና ስለመዳናችን በሰውነቱ ከድንግል ማርያም ተወለደ። በመለኮቱ ከአባቱ ጋር አንድ ባሕርይ የኾነ እራሱ ፤ በሰውነቱ ከእና ጋር አንድ ባሕርይ ነው ከኹለት ባሕርይ የኾነ ተዋሕዶ ተካሂዷልና ፤ ስለዚህም አንድ ክርስቶስ ፣ አንድ ወልድ ፣ አንድ ጌታ እንደኾነ እንመሠክራልነ"
❤ 4 🥰 1
27 April 2024
ኪ
09:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
የአልዓዛር ቅዳሜ

ጌታ የሚወደው የቢያታንያው ወዳጅ አልዓዛር ታመመ እኅቶቹ ማርታና ማርያም ወደ ኢየሱስ "የምትወደው ወዳጅህ ታሟል" ብለው ቢልኩበትም ኢየሱስ ግን የመሰቀያው ጊዜ መድረሱን አውቋልና ኾን ብሎ ዘገየ አልዓዛርም ሞተ።
የክርስቶስ መሰቀያ ጊዜ እና የአልዓዛር ሞት ምን አገናኘው? የተገናኘው የካህናት አለቆች ጌታን ይገድሉት ዘንድ የተማከሩት አልዓዛርን በማስነሣቱ ምክንያት ነውና ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ "ሕዝቡ ኹሉ ከሚጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት ይሻለናል" ብሎ የተናገረው አልዓዛርን ካስነሣው በኋላ ሕዝቡ ኹሉ ስለተከተለው ነው። (ዮሐ 11፡50) በነጋታው ሕዝቡ ኹሉ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያለ የተከተለውም ትልቁ ምክንያት አልዓዛርን በምስነሣቱ ነው።

አልዓዛርን ማስነሣት ለምን እንዲህ ትልቅ ነገር ኾነ ጌታ ከእርሱ በፊት እኮ 2 ሰዎችን አስነሥቷል ምነው የአልዓዛር ተጋነነ? ከዚህ በፊት ጌታ ያስነሳቸው ሰዎች በሞቱበት ቀን ነው አይሁድ ደግሞ በአስተምህሮዋቸው አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ትለይና ምናልባት የመመለስ እድል ካገኘው ብላ ከሥጋዋ አከባቢ ለ3 ቀናት ታንዣብባለች ፤ ለ3 ቀን ካልተመለሰች ተስፋ ትቆርጥና ወደ ማደሪያዋ ትገባለች ስለዚህ በ3ኛው ቀን ሰው ላይነሣ ፈጽሞ ሞተ ይባላል።

ጌታም አልዓዛር ሞተ ብለው እኅቶቹ ሲልኩበት የዘገየበት ምክንያት የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ "ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝም ቢሞት እንኳን ይነሣል" በማለቱ የሰው ልጅ ፈጽሞ ከሞተ በኋላ እንኳን የሚያስነሣ እርሱ መኾኑ ለሕዝቡ ኹሉ ይገለጥ ዘንድ ነው። (ዮሐ 11፡25) ስለዚህም ጌታ ወደ ቢታንያ ሲደርስ አልዓዛር ከሞተ 4 ቀን ኾኖት ነበር አይሁድም ፈጽሞ መሞቱን ስላመኑ ከዚህ በኋላ ይነሣል የሚል ተስፋ እንኳን አልነበራቸውም። እንኳን አይሁድ በኢየሱስ ያመኑ እኅቶቹ ማርታ እና ማርያም እንኳን ጌታ መቃብሩን ክፈቱልኝ ባለ ጊዜ "አራት ቀን ኾኖታል ይሸታል" ብለው ታቀወሙ ፤ ትንሣኤ እና ሕይወት ክርስቶስ ግን "አልዓዛር ፣ አልዓዛር ና ውጣ" በሚል ቃል ብቻ ፈጽሞ የሞተውን አልዓዛር ከመቃብር ከነመግነዙ አወጣው ፤ ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ መኾኑ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ሆሳዕና (አዳኝ) እርሱ መኾኑም በዛ ላለ ሕዝብ ኹሉ ተገለጠ።

የአልዓዛር ከሙታን መነሣት በቢታንያ እና በኢየሩሳሌም ምድር ኹሉ ተሰማ ሕዝቡ ኹሉም የተነሣውን አልዓዛርን ያዩ ዘንድ ወደ ቢያንያ ተሰበሰቡ ያስነሣውን ሆሳዕና (አዳኝ) ያዩ ዘንድም ናፈቁ ኢየሱስ ግን ወደ ኤፍራታ ከተማ ትቶአቸው ሄዶ ነበር (ዮሐ 11፡54)። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ አይደለም ለአንድ ቀን ብቻ ነው እንጂ በነጋታው ይመጣል! ሕዝቡ ኹሉም የናፈቁትን ሆሳዕና (አዳኝ) በዘንባባ ይቀበሉታል!
❤ 4 👍 4 🥰 1
28 April 2024
ኪ
00:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
✝️አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት✝️

መኳንንት ሆይ ደጆችን ክፈቱ የክብር ንጉሥ እየመጣ ነውና ደጆችን ክፈቱ! ንጉሥ በሰረገላ እንጂ እንዴት በአህያ ይመጣል ያላችሁ እንደሆነ ይህስ ንጉሥ እንደ ማንኛውም ምድራዊ ንጉሥ አይደለም ፣ የኃጢአትን ቀንበር ከሰዎች ላይ ሊፈታ “ፍትሕዎን ወአምጽእዎን ሊተ “ ብሎ በአህያዋ መፈታት አንጻር ነጻ ሊያወጣን የመጣ ንጉሥ ነው።

መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት

ይህ የክብር ንጉሥ ማነው ያላችሁ እንደኾነማ እነግራችኋለው ይህ ንጉሥ የክብር ንጉሥ ፣ የኃያላን አምላክ እግዚአብሔር ነው። ሥጋ ለብሶ ብታዩት እንደኛ ሰው ብቻ አይምሰላችሁ እርሱስ የአማልክት አምላክ ነው። የእኛን ፈተና ኹሉ ተፈትኖ እኛን ከፈተና ነጻ ያወጣን ዘንድ ሥጋን የተዋሐደ መለኮት ነው ። አዳምን ይክስ ዘንድ ፣ ሔዋንንም ከሞት ፍርድ ነጻ ያወጣ ዘንድ ፣ የእዳ ደብዳቤውን ይደመስስ ዘንድ ፣ ሰውንም ድጋሚ በደሙ ሰርቶ አዲስ ፍጥረት ያደርገው ዘንድ ከሰማየ ሰማያት የወረደው እግዚአ ጸባዖት “ የሠራዊት ጌታ” ነው። የድንግል ልጅ ቢኾንም ዳሩ ግን የአብ ልጅ ነው ፣ መከራን የተቀበለ ቢኾንም ከመከራው ኹሉ በላይ ነው።

ይባዕ ንጉሠ ስብሐት ፣ ይባዕ አምላከ ምሕረት

የክብር ንጉሥ ይግባ ፣ የምሕረትም አምላክ ይግባ ግድ የለም ኢየሩሳሌም ሆይ ንጉሥሽ በአህያ ላይ ተጭኖም ቢሆን ይግባ። ሰው ቢሆንም እርሱ በእግዚአብሔር ስም ሊያድንሽ የመጣ ነውና “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" እያልሽ ተቀበዪው። እርሱስ ስሙ ኢየሱስ "መድኃኒት" ነውና በእውነት ለዚህ ከዳዊት ወገን ከሆነች ድንግል ለተወለደው ለኢየሱስ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ” መባል ይገባዋል። ዳግመኛ ስሙ ከሰማይ የመጣ እግዚአብሔር ነውና "በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" መባል ከእርሱ በላይ የሚገባው የለም ። ጽዮን ሆይ ለንጉሥሽ ልብስሽን አንጥፊለት የዘንባባ ዝንጣፊም ያዢ ፣ ሕፃናቶችሽም ሆሣዕና በአርያም እያሉ ያመስግኑ ወደ ክብር ቤቱም ይግባ ፣ የመክበሪያው ጊዜ ደርሷልና ኃጢአትሽን ሊያስውግድ ሊሰቀል ደርሷልና ኢየሩሳሌም ሆይ መድኃኒትሽ ይግባ በእልልታ ተቀበዪው ፣ እርሱስ ባታመሰግኚው የቢታንያ ድንጋዮች ራሱ ያመሰግኑታልና።

✝️አቤቱ የምሕረት አምላክ ሆይ ግባ ፣ የክብር ንጉሥ ሆይ ግባ!!✝️
🥰 2
29 April 2024
ኪ
05:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም

አማኑኤል አምላኬ ሆይ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አይሁድ ቤተመቅደሱን ባነጻህ ጊዜ በማን ስልጣን በማን ኃይል ነው ይህን ምታደርገው ብለው ጠየቁህ እኔ ግን ኃይል ፣ ክብር፣ እና ምስጋና ጽናትም እስከ ዘለዓለሙ ላንተ ናቸው እያልኩ እሰግድልሃለው። እንደ በለሷ ፍሬ ፈልገህብኝ ከማጣት እና ከመረገም ጠብቀኝ ጌታዬ ሆይ እኔ ባዶ ነኝና ባንተ ግን ኹሉን እችላለሁ ኃይሌ መደገገፊያዬ አንተ ነህና ስለዚህም "በሰማያት ያለህ አባታችን ሆይ" እያልኩ ስምህን እጠራለሁ እኔም ኃይሌ መታመኛዬም ጌታዬ ነው እላለሁ ረዳት ኾነከኛልና በመከራዬ ኹሉም ተሳትፈህ እኔን ከመከራ አውጥተሃልና አማኑኤል አምላኬ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሥልጣን ኹሉ ላንተ ነው ክብር ኹሉ ላንተ ነው አምልኮም ኹሉ ላንተ ነው።

ጌታዬ ሆይ ቤተመቅደሱን ብቻ ሳይኾን ልቤንም አንጻልኝ ፣ እንደ በለሷ ፍሬ የሚያሳጣኝን መንፈስ እርገምልኝ በፍሬ የሚሞላ የምንፈስህንም ጸጋ ላክልኝ ያለ ጸጋህ ባዶ ነኝና። አዳኝ ለኾንከው ላንተ አምላኬ ለሕማምህ ክብር እና ምስጋና ጽናትም ኹሉ ይገባል።
ለከ ይደሉ ኃይል ፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኮቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም።

ነአምን ሕማሞ ለዘኢይሐምም - የማይታመመው መታመሙን እናምናለን!
👍 2 🥰 2
1 May 2024
ኪ
09:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
አኬልዳማ

ሊቃነ ካህናት ጌታ አልዓዛርን ካስነሣበት ቅዳሜ ጀምሮ ክርስቶስን ሊገድሉት ቢፈልጉም ሰሞኑ የፋሲካ በዓል ነበርና ኢየሱስን በሕዝብ መሃል ሊይዙት አልቻሉም ስለዚህ ሕዝብ የማይኖርበት አመቺ ጊዜን ይጠብቁ ነበር። ይህም አመቺ ጊዜ ባልጠበቁት ሰው በኩል መጣላቸው በደቀመዝሙሩ ይሁዳ።

ይሁዳ በዛሬዋ ረቡዕ ቀን ሕዝብ በማይኖርበት አመቺ ጊዜ ጌታን አሳልፎ ሊሰጣቸው ከሊቃነ ካህናት ጋር ተስማማ ለዋጋውም ሠላሳ ብርን መደቡለት። ዓለማትን ኹሉ ብርና ወርቁን ሳይቀር የፈጠረ ጌታ ዋጋው ሠላሳ ብር ኾነ ጌታስ ምን ያህል ስለእኛ ተዋረደ! ይሁዳ ግን ይህ አልጠቀመውም የዓለሙን ውድ ጌታ በሠላሳ ብር ሸጦ ህሊናው አላረፈምና ብሩን በተነ በብሩም መሬት ተገዛ ፤ አኬልዳማ-የደም መሬት!

ጌታ ሆይ አኬልዳማስ በሠላሳ ብሩ የተገዛው መሬት ብቻ አይደለም እኛም አኬልዳማ የደም መሬቶች ነን፤ ከመሬት ከተገኘ አዳም መሬቶች ስንኾን በአንተ ደግሞ በደም ተገዝተናልና ጌታ ሆይ አኬልዳማ ነን! መክፈል በማንቸል በውድ ዋጋ ተገዝተናል በአምላካዊ ደም! ከአሁን ወዲህ ሕይወታችን የእኛ አይደለም ጌታ ሆይ ሕይወታችን አንተ ነህ በምድራዊ ሳይኾን በመለኮት ደም ተገዝተናልና ጌታ ሆይ አኬልዳማ እኛ ነን።

"በሠላሳ ብር በርካሽ ዋጋ የተሸጠው እርሱ ዓለምን በውድ ዋጋ ገዛ፤ ይኸውም ክቡር ደሙ ነው።"
(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ)
❤ 7 🥰 2 👍 1
5 May 2024
ኪ
09:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል የሞት ኃይሉም ተነጥቋል አዳኙን ይይዝ ዘንድ አልቻለምና፤ በግርማው ተንሥቷል ሲዖልም ባዶውን ቀርቷል ክርስቶስ ተነሥቷልና፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞትን ማን ይፈራል በክርስቶስ ተሸንፎ ደካማ ኾኗል፤ በክርስቶስ የኾነ ኹሉ ያሸንፈዋል ክርስቶስ ተነሥቷልና! ሞት ሆይ አዳኙን ለመያዝ ስትሞክር ምን ተሰምቶህ ይኾን? ሲዖል ሆይ ፈታኙ ኹለመናህን ሲፈትንህ ምን ተሰማህ? ምርኮህን ማረከ ነፍሳትን ኹሉ በደሙ ገዛ፤ እይዘዋለው እውጠዋለው ያልከው በመስቀል የተሰቀለው ደካማ ሰው ለካስ መለኮት ነው!፤ የሰው ልጅ ነው ያልከው ለካስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው!፤ ክርስቶስ በድካሙ ከኃይል የሚበልጥ ኃይል ገለጠ፤ የሞት ኃይል በክርስቶስ ድካም ተሸነፈ፤ ክርስቶስም በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ ለሰው ልጅ በሙሉም ትንሣኤን አወጀ፤ ስለዚህም በክርስቶስ የሞቱት ኹሉ ድል ከነሣው ከተነሣው አዳኛቸው ጋይ ይነሣሉ!

"ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ? ክርስቶስ ተነሥቶአል አንተም ተገልብጠሃል። ክርስቶስ ተነሥቷል፣ አጋንንትም ወድቀዋል። ክርስቶስ ተነሥቷል መላእክትም ደስ ብሏቸዋል። ክርስቶስ ተነሥቷል ሕይወትም ነግሧል። ክርስቶስ ተነሥቷል ከሙታን አንድም በመቃብር አልቀረም። ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ላንቀላፉት ኹሉ በኩራት ኾኖአልና።"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

Christos Anesti (Χριστός Ανέστη), Alithos Anesti (Aληθώς ανέστη!)- ክርስቶስ ተነሥቷል በእውነት ተነሥቷል!
❤ 2 👍 1 🥰 1
14 May 2024
ኪ
13:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
የ "iota ልዩነት"

Homoousios እና Homo"i"ousios የግሪክ ቃላት ሲኾኑ ልዩነታቸው "i" ወይም የግሪኩ ፊደል iota ልዩነት ነው። ይህቺ አንድ ፊደል ግን ታላቅ የነገረ መለኮት ልዩነትን አምጥታለች።

Homoousios ማለት "አንድ ባሕርይ" ማለት ሲኾን የኒቅያ አባቶች ክርስቶስን ከአባቱ ጋር አንድ ባሕርይ ነው ለማለት ተጠቅመውበታል። Homo"i"ousios ማለት ደግሞ "ተመሳሳይ ባሕርይ ፣ የሚስተካከል ባሕርይ" ማለት ሲኾን አርዮሳውያን ክርስቶስ ከአባቱ ጋር አንድ ባሕርይ ሳይኾን አብ ፈጥሮት በጸጋ ከራሱ ጋር ያስተካከለው የጸጋ አማላክ ነው ለማለት ተጠቅመውበታል።

አሁን ላይ ግን እኛ የኒቅያ አባቶች ውሳኔን በጸሎተ ሃይማኖታችን ላይ በአማርኛ ስንጸልይ "ከአብ ጋር በመለኮቱ አንድ የኾነ" ማለት ሲገባን "ከአብ ጋር በመለኮቱ የሚስተካከል" በማለት የአርዮሳውያኑን Homo"i"ousios ስህተት እየሰራን ነው። ይህ ስህተት የተከሰተው ግእዙ "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ" የሚለው ላይ ዕሩይ የሚለው ቃል የግስ ትርጉሙ "የተሰተካከለ" ማለት ስለኾነ ነው ፣ ነገር ግን ሃይማኖተ አበውን የተረጎሙ ሊቃውንት አባቶች ዕሩይ የሚለውን ቃል እዚህ ጋር እንደ ግሱ ሳይኾን እንደ አገባቡ ነው መተርጎም ያለበት ብለው "በመለኮቱ ከአባቱ ጋር አንድ የኾነ" ብለው አቃንተው ይተረጉሙታል።

ስለዚህ እኛም ጸሎተ ሃይማኖትን ስንጸልይ " Homoousion to patri- በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሚኾን" በማለት አቃንተን ልንጸልየው ይገባል የ"iota" ልዩነት ክርስቶስን ከባሕርይ አምላክነት አውጥታ የጽጋ አምላክ ታደርገዋልችና።
👍 5 🙏 4 🥰 1
15 May 2024
ኪ
09:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
Athanasius Contra Mundum (Athanasius against the world)

ዓለም በአርዮሳዊ ክህደት ስትዋጥ ብቻውን ኦርቶዶክሳዊነትን የጠበቀ የቤተክርስቲያን ምሶሶ። ኦርቶዶክሳዊነት በኒቅያ ጉባኤ የበላይነት ቢያገኝም ዓለም ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ይልቅ አርዮሳዊነትን መረጠ ከንጉሠ ነገሥቱ ፣ እስከ ጳጳሳት ፣ እስከ ካህናት እና ኃያላን ድረስ ፣ ኹሉም ማለት ይቻላል በአርዮስ ምንፍቅና ቫይረስ ሲጠቁ አንድ ሰው ግን ዓለምን ሞግቶ ተገኘ ቅዱስ አትናቴዎስ! አትናቴዎስ ዓለምን ተቃርኖ ለእውነት ቆመ ፣ በዚህም ምክንያት በ4 የሮማ ነገሥታት ተጠልቶ 5 ጊዜ ከመንበሩ ተሳደደ። እርሱ ግን በዚህ ኹሉ ውስጥ ተስፋ ሳይቆርጥ ለእውነት ቆመ። የአርዮሳውያን መዶሻ ገና በ 19 ዓመቱ " On the incarnation" የተባለውን ዘመን ተሻጋሪ መጽሐፍ የደረሰ ፣ የክርስቶስን ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ መኾን እስከ መጨረሻ የሕይወት እስትንፋሱ የጠበቀ፣ ሕይወቱን በሙሉ ለክርስቶስ የሰጠ ታላቁ አባት ቅዱስ አትናቴዎስ ዛሬ እረፍቱ ነው።

ምናልባት ያለ ቅዱስ አትናቴዎስ ክርስትናን ዛሬ በምናውቀው መንገድ ላናውቀው እንችል ይኾናል ፣ አርዮሳውያን ያሸንፉ ነበር ነገር ግን ክርስቶስ "የገሃነም ደጆች አይችሏትም" ያለውን ቤተክርስቲያኑን አይተውና ለቤተክርስቲያን ቅዱስ አትናቴዎስን አስነሣላት ፣ እርሱም ዓለምን ተቃውሞ እውነትን ጠበቀ ፣ ቤተክርስቲያንም በታመነ ዓለት ላይ ጸናች እርሱም ቅዱስ አትናቴዎስ የታገለለት እውነት "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ፣ እግዚአብሔር ነው ፣ ከአባቱ ጋርም አንድ ባሕርይ ነው" የሚለው የማይነቃነቅ ፣ የማንለውጠው ሃይማኖታችን ነው።

“If the world is against the truth, then I am against the world.”
― Athanasius of Alexandria

St. Athanasius the Apostolic my patron saint ❤️
❤ 8 🙏 2 👍 1 🥰 1
09:21
Lord Jesus Christ, Son of God by intercession of St. Athanasius the Apostolic have mercy on us sinners 🙏
❤ 6
16 May 2024
ኪ
21:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል

መለኮት ማለት የአብ ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድ ባሕርይ ነው። መከፈል የለበትም ይልቅስ በሦስቱም አካል ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ እንጂ። አብ የመለኮት 1/3ኛ ፣ ወልድ የመለኮት 1/3ኛ ፣ መንፈስ ቅዱስ የመለኮት 1/3ኛ ኾነው አንድ ላይ አንድ መለኮት የሚኾኑ አይደለም ይልቅስ አብ ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ፣ ወልድም ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ ፣ መንፈስ ቅዱስ ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ ስለዚህም እያንዳንዱ አካል ለየብቻቸው መለኮት ፣ መለኮት፣ መለኮት ተብለው መጠራት ይችላሉ። ነገር ግን ሦስት መለኮት ሳይኾን አንድ መለኮት ነው ያለው መለኮት በአካላት ሦስትነት አይከፈልምና ይልቁንም ይገናዘባል እንጂ። አብ ቃሉን ወልድ ፣ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስ አድርጎ መለኮት ይባላል ፣ ወልድም መሠረቱን አብ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስ አድርጎ መለኮት ይባላል ፣ መንፈስ ቅዱስም መሠረቱን አብ ቃሉን ወልድ አድርጎ መለኮት ይባላል ስለዚህ በመለኮት ዘንድ ተገናዝቦ እንጂ ተከፍሎ ስለሌለ ሦስት አንለውም፤ በሦስት አካላት ሕልው የኾነ አንድ ነው እንጂ።

አካሉ ውስጥ የመለኮት ሙላት ያለው ወልድ ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ሰው ኾነ ፣ ተለይቶ ሰው ኾነ ስንል ግን የተለየው ተገናዝቦውን አይደለም ወልድ ያለ መሠረቱ አብ እና ያለ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ የኖረበት ጊዜ የለምና። ይልቅስ ተለይቶ ስንል በአካል እና በቃልነት ከዊኑ ነው። ተለየ ስንልም በቦታ አይደለም የመለኮት አካል በኹሉ የመላ ነውና ይልቅስ የተለየው ሥጋን በመዋሐድ ነው፤ አካሉን ከማርያም ከተነሣው ሥጋ ጋር አንድ ያደረገው ወልድ እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይደሉም እንዲሁም የቃልነት ከዊኑን ከሥጋ ባሕርይ ጋር አንድ አድርጎ፤ ሥጋ ዓለም የተፈጠረበት የእግዚአብሔር ቃል ያደረገው ወልድ እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይደሉም። ስለዚህም ከአባቱና ከሕይወቱ የማይለየው ወልድ በተዋሕዶ ግን ተለየ ፣ ብቻውን ሥጋን በላ። "ምነው አብና መንፈስ ቅዱስ ቀሩ ሥጋ አያምራቸውምን? ልጅ ለሥጋ ስሱ ስለኾነ ተቅለብልቦ መጣ እንጂ ኹለቱስ እሳት ናቸው ጥበባቸውም አይታወቅ። ይልቁንስ ልጅየው ዘመዳችን ነው ኹሉንም አጫውቶናል 😁" (መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)።

ይህ ልጅ ሥጋን በመብላቱ ዘመዳችን ኾነ እንደእኛ ሥጋ ኾኗልና "በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ-ሥጋን በመልበስ ዘመድ ኾነን" ብለን እንድንዘምር አድርጎናል። አባቱ እና መንፈሱ በመቅረታቸው አንቆጭም ፤ አባቱን በእቅፉ ያለ አንድያ ልጁ ተርኮታልና መንፈሱንም በአምሳለ እሳት በበዓለ ጰንጠቆስጤ ሰዶልናል በዚህም ፍጹም ዝምድናውን አሳየ። ነገር ግን ይህ ልጅ ከአባቱና ከመንፈሱ ተለይቶ ብቻውን ሥጋ በልቷልና ብቻውን ይሞት ዘንድ ተገባው ፣ በመለኮት ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ቢኾንም ሥጋን የተዋሕደ መለኮት እርሱ ብቻ ነውና ሞት ለእርሱ ብቻ ተገባው ስለዚህም እኛ "ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ-በሥጋ ሞትን የቀመሰ" አልነው እርሱ መለኮት በሥጋ ሞቷልና። መለኮትስ ሞተ አይባልም አብና መንፈስ ቅዱስ ሥጋ አልበሉምና ነገር ግን ሥጋን የበላው መለኮት ወልድ ሞቷልና መለኮት በሥጋ ሞተ ይባላል "ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት ታረቀን" እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ። (ሮሜ 5፡10)

"ሐሜተ ክልዔቱ አኃው ዘኢፈርሀ ወልድ በልዐ በተከብቶ
ሥጋ ጥዑመ እንዘ የዐጹ ኆኅቶ
ወፍሉጠ ሞት ኮነ ባሕቲቶ ዘበልዐ እስመ ይመውት ባሕቲቶ

የኹለቱን ወንድሞች ሐሜት ያልፈራ ወልድ
ጥዑም ሥጋን በሩን ዘግቶ በሥውር በላ
ስለዚህም ብቻውን ሞተ ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታልና" መጽሐፈ ቅኔ (ዝክረ ሊቃውንት)

ምእመናን ሰው እያለማስ ብቻችሁን እንዳትበሉ ብቻን መሞት አለና 😁
❤ 7 👍 3 🥰 1
28 May 2024
ኪ
11:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
When you live in Rome live like Romans

ኹላችንም ይህቺን አባባል እናውቃታለን ይህ አባባል ግን የተወሰደው ከቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ አምብሮስ ዘሚላን እንደኾነ ያውቃሉ? ታሪኩ እንዲህ ነው፡

ሊቁ አውግስጢኖስ ዘሂፖ ገና በወጣትነቱ ሳለ እናቱ እርሱን ተከትላ ከሰሜን አፍሪካዋ ከተማ ሂፖ ወደ ጣሊያኗ ሚላን ትመጣለች። በዛን ጊዜ ሂፖ የምትተዳደረው በሮም መንበር ስር ነው ፣ ሚላን ደግሞ በራሷ መንበር ትተዳደራለች። እንደ ሮም ቤተክርስቲያን ልማድ ደግሞ ቅዳሜን በጾም ነው የሚያሳልፉት በሚላን ቤተክርስቲያን ግን ቅዳሜን መጾም አይቻልም። ስለዚህ ቅዳሜ ፣ ቅዳሜን በሂፖ መጾም የለመደችው የአውግስጢኖስ እናት ሚላን ስትመጣ መጾም አይቻልም ስትባል የለመደችውን መተው ከበዳትና ተጨነቀች። በዚህ ጊዜ የእናቱን ጭንቀት የተረዳው ወጣቱ አውግስጢኖስ በወቅቱ የሚላን ሊቀ ጳጳስ የነበረውን ቅዱስ አምብሮስን ያማክረዋል። ቅዱስ አምብሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት "When I visit Rome, I fast on Saturday; when I am here, I do not fast" ይሄም አባባል በጊዜ ሂደት ተለውጦ "When you live in Rome live like Romans" ኾነ።

አውግስጢኖስ እንግዲህ በወጣትነቱ የተማረው "Diversity of local tradition"ን ነው። ክርስቶስ አንድ እንደኾነ ቤተርክስቲያንም እንዲሁ በክርስቶስ አንድ ናት። አንድ ናት ስንል ግን በሃይማኖት (በዶግማ) እንጂ በሥርዓት እና ቀኖና ላይኾን ይችላል አንድ ቦታ የሚሰራ ቀኖና ሌላው ጋር ላይሰራ ይችላልና ይሄ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የሚታወቅ ነው። አውግስጢኖስ ከዚህ በኋላ እንዳስተዋለው አብያተ ክርስቲያናት ሌሎች ብዙ የሥርዓት ልዩነቶች እንዳሏቸው ነው። ለጀኗሪየስ በላከው መልእክቱ ላይ እንዲህ ሲል ያየውን ይገልጻል "ይሁን እንጂ በተለያዩ ቦታዎችና አገሮች የሚለያዩ ሌሎች ነገሮች አሉ፡- ለምሳሌ አንዳንዶች ቅዳሜን ይጾማሉ፣ ሌሎች ግን አያደርጉም። አንዳንዶች የክርስቶስን ሥጋና ደም በየቀኑ ይካፈላሉ፥ ሌሎችም በተወሰኑ ቀኖች ይቀበላሉ፤ በአንዳንድ ስፍራ ያለ መሥዋዕት አንድ ቀን አያልፍም። በሌሎች ደግሞ ቅዳሜ እና እሑድ ብቻ ቁርባን ያደርጋሉ, ወይም አንዳንዱ እሑድ ቀን ብቻ ቁርባን ያደርጋሉ።... ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ለጥበበኛ እና ለቁም ነገር ያለው ክርስቲያን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ሕግ ከመከተል የተሻለ አማራጭ የለም። ለእንዲህ ዓይነቱ ልማድ፣ በግልጽ ከእምነት ወይም ከሥነ ምግባር ጋር ስለማይቃረን፣ እንደ ግድየለሽነት ተቆጥሮ ከምንኖርባቸው ሰዎች ጋር ኅብረት እንዳይኖረን ልንኾን አይገባም።"

እኛ ከዚህ የምንወስደው መልእክት አሁን ላይ በቤተክርስቲያናችን እየሰፋ የመጣው ይህ እኮ ቀኖና ነው ምን ችግር አለው ፣ የግብጽ ቤተክርስቲያን እኮ እንዲህ ነው ምታደርገው ምን ችግር አለው የሚሉ ሰዎች አሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ እስከኖርክ ድረስ የምትመራው በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ነው ስለዚህ ችግር አለው፣ እንደ ግብጾቹ መኖር የምትችለው ግብጽ ስትኖር ነው ለጊዜው ግን የኢትዮጵያን ትውፊት ፣ ቀኖና እና ሥርዓት ማክበር የግድ ይላል።

Soure: Augustine, Letter 54 to Januarius, CCEL (https://www.ccel.org/ccel/schaff/npnf101.vii.1.LIV.html)
❤ 13 👍 2 🥰 1 🙏 1
29 May 2024
ኪ
09:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
"የማርያም ነፍስ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሷም በእግዚአብሔር ሐሴትን ታደርጋለች ምክንያቱም በነፍሷና በመንፈሷ ለአብ እና ለወልድ በመገዛቷ ኹሉም ነገር የተገኘበትን አንድ አምላክ በቀና ፍቅር ታመልካለች። ነገር ግን እያንዳንዱ በጌታ ደስ ይለው ዘንድ የማርያም መንፈስ ይኑረው። በሥጋ አንዲት የክርስቶስ እናት ብቻ ናት ያለችው፥ በእምነት ግን ክርስቶስ የኹላችን ፍሬ ነው። ነፍስ ኹሉ የእግዚአብሔርን ቃል የሚቀበለው እድፍ ከሌለበት፣ ከኃጢአት ከነጻ እና ነፍሱን በንጽሕና ከጠበቀው ብቻ ነውና።" (ቅዱስ አምብሮስ ዘሚላን)

የማርያም መንፈስ ይኑረን ❤️
❤ 20 🥰 1
30 May 2024
ኪ
01:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ

በሕይወት ዘመኔ ፍጻሜ አንዲት ነገርን እሻለሁ "የኔ ታማኝ ባሪያ በመልካም አገልግለኸኛል" የምትለውን ቃል ለመስማት ነፍሴን እሰጣለሁ። ጌታዬ በሰማይም በምድርም አንድ ነው እኔን ስለማዳን ነፍሱን የሰጠ ክርስቶስ ነው። እርሱ ከባሪያም በላይ ልጅ አድርጎኛል። እኔ ግን ጌታዬ ሆይ እንደ ጠፋው ልጅ"ባሪያህ ልባል እንጂ ልጅህ ልባል አይገባኝም" እልሃለው። በሥጋ ዘመዶችህ የኾኑት ይሁዳ እና ያዕቆብ እንኳን ምንም እኛ የጌታ ወንድሞች ብንላቸውም እነርሱ ግን "የጌታ ወንድም" ከመባል ይልቅ "የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ" ተብለው መጠራትን መርጠዋል።(ያዕ 1፡1 ፣ ይሁ 1) ሕይወቱን ኹሉ በመልካም ያገለገለህ ሐዋርያህ ጳውሎስም "ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም" (ገላ 4፡6) ብሎ ካስተማረ በኋላ እራሱን ሲጠራ ግን "ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ" ብሎ ባሪያህ መባልን ተመኝቷል። (ሮሜ 1፡1)

የሐዋርያት ኹሉ የክብራቸው ስም የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ መባል ነበር (2ኛ ጴጥ 1፡1)። ያንተ ባሪያ በመባላቸው ዓለም ቢያሾፍባቸውም እነርሱ ግን በስምህ አጌጡበት ፤የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ መባልን ከምንም በላይ ወደዱት፤ አንተንም አገልግለው እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ታመኑልህ። ጌታ ሆይ እኔንም ባሪያህን አስበኝ በሕይወት ዘመኔ ኹሉ እታመንልህ ዘንድ መንፈሴን አበርታልኝ አገልግሎቴ ኹሉ ላንተ ይኹን ፤ንጉሤ ሆይ በልቤ ላይ ንገሥ እኔም ባሪያህ ልባል በቤትህም ለዘለዓለም ላገልግልህ ይህቺም ቅድስት ቤተክርስቲያንህ ናት።

ሰው እንዴት ነጻ ኾኖ ሳለ ባርነትን ይመኛል አትበሉኝ እውነቱን ብትሹ እውነት ነጻ ያወጣችኋል፤ ይህም እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ከኾነ ሰው በላይ ነጻ ማንም የለም! እኔስ በባርነቴ አላፍርበትም ያመንኩትን አውቀዋለውና!

"ባሪያ ሆኖ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው። በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ።" (1ኛ ቆሮ 7፡22)
❤ 8 🥰 1
6 June 2024
ኪ
16:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ መጽሐፍ ቅዱስን ሳንጠቀም የኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወት ታሪክ እንጻፍ እውነት ታሪክ ኢየሱስን ይደግፈዋልን? ወይስ ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ፈጠራ ነው?

የልጅነት ሕይወት
ክርስቲያናዊ ካልሆኑ ምንጮች ስለ ኢየሱስ የልጅነት ሕይወት የሚገልጹ ዝርዝሮች በአብዛኛው አይገኙም። እነዚህ ምንጮች በዋነኛነት የሚያተኩሩት ስለ ማስተማሩና ስለ ሞቱ ነው።

ረቢው ኢየሱስ
ክርስቶስ ወይም ክሪስተስ ተብሎ የሚጠራው ኢየሱስ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በአይሁድ ዘንድ ታዋቂ ረቢ (መምህር) ኾኖ ብቅ ብሏል። እውቁ የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ ፍላቪየስ ዮሴፈስ (Flavius Josephus) እንዳለው ከኾነ አስደናቂ ድንቅ ሥራዎችን ያከናወነ ጥበበኛ ሰው ነበር፤ እንዲሁም እውነትን በደስታ የተቀበሉ ሰዎችን ያስተምር ነበር። በተለያዩ ማህበረሰቦች ሰፊ ተቀባይነትን በማግኘት በአይሁዶች እና በግሪኮች መካከል ጉልህ ተከታዮችን አፍርቷል። (Josephus, Antiquities of the Jews, Book 18, Chapter 3, Section 3)

የተሰቀለው ክርስቶስ
ሮማዊው የታሪክ ጸሐፊ ታሲተስ (Tacitus) ስለ ኢየሱስ ሞት ወሳኝ የሆነ መረጃን ሰጥቷል። ታሲተስ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራው ሰው፤ ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ አውራጃ ገዢ በኾነበትና ንጉሠ ነገሥት ቄሳር ጢባርዮስ በሮም በነገሰበት ዘመን፤ በስቅላት እንደተገደለ ተናግሯል (Tacitus, Annals, 15.44)። ይህን ክስተት ዮሴፈስም ጽፎት እናገኘዋለን፣ እርሱም ጲላጦስ በኢየሱስ ሞት ላይ መሳተፉን አውስቷል። (Josephus, Antiquities of the Jews, Book 18, Chapter 3, Section 3)።

በስድት ሰአት የጸሐይ መጨለም
የመጀመሪያዎቹ ሥራዎቹ ጠፍተዋል የሚባለው የታሪክ ጸሐፊው ታለስ (Thalus) በኢየሱስ ስቅለት ወቅት ስለነበረው ጨለማ ጠቅሷል። የእርሱ ሥራ ቢጠፋም በ221 ዓ.እ አካባቢ ይኖር በነበረ በክርስቲያኑ አፖሎጂስት ጁሊየስ አፍሪካነስ የእርሱ ሥራ ተጠቅሷል። ጁሊየስ አፍሪካነስ እንዲህ ሲል ጽፏል:
"ታለስ በጻፈው ታሪክ ሶስተኛው መጽሐፍ ላይ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ የነበረውን ጨለማ የጸሐይ ግርዶሽ ነው በማለት አስተባብሏል ይህ ግን አያስኬድም ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ የአይሁድ ፋሲካ ነበር ያን ጊዜ ደግሞ ጨረቃ ሙሉ ናት፣ ሙሉ ጨረቃ በምትወጣበት ጊዜ ደግሞ የጸሐይ ግርዶሽ ሊፈጠር አይችልም (Julius Africanus, Chronographia, 18.1)

በኹለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው ፍሌጎን (Phlegon) የተባለ ግሪካዊ የታሪክ ምሁርም ስለ ጨለማው ታሪክ መዝግቧል። የእርሱጽሑፍ እንዲህ በሊቁ ኦሪገን ተጠቅሷል፡
" ፍሌጎን በጢባርዮስ ቄሳር የግዛት ዘመን ላይ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠነኛው ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ እንደነበረ ዘግቧል።" (Origen, Against Celsus, Book 2, Chapter 33, quoting Phlegon)

የተነሣው ኢየሱስ እና ተከታዮቹ ክርስቲያኖች
ኢየሱስ ቢገደልም ክርስቲያኖች በመባል የሚታወቁት የኢየሱስ ተከታዮች ለእርሱ አምልኮ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። ዮሴፈስ ኢየሱስን የሚወዱት ከሞቱ በኋላ ለእርሱ ያላቸውን ፍቅር እንዳላቋረጡ ገልጿል፣ እናም በነቢያት እንደተነገረው በሦስተኛው ቀን እንደ ገና በሕይወት እንደተገለጠላቸው ያምኑ እንደ ነበር ጽፏል (Josephus, Antiquities of the Jews, Book 18, Chapter 3, Section 3)። ይህ የትንሣኤው ትምህርት ምንም እንኳን ክርስቲያናዊ ባልኾኑ ምንጮች በጥርጣሬ ቢታይም የክርስትና እምነት ዋና አካል ነው። ለምንስ ሰዎች አንድ የተሰቀለን ሰው ይከተላሉ ተነሥቷል ብለው ካላመኑ በስተቀር።

ሌላኛው የታሪክ ጸሐፊ ታናሹ ፕሊኒ (Pliny the younger) ከንጉሠ ነገሥት ትራጃን ጋር በተጻጻፈው ደብዳቤ ስለ ጥንት የክርስትና አምልኮ ልምምዶች ሲያነሣ ይታያል ፣ ያየውንም እንዲህ ይገልጻል “ ልክ ለአምላክ እንደሚደረገው ለክርስቶስ መዝሙር ለመዘመር ጎህ ሳይቀድ ክርስቲያኖች ይሰበሰባሉ፣ እርስ በእርሳቸውም መልካም ምግባርን ለመጠበቅ ይማማላሉ። (Pliny the Younger, Letters, Book 10, Letter 96).)

ከይሁዳ እስከ ሮም
ሮማዊው የታሪክ ምሁር ሱኢቶኒየስ (Suetonius) በሮም በ"ክሪስተስ" ምክንያት የተፈጠረውን ሁከት በአጭሩ ጠቅሷል፣ ይህም የኢየሱስ ተጽእኖ ከይሁዳ በላይ እንደዘለለ እና በሰፊው የሮማ ኢምፓየር ውስጥ ተጽእኖ እንዳለው ያሳያል።(Suetonius. The Lives of the Twelve Caesars. The Life of Claudius, 25.4)።

የአይሁድ ታልሙዶች ዘገባ
ታልሙዶች ኢየሱስን (Yeshu በሚል ስም ይጠሩታል) እንደ መናፍቅ ሲያነሱት ይታያሉ እንዲሁም ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ እንዳልኾነ ቢመሰክሩም ማርያም ከሮማዊ ወታደር ነው የወለደችው በማለት በድንግልና መወለዱን ለማጣጣል ይሞክራሉ፤ በዚህጥላቻቸውን ቢገልጡበትም ሳያስቡት አባቱ ማን እንደ ኾነ እንደማይታወቅ ገልጠዋል ። እንዲሁም በፋሲካ ዋዜማ መገደሉን እና በጥንቁልና እና በአስማት ብዙ ተአምራት መስራቱን ይናገራሉ። አሁንም በአስማት ብለው ለማጣጣል ቢሞክሩም ታላቅ ተአምር አድራጊ መኾኑን ግን መስክረዋል። (The Babylonian Talmud. Sanhedrin 43a.)

Bibliography
• Josephus, Flavius. Antiquities of the Jews. Translated by William Whiston. Harvard University Press, 1934.
• Tacitus, Cornelius. Annals. Translated by Alfred John Church and William Jackson Brodribb. Macmillan, 1876.
• Pliny the Younger. Letters. Translated by William Melmoth, revised by W.M.L. Hutchinson. Harvard University Press, 1915.
• Suetonius. The Lives of the Twelve Caesars. Translated by Robert Graves. Penguin Books, 1957.
• The Babylonian Talmud. Translated by Jacob Neusner. Hendrickson Publishers, 2011.
🙏 6 👍 2 🥰 1
13 June 2024
ኪ
01:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
መድኃኒታችን ዐረገ

በዚህ ቀን፣ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዕርገት እናስባለን ፣ ከትንሣኤው 40 ቀናት በኋላ፣ በደቀ መዛሙርቱ ፊት ወደ ሰማይ ወደ አባቱ ዘንድ ዐረገ። ሞትን በሞቱ ድል ነስቶ ፣ መፍረስና መበስበስን በትንሣኤው ካጠፋ በኋላ አሁን ደግሞ ባሕርያችንን ያከብረው ዘንድ በአባቱ ቀኝ አስቀመጠው (የተዋሐደውን ሥጋ በመለኮታዊ ክብሩ አክብሮ ከአብ ጋር አስተካከለው)።

ዕርገት የክርስቶስን ምድራዊ ተልእኮ ይኸውም በጽንሰቱ የኛን ባሕርይ በመንሳት የጀመረውን ድኅነታችንን ማጠናቀቅን የሚያመለክት ሲኾ በመንፈስ ቅዱስ መውረድ የሚጀምረውን አዲስ ዘመን - የቤተክርስቲያንን ዘመን ያውጃል። በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥም በክርስቶስ አንድ የኾንን ኹላችን የመጨረሻው ግባችን ወደ ዐረገው መሢሐችን መሄድ እና ከመለኮታዊ ክብሩ በጸጋ መካፈል ነው።

የድኅነታችን ራስ ክርስቶስ የሄደበትን እኛ የእርሱ አካላት ደግሞ እንደምንከተል አውቀን ዕርገቱ በሚያመጣው ተስፋ እና ዋስትና ደስ ይበለን። በዚህ ቀን እውነት በፍጹም ሐሴትን እናድርግ መድኅናችን ክርስቶስ በክብር ድኅነታችንን ፈጽሞ አርጓልና ነገር ግን ከክርስቶስ ድኅነት ለመሳተፍ እርሱ ጨርሶታል ብለን ብቻ የምንተውስ አይደለም የክርስቶስን በክብር ዳግመኛ መምጣት በመጠባበቅ በመልካም ሥራ እንጸናለን እንጂ ምክንያቱም ይህ ከእኛ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳየነው፥ እንዲሁ ይመጣልና።(ሐዋ 1፡11)

ጌታ በመለከት ድምጽ ዐረገ አንኳን አደረሳችሁ!
❤ 7 🔥 1
18 June 2024
ኪ
22:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ
ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ

ዘወትር የተጨነቁትን የምትራዳ ሚካኤል ሆይ
እንደ ልማድህ ትረዳኝ ዘንድ ክንፍህን ዘርግተህ ና!

ናና ሚካኤል ናና ❤️
❤ 8 👍 3
21 June 2024
ኪ
00:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
መለኮታዊ እሳት

የሚያቃጥል የእሳት ልሳን ከሰማያት ወረደ ፣ ከአርያሙ ከፍታ የሚባላ እሳት ወረደ። ይህ እሳት ግን ሰዶምን እንዳጠፋው እሳት የጥፋት እሳት አይደለም ይልቅስ የባቢሎንን ግንብ ያፈረሱ 72 ልሳናትን ይዟል እንጂ። የባቢሎኑ ልሳንስ አንድ የነበረው ሕዝብ የበታተነ ነው የአሁኑ ልሳን ግን እስከ ዓለም ዳርቻ የተበተነውን ሕዝብ የሚሰበስብ ነው። በሰዶም ላይ የወረደው እሳት ሕዝቡን ከነ ኃጢአታቸው ያጠፋ እሳት ነው ፣ የአሁኑ እሳት ግን ለዓለም ሕዝብ ኹሉ የምሥራች ወንጌልን የሚሰብክ የሚያድን እሳት ነው።

ከጽርሐ አርያም እሳት ወረደ በጽርሐ ጽዮንም ላይ አረፈ የሚንበለበል ልሳናትን ይዟል እንደ ሰከረ ሰው በኃይል ያናግራል ፣ በሰይፍ ፊት ድፍረትን የሚሰጥ ስልጣንን ተጎናጽፏል ፤ ስለ እውነትም ይመሰክር ዘንድ ዝም አይልም "እናንተ የሰቀላችሁትን ክርስቶስ እግዚአብሔር በክብር አስነሣው" እያለ በሚገባው ቋንቋ ኹሉ ይወቅሳል፤ ከሰማይ ወርዶ ይቆፍራል መሬትንስ አይደለም የሰውን ልብ ይቆፍራል የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ እንዲፈልቅ ይቆፍራል (ዮሐ 7፡38)። ለዘለዓለም በሚያረካውም ውሃ ልብን ያረሰርሳል። የማይጠፋ ብርሃን አለው፤ በተስፋው ብርሃን እየዋጀ የብርሃን ልጆች እስክንኾን ድረስ አይተወንም ኹሉንም ለእግዚአብሔር ይዋጃል ከማኅጸነ ዮርዳኖስም ወልዶ የሰማያት ልጆች አድርጎናል እርሱም የርስታችን መያዣ ነው (ኤፌ 1፡14) ስሙም ከአብ የሚወጣ አጽናኙ የእውነት መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ነው! (ዮሐ 15፡26)

ኢዩኤል ሆይ ደስ ይበልህ እነሆ ትንቢትህ ተፈጸመ መንፈሱ በሥጋ ለባሽ ኹሉ ላይ ፈሷል ፣ ወንዶችም ሴቶችም ትንቢትን ተናግረዋል ፣ ሽማግሌዎችም ሕልምን አልመዋል፣ ጎበዞቻችንም ራእይን አይተዋል ፣ በሰማያትም ድንቅ ታይቷል (ኢዩ 2፡28-30)። ልባችን በመለኮታዊው እሳት ተቃጠለ እነሆ ጽርሐ ጽዮን በደስታ ተሞላች ፣ ከጽርሐ አርያምም ጋር አንድ ኾነች አጽናኙ መጥቷልና ፣ ድንቅም ከሰማያት ፈሷልና!

አቤቱ መለኮታዊው እሳት ሆይ ነፍሳችንን አንድደው ፣ የክርስቶስ ሕይወት ብርሃን በውስጣችን ይበራ ዘንድ፤ የማትጠፋ እሳት ሆይ ኹለመናችንን ተቆጣጠር። ነፍሳችን በኃጢአት ውሃ ቀዝቅዛለች ፣ በዓለምም ሃሳብ ተጠምዳ የሕይወትን ውሃ ተጠምታለች። የሕይወት ውሃ ክርስቶስ በልባችን ይፈልቅ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ልባችንንን ስበረው ፣ የክርስቶስን ትንሣኤ ብርሃን በልባችን ውስጥ አቀጣጥለው። አጽናኙ ሆይ አጽናናን ፣ የዋሑ ርግብ ሆይ ልባችንን በትሕትና አረስርሰው ምናልባት የሸፈተው ልባችን ትንሽ እንኳን ልመለስ እንደኾነ።

"መንፈስ ቅዱስ አእምሮንና ልብን የሚያበራ ብርሃን፣ መንፈሳዊ ጥማችንን የሚያረካ ውሃ፣ የሚያነጻና የሚቀድስ እሳት ነው። (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በእንተ መንፈስ ቅዱስ)

ከወዲሁ መልካም በዓለ መንፈስ ቅዱስ በእለተ እሑድ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንገናኝ።
👍 4 ❤ 2 🥰 1
22 June 2024
ኪ
11:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ይወርድ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ኅብስቱ ወወይኑ
ሶበ ይብል ካህን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ፈኑ
ይወልጦሙ በቅጽበት አባላተ ክርስቶስ ይኩኑ
በኃይለ ጥበቡ መንክር ወእጽብ ኪኑ

ካህኑ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላክ ባለ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በኅብስቱና በወይኑ ላይ ይወርዳል ድንቅ በኾነ ፍጹም የጥበቡ ኃይልም በቅጽበት የክርስቶስ ሥጋና ደም ወደ መኾን ይለውጣቸዋል" መልክአ ቁርባን

የክርስቶስን ዘልዓለማዊ መሥዋዕት ዛሬም በቁርባኑ ላይ እንድናገኝ የሚያረጋግጥልን መንፈስ ቅዱስ ነው ፣ ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ይጠራል በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወደው መንፈስ ቅዱስም አሁንም ከሰማየ ሰማያት ይወርዳል ኅብስቱና ወይኑንም ወደ ሥጋና ደምነት ይለውጣል እኛንም ከዕለተ አርቡ መሥዋዕት ተካፋይ ያደርገናል መንፈስ ቅዱስ ሆይ ሥራህ ድንቅ ነው!

"የሚነድ ፡ የእሳት ፡ ሰይፍ ፡ ሜሎስ ፡ (መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡) ይገለጽ ፡ ሰማየ ፡ ሰማያትም ፡ በቸርነትህ ፡ ይከፈት ፡ በፈቃድህም ፡ ሕያውና ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህ ፡ ይላክ ፤ ይውረድ ፤ ይምጣም ። በዚህም ፡ ኅብ ስትና ፡ ጽዋ ፡ ላይ ፡ ይረፍ ፡ ይባርከው ፡ ይቀድሰውም ፤ ከአንድ፡ ልጅህ ከጌታችንና ከመድኃኒታችንም፡ ከአምላካችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክ ር ስ ቶ ስ ፡ሥጋና፡ ደም፡ ጋር፡ አንድ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ። ለሚቀርቡት ፡ የበደል ፡ ማስተሥረያ፡ ለሚቀበሉትም ፡ የኃጢአት ፡ ይቅርታ ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ።" ቅዳሴ ቄርሎስ
❤ 10 🥰 1
10 July 2024
ኪ
13:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዕረፍቱ ለዐምደ ሃይማኖት

የተዋሕዶ ጠበቃ ዐምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ዛሬ ዕረፍቱ ነው። ከሃዲው ንስጥሮስ አንዱን የክርስቶስ ባሐርይ ከፍሎ መለኮት የመለኮትን ሥራ ይሰራል ፣ ሥጋም የሥጋን ሥራ ይሰራል ፤ የመለኮት ባሕርይ አይታመም አይሞትም ይልቅስ የታመመው የሞተው የሥጋ ባሕርይ ነው። ማርያምም የወለደችው የሥጋን ባሕርይ እንጂ የመለኮትን ስላልኾነ ወላዲተ ሰበእ (Anthropothokos) ትባላለች የሥጋ ባሕርይ የመለኮትን ባሕርይ ተዋሕዶ 1 ማንነት ክርስቶስ ስለኾነ ደግሞ ወላዲተ ክርስቶስ (Christotokos) ትባላለች እንጂ መለኮትን ስላልወለደች ወላዲተ አምላክ (Theotokos) አትባልም አለ።

ይሄን ጊዜ ዐምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስ ለንስጥሮስ መልስ 2 መልክቶች እና 12 አናቅጸ ውግዘትን (12 Anathemas) ጽፎበታል። ከነዚህ አናቅጸ ውግዘቶች ጥቂቱን እንመልከት:

አንቀጽ 1: ማንም ሰው አማኑኤል አምላክ እንዳልኾነ እንዲሁም ቃልም ሥጋ ኾነ ተብሎ እንደተጻፈ አምላክን በሥጋ በመውለዷ ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ እንዳልኾነች የሚመሰክር ቢኖር ወጉዘ ለይኩን (የተወገዘ ይኹን !)

አንቀጽ 3: ማንም ከባሕርያዊው ተዋሕዶ በኋላ የአንዱን ክርስቶስ ባሕርያት የሚከፋፍል በክብር ተቀባይነት ወይም በሥልጣና ኃይል ተቀባይነት ብቻ የሚያገናኛቸው ይልቅስ በኹለቱ ባሕርያት አንድ ላይ መምጣት ባሕርያዊ ተዋሕዶ መደረጉን የማያምን ቢኖር የተወገዘ ይሁን!

አንቀጽ 12: የእግዚአብሔር ቃል በሥጋ እንደ ታመመ፣ በሥጋ እንደተሰቀለ፣ እንዲሁም በዚያ ሥጋ ሞትን እንደቀመሰና እርሱ አምላክ ፣ ሕይወት እና ሕይወትን ሰጪ በመኾኑ የሙታንም በኵር እንደ ኾነ የማያምን የተወገዘ ይሁን!

12ቱንም አናቅጽ በዚህ ያንብቡ: https://earlychurchtexts.com/public/cyrilofalex_twelve_anathemas.htm

ንስጥሮስ በነዚህ አናቅጸ ውግዘትም ኾነ ወመልእክቶቹ አልመለስም በማለት በክሕደቱ በመቀጠሉ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘይንአስ (Theodosius II ) በ431 ዓ.እ በኤፌሶን ጉባኤ ጠራ ፤ ጉባኤውም የቄርሎስን አንቀጸ ውግዘቶች ኦርቶዶክሳዊነት አጽድቆ ንስጥሮስን አወገዘ።

ታላቁ ዐምደ ሃይማኖት ቅዱስ ቄርሎስም ለተዋሕዶ ጠበቃ ኾኖ ሃይማኖትንም ጠብቆ በዚህች ቀን ዐረፈ ፤ እስካሁንም ድረስ " Miaphysis to theo logue se'sarkomene - የሥግው ቃል አንድ ባሕርይ" በሚለው ንግግሩ ይታወቃል እኛም በእርሱ formula Miaphysite እንባላለን። በረከቱ ይደርብን።
❤ 6 🥰 2 👍 1
ኪ
14:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
🥰 4
12 July 2024
ኪ
09:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ

ዛሬ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለዓለም ለማዳረስ ሕይወታቸውን የሰጡ ሁለቱ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች እና የዓለም ብርሃናት ጴጥሮስና ጳውሎስን እናከብራለን። 🙏

የዮና ልጅ ስምዖን ትሑቱና ትምህርት እንኳን ያልተማረው የገሊላዋ ቤተሳይዳ አሳ አጥማጅ ፣ ለእምነት የፈጠነ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት ግንበኞች ቢንቁትም የማእዘን ራስ የኾነውን ዓለት ኢየሱስን  በመመስከር ቤተክርስቲያን የምስመሠረትበት ዓለት (በግሪክ ጴጥሮስ) የኾነ ፣  በዚህም የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ የተቀበለ። ሕይወቱን በሙሉ ለክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያን በመስጠት የክርስቶስን ወንጌል ያለፍርሃት በሰው ሁሉ ፊት ሰበከ ከይሁዳ ተነስቶ ፣ ከዚያም በአንጾክያ አከባቢዎች ሁሉ ከሰበከ በኋላ ሮም ደረሰና በኔሮን ቄሳር እጅ ይሰቀል ዘንድ ተፈረደበት ። ሮማውያን ስቅላትን እንደ እርግማን እና ውርደት ቢያዩትም ተወዳጁ ጴጥሮስ ግን በመስቀሉ ላይ የታየው የነፍሱ ጌታ ኢየሱስ ነው ፣ከዚህም የተነሳ እኔስ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም በማለት ተዘቅዝቆ እንዲሰቅሉት ጠይቋል ፣ መጀመርያ ከክርስቶስ ጋር መሰቀልን ፈርቶ "ሰውዬውን አላውቀውም" ብሎ ቢክደውም አሁን ግን ልቡ ጸንቶ ለተሰቀለለት ኢየሱስ እርሱም ተሰቅሏል። ✝️

ቀናተኛው ሳውል (በሮማይስጥ ጳውሎስ) ከፈሪሳዊው ገማልያል ዘንድ የተማረ ታላቅ የመጻሕፍት ምሁር ለአይሁድ እምነት በጣም የሚቀና ፈሪሳዊና የቤተክርስቲያን ቀናተኛ አሳዳጅ ነበር። ሆኖም፣ ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ላይ በነበረው የኢየሱስ መለኮታዊ መገለጥ፣ ጥልቅ የሆነ ለውጥን አገኘ የተመረጠ እቃም ተባለ። በሰማያዊ ብርሃን ታውሮ የኢየሱስን ድምፅ በመስማት ሕይወቱን ለአሕዛብ ወንጌልን በመስበክ ራሱን የሰጠ የክርስቶስ ተከታይ ሆነ። እስራትና ድብደባን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችንና መከራዎችን ተቋቁሞ ዛሬም እኛን የሚያበረታታን የእምነት ውርስ  እነርሱም ውድ የሆኑ መልእክቶቹን ትቶልናል። የመዳንን መልእክት ያለ ፍርሃት ለሕዝብ ሁሉ ካደረሰ በኋላ  በመጨረሻም ሮም ሲደርስ በኔሮን ቄሳር ሞት ተፈረደበት እርሱ በዘር አይሁዳዊ ቢሆንም በሮሟ ጠርሴስ በመወለዱ የሮም ዜግነት ስላለው ከአሰቃቂው ስቅላት ይልቅ በፈጣኑ አንገትን በሰይፍ መቀላት ይሞት ዘንድ ተወሰነበት ስለዚህም የቤተክርስቲያን አሳዳጅ በመሆን የጀመረውን ሕይወት ለቤተክርስቲያን ተሳዳጅ በመሆን መራና በመጨረሻም እራሱን ለቤተክርቲያን በመሰዋት ፈጸመ።  🌟

የቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም የተሞላ የተባረከ በዓል ይሁንላችሁ።
❤ 6 👍 1 🥰 1
14 July 2024
ኪ
10:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነአምን በአሐዱ እግዚአብሔር ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ

ከዓለም በፊት በነበረው በአንዱ እግዚአብሔር እናምናለን። እርሱ ዓለማትን ኹሉ አስገኝቷል እርሱን ግን ያስገኘው የሌለ ብቻውን ኹሌ አለ የሚባል አምላክ ነው።

ወነአምን በካልዑ እግዚአብሔር ዘበምልክናሁ ለአብ ይመስሎ

በአምላክነቱ አብን በሚመስለው በኹለተኛው እግዚአብሔርም እናምናለን። እርሱ ከዓለም ኹሉ በፊት ከአብ ያለ ተከፍሎ ባሕርይ ተወለዶ በአካል ብቻ የተለየ ፍጹም አባቱን የሚመስል ልጅ ነው።

ወነአምን በሣልሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘይመልዕ ኩሎ

ኹሉን በሚመላ መንፈስ ቅዱስ በሦስተኛው እግዚአብሔርም እናምናለን። እርሱ እንደ ልጁ ከአብ ወጥቶ ኹሉን የሚመላ በፍጥረታት ኹሉ የሚያድር በባሕርይ ከአባት እና ከልጅ ጋር አንድ መለኮት ነው።

❤️ሥሉስ ቅዱስ❤️
❤ 6 👍 1 🥰 1
17 July 2024
ኪ
15:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ተዋሕዶ እንበለ ውላጤ

አምላክ ሰው ኾነ ስንል አምላክነቱን ወደ ሰውነት በመለወጥ አይደለም ይልቅስ ሰውነትን ከአምላክነቱ ጋር አንድ አደርጎ ይህ አንዱ ባሕርይ በአንድ ጊዜ አምላክም ሰውም በመኾን ነው እንጂ። የአባይን ወንዝ እንመልከት እስራኤላውያን ግብጽ ላይ ካወረዱት 10 መቅሰፍቶች መካከል አንዱ የአባይን ወንዝ ወደ ደም መለወጥ ነበር። ነገር ግን የአባይ ወንዝ ደም ሲኾን ባሕርይው ከውኃነት ወደ ደምነት በመለወጥ አይደለም ይህ አንዱ ውኃ ለግብጻውያን ደም ለእስራኤላውያን ወኃ ኾናቸው እንጂ ኹለት ቦታ ተከፍሎ በእስራኤላውያን በኩል ያለው ውኃ ፣ በግብጻውያን በኩል ያለው ደግሞ ደም ኾኖም አይደለም እራሱ አንዱ ውኃ በአንድ ጊዜ ባሕርይውን ሳይለውጥ ውኃም ደምም ኾነ እንጂ።

የክርስቶስ ባሕርያት ተዋሕዶም እንዲሁ ነው አምላክነቱ እና ሰውነቱ ተዋሕደው አንድ ውሕድ ባሕርይ (One composite nature) ኾነዋል ነገር ግን ሰውነትም ወደ አምላክነት አልተለወጠም ፣ አምላክነትም ወደ ሰውነት አልተለወጠም ይልቅስ አንዱ ውሕደ ባሕርይ በአንድ ጊዜ አምላክም ፣ ሰውም ፤ ኢፍጡርም ፣ ፍጡርም ነው እንጂ።

ከቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ (Theodotus of Ancrya) ማብራርያ የተወሰደ።
❤ 12 👍 2
25 July 2024
ኪ
11:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰላሜን እተውላችኋለሁ

በዚህ ምድር ስንኖር ኹለት አይነት ሰላምን እናገኛለን ውሳጣዊና ውጫዊ ሰላም። አንዱ መኖሩ ሌላኛው ለመኖሩ ዋስትና አይደለም ምክንያቱም በዙሪያቸው ባለው አከባቢ ሰላምን አጥተው ፣ ሀገራቸው በጦርነት ተሞልቶ ሳለ እነርሱ ግን ከውስጣቸው ጋር ሰላምን ፈጥረው የሚኖሩ ሰዎች እንዳሉ ኹሉ ሀገራቸው ፍጹም ሰላም የሰፈነበት ኾኖ ሳለ ከውስጣቸው ሰላምን ያጡ በdepression የሚሰቃዩ ሰዎች አሉና።

ታድያ ኹኔታው እንዲህ ከኾነ እውነተኛው ሰላም የቱ ነው? የውጪው ነው ወይስ የውስጥ? የውጪው ዓለምስ ተለዋዋጭ ነው ዛሬ ሰላም ኾነ ስንል ሁከት ይኾናል ፤ ሁከት ተነሳ ስንል ሰላም ይኾናል ዓለም የማትጨበጥ ተለዋዋጭ ናትና። ከፍጥረት ባሕርይ ውስጥ አንዱ ተለዋዋጭነት (malleability) ነው ፍጥረት ኾኖ የማይለወጥ የለም ወደ ህልውና የመጣው ራሱ በለውጥ (ካለመኖር ወደ መኖር በመለወጥ) ነውና። ስለዚህ ውጫዊው የዓለም ሰላም ከዓለም ጋር ተለዋዋጭ ነው ይህ ደግሞ እውነተኛ ሰላም አይደለም እውነት ሐሰት ሊኾን አይችልምና ዓለም ግን ዛሬ የኾነውን ነገ አይኾንም።

እውነተኛውን ሰላም ከውጪው ዓለም ፣ ከገንዘብ ፣ ከትዳር ፣ ከልጆች ፣ ከንብረት ፣ ከጤና የምንጠብቅ ከኾነ ምስኪኖች ነን እነዚህ ኹሉ ከጊዜ ጋር ይለወጣሉና። ኢዮብን እንመልከት የጠቀስናቸውን ነገሮች ኹሉ ነበሩት ነገር ግን ኹሉንም በአንዴ አጣ ኢዮብ ግን ሰላሙ ውሳጣዊ በመኾኑ የዓለምን ተለዋዋጭነት ያውቃልና እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይኹን ሲል አመሰገነ።

ስለዚህ ነው ክርስቶስ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም።” ያለን። (ዮሐ14፥27) እርሱ ፈጣሪ ነውና ለውጥ በባሕርይው የለበትም ትናንትም ዛሬም ለዘለዓለሙም ያው ነው፤ ስለዚህ የማይለወጠውን ውሳጣዊውን ሰላም ይሰጣል መስጠትም ብቻ አይደለም ሰላምን በውስጣችን ይተውልናል ይኸውም በበዓለ ሀምሳ የተወልን መንፈስ ቅዱስ ነው። የሰው ልጅ ሥጋ ብቻ አይደለም መንፈስም ጭምር እንጂ የመንፈሳችን ሰለም ደግሞ የልጁ መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ነው የማይለወጥ የማይቀማ እውነተኛ ውሳጣዊ ሰላም! ይኸውም ዛሬ ቢኖር ነገ እንደማይኖረው የዓለም ሰላም አይደለም።

ኢየሩሳሌማችን (የሰላም ሀገራችን) ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ምድራዊቷ ኢየሩሳሌምስ አንድ ጊዜ በባቢሎን ፣ አንዴም በሮም ብዙ ጊዜ ሰላሟን አጥታለች የኢየሱስ ሰላም ግን መቼም አይወሰድም ፣ አይታጣም ዘለዓለም ልብን ያሳርፋል እንጂ። ኢየሱስ ላይ የተጣበቀ ሰው በባሕር መሃል ያለ ታላቅ ዐለትን ይመስላል በዙሪያው ባሕሩ ቢጎርፍ ፣ መአበሉ ቢመታ ፣ ነጎድጓድ ቢወርድ አይነቃነቅም ክርስቶስ ላይ ተተክሏልና!

የክርስቶስ ሰላም ከኹላችሁ ጋር ይኹን።
❤ 11 👍 2 🥰 1 🙏 1
26 July 2024
ኪ
12:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
"እኔ ክርስቲያን ነኝ" ሕፃኑ ቂርቆስ

ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ
ድምፃ ለጽርሕት ከመ ነጎድጓደ ክረምት
ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት

ሕፃን እና እናቱ ኹለቱም ገድላቸውን ፈጸሙ
የእሳት ጋኑ ድምፅ እንደ ክረምት ነጎድጎድ ነው
ቅዱሳኑ ሰማዕታት ግን ሞትን አልፈሩም።

የሰማዕታቱን ልብ ይስጠን ❤
❤ 12 ❤‍🔥 1 🥰 1
2 August 2024
ኪ
18:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወተሰቅለ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ

በዓለም ላይ ብዙ "ሃይማኖቶች" አሉ አንዳንዱ እንደ ቡዲዝም አምላክ የላችውም፤ አንዳንዱ እንደ ሂንዱኢዝም በብዙ አማልክት ውስጥ የተገለጠ አንድ አምላክ አላቸው ፣ አንዳንዱም እንደ ግሪክ እና ሮም ብዙ አማልክት አላቸው። ከዚህ በተለየ ደግሞ የይሁዲ ፣ እስልምና እና ክርስትና ሃይማኖቶች አንድ አምላክን ያምናሉ። ኹሉም "ሃይማኖቶች" የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር ግን ከሰው በላይ የኾነ ይህን ዓለምም በማስገኘት ምክንያት የኾነ ኃይል ወይም ኃይሎች አሉ የሚለው ነው። ዓለምን ያስገኘው ኃይል ባሕርይው ምንድነው? ይህን ጥያቄ የተለያዩ "ሃይማኖቶች" በተለለያየ መንገድ ይመልሳሉ ኹሉም በውስጣቸው ይህ ኃይል ምን ይመስላል ለሚለው በራሳቸው አይምሮ ውስጥ ሥዕልን ሥለዋል ይህን ሥዕል divine substance (Ousia) እንለዋለን። ስለዚህ ጥያቄው ይህ ሥዕል በእውነታው አለ ወይስ በሰው አእምሮ ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው? የሚለው ነው። ይህ Ousia በህልውና ሊኖር ይገባል (it must exist) ያለበዚያ ምናባዊ ሥዕል ኾኖ ብቻ ይቀራል። በሕልውና ያለ ስለእርሱ እውነታ ልንናገርለት የምንችለውን ባሕርይ Hypostasis እንለዋለን። በክርስትና አምላካዊ ባሕርይ (The divine Ousia) ምናባዊ ብቻ ሳይኾን በ3 Hypostasis (ኩነት ፣ ክዋኔ) ያለ እውነት ነው።

በዓለም ላይ በአሁኑ ጊዜ ብዙ ተወዳጅ ሚቶሎጂዎች አሉ ለምሳሌ የግሪክ ሚትሎጂን ብናነሳ በምድርም በሰማይም ያሉትን የተለያዩ ፍጥረታት ስለፈጠሩ የተለያዩ አማልክት ይነግረናል መኖሪያቸውም በግሪክ የሚገኘው የኦሎምፖስ ተራራ (Mount Olympus )ነው። ስለነዚህ አማልክት ባሕርይ ብዙ ይነገራል ነገር ግን እነዚህ ትርክቶች አፈ ታሪክ ኾነው ብቻ ይቀራሉ ታሪክን ከአፈ ታሪክ የሚለየው እውነታ ነውና። አፈ ታሪክ ከዕለታት በአንዲት ቀን በእሩቅ ቦታ እንዲህ ኾነ በማለት ይተርካል ፤ ታሪክ ግን በዚህ ቦታ ፣ እንትና በሚባለው ሀገረ ገዢ ዘመን እንዲህ ኾነ በማለት ይተርካል (በቀድሞ ዘመን ታሪክ በሀገረ ገዢው ዘመን ይጻፋል እንጂ ታሪክን በዓ.ም መጻፍ የቅርብ ጊዜ ልማድ ነው)። ስለዚህ ታሪክን በእውነታው ዓለም ማረጋገጥ ይቻላል በተጠቀሰው ዘመን እና ቦታ ይህ ድርጊት ተፈጽሟል ወይ የሚለውን መመርመር ብቻ ነው የሚጠበቅብን ይህም እውነታ ይኹን አፈ ታሪክን ይለይልናል።

የክርስትና ሃይማኖት የኒቅያ-ቁስጥንጥንያ አንቀጸ ሃይማኖቱ ላይ "ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ ሐመ ወሞተ ወተቀብረ ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት-በጰንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሣ" በማለት በታሪካዊ ምርመራ መረጋገጥ የሚችልን (Historically verifiable) እውነታ ያስቀምጥልናል። ይሄም የሚያሳየው የክርስትና እምነት መሠረት ከዕለታት በአንድ ቀን በዕሩቅ ቦታ የተፈጸመ ድርጊት ሳይኾን ፤ በታሪክ እውነታ ውስጥ የምትገኝ የጰንጦሱ ሰው ጲላጦስ ገዢ በኾነባት በይሁዳ ኢየሩሳሌም ዘመኑም 26-36 ዓ.ም ላይ የተፈጸመ ድርጊት ነው። የታሪክ ምንጮችም እንደሚያሳዩን ኢየሱስ ክርስቶስ ከየትኛውም በታሪክ ከሚታወቁ ታዋቂ ሰዎች (ከነ Pythagoras ፣ ከነ Alexander the great ) በላይ የታሪክ ማስረጃዎች እንደሚገኙለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን መካድ ታሪክን መካድ ነው ይህም ክርስትና ከየትኛውም "ሃይማኖት" በላይ በታሪክ ላይ የተመሰረተ እውነታን እንዲይዝ ያደርገዋል። ይህ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሦስቱ አምላካዊ Hypostasis አንዱ ነው እርሱም ስለአባቱ ይመሰክራል እንዲሁም እርሱ የላከው የእውነት መንፈስ ስለእርሱ ይመሰክራል ቤተክርስቲያንን መርቷታልና። አምላካዊው ባሕርይ (The divine Ousia) በኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጧልና የክርስትና አምላክ ምናባዊ አይደለም በእውታው ዓለም ህልው የኾነ Hypostatic እንጂ ስለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ "መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው። " ሲል የመሰከረው። (ዮሐ 1፡18)
🙏 11 🥰 1
15 August 2024
ኪ
13:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
እኔ: ቅዱስ ቁርባን ለምንድነው ማትቀበለው?
እሱ: መች በቃሁና ልቀበል።
እኔ: ታመህ ሐኪም መድኃኒት ሲያዝልህ አልወስድም በትል ምክንያትህንም ብትጠየቅ መች ተሻለኝና ልውሰድ ትላለህ?

በህመም ላይ ኾነን ሐኪሙ ያዘዘልንን መድኃኒት ሳንወስድ ሊሻለን እንደማይችልም ኹሉ ያለ ቅዱስ ቁርባን መቼም ልንበቃ አይችልም። ልብቃ ብንል ከቅዱስ ሚካኤል ፣ ከቅዱስ ገብርኤል በላይ ልንበቃ እንችላለን? መላእክት ምንም ቅዱሳን ቢኾኑ ከቅዱሱ ምሥጢር እንኳን መቀበልና መንካት ራሱ አይችሉም ሰውን ወዳጅ ጌታችን ግን ለመድኃኒታችን ይኾነን ዘንድ ይህን ቅዱስ ምሥጢር ከቅዱሳን መላእክት ደብቆ ለእኛ ኃጢአተኞቹ ገለጠልን። ከቅዱሱ ሥጋና ደም ሳንቀበል ቅዱሳን መኾን አንችልም ፤ ለ24 ሰአት ብንጾም ፣ በቀን 1000 ጊዜ ብንሰግድ ሳናቋርጥ ብንጸልይ ያለ ቅዱስ ቁርባን መቼም ልንበቃ አንችልም ምክንያቱም ባለቤቱ "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" ብሏልና። (ዮሐ 5፥15)
🙏 14 ❤ 9 👍 2 🥰 1
17 August 2024
ኪ
10:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
እርሷ (ድንግል ማርያም) በማኅፀኗ ውስጥ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ሥግው ቃል የወሰነች ኹለተኛ ሰማይ ናት።

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ

ጌታ በማኅፀንዋ ያደረባት ኹለተኛይቱ ሰማይ እርሷም (ድንግል ማርያም) የማይወሰነውን ስለወሰነች የከበረች ናት።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ድንግል ማርያም በሰዎች መካከል ያድር ዘንድ ክርስቶስ የወረደባት ኹለተኛይቱ ሰማይ ናት።

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

ወደ ሰማይ ዐረገች ስንል ለምን ይደንቃችኋል እርሷ ራሱ ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ የወጣባት ሰማይ ናት።
❤ 22 😍 3
19 August 2024
ኪ
07:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
መለኮታዊ ብርሃን: ደብረ ታቦር🌟

የታቦር ተራራ በደመና ተሸፈነ አከባቢውም በነጓድጎድ ድምፅ ተዋጠ ፤ የጌታ ኢየሱስ ፊትም በራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ኾነ። እነ ጴጥሮስ ደነገጡ ፣ ተርበተበቱ ይህ የሚያዩት ብርሃን እንደሚያውቁት አይነት ብርሃን አይደለም። የፀሐይን ብርሃን ያውቁታል ይህ የሚያዩት ብርሃን ግን የተፈጠረስ አይደለም መለኮታዊ ነው እንጂ ። ምንጩም ፀሐይ ሳትሆን ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፣ ለካስ ሰው ብቻ መስሎ ቢታያቸውም እርሱ የአማልክት አምላክ ነው ፣ ብርሃን ከመፈጠሩ በፊት የነበረ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው  ።  ታቦር ሆይ የጸና ተራራ ሳለህ መነሳትህ ስለምንደር ነው? እግዚአብሔር ያድርብህ ዘንድ ወዷልና (መዝ 67:16) አንተም አርሞንኤም ሆይ ብርሃኑ ደርሶሃልና በጌታህ ስም ደስ ይበልህ ( መዝ 87:12)🏔️✨

ሙሴ እና ኤልያስም ብሉይ ኪዳን የሐዲስ ኪዳን ጥላው አይደል እንዴ ብለው ሕግ እና ነቢያትን ወክለው ለአምላካቸው ይመሰክሩ ዘንድ በታቦር ተገኙ እንጂ ዝም ይሉ ዘንድ አላስቻላቸውም። ኢየሱስ ግን የሚመሰክርለት ሰው ብቻ ሳይሆን "የምወደው ልጄ ይህ ነው" ሲል የሰማይ አባቱ ነው ።

ጴጥሮስ ትእይንቱ ቢያስደምመው የክርስቶስን ያልተፈጠረ ብርሃን እያየ ሁል ጊዜ ይኖር ተመኝቶ "በዚህ ብንኾን ለእኛ መልካም ነው" ሲል ጠየቀ። ጴጥሮስ ሆይ ለአንተስ ዘላለም የክርስቶስን ብርሃን እያየህ እዛው መኖር መልካም ነበር ነገር ግን የክርስቶስ ብርሃን አምፖል ለዓለም ኹሉ ይበራ ዘንድ ከፍ ብሎ በእንጨት ላይ መሰቀል ነበረበትና በዛ መኖሩ መልካም አይደለም።

ደብረ ታቦርን ስናከብር እንደ ታሪክ እያወራነው ብቻ አይሁን ይህን ክስተት መነሻ አድርገን ከዕለት ተዕለት ሕይወታችን ጋር እናገናኘው እንጂ። በጥርጣሬ ጊዜያት፣ የክርስቶስ አንጸባራቂ ክብር ኹል ጊዜ በልባችን ያለውን መሰናክል ያስወግድልን ዘንድ ከእኛ ጋር እንዳለ እናስታውስ። ጨለማ ሲያጋጥመን፣ የእርሱ ብርሃን ወደ ርህራሄ፣ ይቅርታ እና ፍቅር ይምራን። 🌟

የክርስቶስ ብርሃን በእኛ እንዲበራ ልባችንን እና አእምሮአችንን እንለውጥ። ደቀ መዛሙርቱ ከመለኮታዊው ጋር በመገናኘታቸው ለዘላለም እንደተለወጡ፣ እኛም በፍቅሩ እንለወጥ። ✨🕊️

እንኳን ለደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ! ይህ ቀን በውስጣችን ያለውን የመለኮታዊ ብርሃን ብልጭታ ያቀጣጥል እና ዓለምን በፍቅር እና በጸጋ እንድናበራ ኃይል ይስጠን!
❤ 12 🥰 1
21 August 2024
ኪ
21:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
የታቦቷ ትንሣኤ

ብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ጥላው ነው ፣  በሐዲስ ኪዳን የሚኾነው ነገር ኹሉ በምሳሌነት(Typology) ደረጃ ቢኾንም እንኳን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ይገኛል። እግዚአብሔር ከጊዜ ውጪ የኾነ አምላክ ነው ስለዚህ ሥራዎቹም በጊዜ አይገደቡም ስለዚህ ወደ ፊት የሚፈጠረቱን ነገሮች በቃል ደረጃ በትንቢት ሊነግረን ይችላል ከቃል በተጨማሪ ደግሞ ተፈጥሮ የእግዚአብሔር መጽሐፍ በመኾኑ በተፈጥሮ ምሳሌነት ሊነግረን ይችላል።

ክርስቶስ በወንጌላት ላይ ስለራሱ የብሉይ ኪዳን ምሳሌያትን (Typologies) ተጠቅሟል። ለምሳሌ "ሙሴ በምድረ በዳ የነሐስ እባብን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅም ሊሰቀል ይገባዋል" በማለት የነሐሱ እባብ የእርሱ ምሳሌ መኾኑን ነግሮናል። (ዮሐ 3፡14 ፣ ዘዳ 21፡19)። እንዲሁም "ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀንም አነሣዋለሁ" በማለት ቤተ መቅደስ የሰውነቱ ምሳሌ መኾኑን ይናገራል (ዮሐ 2፡19)። ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቶቹ ብዙ የብሉይ ኪዳንን ምሳሌዎች ለክርስቶስ ይሰጣል ለአብነት ያህል ፡ "ኹለተኛው አዳም (ሮሜ 5፡14) ፣ የፋሲካው በግ  (1ኛ ቆሮ 5፡17) ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት (ዕብ 7፡15) እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ።

ይህን ምሳሌያትን የመጠቀም ትውፊት ከክርስቶስና ከሐዋርያት የወረሱት ሐዋርያነ አበው (Apostolic Fathers) እመቤታችንንም በብዙ ምሳሌያት መስለዋታል። ከነዚህ ምሳሌያት መካከል ጥንታውያን የሚባሉት ዳግሚት ሔዋን ፣ የሐዲስ ኪዳን ታቦት ፣ ዳግሚት ሰማይ ፣ ሙሴ ያያት ሐመልማል ወዘተ ይገኙበታል ለዛሬ ግን የሐዲስ ኪዳን ታቦት ላይ ትኩረታችንን እናድርግ።

የቃልኪዳኑ ታቦት ለአሠርቱ ቃላት ማደርያ ኾኖ የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ከእስራኤላውያን ጋር ለመኾኑ ምልክት ነው። በሐዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይኾን ዘንድ አዲስ ምልክት ተሰጥቷል ይቺም ምልክት እመቤታችን ናት "ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም፡ አማኑኤል፡ ብላ ትጠራዋለች።" (ኢሳ 7:14)። ስለዚህም አካላዊው የእግዚአብሔር ቃል በድንግሊቱ  ከእኛ ጋር ኾነ ስለዚህም የሐዲስ ኪዳን ታቦት እንላታለን።

ይህንንም እውነታ ኹሉም የቤተክርስቲያን አባቶች በሚባል ኹኔታ ተናግረውታል ስለዚህም እኛ ተቀበልን ምሳሌያት የቤተክርስቲያን አባቶች ምሥክርነት ከሌለበት በራስ መሥራት አይኾንምና። ለአብነት እኒህን እንመልከት:

"በዚያን ጊዜ አዳኙ ከታቧቷ ከድንግሊቱ በመምጣቱ ሰውነቱንም ከዚህችዉ ታቦት በመንሣት ወደ ዓለም መጣ" (ቅዱስ ሂፖሊጦስ ዘሮሜ )

“አሁን ታቦቱ ከቅድስት ማርያም በቀር ሌላ ምንድነው እንላለን? ታቦቱ በውስጡ የቃል ኪዳኑን ጽላቶች ይዟል፡ ማርያም ግን የዚያን ኪዳን ወራሽ ወለደች።" (ቅዱስ አምብሮስ ዘሚላን)

"በወርቅ ፈንታ ንጽሕናን የተጎናጸፍሽ የቃል ኪዳኗ ታቦት ሆይ! እውነተኛው መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለበት ይኸውም መለኮት ያደረበት ሥጋ ያለባት ታቦት አንቺ ነሽ።" (ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ)

በነዚህ ምሳሌዎች ተነሥተን ቅዱስ ዳዊት ስለቤተመቅደሱ ዳግመኛ መሠራት የተናገረውን "አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት"(መዝ 131/132:8) የሚለውን ትንቢት ይዘን እግዚአብሔር ቀድሞ በነበረው የቤተመቅደስ መነሣት ስለእመቤታችን ትንሣኤ እንደ ነገረን አድርገን መተርጎም እንችላለን። እንዲህ ብለን የተረጎመነው ግን ከራሳችን ተነሥተን አይደለም ከአባቶች ትምህርት ወስደን እንጂ በ3ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት (St. Gregory Thaumaturgus ) ይህን ጥቅስ እንዲህ ይተረጉመዋል:

"በተመስጦ በዳዊት በገና ያስተማረንን ዜማ እንዘምራለን “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ” እንበል። አንተና የመቅደስህ ታቦት። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በውስጥም በውጭም በወርቅ የተሠራች የመቅደሱን መዝገብ ኹሉ የተቀበለች ታቦት ናትና።"

እንኳን አደረሳችሁ የትንሣኤውን ጌታ ያመነ ኹሉ ይነሣል እመቤታችን ደግሞ ያመነች በፅዕት ናት! (ሉቃ 1:45)
❤ 14 👍 3 🥰 1
3 September 2024
ኪ
19:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
የወልድ አምላካዊ ባሕርይ ከሥጋ ባሕርይ ጋር ተዋሕዶ አንድ ባሕርይ ከኾነ ሥላሴ በባሕርይ አንድ ናቸውና ሥላሴ ሰው ኾኑ አያስብልምን?

ይህ ጥያቄ በ5ኛው እና በ6ኛው ክፍለ ዘመን በኬልኬዶናውያን እና በኢኬልቄዶናውያን መካከል በተደጋጋሚ የሚነሳ የተዋሥኦ ርእስ ነበር። ኬልቄዶናውያን (የአሁኑ Eastern Orthodox )የሥላሴ አምላካዊ ባሕርይ ከሰውነት ባሕርይ ጋር ድንበራቸውን ጠብቀው በክርስቶስ አካል ውስጥ በመሐዋዳቸው ክርስቶስ በአምላካዊ የተለየ አካሉ ኹለቱን ባሕርያት ይዟል ሲሉ ኢኬልቄዶናውያን (የአሁኑ Oriental Orthodox) ደግሞ  የክርስቶስ ባሕርይ ከኹለት የኾነ አንድ እንጂ በኹለትነት አልቀጠለም በማለታቸው ኬልቄዶናውያን የሥላሴ ባሕርይ በምልዓት ሰው ኾኗል ብለው ያምናሉ በማለት ያሙአቸው ነበር።

ይህን ጥያቄ ለመመለስ ከኢኬቄዶናውያን ወገን እስክንድርያዊው ዮሐንስ ተአቃቢ (John Philoponus) ጥረት አድርጓል። ነገር ግን ዮሐንስ ተአቃቢ ክርስቲያን ከመኾኑ በፊት ፈላስፋ ነበርና ጥያቄውን የመለሰበት ኹኔታ ፍልስፍናው ተጽእኖ አድርጎበት ወደ ስህተት ገባ። እንደ ዮሐንስ ተአቃቢ ሃሳብ አንድ ባሕርይ (Ousia) ከparticularity (Hypostasis) ውጪ ሕልውና (existence) የለውም  ለምሳሌ ድንጋይነት የሚባል ባሕርይ ከአንድ ፊት ለፊቴ ካለ ድንጋይ ውጪ በሕልውና የለም ስለዚህም ይህ ድንጋይነት ባሕርይ ሕልው ኾኖ ያለው በዚህ ፊት ለፊቴ ባለው ድንጋይ ብቻ ነው ማለት ነው ይህ ሃሳብ በፍልስፍና አጠራር nominalism ይባላል። ዮሐንስም ይህን የፍልስፍና ሃሳቡን ሥላሴ ላይ ተጠቀመበት በሥላሴ ዘንድ ደግሞ 3 particularity ነው ያለው እርሱ ደግሞ አንዱ ባሕርይ ከparticular ውጪ ሕልውና የለውም ብሎ ስለሚያምን እያንዳንዱ የሥላሴ አካል የየራሱ ባሕርይ ሊኖረው ይገባል በማለት ደመደመ። ስለዚህም ወልድም ሰው ሲኾን ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ባሕርይ ይዞ ሰው ስለኾነ አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው አልኾኑም በማለት የኬልቄዶናውያንን ጥያቄ መለሰ።

ቤተክርስቲያናችን ግን ይህን የዮሐንስ ተአቃቢ ሃሳብ ታወግዛለች ክርስቶስ ኹለት ባሕርይ አለው የሚለውን ም*ን*ፍ*ቅና ለመራቅ 3 መለኮት ወደሚል  ም*ን*ፍ*ቅና ገብቷልና። ታድያ ቤተክርስቲያናችን የኬቄዶናውያኑን ጥያቄ እንዴት ትመልሳለች? ይህን ጥያቄ በቤተክርሲያናችን ከቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ በኋላ ታላቅ የአንድ ባሕርይ ተዋሕዶ ጠበቃ የኾነው ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ (St. Severus of Antioch) መልሶታል። እንደ ቅዱስ ሳዊሮስ ገለጻ አንድ ባሕርይ (Ousia) በሕልውና የሚታየው በparticularity ቢኾንም በዛ በአንድ particularity ብቻ ሕልው የሚኾን አይደለም ለምሳሌ የአንድ ድንጋይነት ባሕርይ በተለያዩ ቦታ ያሉ ድንጋዮች ሊጋሩት ይችላሉ ልክ የሰው ኹሉ ባሕርይ አንድ እንደኾነ። የሥላሴ አምላካዊ ባሕርይው በየአንዳንዱ particularity ውስጥ ያለ መከፋፈል ሕልው ነው ነው እንጂ እያንዳንዱ አካል የየራሱ Ousia ሊኖረው ግድ አይደለም  ነገር ግን እያንዳንዱ አካል በOuisa ሕልው ነውና የየራሱ Hypostasis አለው። ወልድም ሰው ሲኾን በHypostasis (particularity) ደረጃ አንጂ በOusia (Generality) ደረጃ ስላልኾነ ሥላሴ ሰው ኾኑ አያስብልም። ነገር ግን ኬልቄዶናውያን እንደሚሉት አንዱ የክርስቶስ አካል ውስጥ የኹለት ባሕርይ (Ousia) ተዋሕዶ ካለ የሰው ባሕርይ በሙሉ ከሥላሴ ባሕርይ ጋር ተዋሕዷል ያስብላል (ይህ ሰው ኹሉ አምላክ ኾነ ማለት ነው።) በማለት በGenerality እና particularity መካከል ያለውን መስመር ባለማስመራቸው መሳታቸውን ያስረዳቸዋል።
❤ 9 👍 2 🥰 1
11 September 2024
ኪ
12:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ሰውን ወዳጅ አንተ ሰው አድርገህ ፈጠርከኝ አንተ የኔ አገልግሎት አያስፈልግህም እኔ ግን ያንተ ጌትነት ያስፈልገኛል" (ቅዱስ ጎርጎርዮስ)

ጌታ ሆይ አንተ ብቻ ከዓለም በፊት አለህ ዘመናትን ፈጠርህ እነርሱ ኹሉ ያልፋሉ አንተ ግን ትኖራለህ ፤ አንተ ማንም ምንም አያስፈልግህም አንተ ያው አንተ ነህ ፤ እኔ ግን ያለ አንተ ምንም ነኝ የዓመቱን አክሊል በቸርነትህ የምትባርክ ሆይ ባርከኝ!

እንኳን አደረሳችሁ አዲሱን ዓመት ለኢየሱስ!
🥰 21 👍 2 ❤ 1
24 September 2024
ኪ
12:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
ተዘከሩ ዕለተ ሞትክሙ

ይህ ዓለም ጊዜያዊ ነው ፣ ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ ነገር ኹሉ ከመኖር ወደ አለመኖር ይመለሳል በእግዚአብሔር ጸጋ ወደ ህልውና መጣ እንዲሁ የሚያኖረውም የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እግዚአብሔር የዓለም ፈጣሪ ብቻ ሳይኾን መጋቢም ጭምር ነውና።

እንደ ሳይንሱ ማብራርያ በsecond law of thermodynamics መሠረት ዝግ system ውስጥ entropy (measure of disorder) እየጨመረ ይሄዳል ከውጪ ተጨማሪ energy የሚሰጠው አካል ከሌለ ደግሞ መጨረሻው inevitable disorder (የማይቀር ምስቅልቅሎሽ) ይኾናል። ለምሳሌ 52 የካርታ ካርዶችን ይዘን በዐየር ላይ ብንበትናቸው  መሬት ላይ ምስቅልቅል ይፈጥራሉ ካርታዎቹን መልሰን እንሰብስብ ብንል መሰብሰብ ብንችልም እንደመበተን ቀላል አይደለም ፤ ለመበተን ዓየር ላይ መወርወር ብቻ ነው የሚጠበቅብን ፣ ለመሰብሰብ ግን አንድ በአንድ ከምድር ላይ መልቀም ይኖርብናል። Disorder መፍጠር ቀላል ነው Order መፍጠር ግን ከባድ ነው ለምን? ልዩነቱ entropy ነው entropy ኹሌ ይጨምራል entropy ደግሞ ነገሮችን ከOrder ወደ disorder የሚመራ ነው ስለዚህም Order መፍጠር ከፈለግን entropyን ሚቋቋም ኃይል ያስፈልጋል። ከውጪ entropyን የሚቋቋም ኃይል ከሌለስ? ኹሉም ነገር ማለቂያ ወደሌለው ምስቅልቅሎሽ (disorder) ያመራና መጨረሻው ጥፋት ይኾናል። ከዓለም (Universe) ውጪ ደግሞ ያለው ምንምነት (nothigness) ስለኾነ ዓለም ማቆም ወደ ማይችለው ጥፋት እያመራ ነው። ጥፋቱ በምን ሊኾን እንደሚችል ግን ከመላምት በቀር ሳይንቲስቶች እርግጠኛ አይደሉም ምናልባት Black hole, heat death , big crunch አይታወቅም የሚታወቀው ነገር ቢኖር ግን The inevitable end (የማይቀረው ኅልቀት) ነው።

ወደ ምስቅልቅሎሽ እየሄደ ባለ ዓለም ውስጥ ከዓለሙ ውጪ ኖሮ entropyን መቋቋም የሚችል ኃይል ያለው ብቸኛው አካል ክርስቶስ ነው "እርሱ ብቻ የማይሞት ነውና"። (1ኛ ጢሞ 6፥16) ኹሉም ነገር ያልቃል ፣ ኹሉም ነገር ይጠፋል ፣ ኹሉም ነገር ይሞታል እኛ ግን የማይቀረውን ነገር ማሰብ አንፈልግም ወደ ጥፋት እየሄደ ባለ ዓለም ላይ ስንብከነከን እራሳችንን እናታልላለን።

"ዓለሙኒ ኀላፊ ፍትወቱኒ ኀላፊ እስመ ኩሉ ኀላፊ ውእቱ - ዓለሙም ኀላፊ ነው ምኞቱም ኀላፊ ነው ኹሉ ነገርም ኀላፊ ነውና" (መጽሐፈ ቅዳሴ)

ተዘከሩ ዕለተ ሞትክሙ - የሞታችሁን ቀን አስቡ!
❤ 16 👍 1 🥰 1
26 September 2024
ኪ
10:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ይስሐቅ ለመሥዋዕትነት ያረፈበትን እንጨት ስናስብ መስቀልን እናስብ ። እሳቱን ስንመለከትም ፍቅርን እናስተውል። ‘ሳቤቅ’ በሚባለው ተክል ላይ በኹለት ቀንዶች የተሰቀለውን በግም ስንመለከት። በመስቀል ላይ በኹለት እጆቹ የተሰቀለውን የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስን እንመልከት። ሳቤቅ ትርጉሙ "ይቅርታ" ነው የሽማግሌውን ልጅ ከመታረድ አድኗልና። እርሱም የዓለሙን ኃጢአት ይቅር የሚል ሕይወትንም የሚሰጥ የመስቀል ምሳሌው ነው። በዕፀ ሳቤቅ ላይ የተሰቀለው በግ በምስጢር ይስሐቅን ብቻውን ዋጀው። የእግዚአብሔር በግ ግን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ዓለምን ኹሉ ከሞትና ከሲኦል አዳነ።"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

በመስቀሉ ኮነ ቤዛ ለኩሉ ዓለም - በመስቀሉ ለዓለሙ ኹሉ ቤዛ ኾነ! እንኳን አደረሳችሁ።
❤ 20 👍 2 🥰 1 👏 1
3 October 2024
ኪ
13:59
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገረ ድኅነት (Soteriology)

ድኅነት ምንድነው?

ድኅነት ማለት የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ዓላማ የሚያሳካበት መንገድ ነው።
ፍጥረት ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ ነው። ካላመኖር ወደ መኖር የመጣ ማነኛውም ነገር በመኖር ውስጥ የሚያቆየው “sustainer” ያስፈልገዋል። 
በ5ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ እንዲህ ይጽፋል “ አዳም ፣ ሔዋንና አጠቃላይ የሰው ልጅ ሰውነት ሲፈጠር በጊዜ ሒደት የሚለወጥ በመጨረሻም በስብሶ የሚሞት ነው ይህ እንዳይሆን ግን አምላካዊ ጸጋ ይጠብቃቸው ነበር። አዳም በበደለ ጊዜ ግን ይህን አምላካዊ ጸጋ አጣ” (Yonatan Moss: Incorruptible bodies p.32)

የሰው ልጅ ሲፈጠር በባሕርይዉ ኢመዋቲ አልነበርም ነገር ግን በባሕርይ ኢመዋቲ እስኪኾን ድረስ እንዳይሞት በአምላካዊ ጸጋ ሥር (State of divine grace) ነበር በተጨማሪም ኢመዋቲ የመሆን potential ነበረው። 

በ2ኛው ክፍለ ዘመን ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያ ይህን ሲያጸና እንዲህ ይላል “የሰው ልጅ በባሕርይ መዋቲም ኢመዋቲም አልነበረም። ከመጀመሪያውኑ ኢመዋቲ አድርጎት ቢኾን አምላክ ባደረገው ነበር። መጀመርያውኑ መዋቲ አድርጎት ቢኾን ደግሞ የሞቱ ምክንያት አምላክ በኾነ ነበር። ነገር ግን ኹለቱንም የመኾን አቅም ነበረው። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ቢጠብቅ ኢመዋቲነትን በስጦታ ያገኝና አምላክ በኾነ ነበር” (Theophilus of Antioch to Autolycus 2:27)

አዳም ከውድቀት በፊት በገነት ሳለ ወደ አምላክነት እየሔደ ያለ፤ ኢመዋቲ የመኾን አቅም ያለው ፣ በአምላካዊ ጸጋ ስር ያለ ፍጡር እንጂ ድኅነቱን የጨረሰ አልነበረም። ትእዛዙን ተላልፎ በወደቀ ጊዜ ይህን አምላካዊ ጸጋ በማጣቱ ወደ አምላካዊ ድኅነት የመሔድ አቅሙን አጣ መዋቲነቱም ሰለጠነበት።

ድኅነት ማለት የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ዓላማ ማሳከት እስከኾነ ድረስ የሚጀምረው በአምላካዊ ጸጋ ስር (state of grace) በመኾን ነው። ፍጻሜው ደግሞ ከመለኮት ባሕርይ ተሳትፎ እንደ አምላክ ኢመዋቲ ( አምላክ) በመኾን ነው። 

ስለዚህም ድኅነት 2 ክፍል አለው እንላለን፡ አንደኛው አምላካዊ ጸጋ ስር መግባት (Initial salvation) ሲኾን ኹለተኛው ከአምላካዊ ባሕርይ መሳተፍ (Theosis) ነው።
በአምላካዊ ጸጋ ስር መግባት በአምነት ብቻ ይጀምራል ምሥጢራትን በመሳተፍ በጸጋ ላይ ጸጋ እየጨመረ “መለኮታዊ ባሕርይን ወደ መሳተፍ” ያደርሳል። (1ኛ ጴጥሮስ 1፡4)
በአምላካዊ ጸጋ ስር ለመግባት እኛ ከራሳችን ምንም ልንሠራ አንችልም እንዲሁ በጸጋ እንድናለን እንጂ። አዳም ተፈጥሮ ወደ ገነት state of grace ውስጥ ለመግባት ምንም አላደረገም ኹሉም ከአምላክ የተሰጠው ስጦታ ነው እንጂ። እኛም ይህን ስጦታ በእምነት ከመቀበል በቀር ጸጋው የተገባን እንድንኾን ምንም ልናደርግ አንችልም ስለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም” (ኤፌ 2፡8-9) ሲል አጽንኦት ሰጥቶ የተናገረው። 

በ4ኛው ክፍለ ዘመን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን እንዲህ ያብራራዋል “ ‘በጸጋው ድናችኋል’ ይላል በተሰጠን ነገር እራሳችንን ከመጠን በላይ ከፍ እንዳናደርግ “ በጸጋው ድናችኋል” በማለት እንዴት ወደ ታች እንደሚያወረደን አያችሁን? “ጸጋው በእምነት አድኖአቹአል” በማለት ነጻ ፈቃዳችን እንዳይጠፋ የእኛን ሥራ እምነትን ጨመረ። ነገር ግን እርሱንም መልሶ አጠፋው “ከእናንተ አይደለም” በማለት እምነት ራሱ ከእኛ አይደለምና። ወደ እኛ ወርዶ ባይጠራን ኖሮ እንዴት እናምን ነበር? “ካልሰሙ እንዴት ያምናሉ” ብሏልና (ሮሜ 10፡14) እምነት ራሱ ከእኛ አይደለም። “ (John Chrysostom homily 2 to Ephesians)

ጠላቶቹ ሳለን የወደደን ፣እኛ ጠልተነው በራሳችን መንገድ ስንሔድ ወደኛ ወርዶ የታረቀን እርሱ ራሱ ነውና ወደ ድኅነት ፣ ወደ ገነት የተመለስነው በእርሱ እንጂ የራሳችን ጥረት አንዳች የለበትም። ይህ የመጀመሪያው ድኅነት ነው።

ወደ አምላካዊ ጸጋ ገባን ማለት ድኅነትን ፈጸምን ማለት ግን አይደለም ወደ መጀመሪያው ሰው አዳም ወደ state of grace ተመለስን ማለት እንጂ ። አንድ ጊዜ በእምነት ወደ ጸጋ ገባን ማለትም ኹሉም አበቃ ማለት አይደለም “በጸጋ ላይ ጸጋ” (ዮሐ 1፡16) እየጨመርን የመለኮት ባሕርይ ተካፋይ እንክንኾን Theosis ላይ እንክንደርስ እንወጣለን እንጂ። 

በ4ኛው ክፍለ ዘመን ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘሂፖ እንዲህ ይላል “ መጀመሪያ ጸጋን ተቀበልን ከዛም በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀበልን። የመጀመሪያው ጸጋ እምነት ነው በነጻ ተሰጥቶናልና። ኹለተኛው በጸጋ ላይ ጸጋ ደግሞ የዘለዓለም ሕይወት ነው። እምነት ጥሩ ጸጋ ነው የዘለዓለም ሕይወት ደግሞ በጸጋ ላይ ጸጋ ነው። ... ከኹሉም በላይ ትልቁ ጸጋ የሰው ልጅ በዘለዓለማዊው የእግዚአብሔር ቃል በኩል ከአምላክ ጋር በአንድ አካል ሲዋሐድ ነው” (Augustine of Hippo Tractate 3 on Gospel of John)

በእምነት የጀመረው ጸጋ ከአምላክ ጋር እስክንዋሐድ ድረስ እየጨመረ ይሔዳል አንጂ አንድ ጊዜ ብቻ ተሰጥቶ የሚያበቃ አይደለም ጸጋ ይጨራል! ይህን በእምነት የጀመርነውን ጸጋ በጥምቀት የበለጠው ጸጋ ይጨመርልናል ፣ በቅዱስ ቁርባን ከአምላክ ጋር እየተዋሐድን ተጨማሪ ፍጹም ጸጋ እየተቀበልን ፣ ኃጢአት ስንሠራ በንስሐ እያደስን እንዲህ እያልን በጸጋ ላይ ጸጋ እየጨመርን የተፈጠርንበትን አላማ (አምላክነትን ፣ ኢመዋቲነትን) እስክናገኝ ድረስ እንቀጥላለን። ለዚህ ደግሞ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምናገኘው ጸጋ እኛም መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን እንዲሠራ ምላሽ በመስጠት በሥራችን እያጸናነው እንሔዳለን።

በ2ኛው ክፍለ ዘመን ቅዱስ አግናጥዮስ ዘንጾኪያ እንዲህ ይጽፋል “ ጥምቀትህ ጋሻ ፣ እምነትህ ራስ ቁር ፣ በጎ አድራጎትህ ጦር ፣ ትዕግስትህ የደረት መከላከያ ይኹንህ። ለአንተ የሚገባህን እንቅትቀበል ሥራህ ኹሉ ተቀማጭ ይኹንህ” (Ignatius of Antioch letter to Polycarp,6)

የሰው ልጅ የተፈጠረው ከአምላክ ጋር እንዲሳተፍ ኢመዋቲ እንዲኾን ነበር ይህ ግን ተፈጻሚ የሚኾነው ትዕዛዙን እስከጠበቀ ድረስ ነው። አሁንም ክርስቶስ ሰው ኾኖ እንዲሁ በጸጋ ድኅነትን ካቀዳጀው በኋላ በጸጋ ውስጥ ኾኖ ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ኢመዋቲ እስኪኾን ድረስ ድኅነቱ አያበቃም።
በ2ኛው ከፍለ ዘመን ቅዱስ ዮስጢኖስ ሰማዕት እንዲህ ይጽፋል “ መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን ሰው ይወቅሳል ትዕዛዙን እስከጠበቀ ድረስ አምላክን መስሎ ከመከራ እና ከሞት ነጻ ኾኖ ተፈጥሯልና… ሰዎች ኹሉ አማልክት ለመኾንና የልዑል ልጆች የመባል ኃይልን ለማግኘት የተገቡ ናቸው ስለዚህም እንደ አዳምና ሔዋን እያንዳንዱ በየራሱ ይኮነናል። (Justin Martyr dialogue with Trypho 124.)

በመጨረሻም በ2ኛው ክፍለ ዘመን በነበረው ቅዱስ ሄሬኔዎስ ዘልዮን ቃል ነገራችንን እንጨርሳለን “የእግዚአብሔር ቃል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወሰን ከሌለው ፍቅሩ የተነሣ ወደ እርሱነቱ ያወጣን ዘንድ ፍጹም እኛን ኾነ” (Against heresies 5.)

Salvation upto Theosis! ይቀጥላል...
❤ 23 👍 2 🔥 2 🥰 1
12 October 2024
ኪ
11:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቶስ ጽጌ ጸአዳ ወቀይሕ
ነጭና ቀይ አበባ ክርስቶስ

“ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።”
— መኃልየ. 5፥10
🥰 24 ❤ 4 👍 1
31 October 2024
ኪ
09:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሔዋን ገና ድንግል ሳለች የዲያብሎስ ቃል የሞትን ሕንፃ ለማቆም ሾልኮ ገባ። እንደዚሁ የእግዚአብሔር ቃል የሕይወት መሠረት ይኾን ዘንድ በድንግል በኩል መጣ። በዚሁ ጾታ ወድቆ የነበረው በዛው ጾታ ለድኅነት እንደገና ተሠራ። ሔዋን እባቡን አመነች ማርያም ግን ገብርኤልን አመነች። አንዷ በማመን ያጠፋችውን፣ ኹለተኛዋ በማመንዋ አቀናችው።” (The Flesh of Christ 17:4 [A.D. 210].)


ሊቁ ጠርጡለስ ዘቅርጣግና (Tertulian of Carthage)

መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ ❤️
❤ 27 👍 3 🥰 1
6 November 2024
ኪ
09:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ኦ ወልድ ዋሕድ፣ እግዚአብሔር የወደድከን ቃል ሆይ፣ ከፍቅሩ የተነሣ ከዘለዓለም ሞት ሊበዠን ወደደ።

በመቤዠቱ መንገድ ላይም ሞት ስለነበር ከፍቅሩ የተነሣ በዚሁ መንገድ ሊያልፍበት ወደደ። ስለዚህም የኃጢአታችንን ቅጣት ይሸከም ዘንድ መስቀል ላይ ወጣ።

የበደልነው እኛ ነን፤ መከራን የተቀበለ እርሱ ነው።

በኃጢአት ምክንያት ለመለኮታዊ ፍትሕ ባለ ዕዳ የኾነው እኛ ነን፤ ስለእኛ ዕዳውን የከፈለው ግን እርሱ ነው።

ስለ እኛ ከደስታ ይልቅ መከራን፣ ከዕረፍት ይልቅ ድካምን፣ከክብር ይልቅ መናቅን፣ ኪሩቤል ከሚሸከሙት ዙፋንም ይልቅ መስቀልን መረጠ።

ከኃጢአት እስራት ነጻ ያወጣን ዘንድ በገመድ ለመታሰር እራሱን አሳልፎ ሰጠ። እኛን ከፍ ያደርገን ዘንድ እርሱ ዝቅ አለ። ያጠግበን ዘንድ እርሱ ተራበ፤ ጥማችንንም ይቆርጥ ዘንድ ተጠማ።

የእርሱን የጽድቅ ልብስ ያለብሰንም ዘንድ እርቃኑን መስቀል ላይ ዋለ። ወደ እርሱ ገብተን የጸጋው ዙፋን ላይም እንቀመጥ ዘንድ ጎኑን በጦር ይወጋ ዘንድ ከፈተ።

በእውነት ሞተ፤ በመቃብርም ተቀበረ፤ እንዲሁም ከኃጢአት ሞት አስነሥቶ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጠን ዘንድ ተነሣ።

ኦ አምላኬ ራስህን የወጉት እሾኾች የእኔ ኃጢአቶች ናቸው፤ በዚህ ዓለም ከንቱ ደስታ ተደስቼ ልብህን ያሳዘንኩት እኔ ነኝ።

ኦ አምላኬ ፣ መድኃኒቴ ይህ የምትሔድበት ወደ ሞት የሚያደርሰው መንገድ ምንድነው?

ይህ በትከሻህ የተሸከምከው ምንድነው? ይህ ስለእኔ የተሸከምከው የውርደት መስቀል ነው።

ኦ ቤዛዬ ሆይ ይህ ምንድነው? ለእዚህ ፈቃደኛ እንድትኾን ያደረገህ ምንድነው?

ታላቁ ይጠላልን? ክቡሩ መከራን ይቀበላልን? ልዑሉ ይዋረዳልን? ኦ የፍቅርህ ታላቅነት።

አዎ ስለ እኔ ይህን ኹሉ መከራ እንትታገስ ያደረህ የፍቅርህ ታላቅነት ነው።

ኦ አምላኬ አመሰግንሃለሁ፤ መላእክቶችህ ከፍጥረታትህ ኹሉ ጋር ስለእኔ ምስጋናን ያቀርቡልሃል ፤ እኔ ለፍቅርህ የሚመጥን ምስጋናን ማቅረብ አይቻለኝምና! ከዚህ የሚበልጥ ፍቅርን አይተን እናውቃለን?

ኦ ነፍሴ ሆይ በሩህሩሁ ቤዛዬ ላይ ይህን ኹሉ መከራ ስላደረሰው ኃጢአትሽ እዘኚ ። ቁስሎቹን በፊትሽ ሳዪ የጠላት ቁጣ ሲነሳብሽም በእርሱ ተስፋ አድርጊ።

ኦ አዳኜ ሆይ መከራህን ሀብቴ ፣ የእሾህ አክሊልህን ክብሬ፣ ኃዘንህን ደስታዬ፣ ምሬትህን ማጣፈጫዬ፣ ደምህን ሕይወቴ ፣ ፍቅርህንም ኩራቴና ማመስገኛዬ አደርግ ዘንድ እርዳኝ።

ኦ ስለ ኃጢታችን የቆስልህ ፣ በቁስልህም የተፈወስን ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማሕየዊ በኾነው መለኮታዊ ፍቅህ አቁስለኝ። ኦ ትቤዠኝና ሕይወትን ትሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ሞትን የተቀበልከው ሆይ በመስቀልህ ደም ከኃጢአቴ አንጻኝ፣ በፍቅርህም አጽናናኝ።

ኦ እውነተኛ የወይን ግንድ የእኔ ውድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንደ ደረቀ ተክል አካል ካየኸኝ በጸጋህ ዘይት አለስልሰኝ ሕያው እንደኾነ ቅርንጫፍም በአንተ አጽናኝ። " (Coptic Fraction to the Only Begotten Son )

ኦ ወልድ ዋሕድ መድኃኔዓለም ሆይ ሥራህ ድንቅ ነው ❤️
❤ 26 🥰 5 👍 4
7 November 2024
ኪ
14:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለሕይወት እንጠይቅ

"የዘለዓለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?"ይህን ጥያቄ ጌታን የጠየቀው አንድ ሃብታም ወጣት ነው። ይህ ወጣት የጥያቄውን መልስ ባይተገብረውም የጠየቀው ጥያቄ ግን በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው። እኛ የሰው ልጆች የተፈጠርነው ለሕይወት ነው ለሕይወት ተፈጥረን ሳለ ግን በዙሪአችን ባሉ distraction ተስበን ዋና ዓላማችንን ችላ እያልን ነው። ክርስቶስ የሞተው በእርሱ ለዘለዓለም እንድንኖር ነው ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ክርስቲያን የኾነውም ከክርስቶስ ጋር ለዘለዓለም ለመኖር ነው። አብዛኞቻን ግን ክርስቲያን የኾነው በክርስቶስ ለመኖር ሳይኾን ነፍስ ካወቅን ጀምሮ እራሳችንን በክርስትና ውስጥ ስላገኘነው ነው። ስለዚህም የምንጠይቃቸው ጥያቄዎችም ለሕይወት የሚኾኑ አይደሉም። "በሚካኤል ቀን ልብስ ይታጠባል?" ፣ "አሳማ ይበላል?" ፣ " በሰንበት ቡና ይወቀጣል?"፣ " የሙስሊም ሥጋ የበላ ሰው ቄደር ይጠመቃል?" እያልን ለድኅነት እንኳን ረብ የሌላቸው ጥያቄዎች ላይ ጊዜ እናጠፋለን።

እንዲሁም ልክ ለመንጻት ሥርዓት ብቻ እንደሚጨነቁ ፈሪሳውያን ሰውን በየእያንዳንዱ ነገሮች እያሳቀቅን ከክርስቶስ እናርቃለን እንደው በጌታ "በበዓል ቀን ወፍጮ ፈጨህ ፣ ሥራ ሠራህ"፣ "የአርሴማን ጸበል ተጠምቃ ቡና ጠጣች" ፣ " በማርያም ቀን ልብስ አጠብክ" ፣ " በወር አበባ ላይ ኾና ጸበል ጠጣች" እያሉ ክርስቲያኑን ማሳቀቅ ተገቢ ነው? ይህ በክርስትና ውስጥ የተደበቀ ፈሪሳዊነት ነው! ክርስቶስ አሁን ቢመጣ ኖሮ "ሰንበት ለሰው ተሠራች እንጂ ሰው ለሰንበት አልተሠራም" ብሎ ፈሪሳውያንን እንደ ወቀሰ አንደኛ ተወቃሾች እኛ ነበርን።

ክርስቲያን የኾነው በክርስቶስ የዘለዓለምን ሕይወት እናገኝ ዘንድ ነው ስለዚህ የኹል ጊዜ ጥያቄያችን "ወደ ክርስቶስ እንዴት ልቅረብ?" ፣ "የዘለዓለም ሕይወትን እንዴት ላግኝ?" ይኹን ለሕይወት እንጠይቅ፤ ፈሪሳዊነት ከመካከላችን ይውጣ!
❤ 32 👍 6 🙏 4 🥰 1
12 November 2024
ኪ
11:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
በእንተ ማር ይስሐቅ ሶርያዊ (St. Isaac of Nineveh)

ማር ይስሐቅ (ማር ማለት በሱርስት ቋንቋ ቅዱስ ማለት ነው) በ7ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ በምንኩስና ላይ በጻፋቸው ጽሑፎቹ በዓለማቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ያለ ልዩነት  በቅድስና የሚታወቅ ታላቅ አባት ነው (በOriental and Eastern Orthodox, በCatholic , በAssrian Church of the East , በ Ancient Church of the East)።  በእነዚህ ኹሉ አብያተ ክርስቲያናት ተወዳጅ ያደረገው በምንኩስና ላይ የጻፋቸው ጽሑፎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት በማግኘታቸው ነው። እነዚህ ሥራዎች Ascetical Homilies of Isaac the Syrian ሲባሉ በኢትዮጵያም ከሦስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት ውስጥ አንዱ ኾኖ በጉባኤ ቤት ማር ይስሐቅ በመባል   ይታወቃል።

ታድያ ይህ አባት በቤተክርስቲያን ደረጃ የነበረባት የእኛዋ Oriental Orthodox ሳይኾን አሁን ላይ ወደ ብዙ ቦታ የተከካፈለችው ብዙ ጊዜ በንስጥሮሳዊነት በምትታማዋ የጥንቷ Church of the East ውስጥ ነው። (ይህቺ ቤተክርሲያን አሁን ላይ ብዙ ቦታ ተከፋፍላች እንጂ የለችም ብዙ ሰው Church of the Eastንና Assyrian Church of the Eastን አንድ አድርጎ ያስባል ነገር ግን Assyrian Church of the East , የ17ተኛው ክፍለ ዘመን  የChurch of the East ክፍልፋይ ውጤት ናት እንጂ አንድ አይደሉም። )

Church of the East , የፋርስ ቤተክርስቲያን (Persian Church) ስትባል ጉባኤ ኤፌሶን ከመደረጉ ከ7 ዓመታት በፊት በ424 ዓ.እ ነው ከሮማ ቤተክርስቲያን እራሷን የለየችው። ይህ መለያየትም የፖለቲካ ውጤት ነው እንጂ የሃይማኖት አይደለም  ሮምና ፋርስ ብዙ ጊዜ ወደ ጦርነት የሚገቡ እርስ በእርስ ጠላቶች በመኾናቸው በኹለቱ አብያተክርስቲያናት መካከል ግኑኝነቱን አሻክሮታል ከዚህ በተጨማሪ የቋንቋ ልዩነትም ነበር በምስራቅ ያለችው የሮሟ ቤተክርስቲያን በዋነኛነት ግሪክ ተናጋሪ ስትኾን ፣ የፋርሷ ቤተክርስቲያን ግን ሱርስት ( Syriac) ተናጋሪ ናት። በዚህ መለያየት ምክንያት በሮሟ ቤተክርቲያን 3ተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በ431 ዓ.እ በኤፌሶን ሲጠራ የፋርሷ ቤተክርስቲያን መሳተፍ አልቻለችም። በዚህ ጉባኤ ንስጥሮስ ሲወገዝ በእርሱ መወገዝ ያልተስማሙ ሰዎች ከሮም ወተው ወደ ፋርስ በመሔድ የቴዎዶሮስ ዘመፕሶስትያን (Theodore of Mopsuestia) ትምህርት ሳያስፋፉ አልቀረም። በ7ተኛው ክፍለ ዘመን ከፋርሷ ቤተክርስቲያን የተነሣው Babai the Great , (ይሑፎቹ ላይ የመፕሶስቲያው ቴዎዶር ተጽእኖ ይታይበታል) Book of Union በተባለ መጽሐፉ ክርስቶስ በአንድ Prosopa ያለ መለያየት 2 Qnoma አሉት በማለት ነገረ ክርስቶስን አብራራ (Prosopa እና Qnoma የሱርስት ቃላት ሲኾኑ Prosopa እኔ ባይነት ያለው አካል ነው፣ Qnoma ደግሞ ባሕርይ ነው።) ይህች የፋርስ ቤተክርስቲያንም የእርሱን አስተምህሮ በ7ተኛው ክፍለ ዘመን Official አስተምህሮዋ አድርጋዋ ተቀብላለች።

ታድያ ማር ይስሐቅም ከዚህች ቤተክርስቲያን ሥር በዚህ ነገር ክርስቶስ ላይ ውዝግብ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ነው የነነዌ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ የተሾመው። ብዙ ጊዜ ከእኛ ቤተክርስቲያን ውጪ ኾኖ ሳለ እንዴት በእኛ ቤተክርስቲያን በቅድስና ሊጠራ ቻለ ተብሎ ሲጠየቅ ይህቺ ቤተክርቲያን በነገረ ክርስቶስ ላይ ውዝግብ ላይ ሳለች እርሱ ኦርቶዶክሳዊውን ትምህርት በመያዙ ነው ተብሎ ይመለሳል። ነገር ግን ይህ መልስ አጥጋቢ አይደለም በእኛ ቤተክርስቲያን ማር ስይሐቅ ተብሎ በሚጠራው መጽሐፍ ውስጥ አዎ ምንም አይነት ም*ቅና የለም ሙሉ በሙሉ ኦርቶዶክሳዊ ነው፤ ነገር ግን የማር ይስሐቅ ሥራዎች በሙሉ አልተተረጎሙም ነበር።  በቅርቡ በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጠመቀመው በሶርያ ጥናቶች (Syriac Studies) ላይ እውቅ ምሁር Dr. Sebastian Brock ያልተተረጎሙ የማር ይስሐቅ ሥራዎችን በማግኘት ማሳተም ችሏል ይህ ሥራ "Isaac of Nineveh (Isaac the Syrian): The Second Part, Chapters 4-41 (Corpus Scriptorum Christianorum Orientalium" በመባል ይታወቃል በዚህ ሥራ ላይም አንዳንድ ንስጥሮሳዊ ሃሳቦች እና ምቅናዎች ይገኛሉ ለአብነት ይህን ላሳይ፡

"ኹሉም ነገር የሚነገርለት እርሱ [መለኮት] በእርሱ [ትስብዕት ] ላይ አደረበት፤ መለኮታዊ ክብሩን እና ሥልጣኑንም ሰጠው... መላእክትም እንዲሰግዱለት አደረገ ... ከእርሱ ጋር ያለ ልዩነት እንዲመለክም አደረገው፤ ይህም ጌታ የኾነው ሰውና መለኮት በአንድነት እንዲመለኩ ነው፤ ኹለቱ ባሕርያት የክብር መለያየት ሳይኖርባቸው በመጠባበቅ አሉና" (H Alfeyev, The Spiritual World of Isaac the Syrian, Cistercian Publications, Michigan, 2000, pp. 54-5)

ይህ ፍጹም ንስጥሮሳዊ አስተምህሮ ነው ቅዱስ ቄርሎስ በAnathema 8 ላይ "ማንም ሰው በቃል የተነሣው ሰው ፤ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በአንድነት ይመለካል የሚል ቢኖር የተወገዘ ይኹን" ሲል ያወግዛል። Father Tadros Malatyም በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ እንዲህ በማለት "ይስሐቅ መስቀል የእግዚአብሔር ማደርያ ለኾነው ሰው ምሳሌው ነው ያላል፤ መስቀል "መለኮት ባደረበት ሰው" ስም የተሠራ ነው በማለት የክርስቶስን ሰውነት የመለኮቱ ማደርያ ልብስ ያደርገዋል።(Part II / 11-24) ይህ ጽሑፍ የሚያሳየው የይስሐቅ ነገረ ክርስቶስ ንስጥሮሳዊ እንደኾነ ነው" ( Fr. Tadros Malaty, A PANORAMIC VIEW OF PATRISTICS)

ይህን ስጽፍ ማር ይስሐቅ ቅዱስ አይደለም ለማለት አለመኾኑን ልብ ይበሉልኝ። ምክንያቱም ቅዱሳን ኹል ጊዜ ፍጹም ትምህርት የላቸውም ሰው እንደመኾናቸው አንድ አንድ አስተምህሮ ሊስቱ ይችላሉ፤ ማር ይስሐቅም የነበረበት ቤተክርስቲያን ከሌላው ዓለም ተገላ የዓለም አቀፍ ጉባኤ እንኳን መሳተፍ ያልቻለች ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለኾነ ባልተሳተፈበት ጉባኤ አተስተምህሮ ልንወቅሰው አንችልም።
👍 17 ❤ 4 🥰 1
15 November 2024
ኪ
11:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
"አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም።( ገላትያ 6፡7) ነገር ግን የመርቅያን አምላክ ይዘበትበታል፤ እንዴት መቆጣትና መበቀል እንዳለበት አያውቅምና" (ሊቁ ጠርጡሊያኖስ ዘቅርጣግና) 😂
ሊቁ ይሄን ያለው መርቅያን የብሉይ ኪዳኑ አምላክ ክፉ አምላክ ነው በብሉይ ከመጠን በላይ ቁጣውን ሲያሳይና ሲቀጣ እናየዋለንና ከሐዲስ ኪዳኑ አምላክ ጋር አንድ አይደለም በማለቱ ነው። ስለዚህም የመርቅያን የሐዲስ ኪዳኑ "ደግ" አምላክ ቁጣውን ማሳየት እና መቅጣት እንኳን የማይችል ደካማ አማላክ ነው እና ይዘበትበታል ይለናል ጠርጡሊያኖስ ቀልድ አዋቂ አይደል እንዴ 😆
😁 27 🤣 7 🥰 4 👍 3
21 November 2024
ኪ
17:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
ስንፈጠር Vegan ነን ፤ በመጨረሻው ዘመንም ወደ Vegaንነት እንመለሳለን

“አሁን ላይ ብዙ አውሬዎች ፍሬ እንደማይበሉ አልነበረም፤ ያኔ ግን ነብር ምን ፍሬ ይበላ ነበር? አንበሳውን የሚያጠነክረው የትኛው ፍሬ ነው? ነገር ግን እነዚህ ፍጥረታት ለተፈጥሮ ሕግጋት ሲገዙ ፍሬ በልተዋል። [የመጀመሪያው] ሰው አኗኗሩን ሲቀይር እና በእርሱ ላይ የተጣለውን ገደብ ባሻረ ጊዜ፣ ጌታ፣ ከጥፋት ውሃ በኋላ፣ የሰው ልጆች አባካኝ መኾናቸውን አውቆ ፣ ኹሉንም ምግቦች እንዲጠቀሙ ፈቀደላቸው፡- “ኹሉንም ምግብ እንደ እፅዋት ይኹኑላችሁ። ” በማለት ተናግሯል። [የሰው ልጆች] ይህ ስለተፈቀደላቸው፣ ሌሎቹ እንስሳም [ሥጋ] የመብላት ነፃነት አግኝተዋል። ስለዚህ አንበሳው [አሁን] ሥጋ በላ ኾነ፣ አሞራም ሥጋን ይፈልጋል።

ያኔ ፍጥረት ገና አልተከፋፈለም ነበር ኹሉም ነገር አዲስ ነው። አዳኞች አያድኑም ሰዎች ገና ሥጋ መብላት አልጀመሩምና። አውሬዎችም ሌሎች እንስሳትን አይበሉም ነበር ገና ሥጋ ተመጋቢ አልነበሩምና ... የመጀመሪው ፍጥረት እንዲህ ነበር በመጨረሻው ዘመንም ፍጥረት ወደ ጥንቱ ይመለሳል።

ሰዎች ጠላትነትን በመተው ወደ ጥንት ፍጥረታቸው ይመለሳሉ ... የዕለት ተለት ጭንቀትን ባርነትን በመተው ወደ ደስታ ሕይወት ይመለሳሉ፤ ወደዛ በሥጋ ምኞቶች ወደ አልታሰረ ሕይወት ፤ ወደ እግዚአብሔር የቀረበ ከመላእክት ጋር ወደ ምንሳተፍበት ሕይወት። " (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፡ On the Origin of Man)

ሥጋ መብላት የኃጢአት ውጤት እንጂ የባሕርይ አይደለም፤ እንደ ጥንተ ፍጥረታችን እንኖር ዘንድ በጾም ወራት vegan በመኾን የገነት ኑሮን እንለማመዳለን። የጾመ ነቢያት ማሟሟቂያ 😁
❤ 76 👍 27 😁 15 👎 2 🔥 2 🥰 1
24 November 2024
ኪ
15:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጾመ ነቢያትን ዛሬ ይዘናል ከነቢያት ጋር የነቢያት ኹሉ ነቢይ የአዳኛችን የኢየሱስን መወለድ በትስፋ በፊታችን ሥለን በአካል እንቀበለው ዘንድ ከነቢያቱ ጋር እንጾማለን።

ብዙዎች ጻድቃን ነቢያት ሊያዩት ወደው ያላዩት ሊሰሙትም ወደው ያልሰሙትን እኛ ግን ተወልዶ በበረት አየነው ፣ በግርግም እንደ ሕፃናትም ሲያለቅስ ሰማነው ፤ የነቢያት ኹሉ ማኅተም ክርስቶስን ተቀበልነው ስለዚህም የነቢያት ተስፋቸው በክርስቶስ ተፈጸመ ስንል በግርግም ያየነውን ጌታ ተስፋ አድርግን እንጾማለን እንኳን አደረሳችሁ!
❤ 113 👍 15 🥰 10
25 November 2024
ኪ
16:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
የውጣ ቀዳሜ ስሙ ለመድኃኒነ

የውጣ (Iota) በግሪክ አልፋቤት ዘጠነኛው ፊደል ፣ በኮፕቲክ ደግሞ አሥረኛው ፊደል ነው። የጌታ ኢየሱስ ስም ሲጻፍ የመጀመሪያው ፊደል Iota ነው 'Ιησούς' in greek 'Ⲓⲏⲥⲟⲩⲥ' in coptic. ይህን Iota ነው ግእዙ የውጣ የሚለው።

ኢየሱስ የሚለው ስም ከግሪኩ የተተረጎመ ሲኾን በOriginal Aramaic 'ܝܫܘܥ (Yeshua') ተብሎ ነው የሚጠራው። ኢየሱስ በነበረበት ዘመን በገሊላ በከፍተኛ ቁጥር የሚነገረው ቋንቋ Aramaic በመኾኑ ሰዎች ጌታን Yeshua' እያሉ ነበር የሚጠሩት።

Yeshua' የሚለው Aramaicም ቢኾን ከOriginal hebrew የወጣ ነው ዕብራይስጡ 'יְהוֹשֻׁעַ (Yehoshua)' ይለዋል። 'Yeho' የመጣው ከ 'Yahweh' ነው ፣ Shua ማለት ደግሞ ማዳን ማለት ነው ስለዚህ አንድ ላይ ስናደርገው "የያሕዌ ማዳን" የሚል ትርጉም ይሰጠናል።

በብሉይ ኪዳን ብዙ "የያሕዌ ማዳን" ወይም "የኤል ማዳን" ተብለው የተሰየሙ ሰዎች አሉ ከነዚህ ውስጥ ታላላቅ ነቢያት ኢያሱ (Yehoshua -የያሕዌ ማዳን) ፣ ኢሳይያስ (Yeshayahu - የያሕዌ ማዳን) ፣ ኤልሳዕ (Elishah - የኤል ማዳን) ይገኙበታል። እነዚህ ነቢያት ኹሉ የአምላክ ማዳን ተብለው ቢሰየሙም የያሕዌን ማዳን ለሕዝቡ ማድረስ አልቻሉም ይልቅስ ስለማዳኑ ተንብየው አለፉ እንጂ። ስለዚህ እግዚአብሔር የመጀመሪያ የማዳን ስሙን በገዛ ክንዱ ገለጠ ፣ የገዛ ክንዱም መድኃኒት አመጣለት ፣ የያሕዌ ማዳን እውነተኛ ስሙን በኢየሱስ አገኘ እርሱ የነቢያት ማኅተም የዓለም ኹሉ መድኃኒት ነውና!

የማዳን ስሙ ይባረክ ❤️
❤ 113 👍 9 🥰 6 🙏 1
30 November 2024
ኪ
07:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ከአዳም ጎን በወጣችው አጥንት ሰይጣን የአዳምን ልብ ሠረቀ። ከኹለተኛዋ አጥንት [ከድንግል ማርያም] ግን ሰይጣንን እንደ ዳጎን የቆረጠ ኅቡዕ ኃይል ወጣ በዚህችኛዋ ታቦት አሸናፊነትን የሚሰብክና የሚያውጅ መጽሐፍ ተደብቋልና። ምሥጢርም ተገለጠ ዳጎን በራሱ መማጸኛ ቦታ ወዳደቀ። ይህ ምሳሌ ነው ከድንግል የወጣው ሰይጣንን በተማመነበት ቦታ ጥሎታልና። ምሥጢሩም ተፈጸመ በእውነተኛው በግ የዋጀን አጥፊያችንን ዳጎን እንደ ጠፋ ያጠፋው የተባረከ ይኹን።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ, Rhythm iii, On the Nativity, Morris, p.20) ((Blessed Virgin, p. 66).

ድንግልስ ከታቦተ ጽዮን ትበልጣለች በእርሷ የወደቀው በዳጎን የሚያስተው ሰይጣን ነውና! እንኳን አደረሳችሁ ለሐዲስ ኪዷኗ ታቦት በዓል አደረሳችሁ ❤️
🔥 56 ❤ 40 👍 6 🥰 4 🙏 4
2 December 2024
ኪ
19:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
በኖራ የተለሠነ ግድግዳ

ቅዱስ ጳውሎስ በሊቃነ ካህናት ሸንጎ ፊት ቆሟል ሕዝቡ ሕግን ይሽራል ቤተ መቅደሱን ይቃልላል በማለት አመጽ በማስነሳታቸው ለፍርድ Sanhedrin ታላቁ ጉባኤ ፊት ቆሞ እራሱን ይከላከላል። ጳውሎስ መብቱን የሚያቅ ሰው ነው መች ይሰማል ሺህ አለቃው ያለ ፍርድ ሊያስገርፈው ሲል "የሮሜን ዜጋ ያለ ፍርድ ትቀጣለህን" በማለት ከመገረፍ ቢያመልጥም አሁን ግን ሊቃነ ካህናቱ ፊት ፍርዱን እየጠበቀ ነው። ይሄን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ሀናንያ ጳውሎስን እንዲመቱት አዘዘ:
"በዚያን ጊዜ ጳውሎስ፦ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ፥ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?” አለው።" (ሐዋ 23:3) በማለት ይመልሳል። በዛ የተሰበሰበው ሕዝብ ሊቀ ካህናቱን ተሳደበ ብለው ጮኹ ጳውሎስ ግን እውነቱን ነው ተየናገረው በኖራ የተለሰነ ግድግዳ በውጪ ለሚያዩት ነጭ ነው ከልስኑ ስር ግን ስንት ቆሻሻን ደብቋል እንዲሁ ፈሪሳውያን በሰው ፊት ጻድቅ ጻድቅ ይጫወታሉ ውስጣቸው ግን በኃጢአት የተጨማለቀ ነው ፤ እነዚህን ክርስቶስ "ቀራጮች እና ዘማዎች መንግስተ ሰማያት በመግባት ይቀድሟችኋል" ሲል ይናገራቸዋል።

እኛስ በኖራ የተለሰንን ግድግዳዎች አይደለንም? ከነጩ ነጠላ ውስጥ ስንት ክፋትን ይዘን ነው ወደ ክርስቶስ የምንገባው ሰውን በነጭ ነጠላችን እንሸውዳለን ክርስቶስ ግን በዚህ አይሸወድም ልብና ኩላሊትን ይመረምራልና።

ፈሪሳውያን ተቆጡ እንዴት ሊቀ ካህናታችንን ትሰድባለህ አሉ። ጳውሎስ ግን "ሊቀ ካህናት መኾኑን አላወቅሁም" ሲል በስላቅ ቃል መለሰ በዝያን ጊዜ ሀናንያ ለሮማውያን ጉቦ ከፍሎ በግድ ቦታውን የያዘ ነውና ሕዝቡ የመረጠው ሊቀ ካህናት ግን ዮናታን ነበር። (ጳውሎስ ይቀልደው የለ እንዴ 😋) ። ይህ ብቻስ አይደለም ጳውሎስ የሚያውቀው ሊቀ ካህናት አንድ ብቻ ነው እርሱም ወደ ሰማያዊቷ መቅደስ በደሙ የገባው ኢየሱስ ነው ፤ በደሙ ቀይ ቢኾንም በባሕርይው ጸአዳ ነጭ ነው!
❤ 70 👍 10 🔥 5 🥰 1
3 December 2024
ኪ
20:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
Eastern Orthodox ክርስቶስን ኹለት ባአሕርይ በማለታቸው መናፍቃን ናቸውን?

አጭሩ መልስ አይደሉም ፤ ማስረጃዬ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ነው Liber Contra Impium Grammaticum ላይ ከኤፌሶን ጉባኤ በፊት ክርስቶስን ኹለት ባሕርይ ብለው የገለጹ አባቶች እንዳሉ ይናገራል ነገር ግን እነዚህ አባቶች ክርስቶስን ኹለት ባሕርይ ሲሉት በአንድ ጊዜ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሚለውን ለማመልከት ነው። ንስጥሮስ ግን ኹለት ባሕርይ የሚለውን ለጥጦት ኹለት አካል እስኪመስል ድረስ ወስዶታል (ያው በግልጽ ኹለት አካል አላለም ነገር ግን የእርሱ ኹለት ባሕርይ አስተምህሮ ወደዚያ የሚያመራ ነው።) ስለዚህም ከአሁን በኋላ ኹለት ባሕርይ የሚለውን መጠቀም የለብንም ሲል ሳዊሮስ ይሞግታል።

ከዚህ እንደምንረዳው ቅዱስ ሳዊሮስ ኹለት ባሕርይ የሚለው ትምህርት ሳይኾን ችግር ያለበት ኹለት ባሕርይ የሚለውን በንስጥሮስ አውድ ወደ መረዳት ስለሚያደርስ ነው መጠቀም እንደሌለብን የሚያስረዳው። አስከትሎም እንዲህ ይላል " አማኑኤል ኹለት ባሕርይ አለው የሚሉትን የምናወግዛቸው ስለ ባሕርያት ስለተናገሩ አይደለም ነገር ግን እያንዳንዱ ባሕርይ በየራሱ ይሠራል ብለው ባሕርያቱን በመክፈላቸው ነው"።

ስለዚህ አሁን ላይ ጥያቄያችን ሊኾን የሚገባው Eastern Orthodox ኹለት ባሕርይ ሲሉ እንደ ንስጥሮስ ባሕርያቱን በመክፈል በየራሳቸው ይሠራሉ ይላሉ ወይ የሚለው ነው። ለዚህ መልስ ደግሞ አይሉም።

Read this great article by Father V. C. Samuel: https://www.scribd.com/document/321576370/One-Incarnate-Nature-of-God-the-Word
❤ 41 👍 15
7 December 2024
ኪ
10:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው

ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ ይማልዳል ስንል የክርስቶስ ምልጃ አንድ ጊዜ ቀርቦ ለኹልጊዜ ይሠራል ማለታችን ነው። ቅዳሴ አትናቴዎስ ቁጥር 144 ላይ " ወልድ ሆይ እንደ ታመመ ሰው አሰምተህ ተናገር ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ በል። በአፋቸውም ውስጥ እያለ አባ አባቴ ሆይ ሥጋዬን የበሉትን ደሜን የጠጡትን ማራቸውም ይቅር በላቸው በል" እያለ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ በታላቅ መቃተት ያቀረበው ምልጃ ዛሬም በሥጋውና ደሙ ገና በአፋችን ሳለ እንደሚሠራልን ያስገነዝበናል። የክርስቶስ ምልጃ ፍጹም ነው እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት በየዓመቱ መደጋገም አይጠበቅበትም አንድ ጊዜ ባቀረበው ምልጃ ዘለዓለም ሊያድነን ይችላል "ስለ እነርሱም ሊማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል" እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።

እንዲህ ያለ ከፍ ያለ የታመነ ሊቀ ካህናት በሰማይ አለን ለኃጢአታችን ሥርየት አንድ ጊዜ ባፈሰሰው ደም ዛሬም ይምረናል "ሊቀ ካህናት ዘይቀውም ሎሙ ለቅዱሳን በደብተራ ስምእ እንተ እግዚአብሔር ተከላ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ-እግዚአብሔር በተከላት ምሥክር ድንኳን ውስጥ ለቅዱሳን የሚቆምላቸው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" እንዲል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ። አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በደሙ ገብቷል እኛም የክርስቶስን ደም አንድ ጊዜ በማቅረብ ተቀድሰናል እስከ ሕይወት ፍጻሜያችንም እንቀደሳለን ምልጃው ድግግሞሽ የማይስፈልገው አንድ ጊዜ ለዘለዓለም የቀረበ ፍጹም ነውና!

በአብ ዘንድ የታመነ ጠበቃ አለን ለኃጢአታችን ብቻ ሳይኾን ለዓለም ኹሉ ኃጢአት ሥርየት አንድ ጊዜ የቀረበ አስታራቂ በአብ ቀኝ አለን ልያውም በድካማችን የሚያግዘን ፈተናችንን ኹሉ የተፈተነ ሊራራልን የሚችል ሊቀ ካህናት በሥራው ኹሉ የታመነ ነው ወደ እርሱ እንቅረብ ከኃጢአታችን ኹሉ በቅዱስ ደሙ ያነጻናልና!
❤ 90 👍 17 🥰 5 👏 2
9 December 2024
ኪ
09:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
እግዚአብሔር ግን ለምን ፈጠረን?

ብቻውን በዘለዓለም የሚኖር ጌታ መፍጠር ራሱ ለምን አስፈለገው? እራሳችሁን ይህን ጥያቄ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ማር ይስሐቅ "ከበዛው ፍቅሩ የተነሣ" ይላል ስለዚህ እግዚአብሔር በባሕርይው ፍቅር ስለኾነ ፍጥረትን መፍጠሩ ግድ ነበር እንበል? እስቲ ይህን ጥያቄ ራሳችሁን ጠይቃችሁ የምታውቁ ሃሳባችሁን አካፍሉን። (ሰኞ በጠዋት ሥራ ስትገባ ራስህን የምትጠይቀው ጥያቄ 😁)
❤ 68 😁 14 👍 7 🤔 2
10 December 2024
ኪ
23:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ አሳራፊው ጌታ ስትጠጋ ሌሊቱን በሰላም ታርፋለህ ምንም እንኳን ነገ ምን እንደሚያጋጥምህ ቀርቶ መኖርህን ራሱ እርግጠኛ ባትኾንም ዕረፍትህ ግን በእርሱ ነውና አትናወጥም ብትኖርም የእርሱ ነህ ፣ ባትኖርም የእርሱ ነህ። በመኖራችንም ኾነ ባለመኖራችን ክርስቶስ ይክበርበት ኹሉ ስለ እርሱ መልካም ነውና! ዕረፍታችን ኢየሱስ ነው 😍 መልካም ሌሊት🌒
❤ 107 👍 23 🥰 11 👏 1
12 December 2024
ኪ
10:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
ታቦትና መሠውያ

መምህር ዘበነ ከ5 ቀን በፊት በሠራው Video ላይ እንድ ነገር መናገር ፈለኩ። ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመቅናት የተነሣ ታቦትና ጽላት ያለን ከዓለም እኛ ብቻ ነን ሌሎቹ ኦርቶዶክሳውያን ያላቸው Altar (መሠውያ) ወይም Lord's Table (ጠረጴዛ) ብቻ ነው። እኛ ግን ከመሠውያ በተጨማሪ አሠርቱ ትእዛዛት የተጻፈበት ጽላት እንዲሁም የብሉይ ኪዳን የቃልኪዳኑ ታቦት አለን። መሠውያ የምንለውም ሥጋውና ደሙ የሚሠዋበት ሳይኾን ድርገት ሲወርድ ለምእመናን የሚቀርበበት ነው ይለናል።

ይህ ግን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ፍጹም ኦሪታዊት የሚያስመስል አደገኛ ትምህርት ነው። ቤተክርስቲያን አሠርቱ ትእዛዛት የተጻፈበት ጽላትም ኾነ የብሉዩ የቃልኪዳን ታቦት የላትም። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ አንድ ላይ አዲስ ቤተክርስቲያን እንዴት እንደሚከብር ሲናገር አሠርቱ ትአዛዛት ስለተጻፈበት ጽላትም አያነሳም እንዲሁም ጽላቱ ስለሚቀመጥበት የቃልኪዳን ታቦት አላነሳም ይልቅስ "የመሠውያውን ታቦት በዘይት ያክብሩት ... በመሠዊያው ላይም ይቀድሱ ... ወደ መሠዊያው ቦታ ይስገዱ" እያለ ታቦት እና መሠዊያ የሚባሉትን ቃላት በተለዋዋጭ የክርስቶስ ሥጋና ደም ስለሚሠዋበት ቅድስት ጠረጴዛ ይናገራል ነገር ግን ድርገት ሲወርድ ሥጋወ ደሙ የሚቀርበበትን ንዋይ አንድም ቦታ መሠዊያ አይለውም ፣ ጠረጴዛም አይለውም። ይህ የጌታ ሥጋና ደም የሚቀርበበት ታቦተ ምሥዋዕ ደግሞ የሚገኘው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን የክርስቶስ ሥጋና ደም እውነተኛ መሥዋዕት ነው ተብሎ በሚያምኑ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ነው።

ይህ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ከዓለም ልዩ ለማድረግ ተብሎ ኦሪታዊት ለማስመሰል የሚደረገው ሙከራ መቆም አለበት።
👍 80 ❤ 40 🥰 1
13 December 2024
ኪ
12:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሕፃናት የሚጠመቁት ለኃጢአት ሥርየት ነው

አስተምህሮው በ3ተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ፤ ጉባኤ ኤፌሶን ተረጋግጦ እውቅና የተሰጠው በ418 ዓ.እ የተካሔደው የቅርጣግና ጉባኤ (Council of Carthage) ቀኖና ኹለት ላይ እንዲህ ይላል፡

"የሕፃናትን ጥምቀት የሚክድ ወይም ደግሞ ጥምቀት ለኃጢአት ሥርየት ነው ብሎ ሕፃናት ግን ዳግመኛ በሚወልደው ውኃ መወገድ የሚያስፈልገውን ጥንተ አብሶ ከአዳም አይወርሱም ቢል ፤ ለኃጢአት ሥርየት ነው ማለቱ ሃሰት ነውና የተወገዘ ይኹን! ሐዋርያው እንዳለው "በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ምክንያት ሞት ፤ እንዲሁም ኹሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ኹሉ ደረሰ" ኩላዊቷ ቤተክርስቲያንም ይህን የተረዳችው ሕፃናት እንኳ ገና ኃጢአትን ባይሠሩም በእውነት ለኃጢአት ሥርየት ይጠመቃሉ። በእነርሱ የኾነው [ጥንተ አብሶ] የመወለድ ውጤት እንደኾነ ዳግመኛ በመወለድ ይነጻልና። " (Canon 2 of 418 Synod of Carthage)
👍 45 ❤ 5 🤔 5 😁 2 🥰 1
ኪ
23:36
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
03:37, 38.4 MB
ውይ ቅዱስ ሳዊሮስ እንዴት እንደ ምወደው እራሱን ለጌታና ለቤተክርስቲያን የሰጠ ታላቅ አባት። ለክርስቶስ ያለው ፍቅር ደግሞ ከልብ ነው እኔ ግን ይሄን ያህል ክርስቶስን ልወደው እችላለሁ? ኢየሱስ ሆይ እንደ ቅዱሳንህ እንድወድ አንተ አድርገኝ ብዬ ፍቅሩን እንዲጨምርልኝ እራሱን ልጠይቀው እንጂ እኔማ ከክርስቶስ ይልቅ የኃጢአት ፍቅር በልጦብኛል። በቅዱስ ሳዊሮስ ምልጃ ጌታ ኢየሱስ እርሱን መውደድ ይስጠን ፤ አንተን መውደድ ስጠን በሉት እርሱስ ባለጸጋ ነውና ከፍቅሩ ብዛት እኛ ላይ ጥቂት ሊያፈስብን ይቻለዋልና።
❤ 82 🙏 7
15 December 2024
ኪ
15:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
ንቅረብ ለመድኃኒተ ሕይወት

ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ነው ፤ ኢየሱስ የሕይወት መጠጥ ነው። ለሥጋችን ምግብና ውኃ ሳንሰጥ አንድ ቀን እንኳን መቆየት የሚከብደን ኾነን ሳለ ነፍሳችንን ለምን እናስርባለን? ለምንስ እናስጠማለን? የክርስቶስ ሥጋና ደም ለሥጋችን ፣ ለነፍሳችን ፣ ለመንፈሳችን ቅድስና እና ሕይወት የተሰጠ ዘለዓለማዊ ምግብ ነው። ምነው እኛ ግን መራባችንን ያላወቅን ረሃብተኞች ኾንን? ለምንስ የሕይወት መድኃኒት ከኾነው ጌታ ራቅን? ዳዊት በመዝሙር ቃል "ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ነፍሴም ወደ አንተ ትናፍቃለች" እያለ የነፍሱን ጥም ሊያረካለት ወደ ሚችለው ጌታ ያማትራል ለነፍስ ሕይወት የሚኾነውን ውኃ ሊሰጥ የሚችለው ጌታ ብቻ መኾኑን ያውቃልና። እኛ ግን ነፍሳችን ሕይወትን ናፍቃ ተጠምታ ሳለ ወደ ሕይወት መድኃኒት ላለመቅረብ ምክንያት እንደረድራለን፤ መጀመሪያ ሕይወት ይኑረኝ ፣ ኃጢአትን ላቁም እንላለን። የሕይወትን መድኃኒት ሳንቀበል በራሳችን ሕይወት የለንም፤ ለኃጢአት ሥርየት የተሰጠውን ኃጢአትን የሚያስተወውን መድኃኒት ሳንቀበል ከኃጢአት ልንላቀቅ ከቶ አንችልም!

ክርስቲያኖች ሆይ በነፍሳችን አንቀልድ የያዝነው ሕይወት ነው በነፍሳችን ላይ ቁማር አንጫወት ነፍሳችን ከእኛ ሳትወሰድ በፊት "ወደ ሕይወት መድኃኒት እንቅረብ ጸጋ ኾኖ የተሰጠንን ቅድሳት (ሥጋውና ደሙን) በእግዚአብሔር ጥበብ እንቀበል።" (ቅዳሴ እግዚእ)
❤ 76 👍 11 🥰 1
18 December 2024
Voice chat
Voice chat (5108 seconds)
19 December 2024
ኪ
06:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
Theological Terminologies explained!.ogg
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:11:35, 21.5 MB
Physis , Ousia, Hypostasis and Prosopon definition.

-Hypostatic Union vs Prosopic Union

- Asymmetric vs Symmetric Dyophysitism
❤ 29 👍 6 🥰 1
06:39
የትናንቱ Live stream recording በዚህ pdf ተከታተሉት
❤ 34 👍 4 🙏 1
ኪ
19:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ለዱር አውሬዎች ምግብ እኾን ዘንድ ፍቀዱልኝ በእነርሱ ወደ እግዚአብሔር እደርሳለሁና። እኔ የእግዚአብሔር ስንዴ ነኝ በዱር አውሬዎች ተፈጭቼ  የክርስቶስ ንጹሕ ኅብስት ኾኜ እገኝ ዘንድ ተዉኝ...

ስጽፍላችሁ በሕይወት ብኖርም ልሞት ግን እናፍቃለሁ ፍቅሬ ተሰቅሏልና መመገብም የሚፈልግ እሳት በውስጤ የለም። ነገር ግን ፡- ወደ አብ ና የሚለኝ ሕያውና የሚናገር ውኃ በውስጤ አለ። በሚጠፋ መብል ወይም በዚህ ሕይወት ተድላ ደስ አይለኝም። የእግዚአብሔርን እንጀራ ሰማያዊውን ኅብስት የሕይወትን እንጀራ እመኛለሁ እርሱም በኋላ ከዳዊትና ከአብርሃም ዘር የኾነ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ነው ። የእግዚአብሔርንም መጠጥ እሻለሁ እርሱም ደሙ የማይጠፋ ፍቅርና የዘላለም ሕይወት ነው።"

(ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ለሰማዕትነት ወደ ሮም ኮሎሲየም እየተወሰደ እያለ የሮም ምእመናን ከሰማዕትነቱ ወደ ኋላ እንዳይሉት የላከባቸው መልእክት)

የክርስቶስ ፍቅር
ለሰማዕትነት መሮጥ
ቁርባናዊ ሕይወትና አገላለጽ
ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ
ኢየሱስ ❤️

ሙሉው ይነበበው የክርስቶስ ፍቅር በተግባር ሲሠራ እዩ የቅዱሳን ሕይወት ሕያው ወንጌል ነውና:
https://www.newadvent.org/fathers/0107.htm
❤ 59 👍 6 🥰 4 🔥 2
24 December 2024
ኪ
07:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሄ ከ2 ዓመት በፊት ለጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ ለልደት በዓል ያዘጋጀሁት ጽሑፍ ነው ፤ አሁን ዘመኑ ዘመነ ስብከትም አይደል ስለ ጌታ ልደት እያነበባችሁት በልባችሁ እያሰባችሁት ቆዩ። 😊
❤ 57
ኪ
15:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
የኒቅያ-ቁስጥንጥንያ አንቀጸ ሃይማኖት ግሪኩና ከግሪኩ ጋር አቻ አማርኛ ትርጉም

Πιστεύομεν εἰς ἕνα Θεὸν Πατέρα παντοκράτορα
ποιητὴν οὐρανοῦ καὶ γῆς ὁρατῶν τε πάντων καὶ ἀοράτων·
καὶ εἰς ἕνα Κύριον Ἰησοῦν Χριστὸν
τὸν υἱὸν τοῦ Θεοῦ τὸν Μονογενῆ,
τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων,
Φῶς ἐκ Φωτός,
Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,
γεννηθέντα οὐ ποιηθέντα,
ὁμοούσιον τῷ Πατρί,
δι' οὗ τὰ πάντα ἐγένετο·
τὸν δι' ἡμᾶς τοὺς ἀνθρώπους καὶ διὰ τὴν ἡμετέραν σωτηρίαν κατελθόντα ἐκ τῶν οὐρανῶν,
καὶ σαρκωθέντα ἐκ Πνεύματος Ἁγίου καὶ Μαρίας τῆς παρθένου,
καὶ ἐνανθρωπήσαντα,
σταυρωθέντα τε ὑπὲρ ἡμῶν ἐπὶ Ποντίου Πιλάτου,
καὶ παθόντα, καὶ ταφέντα,
καὶ ἀναστάντα τῇ τρίτῃ ἡμέρᾳ κατὰ τὰς γραφὰς,
καὶ ἀνελθόντα εἰς τοὺς οὐρανοὺς,
καὶ καθεζόμενον ἐν δεξιᾷ τοῦ Πατρὸς,
καὶ πάλιν ἐρχόμενον μετὰ δόξης κρῖναι ζῶντας καὶ νεκρούς,
οὗ τῆς βασιλείας οὐκ ἔσται τέλος·
καὶ εἰς τὸ Πνεῦμα τὸ Ἅγιον, τὸ Κύριον καὶ Ζωοποιόν,
τὸ ἐκ τοῦ Πατρὸς ἐκπορευόμενον,
τὸ σὺν Πατρὶ καὶ Υἱῷ συμπροσκυνούμενον καὶ συνδοξαζόμενον,
τὸ λαλῆσαν διὰ τῶν προφητῶν·
εἰς μίαν ἁγίαν καθολικὴν καὶ ἀποστολικὴν ἐκκλησίαν·
ὁμολογοῦμεν ἓν βάπτισμα εἰς ἄφεσιν ἁμαρτιῶν·
προσδοκῶμεν ἀνάστασιν νεκρῶν,
καὶ ζωὴν τοῦ μέλλοντος αἰῶνος. ἀμήν.

ኹሉን ቻይ በኾነ አንድ አምላክ አብ እናምናለን።
የሰማይና የምድር ፈጣሪ ፣  የሚታየው እና የማይታየው ኹሉ።
እንዲሁም የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ በኾነው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ [እናምናለን]
ከዘመናት በፊት ከአብ የተወለደ
ከብርሃን የኾነ ብርሃን,
ከእውነተኛ አምላክ የኾነ እውነተኛ አምላክ ፣
የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ
በባሕርይም ከአብ ጋር አንድ ኾኖ
ኹሉ በእርሱ የኾነ;
ስለ እኛ ሰዎችና ለእኛ መዳን ከሰማይ የወረደ።
በመንፈስ ቅዱስ ከቅደስት ድንግል ማርያም ሥጋን ለብሶ ሰው የኾነ ፣
ስለ እኛ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን የተሰቀለ
የታመመ ፣ የተቀበረም
መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛውም ቀን የተነሣ።
ወደ ሰማይም የዐረገ።
በአባቱም ቀኝ የተቀመጠ
በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ በክብር የሚመጣ።
ለመንግሥቱም ፍጻሜ የሌለበት;
እንዲሁም ጌታ እና ሕይወትን ሰጪ በኾነ በመንፈስ ቅዱስ [እናምናለን]
ከአብ የሰረጸ፣
ከአብ እና ከወልድ ጋር በአንድነት ይመለካል ፣ ይከበራል
በነቢያት የተናገረው ነው;
እንዲሁም በአንዲት ቅድስት ኩላዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን [እናምናለን]
ለኃጢአት ስርየት አንዲት ጥምቀትን እንመሠክራለን;
የሙታንንም ትንሣኤ እንጠብቃለን
የሚመጣውን ዘመን ሕይወትም አሜን።

አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሠጠን ሃይማኖት እንጋደላለን!
❤ 107 👍 4 🥰 4 🤩 2
25 December 2024
ኪ
08:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ በግሪጎሪያን እና አዲሱ ጁልያን ካላንደር የሚከተሉ ካቶሊካውያንና ኦርቶዶክሳውያን የልደትን በዓል ያከብራሉ ከነዚህ በኦረንታል ኅብረት ውስጥ ያሉት የሶርያና ማላንካራ ኦርቶዶክሳውያን ይገኙበታል እንኳን አደረሳችሁ እንበላቸው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ December 25 , የጌታ ልደት ቀን የኾነው ከጣኦት ተወስዶ ነው የሚባለው ውሸት መኾኑን ላሳስብ እወዳለሁ። ክርስቲያኖች ልደትን በdecember 25 ማክበር የጀመሩት ገና ከ2ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ ነው ፤ ስለዚህ ቅዱስ ሂጶሊጦስ ዘሮሜ በ235 ዓ.እ እንዲህ ይለናል " ጌታችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሥጋ ሲመጣ የተወለደው በቤተልሔም Decembet 25 ረቡዕ ቀን ሲኾን በአውግስጦስ ቄሳር በአርባ ኹለተኛ ዓመት ሲመት ነበር ይህም ከአዳም ጀምሮ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ይኾናል" (Hippolytus of Rome :Commentary on Daniel, translated by T.C. Schmidt from chronicon.net.)

በDecember 25 ልደቱ ይከበራል የሚባለው የፀሐይ አምላክ Dies Natalis Solis Invicti ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ መከበር የጀመረው በ274 ዓ.እ ነው ይህ እንግዲህ ሂጶሊጦስ ራሱ የክርስቶስን የልደት ቀን ከነገረን ከ40 ዓመት በኋላ ነው። ስለዚህ ጣኦት አምላኪያኑ ከክርስቲያኖች ኮረጁ እንጂ ክርስቲያኖች ከጣኦት አምላክያን አልኮረጁም።

ታድያ የጥንት ክርስቲያኖች ገናን December 25 የሚያከብሩ ከኾነ እኛ ለምን January 7 እናከብራለን? መልሱ የእኛ ካላንደር ከግሪጎርያኑ ሳይኾን ከጁልያኑ ጋር ነው የሚገጥመው በእኛ ታኅሣሥ 29 በጁሊያኑ December 25 ላይ ነው የሚውለው። ካቶሊካውያንና አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን ካላንደራቸውን ከጁሊያኑ update ሲያደርጉ እኛ በዛው ቀጥለን እንጂ የጌታ ልደት በየትኛውም ካላንደር December 25 ነው።
❤ 42 👍 25 🥰 1 👀 1
28 December 2024
ኪ
22:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
መጽሐፍ ስጦታ የሚሰጥ ወዳጅ ይስጣችሁ 😍
❤ 88 👍 7 🥰 4 😇 2
22:10
29 December 2024
ኪ
07:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ -ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ

ወደ ዓለም የተላከ እውነተኛ ብርሃን የአብ የባሕርይ ልጁ የኾነ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ዓለም የጸደቀበት እኛም በጸጋው ጻድቃን የተባልንበት ጽድቃችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ወደ ዓለም መጣ የዓለምንም የጨለማ ኃጢአት አበራ ስለዚህም ዮሐንስ "ለሰው ኹሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር። በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።" (ዮሐ 1:9 ) ሲል መሠከረለት። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ይኖር ለነበረ ሕዝብ ብርሃን ወጣላቸው ፤ በኃጢአት ተሸንፎ ለነበረ ሕዝብ የእግዚአብሔር ጽድቅ መጣላቸው በጸጋው ላይ ጸጋም ጨመረ እኛም ጸጋውን በምልዓት ተቀብለን በብርሃኑ አበራን ፣ በጽድቁም ጸደቅን ከእርሱን ተወልደን የብርሃን ልጆች ኾንን ፤ ይህ በሰው ሥራ የሚኾንስ አይደለም ካበራልን ብርሃን ከጽድቅ ልብሳችን አማኑኤል የተነሣ ነው እንጂ!

"አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት ዘይዜንዋ ለጽዮን ቃለ ትፍሥሕት ወካዕበ ይቤ በአፈ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርዓዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳእ ዘተኀጒለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ።
   
ለጽዮን የደስታ ቃልን የሚያበሥራት ወልድ በምስጋና እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ተነገረ ዳግመኛ በዳዊት አንደበት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው አለ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን ለጻድቃን የሚያበራ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ነው የጠፋውን ይፈልግ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደእኛ መጣ።" መዝሙር ዘብርሃን

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ ❤️
👍 41 ❤ 20 🥰 7
31 December 2024
ኪ
12:08
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነየ አመቱ ለእግዚአ ኩሉ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ (እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ)

ገብርኤል ፊቱ ያበራል የክንፉ ድምጽ አጽናፋት ድረስ ይሰማል በልቡ ደስታን ተሞልቷል ከአርያም ከመኖሪያው ከራማ ወረደ ክንፉን እያማታ ወረደ ፣ ወደ አንዲት 15 ዓመት ድንግል ታናሽ ብላቴና ዘንድ ወረደ ፣ ወደ ተናቀች ከተማ "ከእርሷ መልካም ሰው ይወጣልን" ወደ ተባለችዋ ናዝሬት ወረደ ወደ ገሊላዋ ታናሽ እመቤት ዘንድ የዓለምን የመዳን ዜና ይዞ ወረደ።

ጸጋን የተመላሽ ሆይ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ! ሲል ከዚ በፊት ለሰው ያልተባለ ሰላምታን አቀረበላት ድንግሊቱ ግን ተደነቀች እንዲህ አይነት ሰላምታ ሰምታ አታውቅም "እንደምን ያለ ሰላምታ ነው" ስትል በልቧ አሰበች። ገብርኤል ግን ያሰበችውን ገልጦለታልና ማርያም ሆይ ጸጋን የተመላሽ ስላልኩሽ ደነቀሽን እንግዲያውስ ከዚ በላይ የሚያስደንቅ ነገርን ልንገርሽ ትጸንሻለሽ የእግዚአብሔርንም ልጅ ትወልጂያለሽ ሲል ታላቅ ዜናን አወረደባት። ይህ እንዴት ይኾናል? ድንግሊቱ አልቻለችም ፣ ይህ እንዴት ይኾናል? እኔኮ ወንድ አላውቅም እንዴት ይኾናል? እያለች አመላለሰች። ገብርኤልም መች በቀላሉ ተስፋ ይቆርጣል ማርያም ሆይ ይሄ ይገርምሻልን ኤልሳቤጥስ በእርጅናዋ ጸንሳ የለምን ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር ምን አለ? ሲል መርታት የማትችለውን መከራከርያ አነሳባት ፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር ምን አለ? ድንግሊቱ ተረታች አልቻለችም በዚህ ጊዜ ፈቃድዋን ለጌታዋ አሳልፋ ሰጠች "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ስትል ድኅነት የሚከናወንባት ምርጥ እቃ ትኾን ዘንድ እራስዋን በትሕትና አቀረበች "እንደ ቃልህ ይደረግልኝ" ባለችበትም ቅጽበት አካላዊ ቃል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በማኅጸኗ አደረ የኹላችንም ድኅነት በዚያች ቅጽበት ተጀመረ ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ኾነ።

ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም! እናት እና ገረድ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ እራስሽን ባሪያ አድርገሽ በጌታ ፊት ባቀረብሽ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ እናት ኾነሻልና! ስለዚህም እግዚአብሔር አብ ዘመንሽ ዘመኔ ኾነ ይልሻል በባሕርይ የወለደው ልጁ ካንቺ የሰውን ባሕርይ ነስቶአልና። ሔዋን አምላክነትን ሽታ የሰይጣን ባሪያ ኾነች አንቺ ግን ባርያነትን ሽተሽ የአምላክ እናት ኾንሽ ፣ አካላዊ ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ካንቺ ባሕርይ በነሳው ሥጋ ዘመዳችን ኾነ ወንድሞቼ ብሎም ጠራን ስለዚህም ዘመዳችን የኾነው ባንቺ ሥጋ ነውና ትምክህተ ዘመድነ የባሕርያችን መመኪያ እንልሻለን ሌላ ማመስገኛ ቃል ቢያጥረን ከአብሣሪ መልአክሽ ቅዱስ ገብርኤል ተውሰን ተፈሥሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ ቡርክት አንቲ እም አምንስት _ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ እያልን ዘወትር እናመሰግንሻለን።

መልካም በዓለ ብሥራት
መጋቢት 29፣ 2016 ዓ.ም ተጻፈ።
❤ 33 👏 9 👍 3 🥰 1
ኪ
1 January 2025
Voice chat
Voice chat (3172 seconds)
ኪ
22:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
Prelaprasian State.ogg
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
43:10, 16.9 MB
የአዳም ቅድመ በደል አፈጣጠር
🙏 27 👍 7 ❤ 2
22:41
ሪከርዱን በዚህ file ተከታተሉት።
👍 25 ❤ 1
3 January 2025
ኪ
23:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
But God made you without you. You didn't, after all, give any consent to God making you. How were you to consent, if you didn't yet exist? So while he made you without you, he doesn't justify you without you. So he made you without your knowing it, he justifies you with your willing consent to it.

ለመፈጠር ፈቃድ አልተጠየቀንም ባልነበርንበት ፈቃድ አንጠየቅምና ሲያጽድቀን ግን በፈቃዳችን ነው እግዚአብሔር ያለፈቃድ የሚያጸድቅ አስገዳጅ አምላክ አይደለምና ነገር ግን በነጻ ፈቃዳችን ለጸጋው ምላሽ ስንሰጥ እንጸድቃለን እንጂ።

ይሄን ቆንጆ ንግግር የትኛው አባት የተናገረ ይመስላችኋል?
❤ 47 👍 5 🥰 1
7 January 2025
ኪ
02:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
“በወንጌል ዘገባ ወደ ቤተልሔም እንሒድ። በእውነት እረኞች ከኾንን መንጎቻችንንም የምንጠብቅ ከኾነ፣ ይህን ታላቅ ደስታ የምስራች የሚያውጅ የመላእክቱ ድምፅ ወደእኛ በእርግጥ ቀርቧል። እንግዲያው፣ ወደ ሰማያዊ ሠራዊት እንመልከት፣ የመላእክት ማኅበርን
እንይ፣ መለኮታዊ ዝማሬያቸውንም እንስማ። በዓሉን የሚያከብሩት ድምፅ ምንድር ነው ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይኹን " እያሉ ይጮኻሉ። መላእክቱ በአርያም ያለውን መለኮት ያከብራሉን? ብንል እነርሱስ "በምድርም ሰላም" ይላሉ። መላእክት በታላቅ ትዕይንት እጅግ ደስተኞች ኾነዋል፡ "በምድርም ሰላም"። ቀደም ሲል የተረገመው፣ እሾህና አሜከላን ያፈራ፣ የጥል ቦታ ፣ የፍርድ ምርኮኛ፣ ሰላም አግኝቷል። ኧረ ይገርማል! "እውነት ከምድር ወጣች ጽድቅም ከሰማይ አየች።" የሰው ምድር ያፈራችው ፍሬ እንዲህ ነው። እነዚህም ነገሮች የሚፈጸሙት የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ለሰው ልጆች እንዲኾን ነው። የሰው ልጅ ወደ እግዚአብሔር ከፍታ ከፍ እንዲል እግዚአብሔር ከሰው ተፈጥሮ ጋር ተዋሕዷል። ይህንንም ዜና ከሰማን በኋላ ወደ ቤተ ልሔም እንሒድና ይህንን ድንቅ ተአምር እንይ ድንግል በመውለዷ እንዴት ሐሴት እንደምታደርግ፣ ጋብቻን የማታውቅ ሕፃንዋን እንዴት እንደምታጠባ አዲሱን ትዕይንት እንይ። “

(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ትምህርት በእንተ ልደት : St. Gregory of Nyssa homily on the Nativity)

የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ እንኳን አደረሳችሁ ❤️
❤ 60 🥰 4 👍 1
9 January 2025
ኪ
17:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
"By nature, of course, man is mortal, since he was made from nothing; but he bears also the Likeness of Him Who is, and if he preserves that Likeness through constant contemplation, then his nature is deprived of its power and he remains incorrupt. The keeping of His laws is the assurance of incorruption. " (St. Athanasius of Alexandria: On the incarnation Chapter 1 , 4)

"በባሕርይውስ ሰው መዋቲ ነው የተፈጠረው ካለመኖር ነውና። ነገር ግን በእርሱ [እግዚአብሔር] ምሳሌ ተፈጥሯልና ይህን ምሳሌ በጥሞና እስካስጠበቀ ድረስ ግን [መዋቲ] ባሕርይው ኃይሉን ያጣና ኢማሳኒ ይኾናል። የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ነው የኢማሳኒነትን ተስፋ የሚሰጠው። " (ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ፡ በእንተ ተሠግዎተ ቃል ምእራፍ 1 ቁ. 4)
❤ 54 👍 11
Voice chat
Voice chat (2596 seconds)
ኪ
21:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
👍 12 🙏 3
21:46
ኪዳን ዘኢየሱስ – Consequence of the fall
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
35:26, 11.1 MB
👍 21
13 January 2025
ኪ
11:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለቅዳሴ ያለንን ቦታ እንፈትሽ

እስቲ ቅዳሴ የምንቀርበትን ምክንያቶች እንፈትሻቸው ክርስቶስ በአካል ከሚገኝበት ቦታ ምን በልጦብን ነው የምንቀረው? ኳስ መጫወት ፣ ስፖርት መሥራት ፣ እንቅልፍ? እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ጥሩ ቢኾኑም የጌታን ቦታ እየወሰዱ ከኾነ ግን ዝሙት ናቸው። ቅዱስ አውግስጢኖስ "አንድን ነገር የሙሽራውን የክርስቶስን ቦታ እስኪወስድ ድረስ የምንወድ ከኾነ በሙሽራችን ላይ የሚፈጸም ዝሙት ነው" ይለናል። ለአንድ ክርስቲያን በጌታ ቀን በዕለተ እሑድ ቅዳሴ ቀርቶ ሌላ ቦታ መዋል የሙሽራውን ድግስ አልፈልግም በማለት በሙሽራው ላይ የሚፈጸም አመጽ ነው! አሁን በምድራዊው የክርስቶስ ሠርግ ላይ ካልተገኘን እንዴት በሰማያዊው ሠርግ ላይ የመሳተፍ እድል አለን ብለን እናስባለን? ለቅዳሴ ፣ ለክርስቶስ ያለንን ቦታ እንፈትሽ።

መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ጥሩ ነን ብለን እራሳችንን የምናስብ ሰዎችም ቢኾን ለቅዳሴው ያለንን ቦታ መልሰን እንፈትሽ፤ ስንት ጊዜ ነው ማኅሌት ተሳተፍን ብለን ቅዳሴው እየተጀመረ ረግጠን የወጣነው? ስንት ጊዜ ነው በጌታ ቀን ቅዳሴውን ትተን መንፈሳዊ ጉዞ ብለን የሔድነው? በቤተክርስቲያን ውስጥ የትኛውም አገልግሎት ሊቀር ይችላል ቅዳሴ ግን በፍጹም አይቀርም ቅዳሴ ለቤተክርስቲያን ሕይወቷ ነውና!

የታረደው በግ ደም እንዳይፋረደን በበጉ ሠርግ ላይ እንገኝ የሕይወትንም መድኃኒት እንቀበል!
❤ 78 🙏 8 💯 7 😢 3 👍 1 🥰 1
14 January 2025
ኪ
10:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጥዑመ ስም

ጨለማን በብርሃንነቱ የሚያርቅ የሞትን ጥላ በትንሣኤው ኃይል የሚያፈራርስ ስም ኢየሱስ ፤ የመላእክት መዝሙር የፍጥረታት የፍቅር ዜማ ስም ኢየሱስ፤ የሚጠራውን ኹሉ የሚቀድስ ከለመኑበት የአብን ልብ የሚያረሰርስ ስመ ተማጽኖ ኢየሱስ፤ የጎሰቆለውን የሚያድስ ሕሙማንን የሚፈውስ የድኩማን ብርታት ስም ኢየሱስ ፤ የዘለዓለም ሕይወትን ለሚጠራው ኹሉ የሚያጎናጽፍ ሰማይና ምድርን የሚያገናኝ የጥልን ግድግዳ የሰባበረ ስመ መድኃኒት ኢየሱስ!

በዓለም ማእበል ለምትናወጥ ነፍሳችን መልሕቅ ፤ ሰማያትን የምንወርስበት ኪዳናችን ፤ ዓለምን የምናሸንፍበት ተስፋችን ፤ ስለ ኃጢአት የምንሠዋው በጋችን ኢየሱስ!

ኢየሱስ ሆይ በምን ቃል ልግለጽህ ያደረክልኝ ኹሉ ከመገለጽ በላይ ነው ብቻ አንተ በልቤ ላይ ንገስ ጉልበቴ ዘለዓለሙን ለስምህ ይንበርከክ፤ የማዳን ስምህ ይባረክ! ኢየሱስ ስምህ ይባረክ! ጌታዬ ስምህ ይባረክ! የሚጣፍጥ ስም ኢየሱስ!

ኢየሱስ ክርስቶስ
Iyyasus Kiristos
Ιησούς Χριστός
Ⲓⲏⲥⲟϒⲥ Ⲡⲓⲭ́ρⲓⲥτⲟⲥ
ܝܫܘܥ ܡܫܝܚܐ
ישוע המשיח
يسوع المسيح
❤ 74 🥰 7 ❤‍🔥 6 🙏 6 👍 4 🔥 1
17 January 2025
ኪ
11:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች ዛሬ የበይረሙን (Paramoun) ወይም ጋድ ጾም እንደኾነ ታውቃላችኋ?

Paramoun ማለት የግሪክ ቃል ሲኾን የመዘጋጃ ቀን ማለት ነው ለጥምቀትና ገና በዓላት የምንዘጋጅበት። ለጥምቀት ሲኾን በይረሙን ጥር 10 ቀን ነው ነገር ግን ጥምቀት ቅዳሜ ፣ እሑድና ሰኞ ቀናት ላይ ሲውል በእነዚህ ቀናት ጾም አይገባምና አርብ ዕለት አስቀድሞ ይጾማል። የዚህ ዓመትም ጥምቀት እሑድ ስለሚውል ጋድ 2 ቀን ይኾናል አርብና ቅዳሜ፤ አርብ እስከ 12 ሰአት ይጾማል ፣ ቅዳሜ ደግሞ ከጥሉላት ብቻ ይጾማል። ይህ ሥርዓት በኮፕቲክም በኢትዮጵያም አብያተ ክርስቲያናት ያለ ነው። ይህ ጾም ልክ እንደ አብይ ጾም ጠንከር ያለ እስከ ማታ 12 ሰአት የሚጾም ነው (በኮፕቲክ strict fast ይባላል።)

የበዓልን ቀን ኹል ጊዜ በጾም እየተዘጋጀን እንቀበል ዘንድ ሥርዓት የሠራችልን ቤተክርስቲያናችን ግን ደስ ትላለች።
🔥 50 ❤ 34 🙏 15 👏 3 🥰 1
19 January 2025
ኪ
10:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኤጲፋንያ_ አስተርእዮቱ ለመድኃኒነ

ጌታ ኢየሱስ በጥምቀቱ ዳግመኛ ሊወልደን ጥምቀት የማያስፈልገው እርሱ ስለ እኛ ተጠመቀ።

ኤጲፋንያ መለኮታዊ መገለጥንም በጥምቀቱ ሰጠን የአብ የባሕርይ ልጅ ለዓለም ኹሉ ታወቀ። አስተርእዮ ለአባቱ አንድያ የኾነ ክብሩንም አየን ፣ በእርሱ አብንም ሰማን። ቴዎፋንያ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ በመውረዱ ለእኛ የመንፈስ ቅዱስን መገለጥ ባረከልን።

ዘነገሩነ አበዊነ እሙነ ኮነ በከመ ሰማእነ ከማሁ ርኢነ _ አባቶቻችን የነገሩን እውነትም ኾነ እንደሰማን እንዲሁ አየን።

እንኳን አደረሳችሁ!
❤ 59 👍 7 🥰 1
21 January 2025
ኪ
19:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢየሱስ ይወዳችኋል

ብዙ ጊዜ ዕቅበተ እምነት ላይ ብቻ ስናተኩር የክርስትናን ዋና መሠረትን እንዘነጋለን። ዕቅበተ እምነት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢኾንም እኛ ሰዎች ግን በአመክንዮ የታጠርን ብቻ አይደለንም አንዳንድ ጊዜ ሰው "ክርስትና ለምን እውነት እንደኾነ 10 አሳማኝ ምክንያቶችን" የሚል ሙግት ላይፈልግ ይችላል ይልቅስ የፈለግነውን ተዋስኦ ብናቀርብ የምንናገረው ነገር ወደ ልቡ ውስጥ ካልገባ ደረቅ እውነት ብቻ ይኾንበታል።

ሐዋርያት ወደ ዓለም ዳርቻ የተላኩት ወንጌልን ሊሰብኩ ነው εὐαγγέλιον - የምስራች ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ዓለምን እንዲሁ ወዷል ፤ ወልደ እግዚአብሔር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ኃጢአታችሁን በመስቀል ላይ ተሸክሞ እንዲሁ በጸጋው ድናችኋል እያሉ የምስራቹን መልካም ዜና ወደ ዓለም እየሰበኩ አሰራጩ። በእርግጥ ከእነርሱ ስነ አመክንዮን እየተጠቀሙ የተጠበቀው መሢሕ በእውነትም ኢየሱስ እንደኾነ የክርስትናን እውነታ መጽሐፍ እየጠቀሱ ሞግተዋል ይህም ዐቃቤ እምነት ያደርጋቸዋል። ነገር ግን ዐቃቤ እምነት ብቻ አልነበሩም የምስራቹ ወንጌል ሰባኪያን ናቸው እንጂ።

አሁን ላይ ከኦርቶዶክሳዊያን ወገን ጥሩ የዕቅበተ እምነት ሥራዎች እየተሠሩ ነው በዚህም እንደሰታለን። ነገር ግን ከፕሮቴስታንት አንድ መማር ያለብን ነገር አለ የወንጌል ሥርጭት። ወንጌል ዕቅበተ እምነት ብቻ አይደለም ለተጨነቁት መድኃኒት ላጡት ይኸው መድኃኒት ብሎ መስበክ ነው ፤ ደስታ ለራቃቸው ኹል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ እያሉ ማስደሰት ነው ፤ ፍቅር ለራቃቸውም ኢየሱስ ይወዳችኋል ስለ ኃጢአታችሁ ሞቶላችኋል እያሉ ማጽናናት ነው።

በእርግጥም ፍቅር የኾነው ኢየሱስ ይወደናል ስለዚህ በፍቅሩ እንኑር ፍቅሩንም ለኹሉም እናጋራ ፤ ደቀ መዛሙርቱ መኾናችን የሚታወቀው በምናቀርባቸው ሙግቶችና ባለን እውቀት ደረጃ ሳይኾን ከፍቅራችን የተነሣ ነውና!

❤ 116 👍 16 🔥 7 🥰 7
24 January 2025
ኪ
10:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 44 👍 3 👎 1 🥰 1
26 January 2025
ኪ
23:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገረ ክርስቶስን ለመማር ብዙ ሰው በሳምንት 2 ቀን ከሰኞ እስከ አርብ መርጧል ስለዚህ በቀጣዮቹ ጊዜያት ውስጥ መቼ እንደሚጀመርና በምን በምን ቀናት እንደኾነ አሳውቃለሁ መልካም አዳር።
👍 119 ❤ 8 🥰 1
29 January 2025
ኪ
09:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ዛሬ ለምናከብራት የሴቶች ትምክህት እና ክብር ለኾነችው እናትና ድንግል ምስጋና ይኹን። ፍጥረት ኹሉ ይደሰት ፣ ሴቶችም ይክበሩ  ፣ የሰው ልጅ ይዘምር ፣  ደናግልም ይመስገኑ ኃጢአት በበዛችበት የእግዚአብሔር ጸጋ በዝታለችና! ዛሬ ኤዚህ እንድንሰበሰብ የጠራችን ድንግል ማርያም ናት ... እርሷ የድንግልና ቅድስት መዝገብ፣ የኹለተኛው አዳም መንፈሳዊ ገነት፣ የባሕርያት ተዋሕዶ የተፈጸመባት አውድ፣ የድኅነት ገበያ፣ ክርስቶስ የሰውን ባሕርይ የነሣባት ሰርግ ቤት ፣ የመለኮታዊ ልደት እሳት ያላቃጠላት ሕያዊት ሐመልማል፣ ኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን የተሸከመች ፈጣኗ ቀሊል ደመና ፣ ዝናም የወረደባት የጌድዮን ጸምር ፣ ገረድና እናት ፣ ድንግልና ሰማይ ናት።" (ቅዱስ ኤራቅሊስ ዘቁስጥንጥንያ - Proclus of Constantinople Homily I to the Theotokos)

@KidanZeIyesus
❤ 134 🙏 12 👍 7 🥰 1
ኪ
21:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከልብ የመነጨ ጥያቄ ለፕሮቴስታንቶች

ቤተክርስቲያን የሰዎች ስብስብ በመኾኗ ትሳሳታለች የማይሳሳት ብቸኛ ባለሥልጣን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ይባላል። ጥያቄዬ ቤተክርስቲያን የሰዎች ስብስብ እንደኾነች ኹሉ የትኛውም የፕሮቴታንት "አብያተ ክርስቲያናትም" ቢኾኑ የሰዎች ስብስብ በመኾናቸው የሚሳሳቱ ናቸው። ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ መረዳት የቤተክርስቲያንን ትተን የእናንተን ለምን እንቀበል? ስህተት የሠራችው ቤተክርስቲያን ሳትኾን እናንተ ብትኾኑስ? የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ትርጓሜን እንይ ትሉ ይኾናል በእናንተ Sola scriptura framework የራሳችሁን የግል መረዳት "የማይሳሳተው የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ" በሚል ሽፋን ከቤተክርስቲያን አባቶች ትርጓሜ በላይ በማድረጋችሁ የአባቶች ስምምነት ያለባቸውን አስተምህሮዎች ጭምር ተሳስተዋል በሚል assumption dismiss ታደርጋላችሁ። ለምሳሌ ቀዳምያኑ ሐዳስያን ጆን ካልቪንና ማርቲን ሉተር በunconditional election ያምናሉ ነገር ግን የጥንቷ ቤተክርስቲያን አባቶች በአንድ ድምጽ በ Conditional election ያምናሉ (And don't dare to quote Augustine here) ስለዚህ በዚህ አስተምህሮ መሠረት የተሳሳተው ማነው አብዛኞቹ የቤተክርስቲያን አባቶች ወይስ ሉተርና ካልቪን?

የአባቶች consensus ኖረውባቸው የማትቀበሏቸው አስተምህሮዎች አሉ? ካሉስ እኛ ተሳስተናል ከማለት ይልቅ ቤተክርስቲያን ተሳስታለች ወደ ማለት ለምን አደላችሁ?

@KidanZeIyesus
🥰 32 👍 20 ❤ 3
30 January 2025
ኪ
07:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
Sola Scriptura ወደ Solo Scriptura ሲወድቅ

Sola Scriptura ማለት የማይሳሳተው ብቸኛ ባለሥልጣን መጽሐፍ ቅዱስ ነው ሌሎች ባለሥልጣናት (የቤተክርስቲያን ትውፊት ፣ የቤተክርስቲያን አባቶች) ምንም ጠቃሚ ቢኾኑም ሊሳሳቱ ይችላሉ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መመዘን አለባቸው የሚል ሃሳብ ነው ይህም የቀዳምያኑ ሐዳስያን ታሪካዊ ፕሮቴስታንታዊ አቋም ነው። Solo Scriptura ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛ የማይሳሳት ብቻ ሳይኾን ብቸኛ ባልሥልጣን ነው ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም የቤተክርስቲያን ትውፊትም ኾነ የአባቶች ትርጓሜ አያስፈልጉም ይላል።

እነዚህ ኹለቱ አቋሞች በtheory ደረጃ የተለያዩ ናቸው ነገር ግን ወደ practice ስናመጣቸው ወደ አንድነት መምጣታቸው አይቀርም ምክንያቱም Sola Scriptura ነው የምናምነው የሚሉ ሰዎች እነርሱ የማይቀበሏቸውን አስተምህሮዎች የቤተክርስቲያን አባቶች በስምምነት አስተምረው ሲያገኙት አባቶች ለመተርጎም አስፈላጊ ቢኾኑም አይሳሳቱም አላልንም ስለዚህ በዚህኛው ጉዳይ ተሳስተዋል ስለዚህ አልቀበልም ይላሉ። ታድያ በSolo Scriptura የሚያምኑትስ ከዚህ የተለየ ምን አደረጉ ከራሳቸው አስተምህሮ ጋር ሲገጥምላቸውማ እነርሱም ቢኾኑ የአባቶችን ትርጓሜ ልክ ነው ማለታቸው አይቀርም። ለምሳሌ አንድ ጊዜ ያጋጠመኝን ልንገራችሁ ልጁ በ Sola Scriptura ነው የማምነው አለኝ እሺ የአባቶች ትርጓሜ value አለው ብለህ የምታምን ከኾነ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኹለተኛይቱ ሔዋን መኾኗን ከ2ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያሉ አባቶች በአንድ ድምጽ አስተምረዋል ትቀበላለህ? ስለው "አልቀበልም መጽሐፍ ቅዱስ አይላትምና አባቶቹ ተሳስተዋል" አለኝ። አባቶች ከእናንተ ጋር ሲስማሙ ብቻማ መቀበል የአባቶች ትምህርት value አለው ብሎ ማመን ሳይኾን post fact justification ይባላል already የምታምኑበት የ reformers tradition አለ ከእዚህ tradition ጋር የሚስማሙ አባቶችን ትቀበላላችሁ የማይስማሙትን ደግሞ አትቀበሉም።

አባቶች በስምምነት ያስተማሩትን ከእናንተ tradition ጋር ስላልገጠመ ተሳስተዋል ብላችሁ የምትጥሉ ከኾነ ሌሎች ደግሞ ተነሥተው ከእነርሱ tradition ጋር ስላልገጠመ ብቻ "የኒቅያ አባቶች ተሳስተዋል ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም" ወይም "የቁስጥንጥንያ አባቶች ተሳስተዋል ጥምቀት ለኃጢአት ሥርየት አይደለም" ቢሉ እናንተ ካደረጋችሁት የተለየ ምን አደረጉ sola scriptura በአባቶች ትምህርት limit የሚበጅለት የቱ ጋር ነው? የአባቶችን መሳሳት እና አለመሳሳት በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የሚለየውስ ማነው?

@KidanZeIyesus
🔥 42 👍 17 ❤ 9 🙏 4 🥰 1 👏 1
ኪ
14:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
በCatacombs of Priscilla የተገኘው የ3ኛው ክፍለ ዘመን የእመቤታችን ምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል። በእጁ የሚጠቁመው ሰው "አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል" ሲል የተነበየው በለዓም እንደኾነ ይታሰባል። (ዘኁ 24:17)
🥰 63 ❤ 27 👍 3
31 January 2025
ኪ
10:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በቂ ነውን?

አንድ ሰው ለመዳን የሚያስፈልጉትን እውቀቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማግኘት ይችላልን? ማለትም ኹሉም እውቀቶች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይገኛሉ ለማለት ሳይኾን ለመዳን የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ዶግማዊ እውቀቶች ግልጽ በኾነ መንገድ (explicitly) ወይም ግልጽ ባልኾነ መንገድ (implicitly) ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማግኘት ይቻላል?

አይቻልም ብላችሁ የምትከራከሩ አንድ ወጥመድ ውስጥ ትገባላችሁ እርሱም ለመዳን የሚያስፈልጉ እውቀቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት እንደሚቻል መጽሐፍ ቅዱስም ኾነ የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ጽፈዋል የቤተክርስቲያን አባቶችማ ከዚህም ገፍተው ስለ ዶግማዊ ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሰን ካላስተማርናችሁ አትቀበሉን ሲሉ ጽፈዋል እስቲ ጥቂት ምሳሌ እንመልከት:

John 20 አማ - ዮሐንስ
30: ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤
31: ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል። (ኹሉ ነገር አልተጻፈም ለእምነትና ለሕይወት በቂ የኾኑት ነገሮች ግን ተጽፈዋል)

2 Timothy 3 አማ - 2ኛ ጢሞቴዎስ
15: ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።
16-17: የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

Gregory of Nyssa
"What then is our reply? We do not think that it is right to make their prevailing custom the law and rule of sound doctrine. For if custom is to avail for proof of soundness, we too, surely, may advance our prevailing custom; and if they reject this, we are surely not bound to follow theirs. Let the inspired Scripture, then, be our umpire, and the vote of truth will surely be given to those whose dogmas are found to agree with the Divine words." (Dogmatic Treatises, Book 12. On the Trinity, To Eustathius.)
“Let the inspired Scriptures then be our umpire, and the vote of truth will be given to those whose dogmas are found to agree with the Divine words.”  (On the Holy Trinity, NPNF, p. 327)
 
Irenaeus of Lyons
 
We have learned from none others the plan of our salvation, than from those through whom the Gospel has come down to us, which they did at one time proclaim in public, and, at a later period, by the will of God, handed down to us in the Scriptures, to be the ground and pillar of our faith. (Against Heresies, 3.1.1)


Athanasius of Alexandria
These are fountains of salvation, that they who thirst may be satisfied with the living words they contain. In these alone is proclaimed the doctrine of godliness. Let no man add to these, neither let him take ought from these. For concerning these the Lord put to shame the Sadducees, and said, ‘Ye do err, not knowing the Scriptures.’ And He reproved the Jews, saying, ‘Search the Scriptures, for these are they that testify of Me.’ (Festal Letter 39, 6–7)

“Vainly then do they run about with the pretext that they have demanded  Councils for the faith’s sake; for divine Scripture is sufficient above all things.” ( Letter, De Synodis, Par. 6; 296)


እነዚህን ካየን ይብቃንና እነዚህ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡልን ለመዳን የሚያስፈልጉ ዶግማዎች በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት እንደምንችል ነው። ይህ ማለት ታድያ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ በቂ ነውን? የሚለውን ጥያቄ ስንመለከት "በቂ" የሚለው ቃል ምን ማለት ነው የሚለውን መገምገም አለብን። እኛ መጽሐፍ ቅዱስ ለመዳን የሚኾኑ እውቀቶችን በሙሉ ይዟል ነገር ግን እነዚህን እውቀቶች በጽሑፍ ደረጃ ነው እንጂ የያዘው ለእነዚህ እውቀቶች contextኡን የያዘው የቤተክርስቲያን ትውፊት ነው እንላለን (The Church is the active agent of infallibility )፤ ይህን Material sufficiency of Scripture ብለን ልንጠራው እንችላለን። ዶግማዎቻችን እንዳለ የሚወጡት ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው ለእዚህ መጽሐፍ ግን infallible በኾነ መንገድ ትርጓሜ የምትሰጠው ቤተክርስቲያን ናት። በአጭሩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቢያንስ implicitly እንኳን የሌለ ዶግማ የለንም።

ይህን በምሳሌ ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሕንፃ የሚሠራበት blue print ነው ፣ ሕንጻው ደግሞ የቤተክርስቲያን ዶግማዋ ነው blue printኡ ላይ የሌለ ነገር አይሠራም ነገር ግን blue printኡ ብቻውን ሕንፃ አይኾንም context የሚሠጠው የቤተክርስቲያን ትውፊት ያስፈልጋል።

በመጨረሻም ይህ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማይገኙ ትውፊቶች የለንም ማለት አይደለም ይልቅስ ዶግማ የኾኑ ትውፊቶች መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የማይገኙ የሉንም ማለት ነው።

@KidanZeIyesus
👍 55 ❤ 8 👏 8 🥰 1
ኪ
22:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
"Therefore, Christ Himself is the doctrine of the Father. He is the Word of the Father, and what Christ teaches is Himself so that believers may acquire Him. He is both the doctrine and the One who is of the Father. He is the divine, unchangeable doctrine—not merely a teaching expressed in words and letters, but the One who is eternally one with the Father. He leads us to the Father for reconciliation and conformity with His love." St. Augustine: On the Gospel of St. John, tractate 29:3

ኧረ ምን አይነት ንግግር ነው ቅዱስ አውግስጢኖስ ልቤን አቀለጠው የማይለወጥ ዶግማችን ኢየሱስ ነው ❤️

@KidanZeIyesus
❤ 65 👍 4 🔥 3 🥰 1
1 February 2025
ኪ
11:44
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሕፃናት ቁርባን

ከካቶሊኮች እና የክርስቶስን ሥጋና ደም አማናዊነት ከሚመቀበሉ ፕሮቴስታንቶች ዘንድ አንድ ግርም ያለኝ ልምምድ ሕፃናትን ቁርባን መከልከላቸው ነው። በእነዚህ "አብያተ ክርስቲያናት" ሕፃናትን ማጥመቅ ትክክል እንደኾነ ይታመናል በተለይ በካቶሊክና በሉተራን ዘንድ ሕፃናት የሚጠመቁት ለድኅነትና ለዳግም ልደት ነው። ነገር ግን እንደዚህ ዳግመኛ በክርስቶስ የተወለዱ ሕፃናት ቁርባን ይከለከላሉ። በጥምቀት የክርስቶስ አካላት ከኾኑ የክርስቶስን አካላት ሥጋና ደሙን እንዴት ይከለከላሉ? በተለይ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሕፃናትም መቁረብ እንዳለባቸው በግልጽ ባስተማሩበት ኹኔታ።

ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘሂፖ እንዲህ ይላል "በሕፃንነት ውስጥ ኢየሱስ የሚያድነው ምንም ነገር የለውም የሚሉ ለእነዚህ ለሚያምኑ ሕፃናት ክርስቶስ ኢየሱስ መኾኑን እየካዱ ነው ... ኢየሱስ ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ነው። በእነርሱ ምንም የሚያድነው የለም ማለት ክርስቶስ ለእነርሱ ኢየሱስ አይደለም ማለት ነው። ለተጠመቁ ሰዎች ክርስቶስ ኢየሱስ አይኾንላቸውም የሚለውን ሃሳብ የምትታገሱ ከኾነ እምነታችሁ ጤናማና ርቱዕ ነው የሚለው ያጠራጥረኛል። አዎ ሕፃናት ናቸው ነገር ግን ምሥጢራቱን ይቀበላሉ፤ ሕፃናት ናቸው ነገር ግን በራሳቸው ሕይወት እንዲኖራቸው ከጠረጴዛው ይካፈላሉ።" (Augustine, Sermon 174, 7)

የሐዋርያት ድንጋጌም እንዲህ ይላል "ጸሎቱን የጸለያችሁ ንዑሰ ክርስቲያን ፣ ሰሚዎችና መናፍቃን ኹሉ ውጡ ማንም አይቆይ። እናቶችም ከልጆቻቸው ጋር ይቁረቡ" (Constitutions of the Holy Apostles, 8.2.12)

ኢየሱስ የሕፃናትም መድኃኒት ነው!

@KidanZeIyesus
❤ 95 👍 16 🥰 1
5 February 2025
ኪ
08:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
Church Infallibilityን ያልተረዳ ሙግት

"ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጠባቂና ባለ አደራ ናት ነገር ግን ይህ ብቻ ቤተክርስቲያንን infallible አያደርጋትም በአንድ ነገር ትክክል ኾነች ማለት በኹሉ ነገር ትክክል ናት ማለት አይደለምና።" የሚለው የፕሮቴስታንቶች ሙግት ነው። ነገር ግን ይህ ሙግት የቤተክርስቲያንን አይሳሳቴነት የተረዳ አይመስልም እኛ ቤተክርስቲያን በኹሉ ነገር ትክክል ናት አላልንም እኛ ያልነው ቤተክርስቲያን በአባቶች ስምምነት ባስተማረችው አስተምህሮ ላይ ስህተትን ልትሠራ አትችልም ነው።

ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ስትወስን ከተጠቀመቻቸው መሥፈርቶች ውስጥ "ሐዋርያዊ ጸሐፊነት (ከሐዋርያትና የእነርሱ ቅርብ ደቀ መዛሙርት) ፣ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትና ትክክለኛ አስተምህሮ" ይገኙበታል። መሥፈርቶቹ እነዚህ መኾናቸውን ፕሮቴስታንቶች ራሱ የሚቀበሉት ነው። እስቲ ከነዚህ መሥፈርቶች ትክክለኛ አስተምህሮን ለይተን እንየው። ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ስትወስን ከነበሩት መጽሐፍት ውስጥ ትክክለኞቹን የለየችው ከሐዋርያት በተቀበለችው ትክክለኛ አስተምህሮ መዝና ነው የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ደግሞ ሊሳሳት ስለማይችል መጽሐፉም ሊሳሳት አይችልም እንላለን።

ፕሮቴስታንቶች ግን ቤተክርስቲያን በአስተምህሮዋ ልትሳሳት ትችላለች ብቻ ሳይኾን ተሳስታለች ብለው ያምናሉ ስለዚህ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን የመረጠችው በተሳሳተ መሥፈርት ነው። መሥፈርቱ ከተሳሳተ ደግሞ የመሥፈርቱ ውጤትም ስህተት ያለበት ነው የሚኾነው። Fallible list of infallible books ነው የምንቀበለው ቢሉ ራሱ እነዛ listኡ ብቻ ሳይኾን መጽሐፍቱም ጭምር ከመጀመሪያውኑ infallible ለመኾናቸው ምሥክርነት አይኖራቸውም መጽሐፍቱ ራሱ የተመረጡት በተሳሳተ መሥፈርት ላይ ተመርኩዘው ነውና።

@KidanZeIyesus
❤ 54 👍 6 🔥 5 🥰 2 🙏 2
6 February 2025
ኪ
07:36
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወልድ ዋሕድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተን ብቻ እንገዛለን ፣ አንተን ብቻ እናመሰግናለን፣ የነፍንሳችን ዕረፍቷ አንተ ነህ፤ ካንተ ውጪ ኹሉ ነገር ሞት ነው ፤ በሞትህ ሕይወትን የሰጠህ አንተ ነህና!! እንዴት ይገርማል! እንዴት ሰው እየሞተ ሕይወትን ይሰጣል ፣ እንዴትስ እየታመመ ይፈውሳል ፣ እንዴት እየቆሰለ ይጠግናል፣ ኢየሱስ ሆይ አስገረምከን፤ አይናችን አይታሃለች፣ በልባችን ላይ ተሰቅለሃል፣ አንዴ ላትጠፋ አብርተህብናል፣ አንተን ባየ አይናችን ሌላው ኹሉ ጨለማ ነው፤ በሞትህ ያልታመነ ኹሉ ሟች ነው፤ በብርሃንህ ያልተመላለሰ ልቡ ጨለማ ነው። በአንተ ሞትን ላንፈራ ቆርጠናል በመስቀል ላይ አይቶህ ልቡ ካንተ ጋር ያልተሰቀለ ሕይወቱ ምንድነው? እኛስ ሕይወታችን አንተን መርጠናል፤ ከጎንህ በፈሰሰ ውኃ ታጥበን ልጆችህ ኾነናል፤ ሥጋህንም በልተን በአንተ ላይ ጸንተናል፤ ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሔዳለን? አንተ የሕይወት ምንጯ ነህና! ኢየሱስ ሆይ በልባችን ፍለቅ።

@KidanZeIyesus
❤ 113 🙏 10 👍 8 ❤‍🔥 7 🥰 1
9 February 2025
ኪ
15:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች ምን ደስ የሚል ሃሳብ ሰማው መሰላችሁ መቁረብ እየፈለጋችሁ ነገር ግን አከባቢያችሁ አላመቻች ያላችሁ ሰብሰብ ብለን አንድ ጀማ ፈጥረን በአንድነት ቀን ተይዞ አንድ ቤተክርስቲያን ብንቆርብስ ምን ትላላችሁ?
❤ 92 👍 19 🔥 4 🥰 1 🤮 1
10 February 2025
ኪ
10:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
በእንተ ጾመ ነነዌ

የነነዌ ሕዝብ በነቢዩ ዮናስ ማስጠንቀቂያ 3 ቀን (Septuagint 3 ቀን ቢልም ፣ ዕብራይስጡ 40 ቀን ይላል ነገር ግን መጽሐፉ የጾሙን ወቅት በሙሉ ምግብ ኣልቀመሱም ስለሚል ትክክለኛው 3 ቀን ነው ወደሚለው ያደላል) በጾማቸው ከእግዚአብሔር ከመጣባቸው ቁጣ እንዴት እንደተረፉ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን። ነገር ግን ቤተክርስቲያናችን እንዴትና መቼ ጾሙን መጾም እንደጀመረች ታውቃላችሁ?

ነነዌ የጥንቷ "ንስጥሮሳዊት" ምስራቃዊት ቤተክርስቲያን ("Nestorian" Church of the East :Nestorian is in quotation because they have nothing to do with Nestorius just their theology is identified as "Nestorian") ስር የምትገኝ መንበር ናት። በ6ተኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ረሃብ ይህቺ ቤተክርስቲያን የምትገኝባትን ጥንቷን ሜሶፖታምያ መታት ስለዚህም ቤተክርስቲያኒቷ የነነዌ ሕዝብ በጾም የእግዚአብሔር ቁጣ እንደተወገደላቸው እነርሱም ከረሃቡ ለመትረፍ እንደ ነነዌ ሕዝብ የጾምና የጸሎት ጊዜን አወጁ ፤ ረሃቡም ስለተወገደላቸው በየዓመቱ ጾሙን ያስቡታል። የዚህች ጥንት ቤተክርስቲያን ቅጥያ የኾኑት የአሦር ምስራቃዊት ቤተክርስቲያን (Assyrian Church of the East) እና ወደ ካቶሊክ የተቀላቀለችው የካልዲያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን (Chaldean Catholic Church) እስካሁን ድረስ ጾሙን ያስቡታል።

የጥንቷ ምእራብ ሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከምስራቅ ሶርያዋ ቤተክርስቲያን ጋር ቅርበት ስለነበረባት ይህንን ጾም ከ7ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንዲሁ ማሰብ ትጀምራለች። እንዲሁም በ10ኛው ክፍለ ዘመን ሶርያዊው የእስክንድርያ ፓትሪያሪክ አብርሃም (የእስክንድርያ 62ኛ ፓትሪያሪክ) ጾሙን ከሶርያ አምጥቶ በእስክድርያ ስር ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ኹሉ እንዲታሰብ አደረገ። እንዲህ ባለው ኹኔታ እንግዲህ ቤተክርስቲያናችን ላለፉት 1000 ዓመታት ጾሙን ስታስበው ቆይታለች።

መልካም ጾም!

@KidanZeIyesus
❤ 54 👍 9 🥰 1
11 February 2025
ኪ
07:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገረ ክርስቶስ

ስለ ክርስትና ለማወቅ መሠረቱ ክርስቶስን ማወቅ ነውና ነገረ ክርስቶስ ትምህርትን ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ዘወትር ማክሰኞና ሐሙስ ምሽት 2:30 ላይ እዚሁ live እንጀምራለን።

የመጀመሪያ ርእስ: ዘለዓለማዊ ልደት ( Eternal Generation)

τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων!

ከዘመናት በፊት ከአብ የተወለደ!


@KidanZeIyesus
❤ 93 👍 6 🫡 2 🔥 1 🥰 1
ኪ
23:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
ምእመናን አላችሁ 😁

ያው የነበረን Discussion ላይ እነርሱ ፖለቲካ ለመሥራት ብለው ወደ ዋናው ነጥብ መግባት ባይፈልጉም እኛ ግን ሐሙስ ማታ 2፡30 ላይ እዚሁ live ገብተን ሃሳቡን በታትነን እናየዋለን እናንተ ግን እስከዛው ይህንን እያነበባችሁ ቆዩልኝ።

@KidanZeIyesus
👍 44 🔥 15 👏 2 🥰 1 🤝 1
12 February 2025
ኪ
12:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
Double Standard and Special Pleading on the Canon

የሐዲስ ኪዳንን የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖናን የማወቅ process በቤተክርስቲያን ውስጥ ከኹለተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ 4ተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ያለቀ ነው። ቤተክርስቲያን በ4ተኛው ክፍለ ዘመን በአብዛኛው 27ቱ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቀኖናውያን ስለመኾናቸው ስምምነት ላይ ደርሳለች (Consensus Patrum) ይህም የኾነው በአባቶች ስምምነት ብቻ ሳይኾን ቤተክርስቲያንንም በሚጠብቃት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው በዚህ ኹሉም አብያተ ክርስቲያናት ይስማማሉ።

በዚህ ጉዳይ ግን በፕሮቴስታንቱ ዘንድ ያለውን inconsistency ላሳያችሁ። የመጀመሪያው Double standard Consensus Patrum ላይ ነው። የቤተክርስቲያን አባቶች በስምምነት የደረሱባቸውን አስተምህሮዎች በሙሉ fallible ስለኾኑ infallible በኾነው መጽሐፍ ቅዱስ መዝነን ብቻ ነው ምንቀበለው ይሉና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቀኖና ላይ ግን የመንፈስ ቅዱስ ጥበቃ አለበት በማለት የአባቶችን ስምምነት ይቀበላሉ። ለምን? በቀኖናው ጉዳይ infallible የኾነው መዛኝ እራሱ እየተመዘነ ስለኾነ የሚመዝኑበት ሌላ infallible መዛኝ ስለሌላቸው እዚህ ላይ ያለውን consensus በእምነት መቀበል ግድ ይላቸዋል you see the double standard. እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ላንሳ በቀኖናው ጉዳይ የአባቶችን consensus ከተቀበላችሁ ሌሎቹን የአባቶች consensus የማትቀበሉበት ምክንያት ምንድነው? ለምሳሌ Apostolic succession, Eucharist as a sacrifice , Conditional election. ወይም ደግሞ የአባቶች ስምምነት ኖረውባቸው የማትቀበሏቸው አስትምህሮዎች የሉም?

ኹለተኛው issue ደግሞ Special Pleading ነው ቤተክርስቲያን generally fallible ናት ብለው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ጉዳይ ስምምነት ላይ ለመድረስ የመንፈስ ቅዱስ ጠብቆት ነበረበት ማለታቸው ነው። እሺ ይሄን እንቀበላችሁና ቤተክርስቲያን generally fallible ብትኾንም በሌሎቾ አስተምህሮዎቿ ላይ በመንፈስ ቅዱስ ጠብቆት አባቶች ወደ ስምምነት መድረሳቸውን ለምን አንቀበልም? (Which is indistinguishable from infallibility at this point.) Why apply one rule (i.e. the Holy Spirit's preservation) to scripture (which is one part of divine revelation) and exempt it from Apostolic tradition (which is the other part of divine revelation)? ይህ classic case of special pleading fallacy ነው።

@KidanZeIyesus
👍 42 ❤ 21 👏 3 🥰 1
13 February 2025
ኪ
22:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – Sola
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:30:38, 27.6 MB
Sola Scriptura discussion. (መጀመሪያ አከባቢ ያለውን የቴክኒክ ችግር ከስንፍና የተነሣ ስላልቆረጥኩ ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ 😁)
https://t.me/KidanZeIyesus
👍 32 🤗 3 ❤ 2 🤝 2 🥰 1
14 February 2025
ኪ
07:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቫላንታይንስ ዴይን ሲንግል ኾናችሁ የፍቅር ደብዳቤ ያልደረሳችሁ ክርስቲያኖች በሙሉ አይዞአችሁ የቅዱስ ጳውሎስን መልክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች አንብቡ "ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።" ይላችኋልና ከዚህ በላይ የፍቅር ደብዳቤ ኬት ታመጣላችሁ 😁

ቲም ፖልነት ይለምልም 🙌🏽
😁 121 ❤ 45 👍 4 🫡 4 🙏 2 🥰 1
15 February 2025
ኪ
21:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
"Against Eunomius" ቀጸዶቅያኖቹ እኮ ተባብረው ቀጠቀጡት 😂
😁 50 🤣 16 🤓 2 👍 1
18 February 2025
ኪ
09:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገረ ክርስቶስ

ስለ ክርስትና ለማወቅ መሠረቱ ክርስቶስን ማወቅ ነውና ነገረ ክርስቶስ ትምህርት ዘወትር ማክሰኞና ሐሙስ ከዛሬ ጀምሮ

ማታ 2፡30
ርእስ: ዘለዓለማዊ ልደት ( Eternal Generation)

τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων!

ከዘመናት በፊት ከአብ የተወለደ!


@KidanZeIyesus
❤ 60 👍 13 🥰 1
ኪ
22:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – ነገረ ክርስቶስ ክፍል 1፡ ዘለዓለማዊ ልደት
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:14:10, 24.5 MB
መሠረታዊ የነገረ ክርስቶስ ትምህርት ክፍል አንድ።
https://t.me/KidanZeIyesus
❤ 47 🙏 9 🥰 6 👍 1
19 February 2025
ኪ
23:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:45:18, 377.8 MB
❤ 23
23:07
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – sola
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:43:30, 34.1 MB
❤ 19 🥰 4 👍 1
23:07
የተነጋገርንበት pdf ይህ ነው ከዚህ ተከታተሉት
https://t.me/KidanZeIyesus
❤ 23 🥰 7 👍 2
21 February 2025
ኪ
18:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
ታላቁ ጾም

በክርስትናችን ከምንም ጊዜ በላይ የምንናፍቀው ጊዜ የአጽዋማት ኹሉ ጾም ዓቢይ ጾም ደርሷል። ዓቢይ ጾም 8 ሳምንታትን ሲይዝ የ3 አጽዋማት ጥምር ነው: የመጀሪያው ሳምንት የዝግጅት ሳምንት ("ጾመ ሕርቃል" (ሕርቃልን በትምህርተ ጥቅስ ያደረኩት ሕርቃል ከመነሳቱ በፊትም ቢኾን ይህ ሳምንት በጾም ይታሰብ ስለነበር ከሕርቃል ጋር መያያዙ ስህተት መኾኑን ያሳያል) ፣ ቀጣዮቹ 6 ሳምንታት (40 ቀናት) ጾመ ኢየሱስ ፣ የመጨረሻው ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ናቸው።

ኢየሱስ የጾመው 40 ቀናት ኾኖ ሳለ ጾሙ ለ8 ሳምንታት መጾሙ ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ማስረጃ ይገኝለታል? አዎ ዛሬ አንድ መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ Egeria's Pilgrimage ይባላል። ኢጌሪያ የምትባል ሴት የጻፈችው ሲኾን ከ381-384 ዓ.እ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛ በቤተክርስቲያን ስላየቻቸው ሥርዓቶች ትጽፋለች። መጽሐፉን ብታነቡት ስለቤተክርስቲያናችን ጥንታዊነት በደምብ ትገነዘባላችሁና ጋበዝኳችሁ።

ዛሬ ግን ማተኮር የፈለኩት ስለዓቢይ ጾም ነውና የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን በ4ተኛው ክፍለ ዘመን የዓቢይ ጾምን እንዴት ትጾም ነበር የሚለውን በChapter 27 ላይ እንዲህ ትጽፋለች
"here they observe the eight weeks before Easter. This is the reason why they observe eight weeks: On Sundays and Saturdays they do not fast, except on the one Saturday which is the vigil of Easter, when it is necessary to fast. Except on that day, there is absolutely no fasting here on Saturdays at any time during the year. And so, when eight Sundays and seven Saturdays have been deducted from the eight weeks—for it is necessary, as I have just said, to fast on one Saturday—there remain forty-one days which are spent in fasting, which are called here eortae, that is to say, Lent."


"እዚህ [ኢየሩሳሌም ] ከፋሲካ በፊት ያሉትን 8 ሳምንታት በጾም ያስቧታል ምክንያቱም እንዲህ ነው የትንሣኤ ዋዜማ ከኾነችው አንዲት ቅዳሜ ቀን ውጪ ቅዳሜና እሑድ አይጾምም። በዚህች ቅዳሜ [ቀዳሚት ሥዑር] መጾም የተገባ ነው በሌሎች ቅዳሜያት ግን ፍጹም አይጾምም። ስለዚህም 8 እሑዶችና 7 ቅዳሜያት ሲቀነሱ 41 ቀናት ይቀራሉ ይህም የዓቢይ ጾም ተብሎ ይጠራል።

ጾምን ለመጾም በጾም የምትዘጋጀዋ ቤተክርስቲያናችን የተባረከች ትኹን እውነተኛ ቅበላ ይህ ነውና።

https://t.me/KidanZeIyesus
❤ 63 🙏 12 👍 6 🥰 1
22 February 2025
ኪ
12:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
አብ አኃዜ ኩሉ (ኹሉን የያዘ አባት)

ብዙ ጊዜ ስለክርስቶስ እናወራለን ፣ እንናገራለን ፣ እንሰብካለን እርሱ የድኅነታችን ቀንድ የሃይማኖታችን ራስ ነውና! እስቲ ደግሞ ዛሬ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ስለተባለው ኹሉን ስለያዘ አባት እግዚአብሔር አብ እንናገር።

የኹሉ አስገኚ አብ ነው ለእርሱ ግን አስገኚ የለውም ይልቅስ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ ራሱ መገኛቸው ነው። አባቶቻችን ሐዋርያት በአመክንዮአቸው "እስመ አልቦ ውስተ ህላዌሁ አመክንዮ ... አላ ባሕቱ ህልው በኩሉ መዋዕል አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት። ወአልቦ ዘይክል ቀሪበ ኀቤሁ። ኢኮነ ክልዔተ ወኢሠለስተ ወኢይትዌሰክ አላ አሐዱ ውእቱ ባሕቲቱ ዘይነብር ለዓለም - ለመገኘቱ ምክንያት የለበትም በአስገኝነት ብቻውን በዘመናት ኹሉ ይኖራል እንጂ ጅማሬም የለውም ፍጻሜም የለውም ማንም ሊቀርበው አይችልም ኹለተኛም አይደለም ሦስተኛም አይደለም አይጨመርበትም ብቻውን ለዘላለም የሚኖር አንድ ነው እንጂ።" እያሉ የአብን አኗኗር እና አስገኚ የማያሻው ብቸኛ አስገኚነት ይነግሩናል።

አብ ለኹሉም ነገር መሠረት ነው ለቃሉ እና ለእስትንፋሱ መሠረት ኾኖ በእነርሱ ዓለማትን ፈጥሯል ፣ ቃሉ እና እስትንፋሱም መገኛቸው ከእርሱ ነው ነገር ግን ይህ አስገኚነት ዓለማትን እንዳስገኘበት ያለ አስገኚነት አይደለም ፣ አብ ከዓለማት በፊት ነበረና ከቃሉ እና ከአስትንፋሱ በፊት ግን አልነበረም አብ ከቃሉ እና ከእስንፋሱ ውጪ የኖረበት ጊዜ አለ ካልን ቃል የሌለው ዲዳ እና እስትንፋስ የሌለው ምውት እናደርገዋለን። የቃል ከአብ መገኘት ዘላለማዊ ልደት (Eternal Begetting) ስንለው የእስትንፋስን ከአብ መገኘት ዘላለማዊ ሥርጸት (Eternal Procession) እንለዋለን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከአብ መገኘታቸው በዘላለማዊ ጊዜ ውስጥ ነዋና ስለዚህ ነው አባቶች "ልደቱ ለወልድ ወጸአቱ ለመንፈስ ቅዱስ ዘኢይኀልቅ-የወልድ መወለድ እና የመንፈስ ቅዱስ መውጣት አያልቅም" የሚሉት በዘላለም ውስጥ ከመሠረታቸው አብ እየወጡ ይቀጥላሉና ይህ ትምህርት በቀጰዶቅያ አባቶች ዘንድ Monarchy of The Father ይባላል።

ከዚ የተነሣ የኹሉ መገኛ የኾነ አንድ አምላክ አብ አለን እንላለን አብ መሠረት ነውና የሥላሴ አንዲት ባሕርይ መገኛ የእግዚአብሔር አብ አካል ነው ፣ ከአካሉ በተገኘ ባሕርይ የተወለደው ወልድም ከአብ የተነሣ ከእውነተኛው አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ እንለዋለን ፣ መንፈስ ቅዱስም ይህንኑ ባሕርይ ተጋርቶ ከእውነተኛው አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ነው።

ዓለምን በቃልህ ፈጠረህ በእስትንፋስህ ሕይወትን የሰጠህ የኹላችን አባት እግዚአብሔር አብ ሆይ በተወዳጁ ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናመሰግንሃለን አንተን ክደን በጠፋን ጊዜ በልጅህ ወደ አንተ ሰበሰብከን ፣ በመንፈስህም አጸናኸን ከፍቅርህ የተነሣ የሚያምንበት ኹሉ ሕይወትን እንዲያገኝ አንድ ልጅህን ለኹላችን ቤዛ አድርገህ ለሞት አሳልፈህ ሰጥተኸዋልና ስለዚህም እኛ ከመላእክት ጋር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እያልን እናመሰግንሃለን የሕይወታችን ባለቤት አስገኚ የሌለህ አስገኚያችን አንተ ነህና!

ያለ እርሱ ሕይወት የለንም ያለ ልጁ መዳን የለንም ያለ መንፈሱም ጽድቅ የለንም ያለ እርሱ ኹሉ አልቦ ነው! የኹሉ አባት አብ ❤️

አባት አባት ሲያሰኘኝ በአንድያ ልጁ በኩል አባ እንድለው ያደረገኝ አብን አስታውሰዋለሁ! ስለ አብ በድጋሜ የተለጠፈ

https://t.me/KidanZeIyesus
❤ 65 👍 8 🔥 3 🥰 1
23 February 2025
ኪ
12:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓቢይ ጾም የዝግጅት ሳምንት ንባብ

ማቴዎስ 6
16: “ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
17-18: አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።

የምናደርገውን ኹሉ ሰው እንዲያይልን ከኾነ የምናደርገው ዋጋችንን ከሰዎች ተቀብለናልና ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ የለንም በስውር የምናደርገውን ግን ከሰማይ አባታችን ዘንድ ወጋ እናገኝበታለን። ጾማችን ለመታየት ፣ ጾመኞች ናቸው ለመባል አይኹን ይልቅስ ብልና ነቀዝ የማያበላሸው ሰማያዊውን መዝገብ ለማግኘት ይኹን እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው "መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሠራቂ ወኢያማስኖ ፃፄ ወቁንቁኔ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ - ሌባ የማይቀርበው ብልና ነቀዝ የማያበላሸው መዝገባችን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" እንዲል አባ ጊዮርጊስ።

እንደ ግብዞች አትጹሙ ፤ እንኳን አደረሳችሁ መልካም የዓቢይ ጾም። ያው የኢትዮጵያን ምንባባት ከብዙ ቦታ ስለምታገኙት እኔ በዚህ ጾም የኮፕቲክን አቀርብላችኋለው የተባረከ የጌታ ቀን።

https://t.me/KidanZeIyesus
❤ 77 👍 3 🙏 3 🥰 1
24 February 2025
ኪ
20:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለመስቀልና ለሥዕላት ስግደት በጥንቷ ቤተክርስቲያን አለን?

አሁን እየተነሣ ካለው claim መካከል ስግደት በጥንቷ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ አካል አይደረግም የሚል ነው። ዛሬ ግን በጥንቷ ቤተክርስቲያን በአንድ አባት ደረጃ ሳይኾን በጉባኤና በቤተክርስቲያን በሥርዓተ አምልኮ ውስጥ ያሉ ኹለት ማስረጃዎችን አሳያችኋላሁ።

የመጀመሪያው በ305 ዓ.እ የተካሔደው የኤልቪራ ጉባኤ ነው። በሚያስገርም ኹኔታ ጋቪን ኦርትላንድ የተባለው ባፕቲስት አፖሎጂስት የዚህን ጉባኤ ቀኖና 36 የተሳሳተ የላቲን ትርጉም በመጠቀም ሥዕላት እንዳይሰገድላቸው ይከለክላል በማለት ጠቅሶታል። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት የጋቪን ደቀመዛሙርትም ሳያጣሩ ሲያስተጋቡት ሰምተናል። ላቲኑ እንዲህ ይላል:

"Placuit picturas in ecclesia esse non debere, ne quod colitur et adoratur in parietibus depingatur.
"
ብዙ ስኮላሮችም በትክክል እንዲህ ይተረጉሙታል "It has seemed good that images should not be in churches so that what is venerated and worshiped not be painted on the walls."
በአማርኛ እንዲህ ማለት ነው " ሥዕላት በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳይኾኑ መልካም ኾኖ ታይቶናል ሥግደትና ክብር የሚገባቸው እነዚህ በግድግዳዎች ላይ መሳል የለባቸውምና"። (Synod of Elvira Canon 36)

እዚህ ላይ ካስተዋላችሁ ሥዕላት ስግደትና ክብር እንደሚገባቸው በግልጽ ይናገራል ነገር ግን ስግደት እና ክብር ስለሚገባቸው በቤተክርስቲያን ግድግዳ ላይ መሳል የለባቸውም ይላል። የቤተክርስቲያን ግድግዳ ላይ መሣል ለምን እንደከለከሉ ግልጽ አይደለም ምናልባት ይህ ጉባኤ የተካሔደው በቤተክርስቲያን ስደት ላይ በነበረችበት የዲዮቅሊጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ስለነበር ሥዕላትን ከክብራቸው የተነሣ ጊዜያዊ ግድግዳ ላይ እንዳይሣሉ በማሰብ ይኾናል ዋና ነጥባችን ግን ስግደትና ክብር የሚገባቸው መኾናቸውን መመስከራቸው ነው።

ኹለተኛ ማስረጃ ደግሞ በ381 ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘችው ኢጌሪያ የተባለች ክርስቲያን በበዓለ ስቅለት ዕለት ኢየሩሳሌም ውስጥ በሥርዓተ አምልኮ ውስጥ እንዲህ ሲደረግ ትዘግባለች "The gilded silver casket containing the sacred wood of the cross is brought in and opened. Both the wood of the cross and the inscription are taken out and placed on the table. As soon as they have been placed on the table, the bishop, remaining seated, grips the ends of the sacred wood with his hands, while the deacons, who are standing about, keep watch over it. There is a reason why it is guarded in this manner. It is the practice here for all the people to come forth one by one, the faithful as well as the catechumens, to bow down before the table, kiss the holy wood, and then move on. "

" የተቀደሰውን መስቀል የያዘው የብር ሳጥን ይመጣና ይከፈታል። መስቀሉና ጽሕፈቱም ይወጡና ጠረጴዛው ላይ ይቀመጣሉ ። ጳጳሱም ተቀምጦ የመስቀሉን አንዱን ጫፍ ይይዛል ዲያቆናቱም ቆመው ይጠብቁታል። ይህ የሚደረግበት ምክንያት አለው ምእመናንና ንዑሰ ክርስቲያን በሙሉ እየመጡ ጠረጴዛው ፊት እየሰገዱ መስቀሉን ተሳልመው የመሔድ ልማድ አላቸውና።" (Egerias Pilgrimage Chapter 37)

ይህ ማስረጃ የሚያሳየን የኢየሩሳሌም ምእመናን ለመስቀሉ የሚያደርጉት ክብር (ስግደት ፣ መሳለም) የሥርዓተ አምልኳቸው አካል መኾኑን ነው።

@KidanZeIyesus
❤ 61 👍 7 🔥 2 🥰 1 🤔 1 🤨 1
25 February 2025
ኪ
12:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዓለም አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን (The Catholic Church)

ከቤተክርስቲያን 4ቱ ባሕርያት መካከል አንዱ ኩላዊነት ፣ ዓለምአቀፋዊነት ነው። ቤተክርስቲያን ገና ከ2ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እራሷን ካቶሊክ - ኩላዊት ብላ ጠርታለች ለምሳሌ ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ እንዲህ ይላል "Wherever the bishop appears, let the people be there; just as wherever Jesus Christ is, there is the Catholic Church - ጳጳሱ ባለበት ቦታ ኹሉ ሕዝቡም ይሰብሰብ ኢየሱስ ክርስቶስ ባለበት ኹሉ ካቶሊካዊቷ ቤተክርስቲያን አለችና” (Letter to the Smyrneans 8:2)

ካቶሊክ καθολικός (katholikos) ከሚል ግሪክ ቃል የመጣ ሲኾን Kata - about ማለት ነው holos- whole ማለት ነው አንደ ላይ About the Whole (ኩላዊ), all encompassing (ኹሉን አቀፍ), Universal (ዓለም አቀፍ) የሚል ትርጉምን ይሰጠናል። ቤተክርስቲያንም ካቶሊክ ናት ስንል በብሔር ፣ በሐገር ፣ በወገን የማትገደብ በኹሉ ያለች ፣ ስለ ኹሉ መዳን የምትሠራ ፣ ኹሉን አቅፋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምታገባ ናት እያልን ነው።

የኒቅያ-ቁስጥንጥንያ አንቀጸ ሃይማኖትም ቤተክርስቲያንን "εἰς μίαν (Mian- አንዲት) ἁγίαν ( Agian - ቅድስት) καθολικὴν (Katholiken- ኹሉን አቀፍ) καὶ ἀποστολικὴν (Apostoliken- ሐዋርያዊት) ἐκκλησίαν (Ecclesian- ቤተክርስቲያን) ይላታል። በእውነትም የጌታ ቤተክርስቲያን በሐዋርያት ተመሥርታ ኹሉን አቅፋ በአንድነት በቅድስና ለጌታ መንግሥት የምታበቃ በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ናትና።

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌምም ስለዚህች ቤተክርስቲያን እንዲህ ይላል "[The Church] is called Catholic then because it extends over all the world, from one end of the earth to the other; and because it teaches universally and completely one and all the doctrines which ought to come to men's knowledge. - [ቤተክርስቲያን] ኹሉን አቀፍ ተብላለች ምክንያቱም በዓለም ኹሉ ከጫፍ እስከ ጫፍ አለችና። እንዲሁም ሰዎች ኹሉ ሊያውቁ የሚገባቸውን አስተምህሮዎች በሙሉ በዓለም አቀፍና ፍጹም በኾነ ደረጃ ታስተምራለችና።" (Catechetical Lectures 18:23 )

ስለዚህ ለአስተምህሮ ኹሉ ማንጸሪያችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትታመነዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ናት። በአስተምህሮ ኹሉ ጉዳይም መዳን ለዓለም ኹሉ ነውና በኹሉ የሚታመነው ትምህርት የመዳን ዶግማዊ ትምህርት ነው ከዚህ በኹሉ ከሚታመነው ትምህርት ፈቀቅ ያለ ከመዳን ትምህርት ውጪ ነው እንላለን። ዶግማዊ ባልኾኑ አስተምህሮዎች ላይ በሎካል ቤተክርስቲያን ደረጃ ብቻ የሚታመን አስተምህሮ ሊኖር ይችላል ዶግማዊ የመዳን ትምህርት ግን በኹሉ የሚታመን ሊኾን ይገባል።

ይህቺን ዓለም አቀፋዊት ቤተክርስቲያን የመሠረቷት እያንዳንዱ የሚሳሳቱ ሎካል አብያተክርስቲያናት ቢኾኑም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን የማይሳሳተውን የመዳን ትምህርት ያስተላልፋሉ። የሚሳሳት + የሚሳሳት + የሚሳሳት= የማይሳሳት እንዴት ሊኾን ይችላል ብለው ለሚጠይቁን ሰዎች ደግሞ እኛ ሳንኾን ሊቁ ጠርጡልያኖስ ዘቅርጣግና ከ1700 ዓመታት በፊት እንዲህ መልሶታል " Grant, then, that all have erred...  is it likely that so many churches, and they so great, should have gone astray into one and the same faith? No casualty distributed among many men issues in one and the same result. Error of doctrine in the churches must necessarily have produced various issues. When, however, that which is deposited among many is found to be one and the same, it is not the result of error, but of tradition. - እስቲ ኹሉም [አብያተ ክርስቲያናት] ተሳሳተዋል ብለን እናስብ... እነዚህ ኹሉ አብያተ ክርስቲያናት ወደ አንድ እምነት ሊመጡ ይችሉ ነበርን? በብዙ ሰዎች መካከል የሚከፋፈል መንስኤ አንድ አይነት ውጤትን ሊያመጣ አይችልም። የአስተምህሮ ስህተት የተለያዩ ችግሮችን ባመጣ ነበር ነገር በኹሉም የተከማቸው አንድ አይነት ከኾነ የስህተት ሳይኾን የትውፊት ውጤት ነው።" (Prescription against heretics Chapter 28 )
ይህም ማለት አንድ ቤተክርስቲያን locally ወደ ስህተት ገብታለች ብንል በሌላው የሚታመነውን ማየት አለብን ምክንያቱም በኹሉም ስህተት ቢገባ ኹሉም ወደ አንድ አይነት አስተምህሮ ሊመጡ አይችሉምና በዓለም አቀፍ ደረጃ በኹሉም ለኹሉም የታመነው ትምህርት የትውፊት ውጤት እንጂ የስህተት ውጤት ሊኾን አይችልም።

በቪንሰንት ዘሌርኒስ ቃል እንዝጋው "Since the canon of Scripture is complete, and sufficient of itself for everything, and more than sufficient, what need is there to join with it the authority of the Church’s interpretation?’ For this reason: Because, owing to the depth of holy Scripture, all do not accept it in one and the same sense, but one understands its words in one way, another in another, so that it seems to be capable of as many interpretations as there are men. . . . Therefore, it is very necessary, on account of so great intricacies of such various errors, that the rule for the right understanding of the prophets and apostles should be framed in accordance with the standard of ecclesiastical and catholic interpretation” (The Notebooks 2:1–2)

ይህኛውን በራሳችሁ ተርጉሙት ዓለም አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን በኹሉ ፣ ስለ ኹሉ ፣ ለኹሉ ያለች!

@KidanZeIyesus
❤ 39 👍 12 🥰 1
ኪ
22:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 2 pdf: ሥጋዌ

@KidanZeIyesus
❤ 17 🙏 4 👍 2 🥰 1
22:24
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:37:09, 323.5 MB
❤ 11 👍 6
22:24
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – Incarnation
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:36:22, 32.5 MB
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 2፡ ነገረ ሥጋዌ ውይይት

@KidanZeIyesus
❤ 16 🙏 4 🥰 1
26 February 2025
ኪ
10:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጥያቄ: አብ የኢየሱስ አምላክ ተብሎ ወልድ ወይም የእግዚአብሔር ቃል የኢየሱስ አምላክ ለምን አይባልም?

መልስ: ወልድ የኢየሱስ አምላክ ከተባለ ኹለት ማንነቶችን የሚያሳይ ነው ወልድ የሚባልና ኢየሱስ የሚባል። ነገር ግን ወልድ ራሱ ኢየሱስ ነው እንጂ ከወልድ ሌላ ኢየሱስ የሚባል ማንነት በክርስቶስ ውስጥ የለም "የማንነት ተዋሕዶ (Prosopic Union)" የንስጥሮስ ምንፍቅና ነው ይልቅስ እኛ ወልድ የተባለው መለኮታዊ ማንነት ከድንግል የሥጋን ባሕርይ ነሥቶ ኢየሱስ ተባለ እንጂ ሰዋዊ ማንነትን አልነሣም ስለዚህም ከእግዚአብሔር ወልድ ውጪ እኔ የሚል ማንነት በክርስቶስ ውስጥ የለም። ወልድ የኢየሱስ አምላክ ነው የምንል ከኾነ የኢየሱስ ማንነት እራሱ ወልድ ስለኾነ እራሱ የራሱ አምላክ ነው ፣ እራሱ ለራሱ ይገዛል የሚል አወዛጋቢ ትምህርትን ያመጣል ይህ ደግሞ ኢየሱስን schizophrenic የሚያስመስል ነው እራሱን በራሱ የሚገዛ እንዲሁም ለራሱ የሚገዛ ያደርገዋል። ለዚህም ቅዱስ ቄርሎስ በአንቀጸ ውግዘት 6 ላይ አውግዞታል የኤፌሶን ጉባኤም አጽድቆታል።

እኛ ግን መጻሕፍት እንደሚመሠክሩት አብ የኢየሱስ አምላክ ነው እንላለን አብና ኢየሱስ በማንነት ልዩ ናቸውና የማንነቶችን ችግር አያመጣም እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል የተባለው የሥላሴ ኹለተኛ ማንነት የሥጋን ባሕርይ በመንሣቱ በሥጋው ለአብ ሊገዛ ይችላልና።

@KidanZeIyesus
❤ 28 👍 5 👌 3 👎 2 🤔 2 🥰 1
ኪ
14:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
ፍጡር የሚለው ቃል ላይ ጥንቃቄ

ፍጡር የሚለው የግእዝ ቃል በኹለት መንገድ ሊተረጎም ይችላል አንደኛው "የተፈጠረ - Created" በሚለው ኹለተኛው ደግሞ "ሕልውናው የጀመረ ፍጡር አካል - Creature" የሚልን ይይዛል።

ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው ወይም የክርስቶስ ሥጋ ባሕርይ ፍጡር ነው ስንል "የተፈጠረ - Created" ነው እያልን እንጂ "ፈጡር አካል- Creature" ነው እያልን አይደለም። ምክንያቱም ክርስቶስ creature ነው ካልን creature ማንነትን ስለሚወክል በክርስቶስ ሕልውናው የጀመረ ፍጡር ማንነት አለ እያልን ነው ከዚህ የተነሣ ክርስቶስ መቼም ቢኾን ፍጡር - Creature (κτίσμα in greek) አይባልም። ስለዚህ ክርስቶስ ማነው? ስንባል መልሳችን ኹል ጊዜ "ፈጣሪ" ይኾናል እንጂ "ፍጡር" አይባልም ፍጡር ማንነት የለውምና።

ነገር ግን በሥጋው ፍጡር ነው ስንል በሥጋው ባሕርይ የተፈጠረ (Created) ነው እንላለን። ፍጡር ስንል እያመለከትን ያለነው የመፈጠር ግብር (act of creation - κτιστός in greek) ነው እንጂ ፍጡር ማንነት (Creature, created being) አይደለም። ስለዚህ ትክክለኛውን ነገረ ክርስቶስ ኹል ጊዜ እናስተውል ክርስቶስ ማነው? ሲባል "ፈጣሪ የኾነ መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል ነው" ስንል ክርስቶስ ምንድነው? ሲባል ደግሞ " ፍጡርም ኢፍጡርም የኾነ አንድ ውሕድ ባሕርይ (One composite nature that is both created and uncreated)" ነው እንላለን።

@KidanZeIyesus
❤ 54 👍 9 🥰 4
ኪ
22:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
የስንቱን ልብ አሸነፍክ ኢየሱስ

ከ2000 ዓመታት በፊት በአንዲት የቤተልሔም በረት ውስጥ ሕፃን ልጅ እያለቀሰ ተወለደ የሚገርመው ግን ይህ ሕፃን በአንድ ጊዜ እንደማንኛውም ሕፃን ነው እንዲሁም እንደ ማንኛውም ሕፃንም አይደለም παράδοξος (Paradoxos).

ከ2 ሺህ ዘመናት በኋላ ይህ ቤተልሔማዊ ሕፃን የዓለም መነጋገሪያ እንደ ሚኾን ከትውልዱ ማን አስተዋለ? የሐዋርያትንስ ቃል ማን አመነ? የቢሊዮኖችን ልብ እንደሚማርክ ማንስ ገመተ? የግሪኮች አይደፈሬ የነበረው ፍልስፍና በፊቱ ሊቆም አልቻለም የተሰቀለው የግሪኮችን ልብ ማረከ ፤ በእስክንድርያ የተከማቸው የፈረኦኖች ጥበብ አልተቋቋመውም የግብጻውያንን ልብ አሸነፈ ፤ የሮማውያን ጣኦታትም በፊቱ ወዳደቁ ማራኪው ማረካቸው። ምድራዊ ሰይፍ የክርስቶስ መለኮታዊ የፍቅር ሰይፍ ፊት አልቆመም ዓለምን ለኹለት ከፈለ የምድርን ታሪክ ቀየረ።

ጳውሎስ ሆይ እስቲ ቃል አውጥተህ ንገረን ማራኪው እንዴት ማረከህ? የደማስቆ መንገዶች ሆይ ንገሩን ሳወል እንዴት ተሸነፈ? መለኮታዊው ብርሃን እንዴት አበራ? እኛስ ምን አንላለን እንደ ጳውሎስ በደማስቆ መንገድ የተማረክን ምርከኞች ነን፤ ላንመለስ ተማርከናል። ከ70 ዓመት በኋላ እንደ ተመለሱት እስራኤላውያን ወደ ባቢሎንስ አይደለም ወደ መንግሥተ ሰማያት ተማርከናል፤ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ ላናይ በሎጥ ሚስት አምሳል ምለናል፤ አዳኙ አድኖናል፤ ማራኪው ልባችንን ማርኳል። ከእንግዲህ ወደ ማን እንሔዳለን? የሕይወት ቃል ከአፉ ይፈልቃል፤ ኹሉን ለዘለዓለም ሕይወት እየማረከ ለአባቱ ያስረክባል፤ ሕይወትን ያየ እንዴት ሞትን ይመኛል!

ንገሥ በልባችን ላይ ኢየሱስ ፤ ለዘለዓለም ንገሥ ኢየሱስ!

Ave Christus Rex!
Hail Christ the King!

@KidanZeIyesus
🥰 80 ❤ 25 🔥 5 ❤‍🔥 2 👍 1
27 February 2025
ኪ
12:58
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሥነ አመክንዮ ግጭትን እንደ ምስጢር ( logical contradiction disguised as mystery)

እግዚአብሔር በባሕርዩ ከኹሉ ስውር ነው የእግዚአብሔርን ባሕርይ እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብሎ መናገር የሚችል ሰው የለም። ነገር ግን ይህ ማለት እግዚአብሔርን በጭራሽ አናውቀውም ማለት አይደለም ይልቅስ እኛ እንድናውቀው አውቀነውም ሕይወትን እንድናገኝ የሚያሰላስል አእምሮን ፈጥሮ አንድያ ልጁን ለድኅነት ልኮልናል (መገለጥ)። ስለዚህ የእግዚአብሔርን በባሕርይው መጠን በምልዓት ባናውቀውም ሊገልጥልን በፈቀደው መጠን በሚያስብ አእምሮአችን እናውቀዋለን፤ አናውቀውም እንዲሁም እናውቃዋለን παράδοξος (Paradoxos).

ነገር ግን በአንድ ጊዜ አናውቀውም እንዲሁም እናውቀዋለን ስንል logical contradiction እየሠራን አይደለም የማናውቀውም እንዲሁም የምናውቀው በአንድ አይነት ነገር (Attribute) አይደለም። እግዚአብሔርን በ οὐσία (ባሕርይ - Essence) አናውቀውም በ ἐνέργεια (የባሕርይ መገለጫ- Energy) እናውቀዋለን። በአንድ ጊዜ በባሕርይ አናውቀውም እንዲሁም እናውቀዋለን ብንል ኖሮ logical contradiction በኾነ ነበር ነገር ግን Essence እና Energy መካከል distinction ስለሠራን ግጭት ሳይኾን ምስጢር ነው። ምስጢረ ሥላሴም እንዲሁ ነው አንድም ሦስትም ነው ስንል አንድም ሦስትም ነው ያልነው በባሕርይ ቢኾን ኖሮ ግጭት ነው እኛ ግን አንድነቱ በባሕርይ ሦስትነቱ በአካል ስላልን ግጭት ሳይኾን ምስጢር ነው። እንድንመራመር አእምሮን የፈጠረ አምላክ የሥነ አመክንዮ ግጭት እያየህ ምስጢር ነው ብለህ እለፈው የሚል አስተሳሰብን ከእኛ አይጠብቅም አስተውሉ ክርስትና ሥነ አመክንዮን የሚቃረን አይደለም ይልቅስ ከአመክንዮ በላይ ነው (Christianity is not illogical it is beyond logic).

ነገር ግን ዛሬ የሥነ አመክንዮ ግጭትን ምሥጢር ነው ብለው የሚያቀርቡ ወገኖቻችንን ላሳያችሁ። ይህም የሉተራኖች ቅድመ ውሳኔ ትምህርት ነው። በሉተራን አስተምህሮ እነዚህ ሦስት ነገሮች በአንድ ጊዜ እውነት ናቸው፡

1. ድኅነት የእግዚአብሔር ምርጫ ብቻ እንጂ የሰው ውሳኔ አይደለም። (Monergism)
2. እግዚአብሔር ኹሉም ሰዎች እንዲድኑ ይወዳል።
3. ኹሉም ሰው አይደንም።

እነዚህን ሦስት statements በሥነ አምክንዮ እንመዝናቸው፡

1 እና 2 እውነት ከኾኑ 3 እውነት ሊኾን አይችልም ፡ ድኅነት የእግዚአብሔር ምርጫ ብቻ ነው ፣ እግዚአብሔር ኹሉም እንዲድን ይወዳል ስለዚህ ኹሉም ሰው ይድናል ፤ የUniversalism እምነት ይህ ነው።

1 እና 3 እውነት ከኾኑ 2 እውነት ሊኾን አይችልም; ድኅነት የእግዚብሔር ምርጫ ብቻ ነው ፣ ኹሉም ሰው አይድንም ስለዚህ እግዚአብሔር ኹሉም እንዲድን አይወድም ፤ የCalvinism እምንት ይህ ነው።

2 እና 3 እውነት ከኾኑ 1 እውነት ሊኾን አይችልም; እግዚአብሔር ኹሉም ሰው እንዲድን ይወዳል ፣ ኹሉም ሰው አይድንም ስለዚህ ድኅነት የእግዚአብሔር ምርጫ ብቻ ሳይኾን የሰውም ትብብር አለበት (Synergism) የArminianism እምነት ይህ ነው።

በሥነ አመክንዮ ሦስቱም በአንዴ እውነት ሊኾኑ የሚችሉበት መሠረት በፍጹም የለም ይሄን ጊዜ ታድያ ሉተራኖች ምስጢር ነው ብለው ለማለፍ ይሞክራሉ። ይህ intellectual laziness ይባላል ስህተት መኾኑን አእምሮአችን ፊት ለፊት እየነገረን ስህተትን ለመሸፈን "ምስጢር ነው" የሚለው ካርድ አይመዘዝም እንዲያማ ከኾነ ማንኛውም እውነታን የሚቃረን ነገር እየተናገርን አስረዳ ስንባል ምስጢር ብለን ማለፍ እንችላለን። ይህ "ምስጢር" የሚለውን ቃል ከተገባው በላይ በመጠቀም abuse ማድረግ ነው። ከዚህ የምንረዳው የቅድመ ውሳኔ ትምህርት ውስጥ ሉተራኖች ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ያስገባቸዋል መሃል የሚባል ነገር የለም ወይ ሙሉ በሙሉ ካልቪኒስት መኾን ነው ወይ ሙሉ በሙሉ አርሚኒያን መኾን ነው። (Double or nothing there ain't something called "Single Predestination")

@KidanZeIyesus
👍 31 ❤ 12 🔥 4 🌚 2 ⚡ 1 🥰 1 😁 1
ኪ
22:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
የተለያዩ አቋሞች በባሕርያት ተዋሕዶ ላይ። ነገረ ክርስቶስ ክፍል 3 pdf
@KidanZeIyesus
❤ 8 👍 1
22:29
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:37:23, 305.0 MB
❤ 1
22:29
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – Incarnation pArt 2
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:36:50, 32.5 MB
ነገረ ክርስቶስ ክፍል ሦስት፡ የባሕርያት ተዋሕዶ
@KidanZeIyesus
👍 15 ❤ 8
2 March 2025
ኪ
11:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓቢይ ጾም አንደኛ ሳምንት ንባብ

ማቴዎስ 6
31: እንግዲህ፦ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤
32: “ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።
33: ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

የሚጠፋ መብልን አሕዛብም ክፉዎችም ይፈልጋሉ ለእርሱም ይሠራሉ ነገር ግን እርሱ ይጠፋል ለዘለዓለም ሕይወት አይኾንም። እግዚአብሔር ለኹሉም የሚኾን ጸጋን (Common grace) ይሰጣል በኃጥአንም በጻድቃንም ፀሐይን ያወጣል ዝናምን ያዘንባል ኹሉንም እንደጊዜው ይመግባል። ክርስቲያን መኾናችን ግን ለሚጠፋ ምግብ ሳይኾን ለዘለዓለም ሕይወት የሚኾን ምግብን ለማግኘት ነው እርሱም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው ለዘለዓለም ሕይወት የሚኾን ብቸኛ ምግብ ይህ ነውና መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ እርሱንም በክርስቶስ ታገኛላችሁ።

መልካም የጌታ ቀን!

@KidanZeIyesus
❤ 67 🥰 2 👍 1
3 March 2025
ኪ
15:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.tiktok.com/@abd.elmessih?is_from_webapp=1&sender_device=pc

Follow አድርጉና tiktok ላይ እንማማራለን።

@KidanZeIyesus
👍 27 ❤ 10 🥰 1
ኪ
19:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
2ኛ ዜና 9
13: ነጋድራሶችና ነጋዴዎች ካመጡለት ሌላ በየዓመቱ ወደ ሰሎሞን የሚመጣ የወርቅ ሚዛን ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበረ።

ሕዝቤ ይሄን ካየ በኋላ ሰሎሞን ኢሉሚናቲ ነው 🙀
😁 58 🤣 9 👍 4 🥰 1
4 March 2025
ኪ
21:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/kidanzeIyesuschat?videochat=a249524e6e5251dd94

ነገረ ክርስቶስ

ርእስ: ሊመጣ ያለው መሢሕ ግቡ
❤ 1
ኪ
23:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:50:00, 586.3 MB
❤ 12
23:12
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – Messiah Concept
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:49:37, 36.9 MB
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 4፡ ሊመጣ ያለው መሢሕ

@KidanZeIyesus
❤ 17 🥰 4 👍 1
5 March 2025
ኪ
08:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሊመጣ ያለው መሢሕ፡ መሢሑ በአይሁድ ፣ በክርስትና ፣ በእልምና

@KidanZeIyesus
❤ 22 👍 4
ኪ
09:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
መሠረታዊ የነገረ ክርስቶስ ትምህርት ክፍል 1
Eternal Generation (ዘለዓለማዊ ልደት) የነበረን ትምህርት pdf ቢዘገይም እነሆ😁
@KidanZeIyesus
❤ 29 👍 3 🙏 1
ኪ
22:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
እናንተ ሰዎች 2K ሞልተናል ኹላችሁንም አመሰግናለሁ 🙌

ጌታ ኢየሱስ ከእኛ ጋር ኾኖ ወደ ፊት እንቀጥላለን 💪
🔥 75 ❤ 23 👍 12 ❤‍🔥 3 👏 3 🥰 1
7 March 2025
ኪ
18:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMBRqjxCD/

Well well well, Fallacious Argument እየሠሩ የእኅቶችን ጥያቄ ዝም ለማስባል ለሚሞክሩ ሰዎች መልስ እንሰጣለን።
🥰 24 👍 7 🔥 2
8 March 2025
ኪ
11:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
የጸጋው ኪዳን

በጸጋው ኪዳን ኢየሱስ በደሙ ፈሳሽነት በመሠረተው ሐዲሱ ኪዳን ስር ኾነን ስለ ክርስቶስና በኪዳኑ ስር ስለታቀፉት የእግዚአብሔር ሕዝብ አዲሲቷ እስራኤል ቤተክርስቲያን በተቻለን መጠን እንማማራለን። እንዲሁም የኪዳኑ መሥዋዕት የክርስቶስን ሥጋና ደምም እየተቀበልን በጸጋው እንበረታለን።

የክርስቶስ ጸጋና ሰላም አብሮን ይኹን 😊
❤ 107 🥰 10 👍 2
Channel photo changed
9 March 2025
ኪ
11:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት ንባብ

ማቴዎስ 4
1: ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
2: አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።

አዳም በገነት ሳለ ሰይጣን ወደ እርሱ መጥቶ ከገነት ወደ ምድር አወጣው ባሕርይውም ደቀቀ። ጌታ ኢየሱስም የእኛኑ ደካማ ባሕርይ ይዞ ወደ ራሱ ግዛት ወደ ምድረ በዳ ወርዶ ሰይጣንን አሸነፈው አዳምንም ወደ ገነት መለሰው።

ኹላችንም በሰይጣን በተፈተነው በጌታ ኢየሱስ ኾነን ሰይጣንን አሸነፍነው ቀድሞ ወድቆ የነበረው አዳማዊ ባሕርይ በዳግማይ አዳም በጌታ ታደሰ ፤ ሰይጣን ወደ መጀመሪያው አዳም ግዛት መጥቶ አሸነፈው ኹለተኛው አዳም ደግሞ ወደ ሰይጣን ግዛት ሔዶ አሸነፈው።

እኛም ኃይልን በሚሰጠን በጌታ ኢየሱስ የሰይጣንን ፈተናዎች ኹሉ እናሸንፍ ዘንድ ተስፋ አለን ባሕርያችንስ ደካማ ነው ባከበረን በፈተናችን ኹሉ በሚራራልን በጌታ ግን እናሸንፋለን!

መልካም የጌታ ቀን!

@KidanZeIyesus
🙏 34 ❤ 21 👍 7 🥰 2
10 March 2025
ኪ
18:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMBNMrDab/

የአላህ ገራሚ ሎጂክ 😁

ደግሞ ማርያም ትመገብ እንደነበር ታውቁ ነበር 😃

@KidanZeIyesus
👍 23 😁 9 ❤ 2 🥰 1
11 March 2025
ኪ
17:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
አዲስ ገቢዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ጥሩ ጊዜ እናሳልፋለን ብለን እንጠብቃለን (ከዚህ በፊት የነበሩ ምስክር ናቸው 😊)

ከመጣችሁ አይቀር ግን ዛሬ ማታ 3፡00 እንዳትቀሩ ስለመካከለኛችን ስለኢየሱስ ፣ ስለ ኪዳን ፣ ስለ ሐዲሱ ኪዳን (ኪዳን ዘኢየሱስ 😁) እንማማራለን።

በዚህ በኪዳን ዘኢየሱስ ቻናል እንደ ተሰበሰባችሁ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ አለበት ወደ ኪዳኑ ሕዝብ ወደ ተመረጡት ቅዱሳን ማኅበር ይሰብስባችሁ 😂 (አሜን ነው ወይ)
❤ 114 😁 21 👍 13 🥰 1
ኪ
20:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሚጠፋ ፖስት 😁

ጨቅጫቃ ሚስት አግብተህ የምትወደው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የትኛው ነው ስትባል፡

መሣፍንት 16
16: ዕለት ዕለትም በቃልዋ ነዘነዘችው አስቸገረችውም፥ ነፍሱም እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች።
😁 99 🤣 47 👍 5 🥴 5 ❤ 3 🫡 2 🥰 1
ኪ
21:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/kidanzeIyesuschat?videochat=cf70e9e542253e1613

የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ግቡ
👍 11 ❤ 5
ኪ
23:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:47:37, 357.1 MB
❤ 11 👍 2
23:03
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – Mediator of the new covenant
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:47:34, 36.1 MB
ነገረ ክርስቶስ ከፍል 5፡ ኪዳን እና የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ

@KidanZeIyesus
👍 18 ❤ 9 🥰 1
23:10
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 5፡ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ

@KidanZeIyesus
👍 21 ❤ 8 🥰 1
12 March 2025
ኪ
16:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
“Thou shalt not kill,” there is no limitation added nor any exception made in favor of any one. And so some attempt to extend this command even to beasts and cattle, as if it forbade us to take life from any creature. But if so, why not extend it also to the plants? For though this class of creatures have no sensation, yet they also are said to live, and consequently they can die; and therefore, if violence be done them, can be killed. Must we therefore reckon it a breaking of this commandment to pull a flower?

"አትግደል" የሚለው ትእዛዝ ምንም አይነት ገደብ አልተቀመጠበትም። አንዳንዶች ደግሞ ምንም ገደብ ስላልተቀመጠበት አትግደል የሚለው ትእዛዝ እንስሳትና አራዊትንም ይጨምራል የትኛንም ፍጡር እንዳንገድል ይከለክላል ብለው ያስባሉ። እንዲያስ ከኾነ ለምን ዕጽዋትንስ አይጨምርም? እነዚህ ፍጡራን ምንም እንኳን ስሜት ባይኖራቸው ሕይወት አላቸው ይሞታሉም ፤ ስለዚህ በእነርሱ ላይ ጥፋት ቢያጋጥማቸው ሊገደሉ ይችላሉ። ስለዚህ አበባ እንኳን ስንቀጥፍ "አትግደል" የተባለውን ትእዛዝ እንዳፈረስን ይቆጠራልን?

ጎርጎርዮስ ዘኑሲስን ጠቅሰን Vegan ኹኑ ብለናችሁ ነበር አሁን ግን ይህ አባት Veganismን እየተቸ ይመስላል ማን ይኹን ይህ የሥጋ በሎች ጠበቃ? ገምቱ 😊
👍 31 ❤ 6 🥰 3
ኪ
18:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMBFTjx5N/

ሌላ የሎጂክ ችግር ከአላህ ቁርአንን እታደጋለሁ ብሎ ቀበረው 😁

@KidanZeIyesus
👍 36 ❤ 3
13 March 2025
ኪ
21:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/kidanzeIyesuschat?videochat=288489ea9674bb11fa

የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ፣ የክርስቶስ ዘለዓለማዊ ምልጃ። ግቡ
❤ 9
ኪ
23:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
2:10:39, 410.0 MB
👍 4
23:22
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – Mediator of the New Covenant part 2
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
2:10:12, 43.7 MB
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 6፡ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ፤ ዘለዓለማዊ ምልጃ

@KidanZeIyesus
❤ 28 👍 2 🙏 2
23:24
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 6፡ የሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ፤ ዘለዓለማዊ ምልጃ

@KidanZeIyesus
❤ 27 👍 2
14 March 2025
ኪ
09:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
ትናንት ከተማማርነው የሚያጽናናኝ ቃል

"መካከለኛው ለአንድ አይደለም እግዚአብሔር ግን አንድ ነው" (ገላ 3:20)

መካከለኛ የሚኮነው ኹለት አካላትን ለማስታረቅ ነው የግድ መካከል የሚኾንላቸው ኹለት አካላት ያስፈልጋሉና ፤ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው ስለዚህ እግዚአብሔር ራሱ መካከለኛ ይኾነን ዘንድ ለእርሱ ባእድ የነበረውን የሰውነትን ባሕርይ ያዘ ከኃጢአትም በስተቀር ፍጹም እኛን በመምሰል በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል መካከለኛ ኾነ። እግዚአብሔር ሊቀ ካህናት ያስነሣልን ከመላእክትም አይደለም ፣ ከሰማይ ኃይላትም አይደለም ይልቅስ እርሱ ራሱ የአብርሃምን ዘር በመያዝ ሊቀ ካህናት ኾነን እንጂ።

ሰው መኾኑ አስታራቂያችን ለመኾን ካልኾነ በቀር ሌላ ምክንያት የለውም ፤ አስታራቂያችንም በኾነበት በዚሁ ሥጋ ወደ ሰማያት አረገ በአብ ቀኝም የኛን ባሕርይ አስቀመጠ። ስለዚህም በአብ ቀኝ የታረደው በግ ጠበቃ ኾኖን አለ ባከበረው የእኛ ሰውነት ኃይልም አምላክ እስኪያደርገን ድረስ በመስቀል ላይ ባሳየን ፍቅር አለ ❤️

በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት በአብ ቀኝ የለንም ይልቅስ የእኛን ፈተና የተፈተነ የሚራራ ስለእኛ የታመመ ሊቀ ካህናት አለን እንጂ!

@KidanZeIyesus
❤ 88 ❤‍🔥 16 👍 4 🔥 3
ኪ
12:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢየሱስን ትወዱታላችሁ?

ከሙስሊም ወገኖች ዘንድ እኛም እኮ ኢየሱስን እንወደዋለን የሚል መፈክር ሲነገር እንሰማለን ነገር ግን እንደ እስልምና ኢየሱስን ያዋረደ እምነት የለም። በእስልምና ኢየሱስ ቢሊዮኖችን ወደ ሲኦል እንዲገቡ ያደረገ ነቢይ ነው።

አላህ ኢየሱስን የሰው ልጆት በሙሉ አምላክን ብቻ እንዲገዙ ላከው ኢንጂልንም ሰጠው ነገር ግን አይሁድ ሊገሉት በፈለጉ ጊዜ አላህ ወደ ራሱ ወሰደውና ኢየሱስ ግን የተሰቀለ ኾኖ እንዲመሰል ተደረገ የኢየሱስ ተከታዮችም ኢየሱስ ተሰቅሏል እያሉ አስተማሩ። አላህ የሰጠው ኢንጂልም ተበርዞ በእርሱ ቦታ ሀሰተኛ ኢንጂሎች ተፈበረኩ የኢየሱስ ተከታዮችም አላህን መገዛት ትተው ኢየሱስን አመለኩ። ይህ በኢየሱስ ስም የተፈጠረው አዲስ እምነትም ወደ ዓለም ኹሉ ተሠራጨ ቢሊዮኖችም አመኑበትና ወደ ሲኦል ገቡ አላህም ለ500 ዓመታት ሳያስተካክላቸው ዝም አለ።

እንግዲህ አስቡት በእስልምና ኢየሱስ የከሰረ ነቢይ ብቻ ሳይኾን በእርሱ መምጣት ምክንያት ቢሊዮኖች ወደ ሲኦል የሚገቡበት ነቢይ ነው። ከዚህ በላይ ኢየሱስን ማዋረድ አለ? ጥፋተኛውስ ማነው ይህን የፈቀደ አላህ አይደለምን?

ሙስሊሞች አታስመስሉ ኢየሱስን አትወዱትም የብዙዎች ሲኦል መግቢያ ምክንያት የኾነ Failed prophet ታደርጉታላችሁ እንጂ። የእኛ ኢየሱስ ግን እንዲህ አይደለም ዓለምን ወደ እርሱ የማረከ ማራኪ ነው። እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ለእኛ ደሙን የከፈለውን ስግው ቃል ኢየሱስን በዓለም ኹሉ እንመሰክራለን ለታላቁ አምላካችን ለኢየሱስም ጉልበታችን ይንበረከካል ስሙ ከስም ኹሉ በላይ ነውና!

ኢየሱስ አምላክ አይደለም ብሎ ከሚክድ በላይ የክርስቶስ ተቃዋሚ ማነው? ክርስቶስስ አልተሰቀለም ከሚል በላይ የኢየሱስ ጠላት ማነው?

@KidanZeIyesus
❤ 128 👍 20 👌 2 🥰 1
16 March 2025
ኪ
11:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ንባብ

ሉቃስ 15

18: ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ “አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥
19: ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ፡” እለዋለሁ’።
20: “ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።

ሁላችንም የጠፉት ልጆች ነን ከአባታችን ዘንድ ጠፍተን በኃጢአት ውስጥ ተገኝተናል አንድም ጽድቅ የለንም ኹሉም በጌታ ፊት በድሏል ጌታ ግን በመስቀሉ በኩል በደም የኾነ ንስሐን ሰጠን።

እኛ ብንበድልም በደም የኾነ የኃጢአት ሥርየት አለንና ወደ አባታችን "በሰማይም በአንተም ፊት በድያለሁ ከእንግዲህ ባርያህ ልባል እንጂ ልጅህ ልባል አይገባኝም" ብለን ወደ ጌታ እንመለስ ያን ጊዜ እርሱ 'አባ አባት' ብለን የምንጮኽበትን የልጅነትን መንፈስ ይሰጠናል እቅፉ ኹሌ ለእኛ ክፍት ነውና።

አባታችን ይወደናል መልካም የጌታ ቀን❤

@KidanZeIyesus
❤ 88 ❤‍🔥 8 👍 3 👎 1 🥰 1
17 March 2025
ኪ
19:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMBMjo8Kt/

ቁራን ከሲሪያክ ንስጥሮሳዊ ክርስቲያን እንደተቀዳ የሚያሳዩ ብዙ ነገሮችን ወደ ፊት እናያለን
👍 42 ❤ 8
20 March 2025
ኪ
18:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ በክርስትናው ዓለም አንድ ታዋቂ የሆነ ጥያቄ አለ ሁላችሁም ተሳተፉበት፡

Was Christ's death necessary? ለኃጢአት ሥርየት የክርስቶስ ሞት ግዴታ ነበረን? ያለ ሞት እግዚአብሔር ይቅር ይል ዘንድ አይችልም ነበረን?

Penal Substitutionary Atonement የምታምኑ ፕሮቴስታንቶችም ብትሳተፉ ደስ ይለኛል 😊
👍 29 ❤ 2 🥰 1
ኪ
21:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/kidanzeIyesuschat?videochat=ab54cb0d7a5b9e8796

ነገረ ክርስቶስ ላይ ጥያቄ ያላችሁ ግቡ
👍 2 🥰 1
ኪ
23:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኪዳን ዘኢየሱስ Chat – Question time
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:51:19, 37.4 MB
ነገረ ክርስቶስ የጥያቄና መልስ ጊዜ

@KidanZeIyesus
🙏 21 🥰 8 ❤‍🔥 4 ❤ 3 🔥 1
21 March 2025
ኪ
11:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለክረሽህ ፍቅርህን ገልጸህላት

ምሳሌ 17
17: ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፤
ወንድምም ለመከራ ይወለዳል።

የሚለውን ጥቅስ ስትልክልህ እንዴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ rejection ፤ Another level of እንደ ወንድሜ ነው የማይህ 😭
🤣 98 😁 12 😭 6 🥰 1 🤔 1
ኪ
18:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMBkT7P54/

የእምነታችን ሐዋርያና እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ

@KidanZeIyesus
❤ 37 👍 3 🥰 1
23 March 2025
ኪ
12:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት - ሳምራዊቷ ሴት

John 4 አማ - ዮሐንስ
25: ሴቲቱ፦ “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል፡” አለችው።
26: ኢየሱስ፦ “የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ፡” አላት።
27: በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን፦ “ምን ትፈልጊያለሽ?” ወይም፦ “ስለ ምን ትናገራታለህ?” ያለ ማንም አልነበረም።
28: ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም፦
29: “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” አለች።

ክርስቶስን ያገኘች ነፍስ ከኋላዋ ያለውን የኃጢአት እንስራ ጥላ ስለ ዳነችበትን የሕይወት ውኃ ትመሠክራለች። ክርስቶስን አግኝታለች ወደ ኋላ አትመለከትም ወደ ፊት ወደ ቅድስና ወደ ክርስቶስ ትራመዳለች ድኅነትንም ለዓለም ኹሉ ትመሠክራለች።

የሕይወት ውኃችን ክርስቶስ ይባረክ ❤️
መልካም የጌታ ቀን

@KidanZeIyesus
❤ 96 👍 3 🙏 2 🥰 1
24 March 2025
ኪ
10:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/ikfkASBcPKQ?si=zwDeu_TNaUuk3cHj

የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምጽአት ቀን መዝሙር ነው። ክርስቶስ ሲመጣ ያለውን ኹኔታ በአስፈሪ አቀራረብ ይገልጻል እንዲህ ጽሑፍ ጽፌለት ነበር:

ክርስቶስ ይመጣል ፣ ጌታ ይመጣል የዓለም መንግስታት ይገለበጣሉ ኃጥአን ዋይ ዋይ ይላሉ ሙታን ይነሳሉ ተራሮች ይወድቃሉ የእግዚአብሔር ልጅ በክብር ይመጣል ጌትነቱን ለዓለም ሁሉ ይገልጣል!

ዋይ ዋይ ያን ጊዜ ማን ፊቱ ይቆማል የሰማይ ሰራዊት ከበውታል ኪሩቤል በፊቱ ይሰግዳሉ ፣ ሱራፌልም ያሸበሽባሉ ኃይላት ፣ አጋእዝት ሥልጣናት ፣ አርባብ ኹሉም መለከታቸውን ይዘው በፊቱ ይቆማሉ ፣ ዋይ ያን ጊዜ የሰው ልጆች ምን ይውጣቸዋል እነሆ ጌታ መጥቷል መጽሐፍ እንደተናገረው ጌታ መጥቷል! በግርማ በክብሩ ይኸው ይታያል። የወጉትም ከሙታን ተነስተዋል የሰቀሉት ኢየሱስ በክብሩ ፊታቸው ቆሟል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈራርሷል ፣ የዓለም መንግስታት ወዳድቀዋል አላመኑበትም እርሱ ግን በግርማው ይታያል። ዋይ ዋይ ያን ጊዜ ኃጥአን ምን ይውጣቸዋል በፊቱ ይንበረከካሉ ማረን ይላሉ ይንቀጠቀጣሉ ያኔ ግን ጊዜው አልፏል አብቅቷል የምሕረት ጊዜ አብቅቷል አሁን የፍርድ ጊዜ ነው ፣ ፈራጁ በክብር ይታያል ፀሐየ ጽድቅ ፀሐይን በእጁ ይዟል እውነተኛው ዳኛ በመስቀል የፈረዱበት ፊት ቆሟል።  የምድር ኃያላን ሃገራት ተርበድብደዋል ፈራጁ ፊታቸው ቆሟል ፍርሃት ምድርን ሸፍኗል የእግዚኢብሔር ልጅ መጥቷል በድብቅ ሳይኾን በግልጥ መጥቷል! ክርስቶስ መጥቷል። ብር እና ወርቅ ካሁን በኋላ አይሰራም ንጉሱ ለዘላለም ሊነግስ መጥቷል አቤት የዓለም ኃያላን ሃገራት ሃብታቸውን ምን ያድርጉት ፣ የአረብ ሃገራት ነዳጃቸው ምን ይኹን ኹሉም ሊጠፋ ነው ኢየሱስ መጥቷልና!!

ጻድቃን ግን ይደሰታሉ ማራናታ ጌታ ሆይ ቶሎ ና ያሉት ጌታቸው መጥቷል መጽሐፍ እንደ ተናገረ መጥቷል በኃጥአን ዘንድ ፍርሃት ሲሰማ በቅዱሳን ዘንድ ግን ደስታ ይሰማል "እነሆ ጌታ እነሆ ጌታ" እያሉ ይጮሃሉ ንጉሳቸው መጥቷል የጠበቁት መጥቷል ዮሐንስ ሆይ ደስ ይበልህ ማራናታ ያልክለት ጌታ መጥቷል ፣ ዳዊት ሆይ ደስ ይበልህ ንግስናን ለዘላለም ይነግስ ዘንድ ንጉሱ መጥቷል ለፍርድ መጥቷል በግራ ለቅሶ ይሰማል በቀኝ ግን ደስታ ይሰማል በላይ የመላእክት መለከት ድምጽ ይሰማል አሁን ኹሉም አብቅቷል ተፈጽሟል እነሆ ጌታ መጥቷል ፈጻሚው ጌታ መጥቷል ሁሉም ነገር ተፈጽሟል።

" እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ኹሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ኹሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።"
(የዮሐንስ ራእይ 1:7)

በዛ አስጨናቂ ሰአት በቀኙ ያቆመን ዘንድ በሃይማኖት በምግባር እንጽና ባልጠበቅነው ሰአት ይመጣልና።

ለደብረ ዘይት የጌታን ምጽአት ለማሰብ ጥሩ ነውና ተጋበዙልኝ።

@KidanZeIyesus
😭 33 ❤ 24 👍 11 💔 3 🥰 1 😢 1
ኪ
16:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጥያቄ ሁላችሁም ተሳተፉ

መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ስህተት አልባ (inerrant) ነው? ወይስ አስምህሮ (doctrinal) በሆኑ ጉዳዮች ብቻ ነው ስህተት አልባ?

ለምሳሌ በሳይንሳዊና ታሪካዊ ጉዳዮች እንኳን ሰህተት አልባ ነው? (እስቲ በዚህ ደግሞ እንባላ 😁)
😁 32 👍 1
ኪ
20:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
የአሁኑ ሎጎ የለመዳችሁ ሰዎች ምንም ማድረግ አይቻልም የኪዳን ዘኢየሱስ ቤተሰቦች አልተቻሉም እንዲህ ሎጎ ከእነ ትርጉም design አድርገው ልከውልናል።
👌 68 🥰 23 🔥 11 👍 9 ❤ 8 👎 1 👏 1
20:24
25 March 2025
Channel photo changed
ኪ
22:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/@KidanZeIyesus

እስቲ YouTube ቻናል ከፍተናል subscribe አድርጉ live records እንለቅበታለን እግዚአብሔር ከረዳን ደግሞ ረዘም ያሉ ቪዲዮዎችን ለመሥራት እንሞክራለን።

@KidanZeIyesus
❤ 52 🔥 4 👍 1 🥰 1
26 March 2025
ኪ
18:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
🤣 108 😁 8 👍 1 🤡 1
29 March 2025
ኪ
09:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
Oriental Orthodox ባትሆኑ ግን ምን ትሆኑ ነበር?

በፊት Oriental Orthodox ባልሆን ኖሮ Eastern Orthodox እሆናለሁ ብዬ አስብ ነበር ነገር ግን የኬልቄዶንን ጉባኤ ባጠናሁ ቁጥር የማየው አንድ ነገር ቢኖር ኬልቄዶን ልክ ከሆነ ካቶሊክ ልክ ናት የሚለውን ነው በኬልቄዶን ጉባኤ ላይ የፖፑን ኃይል ታያላችሁ ሲጀመርም ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ እንደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሳይቆጠር የኬቄዶን ጉባኤ እንደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚቆጠርበት ብቸኛ ምክንያት የሮሙ ፖፕ ልዮን ሁለተኛውን የኤፌሶን ጉባኤ የወንበዴዎች ጉባኤ በማለት ኬልቄዶንን በመቀበሉ ነው። ኬልቄዶንም የተጠራበት ብቸኛ ምክንያት ሮምን በማስደሰት የልዮንን ጦማር ኦርቶዶክሳዊ ለማስባል ነበር ጉባኤው ላይም "ጴጥሮስ በልዮን ውስጥ ተናገረ" በማለት በልዮን ተናግረዋል እንዲሁም "ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ በ 2 ባሕርይ ነው" የሚለው ራሱ የጸደቀው መጀመሪያ "ከሁለት ባሕርይ ነው" ቢሉም "እናንተ ከልዮን ወገን ናችሁ ወይስ ከዲዮስቆሮስ ወገን ናችሁ" በመባላቸው የሮም ተወካዮች ለመውጣት በማስፈራራታቸው ለእነርሱ ተብሎ "በ2 ባሕርይ" የሚለው ጸደቀ። የልዮንን ሌሎቹን ሆሚሊዎችኑም ብትመለከቱ የቫቲካን 1 ጉባኤን ፓፓሲ በ5 ተኛው ክፍለ ዘመን የሚያተምር ሰው ነበር።

Eastern Orthodoxን ብናይ ግን ሁለተኛውን የኤፌሶን ጉባኤ እንደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሳይቀበሉ የኬልቄዶንን ጉባኤ ዓለም አቀፍ የሚሉበት ምክንያት ከCircular reasoning ውጪ የላቸውም ምክንያቱም ኤፌሶን 2ን ሮም ስላልተቀበለችው ነው ማንቀበለው ቢሉ ፣ ኬልቄዶንን ደግሞ እስክንድርያ አልተቀበለችውም በእነርሱ አስተምህሮ ደግሞ እኩል ሥልጣን ነው ያላቸው ስለዚህ ምክንያታቸው ሊሆን የሚችለው ቤተክርስቲያን በጊዜ ሒደት ውስጥ በምልዓት የተቀበለችው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ይሆናል ነው ይህ ግን circular reasoning ነው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የማይሳሳትና ቤተክርስቲያንን የሚመራት ሳይሆን ቤተክርስቲያን እራሷ የምትቀበለውን ጉባኤ ዓለም አቀፍ ታደርገዋለች ይሆናልና። ለካቶሊክ ግን መልሱ ቀላል ነው ሮም ያላጸደቀችው ጉባኤ ዓለም አቀፍ አይሆንም ሮም ደግሞ ኤፌሶን 2ን ሳትቀበል ኬልቄዶንን ተቀብላለች ስለዚህ ኬልቄዶን ዓለም አቀፋዊ ነው ኤፌሶን ግን አይደለም።

ከእዚህ አንጻር አሁን ላይ የእኔ አቋም ኬልቄዶን እውነት ከሆነ ካቶሊክ እውነት ናት ስለዚህ Oriental Orthodox ባልሆን ኖሮ ካቶሊክ ነበር የምሆነው የሚል አቋም ነው ያለኝ። (ደግሞ ሌላ ነገር አስቡ አሏችሁ ኬልቄዶን በየትኛውም መመዘኛ እውነት እንደማይሆን አምናለሁ 😊)

@KidanZeIyesus
🔥 53 👍 20 ❤ 7 😭 2 🥰 1
30 March 2025
ኪ
11:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት - መጻጉዕ

John 5 አማ - ዮሐንስ
5: በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤
6: ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ “ልትድን ትወዳለህን?” አለው።
7: ሰውዩም፦ “ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፡” ብሎ መለሰለት።
8: ኢየሱስ፦ “ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡” አለው።
9: ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።

ጌታ ኢየሱስ የኃጢአተኞች ወዳጅ በመሆኑ ለእኛ ራርቶልን በኃጢአት ቁራኝነት ወደተያዝንበት ወደ ውድቀታችን መጣ እኛ ግን ወደ እርሱ አልመጣንም። ነገር ወደ እኛ ወድቀት ሲመጣ አንድ ጥያቄ እየጠየቀ ነው "ልትድኑ ትወዳላችሁን?" እያለ ያለ ፈቃድ የፈጠረን አምላክ ያለ ፈቃድ አያድነንምና።

ነገር ግን ለመዳን ምክንያት አንደርድር ሰው የለኝም አንበል እርሱ ለድኅነታችን ሰው ሆኖልናልና። ስለዚህ ፈቃዳችን ለፈቃዱ እናስገዛ አሜን ጌታ ሆይ ያንተ ነን እንበለው ከወደቅንበት የኃጢአት አልጋ አንሥቶን በአሸናፊነት ወደ መንግሥቱ ይመራናልና።

ድምጹን ብትሰሙ ልባችሁን አታደንድኑ! መልካም የጌታ ቀን ❤️

@KidanZeIyesus
❤ 42 👍 4 🥰 1
ኪ
15:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMB5rU97v/

ይሄን ፖስትም የፖሰትኩት አስቀድሞ ተወስኖብኝ ነው 😁

@KidanZeIyesus
👍 19 😁 7 🥰 1
1 April 2025
ኪ
10:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
በየስንት ጊዜው እንቁረብ?

"It is good and beneficial to communicate every day, and to partake of the holy body and blood of Christ. For He distinctly says, He that eats my flesh and drinks my blood has eternal life. John 6:54 And who doubts that to share frequently in life, is the same thing as to have manifold life. I, indeed, communicate four times a week, on the Lord's day, on Wednesday, on Friday, and on the Sabbath, and on the other days if there is a commemoration of any Saint." (St. Basil the great: Letter 93, To Caesaria)

"በየቀኑ ከክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ደም መካፈል መልካምና ጠቃሚ ነው። እራሱ [ክርስቶስ] ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ይላልና (ዮሐ 6፡54) ታድያ ከእዚህ ሕይወት ቶሎ ቶሎ መካፈል እጅግ የበዛ ሕይወት ከማግኘት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ማን ይጠራጠራል። እኔ በእርግጥ በሳምንት 4 ጊዜ ቆርባለሁ፡ በጌታ ቀን [እሑድ]፣ በረቡዕ ፣ በአርብ እና በሰንበት [ቅዳሜ] እንዲሁም የቅዱሳት መታሰቢያ ባለበት በየትኛውም ቀን።" (ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ፡ ደብዳቤ 93 ለፓትሪሺያን ቂሳርያ)

ክርስቶስ ሕይወት ነው! ከሕይወት መራቅ ደግሞ ሞት ነው! ስለዚህ በተቻለን መጠን ወደ ሕይወት እንቅረብ፤ ቢቻለንስ በየቀኑ መልካም ነበር ሕይወትን አግኝተን እንዴት መራቅ ይቻለናልና። እርሱን ስለማንችል ግን በሳምንት 4 ቀን እንደ ባስልዮስ እንቁረብ። እርሱም ሊከብደን ይችላል ስለዚህ በጭራሽ ግን በጌታ ቀን ሳንቆርብ አናሳልፍ፤ ከጌታ ርቀን ሕይወት የለንምና!

እስቲ ንገሩን ከሕይወት በየስንት ጊዜ ትካፈላላችሁ ለመጨረሻ ጊዜስ መቼ ተካፈላችሁ?

@KidanZeIyesus
🥰 61 😢 10 👍 8 ❤ 5
ኪ
12:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከሁሉም በላይ የሚያናድደኝ ነገር የሌለ ሥርዓት እየጠቀሱ ሰዉ ላይ ሸክም በመሸከፍ ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቁት ነገር ነው፤ በቃ ልንል ይገባል!

"እንዲህ አይቻልም" ሲሉ 'የቀኖና መጽሐፍ ፣ የቤተክርስቲያን አባቶች' ይጥቀሱ ያለበለዚያ አንሰማም! ጌታን ከመቀበል የሰዎች የግል ሃሳብ አያግደንም፤ የሚያግደን ቀኖና ቤተክርስቲያን ብቻ ነው፤ "የቀኖናው ምንጭ" እያላችሁ ጠይቁ።
ቀኖና ቤተክርስቲያን ለሚያዘው ነገር ያለ ጥያቄ እንገዛለን፤ ነገር ግን ቀኖናው ለማያዘው ለሰዎች ሎጂክ መገዛት ግዴታ የለብንም!

ምንም እንኳን ሎጂካል ቢመስል ከቀኖና ቤተክርስቲያንና ከአባቶች መጠቀስ አለበት "ምንጭ?" በማለት ጠያቂ እንሁን ማንም ልምዱን አይጫንብን፤ ከጌታችንማ አንላቀቅም!
👍 50 ❤ 22 🤝 4 🫡 2 🥰 1
ኪ
12:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
በቅዱስ ቁርባን ዙሪያ በየአካባቢያችን ያለዉን MYTH እና የሚያርቁንን ነገሮች አምጥተን የምንወያይበት እና ጌታችን የሰጠንን ሕይወት ከመቀበል የሚያግዱንን ነገሮች የምንፈታበት መድረክ በቅርቡ ስለሚኖረን ያላችሁን ጥያቄ እና የምታውቋቸውን ሰውን የሚያርቁ ድርሳነ ባልቴቶች Comment ላይ አስቀምጡ ወይም በውስጥ @Kidel19 ላይ አናግሩኝ።
❤ 53 👍 9 😁 9 🤗 2 🥰 1
2 April 2025
ኪ
19:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMBuMECWs/

አላህ እኮ ልጅ መያዝ ቢፈልግ ይይዝ ነበር አይገርምም... ደሞኮ ልጅ ቢፈልግ ራሱ ሚስት ስለሌለው አይችልም 🙈

@KidanZeIyesus
❤ 12 👍 3 🔥 3 🥰 1
ኪ
19:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
አልበቃሁም?

"Tell me, suppose any one were invited to a feast, and were to wash his hands, and sit down, and be all ready at the table, and after all refuse to partake; is he not insulting the man who invited him? Were it not better for such an one never to have come at all? Now it is just in the same way that you have come here. You have sung the Hymn with the rest: you have declared yourself to be of the number of them that are Worthy, by not departing with them that are unworthy. Why stay, and yet not partake of the table? I am unworthy, you will say. Then are you also unworthy of that communion you have had in prayers. For it is not by means of the offerings only, but also by means of those canticles that the Spirit descends all around...You are no more allowed to be here than the Catechumen is. For it is not at all the same thing never to have reached the mysteries, and when you have reached them, to stumble at them and despise them, and to make yourself unworthy of this thing." (St. John Chrysostom Homily 3 to the Ephesians)

"እስቲ አስቡት አንድ ሰው ወደ ግብዣ ተጠርቶ እጁን ታጥቦ በማዕድ ተቀምጦ ከምግቡ አልካፈልም ቢል የጋበዘውን ሰው መስደብ አይሆንበትምን? እንደዚህ አይነት ሰው ጭራሽ ባይመጣ አይሻለውም ነበርን? በተመሳሳይ ሁኔታ እዚህ መጥታችሁ ከሌላው ጋር ዘመራችኋል (ተሰጥኦ ተቀብላችኋል) [ለመቀበል] ብቁ ካልሆኑት ጋር ባለመውጣታችሁ (ጻኡ ንኡሰ ክርስቲያን ሲባል) እራሳችሁን ከበቁት ቁጥር ጨምራችኋል ። ታድያ ቆይታችሁ ከጠረጴዛው ስለምን አትካፈሉም? ብቁ አይደለሁም ትላላችሁ እንዲያ ከሆነስ ከጸሎቱም ኅብረት ለማድረግ ብቁ አይደላችሁም። መንፈስ በሁሉ የሚወርደው በምናቀርበው [መስዋዕት] ብቻ አይደለም በምናደርገው ተማጽኖ ጭምር ነውና... በዚህ ከንኡሰ ክርስቲያኑ በላይ የመሆን ፈቃድ የላችሁም ወደ ምሥጢራቱ ጭራሽ አለመድረስና ደርሶ በእነርሱ መሰናከል መራቅና እራስን ያልተገባ ማድረግ አንድ ነውና። " (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን 3 በእንተ መልእክተ ኤፌሶን )

አንድ አንድ ጊዜ እንደዚህ ማስፈራራት አስፈላጊ ነው ጻኡ ንኡሰ ክርስቲያን የሚባለው ለምሥጢር ያልበቁት እንዲወጡ ነው። ማዕድ ላይ ቀርቦ አለመሳተፍ ባለ ማዕዱን መናቅ ነውና፤ ስለዚህ ጻኡ ንኡሰ ክርስቲያን ከተባለ በኋላ የሚቆዩት ከማዕዱ ለመካፈል የተገቡት ብቻ ናቸው። ስለዚህ ንኡሰ ክርስቲያን ገና ያልተገቡ ስለሆኑ ይወጣሉ እኛ ግን ከእነርሱ ጋር ባለመውጣታችን ለመቀበል የተገባን ነን እያልን ነው፤ ስለዚህ በእምነት ልንቀርብ ያስፈልገናል አልበቃሁም አይባልም፤ በመብቃትስ ማንም በቅቶ አይቀበልምና!

እናንተዬ ይህ ችግር በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመንም ነበር ታሪክ እራሱን ይደግማል 😭

@KidanZeIyesus
❤ 54 😭 10 👍 6 🔥 6 😢 3 🥰 1
3 April 2025
ኪ
11:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
02:53, 34.8 MB
😂😂😂
The Oriental Orthodox Church is just chilling in the corner, nodding in agreement with:

Catholics and Eastern Orthodox that the Eucharist is the representation of Christ’s once-for-all sacrifice.

Lutherans and Eastern Orthodox that it’s a mystery, while watching the Catholics try a little too hard to explain it.

Eastern Orthodox that a real change occurs—yet leaving it to mystery rather than over-defining it.

Lutherans that both leavened and unleavened bread are fine.

Just vibing with everyone in different ways. 😌
😁 32 🤣 9 👍 7 ❤ 3 🥰 1
5 April 2025
ኪ
08:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
መድኃኔዓለም

ዛሬ መጋቢት 27 ጥንተ በዓለ ስቅለት ነው ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርይው አምላክ ሆኖ ሳለ ፍቅር አስገድዶት ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል በገዛ ፍጥረቱ እጅ ተሰቃየ ፣ ተንገላታ። እኛም ነአምን ሕማሞ ለዘኢይሐምም (የማይታመም መታመሙን እናምናለን) እያልን እምነታችንን እንገልጻለን፤ በመለኮቱ ሕማም ፣ መከራ ፣ ሞት የሌለበት አምላክ ለሰው ልጆች ሲል የሚታመም ፣ መከራን የሚቀበል ፣ የሚሞት ሥጋን ተዋሕዶ የእኛን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጥቶናልና።

ጌታ ሆይ! ሁሉን ማድረግ አቅም እያለህ እንዴት ሲዘባበቱህ ዝም ማለት አስቻለህ? ኪሩቤል እና ሱራፌል በፍርሃት የሚገዙልህ ጸባዖት ሆይ! አይሁድ በንቀት ምራቃቸውን እስኪተፉብህ ዝቅ ያልህ የትሕትናህ መጠን ምን ያህል ነው? ምድርን የመሰረትህ ሰማይንም የሠራህ አዶናይ ሆይ! በመስቀል ላይ እስኪሰቅሉህ የታገሥህ ምን ያህል ትዕግሥት ቢኖርህ ነው? ይህን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቢደንቀው በቅዳሴው እንዲህ ይልሃል "ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው ። ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው ። ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው ። ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው ። ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው ። ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው ። በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት ። ሕይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋራ ቆጠሩት ።"

ብክይዎ ወላህውዎ እለ ታፈቅርዎ
-ወዮ የምትወዱስ ፈጽሞ አልቅሱለት -
ሞተ ዘኢይመውት ሞተ ከመ ይስዓሮ ለሞት
-የማይሞተው ሞተ ፣ ሞትን በሞት ኃይል ይሽረው ዘንድ ሞተ-

ነፍሴ ሆይ! የአዳኝሽ ጎን በጦር መወጋቱን መታገስ እስኪያቅትሽ ፣ በመራራ ሀዘን ሰይፍ ለመወጋት፣ በቀራንዮ መሆን ለምን አቃተሽ? የፈጣሪሽን እጅና እግር ችንካር ሰርስሮ ሲገባ እያየሽ የታገሽ ስለምንድነው?

የእግዚአብሔር ልጅ ወዶን ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፣  በሞቱ ሞትን ያፈርስ ዘንድ በትንሣኤውም ሕይወትን ይመሠርት ዘንድ ለእግዚአብሔርም መልካም መዓዛ ያለው መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ ይሰጥ ዘንድ።
❤ 117 👍 8 😢 8 ❤‍🔥 6 🥰 5 🙏 4 🤣 1
7 April 2025
ኪ
08:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
የክርስቶስ ሰውነት Essence ወይስ Hypostasis?

በኬልቄዶናዊ ነገረ ክርስቶስ እሳቤ አካለዊ የእግዚአብሔር ቃል ከእመቤታችን ሥጋን ሲነሳ የሥጋን essence ነሳ ሥጋ ግን በራሱ anhypostatic ነው በቃል hypostasis ላይ subsist በማድረግ enhypostasis ይሆናል።

ይህ በነገረ ክርስቶስ ላይ ትልቅ ችግር ያስከስታል ቃል የተዋደው ሥጋ essence እንጂ hypostasis አይደለም ማለት የክርስቶስን ሰውነት እውነተኛነት አደጋ ውስጥ ይጥላል። Ousia ወይም Essence የሰው ልጆች በሙሉ የሚኖራቸው hypothetical የሰውነት ባሕርይ ነው ይህ ባሕርይ ወደ ህልውና ሲመጣ በአንድ ግለሰብ individuated በሆነ ባሕርይ ነው ስለዚህም ሁሉም ሰው አንድ የሰውነት ባሕርይ ቢኖረውም የተለያየ attributes አለን (አጭር ፣ ረጅም ፣ ቀጭን ወዘተ) ይህን ወደ እውነታ particularized በመሆን የመጣውን ከሌሎች ጋር የማንጋራው ባሕርይ ከጥንት ጀምሮ Hypostasis ይባላል። ስለዚህ ቃል የተዋሐደው ሰውነት essence እንጂ hypostasis አይደለም ማለት ክርስቶስ እውነተኛ የሆነ ለእርሱ ብቻ የሚነገርለት የሰውነት attributes የሉትም እንደማለት ነው ስለዚህ ቃል የተዋሐደው hypothetical የሰውነት ባሕርይ ብቻ ነው ይህ ደግሞ የሰውነቱን እውነተኝነት ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ይከታል (It becomes an abstract or universal humanity not an actual, lived human condition with personal attributes and uniqueness which means Christ didn’t assume actual human existence only the potential for it.)

ሁለተኛ ደግሞ ቃል የተዋደው general human essence እንጂ particular አይደለም ማለት የሰውነት ባሕርይ በሙሉ ከቃል ጋር ተዋሕዷል ማለት ነው ስለዚህም ተዋሕዶውም ከ2 particularity ይልቅ 1 particularity ከ1 generality ጋር ያደረገው ይሆናል።

ይህ ደግሞ ከኤፌሶናዊ ነገረ ክርስቶስ የተደረገ ግልጥ ማፈንገጥ ነው። የኤፌሶን ጉባኤ የቄርሎስን 12 አንቀጸ ውግዘቶች ዶግማዊ በማድረግ አጽድቋል አንቀጸ ውግዘት 3 ላይ ደግሞ በክርስቶስ የተደረገው ተዋሕዶ ከ2 hypostasis (particularity) እንደሆነና ከተዋሕዶ በኋላም በማይለወጥ ባሕርያዊ ተዋሕዶ እንደ ቀጠሉ ይናገራል።

If anyone shall after the [hypostatic] union divide the hypostases in the one Christ, joining them by that connexion alone, which happens according to worthiness, or even authority and power, and not rather by a coming together, which is made by natural union: let him be anathema.

ይሄ በአጭሩ እንድትረዱት ነው ሌላ ቀን በሰፊው እናየዋለን 😊

@KidanZeIyesus
👍 36 ❤ 7 👏 3 ❤‍🔥 1 🔥 1 🙏 1
ኪ
09:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ጥንተ ዕለተ ሥጋዌን (The day of the incarnation) በማስመልከት የተጻፈ የክርስቶስን ሥጋዌ ስንዘክር ትክክለኛውን የሥጋዌ አስተምህሮ መዘከር አለብንና።

መልካም በዓለ ሥጋዌ እንዲሁም ጥንተ ዕለተ ትንሣኤ 😊

https://t.me/KidanZeIyesus
🙏 38 ❤ 18 👍 1
ኪ
19:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት

መኳንንት ደጆችን ክፈቱ የሚል Challenge በዚህ ሳምንት እንጀምር ስለቁርባን ብዙ myths ልካችሁልኛል እነርሱ ላይ 2 ቀን እንግባና እሑድ በሆሳዕና ቀን አንድ ላይ የሰላም ንጉሥ ይገባ ዘንድ እንክፈትለት በኅብረት እንቁረብ። ምን ትላላችሁ?

https://t.me/KidanZeIyesus
❤ 84 👍 8 🙏 1
8 April 2025
ኪ
08:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች live ከገባን ቆየን አይደል?

ዛሬ ማታ 3 ሰአት ስለ ቁርባን live እንገባለን እንዳትቀሩ

https://t.me/KidanZeIyesus
❤ 54 👍 10 🥰 2
ኪ
15:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንዴ 3k ሞላን 🙌🏽

አሁን ኣይደል እንዴ የማየው ገና እንቀጥላለን 💪🏾 በርቱ ያጀማአ ኢንሻ አላህ 10kም ገና እንገባለን 😊

https://t.me/KidanZeIyesus
🤣 49 ❤ 29 👍 6 🥰 3 😱 1 🙏 1
Voice chat
ኪ
21:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
👍 12 ❤ 2
Voice chat (6657 seconds)
9 April 2025
ኪ
07:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:40:50, 333.3 MB
👍 2
07:47
ኪዳን ዘኢየሱስ – ቁርባን ክፍል 1
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
1:39:45, 32.9 MB
የትላንቱ በእንተ ቁርባን ውይይታችን እነሆ!
ከ 2ተኛው ደቂቃ ጀምሩት😁
@KidanZeIyesus
👍 29 ❤ 17
ኪ
14:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሃሳብ ስጡ

የአሁኑ እሑድ በኅብረት እንቁረብ ካልን በሌሊት መምጣት ስለማይሆን ማታ ላይ ለማኅሌት ነው መገናኘት ያለብን (ሆሳዕናም አይደል)።

አይ ካላችሁ ደግሞ ሁላችንም በያለንበት ደብር በቻሌንጅ እንቁረብና ፎቶ share ማድረግ ምትፈልጉ ማድረግ ካልፈለጋችሁም ቻሌንጁን እንደተወጣችሁ ማሳወቅ። በኮሜንት አሳውቁ
❤ 91 👍 7 👏 2 😢 1
11 April 2025
ኪ
12:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
ማታ 3 ሰአት

Live: ቁርባን ላይ በድርሳነ ባልቴት የሚነገሩ ሐሰቶችን በመጽሐፍ ቅዱስና በአባቶች ትምህርት እናፈርሳለን 😁
❤ 38 😁 8 ⚡ 3
ኪ
13:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሄን ነገር አስተውሉት እስቲ የክርስትና አስተምህሮ በሙሉ የክርስቶስ ትንሣኤ ጫንቃ ላይ እንደሚቆም ታውቃላችሁ? ክርስቶስ ካልተነሣ ክርስትና ሐሰት ነው ሌላ ምንም አማራጭ የለም። ብዙ ጊዜ አምላክ ነኝ ቢል ፣ እንዲሁም ስቅለቱም እውነት ቢሆን ከሙታን ካልተነሣ ግን ክርስትና ውሸት ነው፤ ምክንያቱም ብዙ አምላክነትን claim አድርገው የሞቱ ሰዎች አሉ። የክርስቶስ የሚለየው ግን ሞቼ እነሣለሁ ብሎ መለኮታዊነቱን በትንሣኤው ማረጋገጡ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እውነት የእግዚአብሔር ቃል የሚሆነው የተነሣው ክርስቶስ ስለመሠከረለት ነው። በአጠቃላይ የክርስትና እውነት በሙሉ በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ የተመሠረተ ነው ጳውሎስ እንዳለው "ክርስቶስ ካልተነሣማ እምነታችን ከንቱ ነው።"

ተስፋ ምናደርግበት አንድ ትልቅ ነገር ግን የክርስቶስ ትንሣኤ እንደ ግሪክ አማልክት አፈታሪክ ብቻ አይደለም፤ ይልቅስ በታሪክ ውስጥ ያለ እውነታ ነው። እውነቱን ማወቅ ለሚፈልግ historically verifiable ነው። (በዚህ ጉዳይ ብዙ ጥሩ ሥራ የሠሩ አሉ eg. Gary Habermas, N.T. Wright እንዲሁም ብዙዎች ዘንድ popular የሆነው The Case for Christ by Lee Strobel በዓለ ሐምሳ ውስጥ ጌታ ቢፈቅድ እናያቸዋለን) ስለክርስትና እውነተኝነት ማወቅ የሚፈልግ በሙሉ በታሪክ ውስጥ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ማጥናት ይችላል። እንዲህ ያለ እምነት ሌላ የት አለ? ሙስሊም ለመሆን basically ታሪክን መካድ አለብን የክርስቶስን ሞት ፣ የካዕባን አብርሃም መገንባት ፣ ከሙሀመድ በፊት እስልምና የመኖሩ ፣ መካ ከእስልምና በፊት የንግድ ቀጠና ስለመሆኗ ይህን ሁሉ ታሪክን ብናጠና ከእስልምናው claim ተቃራኒ ሆኖ ነው የምናገኘው ነገር ግን ታሪክን ክደን እንዲሁ ቁርአንን ማመን አለብን? አንተ የምትተኛ ንቃ ክርስቶስ ያበራልሃል!
❤ 63 👍 7 🔥 7 🥰 1
ኪ
19:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMBVyXLKU/

ኦርቶዶክሳውያን አላህ በስም ኦሬንታል ኦርቶዶክስን ጠርቶን እንዲህ ነው ምታምኑት እያለን ነው። አላህ ደግሞ ቢጠይቀን እኮ እናስረዳው ነበር 😒

@KidanZeIyesus
👍 12
ኪ
20:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
የት እንቁረብ?
ያው ቦታ ጠቁሙ ብትባሉ አሻፈረኝ ብላችኋል😒ያሰብነውን አካፈልን🙄
Anonymous poll
- መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን (4 ኪሎ)
- ምስካየ ኀዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
- ቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን
- ደብረ ሳሌም ቦሌ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
- ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
- ቅድስተ ማርያም ኮኘቲክ ቤተ ክርስቲያን (5 ኪሎ)
- በያለንበት
377 votes
👍 16 ❤ 7
12 April 2025
ኪ
07:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
የአልዓዛር ቅዳሜ

ጌታ የሚወደው የቢታንያው ወዳጅ አልዓዛር ታመመ፤ እኅቶቹ ማርታና ማርያም ወደ ኢየሱስ "የምትወደው ወዳጅህ ታሟል" ብለው ቢልኩበትም ኢየሱስ ግን የመሰቀያው ጊዜ መድረሱን አውቋልና ኾን ብሎ ዘገየ፤ አልዓዛርም ሞተ።
የክርስቶስ መሰቀያ ጊዜ እና የአልዓዛር ሞት ምን አገናኘው? የተገናኘው የካህናት አለቆች ጌታን ይገድሉት ዘንድ የተማከሩት አልዓዛርን በማስነሣቱ ምክንያት ነውና ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ "ሕዝቡ ኹሉ ከሚጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት ይሻለናል" ብሎ የተናገረው አልዓዛርን ካስነሣው በኋላ ሕዝቡ ኹሉ ስለተከተለው ነው። (ዮሐ 11፡50) በነጋታው ሕዝቡ ኹሉ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያለ የተከተለውም ትልቁ ምክንያት አልዓዛርን በማስነሣቱ ነው።

አልዓዛርን ማስነሣት ለምን እንዲህ ትልቅ ነገር ኾነ? ጌታ ከእርሱ በፊት እኮ 2 ሰዎችን አስነሥቷል፤ ምነው የአልዓዛር ተጋነነ? ከዚህ በፊት ጌታ ያስነሳቸው ሰዎች በሞቱበት ቀን ነው። አይሁድ ደግሞ በአስተምህሮዋቸው አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ትለይና ምናልባት የመመለስ እድል ካገኘው ብላ ከሥጋዋ አከባቢ ለ3 ቀናት ታንዣብባለች፤ ለ3 ቀን ካልተመለሰች ተስፋ ትቆርጥና ወደ ማደሪያዋ ትገባለች ስለዚህ በ3ኛው ቀን ሰው ላይነሣ ፈጽሞ ሞተ ይባላል።

ጌታም አልዓዛር ሞተ ብለው እኅቶቹ ሲልኩበት የዘገየበት ምክንያት የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ "ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝም ቢሞት እንኳን ይነሣል" በማለቱ የሰው ልጅ ፈጽሞ ከሞተ በኋላ እንኳን የሚያስነሣ እርሱ መኾኑ ለሕዝቡ ኹሉ ይገለጥ ዘንድ ነው። (ዮሐ 11፡25) ስለዚህም ጌታ ወደ ቢታንያ ሲደርስ አልዓዛር ከሞተ 4 ቀን ኾኖት ነበር፤ አይሁድም ፈጽሞ መሞቱን ስላመኑ ከዚህ በኋላ ይነሣል የሚል ተስፋ እንኳን አልነበራቸውም። እንኳን አይሁድ በኢየሱስ ያመኑ እኅቶቹ ማርታ እና ማርያም እንኳን ጌታ መቃብሩን ክፈቱልኝ ባለ ጊዜ "አራት ቀን ኾኖታል ይሸታል" ብለው ታቀወሙ ፤ ትንሣኤ እና ሕይወት ክርስቶስ ግን "አልዓዛር ፣ አልዓዛር ና ውጣ" በሚል ቃል ብቻ ፈጽሞ የሞተውን አልዓዛር ከመቃብር ከነመግነዙ አወጣው ፤ ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ መኾኑ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ሆሳዕና (አዳኝ) እርሱ መኾኑም በዛ ላለ ሕዝብ ኹሉ ተገለጠ።

የአልዓዛር ከሙታን መነሣት በቢታንያ እና በኢየሩሳሌም ምድር ኹሉ ተሰማ ሕዝቡ ኹሉም የተነሣውን አልዓዛርን ያዩ ዘንድ ወደ ቢታንያ ተሰበሰቡ ያስነሣውን ሆሳዕና (አዳኝ) ያዩ ዘንድም ናፈቁ፤ ኢየሱስ ግን ወደ ኤፍራታ ከተማ ትቶአቸው ሄዶ ነበር (ዮሐ 11፡54)። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ አይደለም ለአንድ ቀን ብቻ ነው እንጂ፤ በነጋታው ይመጣል! ሕዝቡ ኹሉም የናፈቁትን ሆሳዕና (አዳኝ) በዘንባባ ይቀበሉታል!

@KidanZeIyesus
❤ 49 👍 10 🔥 2 🥰 2
ኪ
14:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሥርዓተ ዑደት ዘሆሣዕና (በአራቱ አቅጣጫ እየተዞረ የሚባለው የዑደት ሥርዓት በግእዝና በአማርኛ ነው)
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
🌿አቡን በ፪ ሀሌታ-
አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ እምጽዮን ይወጽህ ህግ ወቃለ እግዚአብሔር እም ኢየሩሳሌም ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይዕቲ ወብርሐን

ቤቱ እንሔድ ዘንድ መንገዱን አሳዩን ከጽዮን ሕግ ይወጣል የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም መድኃኒታችንን እንሳለማት በደስታ ታቦቷን ተቀበሏት ዋካ እና ብርሃን ናትና።
ምልጣን፦
ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይዕቲ ወብርሐን

መድኃኒታችንን እንሳለማት በደስታ ታቦቷን ተቀበሏት ዋካ እና ብርሃን ናትና።
ይ.ሕ. እየወጡ እንዲህ ይበሉ

ዋካ ይእቲ ወብርሃን ዋካ ይእቲ ወብርሃን
ዋካ እና ብርሃን ናትና ዋካና ብርሃን ናትና።

ይ.ዲ. ምስባክ፦ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘየኀድር ውስተ ጽዮን። ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ። እስመ ተዘከረ ዘይትኀሠሥ ደሞሙ።

በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ። በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ። ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቧልና። ...
ይ.ካ. ወንጌለ ማቴዎስ ፳፩፤ ፩

🌿አቡን  በ፮ ሀሌታ-
ሰመያ አብርሃም ወይቤላ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ በእምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

አብርሃም ዕለቷን የእግዚአብሔር በዓል ናት ብሎ ጠራት በመባቻ ዕለትም መለከትን ንፉ በዚች ዕለትም ጽዮንን አስበናታልና በዓላችን ነው።

🌱ምልጣን፦
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ በእምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

በመባቻ ዕለትም መለከትን ንፉ በዚች ዕለትም ጽዮንን አስበናታልና በዓላችን ነው።

ይ.ሕ.  ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ
ይ.ዲ. እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ።  በእንተ ጸላዒ። ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ።

ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን። አዘግጀህ ስለ ጠላትህ። ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።...
ይ.ካ. ወንጌለ ማርቆስ ፲፩፥፩

🌿አቡን በ፮ ሀሌታ-
ወትቤ ጽዮን አርኅዉ ሊተ አናቅጸ ይባኡ ሕዝብ ብዙሃን ወያእትቱ እብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም

ጽዮን ሕዝቡ ኹሉ ገብተው ለዳዊት ልጅ ለንጉሡ ከመንገድ ድንጋይን ያነሡ ዘንድ ደጆች ይከፈቱ ትላለች ለእስራኤል ንጉሣቸው ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ።

🌱ምልጣን፦
እብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም

ለዳዊት ልጅ ለንጉሡ ከመንገድ ድንጋይን ያነሡ ዘንድ ደጆች ይከፈቱ ትላለች ለእስራኤል ንጉሣቸው ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ።
ይ.ሕ. ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ይብሉ ሆሳዕና በአርያም

ሆሣዕና በአርያም ይላሉ ፣ ሆሳዕና በአርያም ይላሉ

ይ.ዲ. ምስባክ፦ እምሥራቀ ፀሐይ እስከነ ዐረብ።  ወእምጽዮን ሥነ ስብሐቲሁ።  እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ።

ከፀሐይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ... ከክብሩ ውበት ከጽዮን  እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።
ይ.ካ. ወንጌለ ሉቃስ ፲፱፥፳፰


🌿አቡን በ፮ ሀሌታ-
ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽሕ እምኔከ ዘየሐፅብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦም ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም

ያዕቆብ ልጁ ይሁዳን እንዲህ እያለ ባረከው ልብሱን በወይን በፍታውንም  በዘለላ ደም የሚያጥብ ንጉሥ ከአንተ ይወጣል የእስራኤል ንጉሣቸው  ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ

🌱ምልጣን፦
ዘየሐፅብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦም ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም

ልብሱን በወይን በፍታውንም  በዘለላ ደም የሚያጥብ ንጉሥ ከአንተ ይወጣል የእስራኤል ንጉሣቸው  ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ

ይ.ሕ. ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ይብሉ ሆሳዕና በአርያም

ሆሣዕና በአርያም ፣ ሆሣዕና በአርያም ይላሉ።

ይ.ዲ.  ምስባክ፦ ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ። በዕምርት ዕለት በዓልነ። እስመ ሥርዓቱ ለእሥራኤል ውእቱ።

በመባቻ ቀን በከርተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ ፤ ለእሥራኤል ሥርዓቱ ነውና።...
ይ.ካ. ወንጌለ ዮሐንስ ፲፪፥፲፪


🌿አቡን በ፪ ሀሌታ-
ባኡ  ውስተ ሀገር ወበዊአክሙ ትረክቡ ዕዋለ አደግ እቡረ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ

ወደ ከተማ ግቡ አህያ ከውርንጭላም ጋር ታገኛላችሁ ፈታችሁም አምጡልኝ
ምልጣን፦
ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ

ፈታችሁም አምጡልኝ ፣ ፈታችሁ አምጡልኝ

🌿ሰላም፦
ሃሌ ሉያ አልጺቆ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ርእያ ለሀገር ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃንኪ ዮም ሰላምኪ

ሃሌሉያ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ቀርቦ አያትና እንዲህ አላት ጽዮን ሆይ ታውቂ ዘንድ ንጉሥሽ ይኸውና ፣ ብርሃንሽ ደርሷል ፣ ሰላምሽ ዛሬ ነው።

🌱ምልጣን፦
ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃንኪ ዮም ሰላምኪ

 እንዲህ አላት ጽዮን ሆይ ታውቂ ዘንድ ንጉሥሽ ይኸውና ፣ ብርሃንሽ ደርሷል ፣ ሰላምሽ ዛሬ ነው።
❤ 35 👍 11 🥰 5
ኪ
21:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
በያለንበት እንቁረብ

ሁላችንም በዕለተ ሆሣዕና ክርስቶስን ሳንቀበለው እንዳናሳልፍ ነገ ሁላችሁንም ነው ምጠይቃችሁ የምሕረት ጌታ የሰላም ንጉሥም ይግባ ሆሣዕናውን መድኃኒቱን ዕንቀበለው ሕይወትን እንቀበለው 😊
❤ 68 🥰 12 🙏 9 👍 6
13 April 2025
ኪ
20:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንደምን አመሻችሁ ዛሬ ጠፍተን ዋልን በሆሣዕና ቀን ቢመሽም እንኳን አደረሳችሁ። እስቲ ቻሌንጁን የፈጸማችሁ ግን ንገሩን አታስቡ ውዳሴ ከንቱ አይደለም 😊
❤ 67 👍 4 😭 4
14 April 2025
ኪ
11:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቶስ አምላክነ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ

ክርስቶስ አምላካችን መጥቶ ስለእኛ ታመመ በሕማሙም ተቤዠን

መልካም የሕማማት ሳምንት የተከፈለልን ዋጋ ታላቅ ነው!
❤ 100 🙏 15 👍 1 🔥 1
15 April 2025
ኪ
20:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስትና የሞት ወይም የሕይወት ጉዳይ ነው እንጂ ከብዙ ርእዮተ ዓለማት መካከል አንዱ አይደለም! ይህንን እውነት በሃሳባችን ከመናገር አልፈን እንኑረው እንተግብረው ከክርስቶስ ውጪ ሞት ነው በክርስቶስ መሆን ደግሞ ሕይወት ነው።
🔥 42 ❤ 15 👍 1
20:31
https://www.youtube.com/watch?v=dcR7UjgD5Ec&ab_channel=VictorMahran

Ⲑⲱⲕ ⲧⲉ ϯϫⲟⲙ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲱ̀ⲟⲩ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲥ̀ⲙⲟⲩ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲁ̀ⲙⲁϩⲓ ϣⲁ ⲉ̀ⲛⲉϩ ⲁ̀ⲙⲏⲛ: Ⲉⲙⲙⲁⲛⲟⲩⲏⲗ ⲡⲉⲛⲛⲟⲩϯ ⲡⲉⲛⲟⲩⲣⲟ.

Ⲑⲱⲕ ⲧⲉ ϯϫⲟⲙ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲱ̀ⲟⲩ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲥ̀ⲙⲟⲩ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲁ̀ⲙⲁϩⲓ ϣⲁ ⲉ̀ⲛⲉϩ ⲁ̀ⲙⲏⲛ: Ⲡⲁⲟ̅ⲥ̅ Ⲓⲏ̅ⲥ̅ Ⲡⲭ̅ⲥ̅: ⲡⲁⲤⲱⲧⲏⲣ ⲛ̀ⲁ̀ⲅⲁⲑⲟⲥ ⲧⲁϫⲟⲙ ⲛⲉⲙ ⲡⲁⲥ̀ⲙⲟⲩ ⲡⲉ Ⲡⲟ̅ⲥ̅: ⲁϥϣⲱⲡⲓ ⲛⲏⲓ ⲉⲩⲥⲱⲧⲏⲣⲓⲁ̀ ⲉϥⲟⲩⲁⲃ.

Ⲑⲱⲕ ⲧⲉ ϯϫⲟⲙ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲱ̀ⲟⲩ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲥ̀ⲙⲟⲩ ⲛⲉⲙ ⲡⲓⲁ̀ⲙⲁϩⲓ ϣⲁ ⲉ̀ⲛⲉϩ ⲁ̀ⲙⲏⲛ.

+ لك القوة والمجد والبركة والعزة إلى الآبد آمين. عمانوئيل إلهنا وملكنا.

 والمجد والبركة والعزة إلى الآبد آمين ياربى يسوع المسيح مخلصى الصالح قوتى وتسبحتى هو الرب وقد صار لى خلاصاً مقدساً.

لك القوة والمجد والبركة والعزة إلى الآبد آمين.

አማኑኤል አምላኪየ ወንጉሥየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም አሜን።

ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሠናይ መድኃኒትየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም አሜን። ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ ወኮነኒ ቅዱስ መድኅን።

ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም አሜን።

አማኑኤል አምላኬና ንጉሤ ለአንተ ኃይል ክብር ምስጋናና አዛዥነት ለዘለዓለሙ ይገባል አሜን።

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የኔ መልካም አዳኝ ለአንተ ኃይል ክብር ምስጋናና አዛዥነት ለዘለዓለሙ ይገባል አሜን። ኃይሌና ምስናናዬ ጌታዬ ነው እርሱም ቅዱስ መድኃኒት ኾነኝ።

አንተ ኃይል ክብር ምስጋናና አዛዥነት ለዘለዓለሙ ይገባል አሜን።

Thine is the power, the glory, the blessing, and the majesty, forever Amen. Emmanuel our God and our King.

Thine is the power, the glory, the blessing, and the majesty, forever Amen. O my Lord Jesus Christ my good savior. The Lord is my strength, my praise, and has become my holy salvation.

Thine is the power, the glory, the blessing, and the majesty, forever Amen
❤ 48 👍 4 😭 2
16 April 2025
ኪ
09:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
አኬልዳማ "Ḥaqel D'ma" (חקל דמא)"

ሊቃነ ካህናት ጌታ አልዓዛርን ካስነሣበት ቅዳሜ ጀምሮ ክርስቶስን ሊገድሉት ቢፈልጉም ሰሞኑ የፋሲካ በዓል ነበርና ኢየሱስን በሕዝብ መሃል ሊይዙት አልቻሉም ስለዚህ ሕዝብ የማይኖርበት አመቺ ጊዜን ይጠብቁ ነበር። ይህም አመቺ ጊዜ ባልጠበቁት ሰው በኩል መጣላቸው በደቀመዝሙሩ ይሁዳ።

ይሁዳ በዛሬዋ ረቡዕ ቀን ሕዝብ በማይኖርበት አመቺ ጊዜ ጌታን አሳልፎ ሊሰጣቸው ከሊቃነ ካህናት ጋር ተስማማ ለዋጋውም ሠላሳ ብርን መደቡለት። ዓለማትን ኹሉ ብርና ወርቁን ሳይቀር የፈጠረ ጌታ ዋጋው ሠላሳ ብር ኾነ ጌታስ ምን ያህል ስለእኛ ተዋረደ! ይሁዳ ግን ይህ አልጠቀመውም የዓለሙን ውድ ጌታ በሠላሳ ብር ሸጦ ህሊናው አላረፈምና ብሩን በተነ በብሩም መሬት ተገዛ ፤ አኬልዳማ-የደም መሬት!

ጌታ ሆይ አኬልዳማስ በሠላሳ ብሩ የተገዛው መሬት ብቻ አይደለም እኛም አኬልዳማ የደም መሬቶች ነን፤ ከመሬት ከተገኘ አዳም መሬቶች ስንኾን በአንተ ደግሞ በደም ተገዝተናልና ጌታ ሆይ አኬልዳማ ነን! መክፈል በማንችለው በውድ ዋጋ ተገዝተናል፤ በአምላካዊ ደም!  ከአሁን ወዲህ ሕይወታችን የእኛ አይደለም። ጌታ ሆይ! ሕይወታችን አንተ ነህ፤ በምድራዊ ሳይኾን በመለኮት ደም ተገዝተናልና።
ጌታ ሆይ! አኬልዳማ እኛ ነን።

"በሠላሳ ብር በርካሽ ዋጋ የተሸጠው እርሱ ዓለምን በውድ ዋጋ ገዛ፤ ይኸውም ክቡር ደሙ ነው።"
(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ)
❤ 74 👍 2
ኪ
09:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሁዳ እንዴት ሞተ መሬቱስ እንዴት አኬልዳማ ተባለ?

መጽሐፍ ቅዱስ የሚጋጩ የሚመስሉ 2 ዘገባዎችን ያቀርብልና፤ ማቴዎስ 27 እና ሐዋ 1

Matthew 27 አማ - ማቴዎስ
3: በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦
4: “ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፡” አለ። እነርሱ ግን፦ “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፡” አሉ።
5: ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።
6: የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው፦ “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም፡” አሉ።
7: ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት።
8: ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ።
9: በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው፦
“ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥
10: ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት፥” የሚል ተፈጸመ።

Acts 1 አማ - ሐዋ. ሥራ
16: “ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤
17: ከእኛ ጋር ተቈጥሮ ነበርና፥ ለዚህም አገልግሎት ታድሎ ነበርና።”
18: ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤
19: በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው ‘አኬልዳማ’ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም ‘የደም መሬት’ ማለት ነው።
20: “በመዝሙር መጽሐፍ፦
‘መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባትም አይኑር፤’
ደግሞም፦ ‘ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት፥’
ተብሎ ተጽፎአልና።

ምን ይመስላችኋል መሬቱን የገዛው ማነው ራሱ ይሁዳ ወይስ የካህናት አለቆች? ይሁዳስ እንዴት ሞተ ታንቆ ወይስ በግንባሪ ተደፍቶ አንጀቱ ተዘርግፎ? መሬቱስ የደም መሬት የተባለው በደም ገንዘብ ስለተገዛ ወይስ ይሁዳ አሰቃቂ ሞት ስለሞተበት? ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ ግጭት አለበት? ሞክሩ
👍 27 🤔 9 ❤ 3 😢 1
17 April 2025
ኪ
14:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
የኪዳኗ ሐሙስ

አሮጌው ኪዳን አለፈ ጌታ ኢየሱስ ከብሉዩ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ኾነ ፤ 'ስለ እናንተና ስለብዙሆች የሚፈሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው' በማለት በደሙ ሐዲሱን ኪዳን መሠረተ።

የብሉዩም ቢኾን ያለ ደም አልጸናም ኑዛዜ የሚጸናው በሞት ነው። የብሉዩ ኑዛዜ የጸናው በእንስሳ ደም ነውና ጊዜያዊ ነበር በሐዲሱ ኑዛዜ ግን ራሱ ኪዳን ገቢው ጌታ ደሙን ስላፈሰሰ የዘለዓለም ኪዳን ነው! በዘለዓለም ኪዳን በቅዱስ ደም ተገዝተናል የሞት ዋጋ አለብን!

አቤቱ ዘለዓለማዊውን ኪዳን በዚህች ዕለት የገባኸው ሆይ በደምህ ዋጋ ገዝተኸናል እኛም ያንተ ኾነናል ፤ ያን ጊዜ እንደቆረስህ ዛሬም የቆረስኸው ሆይ ሥጋህን ተቀብለናል ፤ ያን ጊዜ እንደቀደስህ ዛሬም የቀደስኸው ሆይ ደምህንም ጠጥተናል በጸጋህ ኃይል በኪዳንህ አጽናን በዘለዓለም ፍቅር ሰንሰለትም ወደ አንተ ሳበን። ቅዱሰ ቅዱሳን ሆይ ቀድሰን!

የዘለዓለም ኪዳን ❤️

@KidanZeIyesus
❤ 85 🔥 6 👍 2
18 April 2025
ኪ
16:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
አንተ ሌባ በቀኝ የተሰቀልህ ወንበዴ ሆይ እንዴትስ አመንህ በመንግሥቱ አላየኸው ፤ በታቦር አልነበርህ ያየኸው በመስቀል ሲሳለቁበት ሲዘብቱበት ነው። ይህ ምን አይነት እምነት ነው ምን አይነት መንግሥትስ ነው? በመስቀል የነገሠ ንጉሥ አላየንም የእሾህ አክሊል የደፋ ንጉሥም አልሰማንም አንተ ወንበዴ ግን ምን አየህ? ንግሥናውንስ ማን ነገረህ? የጨለመችው ጸሐይ አወጋችህን? ወይስ ደም የኾነችው ጨረቃ ሹክ አለችህ? እድሜህን በሙሉ በውንብድና ያሳለፍህ ጥጦስ (ዴማስ) ሆይ በል ንገረን እንዴት መንግሥተ ሰማያት ገባህ ፤ ገነትንስ እንዴት ወረስህ? አንዲት ቃል በመናገር አንዲት ብቻ:

Ⲁ‌ⲣⲓⲡⲁⲙⲉⲩⲓ‌ ⲱ‌Ⲡⲁϭⲟⲓⲥ: ⲁⲕϣⲁⲛⲓ‌ ϧⲉⲛ ⲧⲉⲕⲙⲉⲧⲟⲩⲣⲟ

Ⲁ‌ⲣⲓⲡⲁⲙⲉⲩⲓ‌ ⲱ‌Ⲡⲁⲟⲩⲣⲟ: ⲁⲕϣⲁⲛⲓ‌ ϧⲉⲛ ⲧⲉⲕⲙⲉⲧⲟⲩⲣⲟ.

Ⲁ‌ⲣⲓⲡⲁⲙⲉⲩⲓ‌ ⲱ‌Ⲫⲏⲉⲑⲟⲩⲁⲃ ⲁⲕϣⲁⲛⲓ‌ ϧⲉⲛ ⲧⲉⲕⲙⲉⲧⲟⲩⲣⲟ.

Ⲙ‌ⲛⲏⲥ ⲑⲏⲧⲓ ⲙⲟⲩ Ⲕⲩⲣⲓⲉ‌: ⲉⲛⲧⲏ ⲃⲁⲥⲓⲗⲓⲁ‌ⲥⲟⲩ.

Ⲙ‌ⲛⲏⲥ ⲑⲏⲧⲓ ⲙⲟⲩ ⲁ‌ⲅⲓⲉ‌: ⲉⲛⲧⲏ ⲃⲁⲥⲓⲗⲓⲁⲥⲟⲩ.

Ⲙ‌ⲛⲏⲥ ⲑⲏⲧⲓ ⲙⲟⲩ ⲇⲉⲥⲡⲟⲧⲁ: ⲉⲛⲧⲏ ⲃⲁⲥⲓⲗⲓⲁ‌ⲥⲟⲩ.

اذكرنى يارب متى جئت فى ملكوتك.

اذكرنى يا ملكى متى جئت فى ملكوتك.

اذكرنى يا قدوس متى جئت فى ملكوتك.

ተዘከረኒ እግዚኦ አመ ትመጽእ በመንግሥትከ

ተዘከረኒ ኦ ቅዱስ አመ ትመጽእ በመንግስትከ

ተዘከረኒ ኦ እግዚእ አመ ትመጽእ በመንግስትከ

አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ

ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ

ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ

Remember me O Lord, when You come into Your kingdom.

Remember me O Holy One, when You come into Your kingdom.

Remember me O Master, when You come into Your kingdom.

አስበኝ ጌታ ሆይ አስበኝ ፤ የመስቀሉ ንጉሥ ሆይ በመንግሥትህ አስበኝ ❤️
❤ 105 👍 11 🔥 2 😴 1
19 April 2025
ኪ
08:18
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ (ግእዝና አማርኛ)

ደወል እንደተደወለ ከኹሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል።

"ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ሥዕል አይባልም።

ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት 3ቱ ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።


እግዚአብሔር ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ተነሣ
የወይንም ስካር እንደተወው እንደ ኃያል ሰው
ጠላቶቹንም በኋላው መታ

አርያም፦
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ  በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ፤   ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።


ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በመጀመሪያ ዜማ በደስታ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በዓልን አድርጉ እርሷም የመጀመሪያዋ ሕግ ፋሲካ ናት።

ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በሰማያት በዓልን ያደርጋሉ፤ በደመናት በዓልን ያደርጋሉ፤ ምድርም ፋሲካን(ደስታን) ታደርጋለች በክርስቶስ ደም ታጥባለችና።

ምልጣን፦
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።

ዛሬ በክርስቲያን ሰንበት ደስታ ኾነ፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷልና፤ ከቀናቶች ኹሉ ቀደሳት፣ አከበራት፣ ከፍ ከፍም አደረጋት፤ በእውነት ከሙታን ተነሥቷል።

'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/


'እውነት በእውነት'/2/ ተነሣ 'እውነት በእውነት"/2/
ከሙታን ተለይቶ ተነሣ /4/

ወረብ፦
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/


ዛሬ በክርስቲያን ሰንበት ደስታ ኾነ /2/
ከቀናት ኹሉ ቀደሳት አከበራትም /2/

እስመ ለዓለም፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።

ትንሣኤህን ለምናምን፤ ብርሃንህን ወደእኛ ላክልን።

አመላለስ፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/


ትንሣኤህን ለምናምን/2/
ብርሃንህን ወደእኛ ላክልን/2/

ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ  ሰላም ይፃፋል
ሰላም፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ።

ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ማርያም እናታችን ናት፤ ለጌታችንም እናቱ፤ ስለእኛ ለምኚ፤ ይምረን እና ርቅር ይለን ዘንድ፤ ቸርነቱንም በእኛ ላይ ያሳይ ዘንድ፤ ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን፤ ለምናምን ደስታ እና ሰላም ይኾነን ዘንድ።

አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፬/


ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን/2/
ሰንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን/4/

ኪዳንን ከተደረሰ በኃላ

መዝሙር በ፩፦
ሃሌ ሉያ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይወውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

ሃሌሉያ ሰማይ ይደሰት ምድርም ሃሴትን ታድርግ፤ የጭፍሮች መሠረቶችም ኹሉ መለከትን ይንፉ፤ ተራሮች እና ቁልቁለቶችም ይደንፉ፤ የምድረ በዳ ዕፅዋትም በሙሉ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ነው፤ ምድርም ፋሲካን(ደስታን) ታደርጋለች በክርስቶስ ደም ታጥባለችና።

አመላለስ፦
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/

ምድርም ፋሲካን ታደርጋለች/2/
በከርስቶስ ደም ስለታጠበች /4/

ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።


ፍጹም ነጉሥ ላይ አይሁድ ፈረዱ፤ ወታደሮችም ልብሶቹን ተካፈሉ፤ ራሱንም በዘንግ መቱት፤ በጦርም ጎኑን ወጉት፤ ትንሣኤውንም በሰንበት አደረገ፤ ለነገሥታት፤ ለአህዛብ እና ለሕዝቦች በሙሉ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ።

ከዚህ በኃላ ወደ ሥርዓተ ቅዳሴ።
❤ 62 👍 13 🥰 10 ❤‍🔥 1 🔥 1
ኪ
23:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
Ⲡⲓⲭ‌ⲣⲓⲥⲧⲟⲥ ⲁϥⲧⲱⲛϥ ⲉ‌ⲃⲟⲗ ϧⲉⲛ ⲛⲏⲉⲑⲙⲱⲟⲩⲧ: ⲫⲏⲉ‌ⲧⲁϥⲙⲟⲩ ⲁϥϩⲱⲙⲓ ⲉ‌ϫⲉⲛ ⲫ‌ⲙⲟⲩ ⲟⲩⲟϩ ⲛⲏⲉⲧⲭⲏ ϧⲉⲛ ⲛⲓⲙ‌ϩⲁⲩ ⲁϥⲉⲣϩ‌ⲙⲟⲧ ⲛⲱⲟⲩ ⲙ‌ⲡⲓⲱⲛϧ ⲛ‌ⲉ‌ⲛⲉϩ!

Χριστὸς ἀνέστη ἐκ νεκρῶν,
θανάτῳ θάνατον πατήσας,
καὶ τοῖς ἐν τοῖς μνήμασι,
ζωὴν χαρισάμενος!

المسيح قام من بين الأموات، الذي مات داس الموت والذين في القبور أنعم لهم بالحياة الأبدية!

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሃበ ሕይወተ ዘለዓለም!

ክርስቶስ ከሙታን መሃል ተነሣ በሞተ ሞትን አጠፋ በመቃብር ላሉትም የዘለዓለም ሕይወትን አደለ!

Christ is risen from the dead; He who died trampled down death and upon those in the tombs bestowed eternal life!

Kiristoos ka'eera warra du'an keessaa du'aan ballessee du'aa , awwaala keessa kan jiraniif jirenya bara baraa kennee!

Christos Anesti!
Alithos Anesti!

Pi-Ekhrestos Aftonf!
Khen O Methmi Aftonf!

ክርስቶስ ተንሥአ!
በአማን ተንሥአ!

ክርስቶስ ተነሥቷል!
በእውነት ተነሥቷል!

Chirst is risen!
Truly he is risen!

Kiristoos ka'eera!
Dhugaan ka'eera!

المسيح قام
بالحقيقة قام

Χριστὸς ἀνέστη!
Ἀληθῶς ἀνέστη!

በእውነት ተነሥቷል!
❤ 76 👍 5 🔥 5 🙏 4
20 April 2025
ኪ
11:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች ተረጋጋችሁ ወይ 😁

ለማንኛውም ቀስ ብላችሁ ብሉ በጾም የታሠረ ጨጓራ በአንዴ አይፈታበትም። ፋሲካ የመብል በዓል አይደለም የድል በዓል እንጂ ቀኑን በመንፈሳዊ ኹኔታ እናሳልፈው ክርስቶስ የተነሣው ከእርሱ ጋር መንፈሳችንን አስነሥቶ እንጂ በሥጋዊ ደስታ ብቻ እንድናሳልፈው አይደለም።

Cultural Christian መኾን የለብንም ተሰባስቦ በምግብ በልብስ በዓል ማክበር ጥሩ ነው ነገር ግን በዓሉ ከዚያም በላይ ነው ክርስቶስ ካልተነሣማ እምነታችን ከንቱ ነው እስካሁንም በኃጢአታችን አለን እንዳለ ጳውሎስ የክርስቶስ ትንሣኤ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ፣ የኃጢአት እና የጽድቅ ጉዳይ ነው።

የትንሣኤውን ጌታ ባከበረ መንገድ በዓሉን እናክበረው መልካም በዓል!

Χριστὸς ἀνέστη!
Ἀληθῶς ἀνέστη!
❤ 162 👍 10 🥰 4 ❤‍🔥 1
22 April 2025
ኪ
20:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰሞኑን ጠፋ ብያለሁ እንደ በፊቱ በደምብ ለመማማርም ሆነ ወይም document ነገር ለማዘጋጀት በምን ርእስ ብንመጣ ጥሩ ነው ትላላችሁ?
❤ 34
23 April 2025
ኪ
09:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቀጣይ ትምህርት
Anonymous poll
- ትንሳኤ
- ሃዋርያዊ ቅብብሎሽ እና የቤተ ክርስቲያን አይሳሳቴንት
- ነገረ ድኅነት
- ምሥጢረ ሥላሴ
- ነገረ ቤተ ክርስቲያን
788 votes
❤ 18 👍 3
24 April 2025
ኪ
21:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዉ ግን ለምንድን ነው እንደዚህ  ጨካኝ የሆነው?

ለወንድሞቹ የማያዝን በሀጢአትም ሆነ በምንፍቅና ሲወድቁ ቶሎ ደጋግፎ ከማንሳት እዛው እየረገጡ እንዲጠፉ በማድረግ ለምንድን ነው የሚደሰተው?....

የምር ግን የክርስቶስ ልብ ስለሌለን ነውኮ

@Yesua_Panagia
@Yesua_Panagia
😢 99 👍 22 😭 14 ❤ 13 🤔 2 🔥 1
25 April 2025
ኪ
20:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዕለተ አርብ የፍስክ ምግብ እየበላህ weird ስሜት ሲሰማህ

ለ50 ቀን ጴንጤ ኾንኩ ማለት ነው 😁

No offense to ጴንጤስ tho 🙌
😁 155 🤣 57 🥴 3 👍 2 💯 1 🙊 1
28 April 2025
ኪ
10:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
እሺ ባትል ኖሮ?

ላቲ ስብሐት ለርሷ ክብር ይሁንና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለመልአኩ የብሥራት ቃል ያቀረበችው የይሁንልኝ እሽታ ቃል በነገረ ድኅነት ታሪክ ውስጥ ቀላል ቦታ የሚሰጠው አይደለም። "ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" የሚል ብሥራት ነው የመጣላት ይህ የብሥራት ቃል የእርሷንም ሆነ የዓለምን ታሪክ የሚለውጥ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው "የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ" የተባለላት የዘመን ፍጻሜን የሚያበሥር ብሥራት ነው። እርሷም "ይሁንልኝ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ" አለች በዚህም ዘለዓለማዊው የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኛ የጊዜ ውስንነት ውስጥ ገባ (The infinite became finite) ዘለዓለማዊው የእግዚአብሔር ማዳን እቅድም (Eternal plan of salvation) አንድ ተብሎ ተጀመረ። ስለዚህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፍጹም ታዛዥነት ራሷን ሰጥታለችና ቅዱስ ሔሬኔዎስ እንዳለው "ለእራሷም ሆነ ለዓለም ሁሉ የመዳን ምክንያት ሆነች" ከዚህ የተነሣ ከፍ ከፍ እናደርጋታለን "በሔዋን ወደቅን ፣ በአንቺ ግን ተነሣን" "በሔዋን ሞትን ፣ በአንቺ ሕይወትን አገኘን" "በሔዋን የገነት ደጆች ተዘጉ በአንቺ ግን ተከፈቱ" "በሔዋን ዓለም ጎሰቆለ በአንቺ ግን ዓለም ዳነ" እያልን እናመሰግናታለን። (ብኪ ድኅነ ዓለም - በአንቺ ዓለም ዳነ የሚሉ አረፍተ ነገሮች ላይ "ብኪ ፣ በአንቺ ፣ Through you የሚሉ ቃላትን ስንናገር ክርስቶስን እንደሚያመላክት ልብ ይበሉ ክርስቶስ በእርሷ በኩል ሰው ሆኗልና። በአንቺ ዓለም ዳነ ሲባል በአንቺ በኩል ሰው በሆነ ክርስቶስ ዓለም ዳነ ማለት ነው ቅዱስ ሔሬንዮስ ለራሷም ሆነ ለዓለም ሁሉ የመዳኛ ምክንያት ሆነች ሲል ከዚህ ጋር የተስማማ ነው ምክንያቱም ራሷን ማዳን አትችልም በርሷ ሰው የሆነ ክርስቶስ ለእርሷም መድኃኒት ሆናት እንጂ። ረጅም ቅንፍ አሁን ወደ ዋናው ሃሳብ 😄)

እንዲህ ስንል ግን ብዙ ጊዜ አንድ ጥያቄ ይጠየቃል "እሺ ባትል ኖሮስ?" የሚል ነው። እሺ ባትል ኖሮስ የእግዚአብሔር ልጅ ሰው አይሆንም ነበር? የሰው ልጅ አይድንም ነበር? ሥላሴም የተገለጠው በክርስቶስ ነውና ሥላሴንም አናውቅውም ነበር? (ከዚህ በፊት አንድ ጳጳስ ማርያም ከሌለች ሥላሴ የለም አይነት ንግግር ተናግረው ነበር ንግግራቸው ግን የተጣመመ ይመስለኛል በህልውና ደረጃ ማርያም ባትኖር ሥላሴ አይኖርም ያሉ ሳይሆን በማወቅ ደረጃ ነው የተናገሩት ማለትም ነገሩ epistemic ነው ማርያም ባትኖር ሥላሴ በexistence ደረጃ አይኖሩም ሳይሆን በማወቅ ደረጃ መኖራቸውን አናውቅም ነበር አብን ያወቅነው መንፈስ ቅዱስም የወረደው በክርስቶስ ሥጋዌ ነው ፣ የክርስቶስ ሥጋዌ ደግሞ በማርያውም በኩል ነው የሚል ነበር የጳጳሱ ሃሳብ። አሁንም ቅንፉ ሳይረዝም ወደ ሃሳቡ እንመለስ 😁 )

ይህ ጥያቄም ሆነ ብዙ ጊዜ የሚሰጠው መልስ ትክክል አይደለም "እሺ ባትል የእግዚአብሔር ልጅ ሰው አይሆንም ነበር ፣ እኛም አንድንም ነበር ፣ ሥላሴንም አናውቅም ነበር" የሚል ድፍረት ከየት እንዳመጣን አላውቅም የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ የማዳን እቅድ በፍጡር ሊገደብ አይችልም የፍጡር ነጻ ፈቃድ አስቀድሞ የእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ አለ እንጂ ማለትም የማርያም እሺ ማለት አስቀድሞ በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ውስጥ አለ ስለዚህም ነው መልአኩን የላከው እንጂ "እሺ" የማትል ቢሆን ኖሮ መጀመሪያውኑ እግዚአብሔር መልአኩን አይልክም ነበር እርሱ የእኛን መልስ አይጠብቅምና። ስለዚህ ጥያቄው "እሺ ባትል ኖሮ" የሚል ሳይሆን መሆን ያለበት "እሺ እንደማትል አስቀድሞ የእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የሚታወቅ ቢሆን ኖሮ" ነው መሆን ያለበት። ጥያቄው እንዲህ frame ከተደረገ የእኛም መልስ ማርያም እሺ የማትልበት ዓለም ምን አይነት ሊሆን ይችል ነበር የሚለውን በማየት ሊሆን ይገባል። እግዚአብሔር ሊፈጥራቸው ከሚችላቸው ዓለማት ሁሉ የክርስቶስ የቤዛነት ሞት ያለበት ዓለም ከሁሉ የላቀ ነው ስለዚህ የክርስቶስ ቤዛነት የሌለበት ዓለም ዘለዓለማዊ የማዳን እቅድ ውስጥ ይኖራል ብሎ ማሰቡ ይከብዳል። ስለዚህ "ማርያም እሺ እንደማትል የሚታወቅበት" ዓለም ላይ የክርስቶስ ቤዛነት ሊኖር አይችልም ብለን መደምደም አንችልም እንደዛ ብለን ከደመደምን በዛ ዓለም የአዳምም ውድቀት የሌለበት ነው ማለት አለብን የእግዚአብሔር መለኮታዊ መግቦት የሰው ልጆች ውድቀት ክፋት ኖሮ ከክፋቱ የሚወጣ የክርስቶስ ቤዛነት መልካምነት የማይኖርበትን ዓለም ሊፈቅድ አይችልምና።

እዚህ ላይ የሚታወቅ ጥንታዊ ሙግትም ሊነሳ ይችላል "አዳም ባይወድቅ ኖሮ እግዚአብሔር ሰው ይሆን ነበርን?" የሚል ሙግት አለ ይህ ሙግት በካቶሊኩ ዓለም ራሱ የሚያከራክር ነው ነገር ግን የአዳም ውድቀት የሚኖርበት ዓለም ላይ የክርስቶስ ቤዛነት እንደሚያስፈልግ እሙን ነው። ስለዚህ እዚህ ጥያቄ ላይ ለሙግት ሲባል እንደዚህ አይነት ዓለምን በምናባችን እንሳል "አዳም የሚወድቅበት ፣ የክርስቶስ ቤዛነት የሚያስፈልግበት ፣ ነገር ግን ማርያም እሺ የማትልበት" እንደዚህ አይነት ዓለም ሊኖር ይችላልን የሚለው ጥያቄ ራሱ ሌላ ጉዳይ ነው ነገር ግን ቢኖር ብለን ብናስብ የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ የማዳን እቅድ ውስጥ የክርስቶስ ቤዛነት እስካለ ድረስ ተፈጻሚ የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም።

ይህ ሁሉ ግን speculation እንደሆነ አስተውሉ ከተገለጠው እውነታ አልፈን speculation ውስጥ ስለሚያስገቡ እኔ "አዳም ባይወድቅ ኖሮ ፣ እሺ ባትል ኖሮ" አይነት ጥያቄዎች አይመቹኝም ነገር ግን ዘለዓለማዊውን የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ በፍጡር እውቀትም መገደብ አይመቹኝም ስለዚህ በዚህ በኩል ነገረ ማርያማችን የተለጠጠ እንዳይሆንም እንጠንቀቅ። ሰላም ዋሉ።

@KidanZeIyesus
❤ 104 👍 11 🔥 10 😁 1 😭 1
30 April 2025
ኪ
23:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
the mental gymnastics they go through 😭
😁 113 🤣 48 😭 5 👍 4 🔥 4 ❤ 3 👎 3 👌 1
2 May 2025
ኪ
09:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
ምሳሌ 27
14: ባልንጀራውን በታላቅ ቃል ማለዳ የሚባርክ ሰው፡ እንደሚራገም ያህል ነው።

እውነት ነው የእግዜር ሰላምታ እያላችሁ በጠዋት የምትደውሉ ሰዎች ዕረፉ እርግማን አትሁኑብን 😁
😁 52 🤣 23 👍 2 👏 1 🥴 1
ኪ
11:08
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰሞኑን meme አብዝተናል ይህ የመጨረሻ ነው 😁
😁 59 🤣 22 👎 3 ❤ 2 👍 1
3 May 2025
ኪ
20:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
ያለ ማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን የክርስትናን እውነት ማወቅ እንችላለን?

ክርስትና እውነት ስለ መሆኑና ስላለመሆኑ ማስረጃ የምንጠቅሰው ምንድነው? የማትሳሳተዋን ቤተክርስቲያን ነው? ክርስትና እውነት መሆኑን በምን አወቃችሁ ቤተክርስቲያን በማትሳሳት ሥልጣን እውነት መሆኑን ስለነገረችን ፣ ቤተክርስቲያንስ እንደማትሳሳት በምን አወቃችሁ? ክርስቶስ በማይሳሳት ሥልጣኑ ስለመሠረታት ፣ ክርስቶስስ እንደማይሳሳት በምን አወቃችሁ? ሞቶ እንደሚነሣ ነግሮን በትንሣኤውም እውነትነቱን ስላስመሠከረ ፣ ክርስቶስስ በእውነት ስለመነሣቱ በምን አወቃችሁ? የማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን ስለነገረችን።

ይህን ምልልስ ካያችሁት Circular reasoning fallacyን ይሠራል ለማረጋገጥ የተነሣውን claim assume በማድረግ ነው የጀመረው እርሱም የቤተክርስቲያንን አይሳሳቴነት ነው በመጨረሻም ለቤተክርስቲያን አይሳሳቴነት ማስረጃው እራሱ የቤተክርስቲያን አይሳሳቴነት ይሆናል። ስለዚህ እዚህ ላይ አንድ epistemological ጥያቄ እንጠይቅ የክርስትናን እውነት ማወቅ የምንችለው በማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን በኩል ብቻ ነው? መልሱ ግልጽ አይደለም ነው ቤተክርስቲያንን Axiomatic truth ካላደረግናት በስተቀር። Axiomatic Truth ማለት ለእውነትነቱ ማረጋገጫ ወይም ማስረጃ የማያስፈልገው በራሱ እውነት መሆኑ የሚታወቅ ነገር ነው። እነዚህ ውስጥ የሎጂክና የሒሳብ ሕጎች ይገባሉ ለምሳሌ 1+1=2 የሚለው በራሱ የሚቆም እውነታ ነው። ቤተክርስቲያንስ እንዲህ ነችን ካልን አይደለችም ያለ ምንም ማስረጃ አይሳሳቴነቷ በራሷ የታወቀች ሳይሆን ስለአይሳሳቴነቷ በማስረጃዎች እናስረግጣለን እንጂ።

ታድያ የክርስትናን እውነትነት ያለ ማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን ማወቅ እችላለን? የሚለውን ጥያቄ ስናየው መልሱ የሚሆነው አዎ እችላለን ነው እርሱንም የክርስቶስን ትንሣኤ እውነትነት በታሪካዊ ማስረጃና እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን ውሳጣዊ ምሥክርነት በመያዝ ይሆናል። ከእነዚህ ተነሥተን ክርስትና እውነተኛ ሃይማኖት ነው አይደለም የሚለውን በትክክል ማወቅ እንችላለን ክርስቶስ በእውነት ከተነሣ ክርስትና እውነት ነው ካልተነሣ ደግሞ ክርስትና ሐሰት ነው። የክርስቶስን ትንሣኤ ለማስረገጥ ደግሞ ቤተክርስቲያን የማትሳሳት ናት ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የማይሳሳት ነው ፣ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያትንም ሆነ የቤተክርስቲያን አባቶችን አነሳስቷቸዋል የሚለውን assume ማድረግ የለብንም (we don't have to assume inspiration and infallibility) ይልቅስ በተቃራኒው ነው ከክርስቶስ ትንሣኤ ተነሥተን ነው የመጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ የቤተክርስቲያንን አይሳሳቴነት የምናስረግጠው።

ክርስትና እውነት መሆኑን አወቅን ማለት ግን የክርስትናን አስተምህሮ በምልዓት አወቅን ማለት አይደለም እዚህ ጋር ነው ቤተክርስቲያን የምትመጣው ትክክለኛውን የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ለማወቅ የቤተክርስቲያን ትውፊት አስፈላጊ ነው። ይህንን ፕሮቴስታንቶችም ይስማማሉ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ሁሉንም አስተምህሮዎች በማይሳሳት ሥልጣኗ አልወሰነችምና ስለዚህ ልትሳሳት በምትችል ቤተክርስቲያንም ስለክርስትና አስተምህሮ ማወቅ የምንችላቸው እውነታዎች አሉ። ነገር ግን ያለ ማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን ማወቅ የማንችላቸው የክርስትና አስተምህሮዎችም አሉ ለምሳሌ ከዚህ በፊትም እንዳየነው ከክርስቶስ ትንሣኤ ተነሥተን ወደ 27ቱ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አይሳሳቴነት ያለማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን ልንደርስ አንችልም የተነሣው ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያት የመጻሕፍቱን ዝርዝር አልሰጡንም ስለዚህ የግድ ወደ ቤተክርስቲያን ትውፊት መግባት ይኖርብናል ፤ ወደ ትውፊቱ ስንገባ ግን የ27ቱ መጻሕፍት ታሪክ እንደምናስበው smooth አይደለም 300 ዓመታት በፈጀ ንትርክ አልፋ ነው ቤተክርስቲያን ወደ ስምምነት የደረሰችው እነዚህም ቢሆኑ የቤተክርስቲያንን አይሳሳቴነት ካልተጠቀምን በስተቀር ጥያቄ ውስጥ እንወድቃለን ስለዚህም ነው አሁን ላይ የሚደረጉ የሐዲስ ኪዳን scholarshipኦች የአንድ አንድ መጻሕፍት ትክክለኝነት ላይ ጥያቄ የሚያነሱት።

ስለዚህ ስንጠቀልለው ያለ ቤተክርስቲያን በታሪክ ማወቅ የምንችለው የክርስትና እውነት አለ ፣ እንዲሁም ያለ ማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን ሊሳሳት በሚችል ትውፊት ማወቅ የምንችለው የክርስትና እውነታ አለ እንዲሁም በማትሳሳተዋ ቤተክርስቲያን ብቻ ማወቅ የምችለው እውነታ አለ።

@KidanZeIyesus
👍 59 ❤ 20 🔥 7 🤔 3
5 May 2025
ኪ
11:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
በቤታችን ያለን anti-intellectualism አካሔድ ግድ ማጥራት አለብን ወገን። ማኅበረ ቅዱሳን ላይ መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 በሚል ርእስ የተለቀቀ ቪዲዮ እያየሁ ተሳቅቄ ልሞት።

1. መጽሐፍ ቅዱስ 81 አድርገው የወሰኑልን በ3ተኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ሠለስቱ ምእት ናቸው ይላል። እኛ ግን የተገኘውን ነገር ሁሉ ያለ ጥናት ሠለስቱ ምእት ላይ ለምን እንደምናሳብብ ይገርመኛል። አንደኛ ሠለስቱ ምእት በ3ተኛው ሳይሆን በ4ተኛው ክፍለ ዘመን ነበሩ (ይህ እንኳን understandable ስህተት ነው 325 ዓ.ም ሲባል ብዙ ሰው 3ተኛው ክፍለ ዘመን ይመስለዋል) ሌላው የሚያሳቅቀው ነገር ግን 318ቱ ሊቃውንት በኒቅያ ጉባኤ የመጻሕፍትን ቁጥር የወሰኑበት ምንም አይነት ሒደት አለመኖሩ ነው። የመጻሕፍትን ቁጥር የወሰኑ ጉባኤያት ላይ ሠለስቱ ምእት ተሳትፈው አያውቁም ይልቅስ ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ የተደረጉት የለዶቅያ ፣ የሂፖ ፣ የቅርጣግናና የሮም ጉባኤያት ናቸው የመጻሕፍትን ቁጥር የወሰኑት ነገር ግን እነዚህ ጉባኤያት 81 የመጻሕፍት ቁጥር አልወሰኑም ይልቅስ 73 መጻሕፍትን የወሰነ ጉባኤ አለ።

2. የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጠፍቶ ነበር ነበር ከዛ ዮሐንስ አፈወርቅ በጸሎት ተገልጦለት ዮሐንስ አፈረወርቅ ነው የመጨረሻውን "በዚህ ትንቢት መጽሐፍ የጨመረ ወይም የቀነሰ" የሚለውን አረፍተ ነገር የጻፈው ይለናል። ይህም በምንም አይነት የታሪክ ጥናት ላይ ያልተመሠረተ መላ ምት ብቻ ነው።

3. 81 መጽሐፍ ከየት መጣ የሚለውን ሲያስረዳ የዮሐንስ ወንጌል 2፡20 ላይ "ስለዚህ አይሁድ። ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።" የሚለውን ጥቅሶ 46 የሚለው ቁጥር 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ያሳያል ስለዚህ እዚህ ጋር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 46 መሆናቸውን እየነገረን ነው ይላል። እዚህ ጋር ይገባኛል allegory or metaphor እየተጠቀምን አስተምህሯችንን ልናሳይ እንችላለን ነገር ግን allegory እንደ ማስረጃ አይቀርብም ሲጀመርም ያንን connection የሠራው ሰው መጀመሪያውኑ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 46 መሆናቸውን ካመነ በኋላ ነው እንጂ ለማመን አይደለምና።

4. 81 መጻሕፍትን ለማሳየት የቃኤልን ሚስት ጥቅሶ ሚስቱ ማን እንደ ሆነች የሚነግረን መጽሐፈ ኩፋሌ ነው ስለዚህ 81 ትክክል ነው ይላል። ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳቅቅ አካሔድ ነው commentary ራሱ አያስፈልገውም ነገር ግን የቃኤልን ሚስት ማን እንደሆነች ለማወቅ ቢያስፈልግ እንኳን የቃኤል ሚስት ማን እንደሆነች የሚነግረን መጽሐፍ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ሊሆን ነው ማለት ነው? እንደዛ ከሆነ የአይሁድ ሥራዎች መካከል ሴዴር ሃዶሮት የተባለው መጽሐፍ የቃኤል ሚስት ካልማና እንደምትባል ይነግረናል ለምን መጽሐፍ ቅዱስ አይሆንም ታድያ? እንዲሁም በዚህ ሎጂክ ትክክል ቢሆን ራሱ መጽሐፈ ኩፋሌን ትክክል ያደርገዋል እንጂ 81 መጻሕፍትን አያሳይም።

5. ሌሎችም እንዲሁ አንድ አንድ መጻሕፍትን የሚያሳዩ ከመጽሐፍ ቅዱ ተጠቅሰዋል ለጊዜው እነርሱን ልተዋቸውና የመጨረሻው ሃሳብ ላይ ላተኩር "81ዱን መጽሐፍ ባልቀበል በነፍስ ያስጠይቃል ወይ?" የሚለውን ጥያቄ ሲመልስ ያስጠይቃል እንጂ በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ታንጻችኋል ይላል ስለዚህ የሐዋርያትን አስተምህሮ ያልተቀበለ ጌታ አልተቀበለም ማለት ነው በማለት ይመልሳል። Interviewወሯ የቁጥሩን ጉዳይ ነው ብላ clear ለማድረግ ብትሞክርም መልሶ አዎ ቁጥሩም የሐዋርያት አስተምህሮ ነው በማለት ይመልሳል። ይህኛው ደግሞ ከሁሉም አደገኛ ሃሳብ ነው የመጀመሪያ "81" የሚለውን የመጻሕፍት ቁጥር ከሐዋርያት አስተምህሮ (Deposit of Faith) ውስጥ አስገብቶታል ይህ ደግሞ መሠረት አልባ ነው deposit of faith ውስጥ ለመግባት መጀመሪያ በሁል ጊዜ ፣ በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም አባቶች የሚታመን መሆኑን ማሳየት ግድ ይላል ነገር ግን እንደማያሟላ ግልጽ ነው ለምሳሌ 81 የመጻሕፍት ቁጥር ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ተቀባይነት እንደነበረው ማሳየት ይቻላል? ይቻላል ከተባለ burden of proof አለበት ነገር ግን ሙሉ ትምህርቱ ላይ ማሳየት አልቻለም ፣ ሁለተኛ በሁሉ ቦታ የሚታመን መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል ይህ ደግሞ ወዲያው ይፈርሳል ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ውጪ አይታመንምና ፣ ሦስተኛ ደግሞ በሁሉም አባቶች የሚታመን መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል ነገር ግን ይህንንም እንደማያሟላ ለማሳየት ብዙ መልፋት አያስፈልግም። ደግሞ የዚህኛው አቋም ትልቁ ችግር የመጻሕፍት ቁጥር 81 መሆናቸውን ማመን የመዳን ጉዳይ አድርጎታል ስለዚህ ከኢትዮያና ከኤርትራ ውጪ ያሉ አማኞች በነፍሳቸው ይጠየቁበታል ማለት ነው።

የዚህ ትችት ዓላማ ለምናምናቸው አስተምህሮዎች የተሻሉና በታሪክ ጥናት ላይ የተመሠረቱ ሙግቶችን እንድናመጣ ነው።
❤ 97 👍 25 🔥 5 🤔 4 👎 1 🥰 1 😁 1 🤯 1
ኪ
18:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቲያኖች ፍጡር እናመልካለን?

ኢየሱስ በሥጋው ፍጡር ነው የሚለውን የሰሙ ሙስሊሞች "ፍጡር ታመልካላችሁ?" እያሉ ክርስቲያኖችን ሲጠይቁ ይደመጣል። ይህ ጥያቄ የመጣው "በሥጋው ፍጡር ነው" የሚለውን አስተምህሮ ካለመረዳት ነው። በሥጋው ፍጡር ነው ሲባል "ፍጡር" የሚለው ቃል የሚያመላክተው ባሕርይን እንጂ ማንነትን አይደለም። ምክንያቱም ክርስቶስ ፍጡር ወኢፍጡር ሲባል ተዋሕዶ የተፈጸመባቸውን ሁለት ባሕርያት የሚያመላክት ቃላት ናቸው እንጂ ሁለት ማንነቶችን የሚያመላክቱ አይደሉም። በተዋሕዶ ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሆኑ እንጂ ሁለት ማንነቶች አንድ የሆኑ አይደለም ይልቅስ አንዱ መለኮታዊ ማንነት የሥጋን ባሕርይ ነሣ እንጂ።

ስለዚህ ፍጡር ታመልካላችሁን? ከተባለ አናመልክም የምናመልከው በማንነቱ መለኮታዊ የሆነውን ክርስቶስ ነው እንጂ ፍጡር ማንነት ያለውን መኖር የጀመረ አካል አይደለም። "ማንን ታመለካላችሁ?" የሚለው ጥያቄም የማንንነት ጥያቄ ነው በክርስቶስ ውስጥም ፍጡር ማንነት ስለሌለ የምናመልከው መለኮታዊውን ማንነት ነው ብለን እንመልሳለን።

አምልኮ ለባሕይር አይቀርብም ይልቅስ መለኮታዊ ባሕርይ ላለው አካል ይቀርባል እንጂ "አምልኮ" በአምላኪውና በተመላኪው አካል መካከል ግኑኝነትን ያመላክታልና ። የሚመለከው ማንነት ቢሆንም ማንነቱ ደግሞ የሚመለክበት ምክንያት መለኮታዊ ባሕርይ ስላለው ነው። ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመለክ የሚመለከው ማንነቱ ነው ማንነቱ ደግሞ መለኮታዊ ባሕርይ አለውና በእርግጥም አምልኮ በትክክለኛው ትርጉሙ ይገባዋል። ሥጋው ይመለካል ወይ ተብሎ ቢጠየቅ የሚመለሰው ሥጋው object of worship ሆኖ አይመለክም የአምልኮ ተቀባይ ሁል ጊዜ ማንነት (Person) ነውና ይልቅስ የመለኮታዊው ማንነት ስለሆነ ስለ መለኮታዊነቱ ይመለካል እንጂ።

አስታውሱ ሁል ጊዜ አምልኮ ከተባለ የአምልኮ ተቀባይ አካል (ማንነት) ነው ኢየሱስ ደግሞ መለኮታዊ ማንነት እንጂ ፍጡር ማንነት አይደለም።

@KidanZeIyesus
❤ 71 🔥 12 👍 7 💯 2 👏 1
9 May 2025
ኪ
09:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዳግሚት ሰማይ

የሰማይ መስኮቶች ተከፈቱ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየነው። በዙሪያው አእላፍ መላእክት አሉ ፤ ዓይኖቻቸው ብዙ የሆኑ ሱራፌል ክንፎቻቸውም ስድስት የሆኑ ኪሩቤል ያመሰግኑታል። መናብርት ፣ አጋእዝትና ሥልጣናት "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ" እያሉ ድምጻቸውን ያሰማሉ። 24ቱ ካህናተ ሰማይ በወርቅ ጽናዎች ዙፋኑን ያጥናሉ ፤ አርባዕቱ እንስሳም ዙፋኑን ተሸክመዋል። በዘመናት የሸመገለው ግን በዙፋኑ ተቀምጧል።

የሰው ልጅም ወደ ዙፋኑ ቀረበ በዘመናት ወደ ሸመገለውም አቀረቡት "አባ አባቴ ልጅህን አክብረው" እያለ ይጣራል አባትም ልጁን "ዙፋኔ ዙፋንህ ነው ፣ መንግሥቴ መንግሥትህ ነው። ልጄ አከብርሃለሁ ከዚህ ሌላ መንግሥት ሌላም ዙፋን እሰጥሃለሁ አንተ በምትቀመጥበት ዙፋን ግን እኔ አልቀመጥም" ሲል ተናገረ። አባትም ለልጁ ዙፋን ይፈልግ ዘንድ ሰማያትን ፣ አየራትን ፤ ምሥራቃትን ፣ ምእራባትን ሁሉ ተመለከተ ለልጁ የሚመጥን ሰማያዊ ዙፋን ግን አላገኘም።

ነጸረ አብ እምሰማይ - አባትም ከሰማይ ሆኖ ተመለከተ የምድርንም ዳርቻዎች ሁሉ ዳሰሰ ፤ ወኢረከበ ዘከማኪ - ድንግል እናታችን ሆይ ልጁን የሚመጥን ሰማይ እንዳንቺ ያለ አላገኘም።
ፈነወ ዋሕዶ ወተሰብአ እምኔኪ- አባትም የሚወደውን μονογενής - አንድያ ልጁን ወደ አንቺ ሰደደ ሥጋሽንም ነሥቶ ዘመዳችን ሆነ ፣ በሰማያት ከፍ ያለው ጌታ በአንቺ ሥጋ ከበረ!

በመጀመሪያው ሰማይስ የሠራዊት ጌታ በቅዱሳኑ ክብር ተገለጠ እንጂ እግዚአብሔርን በባሕርይው ያየው ማንም የለም ፤ በሁለተኛይቱ ሰማይ በድንግል ግን በእቅፉ ያለ አንድያ ልጅ በባሕርየ ሥጋ እግዚአብሔርን ተረከው። ከድንግል የተወለደውን ባየነው ጊዜ አብን አየነው፤ ሁለተኛይቷን ሰማይ ባየናት ጊዜ የመጀመሪያዋን ሰማይ አየናት ፤ በሰውነቱ የመሠረተውን መሢሐዊ መንግሥት ባየን ጊዜ የአብን ሰማያዊ መንግሥት አየን። የአብ አንድያ ልጁ በሁለኛይቱ ሰማይ ከበረ!

እነሆ ለአብ አንድያ ልጁ ሰማይ የምትሆን እመቤት ዛሬ ተወለደች!

@KidanZeIyesus
❤ 140 ❤‍🔥 20 👍 9 🔥 6
10 May 2025
ኪ
10:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
በአብ ቀኝ ያለ ጠበቃ

ብዙ ሰው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለኃጢአታችን ማስተሠርያ ከሆነ በኋላ በአብ ቀኝ ለፍርድ የተቀመጠ ዳኛ ኃጢአት ስንሠራ ለምን ሠራችሁ ብሎ የሚቆጣ ፈራጅ አድርገን እንስለዋለን ስለዚህም ኢየሱስ ተቆጪ አምላክ ስለሆነ ርኅርኅተ ህሊና በሆነችው በእመቤታችን በኩል እናገኘዋለን እሱ ፈራጅ እርሷ ግን ሩኅሩኅ አድርጎ መሳል አለ።

ነገር ግን አንድ ነገር አስታውሱ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባለ ፍቅሩ አሁንም በአብ ቀኝ አለ ፤ በመስቀል ላይ ለኃጢአታችን ማስተሠርያ እንደሆነው አሁንሞ በአብ ቀኝ ለኃጢአታችን ማስተሠርያ ነው ለኃጢአታችን ብቻ አይደለም ለዓለም ሁሉ ኃጢአት እንጂ። ኢየሱስ በአብ ቀኝ የተቀመጠው ኃጢአት በሠራን ቁጥር ለምን ብሎ የሚቆጣን ፈራጅ ሳይሆን አንዴ ባቀረበው ምልጃ የሚያስታርቀን አስታራቂ ነው በገዛ በደሙ ወደ ሰማያት ገብቷልና! ነገር ግን የኃጢአታችን ጠበቃ በሰማያት አለ ብለን ኃጢአትን የመሥራት ነጻነት የምናገኝ አይደለም ይልቅስ በአብ ቀኝ ያለውን ጌታችንን ለመምሰል በቅድስና ሕይወት እንመላለሳለን እንጂ ደካሞች ነንና ብንወድቅም በደሙ እንነጻለን።

በእመቤታችን በኩል ወደ ጌታ መቅረብ መልካም ነው ነገር ግን ጌታን ተቆጪ አደርጎ በመሳል አይደለም "በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለንና። (ኤፌ 3:12)

በመስቀሉ ላይ በታላቅ መቃተት ምልጃን በማቅረብ የወደደን ጌታ አሁንም በዚሁ ፍቅሩ በአብ ቀኝ አለ ስለዚህም ስለእኛ ይማልድልናል ፤ ከአቤል ደም ይልቅ የሚጮህ ደም ❤️

@KidanZeIyesus
👍 77 ❤ 39 🤔 20 🔥 5 👏 1
ኪ
15:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዶግማችን የቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት ይሁን!

ከሰሞኑ በቤተክርስቲያናችን በሰዉ ልብ ዘንድ የተሳለ አንድ ነገር አለ እርሱም ዶግማችን ከፕሮቴስታንቶች መለየት ማስመሰል ነው። ማለትም ወደ ፕሮቴስታንት የቀረበ የመሰለን ማንኛውም ትምህርት ዶግማ እስኪመስል ድረስ ማውገዝ እንዲሁም ከእነርሱ ትምህርት ለመራቅ ተብሎ አባታዊውን ትምህርት እስከ መካድ መድረስ።

ለምሳሌ የሰሞኑን ጳጳሳት ጉዳይ ብናይ "ማርያም ቤዛ አትባልም" ያሉትን ጳጳስ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቃውሞ ነው የተሰማው ምክንያቱም ቤዛ አትባልም የሚሉት ፕሮቴስታንቶች ናቸው። ነገር ግን በተቃራኒው "የምንቀበለው የማርያም ሥጋ ነው" ያሉትን ጳጳስ የተቃወሙ ቢኖሩም ተቃውሞው ግን አልበረታም ለምን "ፕሮቴስታንቶች የማርያምን ሥጋ ነው ምንቀበለው ስለማይሉ" እውነት ለመናገር ፕሮቴስታንቶች እንዲህ ያለ ትምህርት ቢኖራቸው ኖሮ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቃውሞ እንሰማ ነበር። ይገባኛል በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ገብተን ፕሮቴስታንታዊ ትምህርት የሚያስተምሩ ተዋሕዶሶች ስለነበሩ የትኛውም ፕሮቴስታንታዊ የሚመስል ትምህርት ሲሆን ስጋት ይደቀንብናል ነገር ግን የአስተምህሮዋችን ማእከል የአባቶች ትምህርት እንጂ ፕሮቴስታንትን መቃወም ማድረግ የለብንም።

የክርስቶስ ምልጃ ጉዳይ ላይም ተመሳሳይ ነገር ነው የማየው ስለ ክርስቶስ ምልጃ ፕሮቴስታንቶች ስለሚያስተምሩ ከተሐድሶዎች ጋርም በዚህ ጉዳይ የክርክር ጠባሳ ስለነበር የትኛውም የክርስቶስን ምልጃ ያጎላ ትምህርት ስናይ ፕሮቴስታንታዊ ይመስለናል ነገር ግን የራሳችን የቤተክርስቲያን አባቶችም ሆኑ የአምልኮ መጻሕፍቶቻችን በክርስቶስ ምልጃ ትምህርት የተሞሉ መሆናችንን አንዘንጋ የክርስቶስ ምልጃ ትምህርት ኦርቶዶክሳዊ እንጂ ፕሮቴስታንታዊ አይደለም እንዳውም ከማንም ይልቅ ለእኛ የተገባ ነው አንድ ጊዜ በቀረበው መሥዋዕት በቁርባን አማካኝነት እንቀበለዋለንና ፕሮቴስታንቶች ግን ቁርባን የኃጢአት ይቅርታ የሚሰጥ የዕለተ አርቡ መሥዋዕት ነው ብለው ስለማያምኑ ለማስረዳት ይከብዳቸዋል።

እኔ ግን የመጨረሻ ነገር ልበላችሁ ለትምህርት ማንጸሪያዬ የቤተክርስቲያን አባቶች ናቸው እንጂ ፕሮቴስታንቶችን መቃወም አይደለም። ስለዚህ የቤተክርስቲያን አባቶች ያስተማሩትን በልበ ሙሉነት እኔም እናገረዋለሁ።
❤ 132 👍 16 ❤‍🔥 8 🥰 6 💯 5 🫡 3 🖕 2 🔥 1 😢 1 🕊 1
12 May 2025
ኪ
22:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScWdodYzydXGTOBg21otPFOlpyoWNp1cIW0IXo8Lv4RKfWdBw/viewform?usp=header

በወንድሞቻችን ትልቅ ፕሮጀክት ተጀምሯል ይኸውም ብዙ ያላወቅናቸውን የአባቶቻችንን ጽሑፎች ወደ አማርኛ መተርጎም ነው። በቀድሞ ዘመን አባቶቻችን ግሪክን እያጠኑ አሁን ላይ ሃይማኖተ አበው የምንለውን መጽሐፍ አበርክተውልን አልፈዋል እስካሁንም የቤተክርስቲያናችን ትልቁ የአባቶች መጽሐፍ እርሱ ነው።

አሁን በእኛ የአባቶቻችን ልጆችም የቅድመ ኒቅያ አባቶችን ጽሑፍ ወደ አማርኛ በመተርጎም የአባቶቻችንን ፈለግ እንከተል ከላይ ባለው ሊንክ ይመዝገቡ።

ለዚህ አገልግሎት የሚፈለጉት ፶ (ሀምሳ) ሰዎች ብቻ ናቸው። የተቀሩት በ፪ኛ (ሁለተኛ) ዙር ይመዘገባሉ። ለአገልግሎቱ የሚመረጡት ፦

1. ጠቅላላ መስፈርት

፩. ኦርቶዶክሳውያን መሆን አለባቸው።
፪. ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ተነሣሽነት ያላቸው።
፫. ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉትን ትምህርቶች ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ እና ጊዜያቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ።
፬. አጭር የሆነ ስለራሳቸው ማብራሪያ (ለምን እዚህ አገልግሎት ላይ መሳተፍ እንደፈለጉ የሚገልጽ አነስተኛ ማብራርያ ማቅረብ የሚችሉ)።

2. የጽሑፍ ፈተና

፩. የእንግሊዝኛ ነገረ መለኮታዊ ጽሑፎችን የመተርጎም ፈተና (2 አንቀጽ የሆነች አጭር ጽሁፍን)።

በትምህርት ጊዜ መቅረት፣ በሥራ ጊዜ አለመገኘት እና መዘግየት፣ ከወንድሞች እና ከእህቶች ጋር ክርስቲያናዊ ባልሆነ መንገድ ማንኛውንም ነገር ማድረግ ከማኅበሩ ያስባርራል።

እግዚአብሔር ያስፈጽመን ።

https://t.me/Theo_Sophia_apology
❤ 76 🥰 8 👏 8 👍 6 👎 1
14 May 2025
ኪ
10:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስልምና የ"Equivocation and Root Word Fallacy" አባት

ከእስልምና መሠረታዊ አስተምህሮ መካከል አንዱ አላህ ነቢያትን ወደ ምድር ሕዝቦች ሁሉ መላኩና ሙሀመድ የአላህ የመጨረሻ ነቢይ መሆኑ ነው። ከዚህ የተነሣ ሙሀመድ ወደ ምድር አዲስ ሃይማኖትን ይዞ ሳይሆን የመጣው በቀደሙት ነቢያት ፈለግ የመጣ መሆኑን ይናገራሉ። ስለዚህም እስልምናም ሆነ ሙስሊሞች ከሙሀመድም በፊት ነበሩ እያሉ ሙግት ያቀርቡ ነገር ግን የሚያቀርቡት ሙግት የስነ-አመክንዮ ሕፀፅ ያለበት ነው።

ሙስሊም ማለት "ለአንድ አምላክ የሚገዛ ሰው" ማለት ነው። ከሙሀመድ በፊት ለአንድ አምላክ የሚገዙ ሰዎች ነበሩ ፤ ስለዚህ ከሙሀመድ በፊት ሙስሊሞች ነበሩ። እያሉ መሠረታዊ ሕፀፅ ያለበት ሙግት ያቀርባሉ ይህ ሙግት "Root word fallacy" የተባለውን የFallacy አይነት ይሠራል "ሙስሊም" ማለት ለአንድ አምላክ የሚገዛ ማለት ስለሆነ ሙስሊም የሚለው ቃል ሁል ጊዜ ይህን ትርጉም ነው የሚይዘው ማለት ነው። ለምሳሌ እኔ ለአንድ አምላክ እገዛለሁ ስለዚህ እኔ በእምነቴ ክርስቲያን ብሆንም "ሙስሊም" ነኝ ማለት እችላለሁ ነገር ግን የትኛውም ሙስሊም ይህን እንድል አይፈቅድልኝም በዚህ ብቻ "ሙስሊም" የሚለው ቃል "ለአንድ አምላክ የሚገዛ" የሚል ትርጉም ብቻ እንዳልያዘ እንረዳለን። ምናልባት አንዳንድ ሙስሊሞች "አንተ በሥላሴ ስለምታምን ለአንድ አምላክ አትገዛም ስለዚህ ሙስሊም አይደለህም" የሚል ተቃውሞ ሊያመጣ ይችላል እሺ ይሁን እስቲ ለሙግቱ ሲባል ሌላ ምሳሌ እናምጣ። ቤንያሚን የሚባል አይሁዳዊ አሁን እስራኤል ውስጥ ይኖራል በሃይማኖትም አይሁዳዊ ነው ፣ አምላክም በአካል አሐዳዊ ነው ብሎ ያምናል ይገዛለታልም ስለዚህ ቤንያሚን "ሙስሊም" ነው። ይህንንም ምሳሌ ብታዩት የትኛውም ሙስሊም አይቀበለውም እስራኤላውያን ሙስሊም ናቸው ብለው መቼም አይናገሩምና ስለዚህ "ሙስሊም" የሚለው ቃል ትርጉሙ "ለአንድ አምላክ የሚገዛ" ብቻ ሳይሆን ከዚህ የተለየ ትርጉም እንዳለው እንረዳለን ይህም"ሙሀመድ ባስተማረው ሃይማኖት የሚያምን ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ" ማለት ነው። ስለዚህ ሙስሊሞች "ከሙሀመድ በፊት ሙስሊሞች ነበሩ" ሲሉ ለአንድ አምላክ የሚገዙ ሰዎችን ብቻ ማሳየት በቂ ማስረጃ አይደለም ይልቅስ ሙሀመድ ባስተማረው እያንዳንዱ አስተምህሮ የሚያምን ሰው ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ስለዚህ ስምና ታሪካዊ ማስረጃ ይጥቀሱልን።

ሌላኛው ደግሞ ከሙሀመድ በፊት እስልምና ነበረ ብለው ማስረጃ ሲጠየቁ የሚያቀርቡት ማስረጃ ከሙሀመድ በፊት የአንድ አምላክ እምነት (Monotheism) መኖሩን በማሳየት ነው በዚህም "Islam" እና "Monotheism" የሚሉት ቃላት ላይ equivocation ይሠራሉ ምክንያቱም የአንድ አምላክ እምነት መኖሩ ብቻ እስልምናን አያሳይም ይልቅስ አብረሃማዊም የሆኑ (ይሁዲና ክርስትና) እንዲሁም አብርሃማዊ ያልሆኑ (Zoroastrianism, Atenism) የአንድ አምላክ እምነቶች ከእስልምና በፊት ነበሩና ነገር ግን አስተምህሮዋቸው "ከሙሀመድ እስልምና" የተለየ ነው።

ከሙስሊም ወገኖቻችን የምንጠይቀው ከሙሀመድ በፊት የአንድ አምላክ እምነት ወይም ለአንድ አምላክ የሚገዙ ሕዝቦች መኖራቸውን ሳይሆን "የሙሀመድ እስልምና" መኖሩን በታሪካዊ ማስረጃ እንዲያሳዩን ነው።

@KidanZeIyesus
❤ 91 👍 24 🔥 21 🙏 4 👏 1
15 May 2025
ኪ
07:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
Athanasius Contra Mundum (Athanasius against the world)

ዓለም በአርዮሳዊ ክህደት ስትዋጥ ብቻውን ኦርቶዶክሳዊነትን የጠበቀ የቤተክርስቲያን ምሶሶ!
ኦርቶዶክሳዊነት በኒቅያ ጉባኤ የበላይነት ቢያገኝም ዓለም ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ይልቅ አርዮሳዊነትን መረጠ ከንጉሠ ነገሥቱ ፣ እስከ ጳጳሳት ፣ እስከ ካህናት እና ኃያላን ድረስ ፣ ኹሉም ማለት ይቻላል በአርዮስ ምንፍቅና ቫይረስ ሲጠቁ አንድ ሰው ግን ዓለምን ሞግቶ ተገኘ፤ ቅዱስ አትናቴዎስ!
አትናቴዎስ ዓለምን ተቃርኖ ለእውነት ቆመ ፣ በዚህም ምክንያት በ4 የሮማ ነገሥታት ተጠልቶ 5 ጊዜ ከመንበሩ ተሳደደ። እርሱ ግን በዚህ ኹሉ ውስጥ ተስፋ ሳይቆርጥ ለእውነት ቆመ። የአርዮሳውያን መዶሻ ገና በ 19 ዓመቱ " On the incarnation" የተባለውን ዘመን ተሻጋሪ መጽሐፍ የደረሰ ፣ የክርስቶስን ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ መኾን እስከ መጨረሻ የሕይወት እስትንፋሱ የጠበቀ፣  ሕይወቱን በሙሉ ለክርስቶስ የሰጠ ታላቁ አባት ቅዱስ አትናቴዎስ ዛሬ እረፍቱ ነው።

ምናልባት ያለ ቅዱስ አትናቴዎስ ክርስትናን ዛሬ በምናውቀው መንገድ ላናውቀው እንችል ይኾናል ፣ አርዮሳውያን ያሸንፉ ነበር ነገር ግን ክርስቶስ "የገሃነም ደጆች አይችሏትም" ያለውን ቤተክርስቲያኑን አይተውና ለቤተክርስቲያን ቅዱስ አትናቴዎስን አስነሣላት ፣ እርሱም ዓለምን ተቃውሞ እውነትን ጠበቀ ፣ ቤተክርስቲያንም በታመነ ዓለት ላይ ጸናች እርሱም ቅዱስ አትናቴዎስ የታገለለት እውነት "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ፣ እግዚአብሔር ነው ፣ ከአባቱ ጋርም አንድ ባሕርይ ነው" የሚለው የማይነቃነቅ ፣ የማንለውጠው ሃይማኖታችን ነው።

“If the world is against the truth, then I am against the world.”
― Athanasius of Alexandria

St. Athanasius the Apostolic my patron saint ❤️
❤ 131 🥰 14 👍 11 🔥 6
ኪ
09:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/ZAfLgoIvUOs?si=ccAyk4EaLTAIbUbU

1.
Hail to you, O hero, defender of the true faith,
A rock not even the gates of hell could overcome.
2.
In your time, you were a martyr, O Ava Athanasius,
A deep theologian, the pride of the Orthodox.
3.
You honored the Church in the fourth century,
Anba Alexandros chose you as deacon in the councils.
4.
A boy, yet a saint, born to an Egyptian family,
You studied Christian sciences in school.
5.
In your baptismal acts, you were pure and innocent,
Simple in thought, using spiritual means.
6.
You began the path young and grew in knowledge,
Just as Jesus entered the temple as a teacher.
7.
You knew Anba Anthony and became his disciple,
You wrote his life story and followed his example.
8.
Faithful in your service, compassionate to the poor,
Feeding the hungry and hosting strangers.
9.
At the Council of Nicaea, you defended the faith,
Exposing Arius’s heresy with the zeal of the brave.
10.
You struggled greatly in life with selfless love,
And were chosen as shepherd for your pure conduct.
11.
You endured harsh suffering, exile, and conspiracies,
They falsely accused you of sin with a harlot.
12.
But your disciple was courageous and faithful like you,
He exposed the lie, and the people rejoiced.
13.
The sinner repented and became your friend,
You received him with love and treated him as a brother.
14.
They cried out to you, “The whole world is against you!”
You answered, “And I am against the world,” and they fell silent.
15.
The tribulation did not last, through the power of prayer,
And by heavenly justice, Arius quickly died.
16.
Exiled in Rome, you were seen by Western fathers,
They praised and cherished you and held you in their hearts.
17.
You amazed the West by your wondrous humility,
Even in defending yourself, they welcomed you with honor.
18.
The Emperor summoned you and saw your integrity,
He ordered your return and treated you kindly.
19.
You returned to your people after struggle and pain,
Nine long years away from the world.
20.
The Coptic people rejoiced and cried aloud,
And devoutly declared they would die for you.
21.
Persecution intensified by the followers of Arius,
But believers sheltered you in Christ’s care.
22.
The Copts stepped forward, choosing crowns,
They marched joyfully toward martyrdom.
23.
You left persecution and went to the wilderness,
With holy fathers in a consecrated life.
24.
You defended the faith and Orthodoxy,
Overlooking personal grudges.
25.
And when God willed, the persecution ended,
You returned to your people crowned in glory.
26.
A great hero, victorious over enemies,
Even more—victorious over hatred.
27.
You gathered the bishops to establish canons,
In a holy council for those who repented.
28.
You triumphed over Satan when you welcomed sinners,
And those returning to the faith entered God’s Kingdom.
29.
In hardship and trial, you never despaired,
Obedient to the Gospel, relying on God.
30.
Pray for us, that we may learn from you,
To follow your example in trial and tribulation.
31.
Your wisdom and humility drew hearts to you,
A wonder in your Church, glorified by all.
32.
Your struggle was long, like the holy apostles,
They called you apostolic, and your light has shone.
33.
You zealously sought the ingredients for the Myron,
You or your disciple made it—with God’s help.
34.
Your memory lives in our hearts; your place is in heaven,
The seventh of Bashans (ግንቦት) is the day of your departure.
35.
The meaning of your name is on every believer’s lips:
All say, “O God of Pope Athanasius, help us all!”
❤ 51 👍 9 🙏 2
ኪ
15:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ ቲክቶክም Live እንግባ
👍 69 🥰 16 ❤‍🔥 13 ❤ 9
ኪ
23:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
👍 43 ❤ 16 🙏 5
16 May 2025
ኪ
13:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
ትናንት የተማማርንበት PDF

@KidanZeIyesus
❤ 60 🔥 5 👍 3
19 May 2025
ኪ
10:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
ረቡዕ ማታ እንቀጥለዋለን
👍 65 ❤ 20 🔥 13 🥰 2
21 May 2025
ኪ
22:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
ስለ ትንሣኤው እስካሁን የገባነው በቂ ነው መሰለኝ ከዚህ በላይ ሙስሊሞች ምንም objection ሊያመጡ አይችሉም ከዚህ በኋላ በቃ የAtheism ምናምን ነው የቀረው። ስለዚህ ቀጣይ ወደ ሌላ ርእስ እንለፍ መሰለኝ ወይስ አንዴ እንግባ ምን ትላላችሁ? ወይስ መጀመሪያውኑ ጥያቄ ያልሆነባችሁ ነገር ተነሣ?
❤ 65 👍 8 🔥 6
22 May 2025
ኪ
17:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለምን "ክርስቶስ አልተነሣም" ለማለት የሚቀርቡት ማብራሪያዎች በሙሉ ይወድቃሉ?

ትናንት የተማማርነው pdf ያው ብዙው ነገር አላየነውም ነበር ግን።

@KidanZeIyesus
❤‍🔥 45 ❤ 16 👍 5
27 May 2025
ኪ
10:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
እግዚአብሔር አይዘበትበትም!

እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና! አዎ የእግዚአብሔር ምሕረት ወሰን የሌለው ዘለዓለማዊ ነው የእኛ ትንሿ ኃጢአት በእግዚአብሔር ምሕረት ፊት ስትቆም 0 ነው የምትሆነው 1/∞ =0 ይሆናልና። ለምሕረቱ ወሰንና ልክ የሌለው ስለሆነ ምንም ኃጢአት ብንሠራ በእግዚአብሔር ምሕረት ፊት የማይሠረይ ኃጢአት የለም ፤ ከአንድ ኃጢአት በስተቀር መንፈስ ቅዱስን መሳደብ!

የሰውን ልብ የሚያራራ ወደ እውነተኛ ንስሐ የሚጠራ መንፈስ ቅዱስ ነው ስለዚህ ሰው የመንፈስ ቅዱስን ጥሪ ችላ ብሎ ልቦናውን ወደ እውነተኛ ንስሐ ባይመልስ ከዚህም ይባስ ብሎ በእግዚአብሔር መሐሪነት ላይ የሚዘባበት የእግዚአብሔርን ምሕረት ተገን አደርጎ በኃጢአት ላይ ኃጢአት የሚጨምር ኃጢአቱ በዚህም ዓለም ሆነ በሚመጣው ዓለም አይሠረይለትም። የእግዚአብሔር ምሕረት የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ሰውን ወደ እውነተኛ ንስሐ የሚጠራ ነው እንጂ ንስሐ እገባለሁ ብሎ ኃጢአት ለመሥሪያ በር ከፋች አይደለም። እግዚአብሔር ያያል ፤ ውጫዊ ግብርንስ አይደለም ውሳጣዊ ልብን ያያል ኩላሊትን ይመረምራል ሰውን ልናታልል እንችላለን ነገር ግን አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም!

ክርስቲያን ሆኖ ኃጢአትን የማይሠራ የለም ነገር ግን ሁሉም አይነት ኃጢአተኝነት ከክርስትና ሕይወት ጋር ተስማሚ አይደለም። ኃጢአት ሁሉ ለሞት አያደርስም ነገር ግን ለሞት የሚያደርስ ኃጢአት አለ። ዝሙተኝነት ለሞት የሚሆን ኃጢአት ነው ከክርስትና ጋር በፍጹም ሊስማማ ይቅርና ከእግዚአብሔር ይለያል ከቤተክርስቲያን አንድነትም ይለያል። ይህንን ለመገሰጽ ኃጢአት አልባ መሆን አይጠበቅብንም ክርስቲያን መሆናችን ብቻ በቂ ነው ፤ ኃጢአት በደጋፊ ብዛት ጽድቅ አይሆንም ዓለም ሁሉ እንኳን ከእኛ ጋር ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ኃጢአት ኃጢአት ነው። ስህተት በሰው ምስክርነት ብዛት ትክክል አይሆንም ይልቅስ የትክክለኝነት (ጽድቅ) ሁሉ ምንጭ እግዚአብሔር ነው!

እግዚአብሔር አይዘበትበትም!
❤ 149 😢 12 👍 9 🥰 3 ❤‍🔥 1
29 May 2025
ኪ
09:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ትክክለኛውን መጻሕፍተ መቃብያን የያዘ መጽሐፍ ቅዱስ በእጃችን ገብቷል 🙌
❤ 101 🤪 8 😱 7 🔥 4 🤣 2
1 June 2025
ኪ
12:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅዱሱ ቤተሰብ ወደ ምድረ ግብጽ የገባበትን ቀን ግንቦት 24ን በማሰብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቅብጥ ቀን ይከበራል። ግብጽን የባረኩ ቅዱስ ቤተሰብ እኛንም ይባርኩ።

ሰላም ለበዓትከ ውስተ ምድረ ግብጽ ዘኮነ ። ብሉየ መዋዕል አምላክ በጊዜ ኮንከ ሕፃነ ። እምበትረ ዮሴፍ አሜሃ ከመ ታርኢ ሥልጣነ ። ገቢረከ በበስባር ኀበ ተከልከ መካነ ። ማሕተመ ቅድሳት ይኩን አውሐዝከ ሜሮነ ።
❤ 131 🥰 19 👍 7 🔥 2
ኪ
18:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
በቲክቶክም በዚህም ጥሩ የሚሠራ ወንድማችን ነው ሁላችሁም በእኔ ይሁንባችሁ ተቀላቀሉት

https://t.me/a_lr_a_e_d

https://t.me/a_lr_a_e_d
❤ 45 👍 12 👎 1
3 June 2025
ኪ
16:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ መልሱ

አብ አምላክ ነው ፣ ወልድ አምላክ ነው ፣ መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው። ነገር ግን አንድ አምላክ ብቻ ነው ያለው።

ይህ የላዩ ትክክል ከሆነ አብ ፣ ወልድ ፣ መንፈስ ቅዱስ በሁሉ ነገር ተመሳሳይ ናቸው። ምክንያቱም A=C , and B=C ከሆነ A=B መሆን አለበት። እናንተ ግን አብ ወልድ አይደለም ፣ አብ መንፈስ ቅዱስ አይደለም እንዲሁም ወልድ አብም መንፈስ ቅዱስ አይደለም ትላላችሁ ይህ እንዴት ይሆናል?

ምሳሌ: አበበ የA Company CEO ነው ፣ ከበደ የA Company CEO ነው ፣ መለሰ የA Company CEO ነው ነገር ግን A የተባለው company አንድ CEO ብቻ ነው ያለው ይህ አበበ ፣ ከበደ እና መለሰ አንድ ሰው መሆኑን አያሳይም?
❤ 48 😢 6
4 June 2025
ኪ
14:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሻማ ፀሐይን ሊሸፍን አይችልም?

አሁን አሁን abuse እየደረገ ካለው አነጋገር መካከል "ቅዱሳን ምንም ቢከብሩ የክርስቶስን ክብር ሊነኩ አይችልም" የሚለው አነጋገር። ስለዚህ ጉዳይ ቅዱስ አውግስጢኖስ ዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 2 ላይ ክርስቶስ ቤተመቅደሱን ሲያጸዳ በሬዎችን ርግቦችን መበታቱን እንዲህ በማለት ይተረጉማል "They who have dispensed to us the Holy Scriptures are understood to mean the oxen. The apostles were oxen, the prophets were oxen... Those oxen, then, have left to us the narration of the Scriptures. For it was not of their own that they dispensed, because they sought the glory of the Lord... See this ox magnifying his Lord, because the ox knows his owner; observe that ox in fear lest men desert the ox’s owner and rely on the ox: how he dreads them that are willing to put their confidence in him: Was Paul crucified for you? Or were ye baptized in the name of Paul?... Let them say always, The Lord be magnified, they that wish the peace of His servant.” St. Augustine, Tractates on the Gospel of John, Tractate 10:7

በዚህ ላይ ቅዱስ አውግስጢኖስ እየነገረን ያለው በሬ የተባሉት ሐዋርያት ናቸው ፣ ሐዋርያት ወደ ዓለም ሁሉ ወንጌልን ሲሰብኩ እነርሱ እንዲከብሩበት አይደለም ይልቅስ ጌታ እንዲከብር እንጂ ስለዚህም እኛም በሬዎቹን ትተን የበሬው ባለቤት ላይ እንተማመን በማለት "ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቀልን ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን" የሚለውን ጥቅስ ይጠቅሳል።

ከዚህ የምንማረው የቅዱሳን ዓላማ ወደ ክርስቶስ እንዲያቀርቡንና በእርሱ ላይ መተማመናችን እንዲሆን ነው እንጂ በእነርሱ ላይ እንዲሆን አይደለም። እውነት ነው የፀሐይ ብርሃን በሻማ ብርሃን አይሸፈንም ነገር ግን የሻማን ብርሃን ብቻ የለመደ ሰው ወደ ፀሐይ እንዳይደርስ ከራሱ ሊሸፈንበት ይችላል። ልክ እንዲሁ ቅዱሳን ክርስቶስን ሊሸፍኑት አይችሉም ነገር ግን ግለሰቦች ቅዱሳንን ማክበር ብቻ ለምደው ክርስቶስ ሊሸፈንባቸው ይችላል። ከዚህ የተነሣ የኦርቶዶክሳዊነትን መጠን ማወቅ ይገባናል ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከመምህራኑም ከምእመናኑም መጠንን ያለፉ ንግግሮች እንሰማለን መምህራኑም ልክ ጳውሎስና ቅዱስ አውግስጢኖስ እንደተናገሩት "ተክለ ሃይማኖት ስለ እናንተ ተሰቀለን ወይስ በማርያም ስም ተጠመቃችሁን?" ብለው ሲገስጹ አንሰማም ለእነርሱ ፕሮቴስታንትን እስከ ተቃወመ ድረስ በተቃራኒው አቅጣጫ ቢለጠጥ ግድ አይሠጣቸውና!

እንደዚህ አይነት ሀሳብ የሚያነሳ ሰውንም ፕሮቴስታንታዊ እሳቤ ይዞታል ብለው ለማሸማቀቅ የሚሞክሩ አሉ ነገር ግን ሁሉ ነገራችን ክርስቶስን ማእከል ያደረገ መሆኑ ኦርቶዶክሳዊ እንጂ ፕሮቴስታንታዊ አይደለም!
❤ 162 👍 17 🤔 8 💯 3 😢 2 🎉 2
7 June 2025
ኪ
13:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
መለኮታዊ እሳት

የሚያቃጥል የእሳት ልሳን ከሰማያት ወረደ ፣ ከአርያሙ ከፍታ የሚባላ እሳት ወረደ። ይህ እሳት ግን ሰዶምን እንዳጠፋው እሳት የጥፋት እሳት አይደለም ይልቅስ የባቢሎንን ግንብ ያፈረሱ 72 ልሳናትን ይዟል እንጂ። የባቢሎኑ ልሳንስ አንድ የነበረው ሕዝብ የበታተነ ነው የአሁኑ ልሳን ግን እስከ ዓለም ዳርቻ የተበተነውን ሕዝብ የሚሰበስብ ነው። በሰዶም ላይ የወረደው እሳት ሕዝቡን ከነ ኃጢአታቸው ያጠፋ እሳት ነው ፣ የአሁኑ እሳት ግን ለዓለም ሕዝብ ኹሉ የምሥራች ወንጌልን የሚሰብክ የሚያድን እሳት ነው።

ከጽርሐ አርያም እሳት ወረደ በጽርሐ ጽዮንም ላይ አረፈ የሚንበለበል ልሳናትን ይዟል እንደ ሰከረ ሰው በኃይል ያናግራል ፣ በሰይፍ ፊት ድፍረትን የሚሰጥ ስልጣንን ተጎናጽፏል ፤ ስለ እውነትም ይመሰክር ዘንድ ዝም አይልም "እናንተ የሰቀላችሁትን ክርስቶስ እግዚአብሔር በክብር አስነሣው" እያለ በሚገባው ቋንቋ ኹሉ ይወቅሳል፤ ከሰማይ ወርዶ ይቆፍራል መሬትንስ አይደለም የሰውን ልብ ይቆፍራል የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ እንዲፈልቅ ይቆፍራል (ዮሐ 7፡38)። ለዘለዓለም በሚያረካውም ውሃ ልብን ያረሰርሳል። የማይጠፋ ብርሃን አለው፤ በተስፋው ብርሃን እየዋጀ የብርሃን ልጆች እስክንኾን ድረስ አይተወንም ኹሉንም ለእግዚአብሔር ይዋጃል ከማኅጸነ ዮርዳኖስም ወልዶ የሰማያት ልጆች አድርጎናል እርሱም የርስታችን መያዣ ነው (ኤፌ 1፡14) ስሙም ከአብ የሚወጣ አጽናኙ የእውነት መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ነው! (ዮሐ 15፡26)

ኢዩኤል ሆይ ደስ ይበልህ እነሆ ትንቢትህ ተፈጸመ መንፈሱ በሥጋ ለባሽ ኹሉ ላይ ፈሷል ፣ ወንዶችም ሴቶችም ትንቢትን ተናግረዋል ፣ ሽማግሌዎችም ሕልምን አልመዋል፣ ጎበዞቻችንም ራእይን አይተዋል ፣ በሰማያትም ድንቅ ታይቷል (ኢዩ 2፡28-30)። ልባችን በመለኮታዊው እሳት ተቃጠለ እነሆ ጽርሐ ጽዮን በደስታ ተሞላች ፣ ከጽርሐ አርያምም ጋር አንድ ኾነች አጽናኙ መጥቷልና ፣ ድንቅም ከሰማያት ፈሷልና!

አቤቱ መለኮታዊው እሳት ሆይ! ነፍሳችንን አንድደው ፣ የክርስቶስ ሕይወት ብርሃን በውስጣችን ይበራ ዘንድ፤ የማትጠፋ እሳት ሆይ! ኹለመናችንን ተቆጣጠር። ነፍሳችን በኃጢአት ውሃ ቀዝቅዛለች ፣ በዓለምም ሃሳብ ተጠምዳ የሕይወትን ውሃ ተጠምታለች። የሕይወት ውሃ ክርስቶስ በልባችን ይፈልቅ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ልባችንንን ስበረው ፣ የክርስቶስን ትንሣኤ ብርሃን በልባችን ውስጥ አቀጣጥለው። አጽናኙ ሆይ! አጽናናን ፣ የዋሑ ርግብ ሆይ! ልባችንን በትሕትና አረስርሰው ምናልባት የሸፈተው ልባችን ትንሽ እንኳን ይመለስ እንደኾነ።

"መንፈስ ቅዱስ አእምሮንና ልብን የሚያበራ ብርሃን፣ መንፈሳዊ ጥማችንን የሚያረካ ውሃ፣  የሚያነጻና የሚቀድስ እሳት ነው። (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በእንተ መንፈስ ቅዱስ)

መልካም በዓለ ጰንጠቆስጤ ኹላችንም በቅዳሴ ተገኝተን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንባረክ፤ ሕይወት የሆነውን ሥጋና ደምም እንቀበል!

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 100 🙏 11 👍 3 🔥 2 🥰 1
8 June 2025
ኪ
16:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/-4wWKH18x78?si=lPgtdovM-tITsrXp

English Subtitle ስላለው አብርታችሁ መስማት ትችላላችሁ የልሳናት ቀንም አይደል በኮፕቲክ ፣ ግሪክ እና አረብኛ የተዘመረ ነው።

መልካም በዓለ ኀምሳ!
❤ 47 👍 1
13 June 2025
ኪ
10:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
"አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያስኝህ መሥዋዕት የልጅህ ሥጋ እነሆ። በዚህም ኃጢአቴን ሁሉ አቃልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሙቷልና። ፻፮ ስለ እኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹሕ የሚሆን የመሢህም ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮኻል። ይህ የሚናገር ደም የኔን የባሪያህን ኃጢአት የሚያስተሠርይ ይሁን።
፻፯ ስለ እነርሱም ልመናዬን ተቀበል። ወዳጅህ ስለ እኔ ጦርንና ቅንዋትን ተቀብሏልና ደስ ያሰኝህም ዘንድ ታመመ። ከዳንሁም በኋላ ሰይጣን ወደ ልቦናዬ ተመልሶ በፍላፆቹ ወጋኝ፤ አቤቱ ምሕረትህን ስጠኝ፤ ጽኑ ከሳሽ ነውና።
፻፰ ኃጢአትንም ምክንያት (ሥንቅ) አድርጎ ገደለኝ፤ እኔን ከሕይወቴ ማሳትን በቃኝ ከማይል ደፋር አድነኝ።
፻፱ አቤቱ ንጉሤና አምላኬ መድኃኒቴም የምትሆን አንተ የእኔን የባርያህን የነፍሴንና የሥጋዬን ቍስል አድርቅልኝ።"

(ቅዳሴ ሐዋርያት)

ዓለምን ሁሉ የያዝህ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር አብ ሆይ በመሥዋዕቱ ደስ ባሰኘህ በአንድ ልጅህ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአቴን ደምስስ ስለእኔ በሚጮህ ደሙም ይቅር በለኝ።

በእንተ ፍቁር ወልድከ መሐረነ - ስለተወዳጁ ልጅህ ማረን ❤️
❤ 85 🙏 12 👏 1
ኪ
11:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/Amlake_Birhan

እንደዚህ አይነት ቅዳሴያትን ማወቅ ከፈለጋችሁ ገባ ገባ በሉ። ቅዳሴያት እና ሌሎች ሥርዓተ አምልኮ ላይ የሚሠራ ጎበዝ ወንድማችን ነው።
👍 17
17 June 2025
ኪ
20:08
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=OpX5S-j0AnU

"በዘላለም ኪዳን በደም ሰንሰለት(2x) ይዘኸን፣
ታስከትለናለህ በልዩ ፍቅር እስከ ሞት ድረስ ወደኸን። (አዝ)

የጨለማው ለሊት የከበበን መከራ፣
ያስጨነቀን ጠላት ከእንግዲህ ላያወራ።
የያዘን ላይዘን የደም ነው ኪዳናችን፣
ሁሉን የፈጸምከው ተባረክ አምላካችን፣

እውነትና መንገድ ሕይወት ነህ የማትጠፋ፣
ለፍቅርህ መኖሪያ ልባችንን ያሰፋ።
ደጃችንን ዘግተን አሜን! ነው በእንባ ሙላት፣
የፍቅርህ ምርኮኞች አድርጎን ያንተ ምሕረት።

በማግኘት በማጣት በደስታ በሃዘናችን፣
የለንም ሌላ ቃል አንተው ነህ አዋጃችን።
አድኖናል ጸጋህ ጽድቃችን ሰማይ ነካ፣
ኢየሱስ ውሃ ነው ትውልዱን የሚያረካ።

አንተ የሕይወት ራስ የሕይወት ፍጻሜያችን፣
የለመለምከው መስክ መሰማሪያው ቅጥራችን።
ቤዛነትህ ሆኖ ኩነኔው የለም ዛሬ፣
ድነናል በጸጋህ አሜን! በዝማሬ።
❤ 81 🙏 6
18 June 2025
ኪ
10:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
I'm sorry Lutherans ይሄን ነገር ግን አልፋታችሁም 😂
😁 56 🥴 8 ❤ 7
22 June 2025
ኪ
13:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
❓ ሪፎርምድ ሰዎች ካላችሁ ተጠየቁ እስቲ

እግዚአብሔር ሁሉም እንዲድኑ የቀደመ ፈቃድ አለው (antecedent will) (1ኛ ጢሞቴዎስ 2:4)፤
ነገር ግን ምርጦቹን (elect) ብቻ ለማዳን የሚከተል  ፈቃድም አለው (Consequent will)፤
እናም ለምርጦቹ ብቻ irresistible grace ይሰጣል፤ የቀሩትን ግን ሳይመርጥ ያልፋቸዋል (Passing over)።
ስለዚህ ጥያቄው ይህ ነው፦
እግዚአብሔር የሁሉንም ሰዎች መዳን በእውነትና በቅንነት የሚፈልግ ከሆነ (antecedent will)፣ ይህ ፈቃዱ የሁሉንም መዳን የማያስገኝበት ትክክለኛው ምክንያት ምንድን ነው?

የሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ ነው እንዳይባል ሰው ኃጢአትን የመሥራት ነጻ ፈቃድ አለው እንጂ እግዚአብሔርን መምረጥ እንዳይችል የሞተ ነው ድኅነትም በunconditional election እንጂ በሰውየው ላይ ባለ ምንም ነገር አይደለም ስለዚህ ሁሉንም የማዳኑ antecedent will effectual የማይሆነው በምን ምክንያት ነው? ምክንያት ከሌለውስ in any meaningful sense እግዚአብሔር የሁሉንም መዳን ይፈልጋል ማለት እንችላለን?
❤ 47 🥰 5 🔥 1 🤔 1
ኪ
19:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከወንድሞች ጋር ከነገ ጀምሮ ተከታታይ የጽድቅ ትምህርት እንጀምራለን ተሰብስባችሁ ተገኙ።
❤ 86 👍 5 🏆 3
23 June 2025
ኪ
15:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሐዋርያት የእምነት መግለጫ

በቅዳሴያችን ሁለት የእምነት መግለጫዎችን (Creed) እንጸልያለን። አንደኛው በደምብ የታወቀው ጸሎተ ሃይማኖት እያልን የምንጠራው የኒቅያ-ቁስጥንጥንያ የእምነት መግለጫ ነው። ሌላኛው ደግሞ ብዙ ጊዜ ያላስተዋልነው "አመክንዮ ዘሐዋርያት" የተባለ የእምነት መግለጫ ነው። ይህን ክሪድ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ለማየት ሞክሬ አላገኘሁትም ነገር ግን በቤተክርስቲያናችን ለሐዋርያት ተሰጥቶ ቅዳሴ ሐዋርያት ፣ ቅዳሴ እግዚእ ፣ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድና ቅዳሴ ማርያም በተቀደሰ ቀን በጸሎተ ሃይማኖት ቦታ በዜማ ታጅቦ ይታወጃል።

ይህ አመክንዮ ዘሐዋርያት በ9 ምእራፎች የተዋቀረ ሲሆን ለተለያዩ ጥንታውያን ምንፍቅናዎች መልስ ይሰጣል ከእነዚህ ውስጥ ፡ Gnosticism, annihilationists , Judaizers ተጠቃሽ ናቸው። የያዘው ነገረ መለኮትም ጥንታዊነቱን አጉልቶ ያሳያል ብዙ ጥናትም ሊደረግበት ይገባል። አመክንዮ ዘሐዋርያት እንዲህ ይነበባል፡

የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት በሚኾን፥ ፍጥረትን ኹሉ በፈጠረ፥ በአንድ አምላክ እናምናለን።
ለህላዌው (ለአኗኗሩ) ምክንያት የለውምና፥ አስቀድመን እንደ ተናገርን በዘመን ኹሉ ይኖራል እንጂ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ የለውም። በእርሱም የማይጠፋ ብርሃን አለ፤ ወደ እርሱ ለመቅረብም የሚቻለው የለም። ብቻውን የሚኖር አንድ ነው እንጂ፥ ሁለት ወይም ሦስት ወይም ከዚያ በላይ አይደለም። ኹሉን የያዘና በፍጥረቱም ኹሉ ላይ የሠለጠነ መሆኑን በኦሪትና በነቢያት ተረድተን ያወቅነው እንጂ፥ የማይታወቅ የተሠወረ አይደለም። ከእርሱ ጋር የተካከለ፥ ሹመታትንና ሥልጣናትን ኹሉ የፈጠረ፥ ዓለም ሳይፈጠር የተወለደ አንድያ ልጅ የሚሆን፥ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር አንድ ነው።

ጌታችንም በኋለኛው ዘመን ሰው ይሆን ዘንድ ወደደ፤ ያለዘርዐ ብእሲ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነሣ፤ ያለ ኀጢአትና ያለ በደል እንደ ሰው አደገ፤ በአንደበቱም ምንም ሽንገላ አልተገኘም። ከዚህም በኋላ በሥጋው መከራን ተቀበለ፤ ሞተም፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። ወደ ላከውም ወደ አብ ወደ ሰማያት ዐረገ። በኀይልም ቀኝ ተቀመጠ።

በአብና በወልድ ዘንድ ህልው የሚኾነውን፥ ዓለምን ያዳነውንና ከአብ የሠረጸውን የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስን ሰደደልን።

እንግዲህ የእግዚአብሔር ፍጥረት ኹሉ መልካም እንደ ኾነ ግድፈትም እንደሌለበት እንናገራለን ። የሥጋ ሕይወት የምትሆን መንፈስ ግን ኹለመናዋ ንጽሕትና ቅድስት ናት።

እኛስ ጋብቻ ንጹሕ እንደ ሆነ መዋለድም ርኲሰት እንደሌለበት እንናገራለን፤ እግዚአብሔር ሕዝብ ይበዙ ዘንድ አዳምንና ሔዋንን ፈጥሮአቸዋል።

ከሥጋ ጋር የማትሞትና የማትጠፋ ነፍስ በሥጋችን ውስጥ እንዳለች እናስተውል ።

እኛ ግን ሃይማኖትን የካዱት በእኛ ዘንድ የረከሱ ናቸውና፥ መለያየትን፥ ሕገ ወጥ መሆንንም ኹሉ እንጸየፋለን።

ዳግመኛም የጻድቃንና የኃጥኣን የሙታን ትንሣኤ እንዳለ፥ ኹሉ እንደ ሥራው መጠን ፍዳውን የሚቀበልበት የፍርድ ቀን እንዳለ እናምናለን።

ዳግመኛም ክርስቶስ የአብ ሊቀ ካህናት ሆኖ የሰውን ወገን ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀ፥ በእውነት ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነው እንጂ፥ ሰው በመሆኑ ምንም ሕጸጽ እንደሌለበት እናምናለን።

እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ፤ ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደ መጣ እናውቃለንና ፤ አሕዛብ ኹሉ መምጣቱን በተስፋ የሚጠባበቁት ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ከአይሁድ፥ ከዕሤይም ሥር የተገኘ ነው።
ሥልጣኑም በትከሻው ላይ ነው።

ለእርሱም ምስጋና፥ ገናንነት፥ ክብር፥ ባርኮት፥ ውዳሴና ማሕሌት ይገባዋል። ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙም፤ አሜን።
❤ 118 👏 7 🔥 2 ❤‍🔥 1 👍 1 🥰 1
ኪ
23:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/ItgSAAtgj8M?si=4REILQahufWJG1Qd

የዛሬው Live ነው በዛውም ዩቱዩቡን subscribe share አድርጉ
❤ 39 🙏 7 👍 1
26 June 2025
ኪ
20:59
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/U5nBEZn_IfU?si=dnrA6L1hSEYUtV37

Ethnocentrism በኢትዮጵያውያን ዘንድ በጣም በትልቁ ይታያል አንድ አንድ ሰዎችማ ከዓለም ተለይታ ኢትዮጵያ ብቻ እንድትድን እስከ መፈለግ ይደርሳል። ይህ ትልቅ በሽታ ነው የቤተክርስቲያንን ኩላዊነት በአፍ ብቻ የሚመሰክሩ እንጂ በልባቸው የሌለ ብዙ ሰዎች ሞልተዋል በተለይ ደግሞ እነዚህ ሰዎች ጥላቻቸውን የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ሲያስተጋቡ ይሰማል።

ለእንደዚህ አይነት ሰዎች መሠረታቸው ቀሲስ ዘበነን የመሰሉ አስተማሪ ነን ባዮች ናቸው። ቪዲዮው ላይ እንደምትመለከቱት ብሉይ ኪዳንን መቀበልና ቅዳሴ ማርያም መኖሩ ኢትዮጵያን ከግብጽ የበላይ እንደሚያደርጋት ያስባል ይህ ግን እጅግ በጣም የወረደ አስተሳሰብ ነው መንግሥተ ሰማያት የምትገባው ቅዳሴ ማርያምን ስለቀደስክ አይደለም ብሉይ ኪዳንም ቢሆን የማዳን ምንም ኃይል የለውም የሚያድነው በመሠዊያው የሚገኘው ኢየሱስ ነው ኅብረታችንም አንዱን እንጀራ ሰማያዊን ኢየሱስን በመሠዊያው ስለምንቋደሰው ነው። ጭራሽ ግን በነገረ ማርያም ዙሪያ የፕሮቴስታንት ሀሳብ ይሻላል እስከ ማለትም ደርሷል። ይህ የሚያሳየው ለግብጽ ቤተክርስቲያን ያለውን ከፍተኛ ደረጃ ጥላቻ ነው ምክንያቱም ማርያም ኃጢአትን ሠርታለች ብለው ከሚያስተምሩ ፕሮቴስታንት እንዴት ነው እመቤታችንን ፍጹም ንጽሕት አድርገው የሚያከብሯት ግብጻውያን የሚብሱት? በዚህ ንግግራቸው አንዲትን የክርስቶስን ቤተክርስቲያን እንዲህ በመናገራቸው ብዙ ቀኖናዊ እርምጃ ሊወረድባቸው ይገባ ነበር ነገር ግን Ethnocentrism በጣም ተጠናውቶ ስለገባ ምንም አልተባሉም።

ከእንደዚህ አይነት መምህራን ነን ባዮች እየተማሩ ደግሞ ብዙ ጥላቻን የግብጽ ቤተክርስቲያን ላይ የሚያሰሙ ፣ የሚጽፉ ብዙ ምእመናን አሉ (በfacebook ላይ ብዙ ደርሰውኝ ነበር እንዲሁ ዝም ብዬ አለፍኳቸው እንጂ)። ይህ አስተሳሰብ እጅግ አጸያፊ ከመሆኑ የተነሣ ከየትኛውም ክርስቲያን ሊወገድ ይገባል ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ አትወሰንም ተወስናም አታውቅም ከጊዜና ከሕዝብ ሁሉ በላይ ያለች ኩላዊት እንጂ። ስለዚህ "ከሁሉ በላይ በሆነች በአንዲት ቅድስ ኩላዊትና ሐዋርታዊት ቤተክርስቲያን እናምናለን" ብላችሁ የምትመሰክሩለት ጸሎተ ሃይማኖት እንዳይፋረዳችሁ በማስተዋል ተጓዙ አይኖቻችሁንም ከፍ አድርጉና ከኢትዮጵያ አውጡ የናንተ ጭንቅላት በኢትዮጵያ ስለተወሰነ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ትወሰናለች ማለት አይደለም ይህ እጅግ የበዛ ጠባብነት ነው።
❤ 85 👍 12 ❤‍🔥 2 🔥 1
27 June 2025
ኪ
19:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኃጢአት ይወረሳል ሲባል ምን ማለት ነው?

በአዳም ኃጢአት ተጠይቂዎች ሆነን እንወለዳለን ማለት አይደለም (እንደ አውግስጢኖስ)፤
ያለምንም ኃጢአት ንጹሕ ሆነን (morally neutral) እንወለዳለን ማለት አይደለም (እንደ ፐላግያኖስ) ፤
ከአዳም የተነሣ የጎሰቆለ ባሕርይን (ancestral corruption) ብቻ እንወርሳለን ማለት አይደለም (እንደ ኢስተርን ኦርቶዶክስ),

ይልቅስ እንዲህ ማለት ነው:

ከእግዚአብሔር ጸጋ በተራቆተ ማንነት መወለድ በራሱ ኃጢአት ነው ፤ ኃጢአትን በግል እንደ personal act ሠርተን አይደለም ፤ የአዳምን ጥፋተኝነት ወርሰንም አይደለም (inherited guilt) ይልቅስ ነፍስ በዚህ ሁኔታ ( condition) ስትወለድ ፣ የተመሳቀለ (disordered) ፍላጎት አላት ፣ ከእግዚአብሔርም የተለየች ናት ስለዚህም የእግዚአብሔር መንግሥት የማይገባት ናት።

ማስተዋል ያለብን ነገር፡
ኃጢአት ሥራ ( act) ብቻ አይደለም ፤ ሁኔታ (condition) ጭምር እንጂ።(Original Sin)
በዚህ ኃጢአተኛ condition የተወለድነው እግዚአብሔር እንዲህ ስለፈጠረን አይደለም ፣ ከውድቀት በኋላ ጸጋ እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ስለተለየ እንጂ።

ይህ condition በራሱ ኃጢአት ነው ምክንያቱም:

የራስን ፍላጎት ብቻ ወደ ማሟላት ያማትራል (Oriented towards self)

ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የለውም

በራሱ ጽድቅንም ሆነ እውነተኛ ፍቅርን ማመንጨት አይችልም

ስለዚህ ኃጢአተኞች ሆነን የምንወለደው የአዳም ጥፋተኝነት ስለተቆጠረብን አይደለም (Imputation of guilt) ከእግዚአብሔር ጸጋ በተለየ ማንነት ስለምንወለድ እንጂ ። ይህ ማንነትም ሞት የሚገባው ነው የኃጢአት ደሞዙ ሞት ነውና።

A Catechism of the Coptic Orthodox Church፡ The Creation lesson 2 እንዲህ ይላል፡

Q. Did their[Adam and eve's] sin descend to, their posterity ?
ጥያቄ: የአዳምና የሔዋን ኃጢአት ወደ ልጆቻቸው ተላልፏልን?

A, Yes; for they were the origin of all mankind, and, as they had begotten no children except in their sinful condition ,their sin descended to all their seed, and the whole human race thus became in bondage to death (Rom. v. 12).
መልስ፡ አዎ እነርሱ የሰው ልጆች ሁሉ ምንጮች በመሆናቸው ልጆችንም ሲወልዱ በእነርሱ ኃጢአተኛ ሁኔታ (Sinful Condition) ወልደዋል ስለዚህም ኃጢአታቸው በዘሮቻቸው ሁሉ ተላልፏል ስለዚህም የሰው ልጅ ለሞት የተገዛ ሆነ። (ሮሜ 5፡12)

The Shorter Catechism of Syriac Orthodox Church Chapter 12 እንዲህ ይላል፡

Q.- How many kinds of sins are there?
ጥያቄ፡ ስንት አይነት ኃጢአት አለ?
A.- Sin is of two kinds: Original sin and present sin.
መልስ፡ ሁለት አይነት፡ ጥንተ አብሶ እና አሁናዊ ኃጢአት
Q.- What is original sin?
ጥያቄ፡ ጥንተ አብሶ ምንድነው?
A.- This is the sin which embraces all mankind as an inheritance from the disobedience of our father, Adam.
መልስ፡ በአባታችን አዳም አለመታዘዝ ምክንያት የሰውን ልጅ ሁሉ እንደ ውርስ የያዘ ኃጢአት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጥንታዊ አቋምም ይህ ነው አሁን ላይ ከኢስተርን ኦርቶዶክስ የሚማሩ መምህራን የኢስተርንን አቋም እያመጡ ነው እንጂ።

@KidanZeIyesus
❤ 56 👍 8 ❤‍🔥 6 👎 2 🤔 2 🔥 1 😱 1
30 June 2025
ኪ
07:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
መድኃኔዓለም ቅዱስ እንጂ ከቅዱሳን አንዱ አይደለም

ይህን ንግግር ከአንድ ወዳጄ ሰምቼ የወደድኩት ነው። በልጅነታችን መድኃኔዓለም ሲዘከር ከቅዱሳን ዝክሮች አንዱ አድርገን እናስብ ነበር ከጊዮርጊስ ፣ ሚካኤል ዝክሮች እንደ አንዱ። ይህ ሀሳብ ትዝ ያለኝ ከሆኑ ጓደኞች ጋር የምንወደው ቅዱስ (Patron saint) ስናወራ አንድ ሰው መድኃኔዓለም ሲለኝ ነው። መድኃኔዓለምን ከቅዱሳኑ እንደ አንዱ የመቁጠር ልማድ ካለማወቅ በብዙዎች ዘንድ አለ።

አንድ ነገር ግን እናስታውስ ኢየሱስ ቅዱስ ቢሆንም ከቅዱሳኑ አንዱ አይደለም ለቅዱሳኑ የምንሰጠው ክብርና ለእርሱ የምንሰጠውም ይለያል ፤ እርሱን ከቅዱሳኑ ጨምረን የምንዘክረው አይደለም እርሱ ራሱ ቅዱሳኑ የሚዘከሩበት ምክንያት ነው እንጂ። ቅዱሳንን ያወቅናቸው በክርስቶስ ነው እንጂ በቅዱሳን ክርስቶስን አላወቅነውም ፤ ማለትም ቅዱሳን የሚከበሩበት ምክንያት የክርስቶስ ቤተሰቦች ስለሆኑ እኛ ደግሞ የክርስቶስ በመሆናችን በክርስቶስ በኩል ያገኘናቸው ቤተሰቦች በመሆናቸው ነው። ቅዱሳን የታወቁት የክርስቶስ ታሪክ ውስጥ በመግባታቸው ነው እንጂ ዓለም ከተፈጠረ ኖረው ያለፉ ብዙ ሰዎች አሉ።

እንዲህ በምሳሌ እንረዳው እኛ ሙሽሪት ነን ክርስቶስ ሙሽራችን ነው ፤ አንዲት ሙሽሪት ወደ ሙሽራውን በማወቋ ፣ በመውደዷ ከሙሽራው ቤተሰቦች ጋር ትተዋወቃለች ሙሽራውም ሙሽሪት ቤተሰቡን ስትወድለት ደስ ይለዋል ማይረሳው ነገር ግን እነዚህን ቤተሰቦች የተዋወቀቻቸው ማንን ስለወደደችው ነው? ሙሽራውን! ለመሽራውና ለቤተሰቦቹም ተመሳሳይ የፍቅር አይነት የላትም፤ ሙሽራውም ለእርሷ ከቤተሰቡ ውስጥ አንዱ ሳይሆን ለእርሷ ፍቅሯ ባለቤቷ ነው!

ስለዚህ ይህንን ነገር እናስተውል ሁል ጊዜ ሙሽራዊ ፍቅራችን ለክርስቶስ ብቻ ነው ቅዱሳን ደግሞ የክርስቶስ በመሆናቸው ቤተሰባዊ ፍቅር ይገባቸዋል። አንድ ሰው ቅዱሳንን ማክበሩ ጥሩ ነው ነገር ግን ለእነርሱ የሚሰጠው ክበር የሙሽራውን ቦታ መውሰድ ከጀመረ ይህ በመሽራው ላይ የሚደረግ ዝሙት ነው

"But hear a far stronger, a far more expressive testimony. See ye what it is we are treating of; see ye that to love any person in place of Christ is adultery.

ነገር ግን ከዚህ እጅግ የጠነከረና የበለጠ ገላጭ የሆነ ምስክርነትን ስሙ። የምንናገረው ስለ ምን እንደሆነም እዩ፤ በክርስቶስ ቦታ ማንኛውንም ሰው መውደድ ዝሙት መሆኑን ተገንዘቡ።" (St. Augustine Tractates on Gospel of John tractate 13:10)

ቅዱሳንን የምንዘክረው የምናከብረው ከመድኃኔዓለም ዝክር ጋር እንደ አማራጭ እንዲሆን አይደለም ይልቅስ ከቅዱሳኑ ጋር ወደ ክርስቶስ እንድንቀርብ እንጂ። ወደ ቅዱሳኑ የምንሔደው (የምንጸልየው) ወደ ክርስቶስ ከመጸለይ እንደ አማራጭ እንዲሆኑ አይደለም ከእነርሱ ጋር በቅዱሳን አንድነት (Communion of the Saints) ወደ ክርስቶስ እንድንቀርብ እንጂ።

Therefore ask yourself Is your love for the saints an overflow of your love for Christ? Or has Christ become just another object of affection?

@KidanZeIyesus
❤ 102 👍 6 ❤‍🔥 5 🔥 5 🥰 1
ኪ
12:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰብሰብ ብላችሁ ተገኙ brothers and sisters

https://vm.tiktok.com/ZMSCHbvv3/
🥰 29 ❤ 11 👍 4 🔥 2 🤝 2 ❤‍🔥 1
ኪ
19:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
01:06, 14.5 MB
The One , Holy , Catholic and Apostolic Church 🔥
🔥 50 ❤ 25
1 July 2025
ኪ
21:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/zRMQ9S7gvk8?si=kd8icAe4qUY7O3n6

የትናንቱ Record ነው።
❤ 35
5 July 2025
ኪ
11:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
መዝሙር 82

የአሳፍ መዝሙር።
1 እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።
2 እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼ ለኃጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ?
3 ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ፤ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ፤
4 ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤ ከኃጢአተኞችም እጅ አስጥሉአቸው።
5 አያውቁም፥ አያስተውሉም፤ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6 እኔ ግን። አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤
7 ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ አልሁ።
8 አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍርድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።

ይህን መዝሙር ተመልከቱ እግዚአብሔር (Elohim) በአማልክት (Elohim) ማኅበር ቆሞ በአማልክት ላይ ይፈርዳል። ሲፈርድባቸውም እናንተ የልዑል (Elyon) ልጆች ናችሁ አማልክት ናችሁ ነገር ግን ጽድቅን አጓደላችሁ እያለ ነው በዚህም ምክንያት እንደ ሰው ትሞታላችሁ ብሎ ፈረደባቸው። መዝሙረኛውም ይህን ፍርድ ይዞ እግዚአብሔርን ተነሥ በምድር ላይ ፍረድ አሕዛብን ትወርሳለህ ብሎ ይዘምርለታል።

እዚህ ላይ ምን ጥያቄ ያስነሳል መሰላችሁ በጥንታዊያን ከነአናውያን እምነት የአማልክት ማኅበር (The Divine Council) የሚባል እምነት አለ እነዚህ አማልክትም እያንዳንዱን የምድር ሕዝብ ላይ እንዲፈርዱ ተካፍለዋል ከሁሉምን በላይ ታላቁ አምላክ ደግሞ El-Elyon (በብዛት ልዑል እግዚአብሔር ተብሎ ይተረጎማል) ነው። ስለዚህ ይህም መዝሙር እንደሚነግረን ከሆነ El-Elyon እጣው የእሥራኤል ሕዝብ ነበር ሌሎቹ አማልክት ደግሞ ሌሎችን አሕዛብ ላር ይፈርዳሉ ነገር ግን ፍርድን ባጓደሉ ጊዜ El-Elyon ጣላቸው ስለዚህም እርሱም ብቻውን በአሕዛብ ሁሉ ላይ አምላክ ሆነ ስለዚህም መዝሙረኛውም "አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍርድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።" ብሎ ዘመረለት።

ይህንን የሚያጠኑ ሊቃውንትም ይህ መዝሙር እሥራኤል ከብዝሃ አማልክት ወደ አንድ አምላክ አምላኪነት የተሻገሩበት ጊዜን ያሳያል ይላሉ። እናንተ ለዚህ ምን ትመልሳላችሁ?
❤ 26 👍 5 ✍ 3
7 July 2025
ኪ
11:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ የጽድቅ ትምህርታችንን እንቀጥላለን

በተለይ ሮሜና ገላትያ መልእክታት ላይ በማተኮር "የሕግ ሥራ" የተባሉት ምንድናቸው? ጽድቅስ ያለ ሕግ ሥራ በእምነት ሲባል ምን ማለት ነው? የሚሉትን እንቃኛለን።

2 ሰአት እንዳትቀሩ 😊
❤ 66
ኪ
23:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
"The reason Christians are obligated to obey the Ten Commandments is not that they are commanded by the Law of Moses. Christians are not obligated to obey the Law of Moses. In fact, the only people who were ever bound to obey the Law of Moses were the Jewish people prior to the time of Christ

ክርስቲያኖች አሠርቱ ትእዛዛትን እንዲጠብቁ የሚገደዱት የሙሴ ሕግ ስላዘዘ አይደለም። ክርስቲያኖች የሙሴን ሕግ የመጠበቅ ግዴታ የለባቸውም። ይልቅስ ለሙሴ ሕግ መታዘዝ የሚጠበቅባቸው የነበሩት ከክርስቶስ በፊት የነበሩ አይሁዶች ብቻ ናቸው። " Drama of Salvation by Jimmy Akin

"እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ፤ ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደ መጣ እናውቃለንና" አመክንዮ ዘሐዋርያት

ምሽታችንን የሚጠቀልሉ ንግግሮች ናቸው።
❤ 51 👍 4 👎 1 🥰 1 🤯 1
8 July 2025
ኪ
09:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/Y7JqhaaQPAQ?si=ngH8a9aCqF_oeX48

የትናንቱ Record ትንሽ ረዘም ብሏል ይህኛው ቀስ ብላችሁ ስሙት
❤ 25 👍 4 🥰 3
Price per direct message changed to 0 Telegram Stars.
ኪ
13:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
Direct Message ተከፍቶላችኋል በዚህ ላኩ በውስጥ አትላኩልኝ please 😁
😁 21 ❤ 1
9 July 2025
ኪ
08:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታቴቭ የእምነት መግለጫ

"በማጠቃለያ፣ በቀላል ቃላት እንደሚከተለው እንመሰክራለን፦

ባልተፈጠረ፣ ባልተወለደና መጀመሪያ በሌለው፣ የወልድ ወላዲ እና የመንፈስ ቅዱስ አሥራፂ በሆነው በእግዚአብሔር አብ በሙሉ ልባችን እናምናለን፣ እንመሰክራለንም።

ከዘመናት ሁሉ በፊት ከአብ በተወለደውና በወጣው የእግዚአብሔር ቃል እናምናለን፤ ከአብ የሚከተል ወይም የሚያንስ አይደለም፤ ነገር ግን አብ፣ አብ እንደሆነ ሁሉ ወልድም ከእርሱ ጋር ወልድ ነው።

ባልተፈጠረ፣ ጊዜ በማይወስነው፣ ከአብ ባልተወለደ ነገር ግን በሠረጸ፣ ከአብ ጋር በመለኮቱ አንድ በሆነና ከወልድ ጋር ክብርን በሚጋራው በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን።

በአንዲት ቅድስት ሥላሴ፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ መለኮት እናምናለን፤ ሦስት አማልክት ሳይሆኑ አንድ አምላክ፣ አንድ መለኮት፣ አንድ ፈቃድ፣ አንድ ንግሥና፣ አንድ ኃይል፤ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ የፈጠረ።

በቅድስት ቤተክርስቲያን እና በቅዱሳን ኅብረት  በሚገኘው የኃጢአት ሥርየት እናምናለን።

ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነው፣ ከዘመናት በፊት ከአብ የተወለደው እግዚአብሔር ቃል፣ በጊዜው ወደ አምላክ እናት ወደ ድንግል ማርያም እንደወረደ፣ ከደሟም ነሥቶ ከመለኮቱ ጋር እንዳዋሐደው፣ በንጽሕት ድንግል ማኅፀን ውስጥ ለዘጠኝ ወራት በትዕግስት እንደጠበቀ እናምናለን፤ ፍጹሙ አምላክም በመንፈስ፣ በነፍስና በሥጋ ፍጹም ሰው ሆነ፤ አንድ አካል፣ አንድ ገጽ እና አንድ ውሕድ ባሕርይ፤ ያለመለወጥና ያለመቀየር ሰው የሆነ አምላክ፤ ያለዘር ጽንሰትና ንጹሕ ልደት፤ ለመለኮቱ ጅማሬ እንደሌለው ሁሉ ለሰውነቱም መጨረሻ የለውም። "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትናም፣ ዛሬም፣ ለዘለዓለሙም ያው ነው።" (ዕብራውያን 13:8)።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እንደተመላለሰ፣ ከሠላሳ ዓመታት በኋላም ወደ ጥምቀት እንደመጣ እናምናለን፤ አብም "የምወደው ልጄ ይህ ነው" (ማቴዎስ 17:5) ሲል መስክሮለታል፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በእርሱ ላይ ወርዷል፤ በሰይጣንም ተፈትኖ ድል ነሥቶታል።

ለሰው ልጆች መዳንን አውጇል፣ ደክሟል፣ በሥጋ ተራበና ተጠማ። ከዚያም በፈቃዱ ለሕማም መጣ፤ ተሰቀለ፣ በመለኮቱ ሕያው ሆኖ ሳለ በሥጋ ሞተ። ሥጋውም ከመለኮቱ ሳይለይ በመቃብር ተቀበረ፣ ባልተከፋፈለ መለኮቱም ወደ ሲኦል ወረደ። ለነፍሳት ሰበከ፣ ሲኦልን አፈረሰ፣ ነፍሳትንም ነጻ አወጣ። ከተቀበረ ከሦስት ቀናት በኋላም ከሙታን ተነሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ ታየ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያው ሥጋ ወደ ሰማይ እንዳረገ በአብ ቀኝም እንደተቀመጠ እናምናለን። በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ይመጣል፤ ለጻድቃን የዘላለም ሕይወትን፣ ለኃጢአተኞች ደግሞ የዘላለም ስቃይን እንደየሥራቸው ይመልሳል።

ይህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሁልጊዜ በአእምሮውና በአንደበቱ ሊጠብቀው የሚገባው የቀና (ኦርቶዶክሳዊ) እምነት ምስክርነት ነው።"


ምንጭ፦ጎርጎርዮስ ዘታቴቭ፣ "ሆሚሊስ" (የስብከት መድብል)፣ ገጽ 116-117። (Gregory of Tatev: Homilies, 116-117)

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታቴቭ በ14 እና 15ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ አርመንያዊ ቅዱስ ነው። በዛን ወቅት የአርመን ቤተክርስቲያን ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተላኩ ዶሚኒካን ሚሲዮናውያን ስትወረር የቅዱስ ቄርሎስን ሚያፊሳይት እምነት በመጠበቅ ከካቶሊክ ጋር የነበረውን ውሕደት በፍጹም ተቃውሞ ኦርቶዶክሳዊ እምነትን ጠብቋል። ለእስልምናም ብዙ መልስን መልሷል ታላቅ የነገረ መለኮትና የፍልስፍና እውቀትም ባለቤት ነው በረከቱ ይደርብን።

@KidanZeIyesus
❤ 75 🥰 15 🔥 7 🙏 1
11 July 2025
ኪ
12:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
የጽድቅ ትምህርትን ሰኞ ስለምንጨርስ ጥያቄ ያላችሁ እዚሁ አስቀምጡና እንሔድበታለን። እንዲሁም live መጠየቅ ምትፈልጉ ሰብሰብ ብላችሁ ተገኙ
❤ 50 🔥 1
ኪ
23:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ

ዛሬ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለዓለም ለማዳረስ ሕይወታቸውን የሰጡ ሁለቱ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች እና የዓለም ብርሃናት ጴጥሮስና ጳውሎስን እናከብራለን።

የዮና ልጅ ስምዖን ትሑቱና ትምህርት እንኳን ያልተማረው የገሊላዋ ቤተሳይዳ አሳ አጥማጅ ፣ ለእምነት የፈጠነ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት ግንበኞች ቢንቁትም የማእዘን ራስ የኾነውን ዓለት ኢየሱስን  በመመስከር ቤተክርስቲያን የምስመሠረትበት ዓለት (በግሪክ ጴጥሮስ) የኾነ ፣  በዚህም የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ የተቀበለ። ሕይወቱን በሙሉ ለክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያን በመስጠት የክርስቶስን ወንጌል ያለፍርሃት በሰው ሁሉ ፊት ሰበከ ከይሁዳ ተነስቶ ፣ ከዚያም በአንጾኪያ አከባቢዎች ሁሉ ከሰበከ በኋላ ሮም ደረሰና በኔሮን ቄሳር እጅ ይሰቀል ዘንድ ተፈረደበት ። ሮማውያን ስቅላትን እንደ እርግማን እና ውርደት ቢያዩትም ተወዳጁ ጴጥሮስ ግን በመስቀሉ ላይ የታየው የነፍሱ ጌታ ኢየሱስ ነው ፣ከዚህም የተነሳ እኔስ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም በማለት ተዘቅዝቆ እንዲሰቅሉት ጠይቋል ፣ መጀመርያ ከክርስቶስ ጋር መሰቀልን ፈርቶ "ሰውዬውን አላውቀውም" ብሎ ቢክደውም አሁን ግን ልቡ ጸንቶ ለተሰቀለለት ኢየሱስ እርሱም ተሰቅሏል።

ቀናተኛው ሳውል (በሮማይስጥ ጳውሎስ) ከፈሪሳዊው ገማልያል ዘንድ የተማረ ታላቅ የመጻሕፍት ምሁር ለአይሁድ እምነት በጣም የሚቀና ፈሪሳዊና የቤተክርስቲያን ቀናተኛ አሳዳጅ ነበር። ሆኖም፣ ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ላይ በነበረው የኢየሱስ መለኮታዊ መገለጥ፣ ጥልቅ የሆነ ለውጥን አገኘ የተመረጠ እቃም ተባለ። በሰማያዊ ብርሃን ታውሮ የኢየሱስን ድምፅ በመስማት ሕይወቱን ለአሕዛብ ወንጌልን በመስበክ ራሱን የሰጠ የክርስቶስ ተከታይ ሆነ። እስራትና ድብደባን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችንና መከራዎችን ተቋቁሞ ዛሬም እኛን የሚያበረታታን የእምነት ውርስ  እነርሱም ውድ የሆኑ መልእክቶቹን ትቶልናል። የመዳንን መልእክት ያለ ፍርሃት ለሕዝብ ሁሉ ካደረሰ በኋላ  በመጨረሻም ሮም ሲደርስ በኔሮን ቄሳር ሞት ተፈረደበት እርሱ በዘር አይሁዳዊ ቢሆንም በሮሟ ጠርሴስ በመወለዱ የሮም ዜግነት ስላለው ከአሰቃቂው ስቅላት ይልቅ በፈጣኑ አንገትን በሰይፍ መቀላት ይሞት ዘንድ ተወሰነበት ስለዚህም የቤተክርስቲያን አሳዳጅ በመሆን የጀመረውን ሕይወት ለቤተክርስቲያን ተሳዳጅ በመሆን መራና በመጨረሻም እራሱን ለቤተክርቲያን በመሰዋት ፈጸመ። 

የቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም የተሞላ የተባረከ በዓል ይሁንላችሁ።

@KidanZeIyesus
❤ 95 ❤‍🔥 17 🙏 8 🥰 6
12 July 2025
ኪ
09:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
አንዳንድ "ተአምራት" ግን 🤔

በኢስተርን ኦርቶዶክስ ተፈጽመዋል ከሚባሉ ተአምራት የሚያስቀኝ በኬልቄዶን ጉባኤ ተፈጸ የሚባለው የቅድስት አፎምያ ተአምር ነው።

እንደሚታወቀው የኬልቄዶን ጉባኤ የተካሔደው የቅድስት አፎምያ ሥጋ በሚገኝበት በራሷ ስም በተሰየመ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው። አንድ የ11ኛ ክፍለ ዘመን የቢዛንታይን ስንክሳር እንደሚዘግበው ደግሞ "በኬልቄዶን የተሰበሰቡ አባቶች በዳዮፊዛይት እና በሞኖፊዛይት (ቅዱስ ዲዮስቆሮስን ሞኖፊዛይት መናፍቅ ማለታቸው ነው) ክርክሮች መካከል መግባባት ሲያቅታቸው ሁለቱም የእምነት መግለጫን አዘጋጁና ከአምላክ ተአምር ለመጠየቅ የቅድስት አፎምያ መቃብር ውስጥ አደረጉት ጸሎትም ካደረጉ በኋላ የኬልቄዶኑ ዳዮፊዛይት እምነት መግለጫ በቅድስት አፎምያ እጅ ላይ ሲገኝ "የሞኖፊዛይት ምንፍቅናው የእምነት መግለጫ" ደግሞ በእግሯ በታች ተጥሎ ተገኝቷል ስለዚህም ይህ ተአምር የኬልቄዶኑ እምነት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳገኘ መለኮታዊ ማረጋገጫ ነው" 😁
ባይገርማችሁ ይህ ተአምር መታሰቢያ ቀኑ ትናንትና ነበር አዪ ምነው እንኳን አደረሳችሁ ሳንባባል አመለጠን 😁

ብቻ ግን ይህ ተአምር ተብዬ በየትኛውም የኬልቄዶን ቃለ ጉባኤ (Acts of Chalcedon) ሰነድ ላይ አይገኝም ይልቅስ የ11ኛው ክፍለ ዘመን ፈጠራ ነው። ደሞም እኮ ቃለ ጉባኤውን ራሱ ይጋጫል በኬልቄዶን ጉባኤ ላይ "የሞኖፊዛይት የእምነት መግለጫ" የሚል ነገር በጭራሽ የለም ፣ ዲዮስቆሮስም ቢሆን በምንፍቅና አልተወገዘም እንዲሁም የተገኘው ራሱ የመጀመሪያው session ላይ ብቻ ነው። ባይገርማችሁ ደግሞ ይህ ታሪክ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራሱ አይታወቅም በቢዛንታይን ምንጮች ብቻ እንጂ ለዚያውም ከታሪኩ ከተፈጸመ 600 ዓመታት በኋላ።

በመጨረሻም ደግሞላችሁ ተአምር የእምነት ማረጋገጫ አይደለም አባቶች በጉባኤያት ውሳኔ ላይ በተአምር ላይ ተማምነው አያውቁም ነገር ግን ይኸው እስከዛሬዋ ድረስ ይህን ክስተት እንደ ዓመታዊ በዓል እያከበሩ ምስኪኑን ምእመን ያታልሉበታል።
😁 43 🤣 14 ❤ 12 😢 5 👎 3 🙉 3 🤷‍♂ 2
ኪ
19:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
የእሑድ ቅዳሴ ግዴታ መሆኑን ያውቃሉ?

አሁን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየቀለለብን ከመጡት ነገሮች ውስጥ ቅዳሴ እና ቅዱስ ቁርባን ነው። ሰንበትን አክብር የሚለው የኦሪት ሕግ ፍፃሜውን ያገኘው በዕለተ እሑድ ቅዳሴ ነው። አንድ ክርስቲያን ዕለተ እሑድን የማስቀደስ ክርስቲያናዊ ግዴታ አለበት ፤ ፍትሐ ነገሥት ቁ 718 እንዲህ ይላል "ዘወትር በቤተክርስቲያን ተሰብሰቡ። ይልቁንም በዕለተ እሑድና በዕለተ ትንሣኤ፣ ይኸውም ዕለተ እሑድ ነው። እነሆ በበዓላቸው ቀን ከመሰብሰብ ወደ ኋላ እንደማይሉ አሕዛብን እናያቸዋለን። በበዓሉ ቀን ሁሉም ይሰበሰባሉ እንጂ አንደዚሁም በከንቱ አይሁድ የሚባሉ የተሰበሰቡ እይሁድ ከስድስት ቀን በኋላ ሥራቸውን ይተዋሉ። በሰባተኛውም ቀን በምኵራባቸው ይሰበስባሉ በተሰበሰቡም 'ጊዜ የታዘዘላቸውን 'ሥራቸውን ይተዋሉ • እነዚህ ጥቅም ለሌለበት ለማይረባ መሰብሰባቸው የሚተጉ ከሆኑ ግን ከቤተክርስተያን ወደኋላ የምትል እንተ ለእግዚአብሔር የምትመልስለት ምንድር ነው? "

የመጨረሻዋን ጥያቄ ለራሳችን እንጠይቅ ለእግዚአብሔር ከሠርጉ ስለቀረን የምንመልስለት ምንድር ነው? ከጌታ ቀን በአምልኮ ከመገኘት የሚያግድ ነገር ምንድር ነው? ይህን ያላደረገ ንስሐ እስካልገባ ድረስ ለሞት የሚያደርስ ኃጢአት እንደሠራ አታስተውሉምን?

በጥንቷ ቤተክርስቲያን የእሑድን ቅዳሴ 3 ጊዜ ተከታታይ ቀርቶ ምክንያቱን ካላስረዳ ከጉባኤው ይወገዝ ነበር። የኤልቪራ ጉባኤ ቀኖና 21 እንዲህ ይላል " ቤተክርስቲያን 3 እሑዶችን የቀረ ቅጣቱን ለሕዝብ ግልጥ እስኪሆን ድረስ ከጉባኤው ይለይ"

እኛ ግን አሁን ይህን ረስተን እሑድን መንፈሳዊ ጉዞ ሔድን እያልን ከቅዳሴው እንቀራለን ፤ አንተ ሰነፍ የክርስቶስ ሥጋና ደም ከየትኛውም ገዳም በላይ የከበረ እንደሆነ አታውቅምን? ሌሎቻችን ደሞ ማኅሌት አደርን ብለን ቅዳሴ ሲደርስ ጥለን እንወጣለን ፤ ከየትኛውም ማኅሌት በላይ በቅዳሴ የምናገኘው ጸጋ የሕይወት እስትንፋስ መሆኑን አልተረዳንምን?

ሌሎቻችን ደሞ ዓመቱን ሙሉ እኮ እሑድ ቅዳሴ ሔጃለሁ ይህቺን እሑድ ጉዞ ብሔድ ወይስ እንዲህ ባደርግ ምን ችግር አለሁ እንላለን ይህ ምን ማለት መሰላችሁ ዓመቱን ሙሉ ኃጢአት አልሠራውም አሁን ብቻ ኃጢአት ብሠራ ምን ችግር አለሁ? ማለት ነው። ሌሎቻችን ደሞ አርብን አስቀድሼ የእሑድ ግዴታዬን እወጣለሁ እንላለን ይህም የማይሆን ነው የእሑድ አምልኮ የሚቀየር አይደለም ሌላ ቀን የምናደርገው ተጨማሪ እንጂ።

ክርስቲያኖች የሚጮኸው የመሢሑ ደም እንዳይፋረደን በክርስቶስ ሥጋና ደም አንቀልድ የጌታ ቀን ሰው ይበለን!

@KidanZeIyesus
❤ 98 🔥 9 👏 3 ❤‍🔥 1 👍 1 🙏 1 😭 1
ኪ
19:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጴጥሮስ የሚባል ጀለሴ: እሑድ ዕለት ምርጥ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ጻድቃኔ ማርያም ተዘጋጅቷል እንሒድ

Me: Matthew 16 አማ - ማቴዎስ
23: እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል፡” አለው። 😁
😁 75 🤣 27 🤔 8 ❤ 2 🥴 1 😭 1
13 July 2025
ኪ
11:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዛሬው ቅዳሴ ላይ የተነበበው ጸሎተ ፈትቶ

"ኦ ወልድ ዋሕድ፣ እግዚአብሔር የወደድከን ቃል ሆይ፣ ከፍቅሩ የተነሣ ከዘለዓለም ሞት ሊበዠን ወደደ።

በመቤዠቱ መንገድ ላይም ሞት ስለነበር ከፍቅሩ የተነሣ በዚሁ መንገድ ሊያልፍበት ወደደ። ስለዚህም የኃጢአታችንን ቅጣት ይሸከም ዘንድ መስቀል ላይ ወጣ።

የበደልነው እኛ ነን፤ መከራን የተቀበለ እርሱ ነው።

በኃጢአት ምክንያት ለመለኮታዊ ፍትሕ ባለ ዕዳ የኾነው እኛ ነን፤ ስለእኛ ዕዳውን የከፈለው ግን እርሱ ነው።

ስለ እኛ ከደስታ ይልቅ መከራን፣ ከዕረፍት ይልቅ ድካምን፣ከክብር ይልቅ መናቅን፣ ኪሩቤል ከሚሸከሙት ዙፋንም ይልቅ መስቀልን መረጠ።

ከኃጢአት እስራት ነጻ ያወጣን ዘንድ በገመድ ለመታሰር እራሱን አሳልፎ ሰጠ። እኛን ከፍ ያደርገን ዘንድ እርሱ ዝቅ አለ። ያጠግበን ዘንድ እርሱ ተራበ፤ ጥማችንንም ይቆርጥ ዘንድ ተጠማ።

የእርሱን የጽድቅ ልብስ ያለብሰንም ዘንድ እርቃኑን መስቀል ላይ ዋለ። ወደ እርሱ ገብተን የጸጋው ዙፋን ላይም እንቀመጥ ዘንድ ጎኑን በጦር ይወጋ ዘንድ ከፈተ።

በእውነት ሞተ፤ በመቃብርም ተቀበረ፤ እንዲሁም ከኃጢአት ሞት አስነሥቶ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጠን ዘንድ ተነሣ።

ኦ አምላኬ ራስህን የወጉት እሾኾች የእኔ ኃጢአቶች ናቸው፤ በዚህ ዓለም ከንቱ ደስታ ተደስቼ ልብህን ያሳዘንኩት እኔ ነኝ።

ኦ አምላኬ ፣ መድኃኒቴ ይህ የምትሔድበት ወደ ሞት የሚያደርሰው መንገድ ምንድነው?

ይህ በትከሻህ የተሸከምከው ምንድነው? ይህ ስለእኔ የተሸከምከው የውርደት መስቀል ነው።

ኦ ቤዛዬ ሆይ ይህ ምንድነው? ለእዚህ ፈቃደኛ እንድትኾን ያደረገህ ምንድነው?

ታላቁ ይጠላልን? ክቡሩ መከራን ይቀበላልን? ልዑሉ ይዋረዳልን? ኦ የፍቅርህ ታላቅነት።

አዎ ስለ እኔ ይህን ኹሉ መከራ እንትታገስ ያደረህ የፍቅርህ ታላቅነት ነው።

ኦ አምላኬ አመሰግንሃለሁ፤ መላእክቶችህ ከፍጥረታትህ ኹሉ ጋር ስለእኔ ምስጋናን ያቀርቡልሃል ፤ እኔ ለፍቅርህ የሚመጥን ምስጋናን ማቅረብ አይቻለኝምና! ከዚህ የሚበልጥ ፍቅርን አይተን እናውቃለን?

ኦ ነፍሴ ሆይ በሩህሩሁ ቤዛዬ ላይ ይህን ኹሉ መከራ ስላደረሰው ኃጢአትሽ እዘኚ ። ቁስሎቹን በፊትሽ ሳዪ የጠላት ቁጣ ሲነሳብሽም በእርሱ ተስፋ አድርጊ።

ኦ አዳኜ ሆይ መከራህን ሀብቴ ፣ የእሾህ አክሊልህን ክብሬ፣ ኃዘንህን ደስታዬ፣ ምሬትህን ማጣፈጫዬ፣ ደምህን ሕይወቴ ፣ ፍቅርህንም ኩራቴና ማመስገኛዬ አደርግ ዘንድ እርዳኝ።

ኦ ስለ ኃጢታችን የቆስልህ ፣ በቁስልህም የተፈወስን ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማሕየዊ በኾነው መለኮታዊ ፍቅህ አቁስለኝ። ኦ ትቤዠኝና ሕይወትን ትሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ሞትን የተቀበልከው ሆይ በመስቀልህ ደም ከኃጢአቴ አንጻኝ፣ በፍቅርህም አጽናናኝ።

ኦ እውነተኛ የወይን ግንድ የእኔ ውድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንደ ደረቀ ተክል አካል ካየኸኝ በጸጋህ ዘይት አለስልሰኝ ሕያው እንደኾነ ቅርንጫፍም በአንተ አጽናኝ። " (Coptic Fraction to the Only Begotten Son )

ኦ ወልድ ዋሕድ መድኃኔዓለም ሆይ ሥራህ ድንቅ ነው ❤️
❤ 85 ❤‍🔥 4 🙏 3 👍 1
ኪ
13:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
ደሞ 4K ገብተናል ምእመናን ግፉ ከዚህ በላይ ገና እንበዛለን ጌታ ሕዝብህን አበዛለሁ ብሎኛል 🙌
😁 81 ❤ 28 🤣 24 🥰 7 💯 2
14 July 2025
ኪ
11:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነአምን በአሐዱ እግዚአብሔር ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ

ከዓለም በፊት በነበረው በአንዱ እግዚአብሔር እናምናለን። እርሱ ዓለማትን ኹሉ አስገኝቷል እርሱን ግን ያስገኘው የሌለ ብቻውን ኹሌ አለ የሚባል አምላክ ነው።

ወነአምን በካልዑ እግዚአብሔር ዘበምልክናሁ ለአብ ይመስሎ

በአምላክነቱ አብን በሚመስለው በኹለተኛው እግዚአብሔርም እናምናለን። እርሱ ከዓለም ኹሉ በፊት ከአብ ያለ ተከፍሎ ባሕርይ ተወለዶ በአካል ብቻ የተለየ ፍጹም አባቱን የሚመስል ልጅ ነው።

ወነአምን በሣልሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘይመልዕ ኩሎ

ኹሉን በሚመላ መንፈስ ቅዱስ በሦስተኛው እግዚአብሔርም እናምናለን። እርሱ እንደ ልጁ ከአብ ወጥቶ ኹሉን የሚመላ በፍጥረታት ኹሉ የሚያድር በባሕርይ ከአባት እና ከልጅ ጋር አንድ መለኮት ነው።

 ሥሉስ ቅዱስ ዋሕድነት እንበለ ተከፍሎ ፤ ሥሉስነት እንበለ ተሌልዮ ❤️
❤ 93 ❤‍🔥 7 👍 3 👎 1 🙏 1
ኪ
16:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ እስካሁን ሳልነግራችሁ የያዕቆብን መልእክት እና እንዲሁም ከእናንተ ጥያቄዎች እንቀበላለን። በተለይ የያዕቆብ መልእክት ላይ ከብዙ ፕሮቴስታንቶች ዘንድ የሚቀርበው አተረጓገም ለምን አይሠራም? የሚለውን እንዳሳለን ማታ 2 ሰአት ይገኙ
👍 42 ❤ 22
15 July 2025
ኪ
12:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/4qmKWECwoB4?si=FweSolBU7Kms5kp8

የትናንቱ live ይህኛው በጣም የረዘመው ግማሹ ከፕሮቴስታንት ወንድሞች ጋር ውይይት ስለነበረ ነው። ሌላው ደሞ network ሲያስቸግር ነበር ለዛ እንግዲህ ታግሳችሁ ስሙ 😁
❤ 39
17 July 2025
ኪ
18:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
Dispensationalism in Ethiopia?

ኢትዮጵያውያን ዘንድ ለሀገረ እስራኤል ካለን ትልቅ አክብሮት የተነሣ አንድ አንዴ ወደ dispensationalism ሃሳብ የሔደብን ይመስለኛል። Dispensationalism ታሪክን "Dispensations" ወደ ተባሉ ጊዜያት በመክፈል እግዚአብሔር በእነዚህ ጊዜያት ለሕዝቡ የተለያየ እቅድ እንዳለው ያስተምራል። ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ከእስራኤል ሕዝብ ጋር አደርገ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቤተክርስቲያን የተባሉትን አማኞች የቃልኪዳኑ ሕዝብ አድርጎ ይዟል ነገር ግን እስራኤላውያን አሁንም ድረስ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነው ቀጥለዋል እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብም ፣ ለቤተክርስቲያንም የተለያየ እቅድ አለው ይላል።

ነገር ግን ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓገም ቤተክርስቲያን ትቃወመዋለች እግዚአብሔር በተለያየ ዘመናት ውስጥ የተለያዩ ቃልኪዳናትም ሆነ የተለያዩ የቃልኪዳኑ ሕዝብ አልነበረውም ይልቅስ የቃልኪዳኑ ሕዝብ አንድ ነው ፣ ቃልኪዳኑም አንድ ነው ይህም ቃል ኪዳን በእምነት እንጂ በዘር አይደለም።

የመጀመሪያውን የቃልኪዳን ሰው አብርሃምን አስታውሱ " መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።" (ሮሜ 4፡3) የመጀምሪያው ቃልኪዳን የጸናው በእምነት ነበር ነገር ግን በአብርሃም እምነት የመጣው ቃል ኪዳን ለአብርሃም ብቻ አልነበርም ይልቅስ በዘሩ አህዛብ ሁሉ ይባረኩ ዘንድ ነው እንጂ "በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።" (ዘፍ 22፡17-18)። ይህ ቃልኪዳን በአብርሃም ዘር ቢጸናም እምነት ግን አልተለየውም ነበር፤ እንጂ በዘር ብቻ ቢሆን ኖሮ ቃልኪዳኑ በአብርሃም የበኩር ልጅ በእስማኤል በኩል በሆነ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር ይስሐቅን መረጠ። እንዲሁም አሁንም በዘር ብቻ ቢሆን ኖሮ በይስሐቅ የበኩር ልጅ በኤሳው በኩል በሆነ ነገር ግን እግዚአብሔር ያዕቆብን መረጠ ስሙንም እስራኤል አለው በዘሩም በኩል ቃልኪዳንን አደረገ።

ከእራኤል ይኸውም ከይሁዳ የወጣው የአብርሃም ዘር ክርስቶስም የዚህ ቃል ኪዳን ፈጻሚ ሆነ እግዚአብሔር እንደ ሰዶም እንዳንጠፋ በእርሱም በኩል አህዛብ ሁሉ ይባረኩ ዘንድ አቁሞታልና ስለዚህም " ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር። ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን። ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ ነው። " (ገላትያ 3፡16) አህዛብ ሁሉ የሚባረኩበት ዘር ክርስቶስ በመሆኑም በእምነት ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ ሁሉ የአብራህም ቃልኪዳን ባለቤት ነው ቃልኪዳኑ አልተለወጠምና የቃልኪዳኑ ዘር ግን ተገልጧል። በክርስቶስ ያመነ ሁሉ የቃልኪዳኑ ሕዝብ ነው "እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።" (ገላትያ 3፡29) ያላመነ ሁሉም ከቃልኪዳኑ ውጪ ምንም እንኳን በሥጋ እስራኤል ቢሆኑ በክርስቶስ ያላመኑ ከቃልኪዳኑ ውጪ ናቸው "እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና፤ የአብርሃምም ዘር ስለሆኑ ሁላቸው ልጆች አይደሉም፥ ነገር ግን። በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተባለ። ይህም፥ የተስፋ ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ እንጂ እነዚህ የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም ማለት ነው።" (ሮሜ 9፡6-8)

ስለዚህም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በልጁ በኩል የመረጠን አንድ የእግዚአብሔር ሕዝብ አለን እርሱም በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ እስራኤል የተባለን እኛ ነን። የበፊቶቹ ቅርንጫፎች ባለማመናቸው ከግንዱ ላይ ተቆርጠዋል በእነርሱም ቦታ አህዛብ ሁሉ በማመናቸን ቅርጫፍ ሆነናል "መልካም፤ እነርሱ ከአለማመን የተነሣ ተሰበሩ አንተም ከእምነት የተነሣ ቆመሃል። ፍራ እንጂ የትዕቢትን ነገር አታስብ" (ሮሜ 11፡20) ግንዱ አልተለወጠም ቅርጫፎቹ ግን ተለውጠዋል።

ስለዚህም አስተውሉ አሁን እስራኤል የምትባለዋ ሀገርም ሆነች የእስራኤል ሕዝቦች የእግዚአብሔር ሕዝቦች አይደሉም የትኛውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢትም ለእነርሱ አይሠራም ከግንዱ ተቆርጠዋልና ነገር ግን "እነዚያም ደግሞ በአለማመናቸው ጸንተው ባይኖሩ በዛፉ ውስጥ ይገባሉ፤ እግዚአብሔር መልሶ ሊያገባቸው ይችላልና።" (ሮሜ 11፡ 23)

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 63 👍 7 🥰 3
18 July 2025
ኪ
20:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
መከራከራችን ለቃላት አይሁን

አንድ መልካም ብዬ ማስበው ተሞክሮ ከቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልንገራችሁ (ደግሞ ይህን ስል ለመማርያ ብቻ እያቀረብኩ እንደሆነ ይታወቅ ) በቅብጥ ቤተክርስቲያን በሥርዓተ አምልኮ ውስጥ ተወዳጅ የሆኑ ዜማዎች ለእመቤታችን ይቀርባሉ ከእነዚህ መሀል یا م ر ی م (ኦ ማ ር ያ ም) ፤ العليقة التي رآها موسى النبي في البرية (ሙሴ በምድረ በዳ ሳትቃጠል ያያት እጽ) ይገኙበታል። እነዚህ መዝሙራት ላይም የበፊቶቹ versions ላይ አዳምን አዳንሽ ፣ አዳምና ልጆቹን አዳንሽ ከእባብ መርዝም አዳንሻቸው። የሚሉ ቃላት ነበሩ ያው ትርጉሙ ግልጽ ነው በሔዋን በኩል ጥፋት እንደመጣ በአንቺ በኩል ድኅነት መጣ ለማለት ነው ። ነገር ግን ቃላቱ ወደ ተሳሳተ እንዳይተረጎሙ አሁን በሚታተሙት versions ላይ አዳምን አዳንሽ በሚለው ፈንታ ልጅሽ አዳምን አዳነ ፤ አዳምና ልጆቹን አዳንሽ ከእባብ መርዝም አዳንሻቸው በሚለው ፈንታም አዳምና ልጆቹን አዳነ ከእባብ መርዝም አዳናቸው በሚል ተለውጧል።

ከዚህ የምንማረው ክርክራችን የቃላት እንዳይሆን ነው ሀሳብ ሳይሆን ቃላት ሰዎችን ወደ ስህተት የሚመሩ ከሆነ ቃላትን ማስተካከሉ የተሻለ ነው ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎችን በቃላት ምክንያት ወደ ስህተት ከዚህም አልፎ ከቤተክርስቲያን ወደ መውጣት መምራት የለብንምና።

2 Timothy 2 አማ - 2ኛ ጢሞቴዎስ
14: ይህን አሳስባቸው፥ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፥ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።
❤ 136 👍 8 ❤‍🔥 3 🤯 3 🤣 2 🐳 1
21 July 2025
ኪ
18:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወገን ግን ይቺን ቻናል ለምን አታስተዋውቋትም? አታሳዝናችሁም 😁 ደግሞ 1 ሰው ወጥቷል 😑 ማን ነህ?.... ግሩፑን ሳይሆን ቻናሉን ብቻ ... በተቻለ አቅም የአምልኮአችንን ውበት ለማሳየት እንሞክራለን ... ያው ይሄ ሁሉ ችግር የመጣው ካህኑም ምዕመኑም በአብዛኛው አምልኳችንን በደንብ ስላልተረዱት ነው ብዬ አስባለሁ ...Daily አንድ አንድ ጣል እናደርጋለን እንደ እስካሁኑ

@amlake_birhan
@amlake_birhan

ሰዎች ተቀላቀሉት አታሳፍሩኝም ብዬ ገምታለሁ ቅዳሴያችንን ፣ የቅዱስ ያሬድን ድርሰት የሚያሳውቀን ትጉህ ወንድማችን ነው።
❤ 79 👍 2
23 July 2025
ኪ
12:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች ያልተነሡ ርእሶች እና ሒድበት የምትሉትን ጠቁሙ እስቲ እንደባለፈው የጽድቅ ትምህርት ተከታታይ እንገባበታለን
👍 39 ❤ 11
24 July 2025
ኪ
21:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
እነዚህ ሥዕላት መካከል ምን ልዩነት ይታያችኋል?

አንድም ኢየሱስ ነው አንድም ገብርኤል ነው? 🤔

እስቲ ሀሳብ ስጡ
❤ 52 🔥 2 🤔 2 😍 1
21:20
28 July 2025
ኪ
15:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
AI መጥቆ የለ እንዴ ጽሑፉን ብቻ አበላሸው እንጂ ጸዴ ነበር
😁 58 ❤ 6 ⚡ 3
30 July 2025
ኪ
00:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
😁
🤣 97 😁 17 ❤ 3 🤔 2
31 July 2025
ኪ
23:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዚህ ጉዳይ ምንም ባልጽፍ ደስ ይለኛል ግን ቤተክርስቲያናችንን defend ስናደርግ በትክክለኛው መንገድ እንዲሆን ፈልጋለሁ ያለበዚያ ወደ ትችት ያስገባናል። ከፕሮቴስታንት ጋር ስለ Sola Scriptura engage ስናደርግ ደሞ የቤተክርስቲያን አይሳሳቴነት
መምጣቱ አንቀርም። ስለዚህ ይህ አስተምህሮ እንዴት defend መደረግ እንደሌለበት ላሳያችሁ:

“ቤተክርስቲያን ምንም ብትሆን (universal or local የሚባል የለም) አትሳሳትም” የሚለው claim ወደ circular reasoning fallacy ይወስዳናል እንዴት እንደሆነ ላሳያችሁ:

Premise ፦ ቤተክርስቲያን አትሳሳትም።
ታሪካዊ ምልከታ፦ አንዲት የአጥቢያ ቤተክርስቲያን (ወይም ጉባኤ፣ ጳጳስ፣ ግለሰብ እንበለው) ስህተት ሲያስተምሩ እናያቸዋለን የሚል challenge ሲቀርብ ቀጣዩ ምላሽ ይሰጣል
ምላሽ፦ ስህተት የሠሩት ግለሰቦች ናቸው እንጂ ቤተክርስቲያን አይደለችም።
Conclusion፦ ስለዚህ፣ ቤተክርስቲያን በጭራሽ አትሳሳትም፤ ምክንያቱም ስህተት የሰራ ማንኛውም አካል ቤተክርስቲያን አይደለም።

እዚህ ላይ አንድ ያልተጻፈ implied rule እንዳለ አስተዋላችሁ? እርሱም
"ቤተክርስቲያን" ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ትክክለኛ የሆነ አካል ብቻ ነው። የሚል ነው ምክንያቱም ማንኛውም ስህተት የሠራ አካል በታሪክ ሲጠቆም እነርሱ ግለሰቦት ናቸው እንጂ ቤተክርስቲያን አይደሉም ይባላል።

ይህ ግልጽ የሆነ Circular reasoning fallacy ነው
አንድ አካል እውነትን ካስተማረ፣ እርሱ "ቤተክርስቲያን" ነው።
አንድ አካል ስህተትን ካስተማረ፣ እርሱ "ቤተክርስቲያን" አይደለም።

ዙረቱን በዚህ አስተውሉት፦
"ቤተክርስቲያን አትሳሳትም፤ ምክንያቱም ስህተት የሚሰራ ሁሉ ቤተክርስቲያን አይደለም። ቤተክርስቲያን ማን እንደሆነች የምናውቀው ደግሞ ስለማትሳሳት ነው።"
it assumes what it is trying to prove

ይህም ማለት፦
  ቤተክርስቲያን የምትለካው ትክክል በመሆኗ ነው፤
  ትክክል መሆኗ የሚረጋገጠው ደግሞ ቤተክርስቲያን በመሆኗ ነው።
ይህ እንዴት ማለት መሰላችሁ “የሚያሸንፈው ቡድን እርሱ እውነተኛው ነው ፤ እውነተኛው ቡድን ደግሞ መቼም አይሸነፍም”

ይህ fallacy "ቤተክርስቲያን" የሚለውን ቃል ትርጉም አልባ ያደርገዋል፦
ቤተክርስቲያንን በእውን የምትታይ አካል ከማድረግ ይልቅ፣ ትክክለተኛ ለሆነ ነገር ብቻ የሚለጠፍ መለያ ይሆናል። እንዲህ ሲሆኔ ደግሞ ታሪካዊ ስህተቶች ከተፈጸሙ በኋላ ቃላትን በአዲስ መልክ መተርጎም ይመጣል (i.e. ስለተሳሳቱ ቤተክርስቲያን አይደሉም።)
❤ 73 🔥 8 🤔 4
1 August 2025
ኪ
16:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይህን የላዩን መልሼ ሳነብ የካቶሊኮቹ ፓፓ አይሳሳቴነት መጣብኝ። የካቶሊኩ ፓፓ ex-cathedra (ከጴጥሮስ መንበር) ቤተክርስቲያኒቷ በሙሉ ላይ ዶግማን define ሲያደርግ አይሳሳትም የሚል claim አለ ስለዚህም አንዲት ቤተክርስቲያን በእርግጥም ከስህተት የጠራች መሆኗን ለማረጋገጥ ከፓፓው ጋር ኅብረት ማድረግ አለባት ይባላል።

ነገር ግን ይህ ዶክትሪን ትልቁ ችግሩ ታሪክ ነው ታሪክን ስታጠኑ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የያዘችውን አቋሞች ስትለዋውጥ ታገኛላችሁ ታድያ አቋሟችሁን ከለወጣችሁ የመጀመሪያው አቋም ስህተት ነበር ማለት ነው ስለዚህም ሮም ልትሳሳት ትችላለች ስትሏቸው ወደ redefinition ይኬዳል ማለትም የበፊቱ statement infallible አልነበረም ፓፓው infallible የሆነው በጣም በnarrow sense ነው ይባላል። በቃ contradictionኑን ለማስታረቅ ሲባል the infallibility is defined in a very narrow sense which make it unfalsifiable. እና ከላይ እንደጻፍኩት አይነት circular reasoning ያመጣል።

Catholic Circular reasoning: Unfalsifiable Papal Infallibility

Premise: The Pope cannot err when speaking infallibly.

Observation: A Pope appears to have erred (e.g., contradicting previous doctrine).

Response: That teaching wasn’t infallible.

Question: How do we know it wasn’t infallible?

Answer: Because the Pope cannot err when speaking infallibly.

This returns us to the original assumption without external or objective criteria that could falsify it.

This is the structure of circular reasoning:

“The Pope can’t err when speaking infallibly, and we know he wasn’t speaking infallibly because he erred and Popes don’t err infallibly.”

ሳስበው የነበረ ነገር ስለሆነ ላካፍላችሁ ብዬ ነው ይጠፋል 😊
❤ 44 🥱 3
ኪ
18:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
Why is it that one likes being moved to grief at the sight of sad or tragic events on stage, when one would be unwilling to suffer the same things oneself? In the capacity of spectator one welcomes sad feelings; in fact, the sadness itself is the pleasure. What incredible stupidity! The more a person is buffeted by such passions in his own life, the more he is moved by watching similar scenes on stage, although his state of mind is usually called misery when he is undergoing them himself and mercy when he shows compassion for others so afflicted. But how real is the mercy evoked by fictional dramas? The listener is not moved to offer help, but merely invited to feel sorrow; and the more intensely he feels it the more highly he rates the actor in the play. If these tragic human stories—whether referring to events long past or fictional—are played in such a way that they fail to move the spectator to sadness, he walks out in disgust, criticizing the performance; but if he feels sad, he stays on, keenly attentive, and enjoys a good cry.

ፊልም እያያችሁ የምታለቅሱ ሴቶች in the words of Augustine what utter stupidity 😅
😁 29 ❤ 11 😭 3
5 August 2025
ኪ
08:58
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
01:13, 9.4 MB
የኮፕት ቀሳውስት እና ጳጳሳት የሚመቹኝ እኮ ፈታ ያሉ ናቸው። ወጣቱን በመቅረብ በፍቅር ይይዛሉ
❤ 164 😁 21 ❤‍🔥 11 👍 5 🥰 5
6 August 2025
ኪ
15:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኦሬንታል እና ኢስተርን ኦርቶዶክስ መካከል አንድነት እንዴት መምጣት አለበት?

መጀመሪያ እንዴት መምጣት አለበት የሚለውን ከማየታችን በፊት እንዴት መምጣት የለበትም የሚለውን እንይ፡
ሁለታችንም ኦርቶዶክሳውያን ነበርን ልዩነቱ የቃል ብቻ ነበር ውግዘቱም በስህተት ነበር እንጂ በእግዚአብሔር ፊት ሁለቱም የጌታ ቤተክርስቲያን ነበሩ ነገር ግን በፖለቲካ ምክንያት ተለያዩ አሁን ግን ልዩነታቸውን ፈተዋል።

በዚህ መንገድ አንድነት መጣ ማለት ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ቤተክርስቲያን ገደል ገባ ማለት ነው ስለዚህ ይህ በጣም አደገኛ አካሔድ መሆኑን አውቀን እንዲህ ከማለት ልንታቀብ ይገባል።

በኦርቶዶክሳዊ ነገረ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ምሥጢራዊ አካል ናት፤ ክርስቶስ አንድ ስለሆነም ቤተክርስቲያንም እንዲሁ አንድ ናት የማእዘኑ ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዋና። ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ስንል ደግሞ በምድር ላይ የምትታይ ኅብረት እያልን ነው ማለትም አንድ እምነትም የሚመሠክሩ በመሠዊያው ዙሪያም ኅብረት የሚያደርጉ የአማኞች ኅብረት ማለት ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ስንል በምድር ላይ የጌታ ቤተክርቲያን የሆነች አንዲት ብቻ የምትታይ ኅብረት (One visible communion only) አለ እያልን ነው። ይህ statement by necessity የጌታ ቤተክርስቲያን ሁለት ወይም ከዛ በላይ እርስ በእርስ ቁርባናዊ ኅብረት የሌላቸው ተቋማት ውስጥ subsist አታደርግም የሚለውን ያሳያል።

ስለዚህ በኬልቄዶን ጉባኤ ቤተክርስቲያን ወደ 2 እርስ በእርስ ቁርባናዊ ኅብረት ወደ ሌላቸው ተቋማት ስትከፈል የጌታ ቤተክርስቲያን በሁለቱም ተቋማት ውስጥ subsist ታደጋለች ማለት ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ንግግር ነው። ብዙ ሰዎች ያን ጊዜ ልዩነቱ የቃላት ብቻ ነበር ሲሉ ከበጎ አመለካከት የተነሣ ቢሆንም ይህ ንግግር ግን ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ስለሆነ መታቀብ አለበት። ንግግሩ ነገረ ቤተክርቲያንን የሚጎዳ ብቻ አይደለም ታሪክን አለማወቅም አለበት አባቶች ያን ሁሉ ዋጋ የከፈሉት ለቃላት ትርጉም ብቻ አልነበረም ይልቅስ ኦርቶዶክሳዊነትን የሚሸረሽር ምንፍቅናን ተዋጉ እንጂ። ስለዚህ አሁን ላይ አንድነት ላይ ውይይት የምናደርግ ከሆነ ሁለታችንም valid Churches ነበርን አሁን ግን ወደ አንድነት መጣን በሚለው መልክ ሊሆን አይችልም።

ታድያ እንዴት ወደ አንድነት እንምጣ? ወደ አንድነት መምጣት ያለብን የግድ አንዱ side compromise ማድረግ አለበት መታሰብም ያለበት አንዱ side schismኡን ትቶ ወደ መጀመሪያው እውነት ተመለሰ በሚለው መልኩ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ ማለት ግን አንዱ side የግድ schismatic ነበርኩ ወደ እውነት ተመልሻለሁ ብሎ admit ያድርግ ማለት አይደለም "the very act of recanting a position held is by itself a repentance even if they don't admit it".

The Joint Commission of the Theological Dialogue between the Orthodox Church and the Oriental Orthodox Churches ያደረገውም ይሄንኑ ነው። ኢስተርን ኦርቶዶክሶች 3 ነጥቦችን ለእኛ admit አድርገዋል፡

1. "μία φύσις τοῦ θεοῦ λόγου σεσαρκωμένη -One nature of the incarnate Logos" ወይም የእግዚአብሔር ቃል አንድ ሥግው ባሕርይ የሚለው formula valid ነው Oriental Orthodoxም በመጠቀማቸው justified ናቸው ብሏል። (1990 agreement Point 7)

2. Eastern Orthodox 2 ባሕርይ ሲሉ justified ናቸው ምክንያቱም 2 ባሕርይ ሲሉ the distinction " ἐν θεωρίᾳ μόνον - in contemplation alone" ወይም የባሕርያትን ልዩነት የምናስተውለው በሃሳብ ብቻ ነው እንጂ በእውነታው ዓለም አይደለም ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለOriental Orthodox ሌላ ነጥብ የሚሰጥ ነው። (1990 agreement Point 7)

3. ሁለቱም ቤተሰቦች የግድ መቀበል ያለብቻው የዓለም አቀፍ ጉባኤያት ቁጥር ሦስት ናቸው ከ4ተኛው በኋላ ያሉትን ጉባኤያት Oriental Orthodox የእነርሱ [የኢስተርን ኦርቶዶክስ] አተረጓገም ነው ትላለች። ይህም ለOriental Orthodox ሌላ ነጥብ የሚሰጥ ነው ምክንያቱም አንድ ጉባኤ በባሕርይው ዓለም አቀፍ ከተባለ ሁሉም ሊቀበለው ይገባል ማለት ነው ስለዚህ ከ4ተኛው በኋላ ያሉትን ጉባኤያት መቀበል ግዴታ አይደለም ከተባለ በሌላ ቋንቋ የዓለም አቀፍ ጉባኤያት አይደሉም ማለት ነው። (1990 agreement Point 8)

ስለዚህ ይህ ስምምነት ውግዘቶቹ ይነሱ ብሎ ሲወስን እኛ የምናየው የEastern Orthodox recantation of their position ስለሆነ admit ባያደርጉትም እንደ መመለስ (Repentance) በመውሰድ ውግዘቱ ይነሳል ማለት ነው። ለዚህም ነው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንዲህ የተናገሩት " እኛ ሦስቱን የዓለም አቀፍ ጉባኤያት እንቀበላለን ኬልቄዶንን ግን ልንቀበለው አንችልም እናንተ 7 አላችሁ 1 ብታጡ አትጎዱም"

እንዲህ አይነት Reunion ሲካሔድ በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው አይደለም በReunion of 433 የአንጾኪያ ቤተክርስቲያን ንስጥሮሳውያን ተመልሰዋልና። አሁን ይህን Joint declaration በመቀበል Eastern Orthodox ሊመለሱ ይችላሉ actuallyም የተቀበሉ አሉ (የግሪኳ አስክንድርያ ፣ የግሪኳ አንጾኪያ ፣ ሮማንያ) ሌሎቹ ግን በምልዓት ተቀብለው እንዳይመለሱ በቁስጥጥንያ ቤተክርስቲያን ስር የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳም መነኮሳት ትልቅ ተቃውሞ አስነስተዋል። በእኛ በኩል ግን Father Tadros Y. Malaty እንደተናገሩት " We will accept them as long as they accept us by the Joint Declaration"

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 56 🥰 44 🔥 6 👍 5 🆒 3 🤔 2
12 August 2025
ኪ
20:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
ትምህርተ መለኮታዊ ወጥነት (Doctrine of Divine Simplicity)

በእውነታ ሁለት አይነት ህልውናዎችን ማሰብ እንችላለን ፡ Contingent Existence and Necessary existence. ህልውና ለምን ኖረ (Why anything exists at all?) ብለን ስንጠይቅ እነዚህን concepts እናገኛቸዋለን። Contingent Existence ማለት አንድ ነገር ለህልውናው ሌላ ነገር ላይ ጥገኛ ሲሆን ነው ማለትም ጥገኛ የሆነበት ነገር ባይኖር ኖሮ እርሱም አይኖርም ነበር ስለዚህ ለየትኛውም contingent existence logically prior የሆነ ሌላ ህልውና ያስፈልገዋል (Logically prior እንጂ የግድ በጊዜ ቀዳሚ ላይሆን ይችላል።) ወደ ህልውና ከመሔዳችን በፊት Necessary and Contingent የሚሉትን ሃሳቦች በምሳሌ እንይ። ለምሳሌ ቅጠል ለምን አረንጓዴ ሆነ ብለን ብንጠይቅ በ chlorophyll እና ብርሃን ላይ contingent ስለሆነ (Chlorophyll ሌሎችን ብርሃናት በመምጠት አረንጓዴን ያንጸባርቃልና) ስለዚህ ቅጠል አረንጓዴ መሆኑ contingent ነው እንጂ necessary አይደለም። ነገር ግን አንዳንድ necessary የሆኑ ለመሆናቸው አመክንዮ የሌላቸው ነገሮች አሉ ለምሳሌ አራት መአዘን ለምን አራት ጎኖች ኖሩት ብንል አራት መአዝ ራሱ by definition አራት ጎኖች አሉት እንላለን እንጂ ከእርሱ የሚቀድም አስረጂ ምክንያት የለውም ስለዚህም necessary ነው።

ይህን የNecessary እና Contingent ሀሳብ ይዘን ወደ ህልውና ስንመጣ ደሞ አንድ ነገር ህልው ይሆን ዘንድ Logically prior የሆነ ምክንያት ካለው contingent ህልውና አለው እንላለን ምክንያቱም ከእርሱ logically prior የሆነው ምክንያት ባይሆን ኖሮ እርሱም ያለመሆን ወይም ሌላ የመሆን እድል አለውና። ማንኛውም ከክፍላት የተሠራ ነገር ደሞ በክፍላቱ ላይ contingent ነው ፤ ክፍላቱ ምሉዕ ከሆነው ነገር logically prior ናቸው ምክንያቱም ክንላቱን አንድ ላይ አቀናጅቶ ምሉዕ ነገሩን ያመጣ አስጀማሪ ምክንያት ያስፈልጋልና። ከእዚህም በመነሳት ማንኛውም ከክፍላት የተሠራ ነገር necessary existence የለውም ብለን መደምደም እንችላለን። (The whole is contingent on its parts for existence.)

ይህን መሠረት ይዘን ወደ እግዚአብሔር ስንመጣ ደግሞ እግዚአብሔር ለህልውናው ምክንያት የሌለው necessary ነው (አመክንዮ ዘሐዋርያት እንደሚለው እስመ አልቦ ውስተ ህላዌሁ አመክንዮ)። ለምን ምንም ነገር ኖረ ለሚለው የመጨረሻ መልስ እግዚአብሔር ነው ፤ እግዚአብሔር ግን ለምን ኖረ ብንል መልሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው እንጂ ከእግዚአብሔር ውጪ የሆነ እርሱን የሚያብራራ ምክንያት የለም። እግዚአብሔርን የሚያብራራ ምክንያት አለ ካልን እግዚአብሔር በዚህ ምክንያት ላይ contingent ነው ስለዚህም እግዚአብሔር ለህልውናው አስጀማሪ አለው ያስብላል።

Doctrine of divine simplicity የሚመጣው እዚህ ጋር ነው፡
P1: ማንኛውም ክፍል ያለው ነገር በክፍሎቹ ላይ contingent ነው። (The whole is contingent on its parts)
P2: እግዚአብሔር በህልውናው ምንም ነገር ላይ contingent ያልሆነ necessary ነው።
Conclusion: እግዚአብሔር ምንም አይነት ክፍሎች የሌሉት ወጥ ነው። (God is Simple without any composition)

እግዚአብሔር ለህልውናው አስጀማሪ የሌለው ሁሉን ነገር ያስጀመረ አካል ነው ብለን እስካመንን ድረስ divine simplicityን ማመን ግድ ይላል ያለበለዚያ እግዚአብሔርን በክፍሎቹ ላይ contingent አድርገነው እግዚአብሔርን ማን ፈጠረው? ለሚለው ኤቲስቶች ጥያቄ በር መክፈት ነውና። ይህም የሚያሳየው በእግዚአብሔር አምናለሁ ስንል የምናምንበት እግዚአብሔር ከምንም አይነት የአካል ክፍሎች ያልተሠራ ወጥ መሆኑን ነው። እግዚአብሔር ከእጅ ፣ እግር ፣ አይን ፣ ጆሮዎች ወዘተ ከተባሉ የአካል ክፍሎች በፍጹም የተሠራ አይደለም ወይም ያያል የሚባል ግብሩ ማየት ብቻ የሆነ አንድ የአካል ክፍል፣ እንዲሁም ግብሩ መስማት ብቻ የሆነ አንድ የአካል ክፍል ወዘተ የለውም ያለበለዚያ ለህልውናው በእነዚህ ነገሮች ላይ contingent ይሆናልና።

ከዚህ ተነሥተን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር አካል ክፍሎች ሲያወራ በሰውኛ ዘይቤ መተርጎም አለብን እንዲሁም "እግዚአብሔር የአካል ክፍሎች አሉት ግን አይመረመሩም" የሚለውን የኢትዮጵያ ሊቃውንት ማብራርያ መቃወም አለብን ወደ logical conclusion ከወሰድነው ወደ Atheism ሊያመራ ይችላልና!

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 64 👍 7 👏 6 👎 2
14 August 2025
ኪ
10:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
Thomistic Divine Simplicity እና Essence- Energy distinction

የላዩ DDS ጽሑፍ ከቶሚስቲኩ ጋር አንድ አድርጋችሁ እንዳትረዱት በዚህ clarify ላደርግላችሁ ግን ይህን በትንሹ clarify ለማድረግ ያህል ብቻ ነው እንጂ በስፋት የቀረበ አይደለም ፤ ሌላ ቀን በስፋት እናያቸዋለን። እግዚአብሔር መለኮታዊ ወጥና በህልውናው ክፍፍል Physical and metaphysical እንደሌለበት በሁሉም አብያተ ክርስቲያን የሚታመን እውነታ ነው። ነገር ግን የቶማስ አኪናስ Divine Simplicty ግን ከዚህም ገፋ በማድረግ ይሔዳል። በምእራቡ ዓለምም ለረጅም ጊዜ የእርሱ ሀሳብን በመያዝ Classical Theismን ይዟል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህንን Classical conception of divine Simplicity በመሞገት Neo-Classical Theists ተነሥተዋል ከእነዚህም መካከል Alvin Plantiga ተጠቃሽ ነው።

በቶማስ አስተምህሮ መሠረት በእግዚአብሔር ዘንድ ምንም አይነት Metaphysical Composition ማሰብ የለብንም። ለምሳሌ የ“form” እና “matter” (ቅርጽና ቁስ)፣ የ“essence” እና “existence” (ባሕርይና ህልውና)፣ ወይም የ“subject” እና “accident” (ባለቤትና መገለጫ) ጥምረት የለበትም። በዚህ አስተምህሮ፣ የእግዚአብሔር ግብረ ባሕርያት (attributes) እንኳን ከባሕርዩ (essence) የተለዩ አይደሉም። ኃይሉ፣ በጎነቱ、 እውቀቱ、 ሁሉም ከባሕርዩ ጋር አንድና ተመሳሳይ (identical) ናቸው። እኛ በአዕምሯችን “ይሄ ኃይሉ ነው፣ ይቺ ደግሞ ጥበቡ ናት” ብለን የምናደርገው ልዩነት በሀሳብ ደረጃ (conceptual) ብቻ ነው እንጂ በእግዚአብሔር ውስጥ ያለ እውነተኛ ልዩነት (Real distinction) አይደለም። ይህንን Thomistic Divine Simplicty "Absolute Divine Simplicity (ADS)" ብለን ልንጠራው እንችላለን።

Alvin Plantiga ADS ላይ ሁለት የሚታወቁ ችግሮችን ያነሳል እነርሱም Many Properties Problem እና Property Identity Problem ናቸው።

Many Properties Problem የእግዚአብሔር ግብረ ባሕርያት በሙሉ ከባሕርዩ ጋር አንድ ከሆኑ፣ እንግዲያውስ እግዚአብሔር አንድ ‘property’ ብቻ ነው ያለው ማለት ነው” ይላል። ይሄ ደግሞ ከምናውቀው ጋር ይጋጫል። ምክንያቱም በመጽሐፍም በትውፊትም እንደተቀበልነው እግዚአብሔር ብዙህ Properties አሉት ለምሳሌ: ሁሉን ቻይነት ፣ ሁሉን አዋቂነት ፣ መሐሪነት ፣ ጥበብ ፣ በጎነት ወዘተ። በእግዚአብሔር ዘንድ እነዚህ ሁሉ መገለጫዎች እንዴት አንድና ተመሳሳይ ሊሆኑ ይችላሉ?

ነገር ግን ከዚህም የበለጠ ከባድ የሚለው ሁለተኛው ተቃውሞ  “Property-Identity Problem” ነው። አመክንዮው እንዲህ ነው፦ እግዚአብሔር ከግብረ ባሕርያቱ (properties) ጋር አንድ (identical) ነው ከተባለ、 እና ‘properties’ ደግሞ በአብዛኛው ፍልስፍና እንደሚታሰበው “abstract” (ረቂቅ) እና “causally inert” (ምንም ተጽዕኖ መፍጠር የማይችሉ) ከሆኑ、 እንግዲያውስ እግዚአብሔር ራሱ አንድ ረቂቅ ነገር (abstract object) ይሆናል ማለት ነው። እንዲህ ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር የሚገናኝ ፣ የሚፈጥር ፣ የሚያፈቅር ፣ ልጁን የሚልክ Personal (አካላዊ) አምላክ ሳይሆን ዓለም የተፈጠረበት Neccesary Property ብቻ ይሆናል።

በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ እግዚአብሔር ወጥ (simple) እንደሆነና በውስጡ ምንም አይነት ክፍፍል (parts) እንደሌለው ተቀባይነት አለው። ነገር ግን ADSን እንቃወማለን በእግዚአብሔር ዘንድ በባሕርይው እና ግብረ ባሕርይው ልዩነት (Essence-Energy distinction) አለና።

Essence (ባሕርይ)፦ ይህ ከማንኛውም ፍጡር አዕምሮ በላይ የሆነው、 የማይመረመርና የማይታወቀው የእግዚአብሔር ውስጣዊ ህልውና ነው።
Energies (ግብረ ባሕርይ)፦ እነዚህ የእግዚአብሔር ያልተፈጠሩና ዘላለማዊ የሆኑ ተግባራቱ ናቸው። ለምሳሌ ህይወቱ、 ፈቃዱ、 ፍቅሩ、 ኃይሉ እና ጥበቡ። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ግንኙነት የሚፈጥረውና የሚታወቀው በእነዚህ ግብረ ባሕርያት አማካኝነት ነው።
እነዚህ ግብረ ባሕርያት (energies) የተፈጠሩ ነገሮች አይደሉም፤ ከባሕርዩም አይነጣጠሉም። እነርሱ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ መገለጫውና ተግባራቱ ናቸው፤ ሙሉ በሙሉ መለኮታዊ ሲሆኑ፣ ከማይታወቀው ባሕርዩ (essence) ግን በእርግጥም የተለዩ ናቸው። ይህ ልዩነት በሀሳብ ብቻ (Conceptual only)ሳይሆን በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ያለ እውነተኛ ነገር ነው።

ይህ distinction የፕላንቲጋን ተቃዎሞች ይፈታል ምክንያቱም በእግዚአብሔርና በግብራቱ እንዲሁም ግብራቱም እርስ በርሳቸው ልዩነት አላቸውና ስለዚህም "God is not the same as his attributes and the attributes are distinct from each other" ማለት ነው። ይህንንም ስንል በእግዚአብሔር ዘንድ Metaphysical Composition እየሠራን አይደለም ምክንያቱም "ግብራት" በራሳቸው Ontological reality የላቸውም በራሳቸው ከእግዚአብሔር ጋር የቆሙ ህልውናዎችም አይደሉም የራሱ የእግዚአብሔር መገለጫዎች ናቸው እንጂ።

@KidanZeIyesus
👍 30 ❤ 19 🔥 7 🥰 1
15 August 2025
ኪ
15:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሮምን ለማስደሰት በንጉሥ ኃይል የጸደቀ የእምነት መግለጫ

ታውቃላችሁ አይደል የኬልቄዶን ጉባኤ ላይ የእምነት መግለጫ ሲጻፍ መጀመሪያ የተጻፈው የእምነት መግለጫ ክርስቶስን ከሁለት ባሕርይ ይለዋል እንጂ በሁለት ባሕርይ አይለውም።

ይህን ያዩ የሮም ተወካዮች በሁለት ባሕርይ ተብሎ ካልተስተካከለ ወደ ሮም እንመለሳለን ጉባኤውንም ሮም እናረጋለን ብለው አስፈራሩ። ጳጳሳቱ ግን አልሰማም ሲሉ ይህን ጊዜ የንጉሡ ተወካዮች ሮምን ማስቀየም አልፈለጉምና 22 ሰው ያለበት ኮሚቴ አዘጋጅተው ጳጳሳቱን በሁለት ባሕርይ የሚለውን ካልተቀበላችሁ ጉባኤው ይበተንና አዲስ ጉባኤ በሮም ይጠራል ሲሉ አስፈራሯቸው።

ነገር ግን ጳጳሳቱ አሁንም አልሰማም አሉ ይልቅስ እንዳውም
"ንጉሥ ሆይ ሺህ ዐመት ንገሥ አሁን ያቀረብነው የእምነት መግለጫ [ከሁለት ባሕርይ የሚለው] ተቀባይነት ያግኝ ያለበዚያ ወደ ቤታችን እንሔዳለን" ሲሉ ጮሁ።

እንዲሁም የኢላርያ ጳጳሳት "የሚቃረኑን ንስጥሮሳውያን ናቸው ንስጥሮሳውያኑ ወደ ሮም ይመለሱ" እያሉ ጮሁ። (አይገርማቹህም ወደ ሮም እንመለሳለን ብለው ሲያስፈራሩ ከነምንፍቅናችሁ ወደ ሮም ተመለሱ እያሉ ነው 😄)

ይህን ጊዜ ዳኞቹ በአንድ ወጥመድ ያዟቸው "ዲዮስቆሮስም ከሁለት ባሕርይ ይላል ፖፕ ልዮን ግን በሁለት ባሕርይ ከዲዮስቆሮስ ወገን ናችሁ ከልዮን?" ሲሉ አፋጠጧቸው። (ዲዮስቆሮስን አውግዘውት ልዮንን ኦርቶዶክስ ብለውት ስለነበር ነው። )

እነርሱም በመጨረሻ እሺ ብለው "በሁለት ባሕርይ የሚለውን" የእምነት መግለጫ ጽፈው አጸደቁ። ይታያችሁ እንግዲህ ከሁለት ባሕርይ ያለው ቄርሎስ ነው ዲዮስቆሮስ ቄርሎስ ያላለውን አላለም ግን ዲዮስቆሮስን ስላወገዙት ብቻ የቄርሎስን formula ትተው "ወደ ሮም ተመለሱ እናንተ ንስጥሮሳውያን" ያሏቸውን formula ተቀበሉ።

ይህን ታሪክ በራሳቸው ኬልቄዶናውያን ተጽፎ Acts of Council of Chalcedon session V ላይ ታገኙታላችሁ።
❤ 46 😁 8 😭 5 😢 3 🤣 1
ኪ
16:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
ፖስት ባደረኩ ቁጥር ቻናሉን leave የምትሉ ሰዎች የእግዚአብሔር በረከት ከቤታችሁ leave ይበል 😒
😁 113 🤣 68 👎 14 🙉 14 ❤ 6 😱 6 🌚 4
16 August 2025
ኪ
20:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
በጌታ ቀን በመሠዊያው እንገናኝ ማንም እንዳይቀር ክርስቶስን እንቀበለው ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ!

እኔ እሑድ አስቀድሼ ቆርባለሁ እናንተስ?

የሚል ቻሌንጅ ጀምሬያለሁ!
❤ 169 🤗 9 😭 7 🔥 4 👍 1
18 August 2025
ኪ
11:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
T
Theo-Sophia 18.08.2025 11:50:51
ሰላም እንዴት አረፈዳችሁ!
ዛሬ ማታ 3:00 ሰዓት ላይ ከወንድማችን ኪዳን ጋር ነገረ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ላይ ትምህርት ይኖረናል። እንዳትቀሩ!

@Theo_Sophia_apology
❤ 57 👍 5
19 August 2025
ኪ
09:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅዱስ አውግስጢኖስ ማኒኪያን እያለ ብሉይ ኪዳን ሲያነብ በጣም sillly ይመስለው ነበር በተለይ ዘፍጠረት "የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯል" ስለሚል ክርስቲያኖች እግዚአብሔር እንደ ሰው ከአካል ክፍላት የተሠራ ነው ይላሉ ብሎ በማሰብ ክርስትናን ይጠላ ነበር። ብሉይ ኪዳንንም literally እየተረጎመ የእግዚአብሔር ቃል አይሆንም ብሎ ያስብ ነበር። That is until he met Ambrose!

ወደ ሚላን ከተማ ሔዶ አምብሮስን ሲያስተምር ሲሰማው በጣም ተደነቀ ክርስትናም እንዲህ ይብራራል እንዴ ብሎ አሰበ ብሉይ ኪዳንን የሚያይበት አዲስ አይንም ሰጠም ይህም ብሉይ ኪዳንን literally ሳይሆን በምሳሌያዊ (metaphorical) መንገድ መተርጎም ነው። አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጽፋል "This realization was particularly keen when once, and again, and indeed frequently, I heard some difficult passage of the Old Testament explained figuratively; such passages had been death to me because I was taking them literally.

ይህንን በደንብ የተረዳሁት፣ በተለይ አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ደጋግሜ፣ አንዳንድ የብሉይ ኪዳን አስቸጋሪ ክፍሎች በምሳሌያዊ አነጋገር ሲተረጎሙ በሰማሁ ጊዜ ነበር፤ እነዚያን ክፍሎች ቃል በቃል እወስዳቸው ስለነበር ይገድሉኝ ነበር።" Augustine Confessions book V,7

ከአምብሮስ ስር ብዙ ከተማረ በኋላ ግን ማኒኪያኖች ክርስትናን misrepresent አድርገው ነገሩት እንጂ ክርስቲያኖች እንደዛ እንደማያምኑ ሲረዳ እንዲህ ይላል " I came to realize that your spiritual children, whom you had brought to a new birth by grace from their mother, the Catholic Church, did not in fact understand the truth of your creating human beings in your image in so crude a way that they believed you to be determined by the form of a human body.

ከእናታቸው ከኩላዊቷ ቤተክርስቲያን በጸጋህ ዳግም እንዲወለዱ ያደረግሃቸው መንፈሳዊ ልጆችህ፣ አንተ በሰው አካል ቅርጽ የተወሰንክ እንደሆንክ እስከማመን በሚያደርስ ጥሬ ግንዛቤ፣ ሰውን በአምሳልህ የመፍጠርህን እውነት እንደማይረዱ ተገነዘብኩ።" Confessions Book VI ,4

ከዚህም በኋላ አሁን ላይ ባለው መረዳት አምላኩን እንዲህ ሲል አመሰገነው " O God, most high, most deep, and yet nearer than all else, most hidden yet intimately present, you are not framed of greater and lesser limbs; you are everywhere, whole and entire in every place, but confined to none. In no sense is our bodily form to be attributed to you, yet you have made us in your own image, and lo! here we are, from head to foot set in our place!

አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ፣ ከሁሉ በላይ ጥልቅ የሆንክ፤ ከምንም ነገር በላይ ግን የቀረብክ፤ የተሰወርክ ስትሆን ነገር ግን በቅርባችን የምትገኝ፤ አንተ በትልቅና በትንሽ አካላት የተቀረጽክ አይደለህም። በየትኛውም ስፍራ ሙሉ በሙሉ ትገኛለህ፤ ነገር ግን በምንም አትወሰንም። የእኛ የሥጋዊ አካል ቅርጽ በምንም መልኩ ለአንተ ሊሰጥ አይገባም፤አንተ እኛን በአምሳልህ ፈጥረኸናል፤ እነሆም እኛ ከራስ ፀጉራችን እስከ እግር ጥፍራችን በቦታችን ላይ ቆመናል!" Augustine Confessions Book VI ,4

ጌታ እግዚአብሔር በመግቦቱ አውግስጢኖስን ወደ አምብሮስ መራው አምብሮስም ወደ ክርስቶስ አውግስጢኖስም በጌታ ላይ ዐረፈ ያ ዕምባው ልጅ በጌታ ላይ ዐረፈ የእናቱ ሞኒካ እምባው ታበሰ!
❤ 73 🔥 4 🥰 4
ኪ
12:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሥላሴክሙ ፡ ሥላሴ ፡ ይረስየኒ ፡ መካነ ።
ድኅረ ፡ ተዋሐድኩሰ ፡ ዘሥላሴሁ ፡ ብርሃነ ።
ዮርዳኖሰክሙ ፡ ዝየ ፡ እስመ ፡ ኵለንታየ ፡ ኮነ ።
ኢየኀሥሥ ፡ እምዮርዳኖስ ፡ ሰማዕተክሙ ፡ ምእመነ ።
ወኢይትሜነዮ ፡ ለታቦር ፡ እስመ ፡ ታቦር ፡ አነ ።
፪. ትርጕም በዐማርኛ ግጥም
በአካልና በገጽ ዘላለም ሥላሴ፣
ሦስትነት ስማችኍ ግርማዬ ሞገሴ፥
ማረፊያው ያድርገኝ ሥፍራው የቅዳሴ።
ከተዋሐድኹ ወዲያ የሥላሴን ብርሃን ጸጋን በመልበሴ፣
ዮርዳኖስን ኾነ መላው ሰውነቴ አካል እስትንፋሴ።
ስለዚኽ፥
እማኝ ከዮርዳኖስ አይሻም መንፈሴ፤
ታቦር ተራራንም አትመኝም ነፍሴ፤
የአምላክ ማደሪያ ታቦር ነኝ ራሴ።
© ትርጕም፦ ኤፍሬም የኔሰው።

የእግዚአብሔርን ጸጋ የተቀበልን ታቦር እኛ ነን እንኳን አደረሳችሁ ❤️
❤ 88 👍 1
ኪ
22:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=5dBbnJbEXRI&ab_channel=%E1%89%A4%E1%89%B0%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%88%99%E1%88%AD%7CBeteMezmurLyrics

ከመሸም ቢሆን በምርቴ መዝሙር በዓሉን እያጣጣምን ነው መቼስ my favorite ዘማሪት ምርቴ መሆኗን እስከዛሬ ሳትገምቱ አትቀሩም
❤ 49 🙏 7
20 August 2025
ኪ
19:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
ፊልጵስዩስ 2
5: በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።
6: እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
7: ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
8: በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
9: በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤
10: ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
11: መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

ለካስ እግዚአብሔር አብ የሚከብረው ምላስ ሁሉ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ሲመሰክር ነው? እንዴት ደስ ይላል ፤ ልጅ ለአባቱ የባርያን መልክ ይዞ እስከ ሞት ታዘዘ የእግዚአብሔር አብ ክብሩ ዓለም እንዲፈጠር ብቻ ሳይሆን የጠፋው ዳግመኛ እንዲፈጠር ነውና። አባትም ለልጁ ከስምም ሁሉ በላይ ከፍ ያለውን ስም ሰጠው ያለ ልክ ያለ መጠንም አከበረው ለእርሱም ፍጥረት ሁሉ ለልጁ ስም ይንበረከክ ዘንድ እንጂ ሌላ ክብር አልፈለገም።

እስቲ ኑ ሁላችን አብን በልጁ እናክብረው የአብ ክብሩ ምንድነው ካላችሁኝ ምላስ ሁሉ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው! ስለዚህም ምላስ ላለው ፍጥረት ሁሉ እናውጅ አንድም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ የማይመሰክር እስካይቀር ድረስ አብም ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ ጉልበት ያለው ሁሉም ለልጁ ስም ይንበረከክ ዘንድ!

እርሱስ የእኛን ክብር አይሻም ዓለም ሳይፈጠር በነበረ ክብሩ አባቱ ያከብረዋል በእኛ አንደበት በመክበሩ ግን ክብርስ የሚሆነን ለእኛ ነው ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ የሚመሰክር ምን ያህል የተባረከ አንደበት ነው? ለጌታ ስም የሚንበረከክስ ጉልበት ምን ያህል የከበረ ነው? ክብርን ሳይፈልግ ራሱን ባዶ ባደረገው ጌታስ የሚመሰል ሰው ምን ያህል ከፍ ከፍ ያለ ነው?

ኑ ዓለምን ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዋጅ እርሱ ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ ጉልበት ሁሉ ለልጁ ስም ይንበረከክ ዘንድ ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ!
❤ 107 🥰 9 🔥 7 ❤‍🔥 4 👍 2 😢 1 🙏 1
21 August 2025
ኪ
13:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
I had been extremely miserable in adolescence, miserable from its very onset, and as I prayed to you for the gift of chastity I had even pleaded, "Grant me chastity and self-control, but please not yet." I was afraid that you might hear me immediately and heal me forthwith of the morbid lust which I was more anxious to satisfy than to snuff out.

Oh My Augustine 🥹🥹
❤ 66 ❤‍🔥 10 😢 6 👍 1 🙏 1
22 August 2025
ኪ
10:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
"እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤ ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳከዊሁ ብርሃን፤ አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤ ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤ ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤ እመቅድሐ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን ወውስቴታ ተሠርዓ ቁርባን።"

"ከጌቴሴማኒ ወደ ከፍተኛው ስፍራ ፈለሰች፤ መስኮቶቹ ብርሃን ወደሆኑት ወደ ታላቁ ቤተ መቅደስ ( ገባች)፤ የመዳን በርና የቃል ኪዳኑ ጽላት የሆነች ማርያምን፤ ሁሉም በዕብራይስጥ ቋንቋ በአንድነት እንዲህ ይሏታል፦ እርሷ በእውነት ቅድስተ ቅዱሳን የሆነች የጳጦስ ዛፍ (የማትቃጠለው ቁጥቋጦ) ናት፤ ከማኅፀኗ ማዕድ የወይን ዘለላ ተቀዳ፤ በእርሷም ውስጥ ቁርባን ተዘጋጀ።"

"From Gethsemane she departed to the upper place; into the great temple whose windows are light. To Mary, the Gate of Salvation and the Tablet of the Covenant, all say to her in unison in the Hebrew tongue: 'She is truly the Burning Bush, the Holy of Holies; from the vessel of her womb the cluster of wine was poured, and within her the Eucharist was instituted."
❤ 112 🥰 10 👍 1 😁 1
23 August 2025
ኪ
20:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኪ
ኪዳን ዘኢየሱስ 16.08.2025 20:41:42
በጌታ ቀን በመሠዊያው እንገናኝ ማንም እንዳይቀር ክርስቶስን እንቀበለው ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ!

እኔ እሑድ አስቀድሼ ቆርባለሁ እናንተስ?

የሚል ቻሌንጅ ጀምሬያለሁ!
❤ 134 🤗 12 👍 4 😁 2 🙏 2
25 August 2025
ኪ
10:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ ዛሬም አንድ ጥያቄ ተጠየቁ፡

ከብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ ኢየሱስ ከተነገሩ ትንቢቶች ውስጥ በጣም የምንወደው አንድ ትንቢት አለ። ኢሳ 7፡14 "ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች"።

መጀመሪያ ስናየው ግልጽ የክርስቶስ ትንቢት ይመስላል ነገር ግን አውዱን ስታዩት ግን ሌላ ሆኖ ታገኙታላችሁ። በይሁዳ ላይ አካዝ በነገሠ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል (ኤፍሬም) ንጉሥ ፋቁኤ ይሁዳን ሊወጉ ተነሡበት። ይሄን ጊዜ እግዚአብሔር ነቢዩ ኢሳይያስን ከልጁ ከያሱብ ጋር ሆኖ አካዝን እንዲያረጋጋው "ኤፍሬም ይወድቃል ሶርያም አይጸናም" የሚል መልእክት ይልክበታል። ኢሳይያስም ይህ እንደሚሆን እንዲያረጋግጥ ምልክትን ከእግዚአብሔር እንዲለምን አካዝን ቢነግረውም አካዝ ግን "ምልክትን አልለምንም እግዚአብሔርን አልፈታተንም" በማለት መለሰ። ኢሳይያስ ግን የዳዊት ቤት ሆይ ስሙ አምላኬን አታድክሙት ስሙ ምልክት ይሰጣችኋል በማለት ምልክቱም "ከድንግል የሚወለደው አማኑኤል" እንደሆነ ይነግራቸዋል። እነሆም ይህ ሕፃን ክፉንና ደጉን መምረጥ ገና ሳያውቅ ሶርያ እና ኤፍሬም ባድማ ይሆናሉ የተሰጠውም ምልክት ይህ ነው።

ዕብራይስጡ ላይ ካያችሁትም ድንግል የሚለውን "עַלְמָ֗ה (አልማ)" ይለዋል ትርጉሙም ወጣት ሴት ማለት ነው። ዕብራይስጡ ድንግል ማለት ቢፈልግ ከወጣት ሴቶች ደናግል የሆኑትን መለያ ቃል "בְּתוּלָה (በቱላህ) ነበረው። ሀሳቡ አልማ ድንግል ሴትን ወክሎ ሊገባ ይችላል ግን specific አይደለም ለጋብቻ የደረሰች ወጣት ሴት ማለት ነውና። በቱላህ ግን specifically ድንግል ሴት ማለት ነው። ስለዚህ ከአውዱ አንጻር ስናየው በዛ ዘመን ለጋብቻ የደረሰች ወጣት ሴት ነበረች አግብታ ወለደች ስሙንም አማኑኤል አለችው ሕጻኑም ገና ክፉና ደግ እንኳን ሳይለይ ኤፍሬምና ሶርያ ወደቁ ይህ ለአይሁድም ምልክት ሆናቸው ተብሎ ይተረጎማል እንጂ ይህ ስለመሢሑ ትንቢትም አይደለም ፣ ድንግል ሴት ያለ ወንድ ዘር ስለመውለዷ ትንቢትም አይደለም።

ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ?
❤ 26 🤔 9 😢 7
ኪ
19:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
"May she then rest in peace with her husband. She was married to no other man either before or after him, and in serving him she brought forth fruit for you by patience, to win him for you in the end. Inspire others, my Lord, my God, inspire your servants who are my brethren, your children who are my masters, whom I now serve with heart and voice and pen, that as many of them as read this may remember Monnica, your servant, at your altar, along with Patricius, sometime her husband." St. Augustine

O Lord Jesus Christ Son of God by the prayerd of St. Monica have mercy on me a sinner.

She asked only to be remembered at the altar, yet now altars are dedicated in her name. O God, how wondrously You have glorified Your saints! ❤️
❤ 56 👍 11
7 September 2025
ኪ
14:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዛሬዋ ቀን 3 ልጆችን ወደ ቤተክርስቲያን ተቀብለናል።

የእግዚአብሔር ልጅነት ምሥጢር ታላቅ ነው 🤗
🥰 159 ❤ 59 👍 5 👏 1
14:41
8 September 2025
ኪ
16:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
የተሳሳተ የቀኖና (Penance) አረዳድ

ያው እንደ ሚታወቀው ከንስሐ አባቶቻችን ዘንድ ከተናዘዝን በኋላ ንስሐ አባታችን መፈጸም ያለብንን ቀኖና ይሰጠናል (ስግደት ፣ ጾም ፣ ጸሎት ፣ ምጽዋት ወዘተ)። ፍትሐት ዘወልድ (Absolution) ከቀኖናው በፊት በኑዛዜ ጊዜም አልያም ቀኖናው ከተፈጸመ በኋላ ሊጸለይልን ይችላል።

እዚህ ላይ ግን ብዙህ ሰው የቀኖናን ዓላማ የሳተ ይመስላል ፤ የቀኖና ዓላማ ወደ ኃጢአት ካስገባን መንገድ ተመልሰን በመንፈሳዊ ልምምድ ወደ ተሻለው መንገድ እንድንሔድ ነው በዚህም ምክንያት መንፈሳዊውን ሕይወት እንለማመዳለን። ብዙህ ሰዎች ግን ይህንን ስተው ቀኖና ለሠሩት ኃጢአት ክፍያ ሲመስላቸው ታዝቤያለሁ ይህ ፍጹም የተሳሳተ ግንዛቤ ነው የኃጢአታችንን ክፍያ ክርስቶስ በመስቀል ከፍሏል እንጂ እኛስ ልንከፍል አንችልም ስለዚህም የኃጢአት ሥርየት የሚገኘው እኛ በምንፈጽማቸው ነገሮች ሳይሆን በጸጋ ክርስቶስን ስንካፈለው ነው።

የኃጢአትን ሥርየት ጸጋ የሰጠን ኃጢአታችንን በመስቀል የተሸከመ ጌታ ይመስገን!
❤ 191 👏 15 👍 5 🥰 2 😱 2 ⚡ 1
10 September 2025
ኪ
11:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
አዲሱን ዓመት በክርስቶስ!

ያለፈው ዓመት ክፉም ሆነ መልካም ብዙ ነገሮችን ይዞልን የመጨረሻው ቀን ደርሰናል። ስላለፈው ዓመት እና ስላደለን በረከት ሁሉ ጌታችንን እናመስግነው ካለመኖር ሁሉ መኖር መልካም ነውና በመኖራችንም ከእርሱ መኖር መልካምነት ተሳትፈናልና ፤ በችግር እና በፈተናዎች ያሳለፍንም ስለ ፈተናዎቹ ጌታችንን እናመስግነው በፈተናዎቹ ውስጥ ሠርቶናልና ከመስቀሉ በረከትም አካፍሎናልና። በሁሉም ነገር ፣ ለሁሉም ነገር ፣ ስለ ሁሉም ነገር እናመስግነው ለተመረጡት ሁሉ ለበጎ ነውና!

የሚመጣውን አዲሱን ዓመትም በክርስቶስ እንደ ክርስቲያን እንቀበለው ፣ ባሕላዊ ክርስቲያኖች ብቻ አንሁን በእውነትም ክርስቲያኖች እንሁን እንጂ ፤ አብሮ ተሰብስቦ መብላት ፣ መጠጣት ፣ መደሰት መልካም ነው ነገር ግን ክርስቲያንነት ከዚህም የላቀ ነው ለእኛ ምግባችን ፣ መጠጣችን ፣ ደስታችን ፣ አባታችን ፣ እናታችን ሁሉ ነገራችን ክርስቶስ ነው! ክርስቶስን የያዘ ሁሉን ያተርፋል ፤ ክርስቶስን ያጣ ግን ዓለምን ሁሉ እንኳን ቢያተርፍ የከሰረ ነው ስለዚህም አዲሱን ዓመት በክርስቶስ ተባርከን እንድንጀምር በቁርባን ከእርሱ ጋር እንዋሐድ በክርስትና አንድነት አንዱን ክርስቶስ በመቀበል እንጀምር ከዚያም የተቀበልነውን ክርስቶስ ለዓለም እንመስክር። የዓለሙን እውነተኛ ብርሃን ክርስቶስ ተቀብለን እኛም ለዓለም የክርስቶስን ብርሃን የምናበራ በተራራ ላይ ያለች ከተማ እንሁን ልንሠወር አይቻልንምና።

በአዲሱ ዓመት ቁርባናዊ ሕይወት እንኑር የተሰጠንን ክርስቶስ ተቀብለን እኛም ለቤተክርስቲያናችን ፣ ለቤተሰባችን ፣ ለማኅበረሰባችን ፣ እንዲሁም ለሀገራችን እራሳችንን እንስጥ የመሰጠት ሕይወትን እንኑር ፤ በሕይወታችን የክርስቶስ ክብር ይገለጥ "አቤት ክርስቲያኖች እንዲህ ናቸው እንዴ የመምህራቸው የክርስቶስ ልጆች ናቸው" ተብለን ዓለም እስኪደነቅ ድረስ ክርስቲያን እንሁን ፤ ነገር ግን በሥራዎቻችን እኛ አንክበርበት ክርስቶስ ይክበርበት እንጂ መልካሙን ሥራችንን አይተው ሰማያዊ አባታችንን ያከብሩ ዘንድ!

መልካም አዲስ ዓመት!
❤ 133 🥰 2
ኪ
21:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
ስለተሳተፋችሁ እናመሰግናለን ዓመቱ ግን ለእኛ ስኬታማ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው የአሁኑ አመላለስ 😒
🤣 18 😢 15 ❤ 4 😁 2 👍 1
11 September 2025
ኪ
10:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
የአዲስ ዓመት  የወንጌል ንባብ

ሉቃስ 4:
14 ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ።
15 እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።
16 ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።
17 -19 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።
20 መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።
21 እርሱም። ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር።
22 ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ። ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ይሉ ነበር።
23 እርሱም። ያለ ጥርጥር ይህን ምሳሌ። ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ አላቸው።
24 እንዲህም አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ ነቢይ በገዛ አገሩ ከቶ አይወደድም።
25 ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ በምድር ሁሉ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤
26 ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም።
27 በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም።
28 በምኵራብም የነበሩ ሁሉ ይህን ሰምተው ቍጣ ሞላባቸው፥ ተነሥተውም ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፥
29 ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤
30 እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ።

የተወደደችው የጌታ ዓመት በእርሱ ምሕረት መጥታለች እንኳን አደረሳችሁ!

2018 ዓመተ ምሕረት
1742 ዓመተ ሰማእታት

Feast of Nayrouz
❤ 84 👍 3 🙏 2
ኪ
19:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
1. እሥራኤልን በአምደ ደመና እና በእሳት እየመራ ወደ ምድረ ርስት ያስገባቸው የእግዚአብሔር መልአክ ማነው? ጥቅሱስ የት ይገኛል?
2. አንጥያኮስ ኤጲፋንዮስ ቤተመቅደሱን ባረከሰ ሕግን ባፈረሰ እና እስራኤልን ግሪካዊ ለማድረግ ሲሞክር እሱን ተቃውሞ አይሁድን የመራውና በጦርነትም ሰማእት የሆነው ሰው ማን ይባላል? ታሪኩስ በየትኛውም መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል?
3. በኦርቶሶክሳዊ ነገረ ክርስቶስ ትምህርት መሠረት ክርስቶስን ከተዋሕዶ በፊት 2 ከተዋሕዶ በኋላ 1 እንለዋለን "በፊት" እና "በኋላ" የሚሉት ቃላት ምንንን ያመላክታሉ? ከ2 ወደ አንድ ስንልስ ምኑ ነው ከሁለት ወደ አንድ የመጣው? ይሄኛው ጥያቄ በደምብ ይብራራ
❤ 18 👍 3
12 September 2025
ኪ
20:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሁዲነት በክርስትና

ደስ የማይል ርእስ ቢሆንም ግን እንደዚህ አይነት ርእሶች መነሳት ስላለባቸው አነሳለሁ። የይሁዲ እምነት እንደሚታወቀው ከ national identity ጋር የተያያዘ እምነት ነው ዋና ዓላማውም ዓለምን ወደ እግዚአብሔር አምልኮ ማምጣት ሳይሆን የነበረውን national identity ሳይጠፋ ማስቀጠል ነው።

ይህ ግን በክርስቶስ መምጣት ተለወጠ ክርስትና የይሁዲ እምነት ፍጻሜ ነውና ክርስቶስ ተከታዮቹ ዓለምን ወደ እግዚአብሔር አምልኮ እንዲያመጡ ታላቁ ተልእኮ ተሰጣቸው ይህም "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው" የሚለው ትእዛዝ ነው ፤ ዓለምም ሁሉ ክርስቶስን ሳይሰማ ፍጻሜው አይሆንም። ታድያ ሐዋርያትም ይህንን ትእዛዝ ከጌታ ተቀብለው በዓለም ሁሉ አንድም የማይድን እስካይቀር ድረስ ወንጌል ሰበኩ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም መሠረቱ። እውነተኛ የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተክርስቲያንም ይህን የክርስቶስን ታላቅ ተልእኮ ተቀብላ ለሕዝቡ ሁሉ ወንጌልን መስበክ አለባት፤ እንደ መምህራችን ጳውሎስ ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ እያለች ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ለማድረስ ከምንም በላይ መሥራት አለባት።

አሁን አሁን ግን በተለይ ከኦሬንታል ኦርቶዶክስ ኅብረት ይሁዲነት በክርስትና ይታያል ማለትም ክርስትናን እንደ national identity በማየት እምነትን ባሕላዊ አድርገን ታላቁን ተልእኮ ዘንግተናል። ከሁሉም በላይ የሚያስቆጨው እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አቅም አፍሪካን ሁሉ በወንጌል ማጥለቅለቅ እንችል ነበር ሊያውም አፍሪካዊ identityን በማስጠበቅ እኛ ግን ኦርቶዶክሳዊነትን ፣ ከኢትዮጵያዊነት ጋር በጣም ከመያዛችን የተነሣ እምነታችንን ሐገራዊ ማንነት ብቻ አድርገን ይዘን ተቀምጠናል። ይበልጥ ከዚህ በላይ የሚያቆጨው ደግሞ ኢትዮጵያውያን በmass immigration ወደ አሜሪካ ቢገቡም አሁንም ቢሆን በአሜሪካ የምትገኘው የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወንጌልን በኢንጊሊዘኛው ሆነ በአከባቢው ቋንቋ ከማስፋፋት ይልቅ በኢትዮጵውያን ዲያስፖራ ብቻ ተወስነን አለን። ይህ ችግር በኢትዮጵያ ብቻ ያለ አይደለም በጠቃላይ በኦሬንታል ኦርቶዶክስ ኅብረት እንጂ ፤ ወደ አርመንም ፣ ሶርያና ግብጽ ብንሔድም ሁኔታው ተመሳሳይ ሆኖ እናገኘዋለን። (አሁን ላይ ግን በግብጽ ያለችው ቤተክርስቲያናችን ይህን ችግር ተገንዝባ ወንጌል ስርጭት ላይ ጥሩ እየሠራች ይመስላል ለዚህም ነው በውጪው ዓለም ኦሬንታል ኦርቶዶክስ ሲባል በቁጥር ብዙዎች እኛ ብንሆንም በሰዉ ዘንድ ግን መጀመሪያ ኮፕቲክ ምትመጣው።)

ይህንን እናተውል አሁን ላይ ታላቁን ተልእኮ የረሳች ቤተክርስቲያን የተመሠረተችበትን ዓላማ የረሳች ቤተክርስቲያን ናት የቤተክርስቲያን ትልቁ ዓላማ ነፍሳትን ማዳን ነው እንጂ national identity መገንባት አይደለም። National identity በራሱ መጥፎ ሆኖ አይደለም ነገር ግን ከታላቁ ተልእኮ ይበልጥ ቦታን የሚይዝ ከሆነ ዓላማውን የሳተ ይሆንና አዘቅት ውስጥ ይከተናል። ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እና እኅተ ማርያምን የመሳስሉ ሃይማኖት ማለት ሐገር የሚመስላቸውን ሰዎች ያፈራነው።

ስለዚህ አሁን ላይ ምን እናርግ? በቻልነው መጠን ወንጌልን ለማድረስ እንሥራ ከምንም ነገር በላይ ለነፍሳት መዳን እንጨነቅ ፤ ከነፍሳት መዳን በኋላ ያሉት ዓላማዎች ሁሉ secondary ናቸው የቤተክርስቲያን የመጀመሪያና ቀዳሚ ዓላማዋ ታላቁ ተልእኮ ነውና! ይህ ምን ምንን ማካተት አለበት የሚሉትን ነጥቦች ወደፊት እናያለን።
❤ 97 👍 11 🔥 8 👎 1
13 September 2025
ኪ
20:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
የማትቆርቡ ውጡ ☠️

ጻኡ ንኡሰ ክርስቲያን ሲባል የማትቆርቡ መውጣት እንዳለባችሁ ታውቃላችኋ 😃
❤ 48 🤔 12 😁 10 🙉 9 😢 8
ኪ
23:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለማንኛውም ወገኔ እንቁረብ

እኔ በጌታ ቀን አስቀድሼ እቆርባለሁ እናንተስ?
🔥 64 ❤ 23 🥰 6 ❤‍🔥 3
14 September 2025
ኪ
19:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከምርጡ ወንድሜ የተሰጠኝ ስጦታ ዛሬ አስባርኬ ቤቴ ገብተዋል

My Lord and Saviour Jesus Christ the Pantocrator ❤️
St. Athanasius, My Patron Saint ❤️
St. Paul the Apostle , the beloved evangelist ❤️
St. Augustine of Hippo, the Son of tears ❤️

እናንተም እንዲሠራላችሁ ከፈለጋችሁ በዚህ እዘዙት 👉 @John_Chrysostom1
❤ 83 ❤‍🔥 6 😁 1
16 September 2025
ኪ
08:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/alMasih23

እስቲ የዚህን ወንድማችንን ቻናል ተቀላቀሉ እስልምናን መዝናለሁ ብሎ ተነሥቶላችኋል የሚያሳዝነው ግን ክርስትናን በእልምና ማስመዘኑ ነው እስቲ ግቡና የተሻለ ስም አውጣ በሉት 😄

By the way በቅርቡ አንድ ላይ በእልምልና ትችት የሚነሳባቸው ትምህርተ ሥላሴ ፣ ነገረ ክርስቶስ የመሳሰሉት ላይ ለመሥራት ስላቀድን ሁላችሁም ተቀላቀሉት አታሳፍሩኝም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
🔥 20 ❤ 10 👍 5
ኪ
09:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
By the way በአሁኑ ቅዳሜ ነገረ ሥላሴ ላይ ትምህርት እንጀምራለን እስቲ እኛም ቪዲዮ እንሠራለን እናንተም ሥሩ ሙስሊሞችም ይምጡ
👏 61 ❤ 22 🔥 3
ኪ
21:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች የበፊቱ አካውንቴ ስለሌለ እኔን ማውራት ምትፈልጉ በዚህ ቻናል direct message ብቻ አዋሩኝ ሌላ አድሚን ማየት እንዳይችል ስላረኩ እኔ ብቻ ነኝ ማየው።
❤ 37 👍 2
17 September 2025
ኪ
10:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
The Departure of St. Dioscorus, 25th Pope of Alexandria
On this day of the year 451 AD, the blessed father and the great champion of Orthodoxy, St. Dioscorus, 25th Pope of Alexandria, departed. His departure took place on the island of Gagra after he had fought the good fight defending the Orthodox faith.

ኦርቶዶክሳዊውን እምነት በመለካውያን ፊት የጠበቀ ከሁለት ዓመታት በፊት ከእርሱ ጋር የነበሩት አሁን ፖለቲካው ሲለወጥ ንጉሡን ሲደግፉ እርሱ ግን ለጸናው ኦርቶዶክሳዊ እምነት የቆመ! በቄርሎስ እግር የተተካ ቄርሎሳዊ መለካውያንን የተቃወመ ኦርቶዶክሳዊ!
🔥 73 ❤ 50 😍 2 😐 1
19 September 2025
ኪ
12:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዘለዓለማዊ ምልጃ

በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ክርስቶስ ምልጃ ለማውራት ትንሽ አቸጋሪ ካደረጉት ነገሮች ውስጥ "ምልጃ" የሚለው ቃል ከያዘው ትርጉም የተነሳ ነው። ብዙ ጊዜ ምልጃ የሚለውን ቃል ሰው የሚረዳው ኃይል የሌለው ሰው ላጠፋው አካል ሌላ ኃይል ላለው ሰው ሲማልድለት (ሲለምንለት) ነው። ለሰዎች ሲነገር ይህ የምልጃ ትርጉም ትክክል ነው አንድ ክርስቲያን በራሱ ኃጢአትን ማስተሥረይ አይችልም ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣፋውን ሰው ይቅር እንዲለው መማለድ (መለመን) ግን ይችላል።

ለክርስቶስ ምልጃ ሲነገር ግን እንደዛ አይደለም እርሱ በመለኮቱ ሁሉን ማስፈጸም የሚችል አምላክ ነው ፣ ነገር ግን ስለእኛ መዳን የባርያን መልክ ይዞ መጥቷልና ስለእኛም ሊማልድ ለዘለዓለም ይኖራል። እስቲ በዚህ ጉዳይ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ምንም ፍርሃት እንዳይኖር አንድ አንድ አባቶች ልጥቀስላችሁና ቀጣይ እንጽፍበታለን፡

"Being the Word of the Father and above all, he alone consequently was both able to recreate the universe and was worthy to suffer on behalf of all and to intercede for all before the Father" Athanasius of Alexandria: On the Incarnation 8.

"የአብ ቃል በመሆኑና ከሁሉ በላይ ከፍ ያለ በመሆኑ፥ ዓለሙን በሙላት የማደስ ኃይልም ሆነ ስለ ሰው ልጆች ሁሉ መከራን ተቀብሎ በአብ ፊት ሊያማልድ የሚገባውና ብቃቱም የነበረው እርሱ ብቻ ነበር።"
አትናቴዎስ ዘእስክድርያ፦ "በእንተ ተሠግዎተ ቃል" ምዕራፍ ፰።

"1. No greater gift could God have given to men than in making His Word, by which He created all things, their Head, and joining them to Him as His members: that the Son of God might become also the Son of man, one God with the Father, one Man with men; so that when we speak to God in prayer for mercy, we do not separate the Son from Him; and when the Body of the Son prays, it separates not its Head from itself: and it is one Saviour of His Body, our Lord Jesus Christ, the Son of God, who both prays for us, and prays in us, and is prayed to by us. He prays for us, as our Priest; He prays in us, as our Head; He is prayed to by us, as our God." St. Augustine: Exposition on Psalm 86

"፩. እግዚአብሔር ለሰዎች ከሰጣቸው ስጦታዎች ሁሉ፥ ሁሉን የፈጠረበትን ቃሉን ራስ አድርጎ እኛን ደግሞ አባላቱ አድርጎ ከእርሱ ጋር ከመቀላቀል የበለጠ ታላቅ ስጦታ ሊሰጥ አልቻለም። ይህም የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ እንዲሆን ነው፤ ከአብ ጋር አንድ አምላክ፥ ከሰዎች ጋርም አንድ ሰው።
ስለዚህ ምሕረትን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ስንጸልይ ልጁን ከእርሱ አንለየውም፤ የልጁ ሥጋ (ቤተክርስቲያን) ስትጸልይም ራሷን ከራሱ (ከክርስቶስ) አትለይም። ይልቁንም የሥጋው አንድ መድኃኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ስለ እኛ ይጸልያል፥ በውስጣችን ይጸልያል፥ እኛም ወደ እርሱ እንጸልያለን። እንደ ካህናችን ሆኖ ስለ እኛ ይጸልያል፤ እንደ ራሳችን ሆኖ በውስጣችን ይጸልያል፤ እንደ አምላካችን ሆኖ ደግሞ ጸሎታችንን ይቀበላል።"
ቅዱስ አውግስጢኖስ ፦ በመዝሙር ፹፮ (86) ላይ የተሰጠ ማብራሪያ።

"5. But the Saviour comes in various forms to each man for his profit. For to those who have need of gladness He becomes a Vine; and to those who want to enter in He stands as a Door; and to those who need to offer up their prayers He stands a mediating High Priest. Again, to those who have sins He becomes a Sheep, that He may be sacrificed for them. He is made all things to all men 1 Corinthians 9:22, remaining in His own nature what He is."

Cyril of Jerusalem: Catechetical Lectures, Lecture 10, Section 14

"፭. መድኃኒቱ ግን ለእያንዳንዱ ሰው እንደየጥቅሙ በተለያየ መልክ ይመጣለታል። ደስታ ለሚያስፈልጋቸው የወይን ግንድ ይሆናል፤ መግባት ለሚሹትም በር ይሆናል፤ ጸሎታቸውን ማቅረብ ለሚገባቸው ደግሞ የሚያማልድ ሊቀ ካህናት ይሆናል። እንደዚሁም ኃጢአት ላለባቸው፥ ስለ እነርሱ እንዲሠዋ በግ ይሆንላቸዋል።
በባሕርይው እርሱ የሆነውን ሳይለወጥ፥ ለሁሉም ነገር ሁሉን ይሆናል (1ኛ ቆሮ 9፡22)።"
ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፦ የትምህርተ ክርስትና ንግግሮች፣ ንግግር ፲ ክፍል ፲፬።

"He gives as the Most High, He prays as man. The one is the office of the Creator, the other of a Redeemer. Be the gifts as distinct as they may, yet the Giver is one, for it was fitting that our Maker should be our Redeemer."
Ambrose of Milan :On the Christian Faith, Book 3, Chapter 4.  

"እንደ ልዑል ሆኖ ይሰጣል፤ እንደ ሰው ሆኖ ይጸልያል። አንዱ የፈጣሪ ሥራ ሲሆን፥ ሌላኛው ደግሞ የአዳኝ ሥራ ነው። ስጦታዎቹ ምንም ያህል የተለያዩ ቢሆኑም፥ ሰጪው ግን አንድ ነው። ምክንያቱም የፈጠረን እርሱ አዳኛችንም መሆኑ ተገቢ ነበርና።"
አምብሮስ ዘሚላን፦ "ስለ ክርስቲያናዊ እምነት" መጽሐፍ ፫፥ ምዕራፍ ፬።
❤ 41
12:15
" But Christ Who manifested Himself in the last times above the types and figures of the Law, at once our High Priest and Mediator, prays for us as Man; and at the same time is ever ready to cooperate with God the Father, Who distributes good gifts to those who are worthy... He then prays for us as Man, and also unites in distributing good gifts to us as God. For He, being a holy High Priest, blameless and undefiled, offered Himself not for His own weakness, as was the custom of those to whom was allotted the duty of sacrificing according to the Law, but rather for the salvation of our souls, and that once for all, because of our sin, and is an Advocate for us: And He is the propitiation for our sins, as John saith; and not for ours only, but also for the whole world." Cyril of Alexandria: Commentary on the Gospel of John, Book 11, Chapter 10

"በመጨረሻው ዘመን ከሕጉ ምሳሌዎችና ጥላዎች በላይ የተገለጠው ክርስቶስ ግን፥ በአንድ ጊዜ ሊቀ ካህናችንና መካከለኛችን ሆኖ እንደ ሰው ስለ እኛ ይጸልያል፤ በዚያውም ጊዜ ደግሞ ለሚገባቸው መልካም ስጦታዎችን ከሚያድለው ከእግዚአብሔር አብ ጋር ለመተባበር ሁልጊዜ ዝግጁ ነው። ስለዚህ እንደ ሰው ስለ እኛ ይጸልያል፤ እንደ አምላክነቱ ደግሞ መልካም ስጦታዎችን ለእኛ በማደል ይተባበራል። ምክንያቱም እርሱ ቅዱስ፣ ነውር የሌለበትና ያልረከሰ ሊቀ ካህናት እንደመሆኑ መጠን፥ እንደ ሕጉ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ እንደተሾሙት ካህናት ልማድ ስለ ራሱ ድካም ሳይሆን፣ ይልቁንም ስለ ኃጢአታችን ለነፍሳችን መዳን ሲል ራሱን አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አቅርቧል፤ እርሱም ጠበቃችን ነው። ዮሐንስም እንደሚለው፥ እርሱ የኃጢአታችን ማስተስረያ ነው፤ ስለ እኛ ብቻም ሳይሆን ስለ ዓለሙ ሁሉ ጭምር ነው።"

ቄርሎስ ዘእስክንድርያ፦ በዮሐንስ ወንጌል ላይ የተሰጠ ትርጓሜ፣ መጽሐፍ ፲፩፥ ምዕራፍ ፲።

ስለአማርኛው ትርጉም ይቅርታ እንግዲህ ሁሉንም መተርጎም ስለሚከብድ ከትንሽ ማስተካከያ ጋር በA.I ነው የተተረጎመው ግን ሃሳቡን ማግኘት ይቻላል ብዬ አስባለሁ።
❤ 39 🔥 5
ኪ
18:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMAULqGAj/

እስቲ ከንትርክ ስገላግላችሁ

በቲክቶክ ተከስተናል
👍 21 🔥 9 ❤ 7
20 September 2025
ኪ
09:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
"It is a priest's duty to offer something, and, according to the Law, to enter into the holy places by means of blood; seeing, then, that God had rejected the blood of bulls and goats, this High Priest was indeed bound to make passage and entry into the holy of holies in heaven through His own blood, in order that He might be the everlasting propitiation for our sins."

St. Ambrose of Milan: On the Christian Faith, Book 3, Chapter 12.

"እንደ ሕጉ [መሥዋዕትን] ማቅረብና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በደም መግባት የካህን ሥራ ነው። ነገር ግን ይህ ሊቀ ካህናት (ኢየሱስ ክርስቶስ) እግዚአብሔር የፍየሎችና የጊደሮችን ደም አለመቀበሉን ባየ ጊዜ የኃጢአታችን ዘለዓለማዊ ማስተሥረያ ይሆን ዘንድ በሰማይ ባለችው ቅድስተ ቅዱሳን በደሙ ገባ" ቅዱስ አምብሮስ ዘሚላን

መልካም ቀን
❤‍🔥 45 ❤ 23 🔥 1
ኪ
18:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ምሥጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን
ማታ 3፡00

በቲክቶክ፡ ማንም ሰው እንዳይቀር
❤ 50 👍 1
ኪ
23:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
የተከታተላችሁ በደምብ ተጠራሩ እና ቀጣይ ረቡዕ 3 ሰአት ተገኙ በዛውም መስተካከል ያለበትን ነገሮች ንገሩን

ለነገም ግን እናስቀድስ እንቁረብ
👍 31 ❤ 17
21 September 2025
ኪ
20:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 45
22 September 2025
ኪ
09:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
የኒቅያ አንቀጸ ሃይማኖት

እንደምናውቀው የኒቅያ አንቀጸ ሃይማኖት የእምነታችን መሠረት ነው አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን የሚመሠክረውም ሆነ ክርስቲያን ከሆነ በኋላ በየቀኑ የሚጸልየው ይህን አንቀጸ ሃይማኖት ነው። ይህም ብቻ አይደለም በቤተክርስቲያናችን ሁሉም ቅዳሴዎች ላይ ይታወጃል (አንዳንድ ቅዳሴያት ላይ ግን በእርሱ ቦታ አመክንዮ ዘሐዋርያት ይገባል።) ይህ አንቀጽ አስቀድሞ በኒቅያ ጉባኤ ተዘጋጅቶ በቁስጥንጥያ ጉባኤ ተሻሽሎ በግሪክ የተጻፈ ነው። ወደ ግእዝ ትርጉም የተሠራለት ሲሆን የግእዙ ትርጉም ጥሩ ቢሆንም ብዙዎቻችን በውዳሴ ማርያም የምናውቀው አማርኛ version ግን አንዳንድ ችግሮች አሉበት። ስለዚህ እስቲ ከዚህ በታች አማርኛ ትርጉም ከግሪኩ ጋር እንዲገጥም ለማድረግ ሞክሬያለሁ ይመልከቱት።

Areas of Issues:
παντοκράτορα (pantokratora): አማርኛው ላይ "ሁሉን የፈጠረ" ተደርጎ ተተርጉሟል ነገር ግን "ሁሉን የሚችል" ወይም "ሁሉን የሚይዝ (አሀዜ ኩሉ)" ቢባል የተሻለ ነው።

τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων (tón ek toú Patrós gennithénta pró pánton tón aiónon)፡ አማርኛው ላይ "ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር በነበረ" ተደርጎ ተተርጉሟል ነገር ግን "ከዘመናት/ከዓለማት ሁሉ በፊት ከአብ በተወለደ" ተደርጎ ቢተረጎም የተሻለ ነው።

ὁμοούσιον τῷ Πατρί (omooúsion tó Patrí)፡ አማርኛው ላይ "ከአብ ጋር በመለኮቱ የሚስተካከል" ተደርጎ ተተርጉሟል ነገር ግን "ከአብ ጋር በባሕርይ አንድ" ተደርጎ ቢተረጎም የተሻለ ነው።

σαρκωθέντα... ἐνανθρωπήσαντα (sarkothénta... enanthropísanta)፡ አማርኛው ላይ "ፍጹም ሰው ሆነ" ተደርጎ ተተርሟል ነገር ግን "ሥጋን ነሥቶ ሰው ሆነ (ተሰብአ ወተሰገወ)" ተደርጎ ቢተረጎም የተሻለ ነው።

εἰς μίαν ἁγίαν καθολικὴν καὶ ἀποστολικὴν ἐκκλησίαν (eis mían agían katholikín kaí apostolikín ekklisían)፡ አማርኛው ላይ "ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ክብርት ቤተክርስቲያን" ተብሎ ተተርጉሟል ነገር ግን "በአንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ ቢተረጎም የተሻለ ነው።

በአጠቃላይ እንዲህ ቀርቧል

ሁሉን በሚችል፣ ሰማይና ምድርን፣ የሚታዩትንና የማይታዩትንም ሁሉ በፈጠረ በአንድ አምላክ [እግዚአብሔር] አብ እናምናለን።

ከዘመናት ሁሉ በፊት ከአብ በተወለደ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምንለን፣
ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣
ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ፣
የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፣
ከአብ ጋር ባሕርዩ አንድ በሆነ፣
በእርሱም ሁሉ ነገር በሆነ፤
ስለ እኛ ስለ ሰዎችና ስለ መዳናችን ከሰማያት በወረደው፣
በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያምም ሥጋን ነሥቶ፣
ሰውም በሆነው
፣
ስለ እኛም በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን በተሰቀለው፣
መከራንም በተቀበለው፣ በተቀበረውም፣
በሦስተኛውም ቀን በመጻሕፍት እንደተጻፈው በተነሣው፣
ወደ ሰማያትም ባረገው፣
በአብም ቀኝ በተቀመጠው፣
በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በክብር ዳግመኛ በሚመጣው፣
ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው፤

ጌታና ሕይወት ሰጪ በሆነው፣
ከአብ በሚሠርጸው፣
ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት በሚሰገድለትና በሚከበር፣
በነቢያት በተናገረው በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን።

በአንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊት እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያንም (እናምናለን)።

ለኃጢአት ሥርየት የምትሆን አንዲት ጥምቀትን እንመሰክራለን።

የሙታንን ትንሣኤ ተስፋ እናደርጋለን ፣
የሚመጣውንም ዘመን ሕይወት። አሜን።
❤ 56 👍 6 ❤‍🔥 3 👏 2
ኪ
10:40
ኪዳን ዘኢየሱስ
እነዚህ ሁሉ ችግር ያስከትላሉ ለማለት አይደለም ነገር ግን ትንሽ ከተጻፉበት አውድ ስለሳቱ ነው። ለምሳሌ እያንዳንዱን ላሳያችሁ "ሁሉን የፈጠረ" የሚለው ችግር ስለሚያስከትል አይደለም ነገር ግን አባቶች ፓንቶክራቶር ሲሉ ይበልጥ መግለጽ የፈለጉት ሃሳብ እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል ፣ ሁሉ በእርሱ ቁጥጥር ያለ ፣ ሁሉን የሚይዝ መሆኑን ለማመልከት ነው። ሁሉን መፍጠሩንማ በቀጣዩ ሐረግ ገልጽውታል።

"ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር በነበረ" የሚለውም ትንሽ ሃሳብ ስቷል አዎ ክርስቶስ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ ጋር ነበረ አባቶች ግን ማሳየት የፈለጉት የወልድ ልደቱ ከዘመናት ሁሉ በፊት ከአብ መሆኑንና መወለዱም በጊዜ ውስጥ አለመሆኑን ለማሳየት ነው። ያለበዚያ ዓለም ሳይፈጠር በፊት ከአብ ጋር ነበረ የአብ የመጀመሪያ ፍጡር ነው የሚለውን የአርዮሳውያን ሃሳብ ብቻውን አይመክትም።

"በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚስተካከል" የሚለው ላይም አዎ ክርስቶስ በመለኮቱ ከአብ ጋር የተካከለ ነው ነገር ግን የኒቅያ አባቶች "ሆሞኦሲዮስ" ሲሉ መግለጽ የፈለጉት መተካከሉን ብቻ ሳይሆን ከአብ የተለየ ባሕርይ የሌለው ከአብ ጋር በባሕርይ አንድ መሆኑን ነው። እንጂ Semi-Arians የሚባሉ "ሆሚኦሲዮስ"የሚለውን ሚቀበሉ ነበሩ ማለት ከአብ ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ አለው ማለት ነው። ለአባቶች ግን ይህ በቂ አልነበረም ይልቅስ "ተመሳሳይ እና የሚተካከል ባሕርይ ብቻ ሳይሆን አንድ ባሕርይ" ማለት ነበረባቸው።

"ፍጹም ሰው ሆነ" የሚለው ችግር ኖሮበት ሳይሆን "ተሰብዓ ወተሰገወ/ Incarnated and became Man" የምትለዋ በግሪክም ፣ በግእዝም ፣ በኢንጊሊዘኛ ያለችዋ ፎርሙላ በአማርኛም እንዳትቀር ነው።

"ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ክብርት ቤተክርስቲያን" የሚለውም ችግር ኖሮበት ሳይሆን አባቶች "ካቶሊኬ" ሲሉ "በሁሉ ያለች" ለማለት ነው እንጂ ከሁሉ በላይ መሆኗን ለመግለጽ አይደለም ይህም "ኩላዊት" የሚለው ይበልጥ ይገልጽዋል። "አጊያን" የሚለው ደግሞ ቀጥታ ትርጉሙ "ቅድስት" ሆኖ ሳለ ለምን "ክብርት" እንደተባለ ባይገባኝም (በግእዙም ቅድስት ነው የሚለው) ችግር በመሆኑ ሳይሆን ትክክለኛው ቃል ቢገባ የተሻለ ስለሆነ ነው።
❤ 42 🥰 8 🤷‍♀ 2 🙏 2
ኪ
15:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
Assembly of the Third General Council at Ephesus for Trying Nestor, Archbishop of Constantinople

On this day of the year 431 A.D. assembled the Holy Council at Ephesus which was attended by two hundred bishops. It was the third of the Ecumenical Councils. This was in the twentieth year of the reign of Theodosius the Small, the Son of Arcadius, the son of Theodosius the Great.

በዛሬዋ ቀን ሁለት መቶ ሊቃውንት አባቶች በ431 ዓ.እ በኤፌሶን የተሰበሰቡበት ዕለት ነው። በጉባኤውም የቀናውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት (እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ትባላለች ፣ ክርስቶስም ከሁለት ባሕርይ የሆነ አንድ ነው።) አወጁ ፤ ንስጥሮስንም አውግዘው የቄርሎስን 12ቱን አንቀጸ ውግዘቶች አጸደቁ።

ቅድስት በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር!
❤ 72 👍 15 🥰 1
23 September 2025
ኪ
09:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዲቤቱን መልሼ አይቼ ጥሩ review ልሠራላችሁ ነበረ ግን እውነት ለመናገር ያንን ዲቤት መልሶ የማየት ሞራል የለኝም 😁

በአጠቃላይ ዲቤቱን ስናየው በሁለቱም በኩል የዝግጅት ማነስ ያየንበት ዲቤት ነበር። አንድ ሰው አንድን ዲቤት ሲመለከት የሆነ እውቀት ይዞ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል ነገር ግን በዚህ ዲቤት በሁለቱም በኩል ምንም መያዝ አልቻልንም።

ከታላቁ ልጀምር አንዳንድ ጥሩ ነጥቦችን አንስቶ ነበር (ለምሳሌ በኤፌሶን ጉባኤ የቅዱስ ቴዎዶጦስን እና የቅዱስ ቄርሎስን ሲጠቅስ ነበር) ከዛ ውጪ ግን በአብዛኛው ጥሩ አልነበረም ማለት ይቻላል። የጥያቄው ጊዜ ጥያቄውን ምንም form አድርጎ መጠየቅ አልቻለም ለምሳሌ ባሕርይ ያለ አካል ይገኛል በማለት ጠይቆ ፣ የሰውነት ባሕርይው በወልድ አካል ላይ ነው ሚገኘው ብሎ ሲመልስለት እንዲሁ ወልድ ተለውጧል ማለት ነው ብሎ assert አደረገ እንጂ እንዴት ለውጥን ሊያመጣ እንደሚችል ይዞ መጠየቅ አልቻለም። ቄርሎስ አንድ ባሕርይ ብሏል ትቀበላለህ ሲለውም ቃሌ በተደጋጋሚ የመለሳት መልስ አለች "ቄርሎስ አንድ ባሕርይ ሲል one concrete reality ማለቱ ነው" የሚል። እዚህ ላይ ታላቁም ምን ማለት እንደሆነ የተረዳ አልመሰለኝም በደምብ አድርጎ መያዝ ይችል ነበር ምክንያቱም እኛም አንድ ባሕርይ ስንል one concrete reality ማለታችን ነው። ቃሌ one concrete reality ሲል one person እያለ ይመስላል ነገር ግን ቄርሎስ ቀጥታ የሚናግረው ቃሌ ራሱ ከሰንሴንሰስ ደብዳቤ ላይ እንዳነበበው "ከሁለት የሆነ አንድ ባሕርይ ነው" ይህንን ማለትም one composite hypostasis out of two particular natures ማለት ነው ይህንን ደግሞ ኬልቄዶናውያን አይቀበሉም እና በደምብ በዚህ መያዝ የሚችለውን እድል አስመልጦታል ፤ ቃሌም የእኛን ነገረ ክርስቶስ ምንም የሚያውቅ ራሱ አይመስልም።

ከዚህ በላይ ደግሞ ታላቁ የሚያሳቅቁ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ ነበር ለምሳሌ ፕሮቴስታንት ሆነህ እንዴት ኬልቄዶንን ትቀበላለህ ፣ ካቶሊክ ወይ ኢስተርን መሆንህ ነው ፣ የኬልቄዶን ጉባኤ ላይ ስለ ምንኩስና ፣ ስለ ጥምቀት ፣ ስለ ቁርባን ተወስኗል እነዚህን ትቀበላለህ እያለ ሰአቱን አጥፍቷል። እውነት ለመናገር በዚህ የምንረዳው ታላቁ ፕርቴስታንቲዝምን እንድማያውቅ ነው ምክንያቱም እነርሱ የመጀመሪያዎቹን 6ቱን የዓለም አቀፍ ጉባኤያት ይቀበላሉ (አንዳንዶች 5ቱን ብቻ ይላሉ) ፤ ሲቀበሉ ግን ጉባኤያቱ ሊሳሳቱ የሚችሉ fallible ናቸው ብለው ነው ስለዚህ ጉባኤው ላይ የተወሰነውን ውሳኔያት በሙሉ የመቀበል ግዴታ የለባቸውም ይልቅስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ያሏቸውን ይቀበላሉ እንጂ። ስለዚህም ፕሮቴስታንቶች ኬልቄዶናውያን ነን ሲሉ ፣ የኬልቄዶንን ነገረ ክርስቶስ እንቀበላለን ማለታቸው እንጂ የጉባኤውን ውሳኔያት በሙሉ እንቀበላለን እያሉ አይደለም። ሌላም ደግሞ "የሥጋው ባሕርይ የማርያም ልጅ ነው የአብ ልጅ" የሚመስል ጥያቄም ሲጠይቅ ነበር ይህም ኬልቄዶናዊውን ነገረ ክርስቶስ አለመረዳቱን ያሳያል ኬልቄዶናውያን ባሕርይ በራሱ ልጅ ነው አይሉም የማርያምም ሆነ ፣ የአብ ልጅ ተብሎ የሚገለጸው አንዱ መለኮታዊ Person ነው ይላሉ እንጂ።

በቃሌ በኩል ደግሞ በቀላሉ ሊመለሱ የሚችሉ ጥያቄዎች ሲጠየቁ ነበር ለምሳሌ አንዱ ባሕርይ ምን አይነት ነው? የሚል ታላቁ ግን በሚያሳቅቅ ሁኔታ "ነጭ ነው ልበልህ" ሲል ነው የመለሰው ፣ ሌላም ቃሌ ዋና ጥያቄ ብሎ ያሰበው Double consubstantiality ነበር ታላቁም ይህን ጥያቄ በessence and hypostasis መካከል ያለውን ልዩነት ነግሮ ተዋሕዶውን በessence እንደማንል በማስረዳት በሁለቱም essences ከእኛም ጋር ከአብም ጋር አንድ መሆኑን ማስረዳት ሲችል ብቸኛ የሰጠው መልስ "አንዱ ባሕርይ composite ነው እንጂ ነጠላ አይደለም" ነበር አንዱ ባሕርይ composite ስለሆነ ብቻ እንዴት ከአብም ከእኛ ጋርም አንድ ሊሆን ይችላል የሚለውን አላስረዳም። ቃሌም ቢሆን ይህንን ነጥብ መያዝ ሲችል እንዲሁ double consubstantialityን መቀበል ኬልቄዶናዊ ያደርጋል ሲል ነበር ይህ assertion ብቻ እንጂ እንዴት ኬልቄዶናዊ ሊያደርግ እንደሚችል ምንም አላብራራም (By the way ቄሎስም አንድ ባሕርይ ሲል one concrete reality እያለ እንጂ ኬልቄዶናዊውን አይክድም ለማለትም የተጠቀመውም ይህኑ double consubstantialityን affirm ማድረጉ ነበር 😁) በዚህ ረገድ ቃሌ የጠቀሳቸው አባቶችም እንዳለ ይህንኑ double consubstantialityን affirm ሚያደርጉ ነው ይህን እኛ ላይ መጥቀሱ ምንም damage እንደማያመጣብን አልተረዳም። ብቸኛ ኬልቄዶናዊውን definition affirm ሚያደርግ ሰው ያመጣው ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮትን ነበር። ታላቁ ግሪኩ አይልም በማለት በትክክል ቢመልስም "ግሪኩን አንተ ራስህ አንብበው" በማለት ነጥቡን ማሳየት አልቻለም። በመጨረሻም comminicato idiomatum ተነሥቶ ነበር ማለትም የሁለቱ ባሕርያት attributes ለአንዱ ክርስቶስ predicate መደረጋቸው ፤ ቃሌ ይህንን ይዞ ኬልቄዶናዊውን ያሳያል ቢልም ታላቁም "እኛም በሥጋው ሞተ እንላለን" ከማለት በዘለለ በእኛ ነገረ ክርስቶስ እንዴት የሁለቱ ባሕርያት attributes ለአንዱ composite nature predicate እንደሚደረግ አላብራራም።

ብቻ ግን በመጨረሻም የምለው ሁለቱም የራሳቸውንም ሆነ ፣ ሊወያዩበትን የመጡትን ነገረ ክርስቶስ ጊዜ ወስደውበት ያንብቡበት።
❤ 88 👍 7 🤔 3
24 September 2025
ኪ
17:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMAfHfqJn/

በዛውም የዛሬ ማታ 3 ሰአት እንዳይረሳ ቃለ እግዚአብሔር እና መልአከ እግዚአብሔርን በብሉይ ኪዳን እናያለን
🔥 22 ❤ 11
25 September 2025
ኪ
10:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/eF4HhnDQvX4?si=IuCbWo8vnDv9rBcG

የትናንቱ record ነው። በዛውም ቻናሉ subscribe እንዲደረግ share አድርጉት እንጂ ሰዎች 1K Subscribers ቢያንስ ይሙላ እንጂ
❤ 39 🔥 5
26 September 2025
ኪ
13:36
ኪዳን ዘኢየሱስ
" The cross is the will of the Father, the glory of the Son, the rejoicing of the Spirit, the boast of Paul, "for," he says, "God forbid that I should boast save in the cross of our Lord Jesus Christ." The cross is that which is brighter than the sun, more brilliant than the sunbeam: for when the sun is darkened then the cross shines brightly: and the sun is darkened not because it is extinguished, but because it is overpowered by the brilliancy of the cross. The cross has broken our bond, it has made the prison of death ineffectual, it is the demonstration of the love of God." St. John Chrysostom HOMILY ON THE PASSAGE "FATHER IF IT BE POSSIBLE LET THIS CUP
PASS FROM ME...

"መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የወልድ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የጳውሎስ ትምክህት ነው እንዲህ ይላልና፦ “ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።” መስቀሉ ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራ፣ ከፀሐይም ጨረር የበለጠ አምጸባራቂ ነው፤ ፀሐይ በጨለመች ጊዜ መስቀሉ በደመቀ ሁኔታ አብርቷልና፤ ፀሐይም የጨለመችው ስለጠፋች ሳይሆን በመስቀሉ ድምቀት ስለተሸፈነች ነው። መስቀሉ እስራታችንን በጥሷል፣ የሞትን ወኅኒ ቤት ኃይል አልባ አድርጓል፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር አሳይቷል። " ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን አደረሳችሁ
❤ 130
ኪ
20:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤‍🔥 75 ❤ 34 🥰 8 😭 2
27 September 2025
ኪ
16:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
መልካም በዓል ሰዎች ዛሬ ከይቅርታ ጋር ሥላሴ በብሉይ ኪዳን ትምህርት አይኖረንም ረቡዕ እንቀጥላለን
👍 46 ❤ 13 🔥 4
ኪ
22:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
መከራ ነው እኮ 😂
🤣 73 ❤ 5
29 September 2025
ኪ
11:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቀኖና እና መንጽሔ እሳት

ባለፈው ዕለት ቀኖና ለኃጢአት ሥርየት የምናደርገው ቅጣት እንዳልሆነ ጽፌላችኋለሁ። ለኃጢአት ቅጣት ሲባል የሚፈጸም ድርጊት (satisfaction for sin) ካቶሊካዊ ትምህርት ነው እንጂ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም። በካቶሊክ ስነ መለኮት አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ በእርሱ ዘላለማዊ እና ጊዜያዊ ቅጣት ያከማቻል ፤ አንድ ሰው ሲጠመቅ ከእርሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ቅጣቶች በሙሉ ይወገድለታል (ዘላለማዊም ጊዜያዊም) ስለዚህ አንድ ሰው በተጠመቀ ሰአት ቢሞት ምንም አይነት የኃጢአት ቅጣት ክፍያ ሳይከፍል ገነት ይገባል ፤ ከጥምቀት በኋላ በሚፈጸሙ ኃጢአቶች ግን አንድ ሰው ንስሐ ሲገባ የኃጢአትን ሥርየት አግኝቶ ዘላለማዊ ቅጣት ይወገድለታል ነገር ግን ጊዜያዊ ቅጣት ስለማይቀርለት እርሱን ቀኖና በመፈጸም satisfy ማድረግ አለበት። ስለዚህም ቀኖና ጥቅሙ ሁለት ነው አንደኛው medicinal and penal satisfaction ፤ ቀኖና በመፈጸም አንድም ወደ መንፈሳዊ ቅድስና እና ንጽሕና ይወጣል እንዲሁም ደግሞ ለኃጢአቱ ተገቢውን ክፍያ ይከፍላል። የመጀመሪያውን የመንጻት aspect መፈጸም የሚችለው እርሱ ብቻ ነው ሌላ ሰው satisfy ሊያደርግለት አይችልም ነገር ግን የቅጣቱን aspect ሌላ ሰውም satisfy ሊያደርለት ይችላል በምሳሌ እንድትረዱት አንድ ሰው የሰውን ቤት መስኮት ይሰብራል በኋላም በመጸጸት ሔዶ የቤቱን ባለቤት ይቅርታ ይጠይቃል ሰውዬውም ይቅር ይለዋል ነገር ግን ይህ ሰው ምንም የጥፋቱን ይቅርታ ቢያገኝም የሰበረውን መስኮት ዋጋ መክፈል አለበት (ይህ የኃጢአት ክፍያ ቀኖና ነው) ግን ሌላ ገንዘብ ያለው ሰው የመስኮቱን ዋጋ ከፍሎለት satisfy ማድረግ ይችላል።

ስለዚህ በካቶሊካዊው ትምህርት አንድ ሰው ቀኖና የሚፈጽመው በመንፈሳዊ ሕይወት ለመንጻት ብቻ ሳይሆን የጊዜያዊ ኃጢአት ቅጣት እንዲቀልለት ጭምር ነው ይህም የሚሆነው በጸሎት ፤ በጾም ፣ በምጽዋት ፣ በቅዳሴ መሥዋዕት ነው። አንድ ሰው ግን ይህን ሁሉ በተገቢው ሁኔታ ሳይፈጽምና የኃጢአቶቹን ጊዜያዊ ቅጣቶች ሁሉ ሳያቀል ከሞተ ፤ ከሞት በኋላ በመንጽሔ እሳት (purgatory) በመቀጣት ኃጢአቱን satisfy ያደርጋል። ነገር ግን ከላይ እንዳስቀመጥኩት ሌላ ሰው የኃጢአቱን ቅጣት በመክፈል የመንጽሔ እሳቱን ቅጣት ሊያቀልለት ይችላል (indulgence, ለሙታን ጸሎት ፣ ለሙታን ቅዳሴ etc በመፈጸም)።

እዚህ ላይ የካቶሊኩን view ያቀረብኩት እርሱን ለጊዜው critique ለማድረግ አይደለም (መልስ ለመስጠት ኪይቦርዳቹን ያዘጋጃችሁ ካቶሊኮች ተረጋጉ 😁) ይልቅስ ብዙ ጊዜ በእኛ ምእመን ዘንድ ያለው የተሳሳተ የቀኖና መረዳት ወደ ምን ያህል የተሳሳተ ትምህርት እንደሚመራ ለማሳየት እንጂ። ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ቀኖና የኃጢአት ክፍያ ሳይሆን በመንፈሳዊ ሕይወት ማደጊያ ነው ፤ ከሞት በኋላ ያለው processም እንዲሁ ለመንጻት ብቻ ነው እንጂ ለኃጢአት ክፍያ አይደለም ፤ ለሙታን የምናደርገው ጸሎት ፣ ቅዳሴም ሆነ ምጽዋት እግዚአብሔርን በመንጻት ላይ ያለውን ሰው እንዲረዳው መጠየቂያ እንጂ satisfaction አይደለም።

ስለዚህ ኦርቶዶክሳውያን ንስሐ አባታችሁ ጋር ተናዛችሁ የሚሰጣችሁን ቀኖና በፍጹም ቅጣት አድርጋችሁ ማሰብ ከእናንተ ይራቅ ይልቅስ ስለ ኃጢአት ሥርየታችሁ ቅጣታችሁን አንድም ሳያስቀር የከፈለውን ክርስቶስን ስለጸጋው አመስግኑት እንጂ። ፍታት ዘወልድ (Absolution) እስከ ተጸለየላችሁም ድረስ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ትችላላችሁ እናንተ በምታደርጉት ነገር አይደለምና የበቃችሁ የምትሆኑት።

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 67 🥰 6 👍 3 🤔 2 🔥 1 👏 1
ኪ
20:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
ደሞ ቀልድ ነው መቃብያን ለዚህ አይደለም የወጣው ብላችሁ እንዳመጡብኝ ፕሮቴስታንቶች 😁
🤣 70 😁 20 🗿 2 ❤ 1 🤔 1 🤨 1
30 September 2025
ኪ
09:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
Catholics: Submit to Rome we have the see of Peter

Oriental Orthodox: Actually we have two sees of Peter , submit to Alexandria and Antioch.

ከላይ ፎቶው ላይ የምትመለከቱት የእስንክድራያው ፓትሪአሪክ ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ያለው Title ነው "ብጹዕ ፣ ክቡር ፣ ቅዱስ አባታችን አለቃ እና ጌታችን ፤ የታላቋ ከተማ እስክንድርያ ፣ ሊብያ ፣ ፔንታፖሊስ ፣ ኢትዮጵያ ፣ አፍሪካና የግብጽ ምድር ሁሉ ፓፓ እና ፓትሪአሪክ ፤ የአባቶች አባት ፣ የእረኞች እረኛ ፣ የሊቀ ካህናት ሊቀ ካህን ፣ አሥራ ሦስተኛው ሐዋርያ ፣ የዓለም ዳኛ፣ አለቃችን እና ሊቀ ካህናታችን።"
🔥 29 ❤ 19 🙏 3
ኪ
19:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
አሁን አሁን ፖድካስት ለመጀመር ድፍረት ብቻ እንደሚያስፈልግ እየተመለከትኩ ነው ሰው እንዴት 50 ደቂቃ ካሜራ ፊት አውርቶ አንድም substance ያለው ነገር ሳይናገር ይጨርሳል።

ጭራሽ ደሞ Monarchy of the Father ምንፍቅና ነው ፣ ኢስተርኖች ማርያምን ጥንተ አብሶ አለባት በማለታቸው እንደ ተራ ሴት ያዮአታል ፣ እመቤታችን ባትኖር እግዚአብሔር ሰው አይሆንም ነበር የሚሉ misrepresentations እና የመረጃ እጥረትን የሚሳያሳይ አደገኛ ንግግሮች ሲናገሩ ነበር።

ለጉባኤ ቤቶች የተጨነቁ በማስመሰል patristic ጥናት እንደ አዲስ አያስፈልገንም ዮሐንስ አፈወርቅ የጻፈው ለግሪኮ ሮማን world ነው ከዛ ውስጥ ሚያስፈልገንን ብቻ ጉባኤ ቤቶች ተርጉመውልናል አይነት አደገኛ ንግግሮችም ሲናገሩ ነበር።

ከዚህ በላይ እንዳልጽፍ ምንም substance ያለው ነገር አላገኘሁባቸውም ነገር ግን አካሔዳቸው አደገኛ ነውና የምታውቋቸው ሰዎች ሃይ በሏቸው።

ፖድካስት መጀመር ድፍረት ብቻ ሚያስፈልገው ከሆነ እኔም ልጀምር እንዴ 😁
😁 80 ❤ 17 🤣 6 ❤‍🔥 4 👎 1
1 October 2025
ኪ
20:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይቅር ይበሉን እንግዲህ ምእመናን ወምእመናት ቀጣይ በዚህ ሁኔታ live መግባት ስላልቻልኩ ነው ምናልባት ቅዳሜ እንቀጥል ይሆናል
👍 20 ❤ 11 🙏 9
2 October 2025
ኪ
15:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል

መለኮት ማለት የአብ ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድ ባሕርይ ነው። መከፈል የለበትም ይልቅስ በሦስቱም አካል ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ እንጂ። አብ የመለኮት 1/3ኛ ፣ ወልድ የመለኮት 1/3ኛ ፣ መንፈስ ቅዱስ የመለኮት 1/3ኛ ኾነው አንድ ላይ አንድ መለኮት የሚኾኑ አይደለም ይልቅስ አብ ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ፣ ወልድም ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ ፣ መንፈስ ቅዱስ ውስጥ የመለኮት ሙላት አለ ስለዚህም እያንዳንዱ አካል ለየብቻቸው መለኮት ፣ መለኮት፣ መለኮት ተብለው መጠራት ይችላሉ። ነገር ግን ሦስት መለኮት ሳይኾን አንድ መለኮት ነው ያለው መለኮት በአካላት ሦስትነት አይከፈልምና ይልቁንም ይገናዘባል እንጂ። አብ ቃሉን ወልድ ፣ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስ አድርጎ መለኮት ይባላል ፣ ወልድም መሠረቱን አብ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስ አድርጎ መለኮት ይባላል ፣ መንፈስ ቅዱስም መሠረቱን አብ ቃሉን ወልድ አድርጎ መለኮት ይባላል ስለዚህ በመለኮት ዘንድ ተገናዝቦ እንጂ ተከፍሎ ስለሌለ ሦስት አንለውም፤ በሦስት አካላት ሕልው የኾነ አንድ ነው እንጂ።

አካሉ ውስጥ የመለኮት ሙላት ያለው ወልድ ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ሰው ኾነ ፣ ተለይቶ ሰው ኾነ ስንል ግን የተለየው ተገናዝቦውን አይደለም ወልድ ያለ መሠረቱ አብ እና ያለ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ የኖረበት ጊዜ የለምና። ይልቅስ ተለይቶ ስንል በአካል እና በቃልነት ከዊኑ ነው። ተለየ ስንልም በቦታ አይደለም የመለኮት አካል በኹሉ የመላ ነውና ይልቅስ የተለየው ሥጋን በመዋሐድ ነው፤ አካሉን ከማርያም ከተነሣው ሥጋ ጋር አንድ ያደረገው ወልድ እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይደሉም እንዲሁም የቃልነት ከዊኑን ከሥጋ ባሕርይ ጋር አንድ አድርጎ፤ ሥጋ ዓለም የተፈጠረበት የእግዚአብሔር ቃል ያደረገው ወልድ እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይደሉም። ስለዚህም ከአባቱና ከሕይወቱ የማይለየው ወልድ በተዋሕዶ ግን ተለየ ፣ ብቻውን ሥጋን በላ። "ምነው አብና መንፈስ ቅዱስ ቀሩ ሥጋ አያምራቸውምን? ልጅ ለሥጋ ስሱ ስለኾነ ተቅለብልቦ መጣ እንጂ ኹለቱስ እሳት ናቸው ጥበባቸውም አይታወቅ። ይልቁንስ ልጅየው ዘመዳችን ነው ኹሉንም አጫውቶናል 😁" (መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)።

ይህ ልጅ ሥጋን በመብላቱ ዘመዳችን ኾነ እንደእኛ ሥጋ ኾኗልና "በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ-ሥጋን በመልበስ ዘመድ ኾነን" ብለን እንድንዘምር አድርጎናል። አባቱ እና መንፈሱ በመቅረታቸው አንቆጭም ፤ አባቱን በእቅፉ ያለ አንድያ ልጁ ተርኮታልና መንፈሱንም በአምሳለ እሳት በበዓለ ጰንጠቆስጤ ሰዶልናል በዚህም ፍጹም ዝምድናውን አሳየ። ነገር ግን ይህ ልጅ ከአባቱና ከመንፈሱ ተለይቶ ብቻውን ሥጋ በልቷልና ብቻውን ይሞት ዘንድ ተገባው ፣ በመለኮት ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ቢኾንም ሥጋን የተዋሕደ መለኮት እርሱ ብቻ ነውና ሞት ለእርሱ ብቻ ተገባው ስለዚህም እኛ "ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ-በሥጋ ሞትን የቀመሰ" አልነው እርሱ መለኮት በሥጋ ሞቷልና። መለኮትስ ሞተ አይባልም አብና መንፈስ ቅዱስ ሥጋ አልበሉምና ነገር ግን ሥጋን የበላው መለኮት ወልድ ሞቷልና መለኮት በሥጋ ሞተ ይባላል "ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት ታረቀን" እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ። (ሮሜ 5፡10)

"ሐሜተ ክልዔቱ አኃው ዘኢፈርሀ ወልድ በልዐ በተከብቶ
ሥጋ ጥዑመ እንዘ የዐጹ ኆኅቶ
ወፍሉጠ ሞት ኮነ ባሕቲቶ ዘበልዐ እስመ ይመውት ባሕቲቶ

የኹለቱን ወንድሞች ሐሜት ያልፈራ ወልድ
ጥዑም ሥጋን በሩን ዘግቶ በሥውር በላ
ስለዚህም ብቻውን ሞተ ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታልና" መጽሐፈ ቅኔ (ዝክረ ሊቃውንት)

ምእመናን ሰው እያለማስ ብቻችሁን እንዳትበሉ ብቻን መሞት አለና 😁

Old Post ነው ለካስ ሰዎች በፊት አመሠጥረው ነበር 😁
🔥 42 ❤ 37 ❤‍🔥 5
ኪ
16:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሄም old post ነው 😁
😁 119 🤣 34 ❤ 20 👍 3 🙉 3 😭 1
3 October 2025
ኪ
15:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
ምን አስባለሁ መሰላችሁ ቤተክርስቲያን ኢሬቻን ከምታወግዝ ብትዋጀው

የሆነ ነገር ከማለታችሁ በፊት hear me out. ሰኔ 12 ስንክሳርን ስታነቡት አንድ ነገር ታገኛላችሁ ሰኔ 12 በፊት የዙሃል ጣኦት በዓል ነበር በግብጽ ውስጥ ክርስቲያን ከሆነ በኋላም ሕዝቡ በዓሉን ማክበር አላቆም ሲል የወቅቱ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ እለእስክንድሮስ በዙሃል ጣኦት ቦታ የሚካኤልን በዓል ሠራ እስካሁንም ድረስ የሚካኤል በዓል ሰኔ 12 ይከበራል።

እናማ ኢሬቻም መከበር የጀመረው በዋቄና እምነት ተከታዮች እንደሆነ ግልጽ ነው ክረምቱን ላሳለፋቸው ዋቀ ጉራቻ ምስጋና ሚያቀርቡበት ነገር ግን አሁን ላይ የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ጥቂት ቢቀሩሞ በዓሉ በባሕላዊ መንገድ መከበሩን ቀጥሏል። ስለዚህም ቤተክርስቲያን በዛን ቀን በካህናት የተመራ የተዋጀ በዓል ብታደርገው አስባችሁታል ሕዝቡ በካህኑ መሪነቱ ክረምቱን ላሳለፈው ዋቀ አባ (እግዚአብሔር አብ) በጎፍታ ኢየሱስ በኩል ምስጋናውን ያቀርባል። ውኃውም በአፉረ ቁልቁሉ (መንፈስ ቅዱስ) ተባርኮ ሕዝቡም ተረጭቶት ያመሰግናል።

እንዴት ትላላችሁ ኢጆሌ አባ ገዳ?
😁 50 ❤ 46 👏 17 🥰 7 ❤‍🔥 3 👍 3 👎 2 🔥 2 🤣 1
ኪ
16:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገ ማታ 3 ሰአት ሌላ ፕሮግራም ስላለ እኛ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን የጀመርነውን ማታ 1:30 እንጀምራለን share አድርጉ ማንም እንዳይቀር
❤ 42 🔥 5
4 October 2025
ኪ
18:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
ካፈረኩ አይመልሰኝ ይመስል Monarchy የሚል ቃል በሥላሴ ዘንድ ጥቅም ላይ አይውልም በማለት የተናገሩት ልጆች አሁን ደግሞ ከአባቶች አሳዩን ብለው ቻሌንጅ አቅርበዋል ከአባቶች አቀርብላችኋለሁ እናንተ ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ተስማሙ።

"For the Word, being Son of the One God, is referred to Him of whom also He is; so that Father and Son are two, yet the Monad of the Godhead is indivisible and inseparable. And thus too we preserve One Beginning of Godhead and not two Beginnings, whence there is strictly a Monarchy."

St. Athanasius , Discourse 4 Against the Arians, 1


"Next, I may reasonably turn to those who divide and cut to pieces and destroy that most sacred doctrine of the Church of God, the Divine Monarchy , making it as it were three powers and partitive subsistences and god-heads three... For it is the doctrine of the presumptuous Marcion, to sever and divide the Divine Monarchy into three origins — a devil's teaching, not that of Christ's true disciples and lovers of the Saviour's lessons. "

St. Athanasius, De Decretis Chapter 26

"Worshipping as we do God of God, we both confess the distinction of the Persons, and at the same time abide by the Monarchy. We do not fritter away the theology in a divided plurality, because one Form, so to say, united in the invariableness of the Godhead, is beheld in God the Father, and in God the Only begotten."

St. Basil the great , On the Holy Spirit 45

"Thus the way of the knowledge of God lies from One Spirit through the One Son to the One Father, and conversely the natural Goodness and the inherent Holiness and the royal Dignity extend from the Father through the Only-begotten to the Spirit. Thus there is both acknowledgment of the hypostases and the true dogma of the Monarchy is not lost."

St. Basil the great , On the Holy Spirit 47.

" When then we look at the Godhead, or the First Cause, or the Monarchia, that which we conceive is One; but when we look at the Persons in Whom the Godhead dwells, and at Those Who timelessly and with equal glory have their Being from the First Cause—there are Three Whom we worship."

St. Gregory the Theologian , Orations 31. 14

በጣም ብዙ ማቅረብ እችል ነበር እነርሱ ግን ቻሌንጃቸውን አንድ ብቻ ስላሉ ይሄም ከበቂ በላይ ነው። ግራ የገባቸው የሚመስለኝ Monarchy ሲባል በኢንጊሊዘኛ መሪነት የሚያሳይ ቃል ስለሆነ ነው ነገር ግን በግሪኩ μοναρχία (monarchia) አንድ ምንጭ (one cause or one source) ለማለት ጥቅም ላይ ይውላል። μονo (Mono) ማለት አንድ ማለት ነው ፤ ἀρχή (arche) ማለት ደግሞ ጅማሬ ፣ ማለት ነው (በመጀመሪያ ቃል ነበር ሲል En arche en ho Logos ይላል) ስለዚህ አንድ ላይ ሞኖአርኬ ሲባል አንድ ምንጭ አንድ ጅማሬ ማለት ነው። ይሄን ከላይ ከአባቶችም አይታችኋል ሦስት አካላትን ብናምንም ሦስት ምንጮች በሥላሴ ዘንድ አናምንም ይልቅስ አንድ ምንጭ እናምናለን እንጂ እርሱም እግዚአብሔር አብ ነው።
❤ 74 🔥 16 👏 4
6 October 2025
ኪ
11:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን

ስለ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን መጽሐፍ ትንሽ ነገር ልበላችሁ እዚህ ላይ ዋናው አላማ ቀኖናዊነቱን መፈተሽ ሳይሆን የመጽሐፉን ታሪካዊነት ማጥናት ብቻ ነው። ይዘቱንም ብዙዎቻችን ስለማናውቀው ምንድነው የሚለውን ማሳወቅ።

አንድን መጽሐፍ ይዘቱን ከማየታችን በፊት ጸሐፊውን ማወቅ አለብንና ጸሐፊው ማነው? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ አይታወቅም የሚል ነው። መጽሐፉ ጸሐፊው "Yoseph ben Gorion" ብሎ የሚጠራው የጥንቱ ሮማዊ አይሁዳዊ የታሪክ ጸሐፊ ፍላቢዮስ ዮሴፎስ እንደሆነ ይናገራል። ነገር ግን በአብዛኞቹ አጥኚዎች ስምምነት ያለበት ጸሑፉ የተጻፈው በጠዘነኛው ክፍለ ዘመን መካከል ውስጥ እንደሆነ ነው ስካሊንገር እና ዙንዝ የመሰሉ ጸሐፊያን ደግሞ ዐመቱን ከፍ አድርገው ወደ 940 ሲያመጡት ትሪቢየር ብቻ ግን ከሁሉም ተለይቶ ወደ 4ተኛው ክፍለ ዘመን ያመጣዋል። [1] ስለዚህ በሁሉም አጥኚዎች ዘንድ ስምምነት ያለው መጽሐፉ የአይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ ፍላቢዮስ ዮሴፎስ ሳይሆን በእርሱ ስም የተሰየመ Pseudo-Josephus እየተባለ የሚጠራ መጽሐፍ ነው። ጸሐፊውም በዘጠነኛው ክፍለ ክፍለ ዘመን የደቡባዊት ጣሊያን የኖረ አይሁዳዊ ነው። ይህ አይሁዳዊ መጽሐፉን የጻፈው በዕብራይጥ ሲሆን ከአይሁዳዊው የታሪክ ጸሐፊ ፍላቢዮስ ዮሴፎስ እውነተኛ ሥራዎች ከሆኑት Antiquities and Jewish War ከመሳሰሉ ሥራዎች ምንጭ በስፋት ተጠቅሟል [2] ፤ እንዲሁም የመቃብያን ዘመን አይሁዶችን ታሪክ በስፋት በመጠቀሙ የሰብዓ ሊቃናትን መቃብያን መጽሐፍትም በምንጭነት እንደተጠቀመ ይነገራል ለዚህም ይሆናል ፍትሐ ነገሥት መጽሐፉን ሲጠቅሰው "ዘውእቱ መጽሐፈ መቃብያን" የሚለው። በኋላም ወደ አረብኝ "Yusuf ibn Qaryun" በሚል ስም የተተረጎመ ሲሆን ጥንታዊው ሙሉ ቅጂም የተገኘው በአረብኛ በካይሮ ግብጽ ውስጥ ነው። የ13ተኛን ክፍለ ዘመን የግብጽ ቤተክርስቲያን ቀኖናት ያዘጋጀው ኢብን አሳልም የብሉይ ኪዳን ቀኖና ውስጥ " Yoseph Ibn Karboon that is
the book of Maccabeans." በማለት ያስገባዋል [3] ፍትሐ ነገሥትም የዚህ መጽሐፍ ትርጉም በመሆኑ ቃል በቃል ይወስደዋል።

ስለመጽሐፉ እና ስለጸሐፊው ይህን ያህል ካልን ይዘቱን ስናየው የአይሁድን ታሪክ ለመተረክ ከአዳም በሴት በኩል ያለውን ዘር ሐረግ መተረክ ከጀመረ በኋላ ወደ ባቢሎን እና ፋርስ ነገሥታት ታሪክ ይዘላል። ከዛም ወደ ግሪክ ታሪክ በመሔድ መቀዶንያዊውን እስክንድር (Alexander the great) ታሪክ ይተርካል። ታላቁ እስክንድር ከሞተ በኋላ መንግሥቱ ተከፋፍላ በአይሁዶች ላይ የነገሠውን ንጉሥ አንጥያኮስ ኤጲፋንዮስን ታሪክ ይጀምራል (ይህኛው ክፍል ከመጻሕፍተ መቃብያን ጋር ተመሳሳይ ታሪክን ይይዛል ፤ ክህኑ ማታትያስ ፣ ልጁ ይሁዳ መቃብዮስ ፣ የአንጥያኮስ አሟሟት ፣ አይሁዳውያን በመቃብያን መመራታቸው ወዘተ)። ከዚያም እንዲሁ ከመጻሕፍተ መቃብያን ጋር በተመሳሳይነት የሮም ነገሥታት መነሳትን ያትታል ፤ ከዚህም በኋላ መቃብያን የመሠረቱት መንግሥት (Hashmonean Dynasty) በሮም እጅ ይወድቃል ሮማውያንም ሔሮዳውያንን ይሾማሉ ፤ መጽሐፉም የሔሮዳውያንን ነገሥታት ታሪክ በመተረክ ይቀጥላል። ከዚያም በሐዲስ ኪዳን የምናውቃቸውን ሔሮዳውያን (ታላቁ ሔሮድስ ፣ ሔሮድስ አርኬላዎስ ፣ ሔሮድስ አግሪጳ) ታሪክ ይተርክልናል። በመጨረሻም የአይሁድ ሮማውያን ጦርነት (Jewish Roman War) ይተርክና በሮማዊው ጥጦስ ቤተመቅደሱ እስከ መፍረስ ታሪክ ተርኮ ያበቃል።

የመጽሐፉ ታሪክ በአብዛኛው accurate ቢሆንም ነገር ግን አንዳንድ inaccuracies እንዳሉትም ምሑራን ያትታሉ ለምሳሌ ከአዳም በኋላ ያስቀመጠው መግቢያ legendary ነው ፤ እንዲሁም መጨረሻው ላይ የአይሁድ ጦርነት እና ሮማውያን ጋር ያለው ጦርነት ታሪክ የኋላ ጭማዊ ነው ፤ እንዲሁም ታላቁ እስክንድር እና የእርሱ ተከታዮች ጋር የነበረው ታሪክም የ12ተኛ ክፍለ ዘመን ጭማሪ አለበት ፤ እንዲሁም የስሞች ፣ የከተሞች እና የሰዎች ታሪክ መፋለስ አለበት" እየተባለ ይተቻል ከዚህ የተነሣ አንድ አንድ ምሑራን ጸሐፊው በቀድሞ እንደሚታመነው ቀጥታ ከፍላቢዮስ ዮሴፎስ Jewish war እና ከመጻሕፍተ መቃብያ ምንጭ የተጠቀመ ሳይሆን የፍላቢዮስን እና መቃብያንን በመጠቀም ከጻፉ ጸሐፊያን secondary source እንደተጠቀመ ያምናሉ። [4]

1. https://jewishencyclopedia.com/articles/8929-josippon JOSEPH BEN GORION (JOSEPHUS GORIONIDES; referred to also as Yosippon and Pseudo-Josephus)
2. THE JOSIPPON OF JOSEPH BEN GORIONi A TRANSLATION OF PART II WITH AN INTRODUCTION AND SOURCE ANALYSIS Page X
3. “Al Magmou Al-Safawy Le Ibn Al-Assal” Chapter 2: The Holy Books We are Commanded to Accept in the Holy Church
4. Jewish encyclopedia ቁጥ1ን ይመልከቱ
❤ 56 👏 5 ❤‍🔥 2 🔥 1
7 October 2025
ኪ
17:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/EQsX0rODaHA?si=z_9mxYGuSqb-8qC1

ለድምፅ ረብሻው ይቅርታ እንጠይቃለን
❤ 23 🔥 4 🤝 2
ኪ
18:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
Fayyisaa Addunyaa Motii moototaa

መድኃኔዓለም የጌቶች ጌታ ❤️
❤ 102 😁 1
8 October 2025
ኪ
13:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMA9hUUqJ/

ዛሬ ማታ እንዲሁ እንዳይረሳ
❤ 22 🔥 2
ኪ
15:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አስባለሁ መሰላችሁ ከዚህ ከshame እና honor culture ወጥተን ሃሳቦችን በነጻ የምናንሸራሽርበት ሁኔታ መፍጠር። አሁን ላይ ውስጥ ለውስጥም ሆነ ከሌሎች ቤተእምነቶች ጋር የሚደረጉት ውይይቶች (ውይይቶች አልኳቸው ጭቅጭቆች) ሁሉ በጣም ነው ሚያስጠሉት ሃሳብን ይዘን መነጋገር አንችልም ሃሳብ ላይ የተሰጠ ትችት ግለሰብ ላይ የተቃጣ ጥቃት ይመስለናል (አንተ ማን ስለሆንክ ነው እንትናን የምትናገረው የሚል ምላሽ መዥረጥ ይደረጋል)። እንዲሁም አንድ መስተካከል ያለበት ነገር በማስረጃ ሲነሳ ስም ለመለጠፍ ነው ሚሮጠው (መናፍቅ ፣ ጴንጤ ፣ ወዘተ) ምንም አይነት ሃሳብን honest ሆኖ ሚቀበል የለም ትንሽ ትችት እንኳን ቤተክርስቲያን ላይ የተሰናዳ ጥቃት ተደርጎ ነው ሚወሰደው።

ከሌላ ቤተ እምነት ጋር የሚደረጉትማ ድብድብ ነው የሚቀራቸው ውይይቶቹ ሁሉ አላማቸው እውነትን ወደማወቅ መምጣት ሳይሆን ጨመቀው ፣ ረገጠው ፣ አጥቦ አስተማረው ለማለት ነው በጣም የሚያጠላ culture ነው ያለን።

እኔ ከዚህ toxic apologetics ራሴን ለማግለል እያሰብኩ ነው እስቲ ብቻ
❤ 93 👍 19 😭 7 😢 5 🔥 3 ❤‍🔥 2 💔 2
9 October 2025
ኪ
08:44
ኪዳን ዘኢየሱስ
Agia Sophia our Lord Jesus Christ

ቅድስት ጥበብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ!

ብዙዎቻችን ቁስጥንጥንያ ውስጥ የምትገኘው Agia Sophia ቤተክርስቲያን የሰሟእታ ቅድስት ሶፊያ ቤተክርስቲያን ይመስለናል ነገር ግን በቅድስት ጥበብ ስም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የተሰየመች ቤተክርስቲያን ናት። የግሪኩ ቃል Sophia እንደ ዕብራይስጡ Hokhmah በሴት አንቀጽ የሚጠራ ቃል ነው ስለዚህም Agios Sophia ሳይሆን Agia Sophia ይባላል። (ልክ ሥላሴ የሚለው ስም በግሪክ በሴት አንቀጽ የሚጠራ በመሆኑ Agios Trias ከማለት ይልቅ Agia Trias እንደሚባለው)

ቅድስት ጥበብ ጌታ ኢየሱስ!
❤ 108 🥰 11 🔥 3
ኪ
12:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/fkkHj8fPtPQ?si=qyfuMZJPWWh150hx

የትናንቱ አጠር ያለ ነው ስሙት
❤ 29 👍 6
10 October 2025
ኪ
12:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
የአረብኛው ኮፕቲክ ሥንክሳር ላይ ቅዱስ አውግስጢኖስ ተካትቷል 👊🏾
❤ 52 😁 6 ❤‍🔥 2 👎 1
ኪ
18:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
Sola Scriptura in practice collapses into solo scriptura.

ይህን ለማለታችን ይህ ፖስት ምርጥ ማሳያ ነው። ብዙ ጊዜ በተለይ classical protestant ነን የሚሉትን ከሰማችሁ እኛ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ስንል ትውፊት አያስፈልግም እያልን ሳይሆን ትውፊት ሊሳሳት ይችላል የማይሳሳተው ብቸኛ ባለሥልጣን ግን መጽሐፍ ቅዱስ ነው ትውፊትም ግን fallible authority ነው ይላሉ።

ነገር ግን ወደ ትግበራ ስንመጣ ትውፊት አያስፈልግም የሚሉት "solo scriptura" አማኞችም ቢሆኑ ከእነርሱ መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጓም ጋር ከገጠመላቸው ትውፊትንም ቢሆን ይቀበላሉ ስለዚህ classical ነን ከሚሉት ምንም አይለዩም ትግበራ ላይ። ለምሳሌ ይህ ፖስት በቤተክርስቲያን ሥስትዮሽ አስተዳደር (ጵጵስና ፣ ቅስና፣ ዲቁና) በትውፊትም በታሪክም ጠንካራ መሠረት እንዳለው ያምናል ምክንያቱም ግልጽ ስለሆነ መካድ አይቻልምና ቅዱስ አግናጥኖስ ዘአንጾኪያ በ107/8 ዓመታት በላካቸው መልእክቶች የየአብያተ ክርስቲያናቱን ጳጳሳት ሰላም እያለ ሕዝቡንም ለጳጳሳቸው ካልታዘዙ ምሥጢራት እንኳን እንዳይፈጽሙ ያዛል።

ነገር ግን ይህን ያህል ጠንካራ ታሪካዊ ዳራ ቢኖረው እንኳን ከእነርሱ ግላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጓም ጋር ካልገጠመ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ለማለት ወደ ኋላ አይሉም። ይህ ደግሞ አደገኛ አካሔድ ነው ምንም አይነት ትውፊት አንቀበልም የሚሉት እንኳን ጠንካራ ታሪካዊ ዳራ ያላቸውን አስተምሮቶች ብታቀርቡላቸው እንኳን (ለምሳሌ ጥምቀት ለድኅነትና የቁርባን አማናዊነት) ከእነርሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ግላዊ ትርጉም ጋር ስላልገጠመ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ከማለት ወደኋላ አይመለሱም።

ታድያ በምን ተለያችሁ? ለሁለታችሁም የእናንተ ግላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓገም ከትወፊት የበላይ ስልጣን አለውና።
❤ 78 👏 6 ❤‍🔥 2 👍 2
ኪ
23:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከላይ ለጻፍኩት ጽሑፍ response ተብሎ የተጻፈውን ረዘም ያለ ጽሑፍ አየሁ ጽሑፉ ቢረዝምም ግን እኔ ከጻፍኩት ጋር relevant የሆነው ሃሳብች ጥቂት ነው እርሱ ላይ እላቸዋለሁ ግን የገረመኝ "ስለዚህ ወንድማችን ሶላና ትውፊት ያላቸውን መስተጋብራዊና ተዋረዳዊ ግንኙነት የተረዳ አልመሰለንም" ቢልም በሶላ እና ሶሎ መካከል ልዩነቱን እኔ ካነሳሁት practical collapse አንጻር ምን እንደሆነ ሊያሳየን አልሞከረም እንዲሁ "ሳያውቅ ፣ ሳይረዳ" የሚል ቃላትን ተጠቀመ እንጂ። ብዙ ጊዜ ክላሲካል ነን የሚሉ ፕሮቴስታንቶች ዘንድ ሶላ ስክሪፕቱራ ላይ ትችት ሲሰጥ ትችቱን ከመመለስ ይልቅ "አልተረዳም ፣ አላወቀም" የሚል ምላሽ ይበዛዋል አንዳንዴ አስተምህሮአቸውን quantum physics የሆነ ይመስላቸዋል እንዴ እላለሁ የተቻቸው ሁሉ የማይረዳው።

ብቻ ግን ወደ ዋናው ብቸኛ ነጥብ ስንመጣ "rule of faith ያልሆኑ ትውፊቶችን በመጽሐፍ ቅዱስ መዝነን መጣል እንችላለን ፤ ጳጳሳዊ አስተዳደር rule of faith አይደለም ፤ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝነን መጣል እንችላለን" የሚል ነው። ጸሐፊው ይህን ቢያስቀምጥም የኔ ትችት practically ወደ ሶሎ ይወድቃልና በመሆኑ ይህ እንዴት ወደ ሶሎ እንደማይወድቅ አላሳየንም ምክንያቱም በእርሱ ግላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓገም ጳጳሳዊ አስተዳደር rule of faith አይደለም ስለዚህ ምንም እንኳን በታሪክ ትልቅ ድጋፍ ቢኖረውም በመጽሐፍ ቅዱስ መዝኜ ጥለዋለው ካለ ፤ የሶሎ አማኝስ እንዲሁ ከእርሱ ግላዊ የመስትሐፍ ቅዱስ አተረጓገም ጋር የማይገጥም ነገር ግን በታሪክ ድጋፍ ያለው አስተምህሮ ቢጠቀስበት ይህ rule of faith አይደለም ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝኜ ጠለዋለው ከማለት ምን ያግደዋል። ለምሳሌ ቅዱስ ቁርባን አማናዊ ነው የሚለውን ምንም በታሪክ ድጋፍ ቢኖረውም rule of faith አይደለም ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝኜ ጥለዋለው ቢል በሁለቱ መካከል ውይይቱ የሚሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መሠረት የቁርባን አማናዊነት rule of faith ነው አይደለም የሚል ይሆናል ስለዚህም finally ውይይቱ የኔ መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓገም ካንተ መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓገም ወደ ሚለው collapse ማድረጉ አልቀረም።

እንዲሁም rule of faith የሚሆኑ አስተምህሮቶች የግድ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ላይ መገኘት አለባቸው በሚለው የሶላ አስተምህሮ ይስማማል ሶሎውም ቢሆን እንዲሁ ስለዚህ አሁንም ቢሆን practically የሚለያቸው ነገር አይኖርም።
❤ 64 🔥 14 👍 3
14 October 2025
ኪ
11:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገረ ጥንተ አብሶ

ብዙ ጊዜ ከእኛ ዘንድ ኃጢአት በዘር ይተላለፋል የሚለው ትምህርት ከአባቶች የአውግስጢኖስ ብቻ ነው እንዲሁም ምዕራባዊ እንጂ ምሥራቃዊ አይደለም ፤ እኛ ምሥራቃዊ በመሆናችን ከመወለዳችን ጀምሮ ኃጢአተኞች ነን የሚለው ትምህርት የእኛ አይደለም ይባላል።

በመጀመሪያ እዚህ አስተሳሰብ ላይ ያለው ስህተት አንደኛ ኃጢአት በዘር ይተላለፋል የሚለው ትምህርት አውግስጢኖስ ጋር ብቻ አለመገኘቱ ነው ፤ ሁለተኛው ምዕራባዊ ሳይሆን ምስራቃዊም መሆኑ ነው ፤ ሦስተኛ ምዕራባዊ ብቻ ቢሆን ራሱ ክርስትናን በምሥራቅ ብቻ መወሰን አግባብ አይደለም ከምዕራቡ ክርስትና ጋር ሳንለያይ በፊት የነበሩ የምዕራብ አባቶች የእኛም አባቶች ናቸውና። ስለዚህ በዚህ ጽሑፍ ከምዕራብም ከምስራቅም አባቶች ኃጢአት በዘር እንደሚተላለፍ እና ከመወለዳችን ጀምሮ እድሜያችን አንድ ቀን እንኳን ቢሆን ኃጢአተኞች እንደምንባል አሳያችኋለሁ ፤ የአውግስጢኖስ ግልጽ ስለሆነ ከእርሱ ውጪ ያሉ አባቶች ላይ ነው ማተኩረው።

"በአዳም መተላለፍ እንዴት ብዙዎች ኃጢአተኞች ይሆናሉ? ... እርሱ ወድቆ በሞት ቅጣት ስር ሆነ ባሕርይውም ጎሰቆለ ... ልጆችንም በወለደ ጊዜ የባሕርይውን ጉስቁልና ለዘሮቹ አስተላለፈ። ስለዚህም ነው እኛ ኃጢአተኞች የሆነው ከአዳም ጋር ስለበደልን አይደለም ያኔ እኛ አልነበርንምና ነገር ግን በኃጢአት ሕግ ስር ከወደቀ ከእርሱ ባሕርይ ስለሆንን እንጂ። " ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ፡ Commentary on Romans, P.G. 74, 788-789.

"እያንዳንዱ ነፍስ በክርስቶስ ዳግመኛ እስኪወለድ ድረስ ባሕርይው በአዳም ነው። ይልቅም ያለዚህ ዳግም ልደት እስከቆየ ድረስ [በኃጢአት] ያደፈ ነው ፤ ያደፈም በመሆኑም ኃጢአተኛ (actively sinful) ነው።" ጠርጡለስ ዘቅርጣግና ፡ A Treatise on the Soul: chapter 40

"ስለዚህ ልደት ቅዱሳን ምን እንዳሉ ማወቅ ከፈለክ ዳዊት "በኃጢአት ተጸነስኩ እናቴም በአመጻ ወለደችኝ" ሲል ስማ ስለዚህም በሥጋ የተወለደ ነፍስ ሁሉ በኃጢአት እና በአመጻ ያደፈ ነው" አርጌንስ ዘእስክንድርያ ፡ Homilies on Leviticus: Homily 8

“ወደዚህ ዓለም የሚመጣ ሁሉ በተወሰነ ርኵሰት ውስጥ እንደተፈጠረ ይነገራል። ለዚህም ነው መጽሐፍ፡- ‘ሕይወቱ የአንድ ቀን ብቻ እንኳ ብትሆን ከእድፍ ንጹሕ የሆነ ሰው የለም’ የሚለው፤ ይህም ርኵሰት በእናት ማኅፀን ውስጥ ያለ ነው፤ በእናትም ውስጥ ሕፃኑ በራሱ በጽንሰቱ ጊዜ እንኳ ይረክሳል።” አርጌንስ ዘእስክንድርያ ፡ Homilies on Leviticus: Homily 12

“አዳም በበደለ ጊዜ ኃጢአቱ ወደ ሰው ሁሉ እንደ ደረሰ፣ እንዲሁ ጌታ ሰው በሆነና እባቡን ድል በነሳ ጊዜ፣ ያ ታላቅ ኃይሉ ለሰው ሁሉ ይዳረሳል።” ( አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ፡ Four Discourses Against the Arians: Discourse 1, Chapter 12, Section 51

"እኛ በኃጢአት ታስረን በኃጢአተኝነትም ተወልደን በሞት ስር እንኖር ስለነበር የእግዚአብሔር ቃል ሞትን ሽሮ ሰውን ያድን ዘንድ ከድንግል ሥጋ ሆነ።" ሔሬኔዎስ ዘኤዶም ፡ Demonstration of the Apostolic Preaching : Chapter 37

“ነገር ግን በዚያ፣ ፍርድ ከምሕረት የተለየ አይደለም፤ ምክንያቱም ሰው የአንድ ቀን ዕድሜ እንኳ ቢኖረው ከእድፍ ንጹሕ ሆኖ ሊገኝ አይችልምና” ባስልዮስ ዘቂሳርያ፣Exegetic Homilies: Homily 15, Section 4

“ዓለም ሁሉ በክፋት ሥር ነውና... የአንድ ቀን ሕፃን እንኳ ቢሆን ያለ ኃጢአት አይደለም... በዚህም ምክንያት ዳዊት በመዝሙሩ፡- ‘እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ’ በማለት ይመሰክራል። የእናቱን ‘ዓመፃ’ ወይም ‘ኃጢአት’ አላለም... ይልቁንም የሰው ባሕርይ የሆነውን ኃጢአት ለማሳየት ‘በዓመፃዎች’ እና ‘በኃጢአቶች’ አለ።” ጀሮም፣ Commentary on Ezekiel

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 46 👍 6 👎 3 🤔 3 👏 2
ኪ
20:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 10
17 October 2025
ኪ
06:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 13
06:30
In reply to this message
ሥላሴ በብሉይ ኪዳን ቅዳሜ እንፈጽማለን። እውነት ለመናገር በሐዲስ ኪዳን እና በአባቶችም የመቀጠል ፍላጎት ነበረን እኔ ግን እዚህ ጋር ይብቃኝ ምናልባት ጆ (https://t.me/timelesstruthoo) ይቀጥልላችሁ ይሆናል።

ከዚህ በኋላ አንዳንዴ ጽሑፍ ለቅላችኋለሁ ግን ንባብ ላይ focus ላድርግ አሁን ትመቹኛላችሁ 🙌
💔 33 ❤ 25 🤯 2
18 October 2025
ኪ
14:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 106 🔥 10 👍 3
20 October 2025
ኪ
09:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከእግዚአብሔር አባታችን ከጌታም ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን! [ከ ጆ Timeless Truth እና ከሌሎች ወንድሞች የተጻፈ ነው...የለቀኩትም ጆ ነኝ!]

በኪዳን አገልግሎት በጣም ብዙዎቻችን ተጠቃሚ ነን ብዬ አስባለሁኝ እናም ከዚህ የበለጠ የሱን ሥራ በተለያዩ ቦታዎች ለማስተዋወቅ እና ከዚህ የተሻለ ቦታ ሚድያ ላይ [በተለይ ቲክቶክ እና YouTube] እና በተሻሉ ርዕሶች ብዙ አገልግሎቶቹን እንዲያዳርስ ለምን አናደርግም?

እናም ከዚሁ ከኪዳን አገልግሎት ጋር በተያያዘ በቋሚነት ሁላችንም የምንችለውን በጎ አገልግሎት ለማገልገል አስበናል ጥቂት ሰዎችም ተሰብስበናል

እናም በወር ቢያንስ እንደ አቅማችን ከ50-300 ድረስ መደገፍ የአገልግሎቱ ተካፋይ ለመሆን አስበናል እናም በማቴሪያል፣ ለማገዝ ፈቃደኛ የሆናችሁ sponsor ማግኘት የምትችሉ ተቀላቀሉን [በአሪፍ ፖድካስት እንዲመጣ ከሌሎች መምህራን ጋርም]

ሐሳባችሁን ንገሩን ግሩፑንም [ https://t.me/+GBbaLCu243A1OTY0 ] ተቀላቀሉ

❗️ደግሞ ይኼም በሌላ እንዳይታይ የዚህ ሐሳብ ጀማሪም ጨራሽም የኪዳንን አገልግሎት መደገፍ እና የተሻለ ቦታ ላይ ማድረስ የምንፈልግ ልጆች ሐሳብ ነው ኪዳን በሱ አካውንት ውስጥ ከመግባቱ እና እቃዎቹን ለሱ አገልግሎት ከማዋል ውጪ ምንም ውስጥ እጁ የለም❗️
Joel
❤ 85 🔥 5 👏 4 👍 3 🥰 2 🍓 1 💘 1
21 October 2025
ኪ
13:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች ማኅሌተ ጽጌ እንዴት ይዟችኋል ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ ግን ማኅሌቱን አደርኩ ብላችሁ ቅዳሴ ትታችሁ እየወጣችሁ አይደለም አይደል?

እኔ ያኔ እንዲህ ያደረኩበትን ጊዜ ሳስተውስ በራሴ አፍራለሁ ማኅሌቱን መሳተፍ ጥሩ ቢሆንም ከቅዳሴ አይበልጥም ለክርስቲያን ደግሞ እሑድ ማስቀደስ ግዴታው ነው ከእግዚአብሔር ቃል እና ከምሥጢሩ (ቁርባን) ሊበልጥ የሚችል ነገር የለም። ቅዳሴ ዜማ ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስን የምንሰማበት ፣ ወንጌል የምናደምጥበት ከዛም ስብከት የምንሰማበት እና የምንጸልይበት በቃሉ በኩል የምንባረክበት የቃሉ ቅዳሴ (liturgy of the Word) የምንሳተፍበት ነው። እንዲሁም ክክርስቶስ መሥዋዕት የምንካፈልበት ስለእኛ ኃጢአት የተሠዋውን ክርስቶስን የምናቀርብበት እኛም እርሱን የምንቀበልበት የአማኞች ቅዳሴ (liturgy of the faithful) የያዘ ለቤተክርስቲያን እስትንፋሷ የሆነ ታላቅ መቀደስ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ የትኛውም አገልግሎት ሊቀር ይችላል ቅዳሴ ግን ከቀረ ቤተክርስቲያን ጠፍታለች ማለት ነው።

ስለዚህ የኪዳኑ ሕዝቦች ሆይ የቻልን ማኅሌቱንም ቅዳሴውንም እንሳተፍ ያልቻልን ግን ከቅዳሴው ብቻ እንሳተፍ እንጂ በፍጹም ቅዳሴውን ረግጥን አንውጣ።
Kidan
❤ 160 👍 9 ❤‍🔥 3
22 October 2025
ኪ
23:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።” (ዳንኤል 10:21)

አንዳንዶች ይህንን ጥቅስ ሲጨቁኑት እየተመለከትኩ ነው አንድን ጥቅስ ያለ አውዱ የመመልከት ችግር አለ። አንዳንድ ሰዎች አውዱን ካለማየታቸው የተነሣ ይህ ተናጋሪ ዳንኤል ይመስላለዋል ነገር ግን እዚህ ላይ ተናጋሪው ገብርኤል ነው ፤ ወደ ዳንኤል መልእክት ይዞ እየመጣ ነበር ነገር ግን የፋርስ አለቃ ለ21 ቀናት ተቋቋመው (ገብርኤልን እስከመቋቋም የሚደርስ የፋርስ አለቃ ሰው እንዳልሆነ ግልጽ ነው ይልቅስ በፋርስ ላይ የተሾመ ከማኅበረ መላእክት (divine council) አባል የሆነ ሰማያዊ መልአክ እንጂ በኋላም ፍርድን በማጓደሉ ወደቀ) ገብርኤልም ወደ ዳንኤል ወደ ፋርስ ሲሔድ ከግዛቱ ውጪ እየሔደ እንደሆነ ይታወቅ የያሕዌ ውርሱ እስራኤል ነውና። ስለዚህም ከግዛቱ ውጪ ሲሔድ የፋርስ አለቃ ለ21 ቀናት ተቋቋመው ያን ጊዜም የእስራኤል አለቃ ሚካኤል ሊረዳው መጣ ገብርኤልም ለዳንኤል መልእክቱን አደረሰ ነገር ግን ጥርነቱ አላበቃምና ሊዋጋ ይመለሳል ነገር ግን የግሪክ አለቃም ጥርነቱን ስለሚቀላቀል ገብርኤልን የሚያጸና ከታላቁ አለቃ ከሚካኤል በቀር የለምና ገብርኤል ጥቅሱ ላይ ያለውን ንግግር ተናገረ።

አንዳዶች ይህን ጥቅስ ያለ አውዱ ለሌላ ነገር justification ሲጠቀሙት ስላየሁ ነው ይታረም 👊
❤ 35 🔥 14 👍 1
23 October 2025
ኪ
14:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
"አንተ ጥንታዊም አዲስም ውበት ሆይ፣ አንተን ለማፍቀር አረፈድሁ! አዎን፣ አንተን ለማፍቀር አረፈድሁ!
እነሆ፣ አንተ በውስጤ ነበርህ፣
እኔ ግን በውጭ ነበርኩ፤ በዚያም እፈልግህ ነበር። አንተ በፈጠርካቸው ውብ ነገሮች ላይ እኔ፣ ቅርጽ የለሽ የሆንኩት፣ በጭፍን እወድቅ ነበር።
አንተ ከእኔ ጋር ነበርህ፣ እኔ ግን ከአንተ ጋር አልነበርኩም።
እነዚያ በአንተ ውስጥ ባይሆኑ ኖሮ ህልውና የማይኖራቸው ነገሮች፣ ከአንተ አርቀው ይዘውኝ ነበር።
አንተ ጠራህ፣ ጮህክ፣ መስማት የተሳነውን ጆሮዬን ከፈትክ፤
አንጸባረቅክ፣ በራህ፣ ዓይነ ስውርነቴን አስወገድክ፤
መዓዛህ አወደኝ፣ እስትንፋሴን ሰበሰብኩ፣ አሁንም አንተን እተነፍሳለሁ፤
ቀመስኩህ፣ አሁንም እራባለሁ እጠማለሁም፤
ዳሰስከኝ፣ ለሰላምህም ነደድኩ።"

ቅዱስ አውግስጢኖስ Late have I loved you lord , late have I loved you ❤️
❤ 103 ❤‍🔥 22 🔥 6 🥰 1
24 October 2025
ኪ
12:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
"አሐዱ ነዳይ ዘክሕደ ሃይማኖቶ
ኪያኪ ክሒደ ሶበ አበየ በቅድመ ሰይጣን ዘአስሐቶ
አሚነ ዚአኪ ድንግል ለአድኅኖ ነፍሱ በቊአቶ" ማኅሌተ ጽጌ

ይህን ማኅሌተ ጽጌ ስናዜም ትርጉሙን ያወኩ ቀን ከብዶኝ ነበር እንዲህ ማለት ነው "ሃይማኖቱን የካደ አንድ ደኃ በአሳተው ሰይጣን ፊት አንቺን መካድ እምቢ ባለ ጊዜ አንቺን ማመኑ ነፍሱን ለማዳን በቃችው"

ታሪኩ ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ እና ተአምረ ማርያም ላይ አለ ስለምታውቁት መድገም አያስፈልግም እንዲስተካከልም ወደ ሊቃውንት ጉባኤ ዘንድ እንደ ቀረበ ከአንድ ሰው ሰምቻለሁ (ባላረጋግጥም) ነገር ግን እንደዚህ አይነት አስተምህሮ ምንፍቅና መሆኑ መታወቅ አለበት አንድ ሰው እግዚአብሔርን ክዶ በድንግል ምልጃ ከሞት ተነሥቶ ሊድን አይችልም ይህ ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ድኅነትን በጣም የሚያቃልል ነው እኛም እንደ ቤተክርስቲያን አባልነታችን ምንፍቅና በአውደ ምሕረት ላይ ሲሰበክ መቃወም አለብን።

ለቤተክርስቲያንም የማቀርበው ጥሪ ከዚህ ታሪክ ጋር የተያያዙት ሁሉ ወይ እንዲታረሙ አልያም እንዲወጡ ነው። ይህ ጥሪ ቤተክርስቲያንን ከመውቀስ አንጻር ሳይሆን በትኅትና እንዲስተካከል ከመጠየቅ አንጻር ነው።
🔥 63 ❤ 28 👍 12 😡 4 ❤‍🔥 1
27 October 2025
ኪ
09:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
I like this guy.

ዋናው ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ "ኤጲስ ቆጶስ" እና "ቄስ" የሚለው ቃል በተለዋዋጭነት ጥቅም ላይ ይውል ስለነበር በሐዋርያት ዘመን አንድን ሐገረ ስብከት ለብቻ የሚመራ ጳጳስ አልነበረም ይልቅስ ይመሩ የነበሩት በቀሳውስት ጉባኤ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ጳጳስንና ቄስን የለየው አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ነበር ይላሉ ከአንግሊካን ውጪ ያሉት ፕሮቴስታንቶች።

ይህ ግን ከላይ ያለው ፎቶው ላይ ያለው ወንድማቸው እንደጠቆማቸው ይህ word-concept fallacy ነው። ማለትም አንድ concept እርሱን የሚወክል አንድ specific ቃል ካለ ብቻ ነው የሚኖረው ማለት ነው። እነርሱም የሚሉት በሐዋርያት ዘመን specifically የጳጳሳትን role የሚወክል ቃል ስለሌለ (ምክንያቱም ቀሳውስትም ጳጳሳት ተብለው ይጠሩ ነበርና) የጳጳስ roleም የለም ይላሉ።

ስለዚህ እኛ መፈለግ ያለብን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጳጳሳትን የሚወክል ቃል ሳይሆን role ነው ይህ ደግሞ በእርግጥም አለ ለምሳሌ ፤ ቲቶ እና ጢሞቲዎስ specifically የአንድ ከተማ መሪ ጳጳሳት ነበሩ እንዲሁም ሌሎች ቀሳውትን እንዲሾሙ ከጳውሎስ መመሪያ ይሰጣቸዋል ይህ አሁን ላይ "ጳጳስ" የምንለውን role እንደወሰዱ ያሳያል። ሌላው ደግሞ መረሳት የሌለበት ጳጳሳት ራሳቸው ቀሳውስት ናቸው ልዩነታቸው ጳጳሳት በሥራቸው ብዙ ቀሳውስትን ይቆጠጠራሉ ፤ ሌሎች ቀሳውስትን ይሾማሉ አንድን ሐገረ ስብከት በበላይነት ይመራሉ።

ወደ አግናጥዮስ እንኳን ብንመጣ እርሱ መልእክት የጻፈላቸው ሐገራት በሙሉ አንድ የበላይ ጳጳስ ነበራቸው ይህ የሆነው ደግሞ በ108 ዓ.እ ነ ፤ መቼስ ጳጳሳዊ ሥርዓት ሐዋርያዊ ካልሆነ በቀር እንዲህ በአጭር ጊዜ ውስጥ universal አይሆንም ነበር።

ሌላ ጊዜ በስፋት መጣበታለሁ ለአሁኑ ለማሳየት ብቻ ነው።
❤ 61 🥰 7
ኪ
14:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/betremariyamabebaw/6750

የኔታ ጥሩ ገልጸውታል ዛሬም ትልቁ ፈተና ይሄው ነው።
አንተ ከእነ እንትና በልጠህ ነው!?
እስከ ዛሬ ያቆዩልንን አንተ ልትቀይር ነው!? ይባላል
ስህተት ዘመኑ ስለቆየ ትክክል አይሆንም በቀድሞ ጊዜም ስህተት ሊጻፍ ይችላል ስለዚህ እናስተውል አንድ ነገር በመጻሕፍት ስለተገኘ ብቻ እውነት ነው ማለት አይደለም ወረቀት የጻፉበትን ሁሉ ይይዛልና።
❤ 56
28 October 2025
ኪ
08:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
😂😂
🤣 28 🤔 22
ኪ
09:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
አሁን ወደ ኋላ ልታስመልሱን ነው King Henry VIII ከሚስቱ ጋር ለመፋታት annulment ከፖፑ ይጠይቃል ፖፑ እምቢ ይላል ንጉሡ ምን አገባኝ እንዳውም ቤተክርስቲያኒቷን ለይቻለሁ በማለት የካንተርበሪውን ሊቀ ጳጳስ ዋና የቤተክርስቲያኒቱ መሪ በማድረግ ከሚስቱም ከሮምም ተፋታ።

ንጉሥ ሄንሪ ሞተ ኤድዋርድ ተተካ ፤ ንጉሥ ኤድዋርድ ደግሞ ሪፎርምድ ቲኦሎጂን ወደ እንግልጣሯ ቤተክርስቲያን አስገባ የካንተርበሪው ሊቀ ጳጳስም ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮቴስታንት ሆነ (ቶማስ ክራንመር) የእንግጣርን ቤተክርስቲያንም እንደ ጉድ አደሳት ሮም ክህነታችሁ invalid ነው እስክትል ድረስ። ኤድዋርድ ሞተ ፤ ደመኛዋ ማርያም (Bloody Mary 😁) ነገሠች መልሳ እንግልጣርን ከሮም ጋር ግኑኝነት አስጀመረች ፕሮቴስታንቶችን ጨፈጨፈች ግን አልቆየችም እሷም ሞተች ፤ ንግሥት ኤልሳቤጥ ተተካች መልሳ እንግልጣርን ፕሮቴስታንት አደረገች። ይኸው እስከዛሬ ድረስ የእንግልጣሯ ቤተክርስቲያን ፕሮቴስታንት ሆና ቀረች ነገር ግን ኢንጊሊዝ ውስጥ ብቻ አልተወሰነችም በእንግልጣሮች ኮሎኒ ሁሉ (በተለይ በአፍሪካ) ተስፋፋች ፤ የካንተርበሪው ሊቀ ጳጳስም first among equals ነው።

That is until 2008 , በኢየሩሳሌም ጉባኤ የአፍሪካ እንግልጣር ቤተክርስቲያን ተከታይ ጳጳሳት ተሰብስበው GAFCONንን መሠረቱ የእንግልጣር ቤተክርስቲያንንም liberal እየሆንሽ ነው ብለው ከሰሱ፤ እንግልጣር ግን የት ትሰማቸው fast forward 2025 ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፤ ውርጃ ደጋፊ ፤ የተመሳሳይ ጾታ ደጋፊዋን ወይዘሪት ሳራ የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ አድርጋ ሾመች።

ይህን ጊዜ GAFCON በቃሽኝ እንግልጣር ከነ liberal ጓዝሽ ገደል ግቢ በማለት ከእንግልጣር ተለዩ ራሳቸውን "The global Anglican Communion" ብለው ሰየሙ በእርግጥ በቁጥር ሚበዙት እነሱ ናቸው ነገር ግን የእናት ጡት ነካሽ በመሆን the coldest quote "We are not leaving the Angllican communion , we are the Anglican Communion" drop አደረጉ።
❤ 28 👌 5 🙊 2 👍 1
ኪ
15:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
አሁን ያለንበት ዘመን ዝሙት የነገሠበት እንደሆነ ግልጽ ነው በወጣቶች ዘንድ እንደ ቀላል እና ኖርማል ነገር ነው ሚታየው ይህንንም ለማድረግ ስሙን በማሳነስ ይጀመራል (ለምሳሌ እፎይ ማለት ሲባል ሰምቻለሁ) እንዲህ እየተባለ በቀላሉ ሁሉም ዘንድ ተለምዷል አሁን ሲጀመር የዝሙትን አስከፊነት የሚናገር ሰው እንደ ሃይማኖተኛ fundamentalist ነው ሚታየው ስለዝሙትም በማኅበራዊ ሚዲያ በግልጽ ያለ እፍረት ይወራል ጊዜው ከመቼውም በላይ ዝሙትን የሚያበረታታ ዘመን ነው።

እኔ ስለ ዝሙት አሁን ላወራችሁ አይደለም ነገር ግን ዝሙትን ተከትሎ የሚመጣ በእኛ ሐገር ችላ የተባለውን የነፍስ ግድያ ኃጢአት ነው ሊያውም ገና ያልተወለዱ ሕፃናትን (ውርጃ ብዬ አልጠራውም በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የነፍስ ግድያ ነው)። በሐገራችን በጣም normalize እየተደረገ እየመጣ ነው ካላስተዋላችሁት ወጣቶች በዝሙት እንደፈለጉ ይሆኑና ዕርግዝና ሲመጣ "አስወጪው ፣ አስወጣዋለሁ" አይነት ነገር ይነገራል ውርጃ ማግኘትም በሀገራችን ቀላል ነው ሕጉ ውርጃን ቢከለከልም ነገር ግን ለእናትየው ሕይወት አስጊ ሲሆንና በጾታዊ ጥቃት የተጸነሰ ከሆነ ይፈቅዳል ነገር ግን ይህን ለማጣራት ምንም አይሞከርም አንዲት ሴት ሐኪም ጋር ሔዳ በጥቃት ነው ያረገzኩት ትላለች ሐኪሙም እርሷን ማመን ግዴታ ስላለበት ያለምንም ጥያቄ ውርጃ ይፈጽምላታል በዚህ ሁኔታ በሐገራችን ብዙ ሕፃናት ላይ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል። ይህ ሁሉ እየሆነ ግን እንደ አሜሪካ እኛ ሐገር አንድም pro-life movement የለም (ምናልባት ኖሮ እኔ አላውቅም ይሆናል)።

እስከመቼ ይህ ይቀጥላል ሰዎች? እየጠፋ ያለ ነፍስ እኮ ዛሬ እኔን ፣ አንቺን ፣ አንተን ፣ ሁላችንን የሚሆን የሰው ነፍስ ነው! ኃጣአት በአደባባይ እንዴት እንዲህ ሃይማኖተኛ በተባለች ሀገራችን ይነግሣል?
❤ 71 😢 18 🙏 7 ❤‍🔥 3 🔥 3
ኪ
17:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ይህ ችግር ደግሞ በኢትዮጵያ ለምን እንደሚከፋ ታውቃላችሁ ኢትዮጵያውያን ጨዋ ሕዝቦች ነና ከትዳር በፊት ዝሙት መፈጸም ፤ ከትዳር ውጪ ወልዶ መገኘት ማኅበረሰባዊ እና ቤተሰባዊ መገለል ያመጣል ፤ ኢትዮጵያውያን ማለት በኖራ የተለሰንን ግድግዳዎች ነን ውስጣችንን የክፋት ሁሉ ክፋት እየፈጸምን በማኅበረሰብ ደረጃ ደግሞ ጻድቅ ጻድቅ እንጫወታለን። አሁን በዚህ ጊዜ አንዲት ሴት ከትዳር ውጪ ወልዳ ብትገኝ ቤተሰብ አሰዳቢ ፤ የዲቃላ እናት እያለች ትወቀሳለች ትገለላለች ስለዚህ በማኅበረሰቡ ከመገለል ይልቅ ልጇን መግደል ትመርጣለች።

ይህ እውነት ማኅበረሰባዊ ቀውስ ነው ችግሮቻችንን ሸፋፍነን ምንተዋቸው ከሆነ መቼም መፍትሔ አናገኝም እየባሰ ይሔዳል እንጂ በውጪ በውጪ ጻድቅ ጻድቅ ብንጫወትም አንደኛ ፖርን ተመልካች ፣ አንደኛ ዘማውያን ፣ አንደኛ የልጆች ነፍስ አጥፊ እኛው ነው ስለዚህ በግልጽ ሁሉንም ነገር እየተነጋገርን መፍትሔዎችን መፈለግ አለብን ፤ ከትዳር ውጪ የጸነሰችም ሆነ የወለደች ሴት ልትታገዝ ይገባታል እንጂ ልትሸማመቅ አይገባትም ከዚህ የበለጠ ኃጢአት ውስጥ እንዳትገባ!
❤ 66 👍 13 😢 11
30 October 2025
ኪ
16:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
"የቀራንዮ እና የቅዱስ ቁርባን ምሳሌ የነበሩት የብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች ፤ የተሠዊዎቹን መጥፋት ያካተተ ነበር። የተሠዊዎቹ ሞት እና በእሳት መጥፋት እግዚአብሔር መሥዋዕታቸውን የመቀበሉ ምልክት ነበር። ሥራቸውም በዚህ ያበቃል ስለዚህም በሌላ ጊዜ ሌላ መሥዋዕት ማቅረቡ አስፈላጊ ሆኖ ነበር።

የክርስቶስ መሥዋዕት ግን ልዩ ነው ትንሣኤው አብ መሥዋዕቱን የመቀበሉ ምልክት ነው እንዲሁም ትንሣኤው መሥዋዕታዊ ኃይሉ አሁንም በቤተክርስቲያን እንዲኖር እና ቤዛነቱን መቀበል እንድንችል ምልክት ነው። ስለዚህም ሰማያዊው ሊቀ ካህናት ምሥጢሩን፣ ይኸውም የመሥዋዕትነት ሕይወቱን፣ አደለን። መሥዋዕታዊ ሥጋውንና ደሙንም ሰጠን፤ ይህም የሞቱ፣ የትንሣኤውና የዕርገቱ ምሥጢር ሲሆን፣ በሕይወታችን ውስጥ የሚሠራ ሕያው መታሰቢያ (አናምኔሲስ) ነው።

በመስቀል ላይ ክርስቶስ ሥጋዊ ደሙን አፍስሷል። ይህ መሥዋዕት እንደ ቀደሙት (መሥዋዕቶች) በሞቱ ተጠናቆ ቢሆን ኖሮ፣ እኛን ወደ ሰማይ ማምጣት ባልቻለም ነበር። ነገር ግን፣ አብ ይህን መሥዋዕት መቀበሉን እያወጀ ዳግም ተነሥቷል፤ ይህም እርሱ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሁል ጊዜ የሚገኝ ሕያው መሥዋዕት መሆኑን እና ያንኑ መሥዋዕት በምሥጢራዊ (ቅዱስ ቁርባናዊ) መንገድ፣ ያለ ሥጋዊ ደም መፍሰስም ሆነ ያለ ሥጋዊ ሞት እንደሚያቀርብ ያረጋግጣል፤ ምክንያቱም እርሱ ዳግመኛ ሊሞት አይችልምና።"
Christ in the Eucharist: Fr. Tadros Malaty

የማይሞት ፤ የማይጠፋ ፤ የተነሣ ፤ በአብ ቀኝ ያለ ሕያው መሥዋዕት ❤️
❤ 67
ኪ
19:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
Matthew 9 አማ - ማቴዎስ
36: ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አትታያችሁምን? እኔ ሁሌ ይህን ጥቅስ ሳስበው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትዝ እያለችኝ እምባዬ ይመጣል በሰማይ እንጂ በምድር እረኛ የሌላት ቤተክርስቲያን
❤ 53 😭 39 ❤‍🔥 6 😐 1
31 October 2025
ኪ
09:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዛሬው ቀን የተሐድሶ ቀን ነው አሉ ፤ ጀርመናዊው መነኩሴ ማርቲን ሉተር 95 theses የተባሉ ጽሑፉን ዊተንበርግ የሚገኘው የሁሉም ቅዱሳን ቤተክርስቲያን በር ላይ በመለጠፍ በይፋ ተሐድሶውን አስጀመረ።

95 theses ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ስለመለጠፉ ማስረጃ ባይኖርም (ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማው ሉተር ከሞተ በኋላ በቀኝ እጁ ፊሊጶስ ሜላንክተን በኩል ነው) ለጳጳሱ እንዳልከው ግን ይነገራል ፤ በዚህ ጽሑፍ ላይ ግን እንደሚታሰበው ፖፑንም ሆነ purgatory ወይም indulgence አልተቃወመም እንዳውም በአንቀጽ 71 ላይ እንዲህ ሲል የአሁኖቹን ፕሮቴስታንቶች ሁሉ ያወግዛል ".71. Let him who speaks against the truth concerning papal indulgences be anathema and accursed;" ይልቅስ ተቃውሞው የነበረው indulgence መሸጡ ላይ እና እዛ ላይ የነበረው abuse ላይ ነው አንቀጽ 72 ላይ እንዲህ ገልጾታል"72.But let him who guards against the lust and license of the indulgence preachers be blessed"። ስለዚህ አሁን ላይ ፕሮዎች ራሳቸውን የሚያወግዝ ጽሑፍ ነው የተሐድሶ ቀን እያሉ የሚያከብሩት።

እንዲሁም ያልተሳካ ተሐድሶ ነው "የተሐድሶ ቀን" እየተባለ የሚከበረው ምክንያቱም ቃሉ እንደሚነግረን ተሕድሶ ማለት already ያለው system በማደስ ማነቃቃት እንጂ ሌላ አዲስ system መዘርጋት አይደለም አላማው ፤ ተሐድሶ ጊዜያዊ እንቅስቃሴ ነው የነበረውን system አድሶ ከጨረሰ በኋላ አላማውን ይጨርሳል ፤ ሐዳስያኑም አላማቸው ይህ ነበር አዲስ ቤተክርስቲያን ማስጀመር ሳይሆን የነበረችዋን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማደስ አድሰዋት ሲጨርሱም ተሐድሶው ያበቃል። ነገር ግን ይህ አልሆነም ይልቅስ ከማደስ ይልቅ already ተከፋፍላ የነበረች ቤተክርስቲያን ውስጥ ሌላ ክፍፍል ነው የፈጠሩት ስለዚህ የደስታ ቀን ሳይሆን የኃዘን ቀን መሆን ነበረበት ምንም ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳብ ያለን እኛ ነን ቢሉም። ለምሳሌ በኬልቄዶን ጉባኤ እኛ ትክክለኞቹ ነበርን ብለን ብናስብም የኬልቄዶን ጉባኤ ቤተክርስቲያንን የከፈለ ሒደት ነበርና እናዝንበታለን እንጂ አንደሰትበትም አናከብረውም።

እወቁት እኛ ሐገር ተሐድሶ የሚለውን ቃል ከአንድ ቤተእምነት ጋር ስላያያዝነው ከቃሉ ጋር ፍራቻ አለብን እንጂ ተሐድሶ ጥሩ ነው የነበረውን system ማነቃቃት ነውና አላማው የ16ተኛም ክፍለ ዘመን ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ግን ይህን አላደረገውም it just created another permanent schism so it is more accurately termed as revolution rather than reformation.

ለማንኛውም ለመንቀፍ አይደለም እንኳን አደረሳችሁ ጎረቤቶቻችን 😁
❤ 50 😁 27 👍 3
1 November 2025
ኪ
20:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንዴት ናችሁ ! ጆ ነኝ ከTimeless Truth

ያው ኪዳን ሰፋ ባለ አገልግሎት እንዲመጣ አንዳንድ ነገሮችን እንደጀመርን ይታወቃል እና እሁን ደግሞ ካለፈው ከከፈትነው ግሩፕ ባለፈ አሁን ደግሞ ሥራችን youtubeኡን 1000 subscriber መሙላት ነው ...

አሁን 400 አልፏል ስለዚህ ይኼን የምናይ በራሳችን ባሉን አካውንቶች እና በምናውቃቸው ቶሎ subscribe እናድርግ እና 1000 ሞልተን የመጀመሪያውን ቪድዮ እንጠብቃለን ማለት ነው ... ስለዚህ ከስር ያለውን ሊንክ እየነካን ቶሎ እንሙላው

አካውንቱ - https://youtube.com/@kidanzeiyesus?si=FQi0ItGpo-VFUg9L
Joel
❤ 53 😁 2
2 November 2025
ኪ
20:58
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንኳንም የኢየሱስ ሆንን!
እንኳንም ክርስቲያን ሆንን!

ኢየሱስን ያተረፈ ዓለምን ሁሉ ቢያጣ ምኑም አይደለም ፤ ዓለምን አትርፎ ኢየሱስን ያጣ ግን ከሰዎች ሁሉ የከሰረ ነው። እንኳንም የኢየሱስን ፍቅር አወኩት ፤ እንኳንም ጌታዬን አፈቀርኩት ፤ ለጌታዬ ኖሬ ከመሞት በላይ ሊያስደስተኝ የሚችል ነገር ምንም የለም ምንም እንኳን በየጊዜው ኃጢአት እየሠራው ባሳዝነውም ፍቅሩ ግን አልቀነሰብኝም በጸጋ ላይ ጸጋ ጨመረልኝ እንጂ። በዓለም ላይ የሕይወትን ትርጉም ብዙ ለመፈለግ ሞክሬያለሁ ግን ውስጤን ሊያሳርፍ የሚችል መልስ አላገኘሁም በመጨረሻ ሁሉም የሚያልፍ ከሆነ የሁሉ ነገር ትርጉሙ አልታየኝም ምንም በዓለም ባተርፍ ይጠፋል ያልፋል ፤ ይህ ሁሉ ልፋት የመጨረሻ ግቡ ሊታየኝ አልቻለም ሁሉም እንዳልነበረ ይሆናል ወደ አለመኖርም ይመለሳል እንዳልተፈጠርን እስክንሆን ድረስ ስማችን እስከነ ድራሻችን ይጠፋል ለ10 ዓመት ኖርን ለመቶ ፤ ሃብታም ሆንን ደሃ ፤ ቀይ ሆንን ጥቁር ፤ የዓለም ታዋቂ ሰው ሆንን በማንንም ባንታወቅ በመጨረሻ ሁሉም እንዳልነበረ ይሆናል ታድያ የዚህ ሁሉ መኖር ጥቅሙ ምንድነው? በሕይወት መኖርስ ጥቅሙ ምንድነው? በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ ያለው ቃል አጽናናኝ "ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።" (ገላ 2፡20) ለካስ ሕይወት ባዶ የሆነብኝ እኔ ሕያው ሆኜ ኖሬ ክርስቶስን በውስጤ ስላላኖርኩት ነው ፤ በራሴ ያለ ክርስቶስ ስኖር ሕይወት ትርጉም አልባ ናት ነገር ግን እኔ ለዓለም ሞቼ በውስጤ ክርስቶስ ሲኖር ሕይወቴም ለራሴ ሳይሆን ስለ እኔ ራሱን ስለሰጠው ክርስቶስ ስኖር የሕይወት ትርጉም ግልጽ ይሆናል ምክንያቱም ሁሉም ያልፋል የማያልፍ ግን አንድ አለ እርሱም ክርስቶስ ነው! ስለዚህም ይመስላል ጳውሎስ በመጨረሻ "ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።" ያለው። (ፊል 1፡21)

የቻናሉን description ካያችሁት "በዚህ ኹሉም ነገር አላፊ በኾነው ዓለም ውስጥ እየኖርን ፣ ለማያልፈው ዘለዓለማዊ ለኾነው ለክርስቶስ እንኑር "እርሱ ብቻ የማይሞት ነውና" (1ኛ ጢሞ 6፡16)" ይላል ፤ ቻናሉንም ስከፍተው አላማዬ Apologetics አልነበረም ትርጉም አልባ በሆነ ሕይወት ውስጥ ስኖርና የዚህ ሁሉ ነገር ጥቅሙ ምንድነው ስል የማያልፈው ክርስቶስ እርሱ የመኖርን ትርጉም ስለሰጠኝ ምናልባት ለሌሎችም የመኖርን ትርጉም በክርስቶስ ያገኙ ዘንድ ያገኘኝን ለማሳየት ነው ነገር ግን አሁን ሳስበው የዕቅበተ እምነት የመጨረሻውም ዓላማ ሰውን ሁሉ ለክርስቶስ ማኖር ነው ስለዚህ አሁንም የምለው ለማያልፈው ለክርስቶስ እንኑር እርሱ ብቻ የማይሞት ነውና!

እንኳንም የኢየሱስ ሆንኩኝ!
❤ 178 ❤‍🔥 15 🔥 10 🥰 5 👍 4 👏 1
4 November 2025
ኪ
12:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
አሁንም ገና YouTube ላይ ገና 578 subscribersብቻ ናቸው ያሉት ... መጀመሪያ ከነበረው 200 ሚሆን እንኳን ጭማሪ አላደረገም ግን ባለፈው የለቀኩትን በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ 1400 ሚጠጋ ሰው ግን አይቶታል

እና እዚህ ላይ ቢያንስ ኪዳንን የሚከታተል 500 ሰው የለም እንዴ? ከቻለ በራሱ 2 አካውንት subscribe የሚያደርግ እናም ቢያንስ የሚያውቀውን አንድ ሰው እንኳን ስልኩን ተቀብሎ subscribe የሚያስደርግ ሰው ... ቢያንስ ቤት ውስጥ የእናትና አባታችን ስልክ እኮ አለ አ?

እናንተንም መነዝነዜ እንዲቆም በቃ ይኼንን ቶሎ እንጨርሰውና እኔንም ተገላገሉኝ😅 ስለዚህ በቃ አካንውቱን ይኸው ከስር አስቀምጫለው በቃ ቢያንስ የምንከታተል ሰዎች 1 ተጨማሪ ሰው ብናስደርግኮ ቶሎ ሞልቶ እኔም ይኼንን ድጋሚ አልጽፍም ነበር

በዚህ ጉዳይ ከመጣሁ ጆ እንደሆንኩኝ ታውቃላችሁ ብዬ ነው ስሜን ከላይ ያልተናገርኩት

https://youtube.com/@kidanzeiyesus?si=FQi0ItGpo-VFUg9L
Joel
❤ 47
ኪ
23:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
"2. Given the necessity of explaining Mary’s subordinate role to Christ in the work of Redemption, it would not be appropriate to use the title “Co-redemptrix” to define Mary’s cooperation. This title risks obscuring Christ’s unique salvific mediation and can therefore create confusion and an imbalance in the harmony of the truths of the Christian faith, for “there is salvation in no one else, for there is no other name under heaven given among men by which we must be saved” (Acts 4:12). When an expression requires many, repeated explanations to prevent it from straying from a correct meaning, it does not serve the faith of the People of God and becomes unhelpful. In this case, the expression “Co-redemptrix” does not help extol Mary as the first and foremost collaborator in the work of Redemption and grace, for it carries the risk of eclipsing the exclusive role of Jesus Christ — the Son of God made man for our salvation, who was the only one capable of offering the Father a sacrifice of infinite value — which would not be a true honor to his Mother. Indeed, as the “handmaid of the Lord” (Lk 1:38), Mary directs us to Christ and asks us to “do whatever he tells you” (Jn 2:5)

24. The biblical statement about Christ’s exclusive mediation is conclusive. Christ is the only Mediator, “for there is one God, and there is one mediator between God and men, the man Christ Jesus, who gave himself as a ransom for all” (1 Tim 2:5-6). The Church has clarified this unique place of Christ in light of the fact that he is the eternal and infinite Son of God, hypostatically united with the humanity he assumed. This is exclusive to Christ’s humanity, and the consequences that derive from it can only be properly applied to him. In this precise sense, the Incarnate Word’s role is exclusive and unique. Given this clarity in the revealed Word of God, special prudence is required when applying the term “Mediatrix” to Mary. In response to a tendency to broaden the scope of Mary’s cooperation through this title, it is helpful to specify the range of its value as well as its limits.

" Mater Populi Fidelis

ቫቲካን ያወጣው አዲሱ ዶክመንት ላይ ነው አጨብጭበናል 🙌
👏 32 ❤ 11 👍 3 😁 1
5 November 2025
ኪ
11:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
"በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።" (ኤፌሶን 1፡3)

የመንፈሳዊ ጸጋዎች እና በረከቶች ሁሉ መፍሰሻ ፤ እንዲሁም የጸሎቶች እና የልመናዎች ሁሉ ማረጊያ በእግዚአብሔር እና በእኛ መካከል ያለው መካከልኛ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ ይሁን!

የትኛውም መንፈሳዊ ጸጋ እና በረከት ከእግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ በኩል ካልሆነ በስተቀር ሊሰጠን አይችልም እርሱ በሰውነቱ ከብሮ በአብ ቀኝ በመቀመጡ እኛንም በሰማያዊ ስፍራ በማስቀመጥ አክብሮናልና ፤ በሰማያት በአብ ቀኝ የአዳም ሥጋ በክብር ተቀምጦ ቀና ስንል እናየዋለን ቀድሞ ተዋርዶ የነበረው ይህ ሥጋ ከመለኮት ጋር በመዋሐዱ በባሕርይ ከብሯል የከበረው የእኛ ሥጋ ነውና እኛም እንዲሁ በመለኮታዊ ጸጋ ጋር በክርስቶስ እየተዋሐድን ወደ ከበረው ራሳችን አባላቱ ነንና እንሔዳለን ይህም የሆነው ጸጋውን ሁሉ በክርስቶስ ባፈሰሰብን በእግዚአብሔር አምላካችን ነው።

የትኛውም ጸሎት እና ምልጃ በክርስቶስ ካልሆነ ወደ እግዚአብሔር አያርግም እርሱ ኢየሱስ በሰውነቱ የጥልን ግድግዳ አፍርሶ ወደ ጸጋው ዙፋን እንዲሁም ወደ እግዚአብሔር መግባት እንዲሆንልን አድርጎናልና ፤ እግዚአብሔር ማንም ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ባየ ጊዜ ምልጃዎች በሙሉ ወደ እርሱ ይቀርቡ ዘንድ የገዛ ክንዱን መድኃኒት አድርጎ በመላክ ጸሎታችን በክርስቶስ ለእግዚአብሔር የተወደደ መአዛ እንዲሆን አድርጓል ፤ ስለዚህም አሁን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበው በጌታችን በኢየሱስ በኩል እኛም ሰውነታችንን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገን እናሳርጋለን እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበት የልጁ መሥዋዕት ነውና ፤ በልጁ በኩል በሚደረግ ልመናውም በእርሱ በኩል ጸጋዎችን ሁሉ ያፈስልናል!

ታድያ የቅዱሳን ምልጃ እና ከቅዱሳን ሁሉ የላቀች ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን እናታዊ ምልጃም እንዲሁ ለእግዚአብሔር የተወደደ የሆነው በልጁ በኩል ስለቀረበ ነው ፤ ከክርስቶስ ጋር በፍጹም ውሕደት አንድ በመሆናቸው ለክርስቶስ የሚቀርብ ምልጃቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው። ማንም የሚማልድበት በሌለ ጊዜ ክርስቶስ እራሱ መካከለኛ በመሆን አማኞችን ሁሉ አማላጆች አደረጋቸው ስለዚህም አንድ አማኝ በክርስቶስ ለዓለም ሁሉ እንዲማልድ ነው የተጠራው ፤ ይበልጥ በክርስቶስ በሆነ ቁጥር ደግሞ ምልጃውም እንዲሁ ይበልጥ ለእግዚአብሔር የተወደደ እየሆነ ይሔዳል ቅዱሳን ደግሞ ይበልጥ ከክርስቶስ ጋር በመዋዳቸው ምልጃቸው ከአማኞች ሁሉ ይበልጥ የተወደደ ነው ፤ እንዲሁም በሁሉ ቅድስት የሆነች እመቤታችን ደግሞ በፍጹም አንድነት ከልጇ ጋር ናትና ቅድስናዋም ከሁሉ የላቀ ነውና ምልጃዋ ከሁሉ ቅዱሳን ይልቅ የተወደደ ነው! ይህን ግን አስታውሱ የዚህ ሁሉ ምልጃ ተወዳጅነት የተመሠረተው ከክርስቶስ ጋር ባለ ውሕደት ነው፤ ሁሉ በእርሱ ነውና!
❤ 91
6 November 2025
ኪ
16:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንዲህ አስቤያለሁ አንድ ቶፒክ እንመርጣለን ከዛ በዛ ቶፒክ አንብበን እንወያይባቸዋለን ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን live ይኖረናል።

እናማ እዚህ ያላችሁ የኪዳኑ ሕዝቦች ከኔ ጋር የጥናት ኪዳን መዋዋል የምትፈልጉ በቻናሉ DM አናግሩኝ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምፈልግ የምትፈልጉ ቶሎ በሉ።
❤ 71 🔥 4
9 November 2025
ኪ
14:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
I can't 😂😂
🤣 108 😁 10 ❤ 4
10 November 2025
ኪ
20:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሞቼ ነበር ተቀብሬ ጌታ ወደኔ ባትመጣ
አንተ ሞቴን ባትሞትልኝ ወዴት ነበር የኔ እጣ
❤ 158 ❤‍🔥 22 👍 11 🥰 7 😢 6
11 November 2025
ኪ
17:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
በአርሲ ላይ የምዕመናን ሞት አሁንም እንደ ቀጠለ ነው ከመንግሥትም ሆነ ከሃይማኖት ተቋማት ምንም አይነት ፍትህ እንደማናገኝ ግልጽ ነው ስለዚህ ፍትሐን ለሰማያዊ አባት እያመለከትን እኛ ግን በምድር ልንደራጅ ያስፈልገናል ጠንካራ ክርስቲያናዊ ኅብረት ያስፈልገናል እርስ በእርስ መደጋገፍ የሚያስችለን ሐዋርያዊ ኅብረት የሐዋርያት ሥራን ስታነቡ በኢየሱሳሌም ላይ ረሃብ በሆነ ጊዜ ምዕመናን ናቸው ከየአቅጣጫው እርዳታ ሲሰበስቡላቸው የነበረው እኛም እንደዚህ አይነት mindset እናዳብር ክርስቲያን እስከሆነ ድረስ በክርስቶስ የተወደደ ወንድሜ ነው እርሷም ክርስቲያን እኅቴ ናት ያን ጊዜም በኅብረታችን ብዙ ነገሮችን እናሳካለን ተፈሪም እንሆናለን። ያለበለዚያ እያለቀስን ነው የምንጠፋው!
❤ 193 😢 17 😎 3
12 November 2025
ኪ
17:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://ngl.link/kidel19

ማንነታችሁ ሳይታወቅ በዚህ ጥያቄዎችን መጠየቅ ትችላላችሁ።

Weird questions ያላችሁ ሰዎችም ተመቻችቶላችኋል 😁
🔥 13 😁 5 ❤ 2
ኪ
18:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
እውነት ለመናገር የጥንት ሙፈሲሮች ምክንያቱን አናውቅም ምሥጢር ነው ብለው ነው ያለፉት አሁን ያሉ አቃብያን ናቸው plural of majesty እየተጠቀመ ነው የሚሉት እንጂ በጥንታውያኑ ዘንድ የለም
😁 38 👍 4
ኪ
20:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰይጣን ሐሳዊው መሢሕ አይደለም ሐሳዊው መሢሕ ሰው ነው በእርግጥ አንዳንዶች incarnate satan (ሥጋን የተዋሐደ ሰይጣን) ነው ያሉ አሉ ግን እሱ minor interpretation ነው ዋናው ነገር ግን ሐሳዊው መሢሕ በሰይጣን የተታለለ ሰው ነው።

ሰይጣን ትንቢቶቹን እያወቀ እንዴት ያስፈጽማል? እሱ በጣም ትዕቢተኛ ነው ትዕቢቱ የእግዚአብሔር ትንቢት ራሱ ማስለወጥ የሚችል እስኪመስለው ድረስ ራሱን ያታልላል ይህም ከባድ self delusion ውስጥ ይከተዋል self delusion ውስጥ ያለ ሰው ነገሮች እርሱ በማይፈልገው መንገድ እንደሚሆኑ እያወቀ ራሱ ለመወለጥ በጣም ይጥራል ሰይጣን ደግሞ እራሱ የውሸት አባቷ ስለተባለ ትዕቢቱ ትልቅ delusion ውስጥ ሊጥለው ይችላል።

ሌሎች ሰፊ ማብራርያ ሚፈልጉ ጥያቄዎች የጠየቃችሁ አላችሁ ለእነርሱ ጠብቁኝ መጀመሪያ በአጭሩ የሚመለሱትን ልመልስ (ደግሞ ለምትልኩት ጥያቄ እዛው መልስ መስጠት አልችልም እዚህ ነው ምመልስላችሁ)
👍 32 ❤ 10
ኪ
21:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከዚህ በፊት ጽፌበታለሁ አብዛኞቹ አባቶች የሚስማሙበት ክርስቶስ ነው ብለው ነው። በኢትዮጵያም ቢሆን አንድምታችን መጀመሪያ የሚያስቀምጠው "የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ" ነው ብሎ ነው ገብርኤል ነው የሚለው ሁለተኛ ትርጓሜ ነው (እርሱንም ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ማለት ነው ብሎ ስለዚህ ይህም ቢሆን ክርስቶስን ነው ሚያመለክተው)።
❤ 42 👍 1
ኪ
21:40
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይህንን ቃል የተናገረው ጌታችን ሳይሆን ጌታ እየመሰለው ባለው ምሳሌ ላይ የነበረው መኮንን ነው ከቁጥር 11 ይጀምራል ታሪኩን

Luke 19 አማ - ሉቃስ
11: እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ።
12: ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ መኰንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።

ስለዚህ ይህ መኮንን ነው በፊቴ እረዷቸው ያለው ጌታ ይህንን ታሪክ quote እያደረገ ብቻ ነበር።
❤ 40 👍 3
21:54
1. አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2. የተወለድኩት ወደ ሐረርጌ አከባቢ ነው 12 ጨርሼ ግቢ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደረሰኝ አዲስ አበባ መጣሁ የቅብጥ ቤተክርስቲያን እንዳለ ሰማሁ ልየው ብዬ ሔድኩ በዛሁ አስቀሩኝ በአጭሩ ይሄ ነው።
3. ከሐገር ውስጥ ዲ/ን ያረጋል ፣ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
ከውጪ: አባ ታድሮስ ማላጢ
❤ 61 👍 10
21:54
21:54
13 November 2025
ኪ
09:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 3
09:21
ይሄን ጥያቄ honest ሆኜ ለመመለስ ልሞክር እኔም ለረጅም ጊዜ struggle አደርግበት ነበር ለምንድነው ለመፈጠሬ እኔ ራሱ ፈቃዴን መስጠት የሌለብኝ እያልኩ ብዙ እብከነከን ነበር እኔን ከዚህ ስሜት እንድወጣ የረዳኝን ነገር ልናገር፡

አንደኛ the task is impossible ለመፈጠራችን ፈቃድ ለመስጠት እኛ መጀመሪያ መኖር አለብን መኖር ብቻ አይደለም ምርጫዎችን ሁሉ ማወቅ አለብን ፤ ምርጫዎቹን ለማወቅ ደግሞ መጀመሪያ ሕይወትን ኖረን ማየት አለብን ስለዚህ ጥያቄው ሳንኖር መኖር አለብን እንደማለት ነው which is a contradiction. እግዚአብሔር ምንም ማድረግ ይችል የለ እንዴት ሳይፈጠረኝ መፈጠር እንደምፈልግ ምርጫ አይሰጠኝም? ብዬ አስቤም ነበር ግን ይሄ ሁሉን ማድረግ መቻል ምን ማለት እንደሆነ ካለመረዳቴ የመጣ ጥያቄ ነው ሁሉን ማድረግ ማለት "logically impossible" የሆኑ ነገሮችን ማድረግ ይችላል ማለት አይደለም ይልቅስ "doing all things that are logically possible" እንደማለት ነው ስለዚህ ሳንፈጠር ለመፈጠራችን ምርጫ ይስጠን ማለት is impossible even for God.

ይህ መልስ ከሎጂክ አንጻር ስለሆነ ወደ ልብ ላይገባ ይችላል ግን አንድ ልብን የሚያጽናና የሚያረጋጋ ነገር ነው ይበልጥ የማስበው ማለትም አሁን ላይ ሕይወቴ በማን እጅ ቢሆን ይሻላል? በእኔ ወይስ በእግዚአብሔር? በእኔ እጅ ብቻ ከሆነ እንደማበላሸው አውቃለሁ እኔ ምንም የማላውቅ ደካማ ነኝና እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል ፤ ሁሉን ይወዳል ፤ ሁሉን ማድረግ ይችላል ስለዚህ እሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ለመልካም ነው። እስቲ እናስበው እውነት ሳንፈጠር ምርጫችን መስጠት የምንችል ሆነን ቢሆን ኖሮ ስንቶቻችን ሕይወታችንን እናበላሽ ነበር? ነገር ግን ምርጫው 100% በእግዚአብሔር እጅ ብቻ በመሆኑ ለመልካም እንደሚሆን guaranteed ነው ፤ no one fails this one because God knows no failing. አስቡት እስቲ ሕይወትን የሚያክል ነገር ላይ የእኔ እጅ ቢኖርበት ምን ሊፈጠር እንደሚችል። ይህ ደግሞ ሌላም የሚያረጋጋ መልስ ይሰጠናል እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል የወደፊት ምርጫችንንም ያውቃል ስለዚህ የፈጠረን ራሱ በወደፊት ምርጫችን መሰረት አለመሆኑን በምን እናውቃለን? ወንድሜ ወይም እኅቴ አሁን ላይ ሕይወት ከብዶ እንዲህ አይነት ስሜት ሊመጣ ይችላል ነገር ግን ወደ ፊት የሚሆነውን አናውቅም እኛ ለሕይወታችን ምናመሰግበትም ጊዜ ይመጣል ስለዚህ ልክ ስንፈጠር መሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነው ሁሉ አሁንም ፈቃዳችንን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ለማስገዛት እንጣር because God's will knows no failing.

እንግዲህ ይህንን ነው ልል የምችለው ወንድሜ ወይም እኅቴ እግዚአብሔር ይጠብቅህ/ሽ በDM ብታዋራኝ/ሪኝ ግን ደስ ይለኛል እኔም ይሄን ስሜት ስለማውቀው ማውራት እንችላለን።
❤ 81 ❤‍🔥 11 👍 5
ኪ
18:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሄ መቼስ ሮሜ 8፡34ን ለማመልከት ነው "የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" የሚለው "የሚፈርደው" መባሉ ነው ይህ ደግሞ ኅዳጉ ላይ "ግሪኩ የሚፈርደው ይላል" ስለተባለ፤ ለምን ይህ እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም ግሪኩ የሚማልደው ካለ እና ጳውሎስ በግሪክ ከጻፈ በቦታው መግባት ያለበት የሚማልደው መባል ነው ያለበት። ይህ የተደረገው ምናልባት ከግዕዙ ጋር ለማስማማት ይሆናል መግቢያው ላይ እንዲህ ይላል "የመጀመሪያው ትርጉም በግዕዙ መሠረትነት የተተረጎመ ባለመሆኑ ከግዕዙ እና ከሰብዓ ሊቃናት የዘር ልዩነት ያሳያል" ስለዚህ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ከግዕዙ ጋር ለማስማማት እየሞከረ ይመስላል ግዕዙ "ዘይትዋቀስ በእንቲአነ" ይላል ቀጥታ ሲተረጎም "ስለእኛ የሚከራከር" ማለት ነው ነገር ግን በመከራከር ፍርድን የሚያስፈርድ አድንምታም ስላለው መሰለኝ ብዙ የጥንት አማርኛ ትርጉሞች ስለእኛ የሚፈርደው ይሉታል ይህም ያንኑ ተከትሏል።

ሌላ የተቀየረ ተብሎ ከታሰበ 1ኛ ዮሐ 2፡1 ላይ "በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን" የሚለው "በአብ ዘንድ ጰራቅሊጦስ አለን" ተብሏል ይህም ግዕዙን የተከተለ ይመስላል ግዕዙ "ጰራቅሊጦስ ብነ ኅበ አብ" ይላልና። ነገር ግን ይህ የሚያስነቅፍ አይደለም ግሪኩም ቢሆን ጰራቅሊጦስ ነው የሚለው በዚህ አውድ ደግሞ ትርጉሙ ጠበቃ ማለት ነው።

ሌሎች ደግሞ "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይባረክ" የሚሉትን እንደ ኤፌ 1፡3 ቦታ አምላክ የሚለው ተትቶ "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይባረክ" ይላል ይህም ቢሆን ግዕዙን የተከተለ ነው ግዕዙ "ይትባረክ እግዚአብሔር አቡሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ" ይላልና ግሪኩ ግን አምላክ የሚለው አለው። ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን ይህ የሚያሳየው ግዕዙን ለመከተል በሚያደርገው ጥረት ይመስላል እንደዚህ የሚሆነው ጥያቄውን ለመመለስ።
👍 24 ❤ 18
19:02
ከሁሉም በላይ ደስታ በዚህ ዓለም በእኔ እጅ ከምሆን በጌታዬ እጅ መሆን ይሻለኛል እና ጌታ ሆይ ቶሎ ና እለዋለሁ ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፍርሃት "በቶሎ እመጣለሁ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለዋለሁ" የሚለው ጥቅስ ሽልብ ይልብኛል። ከዚህ ጥቅስ ጋር ተያይዞ ኮፕቲክ ቅዳሴ በጣም የምወደው ፓርት ነው አቡና እንዲህ ይላሉ " በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሣ ወደ ሰማያትም አረገ በአብ ቀኝም ተቀጠ የፍርድ ቀንንም ቆረጠ" ከዚያም አቡና ደረታቸውን እየመቱ እኛም እየመታን " ለእያንዳንዱ በጽድቅ ይፈርድ ዘንድ ይመጣል" ያን ጊዜም እኛ "አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን" እያልን እናዜማለን። ለሁሉም እንደየሥራው ሊፈርድ ይመጣል እኔ ግን በፊቱ የማቀርበው ሥራ የለኝም ይልቁንስ ምሕረቱን በፊቱ በእምባ አቀርባለሁ በደምህ የዋጀሀኝ ነህና ተቀበለኝ እንደ ምሕረትህም አድርግብኝ እለዋለሁ ፤ በዓለም እጅ ከምጣል በጌታ እጅ ብጣል ይሻለኛልና!

ማራናታ! ጌታ ሆይ ና!
❤ 97 🔥 4 👍 3
ኪ
20:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይህን ጥያቄ ልመልስና ይብቃኝ ማብራርያ ወደፊት ጠብቁ ግን በአጭሩ በጥያቄው መሠረት በሦስቱ ላስቀምጥ፡
Logical: Sola scriptura doesn't work.
Historical: Historically the church of the first 5 centuries , was Trinitarian , Miaphysite , Episcopal , sacramental , strongly emphasized synergistic salvation and Theosis etc. therefore the Church that best fits the early Church is Oriental Orthodoxy.
Biblical: Sola fide is born out of misunderstanding of certain pauline epistles especially Romans and Galatians ይሄን ጽድቅ እና ድኅነት video ላይ ሔጄበታለሁ እሱን ማየት ነው።
👍 53 🔥 11 ❤ 7
15 November 2025
ኪ
10:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
10:00
I think that you are making a big mistake.

በአባቶች ዘንድ የሚገኘው ሮም በክብር ቦታ ከፍ ያለች በመሆኗ ተቀዳሚ ቦታ ይሰጣት ነበር እንዲሁም ከተቀዳሚዎቹ ፓትሪያሪኬት አንዷ በመሆኗ ልክ እንደ እንስክንድርያ እና አንጾኪያ ከሌሎቹ appeal ይመጣላት ነበር ፤ እንዲሁም ቅዱስ ሔሬኔዎስ እንደሚነግረን በጴጥሮስ እና ጳውሎስ ሐዋርያነት የተመሠረተች እንደመሆኗ እና የሮም ኢምፓየር ዋና ከተማ እንደመሆኗ ትልቅ ክብር ነበራት።

ይህ ማለት ግን የሮሙ ፓፓ በዓለም በሙሉ የበላይ ሐገረ ስብከት አለው (Universal jurisdiction) ፣ ቤተከርስቲያን ለመባል ከሮሙ ፓፓ ጋር ኅብረት ያስፈልጋል ፤ የሮሙ ፓፓ ከዓለም አቀፍ ጉባኤ የበላይ ሥልጣን አለው ስለዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንኳን ፓፓው ካላረጋገጠው አይሆንም ፤ የሮሙ ፓፓ በጴጥሮስ መንበርነት ላይ ሆኖ ሲናገር በመንፈስ ቅዱስ ከስህተት ይጠበቃል ወዘተ የሚሉት claims በጥንቷ ቤተክርስቲያን በፍጹም አይታወቁም ከጊዜ በኋላ develop ያደረጓቸው ናቸው ይህ ብቻ ሳይሆን በአስተምህሮ ደረጃም ጭምር እርስ በእርስ ሲጋጩ እናያለን ለምሳሌ የዚህ ምርጡ ማሳያ (Heac Sancta by council of constance and Pastor aeturnes by Vatican I) ክርስቶስ በቤተክርቲያኑ ላይ አንድ ሰው የበላይ አላደረገም ፤ አንድ ሰውም የከርስቶስ ቤተክርስቲያን ላይ የበላይ ነኝ ብሎ እራሱን ማወጅ አይችልም ይህ Tyranny ነው።

የካቶሊክ አፖሎጂስቶች ግን ምን ያደርጋሉ የመጀመሪያዎቹን ማስረጃዎች ለሁለተኛው claim ያውሉታል primacy of honor ለvatican I papacy ማስረጃ ሊሆን አይችልም። By the way ካቶሊክ ከማልሆንባቸው ምክንያቶች መካከል ትልቁ ይሄ ነው በጣም ግልጽ ስህተት ነውና ከፈለክ በውስጥ እያውራና ማስረጃ ያልካቸውን ማየት እንችላለን።
❤ 68 👍 8
17 November 2025
ኪ
12:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
በአጭሩ ያስምራል ማለት ነው። የአቤል ደም ወደ እግዚአብሔር ጩኸቱን ያሰማው የተፈጸመብኝን ግፍ እይ ተበቀልልኝ እያለ ነው ፤ የኢየሱስ ደም ግን የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ይቅር ማስባል እንዲያስችል ወደ አብ የቀረበ ነው።

እኛ አብን ደሙን ስላፈሰሰው ልጅህ ይቅር በለን ወለድን ደግሞ ስለ ደምህ ይቅር በለን እያለን እንለምናለን እግዚአብሔርም ስለ ደሙ ይቅር ይለናል በኢየሱስ ደም ፊት የሚቆም የትኛውም ኃጢአት የለምና ይህ past action ብቻ አይደለም አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ወደ ሰማያት ወደ እግዚአብሔር ፊት ገብቷል ስለዚህም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ያለ active ምሕረትን አሰጪ ነው። እንጂ ደም አፍ አውጥቶ ማርልኝ ይላል ማለት አይደለም figuratively ለመናገር ነው። ለምሳሌ በግፍ የፈሰሰ የአቤል ደም ሲታይ ቃል ባያወጣ እንኳን ከቃል በላይ ግፉ ሰማያትን ቀዶ ይሰማል እንዲሁም ኢየሱስ በደሙ ሰማያት በመግባቱ ስለዓለም ያሳለፈው መከራ እና ያፈሰሰው ደም ዓለምን ሁሉ ለማስማር ያለ ቃል ከቃል በላይ ይናገራል።
❤ 65 🔥 8 👏 1
ኪ
16:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
መጽሐፉንም ሆነ መጽሐፉ ላይ ያሉትን statements እያልን አይደለም ሲጀመር መጽሐፍም ሆነ statement inerrant (ስህተት አልባ) ይባላል እንጂ infallible አይባልም። Fallible or infallible ተብሎ የሚገለጸው ስህተት መሥራት ለሚችል ወይም ለማይችል አካል ነው እንጂ አካሉ ለተናገራቸው ወይም ለጻፋቸው statements አይደለም።

ስለዚህ in the appropriate sense infallibility ለመጽሐፍ ቅዱስ ራሱ አይሰጥም። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ infallible ነው ሲሉ መጽሐፉን የጻፉትን ሐዋርያት ለማመልከት ነው ይላሉ ስለዚህ ከተባለ እንኳን መጽሐፉን የሚያመለክት ሳይሆን የመጽሐፍቱን ጸሐፊዎች የሚያመለክት መሆኑን ልብ በሉ።
❤ 45 🥰 4
19 November 2025
ኪ
17:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/LAxQDxao6z8?si=NDJZfMniWfkBMC3u

በትልቁ እስክንገለጥ ድረስ ይሄ ይበቃችኋል 😁
🔥 43 😁 6 ❤ 4 🥱 1
20 November 2025
ኪ
11:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጥያቄ
ስለ እኔ ገበዝ ቅዱስ (Patron Saint) ቅዱስ አትናቴዎስ ቪዲዮ ልሠራላችሁ እያለሁ የልጅነት ሕይወቱ ላይ ያለው ነገር ትኩረቴን ሳበኝ በእርግጥ ከዚህ በፊትም የዲያቆን ያረጋልን "ቅዱስ አትናቴዎስ ሕይወቱ እና ትምህርቱ" የሚለውን መጽሐፍ ሳነብም ጥያቄ ሆኖብኝ ነበር አሁን ግን መልሼ ሳየው I connected the dots 😅

የእስክንድርያ 19ኛው ፓፓ ፣ ፓፓ እለስክንድሮስ ወደ ውጪ ሲመለከት ልጆች ሲጫወቱ ያያል ጨዋታው መሃል አንደኛውን ልጅ ጳጳስ አድርገውት ሲያጠምቃቸው እየተጫወቱ ነው ጳጳስ ሆኖ የተጫወተው አትናቴዎስ ነው። እለእስክንድሮስ ግን ሲመለከት አትናቴዎስ ጥምቀቱን የፈጸመው በትክክለኛው formula and intent ነው ስለዚህም እነዚህ ልጆች validly ተጠምቀዋል በማለት እለስክንድሮስ በሜሮን ብቻ ነው confirm ያደረጋቸው።

እዚህ ላይ ጥያቄው በዚህ ጊዜ አትናቴዎስ ዲያቆን እንኳን አልነበረም ስለዚህ ጥምቀት valid እንዲሆን በውኃ በvalid form and intent መፈጸሙ ብቻ ይበቃል ማለት ነው አጥማቂው ምንም እንኳን ካህን ባይሆን?
❤ 28 🤔 13 👍 1
21 November 2025
ኪ
11:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
The Twelfth Day of the Blessed Month of Hatour

Festival of the Honored Archangel Michael

On this day the church celebrates the feast of the honored Archangel, Michael, the head of the hosts of heaven, who stands at all times before the great throne of God, interceding on behalf of the human race.

His intercession be for us and Glory be to our God, forever. Amen.
❤ 126 🙏 9 🔥 8
22 November 2025
ኪ
11:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቲያኖች ግን እናንብብ እናጥና እንማር የምር በእኛ እውቀት ማጣት ብዙ ነፍሳት እየጠፉ ነው። ብዙ ጥያቄዬን ሚመልስልኝ አጣሁ ስለዚህ ወጣሁ የሚሉ ኤቲስቶች ጥያቄ እያየሁ ነው ፤ ጥያቄዎቹን ሳያቸው ግን እዚህ ግባ የማይባሉ በቀላሉ የሚመለሱ ናቸው እውነት ለመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ ደህና ጥያቄ የሚጠይቅ ኤቲስት የለም። እኔ ካየኋቸው ጥያቄዎች አንጻር እነዛ ጥያቄዎች የሚመልሳቸው ጠፋ ማለት ክርስቲያኖች ምንም አናውቅም ማለት ነው።

ስለዚህ እናንብብ ፣ እናጥና አሁን ላይ እውቀት በደጃፋችን ነው ያለው ላለማወቃችን ምንም ሰበብ መጥቀስ አንችልም ስንፍና ካልሆነ በስተቀር ብዙ ሰው አይቻለሁ ማወቅ እፈልጋለሁ ይላል አንድ መጽሐፍ እንኳን ማንበብ አይፈልግም ታድያ እንዴት ነው ሳታነብ የምታውቀው? "ለሚጠይቋችሁ ሁሉ ለመመለስ የተዘጋጃችሁ ሁኑ" የሚለውን ምንም እየተገበርን አይደለም እኮ ፤ ያ ሁሉ ሰው በፕሮቴስታንት እና ተሐድሶ የተወሰደብን የእኛ ዓለመንቃት ነበር ፤ አሁንም ግን አልነቃንም ብዙዎች እየወጡ ነው። ቀጣዩ ትውልድ ደግሞ አስቡት በብዙ ወገን ለሚመጣ መረጃ የተጋለጠ ነው ስለዚህ ብዙ ነገር መጠየቁ መጣራጠሩ ፣ መመርመሩ አይቀርም እንዲሁ ወላጆቹ ባሰመሩለት መስመር ፣ ባስተማሩት ሃይማኖት ብቻ የሚቀጥል ትውልድ አሁን ላይ እያበቃ ይመስላል ፤ እኛ ግን እሱን ለመመከት ምንም ዝግጅት የለንም ቢቻልስ ዝግጅቱ ተቋማዊ መሆን ነበረበት (ቤተ ክህነትን ማለቴ አይደለም እሱን እርሱት ተስፋም የለው እነርሱ ገንዘብ ብቻ ይበዝብዙ) ነገር ግን በግለሰብ በማኅበር ደረጃ ተነሥተን እንቅስቃሴያችንን ተቋማዊ ማድረግ አለብን ለትውልድ የሚሻገረው ተቋም ነውና።
❤‍🔥 96 ❤ 30 👍 11 🙏 5 💯 5 👌 4 🔥 2 👏 1
ኪ
21:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
pure confession ልጻፍ ብዬ ይህን ጻፍኩ እንግዲህ እንዲመቻችሁ አይደለምና የጻፍኩት የጻፍኩትን ጻፍኩ ብዬ ለቅቄዋለሁ

ትርጉሙ ግን ምንድነው?

ለረጅም ጊዜ የሕይወት ትርጉም ምንድነው እያልኩ አስባለሁ አከባቢዬ ያለው ሰው ሁሉ ይኖራል እኔ ግን እየኖርኩ አይመስለኝም survive እያደረኩ እንጂ በዚህ ዓለም የምኖርለትን ምክንያት አላገኘውምና ሃብት ፣ ንብረት ፣ ዝና እነዚህ ሁሉ የመጨረሻቸው ትርጉም አይገባኝም። ይህ ማለት አልፈልጋቸውም ማለት አይደለም ማን ቢኖረው ይጠላልና ግን የመጨረሻ ግባቸው ምንድነው? በመጨረሻ ሁሉም ይጠፋል ይህቺ ትልቅ አድርገን የምናስባት ዓለም actually a small rock floating around the vastness of a universe that doesn't care about anything ናት ፤ ሊያውም ወደ heat death እያመራ ያለ universe እኛ ግን ምድር አንድ ዙር በጸሐይ ዛብያ ዞረች ብለን እናክራለን hooray አዲስ ዓመት! ምድር ግን ደንታ የላትም እሷ ጸሐይ ላይ መዞሯን ትቀጠላለች ፣ ጸሐይም around the galaxy , the galaxy around the universe , and the universe expanding to its death. We are insignificant at the cosmic level ፤ ሕይወት ፍትሐዊ አይደለችም እንኳን ልትሆን ስለእኛ ፍትሕ system ምታውቀው ነገር የለውም ከ order መጣች ወደ ምስቅልቅልነቷ ትቀጥላለች። ታድያ ይህን እያወኩ ሐብት ንብረት ምናምን ለሚሉት ነገሮች ልኑር ከዛስ? በቀላሉ የሚገኝ ነገር አይደሉም ይህ ሁሉ ልፋት ግን በመጨረሻ ግቡ ምንድነው? ምንም ዐለም ደንታም የላት። ደስታው ፣ ሃዘኑ ፣ ንዴቱ ፣ ጸጸቱ ፣ ሳቁ ፣ እምባው ሁሉም ነገር በመጨረሻ ምንም ግብ የለውም መጀመሪያውኑ እንዳልነበረ ይሆናል "ሰብሰ መዋዕሊኡ ከመ ሳዕር" አለ መዝሙረኛው ፤ በአትክልት ቦታ ላይ ያለች ያማረች ጽጌሬዳ ፣ ለማማር ብዙ ዋጋ የከፈለች ነገር ግን በመጨረሻም የጠወለግች ማማሯ ultimately ያልጠቀማት እንደዛ ነው የሰው ሕይወት ይመጣል ይገነባል የምድር ሃያል የሚባል ሥርወ መንግሥት እንኳን ቢመሠርት እንደ አክሱም ፣ እንደ ሮም ፣ እንደ ፋርስ በመጨረሻው ይጠፋል። በኋላ የሚቀረው በአእምሮው ውስጥ ያለው ትዝታው ብቻ ነው በዓለም ላይ ትንሽ እንኳን influence ካለው ደግሞ የታሪክ መጽሐፍ ግርጌ ላይ ሊገባ ይችላል ፤ እሱም ግን በመጨረሻው ይጠፋል መጀመሪያውኑ እንዳልነበረ ይሆናል፤ ታድያ ጥቅሙ ምንድነው?

ለረጅም ጊዜ nihilist ነበርኩ ዛሬ ሞትኩ ነገ የዛሬ መቶ ዓመት ምን ይጠቅማል ሁሉም ነገር meaningless ነው ዝም ብዬ survive ላድርግ ብዬ ኖራለሁ ስቃለሁ ፣ እጫወታለሁ ግን at the deep level ከማንም ጋር connect አላደርግም even with family አይገባኝም ለምን መኖር እንዳለብኝ ለምን እንደመጣሁ ስለዚህ እስክሞት ድረስ ዝም ብዬ ደስ ያለኝን ነገር እያደረኩ ልኑር። ግን what if ከዚህ ሁሉ meaninglessness በላይ ትርጉም ያለው ነገር ቢኖር? ምናልባትም ይህን ዓለም የፈጠረ አምላክ መቼስ እንዲህ ያለ meaninglessness ውስጥ አይተወንም? አይደል? አይደል? ምን አውቄ የዛኔ ዓለምን የፈጠረ አምላክማ አለ ግን የፈጠረኝ ለምን እንደሆነ የማውቀው ነገር የለም። ይህ search for meaning ብቻ ግን purpose ይሰጠኛል ፤ I love existential shows and sci fis. Time travel , dimensional travel etc. ብቻ out of the ordinary የሆነ ነገር ሁሉ ወዳለሁ ልብ ወለድም ከዚህ ዓለም ያወጣኛል።

የኮሮና ጊዜ ቤት ቁጭ ስል ግን ይበልጥ የማሰቢያ ጊዜ አገኘሁ የልጅነቴን አብነት ትምህርት why not ብዬ ቀጠልኩት ሌላ ሥራ ስለሌለኝ ቅዳሴ ፣ ኪዳን ፣ ማኅሌት ፣ ንግሥ አንድ ነገር አያመልጠኝም ነበር ከዚህ meaningless ዓለም ያወጣኛል የፈጠረኝን ኢየሱስን ያሳየኛል ፤ አየሁት ፣ አየሁት ፣ አየሁት ወደድኩት አፈቀርኩት። ግዕዝ ያወኩት ያኔ ነው አንድ ቀን ደስ የሚል ዜማ ሰማሁ ዲያቆኑ "ጸሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወከዋክብት ወድቁ ፍጡነ ከመ ኢይርአዩ እርቃኖ ለዘ አልበሶሙ ብርሃነ ፤ በአንጻረ መስቀል ቀዊሞ ዮሐንስ በከየ እንዘ ይብል ውይልየ ወይልየ አማኡተ ከርሱ ከመ ነደ እሳት ውእየ" እያለ ያዜማል ከዜማው ጋር ልቤ ቀለጠ አይኔ እንባ በእንባ ተሞላ የኔ ኢየሱስ ይወደኛል የሚል ስሜት ተሞላሁ በእርግጥም ይወደኛል ፣ ይህ ዓለም meaningless ነው እርሱ ግን ከዓለምም ያለፈ ለዘለዓለም የሚኖር ነው ፤ ይህን ሳስብ ሳስብ ሌላ ቀንም መልክአ ሥዕል ላይ ይመስለኛል "ዓለሙኒ ኃላፊ ፍትወቱኒ ኃላፊ እስመ ኩሉ ኃላፊ ውእቱ" ሲያዜም ሰማሁ ልክ ነበርኩ ዓለሙ ያልፋል ፣ የዓለሙ ምኞትም ያልፋል ሁሉ ነገር ሃላፊ ነው የማያልፍ ኢየሱስ ብቻ ነው አሁን ላይ ትርጉሙን ባላውቅም ትርጉም የሚሰጠኝ ግን ኢየሱስ ብቻ ነው ስል ተገዛሁለት ወደድኩት አፈቀርኩት። ያን ጊዜ ነበር ድቁና የተሾምኩት ቁርባንም የጀመርኩት 2 ወርም ሳይሞላኝ ግን የኮሮና ጊዜ አበቃና ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠራን እንግዲህ የትርጉም ፍለጋ ጉዞ ተጀመረ።

ስለማያልፈው ኢየሱስ ማወቅ አለብኝ ብዬ የነገረ መለኮት ጥናት የጀመርኩት ያኔ ነው ጌታዬን እየተቀበልኩት እሱን ፍለጋ የያዝኩት በዚህ ጥናቴ ውስጥ ነበር Theosis የሚል concept ያወኩት ማለትም ጌታ ለካ የፈጠረኝ እርሱን ተዋሕጄ ከእርሱ ጋር እንድኖር ነው አስባለኝ እርሱ ሰው የሆነው እኔ አምላክ እንድሆን ነው። የሆነ ምሳሌ ትዝ ይለኛል "አንድ ሰው የማያልቅ ትልቅ ስጦታ አለሁ ቢሰጥ ቢሰጥ አያልቅበትም ይህ ስጦታ ደግሞ በዋጋ የማይተመን ትልቅ ነገር ነው ፤ ምን ያደርጋል ይህ ሰው? ለሚወዱት ይሰጣቸዋል" ይህንን ያዝኩና እግዚአብሔር የማይቀማ የማያልቅ የባሕርይ አምላክነት አለው ፍቅሩም ደግሞ ገደብ የለውም ስለዚህ ፍቅሩ ሞልቶ ስለፈሰሰ የማያልቀውን ስጦታውን ያካፍለን ዘንድ ፈጠረን እያልኩ አሰብኩ ስለዚህ በዚህ ዓለም ውስጥ ያለኝ ትልቁ ዓላማ አንድ ነገር ብቻ ነው ከኢየሱስ ጋር መዋሐድ ሌላው ሁሉም አይጠቅምም ፣ ሌላው ሁሉም ያልፋል "እርሱ ብቻ ግን የማይሞት ነው" የዐለም ደስታ ይቀማል ፣ የማይቀማ ደስታን የሚሰጥ ግን እርሱ ብቻ ነው ፤ ዓለም እንደሚሰጠው ሰላም ያይደለ የማይቀማ ሰላም ይሰጠናል ይወደናል ለዘለዓለሙም ይጠራናል።

ስለዚህ ሁሌም ሞትህን አስብ ፣ ሞትህን አስብ ፣ ሞትህን አስብ አልኩት ለራሴ በሞት ውስጥ ሕይወት አለና በምስቅልቅሎሽ ውስጥ order አለና ፣ በ meaningless ዓለም ውስጥ ኢየሱስ አለና።
❤ 167 ❤‍🔥 19 🔥 11 👍 6 👏 3 🥰 2 🤯 2 😢 1 👌 1
24 November 2025
ኪ
09:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዛሬዋ ዕለት ታላቁ ገባሬ ተአምራት በሕዝቡ ሁሉ የተወደደ ማር ሚና በሰማዕትነት ዐረፈ።

እናቱ አፎምያ "አሜን" የሚል ቃልን ከእመቤታችን ሥዕል ሰምታ በወለደችው ጊዜ ልጇን "ሚና" አለችው "ታማኝ" ማለት ነው ፤ በእውነትም ታማኙ ሚና አባቱ አውዶክስዮስ በሞተ ጊዜ ገና በወጣትነቱ የአባቱን ሥልጣን ቦታ ቢይዝም ንጉሡ ዲዮቅሊጣኖስ የክርስቲያኖችን ሞት በአወጀ ጊዜ ታማኝነቱን አጸና እንጂ አምላኩን ክርስቶስን አልካደም በታማኝነት አምላኩን በደም መሠከረ።

ዘመነ ሰማዕታት ባበቃ ጊዜ በእግዚአብሔር መልአክ መሪነት ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሥጋውን በግመል አድርጎ ከእስክንድርያ ወጣ አድርጎ ቀበረው ፤ እግዚአብሔር ግን ቅዱሱን መግለጥ በፈለገ ጊዜ ከሥጋው ብዙ ተአምራትን አሳየ የዕረኞችን በጎች ፈወሰ ፣ የንጉሡን ልጅም በመፈወስ የሥጋውን ቦታ ገለጠ ቤተክርስቲያን ሠርተውም ሥጋውን ቀበሩት ታላቁ ሚና ግን ተአምራትን ማሳየት አላቆመም ስለዚህም ሕዝቡ ሁሉ በአንድ ድምጽ ገባሬ ተአምር አሉት።

በመጨረሻው ለዘመናችን ቅርብ የሆኑት የማር ሚና ወዳጅ ፓፓ ቄርሎስ 6ተኛ በቤተክርስቲያኑ ታላቅ ገዳምን ገነቡ እስካሁንም በመላዋ ግብጽ ገዳሙ ይጎበኛል ማር ሚናም ተአምራትን ያደርጋል።

የማር ሚና አማላጅነት ከእኛ ጋር ይሁን ክብርም ሁሉ ለሚና አምላክ ለእግዚአብሔር ይሁን አሜን!

ሰላም ለከ ሐራዊ መስፍን ። ሰማዕተ መድኅን ። ዘሰመየተከ ሚናስ ዘፆረተከ ማሕፀን ። አመ ጸለየት ጸሎተ እንዘ ይእቲ መካን ። እምሥዕለ ማርያም ሰሚዓ ዘይቤ አሜን ።

(ፎቶው የዛሬ ዓመት ሕዳር 15 ነው)
❤ 140 ❤‍🔥 5 👍 4 🥰 4
25 November 2025
ኪ
15:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
ብዙ ሰው አንድ ቤተክርስቲያን ነን የሚለውን አሁንም የተረዳ አይመስለኝም።

እኛ ስንጠመቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ውስጥ ብቻ አይደለም የምንቀላቀለው ዓለም አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የክርስቶስ አካል እንሆናለን ስለዚህ በሁሉም ጊዜ በሁሉም ቦታ ካሉ ክርስቲያኖች ጋር ኅብረት አለን።

ክህነትም እንዲሁ ሰው በክህነት ሲሾም ወደ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ካህን የሚሆነው። ያለበለዚያ ኢትዮጵያ የተሾመውን ሰው ሕንድ መልሼ ልሹመው ካለች basically የኢትዮጵያ ሹመት valid አይደለም እያለች ነው ይህ ደግሞ የማይሆን ነው። እንኳን እኛ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለን ይቅርና በኦርቶዶክስ ክህነትን የተሾመ ካቶሊክ እንኳ ቢሆን መልሳ አትሾመውም valid ክህነት እንዳለን ይቀበላሉና።
❤ 98 🔥 11 👍 2
28 November 2025
ኪ
10:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
ስለ እግዚአብሔር መኖር Atheist ነን ባዮች እየበዙ ስለሆነ እሱ ላይ ልሠራ አስብያለሁ ለእርሱ ጠብቀኝ።

ኢየሱስ እርሱ የተገለጠው አምላክ ለመሆኑ ደግሞ ከዚህ በፊት ትንሣኤ ላይ የሠራሁትን ተመልከተው : https://t.me/KidanZeIyesus/462
❤ 58 👍 8
2 December 2025
ኪ
10:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
I present to you the life of my Personal hero , Crown of the Syrians , champion of Orthodoxy , the man who Chalcedonians feared the most, St. Severus of Antioch.

ኦህ ሳዊሮስን እንዴት እንደምወደው እስቲ please አንብቧት ሥራዎቹንም ወደፊት በደምብ እናያቸዋለን።
❤ 73 🔥 7 👍 4
ኪ
13:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
🔥 42 ❤ 20 👏 1
4 December 2025
ኪ
09:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
የመምህር ግርማ ባቱን "የነገረ መለኮት መግቢያ" መጽሐፍ የሌላችሁ ይህን መልሱና ተሸለሙ

"አቤቱ ፡ የሕማምህን፡መታሰ ቢያ፡እናደርግ ፡ ዘንድ፡ከሙታንም ፡ ተለይተ ህ ፡ በመነሳትህ 'እንመስልህ'ዘንድ፤ የተሰበ ሰብን ፡ እኛም ፤ አቤቱ ፡ አምላክ' ሆይ ' እን ማልድሃለን ። ይህች፡ ኅብስት፡በተራራና ' በኮረብታ፡በበረሃና' በቈላ፡ መካከል ፡የተበ ተነች ፡ ስትሆን ፡ እንደ ' ተሰበሰበች ፤ ተሰብ ስባም ፡ አንዲት ፡ ፍጽምት ' ኅብስት ፡ እንደ ሆነች ፤ እንዲሁ ' እኛንም ፡ በመለኮትህ ፡ ከክፉ ' የኃጢአት ፡ አሳብ ' ሁሉ ' ለይተህ በፍ ጹም ' ሃይማኖትህ ' ሰብስበን ። "

ይህን እና ይህንን የሚመስል አነጋገር የኢትዮጵያ 3 ቅዳሴያት ላይ ይገኛል የትኞቹ ናቸው?

ሦስቱንም influence ያደረገው ደሞ አንድ ጥንታዊ ሰነድ ይመስላል እርሱስ የትኛው ነው?
❤ 51 👍 1
ኪ
17:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ይሄኛው ስለተደመሰሰ ጥያቄ እየላካችሁ ከሆነ ያልመለስኩት እያየኋቸው ስላልሆነ ነው ፤ ሌላ ልከፍት ነበር never again እዚሁ ቻናሉ DM ላይ ጠይቁ
🔥 5 🙏 2
6 December 2025
ኪ
21:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዛሬው presentation በዚህ ነበር record youtube ላይ እስክለቅ ይህን አንብቡት
@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
Kidan
❤ 41 🔥 7 👍 3
7 December 2025
ኪ
18:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 50 🔥 9
10 December 2025
ኪ
19:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
Rebaptism Controversy in the Early Church , council decisions and current state of Oriental Orthodox Churches pdf ነገር አዘጋጅቻለሁ ይለቀቅ ወይስ ይቆያችሁ 🧐
👏 49 👍 15 ❤ 13
ኪ
20:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
አንብቡት እና እንወያይበታለን በዛውም Share አድርጉት።

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 61 👍 7
14 December 2025
ኪ
20:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
“And now hear concerning faith that is based upon the Stone, and concerning the structure that is reared up upon the Stone. For first a man believes, and when he believes, he loves. When he loves, he hopes. When he hopes, he is justified. When he is justified, he is perfected. When he is perfected, he is consummated … then he becomes a house and a temple for a dwelling-place of Christ" Catechism of the Coptic Orthodox Church

እዚህ ላይ ምን አስተዋላችሁ?
❤ 43 👍 3 ❤‍🔥 1
18 December 2025
ኪ
15:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
Exodus 24 አማ - ዘጸአት
4: ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለዳም ተነሣ፥ ከተራራውም በታች መሠዊያን፥ አሥራ ሁለትም ሐውልቶች ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።
5: የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤልን ልጆች ጐበዛዝት ሰደደ።
6: ሙሴም የደሙን እኵሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደረገው፤ የደሙንም እኵሌታ በመሠዊያው ረጨው።
7: የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፦ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም፡” አሉ።
8: ሙሴም ደሙን ውስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፦ “በዚህ ቃል ሁሉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ፡” አለ።
❤ 43 🔥 7 👍 3
ኪ
16:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
አሮጌው ኪዳን እንዴት እንደጸና ተመለከታችሁን? ሙሴ የስምምነቱን ውል በመጽሐፈ ኪዳን ላይ ጻፈ ለሕዝቡም ማድረግ ያለባቸውን ነገረ ሕዝቡም መስማማታቸውን "እንታዘዛለን" በማለት ገለጹ ይህም ስምምነት እንዲጸና እንስሳ ተሠዋ ፤ ደሙም መሠዊያው ላይ እና ሕዝቡ ላይ ተረጨ ፤ ለኪዳኑም ምሥክር ይሆን እግዚአብሔር ሙሴን ታቦት ይሠራ ዘንድ አዘዘው በታቦቱም ላይ ምሥክሩን በሥርየት መክደኛው ላይ አደረገ "Exodus 25 አማ - ዘጸአት
21: የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ።"

ይህ ጊዜያዊው እና አሮጌው ኪዳን በዚህ መንገድ ጸና ነገር ግን ሕዝቡን ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርብ አልተቻለውም ስለዚህም የፊቱን ኪዳን ያስረጀ ዘለዓለማዊ ኪዳንን እግዚአብሔር ለሕዝቡ በማለበት በልጁ በኩል የሚሻል ኪዳንን አበጀ ፤ ሕጉ ሲለወጥ ካህኑም ሊለወጥ ግድ ነውና በመሐላ የተሾመ ከሌዊ ያልሆነ ካህን ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር በልጁ ማለ አይጸጸትምም የዕብርያውያኑ ጸሐፊ እንደሚለን፡

Hebrews 7 አማ - ዕብራውያን
22: እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
23 እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
26 ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤

ይህ ከፍ ያለ እና የታመነ ሊቀ ካህናት ራሱን ሊያቀርብ በበግ እና በኮርማ ደም ሳይሆን በራሱ ደም በሰው እጅ ወደ አልተሠራች መቅደስ ፤ ወደ ማለበት እግዚአብሔር ቀኝ ወደ ሰማይ ገባ ፤ ሰማያትንም በደሙ አሥተየረየ ፤ ደሙንም በሥርየት መክደኛው ላይ አይደለም በሰማያት አቀረበ ፤ በሕዝቡ ላይም አይደለም በአፋችው ውስጥ ረጨ ፤ ጊዜያዊም አይደለም የዘለዓለም ቤዛነትን አገኘ።

የዘጸአት 24ቱ የሙሴ የቃልኪዳን መጽሐፍ በክርስቶስ መጠቅለሉን ሲያበስር የዕብራውያኑ ጸሐፊ እንዲህ አለ፡

Hebrews 9 አማ - ዕብራውያን
20 ሙሴም ትእዛዛትን ሁሉ እንደ ሕጉ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ፥ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውኃና ከቀይ የበግ ጠጕር ከሂሶጵም ጋር ይዞ። እግዚአብሔር ያዘዘላችሁ የኪዳን ደም ይህ ነው ብሎ በመጽሐፉና በሕዝቡ ሁሉ ላይ ረጨው።
21 እንዲሁም በድንኳኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ደምን ረጨ።
22 እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።
23 እንግዲህ በሰማያት ያሉትን የሚመስለው ነገር በዚህ ሊነጻ እንጂ በሰማያት ያሉቱ ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መስዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ።
24 ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ!
❤ 33
16:30
In reply to this message
እግዚአብሔር ይዘዘላችሁ የኪዳን ደም ይህ ነው፡ በምድር ሳይሆን በሰማያት የቀረበ ፣ ከሞተ ተሠዊ የሚፈስ ሳይሆን ሞቶ ከተነሣ ተሠዊ (Victim) የሚፈስ ፣ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ፣ ምሥክሩን በልባችን ውስጥ የሚያጽፍ ፣ ወደ እርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ ፣ የኃጢአትን ሥርየትን የሚያስገኝ ።

Ooof I love the book of Hebrews.
❤ 57 🥰 5
21 December 2025
ኪ
11:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
መድኃኒት የኾነ ልጁን እንሰብካለን

"ወልዶ መድኅነ ንሰብክ ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ፣ ተሰብከ በኦሪት አክሊለ ሰማዕት ሠያሜሆሙ ለካህናት ወተስፋ መነኮሳት ወልዶ መድኅነ ንሰብክ ወልዶ መድኅነ ንሰብክ

መድኃኒት የኾነ ልጁን እንሰብካለን፤ ከዓለም በፊት ያለ በኦሪት የተሰበከ የሰማዕታት አክሊል የካህናት ሿሚያቸው የመነኮሳት ተስፋቸው የኾነ መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን ፣ መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን" መዝሙር ዘስብከት

" እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:23)

መልካም ዘመነ ስብከት መድኃኒት ክርስቶስን በቃል ብቻ ሳይኾን በሕይወታችን እንስበከው ልጁ ያለው ሕይወት አለውና ❤
❤ 150 🥰 10 👍 3 ❤‍🔥 2
22 December 2025
ኪ
11:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እኔ የማልጠቅም ደቃቃ ሰው ነኝ ፣ አንተ ግን ሁሉን የምትችል ከሃሊ ነህ ፤ አንተ ቅዱሰ ቅዱሳን ነህ ፤ እኔ ግን የኃጢአተኞች ዋና ነኝ ፤ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ኃጢአትን ብትቆጥርስ በፊትህ ማን ይቆማል? በደልን ባትሸፍንስ ማን በሰው ፊት በድፍረት ይሔዳል? ከበደሌ የተነሣ እንዳልተፈጠርኩ በጠፋሁ ፣ ምድር ተከፍታ በዋጠችኝ ነበር በቸርነትህ ታምኜ ግን ዛሬም አለሁ ይከውም ወደ አንተም እጸልያለሁ ጸሎቴን ላልከለከልህ ልመናዬንም ያላራቅህ ጌታ ሆይ ተመስገን።

ጌታዬ ሆይ አሁንም ከነኃጢአቴ ብዛት ወደ ቅድስናህ እቀርባለሁ በምሕረትህ ብዛትም በፊትህ እሰግዳለሁ ፤ እኔስ በጉባኤህ ልትቀበለኝ የማይገባኝ መጻተኛ ነኝ እኔ ግን ዋስትናዬን መሢሕህን አድርጌ በድፍረት በፊትህ እቀርባለሁ ፤ የልጅህ ሥጋ ኃጢአቴን የሸፈነልኝ በቀኝህ የተቀመጠ መጋረጃዬ አድርጌ በድፍረት ወደ ጸጋህ ዙፋን እቀርባለሁ አንድያ ልጅህ ጠላት ሳለሁ ስለ እኔ ሞቷልና! በሥራዬ ሳይሆን በጸጋህ ታምኜ ደስ የምትሰኝበትን የልጅህን ሥጋ መሥዋዕት አድርጌ በፊትህ አቀርባለሁ መልካም መአዛ ያለው መሥዋዕት አድርገህ በእርሱ በኩል እንደምትቀበለኝም አምናለሁ።

ምንም እንኳን የማቀርብልህ ነገር ባይኖረኝም ያንተ የሆነውን ላንተ በሁሉም ነገር ለሁሉም ነገር እና ስለ ሁሉም ነገር አቀርብልሃለሁ እርሱም ስለ እኔ ኃጢአት ሥርየት ያቀርብክልኝ የአንድ ልጅህ የመሢሕህ ደም ነው ፤ የመሢሕህ ደም ስለእኔ ኃጢአት እንደ ቀረበ አምናለሁ አሁንም በፊትህ እንደሚቀርብ አምናለሁ ጠበቃዬ ሆኖ ስለእኔ ይጮሃልና ሁሉን የምትይዝ አምላክ ሆይ በእርሱ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ በቅዱሳንህ ማኅበርም እኔን ኃጢአተኛውን ተቀበለኝ ፤ ስለ ታረደው ልጅህ ብለህ ሁሉን ቻይ አብ ሆይ ማረኝ ፤ እስከ ሞት በጨከንክበት ልጅህም ማረኝ!
❤ 91 🔥 5 🙏 5 😭 4
ኪ
12:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
"አባ አባት ሆይ! አንድ ልጅህ መከራ የተቀበለው በከንቱ ነውን? ያ ሁሉ ሕማም ስለ እኔ ኃጢአት ካልሆነ ስለማን ነው? ስለ ቀባኸው መሢሕህ ብለህ ተቀበለኝ፤ ማረኝም።" ብለን የምንጮህበትን የልጅነት መንፈስ የሰጠን የጌታን የአምላካችን እና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት እና አምላክ ይባረክ!
❤ 135 🔥 4
23 December 2025
ኪ
13:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMDNxjFuw/

እስቲ ኤቲስቶች ላይ እንውረድባቸው ደሞ 😃
❤ 38 🔥 11 👍 2 🥰 1
25 December 2025
ኪ
08:44
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዛሬዋ ዕለት የሶርያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እና የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓል ያከብራሉ።

መልካም በዓል በክርስቶስ ለሆኑ ወንድሞቻችን በጌታ ልደት ዓለም ሁሉ ሐሴት አደረገ በእግዚአብሔር እቅፍ ያለ አንድያ ልጅ ጸጋን እና እውነትን ተመልቶ በመካከላችን አድሯልና ፤ እኛም ለአባቱ አንድያ የሆነ ክብሩን ተመለከትን!

December 25 ከፓጋኖች ነው የተወሰደው ለሚለው ሐሰተኛ ክስ ይህን ተመልከቱ፡ https://t.me/KidanZeIyesus/250
❤ 105 👍 7
ኪ
13:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMDFD2t3P/

እንዳይረሳ ለማለት ነው።
❤ 37 🥰 4
ኪ
20:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=36u1FDsACTM&list=PLRX-5yebZgxDZik80ArN8DnUU7_Qep5Qi

ዛሬ ለሶርያ ገና በመሆኑ እስቲ ይህንን የሶርያ ገና መዝሙር ስሙት ።

By the way ሱርስት (Syriac) ቋንቋ ክርስቶስ ይናገር ከነበረው አራማይክ ጋር የአንድ ቋንቋ ሌላ dialect ነው።
❤ 27
ኪ
22:36
ኪዳን ዘኢየሱስ
እሺ ሰዎች እንዴት ነበር መጀመሪያ ጥሩ እየሔድን እያለ ዘጋና አቋረጥብን እንጂ ጥሩ ነበር።

እናንተም እስቲ ሚነሱ objections ላኩና ቀጣይ እንወያይባቸዋለን
❤ 32 🔥 3
26 December 2025
ኪ
08:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMDFVoyxb/

ዛሬ ደሞ በጠዋት መጥተናል 🙌
❤ 27
ኪ
12:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
የኤቲስቶች ቪዲዮዎች ፣ ጽሑፎችም ያገኛችሁትን ላኩልኝ እነርሱ ላይም refutation የመሥራት ሀሳብ አለኝ ሰዎች
🔥 34 ❤ 8 😁 2 👍 1
ኪ
15:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
አምላክ ሊኖር የሚችል ከሆነ አምላክ አለ

እስቲ የAlvin Plantiga'ን Modal Ontological argument ላሳያችሁ ፡ አምላክን Maximally greater being (MGB) አድርገን define እናደርገዋለን የትኛውም maximally making property ያለው እንደማለት ነው። ለምሳኤ ሁሉን ቻይ ፣ ሁሉን አዋቂ ፣ ሁሉን ወዳጅ ፣ ፍጹም መልካም ፣ necessary existence ያለው ፣ ፍጹም አምልኮ የሚገባው ፣ ፍጹም ክብር የሚገባው ፣ ፍጹም ቅዱስ ፣ በሁሉ የሚገኝ መፈሳዊ (incorporeal) አካል ነው።

አምላክን በዚህ መልኩ define ካደረግነው አምላክ መኖሩን ለምሳየት የሚጠመቅብን MGB concept coherent እንደሆነና ምንም አይነት የአመክንዮ ግጭት እንደሌለበት ማሳየት ነው። Alvin Plantiga በአምላክ መኖር ማመን ምክንያታዊ ነው የሚለውን ለማሳየት በዚህ መልኩ ሙግትን ያዋቅራል፡

Premise 1: It is possible that a Maximally Great Being exists. (በሁሉም ባሕርያቱ ፍጹም የሆነ አካል ህልው መሆን ይችላል ማለትም አምላክ ብለን define ያደረግነው አካል ህልውና ቢኖረው ምንም አይነት የአመክንዮ ግጭት አያስከትልም the idea is coherent ማለት ነው።)

Premise 2: If it is possible that a Maximally Great Being exists, then there is at least one possible world where this being exists. (ይሄ ቀጥታ ከ P1 የሚወጣ ነው MGB ህልው መሆን የሚችል ከሆነ ቢያንስ በእኛ ዓለም ውስጥ እንኳን ባይሆን በአንድ ሊኖር በሚችል ዓለም ውስጥ ህልውና ይኖረዋል። )

Premise 3፡ But, by definition, a Maximally Great Being must exist and be great in every possible world.Therefore, if this being exists in one possible world (Premise 2), He must exist in every possible world. (ከላይ MGB define ስናደርግ necessary existence ያለው ብለን define አድርገናል necessary existence ያለው አካል ደሞ በአንድ ሊኖር በሚችል ዓለም ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሊኖሩ በሚችሉ ዓለማት ሁሉ መኖር አለበት ስለዚህ ቢያንስ በአንድ ዓለም ውስጥ ሊኖር ይችላል ካልን በሁሉም ሊኖሩ በሚችሉ ዓለማት ሁሉ መኖር አለበት)

Conclusion: The "Actual World" (our reality) is one of the possible worlds. Therefore, a Maximally Great Being exists in the actual world. (እኛ የምንኖርበት ዓለም ደግሞ ሊኖሩ ከሚችሉ ዓለማት ውስጥ አንዱ ነው ስለዚህ MGB በሁሉም ሊኖሩ በሚችሉ ዓለማት ሁሉ አለ ካልን የእኛ ዓለምም ሊኖሩት ከሚችሉት መካከል አንዱ በመሆኑ በእኛ ዓለምም MGB አለ ማለት ነው።)

ይሄን በአመክንዮ አወቃቀር ካያችሁት valid ነው አንድ ሰው premiseኦቹን ሁሉ ከተቀበለ conclusionኡንንም መቀበል ግድ ይለዋል። ዋናዋ premise ደግሞ የመጀመሪያዋ ናት "It is possible that a Maximally Great Being exists." የሚለውን ከተቀበልን ሌሎቹ naturally flow የሚያደርጉ ናቸው። ስለዚህ "አምላክ" የሚባለውን አካል define ባደረግነው መንገድ መሠረት ሊኖር የሚችል ከሆነ (ማለትም ያለ ምንም አመክንዮአዊ ግጭት coherent idea ከሆነ) አምላክ የግድ መኖር አለበት። አንድ ኤቲስት አምላክ ሊኖር ይችላል ነገር ግን ለመኖሩ ማስረጃ ፈልጋለሁ ማለት አይችልም ማለት ነው አምላክ ሊኖሩ ከሚችሉ አካላት መካከል አንዱ አይደለምና ይልቅስ necessarily ህልው ነው ስለዚህ አንድ ኤቲስት የአምላክን አለመኖር ማሳየት ከፈለገ አምላክ ሊኖር የማይችል አካል ወይም the idea of MGB incoherent መሆኑን ማሳየት ይጠበቅበታል።

የአምላክን መኖር ለሚያምን ሰው ግን የአምላክን መኖር ለማሳየት አምላክ ሊኖር የሚችል አካል ወይም the idea of MGB is coherent መሆኑን ማሳየት ብቻ ነው የሚጠበቅበት ማለት ነው። ስለዚህም ነው Alvin Plantiga "Belief in God is rational (በአምላክ ማመን ምክንያታዊ ነው)" በማለት የሚደመድመው።
❤ 53 🔥 5 👍 2
28 December 2025
ኪ
12:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 25
29 December 2025
ኪ
15:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
🔥 71 ❤ 8 ❤‍🔥 2 👌 2 👍 1 💯 1
30 December 2025
ኪ
17:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከገና በፊት ወደ አሉት 7 ቀናት እየገባን ነው በቤተክርስቲያናችን ከገና በፊት ያለው የመጨረሻው ሳምንት "ኖላዊ" እየተባለ ይጠራል።

ኖላዊ ማለት እረኛ ማለት ሲሆን የፍጥረት ሁሉ ኤጲስ ቆጶስ የሚሆን የእረኞች እረኛ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ነው እርሱ "መልካም እረኛ እኔ ነኝ ብሏልና"። አባቶች የጌታን ምጽአት (advent) በምንጠብቅበት በመጨረሻው ሳምንት ላይ የጌታን እረኝነት ሚያስታውሱን እንዲሁ አይደለም ይልቅስ በኖላዊ ሰንበት ከሚሰበከው ምስባክ ትንቢቱን ወስደው ነው መዝሙረኛው አሳፍ እንዲህ ሲል ሰማያዊውን ኖላዊ ይጠራልና፡

"ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ። ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ ። ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ - የእስራኤል እረኛ ሆይ አድምጥ ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ" መዝሙር 79፡1

ምስባኩ ላይ የሚዜመው ይህ ቢሆንም መዝሙሩ እንዲህ እያለ በሰማየ ሰማያት የተቀመጠውን ኖላዊ ይጠራል "በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም፤ ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና። አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን .. የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ እንግዲህ ተመለስ፤ ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥ ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ።
በሰው ልጅ ለአንተ ያጸናኸውን ቀኝህ የተከላትን አንሣ... ከአንተም አንራቅ፤ አድነን ስምህንም እንጠራለን። የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።"

ይህን መዝሙር ቅዱስ አውግስጢኖስ ሲተረጉመው እንዲህ ይላል ፡ " The song here is of the Advent of the Lord and of our Saviour Jesus Christ, and of His vineyard... this testimony doth confess both Christ and the vineyard; that is, Head and Body, King and people, Shepherd and flock, and the entire mystery of all Scriptures, Christ and the Church.

ይህ መዝሙር ስለ ጌታን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምጽአት እና ስለ ወይን ግንዱ ነው። ይህ ምስክርነት ስለ ክርስቶስም ስለ ወይን ግንዱም ይመስክራል ይህም ራስ እና አካል ፣ ንጉሥ እና ሕዝብ ፣ እረኛ እና መንጋ ፣ እና መላውን የመጻሕፍት ምሥጢር የሚያሳይ ነው እርሱም ክርስቶስ እና ቤተክርስቲያኒቱ ናት" St Augustine : Exposition on Psalm 80.

አቤቱ ጌታ ሆይ የወይን ግንድህ ቤተክርስቲያን ና ትልሃለች! እረኛዬ ሆይ ከሰማይ ና መጋቢዬ ሆይ ከዙፋንህ ውረድ ወደ ምድርም ተመልከት ማረፊያ እንዳላቀርብልህ የለኝም ነገር ግን ላንት ሰማያዊ ጌታዬ የሚሆን በረት እንኳን አላጣም ጌታዬ ሆይ ና ፤ መቀበያ ስጦታ ባይኖረኝም ከሩቅ ምስራቅ ጠቢባን ሰዎች ወርቅ ፣ እጣን ፣ ከርቤ እዋሳለሁና የኔ ኖላዊ አትናቀኝ ና!

"ኖላዊ ዘመጽአ ውስተ ዓለም ወልዱ ወቃሉ ለእግዚአብሔር - ወደ ዓለም የመጣ እረኛ የእግዚአብሔር ልጁ እና ቃሉ" ቅዱስ ያሬድ
❤ 77 🔥 8
ኪ
18:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 18 🔥 1
1 January 2026
ኪ
10:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅዱስ ኒቆላዎስ (በብዙ ቋንቋዎች ውስጥ አልፎ ስሙ Santa Claus የሆነውና ድሆችን መርዳት ይወድ ስለነበር ብዙ modern legend በስሙ የተጨመሩበት) በኒቅያ ጉባኤ ላይ እንደተሳተፈ ይገመታል (ይገመታል ያልኩት የኒቅያ ጉባኤ ተሳታፊዎች በተለያየ list ውስጥ ይለያያሉ ከ200-318 ጳጳሳት እንደተሳተፉ ይጠቀሳል ረጅሙ list ላይ ኒቆላዎስ ቢኖርም አጭሩ ላይ የለም።)

ነገር ግን በስሙ legend የተፈጠረው በsecularኡ ዓለም ብቻ አንደለም በክርስትናም ተፈጥሯል። አንድ አርዮሳዊ ሲከራከረው በጥፊ እንደመታው ይነገራል በኋላም ታሪኩ ኒቅያ ጉባኤ ላይ ራሱን አርዮስን እንደመታው ተደርጎ evolve ሆነ። ነገር ግን ይሄ ታሪክ ቅደስ ኒቆላዎስ ካለፈ ከ800 ዓመታት በኋላ የመጣ ነው so it most probably didn't happen.

ግን still አርዮስን በጥፊ የመታውን የገና አባት ማሰብ መልካም ነው 😄

መቼስ Homoiousious እና Homoousious መሃል ያለውን ልዩነት ባለፈው ስላየነው አትረሱትም።
😁 47 ❤ 17 🤣 7 👍 2
4 January 2026
ኪ
12:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 24 ❤‍🔥 2 👍 1
5 January 2026
ኪ
11:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቴዎፋንያ (አስተርእዮቱ ለእግዚእነ)

ነገ ማለትም January 6 በአርመን ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የጌታ ልደት እና ጥምቀት አንድ ላይ ይከበራል በዓሉም ስሙ Աստվածահայտնություն (Asdvadz-a-haytnutyun) ሲባል ትርጉሙም Θεοφάνεια (ቴዎፋንያ) - አስተርእዮ የእግዚአብሔር መገለጥ ማለት ነው። ክርስቶስ በይፋ ሥራውን በመጀመር ለሕዝቡ የተገለጠበት አብ ከሰማይ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" ብሎ ልጅነቱን የመሠከረለት በዓል በመሆኑ አምላክ ወደ እኛ መምጣቱን መውረዱን ፣ ድኅነትን ስለእኛ መጀመሩን ለአብ በፍጹም ታዛዥነት መኖሩ እየታሰበ "ዘነገሩነ አበዊነ እሙነ ኮነ _ አባቶታችን የነገሩን እውነት ሆነ" የማይታየውን አምላክ በሥጋ አየነው አምላክ ተገለጠልን ከሰማይ መጣ ከላይ የሆነ ሰማያዊ መገለጥ (ኤጲፋንያ) አየን በማለት የሚከበር በዓል ነው።

ታድያ January 6 ጥምቀቱ ከሆነ (Julian calendar ላይም ጥምቀት January 6 ነው ከግሪጎሪያኑ 13 ቀን ወደ ኋላ ስለሚቀር የእኛ በግሪጎርያን January 19 ላይ ይውላል።) ለምን የአርመን ቤተክርስቲያን ልደቱንም በጥምቀቱ ቀን ታከብራለች? ምክንያቱ የጥንቱን ሥርዓት ትከተል ስለነበር ነው በዓለ ኤጲፋንያ የጌታን መገለጥ የምናከብርበት ስለሆነ መወለዱን ለእኛ መገለጡ ነውና የጥንት ክርስቲያኖች ልድቱን ከጥምቀቱ ጋር አንድ ላይ ያከብሩታል በኋላ ግን በሮማ ሥርወ መንግሥት ስር የነበሩ ክርስቲያኖች ዘንድ December 25 የጌታ ልደት ቀን በመሆን popular እየሆነ ሲመጣ ጥምቀቱን እና ልደቱን ለያይተው ማክበር ጀመሩ ኢትዮጵያም የሮማ ሥርወ መንግሥት ስር ከነበረችዋ ግብጽ እምነትን ስለተቀበለች የጌታን ልደት December 25 , ጥምቀቱን January 6 ታከብረዋለች። የአርመን ቤተክርስቲያን ግን ከሮማ ሥርወ መንግሥት ውጪ ስለነበረች በሮም ውስጥ ልደት December 25 ላይ standardize ሲደረግ በአርመን ላይ ተፈጻሚ አልሆነም ስለዚህም የጥንቱን January 6 የጌታ ልደት ፣ ቴዎፋንያ እያለች ማክበር ቀጠለች።

እንግዲህ በጌታ ወንድሞቻን ለሆኑ አርመናውያን መልካም በዓለ ልደት ወ በዓለ ኤጲፋንያ እንላለን።
❤ 72 🔥 6
ኪ
15:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
Brother from another mother 👊
🔥 49 ❤ 21 ❤‍🔥 2 😱 2 🤗 2 👍 1
6 January 2026
ኪ
22:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
Video file
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
03:32, 42.2 MB
ርእይዎ ኖሎት'/፪/ አእኰትዎ መላእክት/፪/
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል/፪/
❤ 74
7 January 2026
ኪ
03:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክብር በቤተልሔም ለተወለደው ሕፃን፣ ክብር ለኢየሱስ ይሁን።
❤ 160
ኪ
11:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
እናንተ አሁን እኮ ነው መዝሙር እየዘመርኩ "በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ" ሲባል የመጣልኝ ሰብአ ሰገል እኮ ክርስቶስን ያገኙት በረት ውስጥ አይደለም የማቴዎስ ወንጌል እንደሚነግረን በቤት ውስጥ ነው። እንዲሁም የተወለደ ቀን ሳይሆን ከተወለደ ቢያንስ 1 ዓመት በኋላ ነው።

እና "በቤት በቤት ሰበአ ሰገል በቤት ሰብአ ሰግል በቤት ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ" ብዬ እየዘመርኩ ነው 😁

በበዓል ቀን እንዲህ ከማሰብ ይሰውራችሁ ለማንኛውም መልካም በዓል 😄
😁 97 ❤ 14 👎 3
8 January 2026
ኪ
18:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለአይሁድ በሰንበት እሳት ማቀጣጠል የትኛውንም electronics መጠቀም አይቻልም የሊፍት button መንካት ደሞ electronics እንደመጠቀም ስለሚቆጠር በሰንበት አይቻልም። ስለዚህ የሰንበት ሊፍት አለ በየ ፍቁ ይቆማል ምትፈልጉት ላይ ትወርዳላችሁ ምንም button ሳትነኩ።

ሃዬ እንግዲህ ምን እንላለን በሰንበት ልብስ ማጠብ ፣ ቡና መውቀጥ ፣ ውኃ መቅዳት አይቻልም የሚሉ ሰዎችን ሳይ የሚመጣልን ይሄ የሰንበት ሊፍት ነው 😄
😁 66 🤣 17 ❤ 6
9 January 2026
ኪ
18:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሄንን ፊልም ዛሬ ገና ማየቴ

አዎ ታሪኩን ትንሽ ለውጠውታል ግን we can day it is one of the best adaptation of a biblical story.

ደግሞ intro songኡስ "Deliver us" masterpiece 👌
🔥 40 ❤ 11
10 January 2026
ኪ
10:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
My Christian Apologists tier list 😆
😁 24 🤔 2 🔥 1
ኪ
21:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
በአንዳንድ ሰዎች ጥያቄ መሠረት የተረሱ ሰዎችን አካተን አሻሽለናል

ሕጻኑን ኤገን ግን B እንዳላደርገው ጎበዝ ነው A እንዳላደርገው ትላልቅ እና ግዙፋን ሰዎች ናቸው እነርሱ ላይ ለመድረስ legacy ገና መገንባት አለበት በመጨረሻም ታግዬ A አረኩት እንግዲህ 😁
❤ 32 🥰 3 🔥 2 🤔 1
12 January 2026
ኪ
13:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዚህ ዓመት የጥምቀት በይረሙን (Paramoun) ወይም ጾመ ገሃድ ሦስት ቀን መሆኑን ላስታውሳችሁ።

ጥምቀት ሰኞ ስለሚውል አርብ ጸሐይ እስክትጠልቅ ይጾማል ፤ ቅዳሜ እና እሑድ ግን ምግብ ቢበላም ከእንስሳት ተዋጽኦዎች ይጾማል።

በይረሙን የሚጾመው የጥምቀት ዋዜማ ዕለት ቢሆንም የዘንድሮ ጥምቀት ሰኞ ነው የሚውለው ፣ በይረሙን ደግሞ strict አጽዋማት ከሚባሉት አንዱ ሆኖ ከአብይ ጾም ጋር ይደመራል የሚጾመውም ጸሐይ እስጠልቅ ነው (በኮፕቲክ ደግሞ ከዚህ በተጨማሪ በሌሎቹ አጽዋማውት የሚፈቀደው አሳም አይፈቀድም) ይህን ማድረግ ደግሞ በቅዳሜ እና እሑድ አይቻልም ስለዚህ ጾሙ 3 ቀን ይሆናል አርብ ጸሐይ እስክጠልቅ ይጾማል ቅዳሜ እና እሑድ ደግሞ ከጥሉላት ብቻ ይጾማል።
🙏 48 ❤ 24 👏 1 💯 1
13 January 2026
ኪ
11:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
ለሙታን የሚደረግ ጸሎት እንዴት ይጠቅማል?

A catechism of the Coptic Orthodox Church : Fourth division : the consummation of Man
"Q. Do believing souls profit by prayers and charity?

A. Yes; the prayers of the Church, the offering of the Holy Oblation, and alms-giving profit those souls departed who are stained by certain human shortcomings and transgressions; [but] not the souls plunged in sins and cruelty, and without repentance or forgiveness.

This doctrine was held by the Catholic Church of Christ from the earliest centuries, and the Church of Israel testifies in the Second Book of Maccabees that Judas Maccabeus used to offer sacrifices for the departed soldiers (xii. 43-45).

ጥያቄ፡ በእምነት የሞቱ ነፍሳት በጸሎት እና በምጽዋት ይጠቀማሉን?
መልስ፡ አዎን ፣ የቤተክርስቲያን ጸሎት ፣ የቅዱስ ቁርባን መሥዋዕት እና ምጽዋት ለሞቱ ነፍሳት ይጠቅማሉ። ይኸውም የሚጠቅመው በአንድ አንድ የሰውነት ድካሞች እና መተላለፎች የወደቁትን ነው እንጂ ያለ ንስሐ እና ይቅርታ በኃጢአት እና ጭካኔ ውስጥ የተዘፈቁትን ነፍሳት አይደለም።

ይህ ትምህርት በኩላዊቷ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከጥንት ክፍለ ዘመናት ጀምሮ የታመነ ነው ፤ እንዲሁም የእስራኤል ቤተክርስቲያንም በ2ተኛው መቃብያን መጽሐፍ ይሁዳ መቃብዮስ ለሞቱ መታደሮች መሥዋዕት ይፈጽም እንደ ነበር ትመሰክራለች (2ተኛ መቃ 12፡ 43-45)"

ይህ የቅብጥ ቤተክርስቲያን ካቴኪዝም ለሙታን የሚደረግ ጸሎት እንዴት እንደሚጠቅም ፍንትው አድርጎ ያሳየናል ፤ ሰው በሞቱ ጊዜ ያለበትን ሁኔታ በሁለት ይከፍለዋል፡

ሰው 1. ያለ ንስሐ በሚገድል ኃጢአት ተዘፍቆ የሞተ ሰው (A person who died in state of unrepented Mortal Sin.)
ሰው 2. በሰዋዊ ድካሞች እና መተላለፎች የሞተ ሰው (A person who died in state of venial sin)

ለሙታን የሚደረገው ጸሎት፣ መሥዋዕት ሆነ ምጽዋት ሰው 1ን ሊጠቅመው አይችልም ይህ ሰው እጣ ፈንታው ሲኦል ይሆናልና። ሰው 2 ግን በእነዚህ ጸሎቶች ይጠቀማል አንድ ሰው ጥቂት ድካሞች እና መተላለፎች እያሉት ገነት ሊገባ አይችልም ስለዚህ ከመግባቱ በፊት መንጻት አለበት በመንጻቱ ላይ ደግሞ በምድር ያሉ ክርስቲያኖች ጸሎት ይጠቅመዋል። ይህ ማለት ግን ቤተክርስቲያን ለሞቱ ሰዎች እየመረጠች ትጸልያለች ማለት አይደለም ማን በምን ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንደሞተ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነውና።

ይህንን በመጽሐፍ ቅዱስ ለማሳየት 2 premise ማረጋገጥ ነው ሚጠበቅብን፡
Premise 1: ማንም በምድር ሳለ እስከ ዕለተ ሞቱ ከኃጢአት ፍጹም ንጹሕ ሊሆን አይችልም።
Premise 2: ከኃጢአት ፍጹም ንጹሕ ያልሆነ ሰው ወደ ገነት ሊገባ አይችልም።
Conclusion: ስለዚህ አንድ ሰው ገነት ከመግባቱ በፊት እና ከሞተ በኋላ ማለፍ ያለበት የመንጻት ሒደት አለ።

Premise 1 እውነት መሆኑ ብዙዎችን አያጠያይቅም መጽሐፍም እንደሚል "ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። " (1ኛ ዮሐ 1፡8) እንዲሁም የቅርጣግና ጉባኤ ይህንን ሲተረጉም እንዲህ ይላል " ኃጢአት አለብኝ የምንለው ለትሕትና እንጂ በእርግጥም ኃጢአት የለብኝም የሚል ሰው የተወገዘ ይሁን" ስለዚህ የሰው ሕይወት የ1 ቀን እንኳን ቢሆን ኃጢአተኛ ነው። በኃጢአት ውስጥ ተዘፍቆ እንኳን ባይኖር ድካሞች እና መተላለፎች አያጡትም በሕይወት እስካለ ድረስ።

Premise 2ን ደግሞ ራዕይ 21፡27 ያሳያል "ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።" በዚህ ጥቅስ እንደምናየው ማንኛውም ርኩሰት ያለበት ሰው ወደ መንግሥቱ አይገባም ፤ premise 1 ላይ እንዳየነው ደግሞ አንድ ሰው በዚህ ሕይወት ከርኩሰት ፍጹም ንጹሕ ሊሆን አይችልም ስለዚህ ከሞት በኋላ እና መንግሥቱ ከመግባት በፊት ከርኩሰት መንጻት ያስፈልጋል ፤ ለሙታን የሚደረግ ጸሎትም የሚጠቅመው እዚህ ጋር ነው።

ይህ ማለት ግን ሰው 1 አይነት ሰው በጸሎት ይነጻል ማለት አይደለም ሰው 1 በሚገድል ኃጢአት ያለ ንስሐ ስለሞተ ፍጻሜው ከእግዚአብሔር መለየት ነው። ሰው 1 ግን ወደ ገነት እና ወደ እግዚአብሔር እንዲገባ የተፈረደለት ነው ነገር ግን መጀመሪያ ከመተላለፎቹ መንጻት አለበት። ስለዚህ እኛ በፍጹም ያለ ንስሐ በኃጢአት ተዘፍቆ የሞተን ሰው በጸሎታችን ከሲኦል እናወጣዋለን ብለን አናምንም።

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 49 👍 2
ኪ
14:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vm.tiktok.com/ZMDh75GPR/

በዓለ ኢየሱስ
❤ 20
14 January 2026
ኪ
11:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ ቤተክርስቲያን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ግዝረት ታስባለች።

ለአብርሃም በ8ተኛው ቀን የመገረዝን ሕግ የሰጠ እርሱ ራሱ ከአብርሃም ዘርን ይዞ ተገረዘና ከእኛ ላይ የመገረዝን ቀንበር አነሣ ስለዚህም እኛ ሕኝ በፈጸመው ጌታችን ሆነን ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ መገረዝን እንገረዛለን እርሱም ከክርስቶስ ጋር አንድ የምንሆንበት ጥምቀት ነው።

እንዲሁም ጌታችን መልአኩ እንደተናገረው "ኢየሱስ" ተብሎ የተጠራው በመገረዙ ነው እኛም የማዳን ስሙን እያሰብን "ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ-ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው የሚጣፍጥ ስም ነው" እያልን እናመሰግናለን የያሕዌን ማዳን በደሙ አሳይቶናልና!

ምላስ ያለው ሁሉ ይህን ስም ይጥራ ፣ ጉልበት ያለው ሁሉም ለዚህ ስም ይንበርከብ እግዚአብሔር ማዳኑን ገልጧልና! ኢየሱስም ታውቋልና!
❤ 133 👍 3
16 January 2026
ኪ
15:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ፈጣሪን ማን ፈጠረው" የሚል objection ሰምታችሁ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ይህ objection ለእኛ ሙግቶች የተነሣ ሳይሆን ለstrawman ሙግት የተተሣ ነው።

ከላይ እንደምታዩት "ሁሉም ነገር ፈጣሪ አለው" ብሎ ይጀምራል ፤ ይህ premise ግን strawman ነው እንጂ እኛ ይህንን premise አናቀርብም ምክንያቱም ሁሉም ነገር ፈጣሪ አለው ካልን በኋላ አምላክ ግን ፈጣሪ የለውም የምንል ከሆነ special pleading ይሆናል ማለትም አንድ general rule ካስቀመጥን በኋላ (i.e. ሁሉም ነገር ፈጣሪ አለው) ይህ general rule የማይሠራበት አካል ያለ በቂ ምክንያት እያመጣን ነውና (i.e. አምላክ)።

ከፍጥረት በመነሳት ወደ አምላክ ከሚውስዱን ሙግቶች ለምሳሌ ሦስቱን እንመልከት:

Leibnizian Cosmological argument : Everything that exists has explanation of its existence in itself or something external to itself , the universe is not self explanatory (i.e. its contingent) therefore it needs explanation of its existence outside of it self.

Kalam's Cosmological argument: Everything that began to exist has a cause.

Argument from motion: Everthing that moves , has a mover.

እነዚህ ሦስቱም ላይ ሁሉም ነገር ፈጣሪ አለው የሚል premise አይገኝም ይልቅስ contingent የሆነ , የሚንቀሳቀስ እና መኖር የጀመረ ነገር ነው ፈጣሪ አለው የሚሉት ስለዚህ አምላክን ማን ፈጠረው የሚለው objection strawman እንጂ ምንም weight የለውም።
❤ 41 🔥 7
18 January 2026
ኪ
10:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://t.me/Philosophyofworld1/3478

ይህ ከላይ የምታዩት ለእኛ መልስ ለመስጠት የተጻፈ ይመስላል እስቲ የሠራቸውን ስህተቶች እናሳየው።

1. Quantum particles ከ quantum fields ያለ ምንም efficient cause ይመጣሉ በማለት እንደተረጋገጠ ሳይንስ claim አድርጓል ነገር ግን ይህ ስህተት ነው እስካሁን ምን ከምን መንስኤ እንደሚመጡ አልታወቀም ማለት ምንም አይነት መንስኤ የላቸውም ማለት አይደለም ይህ arguing from ignorance fallacyን commit ያደርጋል ማለትም ከማናውቀው ነገር መነሳት የለም በማለት ወደ መደምደም መሔድ ማለት ነው። በሳይንስ ታሪክ ደግሞ ከዚህ በፊት ብዙ ማናውቃቸውን ነገሮች እያወቅን ሔደናል ስለዚህ አሁን ላይ quantum particlesን cause የሚያደርጋቸው ነገር አላወቅንም ማለት cause ሚያደርጋቸው ነገር የለም ማለት አይደለም። ብዙህ ጊዜ እነርሱ "God of the Gaps fallacy" ሠራችሁ ብለው የሚከሱን የfallacy አይነት ነው የሠራው ማለትም "Just because we don't know God did it" የሚለው ስህተት እንደሆነው ሁሉ "just because we don't know what caused it therefore there is no cause" ማለትም ስህተት ነው።

2. እዚህኛው ጋር ደግሞ እስቲ የመጀመሪያውን ነጥብ አሳልፈን እንስጠውና quantum particles ያለምንም efficient cause ከ quantum field ይመጣሉ ብለን እንቀበል ነገር ግን ይህ ማለት ምንም መንስኤ አይኖራቸውም ማለት አይደለም ምክንያቱም quantum field ራሱ material cause ነውና። ይህንን ነጥብ ሞጋቻችን ራሱ አምኗል ነገር ግን ስህተት የሠራው የሙግታቸውን premise ያስቀይራቸዋል የሚለው ላይ ነው። ምክንያቱም ሙግታችን ገና ከመጀመሪያው "Everything has an efficient cause" አልነበረም ይልቅስ "Everything that begins to exist has a cause " ነው እዚህ premise ላይ በመጀመሪያ መንስኤ የሚያስፈልገው "መኖር የጀመረ ነገር" የሚል qualifier አለው ፤ ሞጋቻችን ግን በተደጋጋሚ "ሁሉም ነገር አስጀማሪ አለው" የሚል እኛ ያላልነውን ሙግት እየተጠቀመ ነበር። ሁለተኛ ደግሞ ሙግቱ ላይ "everything that begins to exist has a cause" ተባለ እንጂ "has an efficient cause" አልተባለም ስለዚህ ሙግታችንን አይለውጠውም።

እሱ ግን ይህን ባለመረዳት " Everything that begins to exist has a material cause" ወደ ሚለው ያስለውጣችኋል አለ። ይህ ስህተት ነው መጀመሪያውኑ ይህ cause material ይሁን efficient specify ባላደረግንበት ሁኔታ የእኛን ሙግት አያስለውጥም። እሱ ግን ያስለውጣችኋል ያለው የእኛን ሙግት strawman በመሥራት ለማፍረስ እንዲመቸው ነው ምክንያቱም "everything that begins to exist has a material cause" ከሆነ ሙግቱ "The first cause" የምንለው አምላክም material ሊሆን ነው ይህንን ደግሞ የትኛውም አማኝ claim አያደርግም ስለዚህ "እኛ ያላቀረብነውን ሙግት" አፈረሰ ማለት ነው። (Strawman)

እዚህ ጋር ሞጋቻችን እየሳተ ያለው አሁንም quantum field ለ quantum fluctuation material cause መሆኑን ካመነ በኋላ የአጽናፈ ዓለምን የት መጣነት ጥያቄ እዚህ ጋር ማብቃቱ ነው ነገር ግን ጥያቄውን ወደ ኋላ መለሰው እንጂ ጥያቄው አሁንም አላበቃም ምክንያቱም ይህ quantum field ራሱ ከየት መጣ? እንዲሁ ነበረ እንዳንል ሳይንስ አይፈቅድልንም ምክንያቱም quantum field, energy density ነው ማንኛውም ፊዚክስ የተማረ ሰው እንደሚያውቀው ደግሞ density ይኖር ዘንድ volume ያስፈልጋል ማለትም ቦታ (space) ያስፈልገዋል ማለት ነው። ሁለተኛ ደግሞ ይህ field የሚኖረው በ uncertainity ወይም fluctuation ነው። አንድ ነገር fluctuate እንዲያደርግ ደግሞ ጊዜ (time) ያስፈልጋል (Heisenberg Uncertainty Principle ውስጥ time አለ)። ስለዚህ ይህ quantum field የሚኖረው በጊዜ እና በቦታ ውስጥ ነው ማለት ነው ፤ ጊዜ እና ቦታ ደግሞ በ big bang መኖር የጀመረ ነው ስለዚህ the initial singularity , quantum field ቢሆን ራሱ በ big bang ጊዜ መኖር የጀመረ ነው ማለት ነው።

መኖር የጀመረ ነገር ሁሉ አስጀማሪ አለው ካልን ደግሞ ይህ አስጀማሪ cause material ነው ወይስ efficient የሚለውን መጠየቅ አለብን። Material cause ከሆነ matter በቦታ የተወሰነ ስለሆነ ከቦታ ጋር አብሮ የሚጀምር ነው ስለዚህ ከ big bangኡ ጋር አብሮ ይጀምራል እንጂ የ big bang አስጀማሪ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ይህ የመጀመሪያ አስጀማሪ (First cause) , efficient cause መሆን አለበት ማለት ነው እርሱም ከጊዜ እና ከቦታ ውጪ ነው።
🔥 42 ❤ 15 👍 3 👏 2 🤣 1
19 January 2026
ኪ
16:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
John 1 አማ - ዮሐንስ
33: እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ፦ ‘መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው፡’ አለኝ።
34: እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ።”

ከዛሬው ወንጌል የወደድኩት ዮሐንስ መሥክሯል እኔም እንዲሁ እመሰክራለሁ በእወነት በዮርዳኖስ የተጠመቀው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው!

እንኳን አደረሳችሁ
❤ 104
ኪ
19:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=YXIL7MsNNwc

ይህንን እዩትና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የቲክቶክ ዲቤቶችም እንዴት እንደተበላሹ ትረዳላችሁ አሁን ላይ የቲክቶክ ዲቤት አያስፈልግም የሚል አቋም ነው ያለኝ ለዛም ነው ማላደርገው ፤ ሶፊስቶች የሞሉበት ቦታ ነው የሆነው።
👍 21 ❤ 12 🤝 1
20 January 2026
ኪ
20:58
ኪዳን ዘኢየሱስ
መላእክት ስንት ጊዜ ወደቁ እናም መቼ?
Anonymous poll
- አንድ ጊዜ ሳጥናኤልን ተከተለው ወደቁ 357 votes
- ሁለት ጊዜ የመጀመሪያው ሳጥናኤልን ተከትለው የወደቁ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሰው ልጆች ጋር ሊሰስኑ ወደቁ 169 votes
- ሁለት ጊዜ የመጀመሪያው ሳጥናኤልን ተከትለው ወደቁ ፣ ሁለተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ለዓለምን ሕዝብ ዓለቅነት ለመላእክት ካከፋፈለ በሥልጣን ተበላሽተው ወደቁ 45 votes
- ሦስት ጊዜ ሳጥናኤልን ተከትለው ፣ ከሴቶች ጋር ሊሰስኑ እና በሥልጣን ተበላሽተው 102 votes, chosen vote
673 votes
❤ 15 🔥 2 🥱 2
21 January 2026
ኪ
09:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ብዙዎቻችሁ 1ኛውን መርጣችኋል መላእክት አንድ ጊዜ ሳጥናኤልን ተከትለው መውደቃቸው አያጠራጥርም ስለዚህ እርሱን እንተወውና የቀሩት ሁለቱ ላይ እንነጋገር።

2ኛ ጊዜ የወደቁት እግዚአብሔር ዘዳ 32:8-9 ላይ እንደሚነግረን አሕዛብን በእግዚአብሔር ልጆች (ሰብዓ ሊቃናት እና የሙት ባሕር ጥቅሎች መላእክት ይላሉ ፤ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ስለሚባሉ አንድ መሆኑ አያጠራጥርም) ቁጥር ከፈለ በአሕዛብ ላይም አማልክት አድርጎ ሾማቸው ፤ እስራኤልን ግን ለመልአክ አልሰጠውም ይልቅስ የእስራኤል እድል ፈንታ የራሱ የእግዚአብሔር ነበር። ይህንን ትንቢተ ዳንኤል ላይ ስንሔድም እያገኘዋለን ዳንኤል የሚገኘው ከእስራኤል ውጪ በፋርስ ነበር የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ዳንኤልም በተላከ ጊዜ የፋርስ አለቃ የተባለው መልአክ ተቋቋመው በሚካኤል እርዳታም ነበር አሸንፎ ወደ ዳንኤል የሔደው። ማኅበረ አማልክት የሚባለው ይህ ሀሳብ ነው ፣ አሕዛብን የሚገዙ ሰማያውያን የእግዚአብሔር ልጅች (መላእክት) ተሹመዋል ነገር ግን የተፈጠሩ ናቸው ያልተፈጠረው የአማልክት አምላክ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ለዚህም ነው ብዙ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ "ከአማልክት እንዳንተ ያለ ማነው" እያለ የሚያመሰግነው። ነገር ግን እነዚህ አማልክት ሥልጣናቸውን በሥነ ሥርዓት አልተጠቁም ለደሃም እና ለተጨቆነም በአግባቡ አልፈረዱም በሥልጣናቸውም ስለተበላሹ እግዚአብሔር ፈረደባቸው አሕዛብንም ወረሰ። ይሄን መዝ 81/82 ይነግረናል "እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆሞ በአማልክት ላይ ፈረደ ... ሁላችሁም አማልክት የልዑል ልጆች ናችሁ ነገር ግን ፍርድን በማጓደላችሁ እንደ ሰው ትሞታላችሁ በማለት ፈረደባቸው መዝሙረኛውም አቤቱ ተነሥ በምድር ላይ ፍረድ አሕዛብን ትወርሳለህና በማለት አመሰገነው"። ስለዚህ ይህ ሁለተኛው የመላእክት ውድቀት ይሆናል።

ሦስተኛው ውድቀት ዘፍ 6 ላይ የተነገረው ውድቀት ነው የእግዚአብሔር ልጆች ከሰው ልጆች ጋር ተገናኙና ኔፊልም የተባሉ ኃያላን ልጆችን ወለዱ የሰው ልጆችን ብዙ ጥበብ እና አስተማቾን አስተማሩ በምድር ላይ የጥፋት ውኃም እንዲመጣ ተስተዋጽኦ አድርገዋል። እዚህ ላይ ብዙዎች የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሴት ዘሮች ናቸው ቢባልም ከመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጓም አንጻር ሚያስኬድ አይመስልም ይሁዳ 6-7 መላእክት ናቸው ይላልና ""6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።
7 እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።" ይሁዳ 6-7

እዚህ ላይ እንደምናየው መላእክት የተፈረደባቸው መኖሪያቸውን በመተው እና እንደ ሰዶም ሰዎች ከሌላ ሥጋ ጋር በመዘሞት እንደሆነ ያሳያል። ይሁዳ መጽሐፈ ሔኖክንም ስለሚጠቅስ የዘፍ 6 የእግዚአብሔር ልጆች መላእክት ናቸው ብሎ እንደሚያምን አያጠራጥርም።
❤ 41
22 January 2026
ኪ
11:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
እንዲህ አይነት ሰፋ ያለ ዳሰሳ ያለው ጽሑፍ ለማዘጋጀት አስቤ ነበር አጫጭር ጽሑፎች ከሚሆኑ ሰፋ በስፋት የሚዳስስ ነገር እንድታገኙ እስቲ ርእስ ምረጡልኝ እኔ እነዚህን አስቤያለሁ እናንተም መጨመር ትችላላችሁ፡

1. Sola scriptura ፡ from protestant confessions to its current form and its refutation
2. Original Sin : Historical analysis and its current form
3. ነገረ ክርስቶስ፡ ከአንጾኪያ ጉባኤ እስከ ሦስተኛው ቁስጥንጥንያ ጉባኤ
4. የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ፡ ከጥንት ዘመን እስከ አሁን በተለያዩ ትውፊቶች
5. የወንጌላት ተአማኒነት፡ መቼ ተጻፉ ፣ በማን ተጻፉ ፣ ታሪካዊ ይዘታቸው etc
❤ 37 🔥 9
11:54
እስቲ በፖል ይሁን
Anonymous poll
- 1. Sola scriptura ፡ from protestant confessions to its current form and its refutation 135 votes
- 2. Original Sin : Historical analysis and its current form 109 votes
- 3. ነገረ ክርስቶስ፡ ከአንጾኪያ ጉባኤ እስከ ሦስተኛው ቁስጥንጥንያ ጉባኤ 119 votes
- 4. የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ፡ ከጥንት ዘመን እስከ አሁን በተለያዩ ትውፊቶች 127 votes, chosen vote
- 5. የወንጌላት ተአማኒነት፡ መቼ ተጻፉ ፣ በማን ተጻፉ ፣ ታሪካዊ ይዘታቸው etc 175 votes
665 votes
❤ 36
26 January 2026
ኪ
10:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጃን ሀስ በ15ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ የካቶሊክ ቄስ ነበር (ከሉተር 100 ዓመት በፊት)። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደግሞ ያን ጊዜ በሲሞናዊነት እና በሙስና እንዲሁም የኃጢአት ስርየት ደብዳቤ (Indulgence) በመሸጥ የተጨማለቀችበት ጊዜ ነበር። እንዲሁም ሦስት ፖፖች በአንድ ጊዜ የነበሩበት "ታላቁ የምዕራባውያን መለያየት" (The Great Western Schism) የተፈጠረበት ወቅት ነበር። ብቻ ሕዝቡ ሁሉ የትኛው ነው ትክክለኛ ፖፕ የሚለውን ካለማወቁ የተነሳ እና ፖፑ በፈረንሳይ አቪኞን ሲያሳልፍ ከነበረው የሙስና እና የተጨማለቀ ጊዜ በኋላ ፓፓሲው ጥርጣሬ ውስጥ ወድቆ ነበር። ይህ ብቻ አልነበረም ካቶሊኮች በሕብስቱም በወይኑም ክርስቶስ ስለሚገኝ ወይኑ እንዳይፈስ በማለት ለሕዝቡ አይሰጡም ነበር ጭራሽም ከዚህ ብሶ በጉባኤ አውግዘዋል ወይኑን ቄሶቹ ብቻ ነበር የሚጠጡት።

ብቻ ታሪኩ ረጅም ነው፤ ሀስ ይህንን ሁሉ ነው የተቃወመው። በሙስና የተበላሹትን (Corrupt) ቄሶች፣ ጳጳሳት፣ ፖፑን (ወይም ፖፖቹን እንበል በዚህ ጊዜ 😁) ወቀሰ። ፖፑ "የክርስቶስ እንደራሴ" (Vicar of Christ) የሚሆነው እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከኖረ ነው እንጂ ካልኖረ ከቤተክርስቲያን ውጪ ይሆናል ቤተክርስቲያን ግን ትቀጥላለች በሱ ላይ አልተመሠረተችምና አለ። ቁርባን በሁለቱም አይነት (በሥጋውም በደሙም) ለሕዝቡ ሁሉ መሰጠት አለበት አለ። "የባሕርይ ለውጥ" (Transubstantiation) ክዷል ተብሎ ይወቀሳል (በጆን ዊክሊፍ [John Wycliffe] ተጽዕኖ ሥር ስለሆነ) ነገር ግን "በእውነት መገኘት" (Real Presence) አጥብቆ ያምናል፣ ቄሶች እቁባቶችን መያዝ የለባቸውም፣ በሲሞናዊነት የተሾመ ምሥጢራትን የሸጠ ሁሉ መናፍቅ ነው ብሎ ከሰሰ፣ ቄሶች ወንጌልን መስበክ አለባቸው ብሎ ብዙ ሕዳሴዎችን ነው ብቻ የሰበከው።

ፖፑ ግን ሥልጣኑ ሲነካ ደስ አይለውምና መናፍቅ ነህ አለው። በመጨረሻም በ"ኮንስታንስ ጉባኤ" (Council of Constance) እንዲገኝ ተጠራ። ንጉሡም "የደህንነት ማለፊያ" (Safe passage) ቃል ገባለት (ማለትም ከቦሄሚያ ወደ ኮንስታንስ ይመጣል በሰላምም ይመለሳል)። አሳዛኙ ክፍል፣ ጃን አመናቸውና በጉባኤው ተገኘ። ነገር ግን "ተገቢ የሆነ የመደመጥ ዕድል" (Proper hearing) እንኳን ሳይሰጡት አሠሩት። የጻፍኩትን፣ ያስተማርኩትን ሁሉ ክጃለሁ በል አሉት፤ እርሱ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ስህተቴን አሳዩኝ እንጂ አልክድም አለ። በዚህም ምክንያት አቃጥለው ገደሉት። የደህንነት ማለፊያ (Safe passage) እኮ ቃል ተገብቶለት ነበር ቢባልም እርሱ መናፍቅ ነው፤ ለመናፍቅ ተፈጻሚ የሚሆን ቃል የለም ተባለ። ጓደኛው ጀሮም (Jerome of Prague) መጀመሪያ ላይ በፍርሐት ክጃለሁ ብሎ ነበር በኋላ ላይ ግን ተጸጸተ እና ተመለሰ ከዛም በዓመቱ እዛሁ ቦታ ላይ አቃጠሉት።

በዚህ ምክንያት ግን ቦሄሚያውያን ተቃውሞ አስነሱ። ፖፑ ግን ምን እንዳደረገ ታውቃላችሁ? ጦርነት አውጀባቸው ሊያውም ለተዋጊዎቹ "የጽዳት ቦታ" (Purgatory) ጊዜ እንደሚቀንስላቸው ቃል ገብቶ፤ ይህም "የሁሳይት ጦርነቶች" (Hussite Wars) ይባላል።

ዛሬ ላይ ግን በቼክ እና ስሎቫኪያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት (Orthodox Church of the Czech Lands and Slovakia) ዘንድ ጃን ሀስ እና ጀሮም እንደ ሰማዕታት በይፋ ባይሆንም ይከበራሉ (unofficial veneration ነው በሕዝቡ እንጂ በቤተክርስቲያኒቷ አልተቀነኑም)። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ሀስን እንደ ፕሮቴስታንት ሳይሆን፣ የጥንቱን የቤተክርስቲያን ሥርዓት ለመመለስ እንደሞተ እና ከሮም ፈጠራዎች (Innovations) ጋር እንደታገለ ኦርቶዶክሳዊ ሰማዕት አድርገው ይቆጥሩታል።
🔥 29 ❤ 18 👍 5
10:47
❤ 18
ኪ
22:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=Dn8Q1LPtGrU

Explanation of the 12 Anathemas
❤ 27 👍 3
27 January 2026
ኪ
13:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 7
ኪ
14:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
Me right now 😂😂
😁 52 🎉 13 🤔 3 ❤ 2 👀 2
29 January 2026
ኪ
09:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
አዝማንየ አዝማንኪ አምጣንየ አምጣንኪ

እግዚአብሔር ለአብ መራዕቱ የተባለች እመቤታችንን አዝማንየ አዝማንኪ (ዘመንሽ ዘመኔ ሆነ) አላት ዘመናት የማይወስኑትን የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ከዘለዓለም እንደ ወለደ እርሷ በጊዜ ውስጥ ወልዳዋለችና። ከማርያም የተወለደው ህልውናው የጀመረው ከማርያም አይደለም ይልቅስ ለህልውናው ጅማሬ የለውም እርሱ ለዘለዓለሙ ከአብ ነው ዘመኑስ የአብ ዘመን ነው ከማርያምም የተወለደው እርሱ ራሱ ነው ከማርያም የጀመረ ሰውነት ቢኖረውም ይህ ሰውነት የእግዚአብሔር ቃል ሰውነት ሆኗልና ዘመንህ የአብ ዘመን ነው እንለዋለን እመቤታችንም በዘመናት የሸመገለውን እርሱን በመውለዷ ዘመኗ የአብ ዘመን ነው ተባለላት። እኛስ በታሪክ እናቱን በዘመን የሚቀድም ልጅ አይተን አናውቅም ነገር ግን እናቱ የምትቀድመውን ሰውነት የራሱ በማድረጉ ልጅየው የእግዚአብሔርን አብን ዘመን ከማርያም በነሣው ሥጋ አስቆጠረለት። ስለዚህ ከህልውናዎች ሁሉ ዘመን የማይወስነውን ዘለዓለማዊ ወለድን ብለው መናገር የሚችሉ ሁለት አካላት ብቻ ናቸው እግዚአብሔር አብ እና ድንግል ማርያም ስለዚህም እመቤታችን በዚህ አብን መሰለችው።

እንዲሁም አምጣንየ አምጣንኪ (መጠንሽም መጠኔ ሆነ) አላት ሰማይ እና ምድርን የሚሞላን ጌታ አብ እንደ ወለደ እርሷም ወልዳለችና። ይህን ሳስበው አንድ ቅኔ ትዝ ይለኛል እንዲህ ይላል፡

እም ጥንት ኢመልዑ እስከ ይእዜ አዳም ወሔዋን ዘአበዊሆሙ ቤተ፣
- እመ ይወልዱ ክልኤተ ክልኤተ።
- ማርያምሰ ዘኮነት ቅድስተ ቅዱሳን በረከተ፣
- መልዓት ምድረ ወሰማያተ፣
- ወሊዳ ዋሕደ ወተወሊዳ አሐተ፣
- መልዓት ምድረ ወሰማያተ።

ትርጉም፡ ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ አዳም እና ሔዋን መንታ መንታ እየወለዱ ዐለምን አልሞሉም። የቅድስተ ቅዱሳን በረከት የሆነች ማርያም ግን አንድ ሆና ተወልዳ እርሷም አንድ ወልዳ ምድር እና ሰማያትን ሞላች።

ሰማይ እና ምድር የማይወስኑትን እርሱን በመውለዷ እግዚአብሔር አብን መሰለችም ስለዚህም መጠኗ መጠኑ ሆነ እኛምΠλατυτέρα τῶν Οὐρανῶν ( Platytera ton Ouranon - More Spacious than the Heavens) ብለን አመሰገናት የመለኮትን ክፍል ሳይሆን የመለኮት ሙላት በሥጋው ይኖራል የተባለለትን እርሱን በሥጋ ወልዳዋለችና!
❤ 117 🥰 9 ❤‍🔥 7 🔥 5 👍 1
30 January 2026
ኪ
10:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
እኔ ለእናተ የማልሆነው ነገር የለውምና የአባቶችን ስም ከልሳነ እንግልጣር ወደ አማርኛ ማምጣት ስትቸገሩ ስላየሁ lol
👍 43 🤣 22 😁 7 ❤ 4 🔥 4 🥰 3 🙏 1
31 January 2026
ኪ
08:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
08:55
እንደዚህ አይነት የማይሆን argument እኔ አላየሁም። በአማን ምስራቁን ከፍ ለማድረግ ብሎ እንደጣለው አልገባውም። በእርሱ አባባል vernacularism (ሥርዓተ አምልኮ ሕዝብ በሚሰማው ቋንቋ መሆኑ) የፕሮቴስታንት ተጽእኖ ነው ፤ ስለዚህ ቅዱስ ፍሬምናጦስ የግሪኩን ቅዳሴ ወደ ግዕዝ (ሕዝቡ ያኔ የሚሰማው ግዕዝ ስለነበር) መተርጎሙ ፕሮቴስታንታዊ ተጽእኖ ነዋ? ምስራቁ ዓለምም ሕዝቡ የሚጽልየውን ነገር እንዲገባው ከማድረግ ይልቅ "vibe" ላይ ብቻ ነዋ የሚያተኩረ? (የሚባለው ነገር ሳይገባህ እንዲሁ በዜማው vibe መመሰጥ ከሆነ አምልኮን ወደ ritualism and vibe መለወጥ ነው) ይሄ rewriting history ይባላል። በአማን እንዲህ ያስባለው አሁን ላይ በአብዛኛው ምስራቁ ዓለም ሕዝቡ የማይሰማው liturgical language ስላለው ነው (ግሪኮች ኮይኔ ግሪክ ፣ ግብጾች ቅብጥ ፣ ሩሲያ ቸርች ስላቮኒክ ወዘተ) ይህ ግን anachronistic reading ነው ምክንያቱም እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ሕዝብ የማይሰማው liturgical language የኖራቸው by design ሳይሆን by flaw ነው ምክያቱም ያኔ እነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች ሕዝብ የሚሰማቸው ነበሩ ከጊዜ በኋላ ግን ሕዝቡ እነዚህን ቋንቋዎች መስማት አቆመ።

ይህንን ለመረዳት የፕሮቴስታንት ሐዳስያንን ሙግቶች ማየት ነው። በእነርሱ ዘመን ካቶሊክ በላቲን ብቻ ነበር የምትቀድሰው እነርሱም ቅዳሴ ሕዝብ በሚሰማው ቋንቋ መሆን አለበት ለማለት የሚጠቁሙት ምስራቃውያንን ነበር ያኔ አብዛኛው ምስራቃውያን የሚቀድሱት ሕዝብ በሚሰማው ቋንቋ ነበርና ስለዚህ ነገሩ የምስራቃውያን "vibe" ላይ ማተኮር አይደለም ይልቅስ የቤተክርስቲያኒቱን ቋንቋ የሚሰማ ሰው በጊዜ ሒደት መጥፋቱ እንጂ።

አሁን ላይ ደግሞ የሚገርመው ነገሩ ተገላቢጦሽ መሆኑ ነው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከቫቲካን 2 ጉባኤ በኋላ ቅዳሴ ህዝብ በሚሰማው ቋንቋ እንዲሆን ወስናለች ስለዚህ አሁን ላይ በአብዛኛው ቅዳሴ የሚቀደሰው ሕዝብ በሚሰማው ቋንቋ ነው። እንዲሁም ኢትዮጵያ ላይ ያሉ ካቶሊኮች የሚጠቀሙት latin rite and geez rite በአማን ያልተረዳው ቋንቋን የሚያመላክት ሳይሆን ሥርዓትን የሚያመላክት ነው። Latin rite የሚከተሉትም በላቲን ሥርዓት በቋንቋቸው ነው የሚቀድሱት ፣ የግዕዝ ሥርዓት የሚከተሉት ደግሞ በግዕዙ ሥርዓት የግዕዝም የአማርኛም ቅዳሴ አላቸው።
❤ 62 👎 10 👍 8 🔥 5 👏 4 ❤‍🔥 1
1 February 2026
ኪ
13:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vt.tiktok.com/ZSaqaQ7DE/

በጌታ ቀን ሽክ ብለን
❤ 29 👍 1
ኪ
21:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/JK9Zg8mvfVo?si=icLEWi56ykj7bSav

እስቲ ደሞ እንደዚህ ቪዲዮ ለመሥራት እንሞክር ፤ ዝም ብላችሁ እዩ ደሞ
❤ 37
3 February 2026
ኪ
09:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
ግቢ ጉባኤያት ሥራ አመራሮች ካላችሁ የማሳስባችሁ ነገር ቢኖር እሑድ ጉዞ እንዳታዘጋጁ ነው ክርስቲያን በጌታ ቀን በቤተክርስቲያን ተገኝቶ ወንጌል ሰምቶ መሥዋዕተ ቁርባን አሳርጎ እርሱም ከቁርባን ተቀብሎ ነው መዋል ያለበት።

እኔም የግቢ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ የነበርኩ ጊዜ በተቻለኝ መጠን ሞክሪያለሁ ይህ እንዳይሆን በዕለተ እሑድ ሁላችንም በአምልኮ ልንገኝ ግድ ይለናል ጉዞ ካስፈለገ ቢያንስ ቅዳሜ አድርጉ ነገር ግን ሌላ ማድረጊያ ቀን ካጣችሁ የእሑድ ቅዳሴ ላይ ጉዞ ከምትደርቡ ጉዞ ሳታደርጉ ቢቀር ይሻላል።
❤ 73 👍 16 👏 4 🔥 2
ኪ
09:40
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
እሑድ ቅዳሴ ሁሌ አለ ጉዞ ግን በዓመት አንዴ ነው የምናዘጋጀው የሚለውም ምክንያት አይሆንም እሑድን schedule የምታደርጉት የናንተ ቀን አይደለም እሑድ የጌታ ቀን ነው ፤ የጌታ የሆነውን ለጌታ መስጠት አለብን ያለበለዚያ በቅዳሴ ሰአት ጉዞ ካዘጋጃችሁ የጌታ የሆነውን እየሠረቃችሁት ነው። (ይሄ ማኅሌት እኮ በዓመት ጥቂት ጊዜ ነው ቅዳሴ ግን ሁሌም ነው ብለው ቅዳሴ ለሚወጡትም ይሠራል የጌታ የሆነውን ለጌታ ስጡ)
🔥 41 ❤ 30 👏 5 👌 2
4 February 2026
ኪ
22:58
ኪዳን ዘኢየሱስ
🔥 35 ❤ 10 👏 2 👍 1
6 February 2026
ኪ
13:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
አንድን ጉባኤ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሚያደርገው ምንድነው?
Anonymous poll
- በንጉሥ የተጠራ እና በመንግሥቱ በምልዓት ተፈጻሚነት ካለው 19 votes, chosen vote
- አራቱ ፓትሪአሪኬቶች ከተቀበሉት automatically ይሆናል 102 votes
- ፖፑ ዓለም አቀፍ ጉባኤ አድርጎ ካወጀው 21 votes
- በአማኞቹ ሁሉ ተቀባይነትን ካገኘ 46 votes
- መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ካብራራ 132 votes
- ፓትሪያሪኬቶቹ ተቀብለውት ቀድሞ ከነበረው እውነት የሚገጥም ከሆነ 360 votes
- ሲጀመር የዓለም አቀፍ ጉባኤ በሮም መንግሥት ጊዜ መጠቀሚያ tool እንጂ አሁን የለም 48 votes
728 votes
❤ 20
7 February 2026
ኪ
20:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
Offline for a while
😢 50 ❤ 8 😭 3 👍 2 👎 1 👏 1 🤔 1 🤣 1
17 February 2026
ኪ
09:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
The 21 Coptic Martys of Libya were martyred by ISIS on February 15 may their holy blessings be upon us.
❤ 57 😁 19 🙏 8 🤣 6
ኪ
16:12
ኪዳን ዘኢየሱስ
እኛ ፣ ቅብጣውያን እና የማላንካራ ሕንዶች ትናንት ሰኞ ጀምረናል (ማላንካራውያን ግን ከእኛ አንድ ሳምንት ቀድመው ይጨርሳሉ) ፤ የእኛዋ ሶርያ እና ኢስተርኖች ቀጣይ ሳምንት ሰኞ ይጀምራሉ (ከእኛ እኩል ይጨርሳሉ) ፤ የላቲን ካቶሊኮች ፣ ሉተራኖች ፣ አንግሊካኖች እና ሌሎችም ጥንታዊ ፕሮቴስታንቶች ነገ በአመድ ረቡዕ ይጀምራሉ (ከማላንካራውያን እኩል ይጨርሳሉ) ፤ የአገሩ ውስጥም ሆኑ የውጪ ባፕቲስቶች እና ጴንጤዎች ደግሞ ጩከታቸውን ገና ከአሁኑ ጀምረዋል 😄

ብቻ እንኳን አደረሳችሁ ለታላቁ ጾም
❤ 97 😁 30
19 February 2026
ኪ
11:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ አንድ ጥያቄ ተጠየቁ

አሁን ያለንበት ሳምንት ዘወረደ ይባላል በሌላ ስሙ ጾመ ሕርቃል የሚል ስም ይሰጠዋል ይባላል ይህ ሳምንት የሚገኘው የእስክንድርያን ሥርዓት (Alexandrian rite) በሚከተሉት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ነው አሁን ላይ (ግብጽ ፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ) ነገር ግን ጾሙ ሕርቃል በሚባል ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ በ7ተኛው ክፍለ ዘመን በነገሠ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ ስም ይጠራል ይባላል።

ነገር ግን ይህንን narrative ትንሽ challenge የሚያደርጉ ነገሮች አሉ። አንደኛው የጾሙ ሳምንታት በቅዱስ ያሬድ ነው የተሰየሙት ቅዱስ ያሬድ የነበረው በ6ተኛው ክፍለ ዘመን ነው እንዴት እሱ በነበረበት ጊዜ ያልነበረ ጾምን ሊሰይም ቻለ?

ሁለተኛው በ4ተኛው ክፍለ ዘመን (ወይም 5ተኛው) የሚገመተው የኢጌሪያ ጉዞ ማስታወሻ (Egeria's pilgrimage) ኢየሩሳሌም ውስጥ ዓብይ ጾምን 8 ሳምንታት ለ55 ቀናት (ይህን የመጀመሪያውን ሳምንት ጨምሮ) እንደሚጾሙ ይዘግባል። እሷ የሰጠችው ማብራርያ በ8 ሳምንታት ውስጥ 15 ቅዳሜ እና እሑድ አለ 14ቱ አይጾምበትም (ከቀዳሚት ስኡር በቀር) ስለዚህ 41 ቀን ይሆናል ስለዚህ 40ውን ቀን ለማምጣት ነው የዘወረደ ሳምንት እና የሕማማት ሳምንት ጾም የተጨመረው ማለት ነው። ይህ እውነት ከሆነ ጾሙ ከሕርቃል በፊት ስለመኖሩ ጠቃሚ አይደለምን?

ሦስተኛ ሕርቃል ኬልቄዶናዊ ነው ሊያውም ኦርቶዶክሳውያንን ያሳደደ ነገር ግን ይህ ጾም በኬልቄዶናውያን አብያተ ክርስቲያናት በየተኛውም አይታሰብም የሚታሰበው በእኛዎቹ የእስክንድርያ ሥርዓት ተከታዮች ዘንድ ብቻ ነው እና ታድያ የኬልቄዶናውያንን ጾም እኛ ብቻ እንዴት ልንጾም እንችላለን?

እስቲ ሐሳብ ስጡ
🤷 23 ❤ 13 🤷‍♀ 3
20 February 2026
ኪ
20:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰው ሆይ ይህን አስታውስ አፈር ነህ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።

ተዘከሩ ዕለተ ሞትክሙ።
❤ 76 👍 7 😢 6
23 February 2026
ኪ
09:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዚህ ሳምንት የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አብይ ጾምን ጀምራለች ይህን የጀመረችበትን እሑድም በደስታ ነው የሚጀምሩት እርሱም የቃና ዘገሊላ እሑድ በመባል ይጠራል። በአጠቃላይ 48 ቀናትን ትጾማለች 5ቱ ሳምንታት የ4ኦው ጾም የቀረው ሳምንት ሕማማት። እነዚህ እሑዶች ጅማሬያቸው እና ፍጻሜያቸው ደስታ ነው በቃና ዘገሊላ እሑድ ጀምራ በሆሳዕና ትፈጽማለች በመካከሉ ያሉት 5 እሑዶች ደግሞ ክርስቶስ የፈወሳቸው የተለያዩ ሰዎች ይታሰቡበታል (pdfኡ ላይ አስቀምጬዋለሁ ንባባቱን)።

የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ከኢትዮጵያ ጋር አንድ ላይ ባለፈው እሑድ ጾሙን ብትጀምርም ያለፈውን ሳምንት የአብይ ጾም ውስጥ አትቆጥረውም የዝግጅት ሳምንት ትለዋለች እንጂ። ይህኛውን የመጀመሪያውን እሑድ ደግሞ "ብል እና ነቀዝ በሚበላው መዝገብ በምድር አትሰብስቡ ይልቅስ ሰሰማይ መዝገብ ሰብስቡ" በማለት የሰማያዊ መዝገብ እሑድ ትለዋለች ይህም መዝገብ ክርስቶስ ነው! (ሌሎቹን እሑዶች pdfኡ ላይ ይመልከቱ)።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶም የቅድስት ሳምንትን ጀምራለች ፤ መላክም የሰማያዊ መዝገብ ቅድስት ቃና ዘገሊላ ሳምንት (ስናደባልቀው 😁)
❤ 48 ❤‍🔥 1 👍 1
24 February 2026
ኪ
14:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
I can't 😂😂

1. A Chalcedonian author compiles a florilegium that misrepresents St. Cyril of Alexandria's Christology.

2. Severus of Antioch cites this Chalcedonian author in his Philalethes to systematically refute the misrepresentation.

3. Decades later, the Julianists misinterpret and miscite Severus's Philalethes to argue for their doctrine of incorruptibility.

4. Severus is forced to write an Apology for the Philalethes, citing the Julianists who miscited him, who was citing the Chalcedonian, who miscited Cyril.
😁 22 🤔 3 🤣 3 ❤ 1 🙉 1
ኪ
15:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
በቅርቡ ስለዚህ ጉዳይ ከአንድ ሉተራን ወንድም ጋር discussion ይኖረናል እስቲ confirm ሲደረግ ይነገራችኋል
🔥 38 ❤ 10 ❤‍🔥 3
25 February 2026
ኪ
21:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
እኔ ከዲቤቶች በኋላ ግርም የሚለኝ በሁለቱም ወገን ያሉ ሰዎች የሚደግፉት ሰው አሸንፎ የሚወጣው ነገር ነው
🤣 131 😁 12 ❤ 3 😭 2 👍 1
2 March 2026
ኪ
10:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
አድዋ ዛሬ ናት 🙌
🤣 86 😁 21 🥰 6 🥱 1
ኪ
11:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
መስሎት ነበር ጣልያን መስሎት ነበር ሮማ፣
በፓስታ የጠነከረ ጉልበት ያለውማ፣
የአድዋን አርበኛ ቆጣ ብሎ ሲያየው፣
ማካሮኒውን ጥሎ እግሬ አውጪኝ አለው!
🤣 74 😁 10 ❤ 2 🌚 1
ኪ
11:44
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
መስሎት ነበር ጣልያን መስሎት ነበር ሮማ፣
ጴጥሮስ ተሰቅሎለት ጳውሎስም ቢደማ፣
ገሰገሰ ኢትዮጵያ መድፍ ተሸክሞ፣
ኢትዮጵያዊው ዲያቆን ሳለ በአርምሞ።
እጣኑን ተወና ቢያጤሰው ባሩዱን፣
አሳጣው ለጠላት መሸሻ መንገዱን

ዛሬ አልፋታችሁም 😁
🔥 59 😁 27 ✍ 2 👏 2 ❤ 1
ኪ
12:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
Jokes aside ግን የምር አድዋ ትልቅ የሚያኮራ ድል ነው አውሮፓውያን በጣም ጥቁሮችን ከመናቃቸው የተነሣ underestimate አድርገውን ነበር የመጡትም በ over confidence ነበር። ኢትዮጵያውያን ግን ለሃገራቸው እንደማይደራደሩ አሳይተዋል ምንም እንኳን ውስጣዊ ልዩነት ቢኖርባቸውም ሃገራቸው ስትነካ ግን በአንድነት ቆመዋል ወንድሜ አስቀይሞኝ ከእርሱ ጋር ልጣላ እችላለሁ ነገር ግን ወንድሜን ከእኔ ውጪ ማንም እንዲነካው አልፈለግም በሚል መንፈስ በአንድነት ቆመው ለአፍሪካውያን የነጻነት pan-African movement መሠረት ሆኑ። ለዚህም ትልቁ ማሳያ የብዙ አፍሪካ ሃገራት ባንዲራ የኢትዮጵያው variation ነው inspire አድርጓቸዋልና።

ዛሬም ውሳጣዊ ልዩነት ቢኖሩብንም እስቲ አንድ ለመሆን ውጪያዊ ጠላት አንጠብቅ ከነልዩነታችን አንድ እንሁን እንጂ ጌታ በእውነት አንድ ያድረገን ፤ እግዚአብሔር ሃገራችንን ይጠብቅልን ፍጹም ሰላሟንም ይስጣት።

ጸልዩ በእንተ ሃገሪትነ ኢትዮጵያ!
❤ 134 🔥 9 😁 2
ኪ
18:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
T
Timeless Truth 02.03.2026 18:48:26
https://vt.tiktok.com/ZSmT21MVL/

ቅዳሜ ጠይቁ ብዬ ከተጠየቁ ጥያቄዎጽ መካከል ክርስቶስ ሲያርቅ ሰውነቱን ይዞ ነው? ካድያ በቦታ ከመገደብስ አንጻር እንዴት ይታያል? የሚለውን ኪዳንን መልሶልናል

ቲክቶክ ላይ active ስላልሆንኩ በደንብ copy link አድርጉ ሰውም እንዲያየው
❤ 16
3 March 2026
ኪ
18:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
O
Orthodoxy eLibrary 03.03.2026 18:05:55
ዛሬ ደግሞ በክርስቶስ ህማም ላይ ከተጻፉ የሁልጊዜ ምርጥ መጽሐፍት መካከል አንዱ የሆነውን "The Crucification Of The King Of Glory" የሚለውን መጽሐፍ የምንወደው ወንድማችን @KidanZeIyesus ይጋብዘናል 😊

መጽሐፉ ይኸው 👉🏼 https://t.me/Orthodoxy_eLibrary/2208

መልካም ንባብ!

@Orthodoxy_eLibrary
❤ 23
ኪ
18:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
አንብቤ ከወደድኳቸው መጻሕፍት መካከል ዋነኛው ነው
👍 18 ❤ 8 🙏 1
7 March 2026
ኪ
10:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንደዚህ አይነት ነገር እያያችሁ መጥታችሁ ይሄ የምዕራባዊ ነው እኛ አናምንበት እንዳትሉ please. This is a modern 20th Century Eastern Orthodox polemical oversimplification to distance themselves from western scholasticism (not all eastern Orthodox but by thinkers like John Romanides) አሁን ደግሞ ወደ እኛ ቤተክርስቲያንም ሰተት ብለው እየመጡ ነው but historically both the east and west believed that:

Sin is both a Spiritual ilness and breaking God's law.
Salvation is both legal acquittal and Union with God.
Church is both life with Christ and authority structure.
🔥 24 ❤ 10 👍 5 🎄 2 🤣 1
ኪ
18:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
Who has a cooler Icon collection than me 😎
❤ 56 ❤‍🔥 5 😁 5
18:28
18:28
18:28
18:28
18:28
ኪ
19:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
Top 3 Favorite መዝሙርስ for me፡
1. ኃይሌም ዝማሬዬም
2. ስምህ ይጣፍጣል
3. ይቅርታ

Special event ፡ ተነሥቷል በዚህ የለም
❤ 69 🥰 7
8 March 2026
ኪ
11:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
'86 ዓመት ሳገለግለው አንድም ቀን ያላሳዘነኝን ጌታ እንዴት እከዳዋለሁ!

እነሆ በዚህች ቀን የሰርምኔሱ ሊቀ ጳጳስ የዮሐንስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ፖሊካርፖስ በሰማእትነት አረፈ!
❤ 160 🙏 4
9 March 2026
ኪ
07:41
ኪዳን ዘኢየሱስ
On this day also of the year 1971 A.D., the holy and righteous father Abba Kyrillos the Sixth, the one hundred and sixteenth Pope of Alexandria, departed. God has accorded this pure father the gift of working great miracles even after his departure.
His prayers and blessings be with us. Amen.

Baba Kyrillos ❤️
❤ 129 🙏 4
10 March 2026
ኪ
11:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
አርሴማ "Aesthetica" የሚባል አይከን ስቲከርስ ፣ ቲ-ሸርቶች እና ሌሎች ከሥዕላት ጋር የተያያዙ ነገሮች መሸጫ ሾፕ ከፍታለች።

ሰዎች ተቀላቀሉ ፣ እዘዟትም እኛ ኦርቶዶክሳውያን እርስ በእርስ መተጋገዝ አለብን እኛው ነን ለእኛው ያለነው።
https://t.me/aesthetica_merch
❤ 37 🔥 9 💯 1 🤝 1
ኪ
12:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሦስተኛውን ጥያቄ የመለሰበትን መንገድ እዩልኝማ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞችም ይጠይቃሉ ይህን።

ጸሐፊው ማን እንደሆነ ገምቱ ፤

NB: ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ አይደለም ነገር ግን አመላለሱ ከሳዊሮስ ጋር ተመሳሳይ ነው
🔥 7 ❤ 1
12:16
ኪ
20:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=m6cowtwedvU&t=1832s

Damn ይህን ቪዲዮ አሁን አይቼ ጨረስኩት እውነት ለመናገር ጉዳዩን ከዚህ በፊት ባውቀውም ይህን ያህል አልመሰለኝምና ደንግጫለሁ።

ስለ "ተአምራዊው" ቅዱስ ብርሃን (እሳት) ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ከዛሬ 3 ወይም 4 ዓመታት በፊት ይመስለኛል ያኔ ተገርሜ ነበር እንዴት ያለ ተአምር ነው ብዬ። ከዛሬ 2 ዓመት በፊትም እንዲሁ የፋሲካ ዋዜማ ቅዳሜ ብዙዎች ስለ "ተአምሩ" አዳንቀው ሲጽፉ አየሁና እኔም ልጽፍ ተነሳሁ ፤ ከመጻፌ በፊት ግን ላጣራ ብዬ ለማጣራት ተነሣሁ ያገኘሁት ነገር ግን ተአምር መሆኑን ሊደግፍ ይቅርና ተአምር ነው ለማለት የጠቀሱት ነገሮች አሳማኝ ሳይሆኑ አገኘኋቸው። ለምሳሌ ፓትሪያሪኩ ምንም አይነት አቀጣጣይ ነገር እንዳይዝ ይፈተሻል ይባል ነበር ነገር ግን እሱም ሐሰት መሆኑን አየሁ ፣ እንዲሁም እሳቱ ለ33 ደቂቃ አያቃጥልም ይሉ ነበር ነገር ግን የማያቸው እያንዳንዱ ቪዲዮዎች ላይ እጃቸውን እሳቱ ላይ አንድ ጊዜም ከ1 ሰኮንድ በላይ ሲያስቀምጡ አላይም በላዩ ያመላልሱታል እንጂ ይሄን ደሞ እኔ ቤቴ ባለ ሻማ አደርጋለሁ ፣ ከዚህ የበለጠ ደግሞ ከግሪኩ ፓትሪያሪክ ጋር የሚገባው የአርመኑ ጳጳስ ውሸት ነው እሳቱ ተአምር አይደለም እዚያሁ ቀድመው ካበሩት ሻማ ነው ሚያቀጣጥሉት የሚል ቪዲዮ አየሁ። ይህን ሁሉ አይቼ ያን ቀን ስለ እሳቱ ከመጻፍ ተቆጠብኩ ነገር ግን በፍጹም አላመንኩበትም ነበር።

ከጊዜያት በኋላ ግን ከኢስተርኖች ዘንድ ብዙ claims ሰማሁ በ13ተኛው ክፍለ ዘመን የላቲን ክሩሴዶች ኢየሩሳሌምን በተቆጠጠሯት ጊዜ የላቲኑ ጳጳስ እሳቱ እንዲመጣለት ሞክሮ አልቻለም ይህ የሚያሳየው እውነተኛው እምነት ኦርቶዶክስ ነው ይላሉ ፤ እንዲሁም በ16ተኛው ክፍለ ዘመን የአርመኑ ጳጳስ ሞክሮ እምቢ አለህ ስለዚህ አርመኖችም ትክክለኛ እምነት የላቸውም ብቻዋ እውነተኛ እምነት ኢስተርን ኦርቶዶክስ ናት ይላሉ። ይህን ሁሉ ለማረጋገጥ ሞከርኩ ግን ታሪኩ ሐሰት ከመሆኑ በላይ ሪፖርቶቹ ሁነቱ ተካሔደ ከተባለበት ዘመን በጣም በብዙ 100 ዓመታት እንደሚርቁ አየሁ ፣ እንዲሁም ስለ "ተአምራዊው ብርሃን" እድገትም በዘመናት ሒደት ምን ይመስላል የሚለውን ሳይም መጀመሪያ ላይ እኛ በየፋሲካው እንደምናደርገው እነሱም እሳት አቀጣጥለው "ትንሣኤከ ለዕለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ" ከሚመስል ሁነት ተነስቶ ከዛም ሕዝቡ ሁሉ ከነካህናቱ ውጪ ላይ ሆነው እሳቱ እንደሚወርድ ወደ ሚል ታሪክ አደገ ፣ ከዛም ፓትሪያሪኩ ብቻውን ገብቶ እሳቱን ያመጣል ወደሚለው አደገ።

ይህን ሁሉ አይቼ በቃ ይህ ነገር ሐሰት ነው ብዬ አልደመደምኩም ነበር ግን ከራሳቸው ከኢየሩሳሌሙ ጳጳሳት እሳቱ natural እንደሆነ ቪዲዮዎች አየሁ እናም ማረጋገጫ ሆነልኝ። ብቻ በመጨረሻው ይህን እያሰብኩ በታሪክ የተረጋገጠ ተአምር አለን እያልኩ ትናንትና እያሰብኩ ስለዚህ እሳት ሀሳቡ መጥቶልኝ ፣ ፋሲካም እየቀረበ አይደል ልጻፍበት ብዬ ሳስብ ይሄ የኤገን ቪዲዮ ተለቀቀ አይ አጋጣሚ 😁

ግን ነገሩ ካሰብኩት በላይ አስደንጋጭ ነው ይህን ያህል ውሸት ፣ ይህን ያህል ማጭበርበር ለዚያውም በፓትሪያሪኬት ደረጃ በጣም ከባድ ነው። ብቻ ከአሁን በኋላ አንድ claim ስታገኙ ቶሎ ከማመናችሁ በፊት መጀመሪያ አረጋግጡ ሌላ ምን ይባላል።
👍 28 ❤ 12 🔥 4
11 March 2026
ኪ
10:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
በመጨረሻው ሰአት ዛሬ አልቻልኩም ብሎ አሳወቀኝ በቃ እኛ በራሳችን ቤት ገብተን እንወያይባቸዋለን
👍 21 ❤ 5 😁 3
ኪ
10:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vt.tiktok.com/ZSuB2a8qR/

Esti Copy link adrgu
🫡 5 ❤ 3
ኪ
20:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vt.tiktok.com/ZS9dphVBksJGv-MTz4f/

ኧረ ኑ ብቻዬን ቁጭ አልኩ
😁 17 🤣 8
13 March 2026
ኪ
21:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 33
17 March 2026
ኪ
09:56
ኪዳን ዘኢየሱስ
እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ሕፃናት ጥምቀት ብዙህ ተብሏል ብዙህም ተከራክረናል ለምድነው ግን ስለ ሕፃናት ቁርባን ምንም ያልተባለው?

በምዕራቡ ዓለም የሕፃናት ቁርባን ላይ ካቶሊኩም፣ ፕሮቴስታንቱም በአጠቃላይ ይስማማል ሁሉም በአንድነት ቁርባን አንድ ሰው ተረድቶት የሚፈጽመው ስለሆነ ሕፃናት መቁረብ የለባቸውም ይላል። በምስራቁ ዓለም ግን ሁሉም ሕፃናት መቁረብ እንዳለባቸው ይስማማል ሲጀመርም ጥምቀት ያለ ቁርባን አይፈጸምም (የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንም ራሷን ምሥራቃዊት ነኝ ብትልም ሕፃናትን እንደ ላቲኖቹ አታቆርብም)።

ሕፃናት መጠመቅ አለባቸው ፣ በጥምቀትም ጸጋ እግዚአብብሔርን ይቀበላሉ እያሉ ፣ ሕጻናትን ቁርባን መከልከል ምንም ምክንያታዊ አይደለም ሁለቱም ጸጋ መቀበያ መንገዶች ናቸው ጥምቀት ሲፈጽምለት መረዳቱ ግድ ያላለው ሕጻን ለምን ቁርባን ላይ መረዳት ይጠበቅበታል እንደሚባል ግልጽ አይደለም። ቁርባን የክርቶስ ሞት እና ትንሣኤ መታሰቢያ ነው ሕጻናት ደግሞ ማሰብ አይችሉም የሚሉም አሉ። ጥምቀትም እኮ እምነትን መመስከሪያ ነው ለዚህም ነው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ በጥምቀት ጊዜ የሚመሰከር የእምነት ድንጋጌ የነበረው (በሐዋርያት ዘመን ኢየሱስ ጌታ ነው ብሎ መመስከር ነበር ኋላ እየሰፋ የሐዋርያት የእምነት መግለጫ ፣ የኒቅያ የእምነት መግለጫ ሆነ)ታድያ እምነታቸውን ሳይረዱ በእግዚአብሔር ላይ ባላቸው የዋሕ እምነት ብቻ ሕፃናት ከተጠመቁ እና በእውነትም ክርስቲያን ከሆኑ ቁርባንስ ምን ይከለክላቸዋል?

ይህ ክርክር በአውግስጢኖስ ዘመን መኖሩን ራሱ አውግስጢን በድርሳኑ ለሕጻናት ደግፎ "ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ከሆነ ሕፃናት ኢየሱስን በቁርባን መቀበል አያስፈልጋቸውም ማለት ለሕፃናት ኢየሱስ አይደለም ማለት ነው።" እያለ ይጽፋል (ከዚህ በፊት እንዲህ ጽፌበታለሁ፡ https://t.me/KidanZeIyesus/287) ፤ ይህ የሚያመላክተው ይህ ጥያቄ ጥንታዊ ጥያቄ መሆኑን ነው።

ከሐዋርያት ድንጋጌ በተጨማሪ በሦስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ቅዱስ ቆጵርያኖስ ዘቅርጣግና በሱ ዘመን ቅዳሴ ላይ ሕፃናት ሁሉ እንደሚቆርቡ እንዲህ ይጽፋል "ይሁን እንጂ፣ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቱ ሲጠናቀቅ እና ዲያቆኑ በቦታው ለነበሩት ሰዎች ጽዋውን ማቅረብ ሲጀምር፣ ሌሎቹ ተቀብለው የሷ ተራ በደረሰ ጊዜ፣ ትንሿ ልጅ በመለኮታዊ ግርማ ስሜት ፊቷን አዞረች፤ ከንፈሮቿን አጥብቃ በመዝጋት ጽዋውን አልቀበልም አለች። ዲያቆኑ ግን አሁንም አጥብቆ በመያዝ፣ ምንም እንኳን እሷ ብትቃወምም፣ ከጽዋው ቅዱስ ቁርባን በግድ አጠጣት።" (Cyprian of Carthage , treatise on the Lapsed Chapter 25) (ዲያቆናት ሆይ አይዟችሁ ሕፃናትን ለማቁረብ የምታዩት መከራ ጥንታዊ ነው 😄)

እስቲ እዚህ ያላችሁ ሕፃናት መቁረብ የለባቸውም የምትሉበትን ምክንያት ጻፉ
❤ 48 👏 5 👎 1
ኪ
13:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
T
Theo-Sophia 17.03.2026 13:03:20
እነሆ እገዛችሁ የሚስፈልግበት ቀን መጥቷል። ከመቼውም ጊዜ በላይ ለእኛ የምትተጉበት ጊዜ እና አገልግሎታችንም እንዲቀጥል የምታደርጉበት ጊዜ መጥቷል። ይህንን በምትችሉት ሁሉ Share አድርጉ፦ በፌስቡክ (Facebook)፣ በቴሌግራም ስቶሪ በግሩፖችና ቻናሎች፣ በኢንስታግራም ስቶሪ ፣ በቲክቶክ (TikTok)፣ በግል መልእክቶች ልባቸው ክፍት ለሆኑ ሰዎች ሊደርስ በሚችልበት በማንኛውም ስፍራ አድርሱ ዜናው በሁሉ ዘንድ እንዲሰማ እና እንዲወራ የሁሉንም ሰው ጆሮ ልንወር ይገባናል። የአባቶችን ጽሁፍ ሁሉም ሰው ሊያነበው ይገባል!።
❤ 112
18 March 2026
ኪ
12:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
"ክርስቶስ የእምነታችን ሊቀ ካህናት" የሆነው መቼ ነው? ስለ እኛ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ካቀረበ በኋላ ሥጋውን ከሙታን ሲያስነሳ፤ እንዲሁም አሁን እንደሚያደርገው፣ ሁሉንም እየዋጀና ስለ ሁሉም ለእግዚአብሔር ማስተስረያ እየሆነ በእምነት ወደ እርሱ የሚቀርቡትን ራሱ ወደ አብ ሲያቀርባቸው አይደለምን?
❤ 44 👍 5 🔥 4
21 March 2026
ኪ
20:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
ባንተ ስለ መዳኔ
ምስክርህ ነኝ እኔ ❤️
❤‍🔥 138 ❤ 38
23 March 2026
ኪ
11:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
"አሁን ሁሉ ነገር በእርሱ ይፈጠር ዘንድ እርሱ ስለእኛ ተፈጠረ"

ይህን ማን የተናገረ ይመስላችኋል?
❤ 23
ኪ
12:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
አርዮሳውያን ምሳሌ 8፡22 ላይ "እግዚአብሔር ለሥራው የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ" የሚለውና ቆላ 1፡16 ላይ" ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው።" የሚለውን ይዘው ወልድ የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ፍጥረት ነው ብለው ሲከራከሩ። አትናቴዎስ ሲተረጉመው መጽሐፍ ቅዱስ የወልድን ሥጋዌ ሲናገር ሁሌም ምክንያቱን ያስቀምጣል ነገር ግን ቅድምናውን ሲናገር ምክንያት አያስቀምጥም ለምሳሌ "በመጀመሪያ ቃል ነበር" ይላል እንጂ "ቃል ለእግዚአብሔር ሥራ ሆነ ለፍጥረት ነበር" አይልም፣ እንዲሁም እዛሁ ምሳሌ 8 ላይ "ከተራሮች በፊት ተወለድኩ" ይላል እንጂ "ከተራሮች በፊት ለሥራው ተወለድኩ" አይልም እዚህ ላይ ግን ምክንያቱን ያስቀምጣል እርሱም "እግዚአብሔር ለሥራው" ይላል ስለዚህ በዚህ ጥቅስ መሠረት ጥበብ የተፈጠረው "ለሥራው" ነው ነገር ግን መወለዱ ለምንም ምክንያት አይደለም እንዲሁ አለ ይባላልና።

"እግዚአብሔር ለሥራው ፈጠረኝ" መባሉም ከጥበብ መፈጠር በፊት ሥራው እንደሚቀድም ያሳያል ጥበብ ራሱ የመፈጠሩ ምክንያት ለሥራው መሆኑን ያሳያልና ነገር ግን ቃል "መጀመሪያ ነበረ" የተባለለት ቀዳሚ ነው ስለዚህም የምሳሌው ጥቅስ ስለ ወልድ ወደ ህልውና መምጣት እየተናገረ ሊሆን አይችልም ይልቅስ ለድኅነት የተፈጠረ ሥጋን መዋሐዱን ያመለክታል እንጂ። "እግዚአብሔር ለሥራው የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ" መባሉም የእግዚአብሔር ሥራ በአዳም ኃጢአት የተነሣ በመውደቁ ቃል በሰውነቱ የተፈጠረው "ሥራውን" ዳግመኛ በእርሱ ውስጥ ሊፈጥረው ነው ስለዚህም ነው ቅዱስ አትናቴዎስ "ሁሉ በእርሱ ይፈጠር ዘንድ እርሱ ስለ እኛ ተፈጠረ" ብሎ የተናገረው።

በመጨረሻም ስለ ቆላስያሱ ጥቅስ እንዲህ በራሱ ቃል የተናገረውን እናስቀምጣለን ""እርሱ ስለ እኛ ከእኛ በኋላ ሰው ቢሆንም፣ በሥጋም ተፈጥሮ ወንድማችን ቢሆንም፤ የእኛ 'በኵር' ተብሎ ይጠራል፣ በእርግጥም በኵራችን ነው። ምክንያቱም፣ በአዳም መተላለፍ ምክንያት የሰው ልጅ ሁሉ ጠፍቶ ሳለ፣ የእርሱ ሥጋ የ'ቃል' (የእግዚአብሔር ቃል) ሥጋ በመሆኑ ምክንያት፣ ከማንም አስቀድሞ ድኗልና፣ ነፃም ወጥቷልና። ከእንግዲህም ወዲህ፣ እኛ ከእርሱ ጋር በመዋሐድ (አንድ በመሆን)፣ በእርሱ አርአያነት እንድናለን።"

— ቅዱስ አትናቴዎስ: Athanasius, 2nd discourse against Arians
🔥 38 ❤ 14 🥰 5 👍 2 👌 2
24 March 2026
ኪ
08:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኬልቄዶናውያን ኬልቄዶንን እንቀበላለን ሲሏችሁ መጠየቅ ያለባችሁ የትኛውን ኬልቄዶን? ብላችሁ ነው ኬልቄዶን አንድ አይደለም ሁለት ነው።

ንስጥሮሳውያኑ ኢባስ ዘኤዴሳ ፣ ቴዎድሪጦስ ዘቂሮስ እና ቴዎዶሮስ ዘመፕሶስትያ ኦርቶዶክስ የተባሉበት ኬልቄዶን ወይስ የተወገዙበት ኬልቄዶን?

"ቄርሎስ አዳሪውንና ማደርያውን ባለመለየት መናፍቅ ሆኖ ነበር አሁን ንስሐ ገባ እንጂ" የሚል ደብዳቤ ተነቦበት ኦርቶዶክሳዊ የተባለው ኬልቄዶን ወይስ ይኸው ደብሳቤ የተወገዘበት ኬልቄዶን?

"ከሥላሴ አንዱ በመስቀል ላይ ሞተ" መባልን መቀበል ያቃተው ኬልቄዶን ወይስ ይህንኑ አነጋገር ያወጀው ኬልቄዶን?

"ከሁለት ባሕርይ በተዋሕዶ አንድ የእግዚአብሔር ቃል ሥግው ባሕርይ" መባልን የዲዮስቆሮስ አነጋገር ነው ብሎ ከእምነት መግለጫው ላይ አውጥቶ ያስቀየረው ኬልቄዶን? ወይስ ይህንኑ አነጋገር "ባሕርዮቹ ተቀላቅለዋል ብሎ እስካልተረዳው ድረስ ትክክል ነው" ያለው ኬልቄዶን?

"አንድ ሃይፖስታሲስ በሁለት ባሕርይ" ብሎ ቢያውጅም እንዴት ያለ ሃይፖስታሲስ ባሕርይ ይኖራል ለሚለው መልስ በማጣቱ ንስጥሮሳውያኑ አንጾኪያውናይ የተሟገቱለት ኬልቄዶን? ወይስ "የሰውነት ባሕርይ በመለኮት ሃይፖስታሲስ ውስጥ ህልው ሆነ" በማለት አዲስ አነጋገር ያመጣው ኬልቄዶን?

በአጭሩ የ451ዱን ኬልቄዶን? ወይስ በ553ቱ የቁስጥንጥንያ ጉባኤ የታረመውን ኬልቄዶን? የቱን ነው የምትቀበሉት በሏቸው በመካከላቸው ከመቶ ዓመታት በላይ አለና።
❤ 61 🔥 4 🤝 4 💯 2 🥴 1
27 March 2026
ኪ
11:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንዴት አላመናችሁኝም ብሎ እግዚአብሔር ሰውን ወደ ሲኦል ይከታል?

እንዲህ የሚል ጥያቄ ደርሶኝ ነበር ፣ ይህ የሲኦልን ባሕርይ አለመረዳት ነው። ከሞት በኋላ ሲኦል ቅጣት ነው ብለን ብንናገርም ቅጣቱ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር እየፈለኝ እግዚአብሔር አላመናችሁኝም ስለዚህ ከእኔ ጋር አትኖሩም ብሎ እየቀጣን አይደለም።

ከላይ የለጠፍኩት አባ ቪሲ ሳሙኤል የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያዘጋጁት ካቴኪዝም ነው። ሰማይ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ነው ፣ ሲኦል ማለት ደግሞ ከእግዚአብብሔር መለየት ነው ፣ ሰው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረው በእምነት ነው ስለዚህም እግዚአብሔርን ያመነ ሰው በምድር እየኖረ ራሱ በሰማይ ነው ያለው ፣ ሰማያዊት መንግሥት ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ነው እንጂ ሌላ አይደለምና። እንዲሁም ሲኦል ማለት ደግሞ ከእግዚአብሔር መለየት ነው ፣ ስለዚህም ከእግዚአብሔር የተለየ ሰው በራሱ ላይ ሲኦል መኖርን ያመጣል (ምንም እንኳን ቅጣቱ ከእግዚአብሔር ቢሆንም) ይህም ማለት እግዚአብሔር አላመናችሁኝም ብሎ ዘለዓለም እየቀጣን ሳይሆን እኛ ዘለዓለም ስለማንፈልገው ለፍላጎታችን አሳልፎ እየሰጠን ነው በዚህ ነው የእግዚአብሔር ቅጣት።
❤ 78
ኪ
12:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
መ
መልህቅ 27.03.2026 12:05:03
…

ተወያዮቹን ነገ የማሳውቃቹ ይሆናል! እስከዛ ብዙዎቸ ጋር እንዲደርስ ሼር አድርጉ!

@zanchor
❤ 18
ኪ
12:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
እነማን ይሆኑ ይሆን ተወያዮቹ 😁
😁 30
28 March 2026
ኪ
10:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሙስሊም ጳጳስ ኢትዮጵያ ላይ ስለመጣ ቅብብሎሹ ተቋርጧል?

እኛ attack ተደርገናልና መልሰን ባገኘነው ነገር ሁሉ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን attack እናድርግ ለሚባል ቲክቶክ ፖለቲካ ካልሆነ በስተቀር እኛ የምናውቀውን ታሪክ እንደ አዲስ መገለጥ ማንሳታቸው ምን ያህል desperate እንደሆኑ ነው የሚያሳየው ቤተክርስቲያናችንን attack ለማድረግ።

በመጀመሪያ metropolitan እና Patriarch አለዩም ፤ "በማርቆስ መንበር ላይ ሙስሊም ተቀምጧል" ብለው ሲጮሁ ነበር ፤ ነገር ግን አልተቀመጠም የማርቆስ መንበር ላይ የሚቀመጠው የእስክድርያው ሊቀ ጳጳስ እና የመላዋ አፍሪካ ፓትሪያሪክ ነው እንጂ የኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ (metropolitan) አይደለም።

ሁለተኛ ይህ ሙስሊም የእስክንድርያ የተሾምኩ ነው ብሎ በማታለል መጣ እንጂ በእስክድርያ የተሾመ አልነበረም። ነገር ግን even በእስክድርያ የተሾመ ነው ብንል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የቀጠለው በእስክድርያው ጳጳስ በኩል እንጂ ወደ ኢትዮጵያ በሚላኩት ጳጳሳት በኩል መሆኑን አላወቁም ወይስ ሆን ብሎ ቤተክርስቲያኒቱን ለመምታት ብቻ ነው? ምክንያቱም ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩት ጳጳሳት መጥተው ጳጳሳት አልሾሙም የሚሾሙት ቀሳውስት እና ዲያቆናትን ብቻ ነው ፤ እኛ እንደምናምነው ደግሞ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የሚተላለፈው በጳጳሳት በኩል እንጂ በቀሳውስት በኩል አይደለም ስለዚህ ይህ ጳጳስ ነኝ ያለ ሙስሊም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ቀሳውስትን ቢሾም እንኳን እሱ የሾማቸው ቀሳውት ይሞታሉ በኋላ ላይ ከእስክድርያ የተሾመ ጳጳስ ነው መጥቶ ሌሎችን ጳጳሳት የሚሾመው ይህ ማለት ቅብብሎሹ የሚቀጥለው በእስክድርያ ሊቃነ ጳጳሳት በኩል ነው ማለት ነው። ይህም የሆነው ኢትዮጵያ ራሷን የቻለች ሲኖዶስ በ1959 እስክታቋቁም ድረስ ስለሆነ እስከዚያ ዓመት ድረስ ቅብብሎሿ የቀጠለው በእስክድርያ በኩል ነው።

ይህ የሚያሳየን እስከ 1959 ድረስ የኢትዮጵያን ቅብብሎሽ ትክክል አይደለም ለማለት የእስክድርያን ቤተክርስቲያን ትክክል አይደለም ማለት ያስፈልጋል እንጂ ኢትዮጵያ የሚመጡት ጳጳሳት ምንም አይነት ቅብብሎሽ አላስተላለፉም።

ብቻ አሁንም የምላችሁ ከተራ የቲክቶክ ሃይማኖታዊ ብሽሽቅ ራቁ።
❤ 87 👍 12 💯 8 🔥 6 🙏 2 ❤‍🔥 1
ኪ
16:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ ኑና እኛም በቲክቶክ እንቀጣቀጥ lol 😁

Jk Jk ጨዋ ውይይት ነው የሚሆነው
❤ 64 🔥 16 👏 1
29 March 2026
ኪ
20:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
🔥 18
ኪ
23:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 1
30 March 2026
ኪ
08:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰዎች እንዴት አደራችሁ?

የትናንቱ ውይይት እንዴት ነበር? እንዴት አያችሁት? ምንስ ይስተካከል?
❤ 45 👍 3
1 April 2026
ኪ
09:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ዛሬ ማታ 3 ሰአት ላይ ድኅነት ፣ነጻ ፈቃድ እና ምርጫ ላይ በእኛ ቤት እንሔድበታለን

የኦርቶዶክስ አስተምህሮ ምን ይመስላል ፤ የሉተራኖች እርስ በእርስ የሚጋጭ አስተምህሮስ እንዴት ነው የሚለውን እናያለን።

ተገኙ
👍 61 ❤ 27 ⚡ 2
ኪ
18:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 84 🥰 8
ኪ
21:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 3
2 April 2026
ኪ
11:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጸሎተ ሐሙስን ቅዳሴ በዛሬው ቀን እያከበረች ነው ፤ የአርመን ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንም ምታከብረው እንዲሁ በዛሬው ቀን ነው።

ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ የጌታን ሞቱን ታስበዋለች።
❤ 139 🔥 15 ❤‍🔥 3 👍 1
11:14
3 April 2026
ኪ
08:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ የአርባው ጾም መጨረሻ ነው ክርስቶስ የጾማቸውን 40 ቀናት ፈጸምን እግዚአብሔር ይመስገን!

ጌታ ኢየሱስ ከሁላችን ጋር ይሁንና ከነገ ጀምሮ እስከ ስቅለቱ የሚመሩትን ሁነቶችን ቀን በቀን እንከታተላለን።

በቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዛሬዋ ቀን የአርባውን ጾም ፍጻሜ በማስመልከት ለሁሉም በኅብረት ምሥጢረ ቀንዲል ከቅዳሴ በፊት ይፈጸማል ፤ ምሥጢረ ቀንዲል ለሕሙማን ብቻ የሚፈጸም ምሥጢር ቢሆንም በሕማማት ሳምንት ውስጥ የታመመ ሰው ቢኖር ምስጢራት መፈጸም ስለማይቻል ለሁሉም በኅብረት በዛሬዋ ቀን ምሥጢረ ቀንዲል ይፈጸማል ፤ ሕሙማን ይፈወሳሉ ፣ ለኃጢአትም ሥርየት ይሆናል።

የጌታን ሕማማት ለማሰብ ያብቃን።
❤ 164 👍 7
4 April 2026
ኪ
08:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ መስቀሉ ጉዞ - ቀን 1

የአልዓዛር ቅዳሜ


ጌታ የሚወደው የቢታንያው ወዳጅ አልዓዛር ታመመ፤ እኅቶቹ ማርታና ማርያም ወደ ኢየሱስ "የምትወደው ወዳጅህ ታሟል" ብለው ቢልኩበትም ኢየሱስ ግን የመሰቀያው ጊዜ መድረሱን አውቋልና ኾን ብሎ ዘገየ፤ አልዓዛርም ሞተ።
የክርስቶስ መሰቀያ ጊዜ እና የአልዓዛር ሞት ምን አገናኘው? የተገናኘው የካህናት አለቆች ጌታን ይገድሉት ዘንድ የተማከሩት አልዓዛርን በማስነሣቱ ምክንያት ነውና ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ "ሕዝቡ ኹሉ ከሚጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት ይሻለናል" ብሎ የተናገረው አልዓዛርን ካስነሣው በኋላ ሕዝቡ ኹሉ ስለተከተለው ነው። (ዮሐ 11፡50) በነጋታው ሕዝቡ ኹሉ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያለ የተከተለውም ትልቁ ምክንያት አልዓዛርን በማስነሣቱ ነው።

አልዓዛርን ማስነሣት ለምን እንዲህ ትልቅ ነገር ኾነ? ጌታ ከእርሱ በፊት እኮ 2 ሰዎችን አስነሥቷል፤ ምነው የአልዓዛር ተጋነነ? ከዚህ በፊት ጌታ ያስነሳቸው ሰዎች በሞቱበት ቀን ነው። አይሁድ ደግሞ በአስተምህሮዋቸው አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ትለይና ምናልባት የመመለስ እድል ካገኘው ብላ ከሥጋዋ አከባቢ ለ3 ቀናት ታንዣብባለች፤ ለ3 ቀን ካልተመለሰች ተስፋ ትቆርጥና ወደ ማደሪያዋ ትገባለች ስለዚህ በ3ኛው ቀን ሰው ላይነሣ ፈጽሞ ሞተ ይባላል።

ጌታም አልዓዛር ሞተ ብለው እኅቶቹ ሲልኩበት የዘገየበት ምክንያት የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ "ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝም ቢሞት እንኳን ይነሣል" በማለቱ የሰው ልጅ ፈጽሞ ከሞተ በኋላ እንኳን የሚያስነሣ እርሱ መኾኑ ለሕዝቡ ኹሉ ይገለጥ ዘንድ ነው። (ዮሐ 11፡25) ስለዚህም ጌታ ወደ ቢታንያ ሲደርስ አልዓዛር ከሞተ 4 ቀን ኾኖት ነበር፤ አይሁድም ፈጽሞ መሞቱን ስላመኑ ከዚህ በኋላ ይነሣል የሚል ተስፋ እንኳን አልነበራቸውም። እንኳን አይሁድ በኢየሱስ ያመኑ እኅቶቹ ማርታ እና ማርያም እንኳን ጌታ መቃብሩን ክፈቱልኝ ባለ ጊዜ "አራት ቀን ኾኖታል ይሸታል" ብለው ታቀወሙ ፤ ትንሣኤ እና ሕይወት ክርስቶስ ግን "አልዓዛር ፣ አልዓዛር ና ውጣ" በሚል ቃል ብቻ ፈጽሞ የሞተውን አልዓዛር ከመቃብር ከነመግነዙ አወጣው ፤ ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ መኾኑ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ሆሳዕና (አዳኝ) እርሱ መኾኑም በዛ ላለ ሕዝብ ኹሉ ተገለጠ።

የአልዓዛር ከሙታን መነሣት በቢታንያ እና በኢየሩሳሌም ምድር ኹሉ ተሰማ ሕዝቡ ኹሉም የተነሣውን አልዓዛርን ያዩ ዘንድ ወደ ቢታንያ ተሰበሰቡ ያስነሣውን ሆሳዕና (አዳኝ) ያዩ ዘንድም ናፈቁ፤ ኢየሱስ ግን ወደ ኤፍራታ ከተማ ትቶአቸው ሄዶ ነበር (ዮሐ 11፡54)። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ አይደለም ለአንድ ቀን ብቻ ነው እንጂ፤ በነጋታው ይመጣል! ሕዝቡ ኹሉም የናፈቁትን ሆሳዕና (አዳኝ) በዘንባባ ይቀበሉታል!

@KidanZeIyesus
❤ 100
ኪ
15:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=MPA4RPz1dGk

ይህን መዝሙር ተጋበዙልኝ ኢንጊሊዘኛው subtitle ላይ አለ አማርኛው እንዲህ ይላል፡

"በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ዳግመኛም በጌታ ስም።
ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፤ ዳግመኛም ለዳዊት ልጅ።
ሆሣዕና በአርያም፤ ዳግመኛም በአርያም።
ሆሣዕና ለእስራኤል ንጉሥ፤ ዳግመኛም ለእስራኤል ንጉሥ።
እንዲህ እያልን እንዘምር፡ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሉያ።
ክብር ለአምላካችን ይሁን፤ ዳግመኛም ክብር ለአምላካችን ይሁን።
ሆሣዕና በአርያም፣ ይህ የእስራኤል ንጉሥ ነው፣ በሠራዊት ጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው።"
❤ 28 👍 6 🥰 1
ኪ
19:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰላም ተወዳጆች
በ4 ኛው ክፍለ ዘመን [ከ1600 ዓመት በፊት] በኢየሩሳሌም ሰሙነ ሕማማት እንዴት እንደሚከበር ታውቃላችሁ?

ኢጌሪያ የተባለች አንዲት ሴት ወደ ወደኢየሩሳሌም ሄዳ እንዴት እንዳከበረች በማስታወሻዋ የዘገበችልንን እንዲህ ቀርቧል ተጋበዙልን🙏

https://youtu.be/kExtN1K5vHw?si=9uAFidB-qeDBytTc
🥰 27 🙏 5 ❤ 3 👏 3
19:40
In reply to this message
ወንድማችን ጆ ጥሩ አድርጎ አቅርቦታል
5 April 2026
ኪ
07:59
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ መስቀሉ ጉዞ- ቀን 2

የሆሳዕና እሑድ

ቀኑ ከፋሲካ 6 ቀናት ቀደም ብሎ ነው ብዙህ ተጓዦች ፋሲካን በኢየሩሳሌም ለማክበር ከገሊላ ይወርዳሉ ፤ ኢየሩሳሌምም በሕዝብ ትጥለቀለቃለች። ጊዜው ለአይሁድ የደስታ ቢሆንም ለሮም ግን የስጋት ነው። የፋሲካ በዓል እስራኤላውያን ከግብጽ የወጡበት በዓል ስለሆነ ከፍተኛ የሐገር መውደድ ስሜት የሚሰማበት ጊዜ ነው ፤ በዚህ በ1ደኛው ክፍለ ዘመን የያዛቸው ጠላት ግብጻውያን ሳይሆኑ ሮማውያን ናቸው ስለዚህም በፋሲካ ወቅት ከሮም ነጻ የሚያወጣቸውን መሢሕ የመጠበቅ ስሜት ከፍ ይልባቸዋል። ሮማውያንም ይህን ስለሚያውቁ በተጠንቀቅ ኢየሩሳሌምን ይጠብቃሉ።

የደብረ ዘይት ተራራ ሲደርሱ ግን አንድ ያልጠበቁትን ድምጽ ሰሙ አንድ ገሊላዊ በአህያይቱ ውርጭላ ላይ ተቀምጧል ፣ ገሊላውያኑ ልብሳቸውን ያነጥፉለታል ፣ ከፊት ያሉት ሕዝብ የዘንባባ ዝንጣፊውን ይዘዋል "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" "ሆሳዕና በአርያም" እያሉ ይጮሃሉ። የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተሸበረ "ይህ ማነው?" እያሉ ይጠይቃሉ ፤ መሢሑ ይሆንን? በሮም እጅ ነጻ የሚያወጣን ይሆንን? የእስራኤል ንጉሥ ይሆንን? ይህ የክብር ንጉሥ ማነው?

አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት- መክኗንንት ሆይ ደኞችን ክፈቱ
ኢየሩሳሌም ሆይ ንጉሥስሽ ደርሷል ፤ ሰላምሽም ቀርቧል ጽዮን ሆይ ዘምሪ የያሕዌ ማዳን መጥቶልሻል! ደጆችሽን ክፈቺ የክብርም ንጉሥ ይግባ ፤ አህያ ላይ የተጫነው ንጉሥሽ ይግባ። መኳንንት ሆይ ደጆችን ክፈቱ የሰላም ንጉሥ ሰላሙን ያጸናልን ዘንድ መጥቷል ፣ ዘካርያስ የተነበየለት ንጉሥ እነሆ በውጭንላይቱ ላይ መጥቷል ፤ ያድን ዘንድ በሠራዊት ጌታ ስም መጥቷል ሆሳዕና እነሆ አሁን ያድናል!

መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት- ይህ የክብር ንጉሥ ማነው?
ኢየሩሳሌም ሆይ ስሚ ጽዮን ሆይ አድምጪ ይህ ንጉሥ ዙፋኑ በመስቀል ነው፣ መንግሥቱ ሰማያዊ ነው ፤ ድኅነቱ ከኃጢአት እና ከሲኦል ነው። ሆሳዕና እነሆ አሁን ያድናል ከሮማውያን ሳይሆን ከኃጢአት ያድናል! ይህ ንጉሥስ ማነው ያልሽ እንደሆነ እርሱ የዳዊት ልጅ ነው በሠራዊት ጌታ ስም የሚመጣ መሢሕ ነው ዓለምን በፍቅር የሚገዛ ኃያል ነው። በሥጋ የተገለጠ ኃያሉ እግዚአብሔር ነው! የያሕዌ ማዳን የተባለ ኢየሱስ ነው! ሆሳዕና እነሆም አሁን ያድናል!

ይባዕ ንጉሠ ስብሐት ፣ ይባዕ አምላከ ምሕረት!
የክብር ንጉሥ ይግባ ፣ የምሕረት አምላክ ይግባ!


@KidanZeIyesus
❤ 91 🔥 9
6 April 2026
ኪ
08:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ መስቀሉ ጉዞ- ቀን 3

የመርገመ በለስ ሰኞ

ለእርሱ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኛን ማሳኒ ሥጋ በመያዙ ተራበ ፤ ረሃቡንም ያስታግስ ዘንድ ወደ አንዲት በለስ ዛፍ ተመለከተ ነገር ግን በለሲቷ ጊዜዋ አልነበረምና በቅጠል በስተቀር ፍሬ አልተገኘባትም ጌታም ከእንግዲህ ፍሬ አይገኝብሽ በማለት ረገማት በለሲቷም ደረቀች።

ጌታ ጊዜው በለስ የማያፈራበት መሆኑን አያውቅምን? ያውቃል! ነገር ግን ፍሬ እንደማይገኝባት እያወቀም ፍሬን ፍለጋ ይመጣል ፤ ወደ አይሁድ ስንት ጊዜ መጣ? ፍሬ እንደማይገኝባቸው እያወቀ ነገር ግን በመጣ ቁጥር ፍሬ አላገኘባቸውም ስለዚህም ክርስቶስ እንዲህ ሲል ተናገራቸው "ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።" (ማቴ 23፡37) ኢየሩሳሌምም እንደ በለሲቷ ደረቀች ቤቷም የተፈታ ሆነ ፤ ሮማውያን አጠፏት ስሟንም ከምድረ ገጽ ደምስሰው "Aelia Capitolina" አሏት ፤ የጌታ ትንቢት ተፈጸመባት። ይህ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ነው የጌታ ምርጥ ሕዝብ የተባለች እስራኤል እንኳን ፍሬ በማጣቷ ከጠፋሽ ከጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድም ከተፋቀች እኛስ ፍሬ የማይገኝብን በለስ ሆነን ከተገኘን ከጌታ ዘንድ እንፋቃለን "በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" ብላ ኢየሩሳሌም ተቀብላው ነበር ፤ እኛም እንዲሁ ተቀብለነዋል ያለ ፍሬ ከሆንን ግን እርሱ በጌታ ስም ሲመጣ እንጠፋለን።

የኢየሱስ በለሲቷ ፍሬ ይኑርባት ፣ አይኑርባት አለማውቁ ብዙ ትርጉም አለው እንዲሁም በለሲቷ ነገር ግን አንድ ነገርን እናውቃለን በዚሁ በለሲቷን በረገመበት ቀን ቤተ መቅደሱን ማንጻቱም ይታሰባል ፤ ሁለቱን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ ሁለቱም ፍሬ አልተገኘባቸውም! ስለዚህ በለሲቷም ደረቀች ቤተመቅደሱም ፈረሰ። የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሰው ሆይ ሳትፈርስ በፊት ጌታ ውስጥህን ያነጻልህ ዘንድ ልብህን ክፈትለት ፤ የአባታችንን ቤት ሰውነትህን የወንበዴዎች መናኸሪያ አታድርገው።

እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሓነ ለትንሣኤሁ በፍሥሐ ወበሰላም!

@KidanZeIyesus
❤ 110 🙏 1
7 April 2026
ኪ
08:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ መስቀሉ ጉዞ-ቀን 4

የመንግሥቱ ምሳሌዎች እና የሚመጣው ሙሽራ

ጌታ ኢየሱስ በረገማት የበለስ ዛፍ በኩል ሲያልፍ ጴጥሮስ "እነሆ የበለሲቷ ደረቀች" አለው ጌታም "በእግዚአብሔር እመን አለው"። ጌታ ኢየሱስም ወደ ቤተመቅደስ ገብቶ ትምህርትን አስተማረ "ምንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገን ንጉሥን ትመስላለች" በማለት ስለ መንግሥቱ በሰርግ ምሳሌነት አስተማረ። ወዲያውም ፈሪሳውያን "ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባልን?" በማለት ጥያቄን አመጡበት ጌታ ግን "የቄሳርን ለቄሳር ስጡ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር" በማለት መለሰ እኛ ባለቤታችን ለልጁ ሠርኝ ያዘጋጀው ጌታ ነውና። እንዲሁም ትንሣኤ ሙታንን የማያምኑ ሰዱቃውያን ጥያቄን ይዘውበት ሲመጡ በመንግሥቱ ሠርግ "እንደ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡም" በማለት ሰማያዊቷ ሰርግ መንፈሳዊት መሆኗን እንጂ ስጋዊ አለመሆኗን አስተማረን።

ጌታ አሁንም ስለ መንግሥቱ በሌላ ምሳሌ አስተማረ "የወይን አትክልት የተከለ ሰው ነበረ ባሮቹን ገበሬዎቹ ገደሉት ልጁንም ያፍሩታል ብሎ ቢልክባቸው ወራሹ ነው በማለት ገደሉት በመጨራሻም እኒህን ገበሬዎች ያጠፋቸዋል መንግሥተ ሰማያትን በመግባትም ከገበሬዎቹ (ጻፎች እና ፈሪሳውያን) ይልቅ ዘማዎች እና ቀራጮች ይቀድማሉ" መንግሥተ ሰማያት መግቢያው የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ነውና እርሱ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ነው ፣ ለማያምኑ ግን የማሰናከያ ዓለት ነው።

ጌታ ኢየሱስ እንዲህ እያለ ብዙህ ትምህርት ካስተማረ እና ጥያቄዎችን ከተቀበለ በኋላ ከመቅደስ ወጣ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግን ሊያሳዩት ቀረቡ ፤ ጌታ ኢየሱስ ግን "ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ አይቀርም" በማለት የቤተ መቅደሱን መፍረስ እንዲሁም ፣ የሰውን ልጅ መምጣት ምልክቶች ነገራቸው። በትምህርት ብቻ አይደለም በምሳሌም "5 ብልህ ደናግሎች እና 5 ሰነፍ ደናግሎች የሙሽራውን መምጣት ሲጠባበቁ ዘይት አለመያዛቸው ሰነፎቹን ከጌታ ሰርግ አወጣቸው፤ ስለዚህም መሽራው መቼ እንደሚመጣ አታውቁምና ዘይታችሁን ሁል ጊዜ አዘጋጁ" ሲል አስተማራቸው።

አቤቱ ለልጅህ ሰርግ ያዘጋጀው አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ፣ ከሰማያዊው ሰርግ አትጣለን እኛ ኃጢአተኞች እና ዘማዎች ነንና በመንግሥትህ ተቀበልን ልጅህን የምንጠብቅበት ዘይት ባይኖረንም መሢሕህን በቀባኸው ዘይት የእኛንም መብራቶች በዘይት ምላ ፤ እኛ መራሳችን ምንም ማድረግ አይቻለንምና በልጅህ ዳግመኛ የፈጠርከን ፣ በመንፈስህም ያተምከን አምላክ ሆይ ፤ ሥራችን ልጅህ ነው ፣ መብራታችንም መንፈስህ ነው። ጌታ ሆይ ባልተዘጋጀንበት ጊዜ መጥቶ ልጅህ ባዶአችንን አያግኘን ፤ የምናቀርበው ባይኖረንም ራሱ ልጅህን እናቀርብልሃለን ፣ በእርሱ ኃጢአታችንን ይቅር በለን ከሰማያዊው ሰርግም አታስወጣን።

@KidanZeIyesus
❤ 103 🔥 2 👍 1
8 April 2026
ኪ
10:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ መስቀሉ ጉዞ ቀን 5

የሁለቱ ደቀ መዛሙርት ወግ

ሁለት ደቀ መዛሙርት ነበሩ አንደኛው ከአስራ ሁለቱ ነው ፣ አንደኛዋ ከአንስት ደቀ መዛሙርት ናት። አንደኛው ለጌታ ቅርብ ነው ፣ አንደኛዋ በሩቁ ከእርሱ ምትማር ናት። አንደኛው ጌታውን አሳልፎ የሰጠ ነው ፣ አንደኛዋ ግን ለመቃብሩ ሽቱን ያፈሰሰችበት ናት ፤ የአስቆሮጡ ይሁዳ እና የቢታንያዋ ማርያም።

አይሁድ ጌታን ይገሉት ዘንድ ተስማምተው ነበር ነገር ግን ወቅቱ የፋሲካ በዓል ስለ ነበር በሕዝብ መሃል ሊይዙት አይችሉም ስለዚህ ከሕዝብ ርቆ ብቻውን የሚያገኙበትን ምቹ ሰአት ይጠብቁ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ይሁዳ የመጣላቸው ሕዝብ በማይኖርበት ምቹ ሰአት ጌታን አሳልፎ ሊሰጣቸው ተስማማ እነርሱም በ30 ብር ከእርሱ ጋር ተዋዋሉ። ዓለምን ሁሉ የፈጠረ ጌታ በርካሽ ዋጋ በሠላሳ ብር ተሸጦ እኛን በውድ ዋጋ በደሙ ገዛን! ስለዚህ ይህቺን ረቡዕ ቀን በማሰብ እንጾማት ዘንድ ሐዋርያት በዲዳኬ በኩል አዘውናል።

ወደ ሌላኛዋ ደቀ መዝሙር ወደ ቢታንያዋ ማርያም እንሒድ ፤ እርሷስ ከጌታ ስር ቁጭ ብላ ትማር ስለነበር ራሱ ጌታ "ማርያምስ የማይቀሟትን በጎ እድል መረጠች" ሲል አመስግኗታል። ጌታንም ትወደው ስለነበር ወንድሟ አልዓዛር በሞተ ጊዜ ጌታ ሲመጣ ፤ ማርታ "መምህር መጥቷል" ብላ ስትነግራት ሮጣ ወጥታ እግሩ ስር ወድቃ አለቀሰች ፤ ጌታ ኢየሱስም በማርያም ልቡ ተነክቶ "እምባውን አፈሰሰ"። የማርያምን ፍቅሯን ተመልከቱ በዚህ ብቻ አላበቃችም የዓመት ገቢ ሊሆን የሚችል ውድ የናርዶስ ሽቱ ወስዳ የጌታ ራስ ላይ አፈሰሰች በጸጉሯም እግሩን አበሰች፤ ጌታም "ይህን ስለ መቃብሬ አደረገች ወንጌል የሚነገርበት ቦታ ሁሉ ሥራዋ ይነገርላታል" በማለት አመሰገናት። ለእራኤላዊት ሴት ጸጉሯን መልቀቅ ውርደት ነበር ፤ ማርያም ግን የተመለከተችው ጌታዋ እግር ስር መውደቋን ብቻ ነበር። እግሩ ስር ቁጭ ብላ ትማር እንደ ነበር አሁን ግን እግሩ ስር ወድቃ በጸጉሯ አበሰችው ፤ ይህስ ምን አይነት ፍቅር ነው? ሐዋርያ የተባለው ሲከዳው ፤ ማርያም ግን ወደደችው!

Historical critical note: አራቱም ወንጌላት ባለ ሽቱ ሴቶች ሲኖሯቸው ታሪካቸው ግን ትንሽ ይለያያል። ከሁሉም የሚለየው የሉቃስ 7 ባለሽቱ ናት። ይህቺ ባለ ሸቱ ስሟ ባይጠቀስም "ኃጢአተኛዋ ሴት" ተብላ ተጠቅሳለች። ታሪኩም የተፈጸመው በቢታንያ ሳይሆን በገሊላ ሲሆን በፈሪሳዊው ስምኦን ቤት ነው። ጌዜውም የጌታ ትምህርቱ መሃል አከባቢ ነው እንጂ ወደ ፍጻሜው አይደለም። ሴቲቱም እዚህ ታሪክ ላይ ሽቱን የቀባችው ለኃጢአቷ ሥርየት ነው እግሩን ያበሰችውም እያለቀሰች ስትማጸን ነው። ጌታም መልሱ "ብዙህ ስለወደደች ብዙህ ተሠርዮላታል" በማለት ነው እንጂ "ለመቃብሬ አደረገች" አይደለም ስለዚህ የሉቃስ ወንጌሏ ባለሽቱ ከቢታንያዋ ማርያም ሌላ ሴት መሆኗን መናገር እንችላለን ፤ የቢታንያዋ ማርያም "ኃጢአተኛዋ ሴት" አልተባለችው ይልቅስ በጌታ ትምህርት ደስ የሚላት ትጉህ ደቀ መዝሙር ናት እንጂ። አንዳንዶች ደግሞ ይህቺኛዋን ኃጢአተኛ ሴት መግደላዊት ማርያም ያደርጓታል ነገር ይህም ስህተት ነው ስሟ አልተጠቀሰልንም።

ሌሎቹ ወንጌላት ማቴዎስ 26 እና ማርቆስ 14 ላይ ባለሽቱ ሴት መጥታ ክርስቶስ ራስ ላይ ሽቱ እንዳፈሰሰች ሲናገሩ ቦታውን ቢታንያ ያደርጉታል ፣ ቤቱንም ለምጻሙ ስምኦን ቤት ፣ ጊዜውን ደግሞ ከፋሲካ 2 ቀን በፊት። ጌታም ለመቃብሬ አደረገች ብሎ ይመልስላታል። ስለዚህ ይህኛው ታሪክ ከቢታንያዋ ማርያም ጋር አንድ መሆኑን መናገር እንችላለን።

ስሟን ጠርቶልን ያስቀመጠልን ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል 12 ላይ ነው። ዮሐንስ ለምጻሙ ስምኦንን ባይጠቅስም በቢታንያ አልዓዛር ዘንድ ይጠቅሳል ስለዚህ አንድ አይነት ቦታ መሆኑን እንረዳለን። ከማቴዎስ እና ከማርቆስ ወንጌል ልዩ የሚያደርገው ጊዜው ብቻ ነው ከፋሲካ 6 ቀናት በፊት (ከሆሳዕና ዋዜማ) ያደርገዋል። በዚህ ምክንያት አንድ አንዶች የዮሐንስ ባለሽቱና የማቴዎስ (እንዲሁም የማርቆስ) የተለዩ ናቸው ይላሉ፤ ነገር ከታሪኩ ተመሳሳይነት የተነሳ ይህ የማይሆን ነው። ይልቅስ ምክንያታዊ የሆነው ማብራርያ ወንጌላት ሁል ጊዜ ታሪኮች በተፈጠሩት ኡደት (Chronological order) አይጽፉም ይልቅስ የፈለጉትን መልእክት ለማስተላለፍ ሁለት በተመሳሳይ ቀን ያልተፈጸሙ ሁነቶችን ወደ ተመሳሳይ ቀን ሊያመጡ ይችላሉ (ይህ የወንጌላቱ አጻጻፍ ብቻ ሳይሆን የጥንታዊ ጸሐፊያን ሁሉ አጻጻፍ ነው)። ስለዚህም ብዙ ምሑራን ትክክለኛውን ቀን የዘገበልን ዮሐንስ እንደሆነ ይስማማሉ ፤ ማርቆስ እና ማቴዎስ ደግሞ የሁለቱን ደቀ መዛሙርት ልዩነት ያሳዩን ዘንድ ታሪኩን ይሁዳ ወደ ከዳበት ቀን አመጡት።

ከዚህ የተነሳ ይህን conclude ማድረግ እንችላለን ሁለት ባለሽቱዎች አሉ ኃጢአተኛዋ ሴት እና የቢታንያዋ ማርያም። ኃጢአተኛዋ ሴት ለንስሐ ሽቱ ጌታ ላይ አፈሰሰች ፣ ማርያም ግን ለመቃብሩ አፈሰሰችበት ፣ ታሪኩን አንቀላቅል።

@KidanZeIyesus
❤ 73 🔥 2
9 April 2026
ኪ
14:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወደ መስቀሉ ጉዞ ቀን 6 የኪዳኗ ሐሙስ

አሮጌው ኪዳን አለፈ ጌታ ኢየሱስ ከብሉዩ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ኾነ ፤ 'ስለ እናንተና ስለብዙሆች የሚፈሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው' በማለት በደሙ ሐዲሱን ኪዳን መሠረተ።

የብሉዩም ቢኾን ያለ ደም አልጸናም ኑዛዜ የሚጸናው በሞት ነው። የብሉዩ ኑዛዜ የጸናው በእንስሳ ደም ነውና ጊዜያዊ ነበር በሐዲሱ ኑዛዜ ግን ራሱ ኪዳን ገቢው ጌታ ደሙን ስላፈሰሰ የዘለዓለም ኪዳን ነው! በዘለዓለም ኪዳን በቅዱስ ደም ተገዝተናል የሞት ዋጋ አለብን!

አቤቱ ዘለዓለማዊውን ኪዳን በዚህች ዕለት የገባኸው ሆይ በደምህ ዋጋ ገዝተኸናል እኛም ያንተ ኾነናል ፤ ያን ጊዜ እንደቆረስህ ዛሬም የቆረስኸው ሆይ ሥጋህን ተቀብለናል ፤ ያን ጊዜ እንደቀደስህ ዛሬም የቀደስኸው ሆይ ደምህንም ጠጥተናል በጸጋህ ኃይል በኪዳንህ አጽናን በዘለዓለም ፍቅር ሰንሰለትም ወደ አንተ ሳበን። ቅዱሰ ቅዱሳን ሆይ ቀድሰን!

የዘለዓለም ኪዳን ❤️

@KidanZeIyesus
❤ 98
10 April 2026
ኪ
16:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዕለተ ስቅለት ዕለተ መድኃኒት።

"ክርስቶስ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ሊያድን ወደ ዓለም መጣ" የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የሚገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ! (፩ኛ ጢሞቴዎስ ፩፡፲፭)

ጌታዬ ሆይ፤ እኔ ኃጢአተኛው ቆሜአለሁ፤ አንተ ግን ተሰቅለሃል፤ የኔን ቦታ ወሰድህ፤ ያንተንም ሰጠኸኝ።
❤ 114 🙏 7
11 April 2026
ኪ
11:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
ትንሣኤን በመጠባበቅ ላይ

የብርሃኗ ቅዳሜ (የባለ ራእዩ ቅዳሜ)

ቤተክርስቲያን በዚህ ዕለት ክርስቶስን ቀብራ አትተኛም፤ ይልቅስ ሌሊቱን ሙሉ የአቡቀለምሲስ (Apocalypse) ምሽት አለ እንጂ። ከብሉይ ኪዳን ብዙ የነቢያት ምስጋናዎችና ጸሎቶች ይነበባሉ፣ የሠለስቱ ደቂቅ መዝሙር ይነበባል ይዘመራልም። ከዚያም ሰባት መብራቶች በርተው የዮሐንስ ራእይ ሙሉ ይነበባል በመጨረሻም በቅዳሴ ይፈጸማል።

ይህ ቀን ጌታችን በመቃብር ያደረበት ቀን ነው፣ ይህ ቀን ሲኦል የተበዘበዘበት ቀን ነው።

ጌታ በኃይሉ ሲኦልን በዘበዘ ጻድቃንን አወጣ ብርሃንንም አወጀ 'ሞቼ ነበርኩ ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ነኝ የሲኦል እና የሞት መክፈቻ አለኝ' ብሎ በባለ ራእዩ በኩል እንደ ተናገረ በሲኦል ላይም ኃይሉን አሳየ ቤተክርስቲያንም ብርሃንን ባወጁ ስታከብረው ታድራለች የትንሣኤው ብርሃን ሊገለጥ ነውና!
❤ 110
12 April 2026
ኪ
03:23
ኪዳን ዘኢየሱስ
ክርስቶስ ተነሥቷል!
በእውነት ተነሥቷል!
❤ 135 ❤‍🔥 3
03:31
In reply to this message
ሞቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር ❤️
❤ 153 🔥 10
ኪ
10:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
Christos Anesti
🔥 47 ❤ 28
10:59
P'Christos Aftonf
❤ 54
11:02
Kiristos Ka'eera
❤ 61
11:13
Al-Masihu Qam
❤ 48
ኪ
11:40
ኪዳን ዘኢየሱስ
ያው የምርቴን የትንሣኤ መዝሙር እንደምወደው ታውቃላችሁ አሁን ደሞ እስቲ አረብኛ ልጋብዛቹ

https://www.youtube.com/watch?v=-n5CcJYIi0w
❤ 56 🔥 2
15 April 2026
ኪ
17:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ ወንድማችን ጆ (መልህቅ) በባለፈው ሉተራኖች ዲቤት ላይ ላነሳሁት critique መልስ ጽፎልኛልና እኔም ትንሽ መልስ ነገር ልጻፍ።

አንደኛ ወንድማችንን ማመሰግነው ዲቤቱ ላይ በሰአት ገደብ ምክንያት ያለኝን syllogism በአግባቡ አላቀረብኩም ነበር እርሱም ለማለት የፈለኩትን Steelman አድርጎ መልስ ስለሰጠ ጥሩ መልስ ያደርገዋል።

ነገር ግን እኔ ያስቀመጥኩት sylogism ላይ hidden premise ብሎ ያስቀመጠው እንዲህ ብሎ ነው " If the Holy Spirit effects (or works) the omission of willful resistance (P) and that work is not persistently rejected"። ይህ ግን ምን ያህልትርጉም የለሽ አረፍተ ነገር መሆኑን የምትረዱት willful resistance ምን ማለት ነው የሚለው ስትተረጉሙት ነው። Willful resistance ማለት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ኃጢአተኛውን ሰው ለማጽደቅ ሲመጣ ከሰውየው የሚወጣ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የሚቃወም ፈቃድ ማለት ነው። Omission of willful resistance ማለት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በሰው ላይ ለመሥራት ሲመጣ ጸጋውን የመቃወም ፈቃድ በሰው ላይ እንዳይኖር መሆን ማለት ነው። ስለዚህም ወንድማችን ያቀረበውን premise ተርጉመን ስናቀርበው እንዲህ ማለት ነው "The Holy Spirit works for people to not resist him unless they resist him- ማለትም መንፈስ ቅዱስ ጸጋውን እንዳይቃወሙ ይሠራል ካልተቃወሙት በስተቀር"።

አያችሁት ይህ አረፍተ ነገር እንዴት ትርጉም የለሽ እንደሆነ ገና ከመጀመሪያውኑ እኮ omission of willful resistance ያስፈለገው የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ እንዳይቃወሙ ነው ፣ ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ እንዳይቃወሙ ይሠራል ካልተቃወሙት በስተቀር ማለት omission of willful resistance የለም ማለት ነው ፣ ወይም ደግሞ omission of willful resistance የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ብቻ ሳይሆን የሰው ሥራም ይሆናል ማለት ነው ይህን ደግሞ Orthodox Lutherans ይቃወሙታል ለምሳሌ እዛሁ ዲቤቱ ላይ የጠቀስኩት ፍራንዝ ፓይፐር "Refrain from willful resistance is beyond the ability of man , it is solely the Work of the Holy Spirit" ይላል። እንዲሁም ታድያ እኮ ወደ ካልቪኒዝም reduce ያደርግብናል ከ Universalis gratia ጋር እንዴት ነው ምናስታርቀው? ብለውም ሲጠይቁት የመለሰው መልስ "The Lutheran Church refuses to answer this question- ሉተራዊት ቤተክርስቲያን ይህንን ጥያቄ መመለስን እምቢ ትላለች" ብሎ ነው የዘጋው።
🔥 32 ❤ 15 👍 6 👏 3 ❤‍🔥 2
18 April 2026
ኪ
11:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
I no longer intend to engage in public apologetics. I deeply appreciate the time you've spent engaging with my content. To everyone who has supported me up to this point: thank you. I cannot thank you enough.
💔 46 🤔 22 ❤ 7 🤷‍♂ 6 😢 5 😐 5 👀 5 👍 2 💊 2 ☃ 1 🎉 1
19 April 2026
ኪ
10:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
አ
አምላከ ብርሀን 19.04.2026 09:11:29
ዳግመኛም በዚህች ቀን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሊብያ ሀገር በእስላማዊ አሸባሪ IS እጅ ምስክርነታቸውን ፈፅመው ፤ ሀይማኖታቸውን ጠብቀውው ፤ የድል አክሊል ተቀዳጁ ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፤ እኛንም በፀሎታቸው ይማረን ።

ሰላም ለክሙ በቃለ ማሕሌት ወእንዚራ
ምስለ ሰማዕታት ዘግብፅ መከራቲክሙ ዘሐብራ
ቅዱሳን ሰማዕታት ዘኦርቶዶክሳዊት ሐራ እፎ ክሕልክሙ ተዓግሶ ፅኑዕ መከራ
እስከ ክሳውዲክሙ በአይሲስ ተመትራ
❤ 166 👍 6 😁 4 🙏 2
23 April 2026
ኪ
13:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/Q7c5ReamkLo?si=vsFpTIw39VvNwkB1

ኧረ look look የኛዋ ቤቲ ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያን አፈመሰችው።
🤣 56 🥰 14 ❤ 12 😁 4
ኪ
18:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
I have set the Channel to Private so new members can't join.

Already yalachu Kes blachu wtu yhun Hulu sew and be and maswetat kebad new.
👎 42 😁 10 🤔 5 🥱 3
ኪ
18:58
ኪዳን ዘኢየሱስ
Beka ye channel'u owner Timeless Truth Honual ke ahun behuala yalutn melkt miyastelalfew esu new.

Thank you for your time 🫡
😭 60 🤔 7 🔥 3 👀 2
24 April 2026
ኪ
13:04
ኪዳን ዘኢየሱስ
[ጆ ነኝ Timeless Truth] ... ያለ ኪዳን ፈቃድ ነው ይኼንን የምለቀው😅

የኔን ሐሳብ አጭር ነገር ብቻ ላስቀምጥ

አንዳንድ ጊዜዎች ያው የሚያጋጥሙን ነገሮች ይኖራሉ ያኔም ወደኋላ መለስ ብለን ነገሮችን ከመሰረታቸው አስተካክለን መመለስ ምናምን ያስፈልገናል ... እናም ኪዳን ነገሮችን አስተካክሎ ለመመለስ እና ለእረፍት ያው ጊዜ [አጭርም ሆነ ረዘም ያለ] ያስፈልገዋል ... ከዛም ግን እሱም የሚወደው ነገር ይህን አገልግሎት ስለሆነም ብዙም ደግሞ አላማ ገና ስላለው እንደዚሁ ተመለሶ ያገለግለናል

እስከዛ ድረስ ግን ቻናሉ ወደ Public ስለተቀየረ እስኪ የምታውቁትን ሰው ሁሉ እያስገባችሁ ሰውም ይጨምር በደንብ ሲመለስም እንዲያገኘው .... እናም ግን ሁላችሁም በጸሎታችሁ ኪዳነ ማርያም ብላችሁ አስቡት

እንደሁኔታው ቻናሉ Active ሆኖ እንዲቆይ ቆየት ያሉትን ጽሑፎቹን እንደማስታወሻ እለቃቸዋለው
Jo_El
❤ 140 👍 10 🔥 3 👏 3 😢 3 🙏 2 🤗 1
1 May 2026
ኪ
10:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኪ
ኪዳን ዘኢየሱስ 24.05.2023 13:38:45
ክርስቶሳዊነት

ክርስቶሳዊነት
ማለት ክርስቶስን መምሰል ነው የዓለም ብርሃን የሆነ እርሱን በሰውናታችን ሁሉ ላይ ተቀብሎ እንደ እንቁ ማብረቅረቅ ነው። ይህን ታላቅ ጸጋ እንዴት መግለጽ ይቻላል ሰው እንዴት አምላኩን ሊመስል ይችላል? የምንችለውስ በኛ አቅም አይደለም በእርሱ በእራሱ ላይ ተደግፈን ነው እንጂ ፣ ይገርማል በክርስቶስ ላይ ተደግፎ ወደ ክርስቶሳዊነት መውጣት። እኛማ ምን አቅም አለን ከምድራዊ አዳም ተወልደን በስጋችን ሟቿች ሆነን ፣ ነፍሳችንም ኃጢአትን የምትናፍቅ በኃጢአት ሞት ውስጥ ተከባ ያለች ናት ፣ መልካሙን ከመስራት ይልቅ ሁል ጊዜ ኃጢአትን እንመኛለን ፣ በኃጢአታችንም ምክንያት የሞት ባሮች ሆነናል። ሕይወታችንም በጨለማ ተከቦ የሌሊት አውሬ እንዳይውጠን ፈርተናል። ነገር ግን በዚ ሁሉ ጨለማ ውስጥ እንደ ንጋት ኮከብ የሚያበራልን ብርሃን አለ እርሱም የጠፉ ልጆቹን ሊፈልግ የመጣ የአማልክት አምላክ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። አሮጌው አዳማዊ ማንነታችንን ደምስሶ አዲስ ክርስቶሳዊ ማንነትን ሰራለን ፣ እኛ እንደ ተፈጠርንበት ማንነት መኖር ሲያቅነት የአማልክት አምላክ የእኛን ማንነት ይዞ መጣ ፣ አከበረው ወደ እርሱ ማንነትም አወጣው። ወደ ጨለማ ሕይወታችን ወርዶ የብርሃንን ነጸብራቅ አሳየን ፣ በብርሃናዊ ማንነቱ ወልዶ የብርሃን ልጆች እንባል ዘንድ አድሎናል። ከአዳም የተወለደ ሁሉ አዳማዊ ነው ከክርስቶስ የተወለደ ሁሉ ደግሞ ክርስቶሳዊ ነው ፣ ይህም የሆነው ባሕርያችንን ባሕርይው አድርጎ ባደሰው ሁሉ ከእርሱ እና ስለእርሱ በሆነው በክርስቶስ ነው። ከክርስቶስ ውጪ ሕይወት የለንም ፣ ከክርስቶስ ውጪ ብርሃን የለንም ፣ ከክርስቶስ ውጪ የምንመካበት ማንነት የለንም ።

ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በክርስቶሳዊ ማንነት ይኖር ዘንድ በተጠመቀ ጊዜ ክርስቶስን የመምሰል ጉዞ ጀምሯል ፣ ዘላለም የማያልቅ ረጅም ጉዞ ፣ የመለኮትን ባሕርይ በጸጋ ገንዘብ እያደረጉ ዘላለም የሚጓዙበት ጉዞ ። በዚህ ሁሉ የሚገርመው ደግሞ የጉዞው መነሻ ከክርስቶስ ጎን በፈለቀ ውሃ ጥምቀት ነው ፣ የጉዞው መንገድም ክርስቶስ ነው ፣ የጉዞው ስንቅም ክርስቶስ እንበላው እና እንጠጣው ዘንድ የሰጠን የክርስቶስ የእራሱ ስጋና ደም ነው ፣ የጉዞው አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓሶች ክርስቶስን የመሰሉ ቅዱሳን ናቸው ፣ የጉዞው መዳረሻም እራሱን ክርስቶስን መምሰል ነው ከዚህ ጉዞ ያልተሰናከለ ምነኛ ብጹእ ነው!

ክርስቶሳዊነት ማለት እሳት ነው ፣ ኃጢአታችንን ከውስጣችን አቃጥሎ የሚጨርስ እሳት ነው ፣ አዳማዊ ማንነታችንን ለብልቦ እሳት ወደ ሆነ ክርስቶዊ ማንነት የሚያቀርበን እሳት ነው ፣ በጥምቀት ክብሪት ውስጣችን ተለኩሶ ዘወትር የስጋውና ደሙ ጋዝ እየተጨመረበት የሚንበለበል ፣ አጋንንትን የሚያቃጥል እሳት ነው። በዚህ እሳት እንኑር ፣ ወደዚህ እሳት እንጠጋ ፣ ከዚህ እሳት እንሙቅ ፣ ዘወትርም የጽድቅን ስራ እየሰራን ይህን እሳት እናቀጣጥለው እንጂ የኃጢአትን ውሃ አንቸልስበት። አሜን የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
Jo_El
❤ 93 🔥 5 👍 3
ኪ
10:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
የኪዳን የመጀመሪያ ፖስት
Jo_El
❤ 47
7 May 2026
ኪ
16:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
Jo_El
❤ 44 ⚡ 5 👍 2 🔥 1
16:53
In reply to this message
ከኪዳን የተላከላችሁ ጽሑፍ ነው

እኔ ቀድሜ አንብቤው ተመችቶኛል

ክፍል 2ትም በተለይ ከመፍትሔው ጋር አድርጎ እንዲጽፍልን ጠይቄዋለው ... እንጠብቃለን

የእናንተንም ሐሳብ ግሩፑ ላይ እናውራበት
Jo_El
❤ 46 🔥 5
10 May 2026
ኪ
12:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
T
Timeless Truth 10.05.2026 11:55:14
ዮሐ. 12 ላይ ባለው "የብርሃን ልጆች" በሚል ርዕስ በአቡነ አንጌሎስ የተሰጠ ትምህርት

ትርጉም: ዲ.ን ኪዳን

የመጀመሪያው ትንሽ ሰከንዶች record አልተደረጉም ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ይስተካከላል
Jo_El
❤ 45
12:24
T
Timeless Truth 10.05.2026 11:56:45
የብርሃን ልጆች.m4a
Exceeds maximum size, change data exporting settings to download.
21:48, 15.0 MB
Jo_El
❤ 30
15 May 2026
ኪ
10:45
ኪዳን ዘኢየሱስ
Athanasius Contra Mundum (Athanasius against the world)

ዓለም በአርዮሳዊ ክህደት ስትዋጥ ብቻውን ኦርቶዶክሳዊነትን የጠበቀ የቤተክርስቲያን ምሶሶ!
ኦርቶዶክሳዊነት በኒቅያ ጉባኤ የበላይነት ቢያገኝም ዓለም ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ይልቅ አርዮሳዊነትን መረጠ ከንጉሠ ነገሥቱ ፣ እስከ ጳጳሳት ፣ እስከ ካህናት እና ኃያላን ድረስ ፣ ኹሉም ማለት ይቻላል በአርዮስ ምንፍቅና ቫይረስ ሲጠቁ አንድ ሰው ግን ዓለምን ሞግቶ ተገኘ፤ ቅዱስ አትናቴዎስ!
አትናቴዎስ ዓለምን ተቃርኖ ለእውነት ቆመ ፣ በዚህም ምክንያት በ4 የሮማ ነገሥታት ተጠልቶ 5 ጊዜ ከመንበሩ ተሳደደ። እርሱ ግን በዚህ ኹሉ ውስጥ ተስፋ ሳይቆርጥ ለእውነት ቆመ። የአርዮሳውያን መዶሻ ገና በ 19 ዓመቱ " On the incarnation" የተባለውን ዘመን ተሻጋሪ መጽሐፍ የደረሰ ፣ የክርስቶስን ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ መኾን እስከ መጨረሻ የሕይወት እስትንፋሱ የጠበቀ፣  ሕይወቱን በሙሉ ለክርስቶስ የሰጠ ታላቁ አባት ቅዱስ አትናቴዎስ ዛሬ እረፍቱ ነው።

ምናልባት ያለ ቅዱስ አትናቴዎስ ክርስትናን ዛሬ በምናውቀው መንገድ ላናውቀው እንችል ይኾናል ፣ አርዮሳውያን ያሸንፉ ነበር ነገር ግን ክርስቶስ "የገሃነም ደጆች አይችሏትም" ያለውን ቤተክርስቲያኑን አይተውና ለቤተክርስቲያን ቅዱስ አትናቴዎስን አስነሣላት ፣ እርሱም ዓለምን ተቃውሞ እውነትን ጠበቀ ፣ ቤተክርስቲያንም በታመነ ዓለት ላይ ጸናች እርሱም ቅዱስ አትናቴዎስ የታገለለት እውነት "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ፣ እግዚአብሔር ነው ፣ ከአባቱ ጋርም አንድ ባሕርይ ነው" የሚለው የማይነቃነቅ ፣ የማንለውጠው ሃይማኖታችን ነው።

“If the world is against the truth, then I am against the world.”
― Athanasius of Alexandria

St. Athanasius the Apostolic my patron saint ❤️

ሕይወቱን መስማት ከፈለጋችሁ፡ https://youtu.be/Xl_yajcW_p8
❤ 66 💯 3
20 May 2026
ኪ
21:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገ በዓለ ዕርገት ነው ከጌታችን በዓላት አንዱ ነው። የምትችሉ ሁሉ አሰድሳችሁ ቁረቡ ወደ ሰማያት ከፍ ከፍ ያለው ኢየሱስ ፣ በልባችን ዙፋንም ከፍ ከፍ ይበል።
❤ 113 🙏 12 🕊 1
21:27
In reply to this message
በዓለ ዕርገት ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት የወጣበት ታሪካዊ እውነት ብቻ አይደለም ፣ ይልቅስ ሊቀ ካህናት ሆኖ በአባቱ ፊት የቀረበበት በዓል ነው። እግዚአብሔር ለአብርሃም በራሴ ማልሁ ዘርን አበዛዋለሁ ብሎ ቃልኪዳኑን እንዳጸናለት ፣ እንዲሁ "እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም አንተ በመልከጸዴቅ ሹመት የዘለዓለም ካህን ነህ" ብሎ በመሃላ የቃልኪዳኑን ማረጋገጫ ፣ ጌታችን ኢየሱስን በሰማያት ተቀብሎታል። ልጅ ለአባቱ የተወደደ መሥዋዕት ሆኖ ዕረገ ፣ አባትም የልጁን መሥዋዕት በደስታ አሸተተ ፤ ሊቀ ካህናታችን ወደ መቅደሱ ሰማያትን አልፎ ገባ ፤ ለእኛ በእግዚአብሔር ፊት አሁን ይታይ ዘንድ ዐረገ!

ስለዚህም ማረጉ ታሪካዊ ሁነት ብቻ አይደለም ይልቅስ በሰማያት ጠበቃ እንዳለን ፣ ስለ እኛም ዘወትር በአባቱ ፊት እንደሚቆምልን የሚያረጋግጥልን ሕያው ማኅተም ነው።

ወደ መጋረጃው የገባ ፣ በሰማያት ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት በአብ ቀኝ አለን!
❤ 109 🔥 4 🥰 2
23 May 2026
ኪ
14:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://copticorthodox.church/en/2026/05/22/holy-synod-meeting-statement/

እዩት የኮፕቲክ ሲኖዶስ በዚህ ዓመት ርክበ ካህናት ትናንት ወስኖ የተለያየቸው ጉዳዮች ናቸው ፣ ርእሰ ጉዳዮቹ ራሱ ደስ ሲሉ።

እንዲሁም 2 አዲስ ቅዱሳንን ቀንነዋል።
❤ 28 🔥 5 🥱 1
27 May 2026
ኪ
21:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሥዕላትን ማክበር

ብዙህ ጊዜ ለሥዕላት ክብር መስጠትን በተመለከተ ከእኛ ወገን ያሉ ሰዎች ዮሐንስ ዘደማስቆን ሲጠቅሱ አያለሁ ነገር ግን እኛ ያለን የሥዕላትን ማክበር አስተምህሮ ከምስራቅ ኦርቶዶክሶች እንደሚለይ ያስተዋለው ያለ አይመስለኝም። እንዲሁም የእነርሱ የሁለተኛ ኒቅያ ጉባኤ ትምህርት በደምብ የታየ አይመስለኝም ትልቅ ችግር አለበትና።

የመጀመሪያ ትልቁ ችግር እነርሱ "ሥዕል አያስፈልግም" ባዮችን የከሰሷቸው በነገረ ክርስቶስ ጥሰት ነው። ማለትም ክርስቶስ አይሳልም ማለት ክርስቶስ ሥጋ አለበሰም ብሎ መካድ ነው ብለው ነበር ሲሞግቷቸው የነበረው ስለዚህም የማይታየው አምላክ በሚታይ ሥጋ ተገለጠ የሚለውን ለመቀበል የግድ ሥዕላት መኖራቸው አስፈላጊ ናቸው ይላሉ። እኛ በፍጹም ይህንን አንቀበለውም ሥዕላት መኖራቸው ነገረ ክርስቶስን ለመግለጥ የግድ አስፈላጊ አይደሉም ክርስትና ያለ ሥዕላትም ይቀጥላል ፣ መኖርም ይችላል ስለዚህ ሥዕላት መኖራቸው ለአምሏችን የግድ አስፈላጊ እንዳልሆኑ እንናገራለን። በአጭሩ ሥዕላት መኖራቸው ጠቃሚ ነው ብንልም የግድ መኖር አለባቸው ግን አንልም ለዚህም ነው አብያተ ክርስቲያኖቻችን "minimalist" ሊሆኑ እንኳን የሚችሉት በምሥራቆቹ ዘንድ ግን በፍጹም የማይሆን ነገር ነው ቤተክርስቲያኖቹ የግድ በሥዕላት መሙላት አለባቸው።

ሁለተኛው ችግር "ሥዕላትን የማያከብሩ ፣ ሥዕላትን የማይስሙ የተወገዙ ይሁኑ" ብሎ ሁለተኛው የኒቅያ ጉባኤ ማውገዙ ነው። ከላይ እንዳነሳነው ሥዕላት መኖራቸው ለእኛ የግድ ስላልሆነ እንዲሁም ከታች በምመጣበት በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ክፍለ ዘመናት የሥዕላት አክብሮት በቤተክርስቲያን ውስጥ ባለመኖሩ "ሥዕላትን አለማክበር"ስህተት ነው እንጂ የሚያስወግዝ ምንፍቅና ነው ብለን አንናገርም። ይህ ውግዘት በእነርሱ አካሔድ የመጀመሪያዋን ክፍለ ዘመናት ቤተክርስቲያን ሁሉ የሚያወግዝ ነው ምክንያቱም ሥዕላትን ማክበር በቤተክርስቲያን ውስጥ የጊዜ ውስጥ የመጣ ልምምድ ነው እንጂ ከመጀመሪያውኑ አልነበረምና። እንዲሁም ክርስትና ያለ ሥዕላትን ማክበር ሊኖር አይችልም የሚል አመልካችን አለው ይህ ደግሞ ሊታሰብ የማይችል ነገር ነው።

ሦስተኛው ችግሩ ደግሞ "ሥዕላትን አክበር ሐዋርያዊ ትውፊት ነው" ብሎ ሁለተኛው የኒቅያ ጉባኤ መናገሩ ነው። ይሄ ደግሞ ስህተት መሆኑን የታሪክ አጥኚዎች ሁሉ ይመሰክራሉ። የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ከጣኦት አምላክያን ጋር በመነራቸው ተዋሥኦ እናንተ እኮ "ምስሎች የላችሁም" ተብለው ይጠየቁ ነበር ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ ደግሞ "አይ ተሳስታችኋል እኛም እኮ ሥዕላት አለን" ብለው አልመለሱም ይልቁንስ "እኛ የምናመልከው የማይታየውን አምላክ ስለሆነ ሥዕላት የሉንም" ብለው ነበር የሚመልሱት። ይህን የፕሮቴስታንት ምሑራን ብቻ አይደሉም የካቶሊክ ምሑራን ራሱ የሚናገሩት ነገሮች ነው ፣ ሥዕላትን ማክበር "doctrinal development" ወይስ በጊዜ ውስጥ የመጣ አስተምህሮ ነው ብለው ይናገራሉ እንጂ። ታድያ "ሁለተኛው የኒቅያ ጉባኤ እኮ ሥዕላትን ማክበር ሐዋርያዊ ትውፊት ነው" ይላል ተብለው ሲጠየቁም ምላሻቸው ዓለም አቀፍ ጉባኤያት በሁሉም ነገር ስህተት የለባቸው ማለት አይደለም ይልቅስ ዶግማዊ ውሳኔ ሲያስተላልፉ ብቻ ነው ማይሳሳቱት ይላሉ። ምስራቅ ኦርቶዶክሶቹ ናቸው የሁለተኛው ኒቅያ ጉባኤ ሥዕላት ሐዋርያዊ ትውፊት ነው ስለሚል በጥብቅ የሚሞግቱለት ፤ ነገር ግን ይህ አቋም በምሑራኑ ዘንድ seriously የሚወሰድ አቋም አይደለም አብዛኞቹ ምሑራን ዘንድ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ክፍለ ዘመናት ሥዕላትን ማክበር አለመኖሩ ላይ ስምምነት አለ።

ታድያ ምስራቅ ኦርቶዶክሶችን ሆኑ ካቶሊኮች በዚህ ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ይወድቃሉ ፤ ካቶሊኮቹ ሥዕላትን ማክበር በጊዜ ውስጥ የመጣ አስተምህሮ ነው በማለታቸው ከታሪካዊ ጥናቱ ጋር ቢስማሙም "ከማይሳሳተው" ጉባኤያቸው ጋር ይጣላሉ። ምስራቅ ኦርቶዶክሶቹ ደግሞ "ሥዕላትን ማክበር ከሐዋርያት ዘመን ጀመረ" በማለት ጉቤያቸውን ቢቀበሉም ከታሪካዊ ጥናቱ ጋር ይጣላሉ። እኛ እንደ ኦሬንታል ኦርቶዶክስ ሁለተኛውን የኒቅያ ጉባኤ ስለማንቀበለው ከሁለቱም አጣብቂኝ እናመልጣለን።

እዚህ ላይ ሥዕላትን ማክበር በጊዜ ውስጥ የመጣ መሆኑ ችግር ነው ብሎ አንድ ሰው ሊያስበው ይችላል። ነገር ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙህ ነገሮች በጊዜ ውስጥ እየተብራሩ እንደመጡ ማወቅ አለብን። ስለዚህም ሥዕላትን ማክበር ላይ በብሉይ ኪዳኑ የታቦት ማክበር (The Logic of divine images) እንዲሁም በመልካዊ ነገረ ክርስቶስ (Image Christology) በዘር ደረጃ ቢኖርም ተብራርቶ የመጣው ግን በኋለኞቹ ክፍለ ዘመናት ነው ፤ ቤተክርስቲያን ደግሞ ቀድሞ የነበረውን ትምህርት የሚቃወም አይሁን እንጂ Doctrineም ሆነ practice develop ልታደርግ ትችላለች። ይህን በሰፊው ሌላ ቀን እንመጣበታለን አሁን ግን ማወቅ ያለብን እንዲሁ "እኛ ምስራቃዊያን ነን" እያልን የምስራቅ ኦርቶዶክሶችን ትምህርት ወደ እኛ ማምጣት እንደሌለብን ነው።
❤ 87 👍 6 🤔 2
30 May 2026
ኪ
16:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
ማርቆስ 14
61 እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና። የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው።
62 ኢየሱስም። እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።
63 ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና። ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል?
64 ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ። ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት።

እዚህ ላይ የሊቀ ካህናቱን እና የኢየሱስን ቃለ ምልልስ አስተውሉ ሊቀ ካህናቱ "የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን?" ብሎ ይጠይቀዋል። ኢየሱስም "እኔ ነኝ" ብሎ ቢመልስም መልሱን በዚህ ብቻ አላበቃም ይልስ በሁለተኛው ቤተመቅደስ ይሁዲ ዘንድ የሚታወቅ አንድ concept አነሳ "የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።" ሲል መለሰ ፤ ሊቀ ካህናቱም ልብሱን በመቅደድ "ስድቡን ሰማችሁን?" ሲል ተቆጣ።

ሊቀ ካህናቱ "ተሳድቧል" ለማለት ያስቻለው ነገር ምንድነው? "እኔ ክርስቶስ ነኝ" ብሎ መናገር በዝን ጊዜ ስድብ አልነበረም ብዙዎች ክርስቶስ ነን በማለት ተናግረዋል። እንዲሁም "የቡሩክ ልጅ ነኝ" ማለትም ስድብ አይደለም የእስራኤል ነገሥታት የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል። ታድያ አንድ ሰው ራሱን ክርስቶስም ስላደረገ ፣ ወይም የእግዚአብሔር ልጅ ስላደረገ ሳይሆን ራስን ከእግዚአብሔር ጋር ስላስተካከለ ነው በእግዚአብሔር ላይ ስድብ ተናግሯል የሚባለው።

ኢየሱስ እዚህ ጋር ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካከለው "የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ" በማለቱ ነው። ዳንኤል 7 ላይ አንድ መለኮታዊ አካልን እናያለን በሰማይ ደመና በዘመናት ወደ ሸመገለው የሰው ልጅ የሚመስል ይመጣል ፣ መንግሥትም ገዢነትም ይሰጡታል ፣ ምድር አለቆች ሁሉም ይገዙለታል። እዚህ ላይ "በሰማይ ደመና መምጣት" እንዲሁ የሚታለፍ ነገር አይደለም የራሱ የያሕዌ አንድ መጠሪያ "rokhev ba'aravot" (Rider of Clouds) ወይም በደመና ላይ የሚጫን የሚለው ነው።

ይሄ መጠሪያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ራሱ ብዙህ ታሪክ ያለው ነው። የከነዓናውያን አምላክ በኣል "የወጀብ አምላክ (Storm god)" ነው። ዝናብን ፣ ነጓድጓድን ፣ የምድርን ፍሬያማነት ሁሉ እንደሚቆጣጠር ይታመናል ዋና መጠሪያውም "በደመና የሚጫን (Rider of Clouds)" ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ያነበበ ሰው ሁሉ እንደሚያስተውለው ደግሞ በብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን እና ከነአናውያን ቀጥታ ጥል ላይ ስለነበሩ የያሕዌ አምልኮት እና የበኣል አምልኮትም እንዲሁ የበላይነትን ለማግኘት ጥል ላይ እንደነበር እናውቃለን (የኤልያስ እና የበኣልን ነቢያት ታሪክ ማስታወስ ነው።) ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እስራኤላውያን የበኣል አምላኪያን ላይ polemic ለማድረግ ሲሞክሩ እና "የዝናብ ፣ የነጓድጓድ ፣ የምድር ፍሬያማነት" ተቆጣጣሪ በኣል ሳይሆን ያሕዌ ነው የሚሉ መልእክቶችን አስተላልፈዋል ፣ ለዚህም ሲባል የያሕዌ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ "በደመና የሚጫን" የሚለው መጠሪያ ጥቅም ላይ ውሏል ፤ ለሌላ ለማንም ፍጡርም ጥቅም ላይ አልዋለም። ለምሳሌ፡

"ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።" (ኢሳ 19፡1)

"26 ፤ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።" (ዘዳ 33፡26)

"3 እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ሰረገላውን ደመና የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥"(መዝ 104፡3)

ከዚህ እንደምንረዳው በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ "በደመናት የሚመጣ" የሚለው ቀጥታ የያሕዌ መጠሪያ እንደሆነ ነው። በዳንኤል 7 ላይ የምናገኘው የሰው ልጅም በዘመናት ከሸመገለው የተለየ ቢሆንም ዘለዓለማዊ መንግሥት ሲቀበል እናየዋለን። ከዚህ የተነሣም በሁለተኛው ቤተመቅደስ ይሁዲ ጊዜ "ሁለተኛው ያሕዌ" የሚባል አካል ይታመን ነበር። እንግዲህ ኢየሱስ " እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ" ብሎ ሲናገር ፤ በእምነታችሁ "ሁለተኛው ያሕዌ የሚለውን አካል ታውቃላችሁ አይደል? እርሱ እኔ ነኝ" ብሎ እየተናገረ ነው ፤ ይህም ነው በሊቀ ካህናቱ ዘንድ ልብሱን እስኪቀድ "ተሳድቧል" ያስባለው ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሏልና።

ይህ ጥቅስ ኢየሱስ በራሱ ቃል አምላክነትን claim ስለማድረጉ አንድ ማሳያ ነው።
❤ 49 🔥 31
ኪ
22:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰላም እደሩ ነገ በዓለ ጰንጠቆስጤ መሆኑን እንዳትረሱት
❤ 79 🔥 16
31 May 2026
ኪ
10:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
መለኮታዊ እሳት

የሚያቃጥል የእሳት ልሳን ከሰማያት ወረደ ፣ ከአርያሙ ከፍታ የሚባላ እሳት ወረደ። ይህ እሳት ግን ሰዶምን እንዳጠፋው እሳት የጥፋት እሳት አይደለም ይልቅስ የባቢሎንን ግንብ ያፈረሱ 72 ልሳናትን ይዟል እንጂ። የባቢሎኑ ልሳንስ አንድ የነበረው ሕዝብ የበታተነ ነው የአሁኑ ልሳን ግን እስከ ዓለም ዳርቻ የተበተነውን ሕዝብ የሚሰበስብ ነው። በሰዶም ላይ የወረደው እሳት ሕዝቡን ከነ ኃጢአታቸው ያጠፋ እሳት ነው ፣ የአሁኑ እሳት ግን ለዓለም ሕዝብ ኹሉ የምሥራች ወንጌልን የሚሰብክ የሚያድን እሳት ነው።

ከጽርሐ አርያም እሳት ወረደ በጽርሐ ጽዮንም ላይ አረፈ የሚንበለበል ልሳናትን ይዟል እንደ ሰከረ ሰው በኃይል ያናግራል ፣ በሰይፍ ፊት ድፍረትን የሚሰጥ ስልጣንን ተጎናጽፏል ፤ ስለ እውነትም ይመሰክር ዘንድ ዝም አይልም "እናንተ የሰቀላችሁትን ክርስቶስ እግዚአብሔር በክብር አስነሣው" እያለ በሚገባው ቋንቋ ኹሉ ይወቅሳል፤ ከሰማይ ወርዶ ይቆፍራል መሬትንስ አይደለም የሰውን ልብ ይቆፍራል የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ እንዲፈልቅ ይቆፍራል (ዮሐ 7፡38)። ለዘለዓለም በሚያረካውም ውሃ ልብን ያረሰርሳል። የማይጠፋ ብርሃን አለው፤ በተስፋው ብርሃን እየዋጀ የብርሃን ልጆች እስክንኾን ድረስ አይተወንም ኹሉንም ለእግዚአብሔር ይዋጃል ከማኅጸነ ዮርዳኖስም ወልዶ የሰማያት ልጆች አድርጎናል እርሱም የርስታችን መያዣ ነው (ኤፌ 1፡14) ስሙም ከአብ የሚወጣ አጽናኙ የእውነት መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ነው! (ዮሐ 15፡26)

ኢዩኤል ሆይ ደስ ይበልህ እነሆ ትንቢትህ ተፈጸመ መንፈሱ በሥጋ ለባሽ ኹሉ ላይ ፈሷል ፣ ወንዶችም ሴቶችም ትንቢትን ተናግረዋል ፣ ሽማግሌዎችም ሕልምን አልመዋል፣ ጎበዞቻችንም ራእይን አይተዋል ፣ በሰማያትም ድንቅ ታይቷል (ኢዩ 2፡28-30)። ልባችን በመለኮታዊው እሳት ተቃጠለ እነሆ ጽርሐ ጽዮን በደስታ ተሞላች ፣ ከጽርሐ አርያምም ጋር አንድ ኾነች አጽናኙ መጥቷልና ፣ ድንቅም ከሰማያት ፈሷልና!

አቤቱ መለኮታዊው እሳት ሆይ! ነፍሳችንን አንድደው ፣ የክርስቶስ ሕይወት ብርሃን በውስጣችን ይበራ ዘንድ፤ የማትጠፋ እሳት ሆይ! ኹለመናችንን ተቆጣጠር። ነፍሳችን በኃጢአት ውሃ ቀዝቅዛለች ፣ በዓለምም ሃሳብ ተጠምዳ የሕይወትን ውሃ ተጠምታለች። የሕይወት ውሃ ክርስቶስ በልባችን ይፈልቅ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ልባችንንን ስበረው ፣ የክርስቶስን ትንሣኤ ብርሃን በልባችን ውስጥ አቀጣጥለው። አጽናኙ ሆይ! አጽናናን ፣ የዋሑ ርግብ ሆይ! ልባችንን በትሕትና አረስርሰው ምናልባት የሸፈተው ልባችን ትንሽ እንኳን ይመለስ እንደኾነ።

"መንፈስ ቅዱስ አእምሮንና ልብን የሚያበራ ብርሃን፣ መንፈሳዊ ጥማችንን የሚያረካ ውሃ፣  የሚያነጻና የሚቀድስ እሳት ነው። (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በእንተ መንፈስ ቅዱስ)

መልካም በዓለ ጰንጠቆስጤ ኹላችንም በቅዳሴ ተገኝተን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንባረክ፤ ሕይወት የሆነውን ሥጋና ደምም እንቀበል!

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus

Repost
❤ 80 🔥 7 👏 1
ኪ
21:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከሥላሴ ሦስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስ ከአብ የወጣ ከወልድም የወሰደ ከአብ ወደ ወልድ የሚሠርጽ ፣ ከወልድም ወደ እኛ የመጣ ፣ በእኛ ውስጥም አድሮ በወልድ ውስጥ ለአብ አንድ የሚያደርገን የሚያጸና የሚያጽናና መንፈስ ነው!
❤ 84 🔥 9
1 June 2026
ኪ
11:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
እዚህ ላይ በጻፍኩት አንድ አንድ ሰዎች እነርሱ ስላላወቁ ብቻ የሌለ ይመስላቸዋል እንዲሁም ምንፍቅና የሚመስላቸው አሉ ፤ ይሄ ምን ያህል ከአባቶች ትምህርት እንደ ራቅን ነው የሚያሳየው። እዚህ ጋር ለተናገርኩት ነገር ሁሉ ከአባቶች ልጥቀስላችሁ፡

For the Father is not Son, and yet this is not due to either deficiency or subjection of Essence; but the very fact of being Unbegotten or Begotten, or Proceeding has given the name of Father to the First, of the Son to the Second, and of the Third, Him of Whom we are speaking, of the Holy Ghost that the distinction of the Three Persons may be preserved in the one nature and dignity of the Godhead."
(Gregory of Nazianzen: Oration 31:9)

"አብ ወልድ አይደለም ይህ ግን የሆነው በባሕርይ ማነስ አይደለም ይልቅስ አለመወለድ ፣ መወለድ እና መሥረጽ የሚሉት ግብራት የአንደኛውን ስም አብ አስደረገው ፣ የሁለተኛውን ወልድ ፣ የሦስተኛውንም አሁን እየተናገርንለት ያለነውን መንፈስ ቅዱስ አስባለው ይህም የሆነው የአካላቱ ልዩነት በአንድ ባሕርይ እና የመለኮት ክብር ይጠበቅ ዘንድ ነው" (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘንዘኢናዙ)

"The Son is second to the Father in rank because he is from him. He is second to the Father in dignity because the Father is the principle and cause by virtue of which' he is the Son's Father and because we approach and access the God and Father through the Son. 6 Even so, the Son is not second in nature, since there is one divinity in both of them. Likewise, it is clear that, even if the Holy Spirit is below the Son in both rank and dignity-something with which we too are in total agreement it is still not likely that he is of a foreign nature. What follows will make this conclusion clear. "
(Basil the great: Against Eunomius Book 3, 5)

""ወልድ ከአብ ስለሆነ በሥርዓት ከአብ ቀጥሎ ሁለተኛ ነው። አብ የወልድ አባት በመሆኑ፣ እንዲሁም ወደ አምላክና አብ በወልድ በኩል የምንቀርብ በመሆኑ፣ በአክብሮትም ከአብ ቀጥሎ ሁለተኛ ነው። ያም ሆኖ በሁለቱም ዘንድ አንድ አምላክነት ስላለ፣ ወልድ በባሕርይ ሁለተኛ አይደለም። እንደዚሁም መንፈስ ቅዱስ በሥርዓትና በአክብሮት ከወልድ በታች ቢሆንም [ከአብ ሦስተኛ]—እኛም በዚህ ሙሉ በሙሉ ብንስማማም—የውጭ ባሕርይ ያለው ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም።" (ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ)

"And if, as He says, the Spirit receives of Him, the Spirit Himself being omnipotent, surely He Himself has a power which is universal... But it is because He is Consubstantial with the Son, and divinely proceeds through Him, exercising universally His entire activity and power, that Christ says, "He shall receive of Me." (Cyril of Alexandria : Commentary on Gospel of John 16)

"እርሱ እንደሚለው መንፈስ ከእርሱ የሚወስድ ከሆነ፣ መንፈስ ራሱ ሁሉን ቻይ እንደመሆኑ መጠን፣ እርሱ ራሱ ዓለም አቀፋዊ የሆነ ኃይል እንዳለው የታወቀ ነው። ... ነገር ግን እርሱ (መንፈስ ቅዱስ) ከወልድ ጋር ባሕርይ አንድ ስለሆነ፣ በወልድም በኩል በአምላክነት ስለሚሠርጽ፣ መላውን ሥራውንና ኃይሉን ሁሉ በዓለም ሁሉ እየፈጸመ ስለሆነ ነው ክርስቶስ 'ከእኔ ይወስዳል' ያለው።" (ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ)

"...And the Holy Spirit is connected to the Father and the Son, firm within them, coming forth from the Father to the Son, unseparated from them... The middle and last parts of the finger go down and come up and do not separate from the original part; likewise, we say that the Son came down from heaven and became incarnate, and likewise the Holy Spirit came down upon the Son... and did not separate from the Father; nor from the Son, for He is the Spirit of the Father and the Son who dwells within them..." (Sawirus ibn al-Muqaffa, Al-Durr al-Thamin fi Idah al-Din (كتاب الدر الثمين في إيضاح الدين) )

"መንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ ጋር የተያያዘ ነው፤ በእነርሱም ውስጥ ጸንቶ የሚኖር፣ ከአብ ወደ ወልድ የሚወጣ ነውና፤ ከእነርሱም አይለይም። ... የጣቱ መካከለኛውና የመጨረሻው ክፍል ወደ ታች ወርደው ወደ ላይ ይወጣሉ እንጂ ከመጀመሪያው ክፍል አይለዩም፤ እንዲሁ ወልድ ከሰማይ እንደወረደና እንደተዋሐደ እንላለን፤ መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ በወልድ ላይ ወረደ... ከአብም አልተለየም፤ ከወልድም አልተለየም፤ እርሱ በአብና በወልድ ውስጥ የሚኖር የአብና የወልድ መንፈስ ነውና። " (ቅዱስ ሳዊሮስ ኢብን አል ሙቀፋ ኤጲስ ቆጶስ ዘእስሙናይ)
❤ 26 🔥 2 👍 1
ኪ
14:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬማ ምርጫም አይደል? ከምርጫ ጋር የተያያዘ አንድ thought experiment ልጠይቃችሁ። በመጨረሻም አንድ smuggle የተደረገ theological claim ስላለ እሱን እንወያይበታለን፡

አንድ በ super computer የተጠበቀ ክፍል ውስጥ ሁለት ሳጥኖች አሉ። አንደኛው 10,000 ብር አለበት፣ አንደኛው ደግሞ ምስጢራዊ ሳጥን ነው። ሁለት ምርጫ ነው የሚሰጣችሁ፡ ወይ ሁለቱንም ሳጥኖች መውሰድ፣ ወይም ምስጢራዊውን ሳጥን ብቻ መውሰድ። ነገር ግን ይህ super computer የሰዎችን ምርጫ predict በማድረግ ላይ highly accurate ነው—እስከ 99% ድረስ ልንለው እንችላለን። ምስጢራዊውን ሳጥን ብቻ እንደምትወስዱ predict ካደረገ፣ ምሥጢራዊው ሳጥን ውስጥ 1,000,000 ብር ያስቀምጣል፤ ሁለቱንም ሳጥኖች እንደምትወስዱ predict ካደረገ ግን ምስጢራዊው ሳጥን ውስጥ ምንም ብር አይኖረውም። ይህ super computer ይህን prediction የሚሠራው ገና ክፍሉ ውስጥ ሳትገቡ፣ ጥያቄዎቹን ሳታውቁ ነው። ልክ ስትገቡ already predict አድርጎ ጨርሷል ማለት ነው።

ስለዚህ ምርጫችሁ ምን ይሆናል? ምስጢራዊውን ሳጥን ብቻ መውሰድ ወይስ ሁለቱንም?
❤ 13 🤯 2
ኪ
15:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
እስቲ ምረጡ
Anonymous poll
- ሁለቱንም ሳጥኖች ወስዳለሁ 79 votes, chosen vote
- ምስጢራዊውን ሳጥን ብቻ ወስዳለሁ 98 votes
- ሲጀመር አልገባኝ 81 votes
258 votes
ኪ
16:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ጥያቄው ምን መሰላችሁ ነጻ ፈቃድ አለ ወይ?

ምክንያቱም ኮምፒተሩ ይህን prediction ገና ሳትገቡ በፊት በ99% accuracy predict ለማድረግ እናንተን ማወቅ አለበት እናንተን ማወቅ ብቻ አይደለም ከገባችሁ በኋላ ምርጫችሁን እንደማትቀይሩም ማወቅ አለበት። ለምሳሌ እኔ የማስበው ከገባሁ በኋላ the prediction already made የሆነ ስለሆነ ወይ ገንዘቡ ምስጢራዊው ሳጥን ውስጥ አለ ወይ የለም እላለሁ ይህን ደግሞ 10,000 ብርያለውን ሳጥን መውሰዴ አይለውጠውም ስለዚህ 10,000 ብሩን ጥዬ መሔድ irrational ነው እላለሁ ነገር ግን ኮምፒተሩ እንደዚህ ከሆነ accurate አይደለም ማለት ነው (ይህ contradiction ነው)። ነገር ግን ኮምፒተሩ Accurate ነው ስለዚህ already ከገባሁ በኋላ ይሄን ሁሉ እንደማስብ አውቆ ከመጀመሪያውኑ 1,000,000 ብሩን ምስጢራዊው ሳጥን ውስጥ አያስቀምጥም ስለዚህ ብሩን አላገኝም ማለት ነው so አሁን ላይ ያለው የኔ ድርጊት መጀመሪያውኑ የተወሰነ ነው ማለት ነው ስለዚህ ነጻ ፈቃድ የለኝም ሁሌም ሁለቱንም ሳጥኖች በመምረጥ 1,000,000 ብር የማጣ ሰው ነኝ። (በተቃራኒውም ምስጢራዊውን ብቻ የሚመርጡ ሁሌ ምስጢራዊውን ብቻ መርጠው 1,000,000 ብር የሚያገኙ ሰዎች ናቸው ነጻ ፈቃድ የላቸው።)

ይህ የሚያሳየውን ወደፊትን accurately predict ማድረግ የሚችል አካል እስካለ ድረስ ነጻ ፈቃድ አለን ማለት contradiction ነው ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ወደፊቱን ሁሉ የሚያውቅ ከሆነ ነጻ ፈቃድ የለም ማለት ነው። እስቲ መልሱ።
👀 17 ❤ 10 😁 4 👏 3
ኪ
17:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
እንግዲህ የነጻ ፈቃድ ጥያቄ እንደ ለመድነው "እግዚአብሔር ወደፊቱን ያውቃል እንጂ አይወስንም" በሚሉት ነገሮች ብቻ እንደማይመለስ አይታችሁታል ብዬ አስባለሁ ደከመኝ መልካም ቀን 🏃🏾‍♂️
❤ 32
ኪ
20:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ሰዎች ደግሞ ነጻ ፈቃድ የለም እያልኩ አይደለም በአጭሩ ስለማይመለስ በሰፊው ሌላ ጊዜ ብዬ ነው እንጂ። እስቲ ቋሚ ቲክቶክ ላይም ስላሰብኩ እኔድበታለን እስቲ ዛሬ ማሟሟቂያ 3 ሰአት ኑ
❤ 38
ኪ
21:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://vt.tiktok.com/ZS92SvvpRmRLh-HzGNN/

እስቲ ግቡ ገብተናል
❤ 14
2 June 2026
ኪ
16:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
T
Timeless Truth 02.06.2026 11:19:11
ሦስተኛ መጽሐፋችን ወታለች

ስለ ወንጌላት ብዙ ለየት ያሉ ጠቃሚ ምልከታዎችን ታገኙበታላችሁ

መልካም ንባብ!
🙏 38 ❤ 21 👍 3 🔥 1
ኪ
16:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ወንድሞች እኅቶች በጣም እየለፉ ነው ፤ ሰው ደግሞ የልፋቱ ዋጋ ሲነበብለት ደስ ስለሚለው አንብቡላቸው shareም አድርጉ
👍 44 ❤ 29 👎 1
ኪ
20:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጌታ ሆይ ይሄ በጣም የተደራጀ ጭፍጨፋ እኮ ነው ምን ጉድ ነው ምንስ ይባላል። ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም ሆኗል ጌታ ሆይ ሳንጠፋ አንተው ድረስ እንጂ ሌላ ምን ይባላል። ከቤተ መንግሥትም ሆነ ከቤተ ክህነት እረኛ የለንም ሁሉም የራሱን ጥቅም ብቻ ነው የሚያሳድደው ጌታ ራሱ እረኛ ይሁነን በጎቹን ይሰብሰብ።
💔 101 😭 40 ❤ 7 😢 6 👍 1
3 June 2026
ኪ
20:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሁሌ ሕንጻ ሕንጻ ብቻ ስለ ሰው ነፍስ አይጨንቃችሁም አንድ ቀን ግን ምዕመኑ ሁሉ ወይ ሞቶ ፣ ሃይማኖቱን ቀይሮ ፣ ኤቲስት ሆኖ ሕንጻውን ብቻ ታቅፋችሁ ገንዘብ የሚሰጣችሁ ታጣላችሁ
😭 67 💔 19 ❤‍🔥 4 🔥 4 ❤ 2 👎 1
ኪ
20:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ቤተክርስቲያን ማለት በመጀመርያ ደረጃ ሕንጻ አይደለም ፣ ሕንጻ ሳይኖርም ቤተክርስቲያን ነበረች። በሐዋርያት ዘመን ቤተክርስቲያን በየ ሰዉ ቤት እና በመቃብር ቤቱ ውስጥ ነበረች። ቤተክርስቲያን ማለት ክርስቶስን የሚያምኑ አማኞች ኅብረት ናት ፣ አማኞች እስካሉ ድረስ በመጠለያም ሆነ በድንኳን ውስጥ መሰብሰብ ይቻላል። ኅብረቱ ሲያድግ ነው ወደ ትላልቅ ሕንጻዎች የሚኬደው። አሁን ግን በእኛ ዘመን ኅብረቱ ሞቷል እኮ ምን ቀረው? አብዛኛው ክርስቲያን የስም ክርስቲያን ብቻ አይደለም እንዴ? አብዛኛው ወጣት ክርስቲያን ከቁርባን ርቆ ያለ አይደለም እንዴ? አብዛኛው ወጣት በዝሙት ሕይወት ውስጥ ያለ አይደለም እንዴ? አብዛኞቹ ባለትዳሮች በቤተክርስቲያን ውጪ አግብተው በዝሙት ውስጥ የሚኖሩ አይደለም እንዴ? አብዛኛው ወጣት በፖርኖግራፊ ሱስ የተያዘ አይደለም እንዴ? አብዛኛው አማኝ ቅዳሴ የማይሳተፍ ቢሳተፍም ከስንት አንዴ አይደለም እንዴ? ብዙህ ወጣቶች ልጆቻቸውን ገና በማኅጸን በውርጃ የሚገሉ አይደለም እንዴ? ብዙህ አማኝ ወገኖቻችን በአርሲ በሐረርጌ እየተገደሉ አይደለም እንዴ? አብዛኛው ሕዝበ ክርስቲያን እኮ በስም ክርስቲያን ተባለ እንጂ ኑሮው የኤቲስት ነው።

በዚህ ሁሉ ውስጥ ከቤተክርስቲያን በኩል ምን ተደረገ? ምንም እንዲሁ አንዴ ለሕንጻ ፣ አንዴ ለሕንጻ እድሳት ፣ አንዴ የአጥር ፣ አንዴ ለበር ፣ አንዴ ለሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ እያሉ ማያልቅ ገቢ ማሰባሰብ ላይ ናቸው። ምዕመኑ ሰልችቶታል ይሄ ፤ ከስንት አንዴ ቤተክርስቲያን ቢመጣ ወንጌል መስማት ነው የሚፈልገው ፤ ከዚህ ዓለም ጣጣ የሚያጽናናው የእግዚአብሔር ቃል ነው የሚፈልገው ፤ ተርቧል ነገር ግን ገቢ ስብሰባ መግበውት ይሸኙታል ፤ ሁለተኛ አይመጣም።

ኧረ የቤተክርስቲያን ያለ!
😭 102 ❤ 34 👍 8 🔥 3 😢 2 💔 2 👎 1 🙏 1
9 June 2026
ኪ
21:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
T
Timeless Truth 09.06.2026 17:33:06
4ኛው መጽሐፋችንን እንደጨረስን ለJimmy Akin Email አድርጌለት ነበር

ይህንን ስራችንን በሚድያዎቹ ሁሉ አጋርቶልናል [አሪፍ ስራ እንደሰራን ይሰማኛል]

ይህንን እየጻፍኩላችሁ Email መለሰልኝ እና ከነዚህ ስራዎቹ ባለፈ የትኛዎቹንም ስራዎቹን እንድተረጉም ፈቃዱን ሰቶኛል እግዚአብሔር ይመስገን🙏
❤ 79 🔥 7 👏 1
21:11
T
Timeless Truth 09.06.2026 17:33:06
21:11
T
Timeless Truth 09.06.2026 17:33:06
ኪ
21:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
እዚህ ቻናል የማይቀላቀል ከኔ ቻናል ይባረራል 😒
😁 45 🤝 12 💯 6 😴 3 🥴 2
10 June 2026
ኪ
10:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
?✠
𝕭𝖎𝖓𝖎 ✠ 10.06.2026 10:17:43
ዛሬ አባታችን ካረፉ 5 አመት ሆኗቸዋል። ያለ መታከት የሚወዷትን ቤተክርስቲያናቸውን አገልግለዋል ስለበዛ አበርክቷቸው እናመስግናቸው አምላከ ቅዱስ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይምርልን ዘንድ እንጸልይላቸው

እግዚኦ አእርፍ ነፍሰ ገብርከ ሣሕለ ማርያም
❤ 97 🥰 2 👍 1
10:33
?✠
𝕭𝖎𝖓𝖎 ✠ 10.06.2026 10:17:43
12 June 2026
ኪ
21:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
የአእምሮ ሕመም ልክ እንደማንኛም ሌሎች ሕመሞች ሁሉ በሰውነት ባሉ ኬሚካሎች መዛባት ምክንያት የሚመጣ ሕመም ነው። ስለዚህ ህክምናውም እንዲሁ እንደማንኛውም ሌሎች ሕመሞች ሕክምና ነው። ነገር ግን በተለይ በሐገራችን የአእምሮ ሕመም ያለው ግንዛቤ ትክክል አይደለም። አንዳንዱ ፍልስፍና በማንበብ ይመጣል ይላል ፣ አንዳንዱ ደሞ ሰይጣን ነው ይላል እንዲሁም ሌሎች ነገሮች። ነገር ግን የአእምሮ ሕመም እንደ ማንኛውም ሕመም ስለሆነ በሱ ላይ ያለው መገለል መቆም አለበት!

እንዲሁም ደግሞ በሀገራችን የአእምሮ ሕመሞችን እንዳለ በአንድ በመመደብ "ማበድ" የሚል ስም ይሰጠዋል ብዙህ ጊዜ የቃሉ አጠራር ጥሩ ባይሆንም "ማበድ" የሚባለው የ Schizophreniaን የአእምሮ ሕመም አይነት ነው። ነገር ግን የአእምሮ ሕመም በጣም ብዙህ አይነት ነው። MDD,PTSD, Bipolar Disorder, OCD, Anxiety disorders እያልን ብዙህ መጥራት እንችላለን እንዲሁም ደግሞ ቢታከሙ መፍትሔ የሚያገኙ ናቸው ብዙዎቹ ፣ ነገር ግን ካለው መገለል አንጻር ብዙዎች የህክምናን እርዳታ አይጠይቁም። ስለዚህ እኔ የምለው ነገር በአእምሮ ሕመም ላይ ያለው stigma ይቁም ነው!

ይህ ያለንበት ወር ደግሞ የወንዶች አእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው ፤ ስለዚህ የምለው ነገር ወንድሞች ሆይ "ወንድ አይደለህ እንዴ" እየተባላችሁ አድጋችሁ ብቻችሁን suffer እያደረጋችሁ ያላችሁ እርዳታን ጠይቁ ብዙህ ወንዶች በዚህ ብቻቸው suffer እያደረጉ ነው ፣ ለወንድሞቻችሁ ለጓደኞቻችሁ አውሩ። Lets break the silence! ብዙህ ወንድሞቻችንን አጥተናል በዚህ ጉዳይ ከዚህ በኋላ ግን ክርስቶስ የሞተላት አንዲት ነፍስ እንኳን መጥፋት የለባትም! እንዲሁም እኅቶች ሆይ ወንድሞቻችሁን check አድርጉ።
❤ 124 ⚡ 7 👏 4 👎 1
17 June 2026
ኪ
19:38
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገረ ትዳር

ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ሊሠራበት ይገባል ብዬ ከማስባቸው ነገሮች አንዱ ጋብቻ እና ትዳር ነው። እንደምናውቀው ጋብቻ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ከሰጠው ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ነው በቤተክርስቲያናችንም ከሰባቱ ምሥጢራት እንዱ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስም ከነገረ ሥጋዌ ቀጥሎ "ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው" ተብሏል። የትዳር ተቋምም "ትንሿ ቤተክርስቲያን" እየተባለ ይጠራል ፤ ምክንያቱም ትልቋ ቤተክርስቲያን እንኳን ምትወጣው ከዚሁ ከትዳር ተቋም ውስጥ ነው። ጤነኛ ትዳር ሲኖር ፣ ጤነኛ ልጆች ይወጣሉ ፤ እነዚህ ልጆችም ለማኅበረሰብ ፣ ለሐገር እንዲሁም ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ ይሆናሉ። ካህናት ፣ ጳጳሳት ፣ ዲያቆናት የሚወጡት ከዚህ የተቀደሰ የትዳር ተቋም ነው። እንዲሁም ሁለት አካላት በፍቅር ተሳስረው አንድ እንዲሆኑ እግዚአብሔር ባርኮ የሰጠው ታላቅ የፍቅር መገለጫ ነው።

ኢትዮጵያ ላይ ግን በጋብቻ ጉዳይ ትልቅ ችግር አለ ፤ እንደምናውቀው አብዛኛው ምዕመን የሚያገባው ከቤተክርስቲያን ውጪ ነው። አሁንም ግን አስረግጠን መናገር ያለብን ነገር ትዳር ዓለማዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ተቋም እንደመሆኑ በእግዚአብሔር ፊት ሁለት አካላትን በጋብቻ ማጣመር የምትችለው ቤተክርስቲያን ብቻ ናት! ትዳር መዛጋጃ ቤት የሚመሠክርልን ተቋም አይደለም ፣ ወይም ማኅበረሰብ የሚመሠክርልን ተቋም አይደለም ቤተክርስቲያን ራሷ በመንፈስ ቅዱስ የምትባርከው ተቋም ነው። ከምሥጢራቱ አንዱ እንደ መሆኑም መጠን መፈጸም የሚችለው ካህን ብቻ ነው ጸጋ መንፈስ ቅዱስም ይወርድበታል ሁለቱንም አካላት አንድ ያደርጋል። ነገር ግን ከቤተክርስቲያን ውጪ የተደረገ ጋብቻ በእግዚአብሔር ፊት ቅቡልነት የለውም!

መንግሥት ጋብቻውን ቢመሠክርል ፣ ማኅበረሰብ ሁሉ ቢመሠክር ፣ 90 ዓመታት አብረው ቢያሳልፉ ፣ ከ10 በላይ ልጆች ቢያፈሩ ፣ ሀብት ንብረት የተባለ ቢያፈሩ እንኳን እውነት ፣ በሰው ምስክርነት ብዛት እና በጊዜ ብዛት ሀሰት ልትሆን አትችልም በቤተክርስቲያን ያልተፈጸመ ጋብቻ በእግዚአብሔር ፊት ቅቡልነት የለውም ስለዚህ ሁለት በአንድ ቤት ውስጥ በዝሙት እንደሚኖሩ ፍቅረኞች ይቆጠራሉ እንጂ እንደ ባል እና ሚስት አይቆጠሩም። እንዲህ ሲባል "ይህን ሁሉ ዓመት አንድ ላይ ኖረን ፣ ልጆች ንብረት አፍርተን አልተጋባችሁም ነው የምትሉን?" የሚል ካለ እንግዲህ እውነት ለሰው እንዲመች ተብሎ አይለወጥም አዎ በዝሙት የሚኖሩ ፍቅረኞች ይባላሉ እንጂ በትዳር የሚኖሩ ባል እና ሚስት አይባሉም ፤ ምናልባት ባለማወቅ ስለሆነ ያኔ የተደረገው ነገር ተጠያቂ ላትሆኑ ትችላላችሁ ነገር ግን ይህን ባወቃችሁ ቅጽበት ማስተካከል ያስፈልጋል።

እንዴት ነው የሚስተካከለው ለሚለው ደግሞ መጀመርያውኑ ጋብቻው ተፈጽሟል ስለማይባል ፤ ለጊዜው ጾታዊ ግኑኝነትን በማቆም (ዝሙት ስለሆነ) በቤተክርስቲያን ንስሐ ገብቶ ጋብቻ በቁርባን መፈጸም ነው። እንዲህ ካልሆነ በስተቀር በቤተክርስቲያን ውስጥ በቁርባን መኖር አይቻልም። ቁርባን የሚፈቀደው ኃጢአትን ማቆም ለወሰነ ሰው እንጂ በዝሙት ውስጥ እየኖረ መቁረብ አይሆንም ፤ ስለዚህ ጋብቻቸው መጀመርያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሳይፈጸም ንስሐ ገብቶ መቁረብ አይፈቀድም። ምናልባት አንዱ ወገን ፈልጎ አንዱ ወገን ካልፈለገስ የሚል ጥያቄ ካለ እሱን እንግዲህ ንስሐ አባትን ማነጋገር ወይም በንስሐ አባት ካልሆነ ጳጳስን በማነጋገር "ልዩ ፈቃድ" መሰጠት ያስፈልጋል እንጂ እንዲሁ በቀላሉ የሚሆን ነገር አይደለም።
❤ 72 👍 9 🥰 1
ኪ
20:36
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
አዲስ ለምትጋቡም እንግዲህ የማያወላውል አቋም መያዝ አለባችሁ ጋብቻችሁ መፈጸም ያለበት በቤተክርስቲያን ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ጋብቻው ከተፈጸመ በኋላ የምትፈልጉትን ዓለማዊ ድግስ ማድረግ ትችላሉ it is fine ነገር ግን ምሥጢሩ የግድ መጀመሪያ ቤተክርስቲያን ውስጥ መፈጸም አለበት። አንዳንዶች በቤተክርስቲያን እኮ ከተጋባን መፋታት አይቻልም ይላሉ ቆይ ታድያ መጀመሪያውኑ መፋታትን ምታስቡ ከሆነ ለምን ትጋባላችሁ? በዓለማዊስ አግብታችሁ ምትፋቱ ከሆነ ኃጢአት ማይሆን ይመስላችኋል? ሌሎች ደግሞ እንዲሁ ቁርባንን ስለሚፈሩ አሁን በዓለማዊ እንጋባና በኋላ እንቆርባለን ይላሉ ፤ ይሄም ደግሞ ኃጢአትን አቅዶ ሠርቶ ንስሐ ገባለሁ ማለት ነው ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም! ደግሞም አሁን በዓለማዊ ብቻ ብትጋቡም በኋላ ጋብቻችሁ በቤተክርስቲያን ሳይፈጸም መቁረብ አትችሉም።

ስለዚህ ዓለማዊው ድግስ አይቅርብኝ ካላችሁ it is fine ችግሩ እሱ አይደለም መጀመሪያ ግን ጋብቻችሁን ቤተክርስቲያን ፈጽሙ።
❤ 74 👎 3
19 June 2026
ኪ
08:33
ኪዳን ዘኢየሱስ
On this day, the church celebrates the commemoration of the honorable Archangel Michael, intercessor of the human race.

May his intercession be with us. Amen.
❤ 165 🔥 3
24 June 2026
ኪ
08:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
እኔ ከሚገርሙኝ ነገሮች ውስጥ የኃጢአትን ይቅርታ ያገኘንበት መንገድ ነው። በሕይወታችን ለሠራናት እያንዳንዱ ኃጢአት ይቅርታ ያገኘነው አንድም እኛ ባደረግነው ነገር አይደለም ፤ እኛ የምናደርግነው ጥቂት ነገር የእግዚአብሔርን ይቅርታ ከሰማያት ለማምጣት (merit ለማድረግ) የበቃ አይደለም ይልቅስ እያንዳንዷ ኃጢአታችን የምትሠረየው በክርስቶስ ሥራ ነው ፤ እግዚአብሔር የኃጢአታችንን እዳ በክርስቶስ ላይ አኑሮታልና። በራሳችን ከፍለን የተሠረየልን ኃጢአት ወይም በራሳችን ሠርተን ያገኘነው ጽድቅ የለም ማለት የኃጢአታችንን ሥርየት ሆነ ጽድቃችንን merit ያደረገው ክርስቶስ ነው ስለዚህም ነው መሢሑ "እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው" የተባለው።

ምን ያህል ርህራሄ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ተደረገልን አስተዋላችሁን?

Note: አንዳንድ ሰው ይሄን አይቶ ፕሮቴስታንታዊ እንዳይመስለው የተጨመረ ማስታወሻ ከፕሮቴስታንቶች ጋር ለኃጢአታችን ሥርየት የሚሆነውን ሥራ የከፈለው ወይም ይቅርታን merit ያደረገው or meritorious cause (ይሄን ቃል ለመተርጎም ይከብዳል) የሆነው ክርስቶስ ብቻ እንጂ እኛ merit ማድረግ እንደማንችል ስምምነት አለን ልዩነታችን የሚሆነው formal cause of Justification ላይ ነው። ማለትም በእግዚአብሔር ፊት የምንቆመው በክርስቶስ ባለን ጽድቅ ነው በሚለውም ስምምነት አለን ልዩነቱ ይህ የክርስቶስ ጽድቅ ለእኛ የሚሆነው እንዴት ነው በሚለው ላይ ነው። ጽሑፉ ሳላስበው ከdevotional'ነት ወጣብኝ ይብቃ በቃ።
❤ 35 👍 1
ኪ
10:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
የክርስቶስን ሥጋ እና ደም መቀበል!

እኔንጃ በወደፊት ሕይወቴ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አላውቅም ነገር ግን ነገ ትሞታለህ ብባል ዛሬ በመሠዊያው መገኘት ነው ምፈልገው። ምናልባት ሌላ የቀረ ጊዜ ካለ ከጓደኞቼ ለመጨረሻ ጊዜ አብሮ ማሳለፍ በማዘን ሳይሆን እንደሌላው ጊዜ እያወራን ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ። ከዚህም የቀረ ጊዜ ካለ ተራራ ነገር ላይ ወጥቼ በዛፎች መሃል አረንጓዴ ትእይንት እየተመለከትኩ ነፋስ እየነፈሰ ጸሐይ ስጠልቅ ለመጨረሻ ጊዜ ማየት።
👏 26 ❤ 21 ❤‍🔥 7 🔥 4 😁 2
27 June 2026
ኪ
12:13
ኪዳን ዘኢየሱስ
ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት መሆኑን አየሁና እኔም የዛሬ 2 ዓመት እዛሁ ቦታ እንደ ነበርኩ ትዝ አለኝ ጊዜው እንዴት ይሮጣል 😄

ብቻ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ እንግዲህ እውነተኛውን ሕይወት ትጀምራላችሁ ከዚህ በኋላ free subscription to life is over 🤛🏿
🔥 51 😁 34 ❤ 11
ኪ
16:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
የምን ቤተ እምነት ተከታይ ናችሁ?
Anonymous poll
- ኦርቶዶክስ 915 votes, chosen vote
- ሉተራን 30 votes
- ሪፎርም 16 votes
- ጴንጤ (ሙሉ ወንጌል ፣ ገነት ፣ ጉባኤ እግዚአብሔር etc) 34 votes
- ባፕቲስት (ቃለ ሕይወት ፣ ሌሎችም) 22 votes
- ተሐድሶ (ቃለ አዋዲ ፣ ማኅበረ አኀው etc) 15 votes
- ኢስተርን ኦርቶዶክስ 16 votes
- ካቶሊክ 10 votes
- ሙስሊም 8 votes
1066 votes
😁 26 ❤ 4
ኪ
20:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
እዚህ ቤት በቃ ኦርቶዶክስ ብቻ ነው ያለው ማለት ነው ሌሎቹንም ጥሯቸው እንጂ
😁 61 👀 9 👍 4 ❤ 2 🤔 1
30 June 2026
ኪ
15:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
አጋንንት በማን ስም ነው የሚወጣው
Anonymous poll
- በኢየሱስ ስም ብቻ 75 votes
- በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ስም 364 votes, chosen vote
- በሥላሴ እና ቅዱሳን ስም 244 votes
- እኔ አላውቅም 45 votes
728 votes
👍 19 👎 9 ❤ 2
4 July 2026
ኪ
20:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
እነምን አመሻችሁ ቤተሰቦች

ራርቶ እና ጠብቆ ሳምንቱን አሳልፎ ለጌታ ቀን ያበቃን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።

ነገ የተወደደ የጌታ ቀን ነው ፤ ለአምልኮ የምንሰበሰብበት ፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም የምንቀበልበት የተባረከ እና የተወደደ ቀን! ከክርስቲያን ወገን የሆነ ማንም ቢሆን ይህን ቀን ቅዳሴ አያስታጉል ፤ ጌዜያቱን ሁሉ ለጥቅማችን የፈጠረ ጌታን የምናመልክበት ቀን ነውና። ይህቺ ዕለት ቀላል አትምሰላችሁ በጉ በሰማያት ካለበት መሥዋዕቱን በምድር ወዳለነው በመሠዊያው በኩል የሚወርድበት ነውና።

ማንም ሰው ከቅዳሴ እንዳይቀር ፤ ከቅዱስ ቁርባንም እንቀበል።
❤ 109 😢 8 🥰 3 😁 1
ኪ
20:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
Salus animarum suprema lex!

ከሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ሕግ የነፍሳት ድኅነት ነው!
❤ 79 🔥 8 🥰 1
5 July 2026
ኪ
15:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
Timeless truth ከመሆኑ በፊት "ኢክተስ" እያለ የነበራችሁ ልጆች ታውቁታላችሁ የቀድሞውን የቻናሉን ባለቤት

አሁን ላይ በአዲስ ቻናል መቷል ከላይ እንደምታዩት ያሉትን iconኦች ይስላል ከነሱም ባለፈ ሌሎች traditional ሥዕሎችን በትዕዛዝ ይሰራል

ከዚህም በተጨማሪ እያመቻቸ ጽሑፎችን ምናምን ይለቅልናል (theology ምሩቅ መሆኑን አትርሱ😁)

እና ቻናሉን እንቀላቀል (ከታች ሊንኩ አለ) ግሩፕም ይከፍታል ሞቅ ሞቅ እናድርግለት

https://t.me/Roha_3
Jo_El
👍 28 ❤ 12
15:06
Jo_El
15:06
Jo_El
7 July 2026
ኪ
05:07
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 2 🤝 1
05:08
In reply to this message
ይሄን ሳየው ትዝ ያለኝ ነገር ምን መሰላችሁ? ብዙህ ጊዜ እውቀቱ ላይ እናተኩራለን እውነት ለመናገር ትክክለኛ ነገረ መለኮት በጣም አስፈላጊ ነው ፣ ምሥጢረ ሥላሴን ፣ ነገረ ክርስቶስን ፣ ነገረ ድኅነትን ፣ ነገረ ቤተክርስቲያንን እነዚህን ሁሉ በትክክል ማወቅ በጣም መልካም ነው። ትክክለኛ ነገረ መለኮት አለመያዝ ከድኅነት ሊያስወጣ ይችላል ለዚያውም ነው ብዙህ መናፍቃን በታሪክ ውስጥ የኖሩት ፤ ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

ነገር ግን ይህ ሁሉ ፍቅር ከሌለ ከንቱ ነው! እውነተኛ ነገረ መለኮት ጥናት የሚጀምረው በክርስቶስ ፍቅር ነው ፤ የሚጠናቀቀውም በክርስቶስ ፍቅር ነው። ይህን ሁሉ እንዴት እንደ ጀመርኩት አውቃለሁ ፤ ምንም ነገር ሳላውም ነገረ ክርስቶስ እንኳ ምን እንደሆነ ሳልረዳ የመጀመሪያ ፍቅሬ ክርስቶስ ነው። በዚያች በመቅደሱ ውስጥ ያነባሁት እንባ ትዝ ይለኛል ወደድኩት ከልጅነቴ ጀምሮ ያሳደገኝን ወደድኩት ፤ ምንም ነገር ሳላውቅ የመኖሬን ትርጉም አገኘሁበት ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና ብዬ በመፈክር ተነሣሁ። ስለ ፍቅሬ ማወቅ ያለብኝን ሁሉ ለማወቅ ጣርኩ ፤ የነገረ መለኮት ጅማሬዬ የጀመረው ከዚህ ነው።

አሁንም ምንም አላውቅም እሱን አውቃለሁ ነገር ግን ከመጀመሪያውም አለማወቅ የተሻለ አለማወቅ ላይ ነኝ ብዬ አስባለሁ ነገር ግን በእርግጠኝነት የማውቀው አሁንም አንድ ነገር ብቻ ነው ፤ ፍቅሬን እወደዋለሁ! ኃጢአተኝነቴን ያሳወቀኝን እወደዋለሁ ፣ የፈተነኝን አሁንም የሚፈትነኝን እወደዋለሁ ፤ ብቀየመውም ባሳዝነውም ግን እወደዋለሁ መነደፍን ተነድፌያለሁ። በመስቀሉ ላይ በደሙ ገዝቶኛል ፤ መጋረጃውን ያለፈው የነፍሴ መልሕቅ ወደ እርሱ ወደ ሰማያት ይስበኛል በማይበጠስ በደም ሰንሰለት የታሠረው የኔ የነፍስ መልሕቅ የእኔ ኢየሱስ ይስበኛል።

ጌታዬ ሆይ ሁሉንም ነገር ልጣ ራሴን እንኳ ልጣ አንተን ግን አታሳጣኝ።
❤ 148 ❤‍🔥 25 🥰 7 😭 2
11 July 2026
ኪ
09:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቦኪሜ ነህ ኢየሱስ ቦኪሜ ነህ ጌታዬ
በእግሮችህ ላይ ይፈሳል የማይቆመው እንባዬ ❤️
❤ 92 ❤‍🔥 12
ኪ
10:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሀገራችን በሰማይ ነው ሚወድቅ የለም የሚረሳ
ሰማያትን እንወርሳለን ከበጉ ደም የተነሳ

ጌታ ኢየሱስ ይቅር ባይ ነው ፍቅር
ምህረት ከቦት በሰማያት ሚኖር
❤ 103
ኪ
13:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ መልሰኝ ፣ ወደዛ ወደ ሕፃንነት እምነት መልሰኝ። ጌታ ሆይ ልቤን ስበረው ወደ ቀድሞው ዘመን መልሰኝ ፤ እየተሯሯጥኩ ወደ መደስህ ወደ ገባሁበት ዘመን መልሰኝ ፤ እየተሽቀዳደምኩ ሥጋ እና ደምህን ወደ ተቀበልኩበት ዘመን መልሰኝ። እኔ አላወኩህም ነበር አንተ ግን አውቀኸኛል ከሕፃንነቴ ጀምሮ በእቅፍህ አሳድገኸኛል። አሁን ግን አደኩና ጌታ ሆይ ረሳህው ፣ በተለያዩ ኃጢአቶችም ወደኩ አንተ የሌለህ ያህል ረስቼህ ሕይወቴን ኖርኩ። ጌታ ሆይ አንተ ግን አሁንም አልተውከኝም በደምህ የገዛኸውን ባሪያ ይጠፋ ዘንድ አልፈቀድክምና በምሕረትህ ጎበኘኸኝ ፍቅርህንም አሳየኸኝ ፣ እኔ ግን ልቤ ደነደነ ያ በልጅነቴ ቁጭ ብዬ ያነበብኩት ፣ ማንበብ የተማርኩበት ቅዱስ ቃልህ ከውስጤ ጠፋ። የየዋሕነት እምነቴን በጥርጣሬ ተካሁት ፣ ክብርህ ከውስጤ ጠፋ። ጌታ ሆይ መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ ፣ አድሰኝ እኔም እታደሳለሁ የቃልህን ፍቅር በውስጤ አድስልኝ።

ጌታ ሆይ ማረኝ ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ ፣ የኔ ነገር በነበር እንዳይቀር ጌታ ሆይ ፣ ጌታን ይወደው ነበር ፣ ቤቱ ይመላለስ ነበር በሚል ታሪክ እንዳልታወስ ጌታ ሆይ ልቤን ስበረውና መልሰኝ። ጌታዬ ሆይ "ቃልህን እወድ ነበር" የምልበት ዘመን እንዳይመጣ የደነደነውን ልቤን ስበረው ፣ ፍቅርህን አታሳጣኝ ይልቅስ በውስጤ ጨምረው እንጂ ጌታ ሆይ። በምኞት ብቻ እንዳልቀር ጌታ ሆይ ማረኝ ወደ ፍቅርህም መልሰኝ። ሌላ የማወጣው ቃላት የለኝምና በቀራጩ ቃል ብቻ "ማረኝ" እልሃለሁና ጌታ ሆይ ማረኝ።

Kyrie eleison ፣ ጌታ ሆይ ማረኝ!
❤ 120 ❤‍🔥 11 😭 10 😢 4 🙏 2
ኪ
20:25
ኪዳን ዘኢየሱስ
ከጌታ ኢየሱስ መለየት ፣ "ጌታን ይወደው ነበር" መባል ፤ ሳስበው ሳስበው ያስፈራኛል በጣም ያለ ጌታማ እንዴት እኖራለሁ ኡፍፍ ያስፈራል በጣም።
🥰 54 ❤ 30 ❤‍🔥 4
12 July 2026
ኪ
05:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ

ዛሬ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለዓለም ለማዳረስ ሕይወታቸውን የሰጡ ሁለቱ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች እና የዓለም ብርሃናት ጴጥሮስና ጳውሎስን እናከብራለን።

የዮና ልጅ ስምዖን ትሑቱና ትምህርት እንኳን ያልተማረው የገሊላዋ ቤተሳይዳ አሳ አጥማጅ ፣ ለእምነት የፈጠነ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት ግንበኞች ቢንቁትም የማእዘን ራስ የኾነውን ዓለት ኢየሱስን  በመመስከር ቤተክርስቲያን የምትመሠረትበት ዓለት (በግሪክ ጴጥሮስ) የኾነ ፣  በዚህም የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ የተቀበለ። ሕይወቱን በሙሉ ለክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያን በመስጠት የክርስቶስን ወንጌል ያለፍርሃት በሰው ሁሉ ፊት ሰበከ ከይሁዳ ተነስቶ ፣ ከዚያም በአንጾኪያ አከባቢዎች ሁሉ ከሰበከ በኋላ ሮም ደረሰና በኔሮን ቄሳር እጅ ይሰቀል ዘንድ ተፈረደበት ። ሮማውያን ስቅላትን እንደ እርግማን እና ውርደት ቢያዩትም ተወዳጁ ጴጥሮስ ግን በመስቀሉ ላይ የታየው የነፍሱ ጌታ ኢየሱስ ነው ፣ከዚህም የተነሳ እኔስ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም በማለት ተዘቅዝቆ እንዲሰቅሉት ጠይቋል ፣ መጀመርያ ከክርስቶስ ጋር መሰቀልን ፈርቶ "ሰውዬውን አላውቀውም" ብሎ ቢክደውም አሁን ግን ልቡ ጸንቶ ለተሰቀለለት ኢየሱስ እርሱም ተሰቅሏል።

ቀናተኛው ሳውል (በሮማይስጥ ጳውሎስ) ከፈሪሳዊው ገማልያል ዘንድ የተማረ ታላቅ የመጻሕፍት ምሁር ለአይሁድ እምነት በጣም የሚቀና ፈሪሳዊና የቤተክርስቲያን ቀናተኛ አሳዳጅ ነበር። ሆኖም፣ ወደ ደማስቆ በሚወስደው መንገድ ላይ በነበረው የኢየሱስ መለኮታዊ መገለጥ፣ ጥልቅ የሆነ ለውጥን አገኘ የተመረጠ ዕቃም ተባለ። በሰማያዊ ብርሃን ታውሮ የኢየሱስን ድምፅ በመስማት ሕይወቱን ለአሕዛብ ወንጌልን በመስበክ ራሱን የሰጠ የክርስቶስ ተከታይ ሆነ። እስራትና ድብደባን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችንና መከራዎችን ተቋቁሞ ዛሬም እኛን የሚያበረታታን የእምነት ውርስ  እነርሱም ውድ የሆኑ መልእክቶቹን ትቶልናል። የመዳንን መልእክት ያለፍርሃት ለሕዝብ ሁሉ ካደረሰ በኋላ  በመጨረሻም ሮም ሲደርስ በኔሮን ቄሳር ሞት ተፈረደበት እርሱ በዘር አይሁዳዊ ቢሆንም በሮሟ ጠርሴስ በመወለዱ የሮም ዜግነት ስላለው ከአሰቃቂው ስቅላት ይልቅ በፈጣኑ አንገትን በሰይፍ መቀላት ይሞት ዘንድ ተወሰነበት ስለዚህም የቤተክርስቲያን አሳዳጅ በመሆን የጀመረውን ሕይወት ለቤተክርስቲያን ተሳዳጅ በመሆን መራና በመጨረሻም እራሱን ለቤተክርቲያን በመሰዋት ፈጸመ። 

የቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም የተሞላ የተባረከ በዓል ይሁንላችሁ።

@KidanZeIyesus

የዛሬ ሦስት ዓመት የተጻፈ repost.
❤ 114
14 July 2026
ኪ
14:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
On this day in 107 A.D., St. Ignatius, who succeeded St. Peter as Bishop of Antioch in 69 A.D., was martyred in Rome. When Emperor Trajan failed to force him to renounce Christianity, he ordered Ignatius to be bound and thrown to the beasts. Yearning for martyrdom, Ignatius refused the believers' attempts to save him. On his way to Smyrna, he wrote to the Christians in Rome:

"I am afraid that your love may be harmful. If you wish to prevent my death, that will not be difficult for you. But allow me to be slaughtered wherever the altar has been prepared. I am wheat which must be ground, to make bread, to be offered to Jesus Christ. Whenever the people will not behold me anymore, I will behold our Lord Jesus Christ."

Upon arriving in Rome, he was thrown to the lions and delivered his soul to the Lord. Believers later carried his body to Antioch with great honor.

May his prayers be with us, and Glory be to God forever. Amen."
❤ 79 🙏 8 🥰 4 🔥 1 💋 1
15 July 2026
ኪ
10:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
F
Faith and philosophy 15.07.2026 08:34:35
[የስነ-ጽሑፍ ትችትና የመጽሐፍ ቅዱስ ተአማኒነት]

ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እስካሁን ድረስ እዚህ ቻናል ላይ በጽሁፍ ስንለቅላችሁና ስንወያይበት የቆየነውን በአዲስ ኪዳን የማኑስክሪፕቶች ታሪክና በጽሑፍ ትችት [Textual Criticism] ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶችን በአንድ ላይ አቀናጅተን ወጥ በሆነ ትንተና መልክ ያዘጋጀነውን አጭርና መሠረታዊ ጥናት አሁን በPDF ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ይህ ጽሑፍ በተለይ በአሁኑ ዘመን በአማርኛ ቋንቋ በስፋት የማይገኙ ነገር ግን ለእውነት ፈላጊው እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ታሪካዊና ስነ-ጽሑፋዊ ምላሾችን በውስጡ አካቷል።

ይህ የመጀመሪያ ሥራችን እንደመሆኑ መጠን ስህተቶች ካሉም ለመታረምና ለማስተካከል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን።

° Tahrif ወይስ Textual Variant:- በዚህ ጽንሰ-ሐሳብ ላይ ያለውን ሰፊ መሠረታዊ የትርጉም ልዩነት።

° ​የተቺዎች ምስክርነት:- መጽሐፍ ቅዱስን በጥብቅ የሚተቸው Bart Ehrman ከታዋቂው ምሁር Daniel Wallace ጋር የደረሱበትን አስገራሚ የጋራ ስምምነት።

° በማርቆስ 16፣ በሉቃስ 22፣ በዮሐንስ 5 እና በዮሐንስ 1፥18 ላይ የሚነሱትን የጽሑፍ ልዩነቶችና የምሁራኑን የመጨረሻ ድምዳሜ።


ይህ ጥናት መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀትና በምሁራዊ መነጽር መመርመር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ጥሩ መነሻ ሰነድ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን። መልካም ንባብ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!

Faith and philosophy


https://t.me/Faithandphilosophy
❤ 34 🥰 3
17 July 2026
ኪ
12:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
እስቲ ይሄን ጥያቄ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስናወራበት ስለነበር እናንተንም ስለሚጠቅም ልጠይቃችሁ።

ያው የሥራ ቅጥር interview ላይ እንደሚታወቀው why should we hire you? አንተን/አንቺን ለምን እንቀጥራለን? የሚል ጥያቄ አይጠፋም ፣ ያኔ እናንተም ያላችሁ አቅም ለሥራው የሚመጥን እንደሆነ ታስረዳላችሁ።

ይሄንኑ ያዙትና ሞታችሁ እግዚአብሔር የገነት በር ላይ ሆኖ ፣ Why should I let you in? ለምን አስገባችኋለሁ? ብሎ ቢጠይቃችሁ ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ?
❤ 25 😢 15 👌 5
ኪ
14:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ይሄ ጥያቄ ምን ለማሳየት መሰላችሁ ከጓደኛዬ ጋር ስናወራም መልሷ የነበረው "በንስሐ ሕይወት ስለምመላለስ ስለምቆርብ ፣ ሕጉን ለመጠበቅ የተቻለኝን ነገር ስለማደርግ" የሚል ነበር። ይሄ መልስ የአንዳንድ ኦርቶዶክሳዊያን ሊሆን ይችላል ብዬ ገምታለሁ ይሄ ግን ስህተት ነው።

እዚህ መልስ ላይ focus የሆነው "እኔ" የሚለው ላይ ሆነ "እኔ በንስሐ ሕይወት ስለተመላለስኩ" "እኔ ስለቆረብኩ "እኔ ሕጉን ስለጠበኩ" ስለዚህ ከእግዚአብሔር ክፍያን መጠየቅ ይሆናል "በንስሐ ሕይወት ስለተመላለስኩ ፣ ስለቆረብኩ ፣ ሕግህን ስለጠበኩ የሚገባኝን መንግሥት ክፈለኝ" ማለት ይሆናል። ይሄ ደግሞ እግዚአብሔርን ባለ ዕዳ ማድረግ ነው ምክንያቱም "ለሚሠራ ደሞዙ ይገባዋልና" ተብሏል አንድ አሠሪ ሠራተኛውን ካሠራው በኋላ ፣ ለሠራተኛው ባለ ዕዳ ነው ደመወዙን ሊከፍለው ግድ ይላል ፣ ሠራተኛውም በሕግ ሊከሰው ይችላል።

ነገር ግን ትክክለኛው ኦርቶዶክሳዊ ዕይታ focusኡን ከእኔ ላይ አንሥቶ "አንተ" ላይ ማድረግ ያስፈልጋል። ለምን ገነት አስገባሃለሁ? የሚል ጥያቄ ከተነሣ ከሁሉም በላይ አጭሩ መልስ "ልጅህ ስለ ኃጢአቴ ሞቷልና ፣ ባፈሰሰው ደሙም ገዝቶ የራሱ አድርጎኛል ፣ ወደ አንተም አቅርቦኛል ፣ የልጅህ ደም ለእኔ የፈሰሰው በከንቱ አይደለም ይልቅስ ስለ እኔ ድኅነት ነው ፣ እኔ ባልድንስ የልጅህ ደም ለከንቱ ይሆናልና አምላኬ ሆይ ስለ ተሰቀለው ልጅህ ፣ ስለ ታረደው ልጅህ ፣ ስለ ሞተህ ልጅህ ማረኝ ፣ በቅዱስ መንፈስህም ወደ አተምከኝ የርስቴ መያዣ በሆነው በቅዱስ መንፈስህ መንግሥትህን አድለኝ" የሚል ሊሆን ይገባል። እዚህ ላይ አንድም "እኔ ስላደረኩት" የሚል ነገር የለም ይልቅስ ሁሉም ነገር "ለእኔ ስላደረክልኝ" ነገር የሚል ነው። እኛ ምንም እንኳን ብንሠራ ምን ተብለናል? "እኛ የማንጠቅም ባሮች ነን ፣ የሠራነው መሥራት የሚጠበቅብንን ብቻ ነው" በሉ ተብለናል። መንግሥቱን ለመውረስ ማንድረግ የሚጠበቅብን ነገር አለ ፣ ነገር ግን መንግሥቱ የሚሰጠን ስላደረግነው ነገር ሳይሆን ስለ ሰጪው መልካም ፈቃድ ነው። ስለዚህም ነው መንግሥተ ሰማያት የሥራ ክፍያ ሳትሆን የሰጪው መልካም ስጦታ ናት የምንለው።

በጌታ እና በባሪያ ምሳሌ ተረዱት ፤ አንድ ባርያ ጌታውን ሁሉን ነገር በመሥራት ፣ የሚጠበቅበትን ሁሉ በማድረግ ያስደስተዋል ስለዚህ ጌታው በዚህ ይደሰትና ነጻ ይለቀዋል። ይህ ጌታ ባሪያውን ስላደረገው ነገር ብሎ አይደለም ነጻ ያወጣል ከራሱ በጎ ፍላጎት የተነሣ እንጂ ምክንያቱም ባሪያው ምንም ቢሠራ የሠራው የሚጠበቅበትን ነው ፣ ጌታው ለሠራው ነገር ደሞዙ ምግብ እና ማደሪያ እንጂ ነጻ መለቀቅ አይደለም ፣ ነጻ መለቀቁ ፈጹም ስጦታ ነው።

ለመዳን እንሠራለን ማለት እና ስለ ሠራን እንድናለን ማለት ልዩነት አለው። ደህና ዋሉ።
❤ 90 🔥 4 🙏 4 👎 2 👏 2 🥰 1 🤔 1
ኪ
21:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
ያለ ልክ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያረገው
ከስም ሁሉ በላይ ስምን የወረሰው
እንመሠክራለን ኢየሱስ ጌታ ነው
እንመሠክራለን ኢየሱስ ጌታ ነው
❤ 126 🔥 11 ❤‍🔥 5 🙏 5
18 July 2026
ኪ
21:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
እሑድን ለክርስቶስ!
ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የጌታን ቀን በጌታ ቤተክርስቲያን!
❤ 75 💯 4 🔥 3
20 July 2026
ኪ
20:36
ኪዳን ዘኢየሱስ
መንፈሳዊ ትምህርት በርቀት እና በ online መማር ለምትፈልጉ (ሐገር ውስጥም ከሐገር ውጪም ላላችሁ) በሙሉ ፣ ከ 25 ዓመት በላይ በማስተማር የሚታወቀው መንበረ መንግሥት ጊቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የርቀት ትምህርት ማዕከል አመቺ በሆነ የትምህርት ፕሮግራም ይጠብቃችዃል።

ለበለጠ መረጃ

0953191919 / 0921599344

https://t.me/amdehaymanotdistance
❤ 36
22 July 2026
ኪ
20:24
ኪዳን ዘኢየሱስ
ኢላሂ ኢላሂ ሊመዘ ተረክተኒ
❤ 24 🥰 5 😢 2
ኪ
20:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ማለት ነው። ብቻ ጌታዬን ኢላሂ ብዬ ስጠራው ደስ ይለኛል የኔ አምላክ ፣ ረቢ ፡ የኔ ጌታ ፣ እርሱ ነው። የጌታዬ የአምላኬ የመድኃኒቴ የልቤ ውድ የሆነ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እርሱ ነው። በተወዳጁ ልጁ በኩል ኢላሂ ፣ ኢላሂ እያልኩ እጠራዋለሁ። አንድ ችግረኛ እግዚአብሔርን ጠራው ፣ እግዚአብሔርም ሰማው ከመከራውም ሁሉ አዳነው የሚለው መዝሙር ውስጤ ያቃጭላል ለምን እንደምጠራው አላውቅም ነገር ግን ዝም ብዬ ኢላሂ ኢላሂ እላለሁ። ቃላት ማውጣት ይጠበቅብኛል እንዴ? አባቴ ነው በአንድያ ልጁ በኩል ወልዶኛል የምፈልገውን ገና ሳልጠራው ያውቃል ፤ ደግሞም ለአንድያ ልጁ እንኳ ያስራራ አሳልፎ የሰጠኝ ጌታ በመከራዬ እንዴት ይተወኛል?

"ኢላሂ ኢላሂ ሊመዘ ተረክተኒ" እያለ አንድያ ልጅህ በመስቀል ላይ የጮኸው ጩከት አምላኬ ሆይ የኔ ነውና ጌታዬ ሆይ በተሰቀለው ልጅህ ፣ በታመመው ፣ በሞተው ፣ በክብር በተነሣው እና በቀኝህ ሆኖ በመስቀሉ ችንካሮች ፊትህ በሚታይልኝ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እለምንሃለሁ።

ኢላሂ ኢላሂ ለተትሩክኒ!
❤ 112 🥰 12 ❤‍🔥 4
30 July 2026
ኪ
10:55
ኪዳን ዘኢየሱስ
Ergamoonni samii irratti maqaa kee ni faarfatu; Kiruubeel 'Qulqulluu, Qulqulluu, Qulqulluu' jedhanii yommuu galateeffatan, Suraafeelis sagaduun siif bitamu. Nutis ilmaan Addaam lafa kana irratti, hanga uumamni afaan qabu hundinuu 'Iyyesuus Gooftaa dha' jedhee ragaa ba'uun jala keetti bitamutti, Kiristoos isa fannifame ni lallabna.
❤ 71 🥱 10 👎 1 🙏 1
31 July 2026
ኪ
18:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? (መኃ 3፡3)

ፍቅር ይዞኛል ሊያውም ነፍሴ ከሥጋዬ ልትለይ እስኪመስለኝ ድረስ ነፍሴን የሚያከንፋት ፣ ከምድር ተለይቼ ወደ መሠወርያው ሊያደርሰኝ የሚያቃጣኝ ፍቅር ፣ ነፍሴ ወዳዋለች ኹለመናው በልቤ ላይ ነግሧል ካፈቀረኝ እስከሞትም በመስቀል ላይ እርቃኑን ከኾነልኝ ከርሱ በልቤ ላይ ቤቱን ከሠራው ንጉሥ ፍቅር ይዞኛል!! ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? እንደ በረዶ ነጭ ልብስን ለብሷል ከፀሐይ በላይ ደምቆ ይታያል በደም ያጌጠ ልብስ አለው ክብሩ ዓለማትን ሞልቷል እንደ ታረደ በግ በዙፋኑ ተቀምጧል።

አዎ እርሱ ነው ነፍሴ የወደደችው እርሱ ነው በኃጢአቴ ጠፍቼ ነበር ወደ ሞትም መንገድ ሄጄ ነበር ነፍሴ የወደደችው እርሱ ግን አገኘኝ በቆሻሻ ማንነት ኾኜ አገኘኝ እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስም ወደደኝ በውድ ዋጋ በደሙ ገዛኝ ውዴ አገኘኝ እኔም አገኘሁት በመሠዊያው ላይ አገኘሁት ከሥጋው እየቆረሰ ሲመግበኝ አገኘሁት ከሆዱም እያፈለቀ ሲያጠጣኝ አገኘሁት ነፍሴ ወደደችው ተገዛችለትም እርሱ የሰማይና የምድር ንጉሥ ነው ስሙም ከስሞች ኹሉ ከፍ ያለ ኢየሱስ ነው።

"እኔ የወዴ ነኝ ውዴም የእኔ ነው፤ በሱፉ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።" (መኃ 6፡3)

Reposted because I love this post ❤️
❤ 144 ❤‍🔥 13 🥰 11 😭 3 🔥 1
6 August 2026
ኪ
11:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
“ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።”
— መኃልየ. 5፥10
❤‍🔥 97 ❤ 28 🥰 5
ኪ
11:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
የኔ ኢየሱስ

ቃሉን ስጠራው በእርሱ ውስጤ በደስታ ይሞላል ፡ የእኔ ኢየሱስ እንዴት ደስ ይላል ናተይ ኢየሱስ ፡ Iyyasus koo ፡ My Jesus ፡ ኢየሱስ ዚአየ ብደጋግመው የማይሰለች ቃል ከልቤ የማትለይ ንጉሥ ፡ መቼ እንደገባህ አላውቅም ነገር ግን ልቤ ይወድሃል ፤ በምን እንደተቆጣጠርከኝ አላውቅም ነገር ግን ልቤ ተነድፏል ፤ እወድሃለሁ የሚለው ቃል ውስጤ ያለውን ስሜት ሊገልጽልኝ አይችልም፡፡

ጌታዬ ሆይ እስካይህና አንድ ጊዜ ብቻ እቅፍ እስከ አደርግህ እናፍቃለሁ፡፡ የኔ ጌታ የልቤ ወዳጅ ምን ብዬ ልግለጽህ ፍቅር ነህ ብልህ ያንስብሃል ፡ ቅዱስ ነህ ብልህም ያንስብሃል ፡ ጣፋጭ ነህ ብልህም ያንስብሃል፡ የምገልጽህ ቃል የለኝም ጌታዬ ቃሌ አንተው ነህ፡፡

ማሕያዊ የእግዚአብሔር ቃል ሆይ ቃል ሁነኝና እስቲ ላመስግንህ ፡ የእግዚአብሔር የቀኝ ኃይሉ ሆይ እስቲ ኃይል ሁነኝና ፍቅሬን ልግለጽልህ፡፡ በሰማያት ከፍ ከፍ ያልከው ሆይ ወደ መሠወሪያህ ንጠቀኝ፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ ፊትህን አሳየኝ ፤ አንድ ጊዜ ብቻ ከዛ እስቲ ልቤ ይረፍ ነፍሴ የወደደችውን ታዋይህ፡፡ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን እንደምትኖር አውቃለሁ ፤ ለሙሴ ፊቴን ሰው አይቶ አይድንም እንዳልከው አውቃለሁ ነገር ግን ጌታ ሆይ የኔን ሥጋ ለብሰሃል በእመቤታችን ቅድስት ድንግል በኩል ተዛምደናል ፡ አንድ ጊዜ ፊትህን አሳየኝ ፡ አንድ ጊዜ ብቻ!!

ነቢዩ ‘እናየው ዘንድ ደም ግባት የለውም’ እንዲል አውቃለሁ ነገር ግን ይህ የሆነው ስለ እኔ ነው ፡ ስለ እኔ መዳን በጥፊ የተመታ ፊትህን ልየው ጌታ ሆይ ያን ጊዜ በጥፊ ስለአስመታህ ኃጢአቴ ይበልጥ አለቅሳለሁ፡፡ የእኔ ኢየሱስ ሆይ ይህ አይገባህም ነበር መገባት አልፎ አይመጥንህም ነበር ፤ አንተ ግን ክብርህ ያደረከው የእኔን መዳን ነው ፡ ክብርህ የአባትህን ፈቃድ መፈፀም ነው ፡ እርሱም ሁሉን ለእግዚአብሔር መዋጀት ነው ፤ እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ ፤ ከዚህ ሁሉ ውስጥ ግን አንዱ እኔ ነኝ ጌታዬ ሆይ ለአባትህ ክብር በቅዱስ መንፈስ ዋጀኝ የኔ እንዳልኩህ ያንተ አድርገኝ ፤ ኃጢአቴን በቅዱስ ደምህ ፈሳሽነት አስወግድ ሁለመናዬ የአንተ ይሁን አምላኬ እኔም ‘በገዛ ደሙ ዋጀኝ ስሙ ይክበር ይመስገን’ ብዬ ላውጅልህ፡፡ ጌታ ሆይ መወደድ ይገባሃል ኢየሱስ ሆይ መመስገን ይገባሃል ፤ የልቤ ወዳጅ ሆይ ጉልበት ሁሉ ሊንበረከክልህ ምላስም ሁሉ “ኢየሱስ ጌታ ነው” ብሎ ሊመሰክርልህ ይገባሃል፡፡ ያልቀመሰህ ፍቅርህን ማን ያውቃል? ፍጥረት ሁሉ ይነደፍ በፍቅርህ ይቃጠል ኢየሱስ ሆይ በሰው ሁሉ ልብ ተወደድ ዝቅ ዝቅ ብለሃልና ይገባሃል!

ታርደሃልና ይገባሃል!

በመቅደሱ ስለ እኛ ትቆማለህና ይገባሃል!

ኢየሱስ ሆይ ይገባሃል!

የእኔ ክርስቶስ ሆይ ይገባሃል!!

የኔ ኢየሱስ ሆይ ክበርልኝ!!
❤ 116 🔥 38 ❤‍🔥 14 🥰 6 😢 2
8 August 2026
ኪ
13:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሱስ ሆነህብኛል … ኢየሱስ

Oh my Lord Jesus you have my ultimate devotion, you captivated my heart.

https://youtu.be/9Lrr_XLIgmw?si=OQXgmlMOHgKEJAfE
❤‍🔥 47 ❤ 26 😁 4 😐 4 😈 1
12 August 2026
ኪ
12:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
አምስቱን የኦሪት መጻሕፍት የጻፈው ማነው?
Anonymous poll
- ሙሉ በሙሉ ሙሴ 215 votes
- አብዛኛውን ሙሴ ሌሎች ጨመሩበት 196 votes
- ጥቂቱን ሙሴ አብዛኛው ከተለያዩ ጸሐፊያን የተሰበሰበ 32 votes
- ከሙሴ የመጣ ትውፊትን ይዟል እንጂ ሁሉም የተጻፉት በተለያዩ ሰዎች ሆነው ከምርኮ በኋላ ተሰበሰቡ 68 votes, chosen vote
- ከሙሴ የመጣ ትውፊትን ይዟል እንጂ ሁሉም የተጻፉት በተለያዩ ሰዎች ሆነው ከምርኮ በፊት ተሰበሰቡ 43 votes
- ከሙሴ የመጣ ምንም ትውፊት የለም ሁሉም ከተለያዩ ጸሐፊያን የተሰበሰቡ ናቸው። 10 votes
564 votes
❤ 4
14 August 2026
ኪ
10:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይደንቀኛል ዘላለም የሰለጠነ ስም ሰምቼ
❤ 63
ኪ
10:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
አ
አምላከ ብርሀን 14.08.2026 07:46:34
"ኦ አብ በእንተ ኢየሱስ ርድአነ ፤ ክርስቶስ ሃበ አቡከ ሄር አማህጽነነ ፤ መንፈሰ አብ ወወልድ ናዝዘነ "

ሰአታት ዘሌሊት ስብሐተ ፍቁር ❤

"አብ ሆይ ስለ ኢየሱስ ብለህ እርዳን፤ ክርስቶስ ሆይ ወደ አባትህ አደራ አስጠብቀን( አማልደን) ፤ የአብ እና የወልድ መንፈስ ሆይ አፅናናን"

@amlake_birhan
@waaqa_ifaa
❤ 83 ❤‍🔥 16 🔥 3
ኪ
12:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 42 🔥 17
15 August 2026
ኪ
12:08
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 46 🥰 6
ኪ
18:30
ኪዳን ዘኢየሱስ
My favorite book from the Old Testament : Ecclesiastes
From the New Testament: Hebrews
❤ 52 💯 4
ኪ
21:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
ደህና እደሩ፤ ነገ የጌታ ቀን መሆኑን አትርሱ። የጌታን ለጌታ ስጡ፣ ቅዳሴ ተሳተፉ፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀበሉ። እሁዳችሁ የበራ ይሆናል። ክርስቲያን ናችሁ፤ ይሄን መቼም አትርሱ። ለተጠራችሁበት አጠራር ታምናችሁ ኑሩ። ክርስቲያን የጌታን ቀን ያከብራል፣ ጌታንም ይቀበላል። ማንነታችሁን መቼም አትርሱ፤ ዜግነታችሁ ሰማያዊ ነው። ስለዚህም ዜግነታችሁ ሰማያዊ እንደሆነ ሰው ኑሩ። በጌታ ቀን በቅዳሴው ሰማይ ውስጥ ተገኙ፤ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ቆሞ ይጠብቃችኋልና!
❤ 132 🔥 12 👍 2 😭 1
17 August 2026
ኪ
13:31
ኪዳን ዘኢየሱስ
T
Timeless Truth 17.08.2026 13:13:29
በአሁኑ እሁድ በአባ አንጌሎስ የተሰጠ ስብከት ነው ... ከቻልኩኝ ከዚህ በኋላ በየሳምንቱ አጋራችኋለው

እናም በጣም አሪፍ ትምህርት ነበር ትወዱታላችሁ [ኪዳን ይተረጉምላችኋል😁]

ድምጹን እና የካሜራ አንግሉ እየተስተካከለ ይመጣል

https://youtu.be/AFSc5h-ld_M
❤ 41 👍 2 👏 2
18 August 2026
ኪ
09:37
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 37
ኪ
20:20
ኪዳን ዘኢየሱስ
ደ
ደቂቀ አትናቴዎስ አማርኛ 18.08.2026 19:12:48
ሰላም እንዴት ናችሁ ?

እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። በእውነቱ በዚህ መልኩ ባልጽፍ እመርጥ ነበር ሆኖም ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ውስጥ ስለገባን ነውና በእርግጥ ልጁ እንዲህ እንድጽፍ አይፈልግም ብቻ ግን አንድ የእኛ ቲም አካል የሆነ ልጅ በጽኑ ታሟልና ለህክምና ብዙ ገንዘብ አስፈልጎታል። በሚኒ ባስ ዕርዱን እያለን ከምንወጣ የቻላችሁትን ያህል ብታግዙን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

በዚህ አካውንት -> 1000750539697  
Lwam Gebregeorgis Tesfay
❤ 55 ❤‍🔥 5 🥰 1
19 August 2026
ኪ
11:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 26
11:33
In reply to this message
ያው በአሁኑ ጽሑፍ መጻፍ ባልችልም የምርቴን መዝሙር ስሙበት በጌታ ኢየሱስ የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ።
❤ 72 ❤‍🔥 8 👏 1
20 August 2026
ኪ
17:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
😁 23 😡 4 ❤ 3 👍 1 😨 1
17:11
In reply to this message
ትናንት ያለምንም context ያልኩት እንደዚህ ዓይነት ስብከቶች ስለበዙብኝ ነው ከዲያቆን ዮርዳኖስ የሚጠበቅ ነው ነገር ግን ሁሉም ቦታ አለ even በጣም የማከብረው ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ እንዲህ ሲናገር በብስጭት ስሜት ነው የተጻፈው።

ቤተክርስቲያን አሁን ልትሠራበት የሚገቡ በጣም ብዙ ችግሮች አሉ ምዕመኑ የስም ክርስቲያን ብቻ ሆኗል፣ ወጣቱ በዝሙት አልቋል፣ ብዙ ጋብቻዎች ከቤተክርስቲያን ውጪ ናቸው፣ በየቦታው ክርስቲያን እየተገደለ ነው፣ ንስሐ አባቶች ከእውቀት እጥረት የተነሣ ምዕመኑን በእረኝነት መያዝ አልቻሉም፣ አብዛኛው ምዕመን መሠረታዊ ትምህርት እንኳን ስለማያውቅ በሌላ እምነት እየተነጠቀ ነው፣ ካህናት በቂ ትምህርት አይሰጣቸውም ከአብነት ትምህርት የሚወጣው ሰውም የዘመኑን ችግር address ማድረግ አይችልም በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን crisis ላይ ናት።

ነገር ግን ይህ ሁሉ ነገር እያለ መምህራኑ የሚያተኩሩት ትናንሹ ነገር ላይ ነው ስለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ አሁን ቢወርድ ግመልን ትውጣላችሁ ትንኝን ታጠራላችሁ ይላቸዋል ያልኩት። ፈሪሳዊነት በጣም ተጭኖናል ከንቱ ኩራት የትም አያደርስም ሁላችንም የቤተክርስቲያን መሪዎች ጨምሮ በንስሐ ካልተመለስን እንደ ሶርያ እንጠፋለን።

ስለዚህ እንመለስ እንመለስ እንመለስ (እኔ ውስጥ የተጨነቁ ሰዎች የያዟቸው ጥያቄዎች ራሱ በጣም እያስጨነቁኝ ነው ደግሞ እኮ ብዙ ናቸው እና በቃ ያለንበት ሁኔታ ያሳዝነኛል ቤተክርስቲያኔ ታሳዝነኛለች የጌታ ሙሽራ ናት እኮ ግን የወንበዴዎች ዋሻ እያደረጓት ነው ጌታ ሆይ ቤተክርስቲያንህን ጠብቅ። ጌታ በሚያውቀው ደግሞ እኔ ለቤተክርስቲያኔ ሁሌ ደኅንነትን ነው የምመኘው አብባ ማየት ነው የምፈልገው ጸሎቴ ውስጥ አለች ሁሌ ልቤ አላረፈም አርፎ አያውቅም Coptic መጥቼም አርፎ አያውቅም ሕዝቤ ያደግሁባት ቤተክርስቲያኔ ታሳዝነኛለች ጥሩ እንድትሆን ነው የምፈልገው ውስጤ እያንዳንዷን ቀን በጭንቀት ነው የሚያሳልፈው እና መከራ በሚቀበልበት ነገር ጥላቻ አለብህ ሲባል ውስጤ ነው የሚደማው ነገር ግን ልብን እና ኩላሊትን የሚመረምር ጌታ ሁሌ ስለቤተክርስቲያኑ የምጮህበት ጌታ ሁሉን ያውቃል እና ምንም አልልም።

ለቤተክርስቲያን ጸልዩ ለቤተክርስቲያን ጸልዩ ለቤተክርስቲያን ጸልዩ!
❤ 133 🥰 13 😢 5 🥱 5 🕊 3 🤝 3 👍 2 🔥 1 😈 1
22 August 2026
ኪ
10:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
መላእክት ቅድስት ሥጋዋን ወደ ሰማይ አሳረጉ የሐዲስ ኪዳኗ ታቦት ሥጋዋ እንዲበሰብስ ክርስቶስ አልፈቀደምና።
እንኳን አደረሳችሁ!
❤ 175 🥰 11 😁 1
23 August 2026
ኪ
21:22
ኪዳን ዘኢየሱስ
አ
አሚነ ተዋሕዶ 23.08.2026 20:46:56
ኢዩአችን 🤝 ይሄንን ሙሉ ቪዲዮ ለማየት ተመዝግባችሁ አናግሩኝ😅 የምር ግን እዚህ ጉሩፕ ላይ ያላችሁና ውጪም ሆናችሁ እዚሁ በርቀት ወይም በ e learning መማር የምትፈልጉ ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ይጠብቃችዃል። በውስጥ አውሩኝ!

ኢዩአችን ግን በጣም በጣም ከምታስቡት እጅግ የተለየ ሰው ነው፣ ጌታ አብዝቶ ይባርከው!
🥰 44 ❤ 15 🤣 7 😁 2 🤗 1
26 August 2026
ኪ
08:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/bG15GzXnWW8?si=P7ShnUldVclatIXr

Uff zare sew lkolgn I can’t stop listening to this mezmur. Where have you been all my life 😭
❤ 22 🔥 3 💯 2 😁 1
ኪ
10:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
አባት ሆይ በአንድ ልጅህ አባት ሆይ በምትወደው ልጅህ በዮርዳኖስ በመሰከርክለት እስከ ሞት በታዘዘልህ ላማ ሰበቅታኒ ብሎ በጮኸው ጩኸት በትንሣኤው እና በእርገቱ በፊትህ ባቀረበው መስዋዕት ስለ እኛ በሚታይልን መታየት ይዘንሃል አባት ሆይ በአንድያ ልጅህ ማረን በተሰቀለው ልጅህ ማረን መስዋዕታችን ልጅህ ነው የሚያጽናናን መንፈስህ ነው በማይነገር መቃተት በውስጣችን ስለሚጮኸው መንፈስህ ስትል ማረን።

አንድ ልጅህን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ያራራህለት ስለምንድነው? ስለ እኛ ድኅነት አይደለምን? ስለዚህ የምህረት ዋስትናችንን በምትወደው በአንድያ ልጅህ አድርገናል ሁሉን ቻይ አብ ሆይ በምትወደው ልጅህ ማረን። የውስጣችንን ጸሎት ሁሉ ታውቃለህ ሊቀ ካህናታችን ያሳርገዋልና ስለዚህ አባት ሆይ በፊትህ የምናቀርበው አዲስ ጸሎት የለንም አንድ ልጅህን ጸሎታችን አድርገን እናቀርብልሃለን እንጂ።

አባት ሆይ በምትወደው አባት ሆይ በአንድ ልጅህ!
❤ 100 🙏 4 😭 2 🤷‍♂ 1
27 August 2026
ኪ
10:10
ኪዳን ዘኢየሱስ
የእሁድ እሁድ ቅዳሴ ተሳትፏችሁ እንዴት ነው?
Anonymous poll
- በየሳምንቱ emergency ካላጋጠመኝ በስተቀር አልቀርም። 151 votes, chosen vote
- በየሳምንቱም ባይሆን በተቻለኝ መጠን እሄዳለሁ። 96 votes
- በተቻለኝ መጠን እሄዳለሁ ግን ቅዳሴ ከተጀመረ ከነጋ በኋላ እንጂ ከመጀመሪያ አልደርስም። 122 votes
- ከስንት አንዴ እርሱንም ከተጀመረ በኋላ። 47 votes
- ኧረ ጭራሹኑ ከቅዳሴው ርቄያለሁ። 156 votes
572 votes
😢 25 ❤ 8
28 August 2026
ኪ
09:29
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
የዚህ ፖል ውጤት በጣም ያሳዝናል እውነት እውነቱን እንነጋገር ከተባለ እሁድን ሳያስቀድስ የሚውል ክርስቲያን አይደለም! እውነታው ይሄ ነው። የመሳለም ክርስትና የሚባል ነገር የለም፣ የምንሳለመው ቤተክርስቲያን ለማስቀደስ እና ለመማር ስንሄድ ነው እንጂ መሳለም በራሱ ግብ አይደለም።

ችግሩ እኮ እየሞከሩ የተቸገሩ ሰዎች መኖራቸው አይደለም ነገር ግን እሁድን አለማስቀደስ normalize አድርገው እየኖሩ ያሉ ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው የሚጠሩ ሰዎች አሉ። ከቅዳሴ ርቀሽ የምን ክርስቲያን ነኝ የምትዪው? አንተስ እሁድ ቅዳሴ እንሂድን ስትባል የምትሰንፍ ራስህን ክርስቲያን ብለህ የምትጠራው በምን አፍህ ነው?

አስተውሉ እንጂ ሰዎች ማንነታችሁ እኮ ታላቅ ነው የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፣ የተመረጡ የንጉሥ ካህናት ናችሁ ለምንድነው እንደ ማንኛውም ሰው የምትኖሩት? የተጠራችሁት እኮ ከክርስቶስ ጋር በሰማያዊ ስፍራ ለመቀመጥ ነው ለምንድነው እንደ ምድራዊ ሰው የምትኖሩት? ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ቆሞ ወደ አለበት ቅዱሳን ሁሉ በህብረት በበጉ እግዚአብሔርን ወደ ሚያመልኩበት ወደ ተከበረው ቅዳሴ ኑ! ይሄ ምክር አይደለም ትዕዛዝ ነው ኑ! የእኔ ትዕዛዝ አይደለም የኢየሱስ ትዕዛዝ ነው ኑ! ቅዳሴ እግዚእ እንደሚለው ደግሞ ከኢየሱስ ትዕዛዝ ልዩ የሆነ ቢኖር ይወገድ!
❤ 101 ⚡ 3
29 August 2026
ኪ
09:06
ኪዳን ዘኢየሱስ
ትናንትና በጣም የተጨናነቀ ቀን አሳልፌ ረሳሁት እንጂ ነሐሴ 22 የታላቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘኤጶን የዕረፍቱ መታሰቢያ ነበር።

ቢያልፍም ግን የምወደው ቅዱስ ነውና ስለእርሱ መናገርን አልተውም ፤ የእናቱ የቅድስት ሞኒካ እምባ ፍሬ አውግስጢኖስ! የመምህሩ የቅዱስ አምብሮስ ፍሬ አግስጢኖስ! የምዕራቧን ቤተክርስቲያን ነገረ መለኮት ደረጃ ከፍ ያደረገ አውግስጢኖስ!

የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በታላቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ምልጃ ማረን ራራልንም ፤ የእርሱን የንስሐ ዕምባም ስጠን በፊትህ አንተ ጥንታዊውም አዲሱም ውበት ሆይ አንተን ለማፍቀር አረፈድኩ ብለን በፊትህ እንደፋ ዘንድ።

ጌታ ሆይ ነፍሳችን በአንተ እስክታርፍ ድረስ አናርፍም ቅዱስህን በአንተ አሳርፈኸዋል እኛንም እንዲሁ አሳርፈን ወደ ቅዱሳንህ አንድነት ወደ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ዶሮ ጫጩቶቿን እንደምትሰበስብ ሰብስበን ስለ ታላቁ ቅዱስህ አውግስጢኖስ ተማጽነንሃል ጌታ ሆይ ማረን!
❤ 108 🤔 6 🙏 2 👍 1 🤬 1
ኪ
21:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
ነገ እሑድ ነው ፣ የጌታ ቀን ነው!

እንዴት ደስ ይላል የጌታን ሞትና ትንሣኤ መታሰቢያ እናደርጋለን ፤ ክርስቶስም እንዳለው በመንግሥቱ ዳግም እስኪገለጥ ድረስ ሞቱን እንናገራለን እንዲሁም ትንሣኤውን እንመሠክራለን። ይህ ቀን የቤተክርስቲያን የበዓሏ ቀን ነው በደስታ እና ሐሴት በየተራራው እና ኮረብታው ጥግ የተበተንን ምዕመናን አንዱን እንጀራ ክርስቶስ ለመቁረስ የምንሰባሰብበት ፤ "ክርስቶስ ተነሥቷል!" ብለን የምናውጅበት እንዲሁም ክርስቶስ ተነሥቶ በሰማያዊው ስፍራ በአብ ቀኝ እንደተቀመጠ እኛንም በእርሱ እንዳስቀመጠን አስበን የምንመሰክርበት ፤ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ወደ ገባባት ሰማያዊቷ መቅደስ እኛም በቤተክርስቲያን በኩል የምንገባበት ፤ ሊቀ ካህናቱ ራሱ ሆኖ ለአባቱ መሥዋዕት ሆኖ ወደ ሚቀርብበት ሰማይ የምንገባበት ታላቅ ቀን ነው እሑድ የጌታ ቀን!

ቅዳሴ አትናቴዎስ ስለዚህች ቀን ክብር ሲናገር "የበዓላትን በኵር ኑ ከፍ ከፍ እናርጋት ፤ ኑ እናመስግናት ፤ ኑ እናክብራት ፣ ኑ በዓል እናርጋት ... በእርሷም ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ እንደ ነቢዩ እንደ አሳፍም በረዳን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ እያልን እንዘምር ... በነቢዪ በዳዊት መዝሙር በታወቀች በበዓላችን ቀን በእውነት ሃሌ ሉያ እንበል... ይህቺ ዕለት አብ የቀደሳት ወልድ የባረካት መንፈስ ቅዱስ ከፍ ከፍ ያደረጋት ናት በእርሷም ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት" እያለ ያመሰግናል።

እናንተ የክርስቲያን ወገኖች ሆይ ኑ! ግድ የለም ኑ በዚህ ቅዱሳን ሁሉ ተሰብስበው አሉ ኑ! በዚህ ታቦት ዘዶር እመቤታችን አለች ኑ! በዚህ አስቀድሞ ሰማያትን ያለፈ መጋረጃውን የገባ የእምነታችን ጀማሪ እና ሐዋርያ የሚሆን የፍጥረታት ሁሉ ኤጲስ ቆጶስ የሚሆን ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ አለ ኑ! የቤተክርስቲያን የደስታ ቀኗ ነው ኑ! ቤተክርስቲያን ሠርግ ጠርታችኋለች ሙሽሪቷ ከዓለም ዳርቻ ሁሉ ትሰበሰባለች ከመንፈሷ ጋርም ሆና ሙሽራዋን ና! እያለች ትጠራዋለች በናፍቆትም ትጠብቀዋለች ስለዚህ እናንተ የክርስቶስ ሙሽሮች ኑ! ወደ ሰርጉ አዳራሽ ኑና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ማራን አታ እንበል አሜን ጌታ ኢየሱስ ይምጣ!

የክርስቲያን ወገን የሆነ ሁሉ ይህን ጥሪ ችላ እንዳይል!
❤ 103 🥰 5
30 August 2026
ኪ
21:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
ብቻ ሳጠናቅቀው ይሄን ዓመት ብዙህ የሚሠራ ነገር እንዳለ ሠራተኛው ግን ጥቂት እንደሆነ አይቻለሁ ስለዚህ በብዙህ projects መምጣት እንዲሁም ከስር ቲም መቅረጽ ምናምን በደምብ መሠራት እንዳለበት አምናለሁ ነገር ግን ታገሱኝ ክርስቶስ ኃይል ከሆነኝ እኔም ሙሉ አቅሜን ለቤተክርስቲያን ነው መስጠት የምፈልገው እስከዛው ግን ኪዳነ ማርያም እያላችሁ ጸልዩልኝ።
❤ 102 ⚡ 4 👍 2 🕊 2 🙏 1 🤝 1
31 August 2026
ኪ
05:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
በዓለም ላይ ለመናገር በጣም ከባዱ ቃል ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?

"እወድሃለሁ" የሚለው ቃል። ለእርሱ ክብር ይግባውና ጌታ ኢየሱስን "እወድሃለሁ" ብሎ እንደመናገር የሚከብድ እና የሚያም ቃል የለም። ለምን? በራሱ ቃል "ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ" ብሏልና።

እኔ ግን የማልጠቅም ባርያ ነኝ ለጌታዬ ትዕዛዛት ሁሉ የማልገዛ ይልቅስ በተደጋጋሚ ትዕዛዙን የምተላለፍ ፣ በውስጤ ኃጢአት እንጂ ምንም የጽድቅ ሥራ የሌለ ፣ ከልቤ ተርፎ በአፌ የሚወጣው ክፋት ብቻ ነው። ኢየሱስ ያዘዘውን አላደርግም በተቃራኒው ደግሞ አታድርግ ያለውን አደርጋለሁ ፤ ውስጤ የተከፈተ መቃብር ቢሆንም በኖራ እንደተለሰነ ግድግዳ በሰው ፊት ነጭ መስዬ እታያለሁ ነገር ግን ውስጤ በኃጢአት የጨቀየ ጠቋራ ነው። የሥጋዬን ፈቃድ ለማስደሰት ብቻ ሠራለሁ ፤ ሥጋዬንም ከመግዛት ይልቅ በምቾት አጠግበዋለሁ ኃጢአትን ደም እስከ ማፍሰስ ልዋጋ ይቅርና ተመቻችቼው እየኖርኩ ነው። ታድያ እንዴት ደፍሬ "ጌታ ኢየሱስ ሆይ እወድሃለሁ" እላለሁ? የሽንገላ ቃል አይሆንብኝምን? ስለዚህም ይከብዳል ስለዚህም ያማል።

ታድያ ይህ ማለት ጌታዬን ነፍሴ ያነባችለትን መድኃኒቴን አልወደውም ማለት ነውን? እንዲያስ ከሆነ ተወዳጁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ "ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን።" ይላል ይሄ ቃል እርግማን ብቻ አይደለም ግሪኩ ἀνάθεμα (Anathema) ይላል የውግዘት ቃል ማለት ነው። ታድያ እኔ ራሴን ክርስቲያን ብዬ የምጠራ የክርስቶስ ኅብረት የተወገዝኩ ከሆነስ ምን ይውጠኛል? ነገር ግን መናኙ ልቤ ሌላኛውን ተወዳጅ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስን አሰበ ጌታን ሦስት ጊዜ ከካደው በኋላ ስምዖን ጴጥሮስ ሆይ ከእነዚህ ሁሉ አብልጠህ ትወደኛለህን? ብሎ ሦስተኛ ጊዜ ሲጠይቀው ጴጥሮስም አዘነና "አንተ ሁሉን ታውቃለህ እንደምወድህም ታውቃለህ" ብሎ መለሰለት። ተወዳጁ ሐዋርያ ጴጥሮስ ሆይ እስቲ ልጠይቅህ ጌታ ኢየሱስ ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ ብሎ አስጠንቅቋችሁ ሦስት ጊዜ ከካድከው በኋላ መልሰህ ሦስት ጊዜ "እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ" ብለህ የመናገርን አቅም ከየት አገኘኸው?

ልቤ በሁለቱ ሐዋርያት መሃል ተሰነጠቀ ስለዚህ ተመልሼ ወደ ተወዳጁ ሐዋርያ ጳውሎስ ተመለሰ እንዲህ የሚለውን ቃልም ሰማ "የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱን አላደርገውም። የማልወደውን ግን የማደርግ ከሆንሁ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ። እንደዚህ ከሆነ ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም፥ በእኔ የሚያድር ኃጢአት ነው እንጂ።" ጳውሎስ ሆይ በሕግ ስር ሳለን ሕጉ መልካም ቢሆንም በእኛ ውስጥ የሚያድር ኃጢአት ስለሆነ የኃጢአት ባርያዎች ነን እንበድላለን አልክን ይህስ ምን ማለት ነው ታድያ "ጌታ ሆይ እወድሀለሁ" ለማለት የሚያስችለኝን ድፍረት ከየት አመጣዋለሁ? በክርስቶስ አምኜ በደሙ ተዋጅቼ ከመንፈሱ ተጠምቄ ለአባቱ ልጅ ካልሆንኩ በቀር? ይህስ እንዴት ይቻላል ብዬ ሌላኛውን በጌታ የተወደደ ሐዋርያ ስጠይቅ "የልጁ የክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል!" ሲል በኃይለ ቃል ነገረኝ አሁን ገና ገባኝ!

በራሴ ኃጢአተኛ እና በደለኛ ትዕዛዙን የማልጠብቅ ነኝ ነገር ግን በክርስቶስ ደም ተዋጅቼ ተቀድሻለሁ! በራሴ ሞቻለሁ በክርስቶስ ግን ተነሥቼ በሰማያዊ ስፍራ ተቀምጫለሁ! በኃጢአት ስኮነን በክርስቶስ ጸድቄያለሁ! በራሴ ትዕዛዙን የመጠበቅ ኃይል የለም ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ግን ሁሉን እችላለሁ! አዎ አሁን ገና ተረዳሁ ለካስ "ጌታ ኢየሱስ ሆይ እወድሃለሁ" ብዬ መናገር የምችለው ራሱ በራሴ አይደለም በክርስቶስ ነው እንጂ! ደስ ሲል በራሴ ሳይሆን በክርስቶስ ጸጋ ተማምኜ ለማለት የሚከብደውን እና የሚያመውን ቃል "ጌታ ኢየሱስ ሆይ እወድሃለሁ" ብዬ በድፍረት እናገራለሁ! ክርስቶስን የምወደው ራሱ ከራሴ የተነሣ አይደለም ከክርስቶስ የተነሣ ነው እንጂ ስለዚህም "እወድሃለሁ" ባልኩት ጊዜ የራሱን ፍቅር ለራሱ እየመለስኩ ነው እንጂ የኔን ፍቅር አይደለም በኔ ፍቅር ውስጥማ ኃጢአት ሞልታለች ነገር ግን ብዙህ ኃጢአት ባለችበት የእግዚአብሔርም ጸጋ እንዲሁ ትበዛለች።

ውዴ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በሱፍ አበባዎች መካከልም መንጋውን ያሰማራል!
❤ 108 ❤‍🔥 7 🔥 4
ኪ
09:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
እዚህ ያልበሰለ ኋላ ቀር ማኅበረሰብ ውስጥ የለመደውን ልማድ እዛም እንዲሁ በሴት እንደፈለኩ ተጫውቼ አመልጣለሁ በሚል ሞክሮ ተጨፍድዷል።

በሐገራችን ውስጥ ያለው የሴቶች ጥቃት እኮ ቆጥረን የማንጨርሰው ነው ጭራሽም normalize የሆነ ነው እንዳውም ጥቃት ተጠቅቻለሁ ብላ የምትወጣ ሴትን የሚያሸማቅቅ ማኅበረሰብ ነው ያለን ስለዚህ በጣም በግፍ የወጡትን ብቻ ነው እንጂ የሰማነው ስንት በዝምታ የያዙት እነርሱ ተጠቅተው ግን እነርሱ ራሳቸው በዝምታ የሚሰቃዩ ብዙህ እኅቶቻችን አሉ። ደሞ እዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ እያለ ሃይማኖተኛ ነን ፣ መንፈሳዊ ነን ይልልኛል ፤ ኢትዮጵያን የሞላው የስም ሃይማኖተኛ ብቻ ነው እንጂ ግፋችን ተቆጥሮ አያልቅም በተለይ ደግሞ ኋላ ቀርነታችን ሲያስጠላ ፤ እነዚህ ኋላ ቀር ሰዎች ደግሞ በቤተክርስቲያንም ስለሚገቡ በእነርሱ ምክንያት ቤተክርስቲያን ትሰደባለች ኤዲያ።

በክርስትናችን እንኮራለን ነገር ግን ከንቱ ትምክህት ከእኛ በላይ ግፍ ሠሪ የለም። በተለይ ደግሞ በሴቶች ጥቃት ጉዳይ እንደዚህ አይነት ጎጂ እና ኋላ ቀር አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች እዚሁ ከተማ ያሉ ናቸው ፣ የገጠሩንማ ሆድ ይፍጀው።

የተወደድሽ እኅቴ ሆይ አይዞኝ ለእያንዳንዱ ድርጊቱ ሰው የሚወጣበት እና በፍርድ ወንበር ፊት የሚመልስበት ቀን ይመጣል ፣ አውቃለሁ የኢትዮጵያ ፍርድ ወንበር መልስ እየሰጠ እንዳልሆነ ነገር ግን በዚህ ምክንያት ተስፋ አትቁረጪ ከክርስቶስ ፍርድ ወንበር የሚያመልጥ ማንም የለምና!
❤ 86 😢 10 🤝 5 ❤‍🔥 1 💘 1
ኪ
13:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
በሕይወታችሁ ደስተኛ ናችሁ?
Anonymous poll
- አዎ በጣም 86 votes
- አዎ ከነችግሮቼም ቢሆን ደስተኛ ነኝ 250 votes
- ኤህ ያው ከመሞት መሰንበት ነው 65 votes
- ባልተፈጥርኩ ይሻለኝ ነበር ነገር ግን መውጫ ስለሌለ እየኖርኩ ነው 54 votes
- ባልተፈጠርኩ ይሻለኝ ነበር አሁን ሞትን ፍለጋ ላይ ነኝ 21 votes, chosen vote
476 votes
😁 18 ❤ 8 😢 5 🤣 1
ኪ
17:51
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰሞኑን በውስጥም፣ በስልክም፣ በአካልም ብዙ ልጆች እርዳታ እየጠየቃችሁኝ ነው። ጥያቄዎችም ሆነ ሌላ፣ እውነት ለመናገር ሁላችሁንም አንድ በአንድ ብረዳ ደስ ይለኛል፤ ለቤተክርስቲያን ጥቅም ነው። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ጊዜዬ ስለማይፈቅድ፣ please ተጨማሪ request ባይመጣ ደስ ይለኛል።

ይሄ ግን እስካሁን የጠየቃችሁትን አይመለከትም፤ እናንተን በውስጥ እናወራለን። ነገር ግን አዳዲስ requests ማስተናገድ ከአቅሜ በላይ ነው even መጽሐፍ ላክልኝ ወይም ጥያቄ መልስልኝ ራሱ። በጣም አስቸኳይ እና አንገብጋቢ ጉዳይ ከሆነ ብቻ በውስጥ ኑና በስልክ እናወራለን፤ እንጂ ሌላው ለጊዜው ይቁም። ቻናል እና ግሩፕ ላይ active ሆኜ ብታዩኝም፣ በትክክል ለጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ስጀምር ራሴ እነግራችኋለሁና እስከዛ ድረስ ታገሱኝ።

እውነት ለመናገር እነዚህ ነገሮች ይበልጥ በተቀናጀ መልኩ በፕሮጀክት መምጣት እንደሚያስፈልጋቸው ነው የተረዳሁት። ከዲያቆን (https://t.me/zeathanAmharic) ጋርም በዚህ ጉዳይ ላይ ስንመክርበት ነበር፤ ወደፊት በደንብ ተዘጋጅተንበት እንመጣለን። ብቻ እስቲ እግዚአብሔር ይርዳን ለሁሉም ነገር።
❤ 48 👍 3 👏 2
1 September 2026
ኪ
15:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
L
Loidi 01.09.2026 14:17:43
AAU፣ASTU እና AASTU ለመግባት አስበዋል ? ሁሉም ሰው እዚህ እንገባለን ብሚልበት ሰዓት እና ውድድሩ ባየለበት ሰዓት የአምና እና ካቻምና ፈተና ሳይሰሩ ሊገቡ ነው? ለዚህ ትልቅ መፍትሄ uatprep.com ይዞ መጥቷል።
👉 የ2016፣2017 እና አይቀሩም የተባሉ ከፈተናው ጋ related የሆኑ የAAU UAT ፈተና ከነ ሙሉ Explanation! 
👉 የ 2007፣ 2016፣ 2017 እና  related የASTU  እና AASTU መግብያ ፈተና ከነ ሙሉ Explanation! 

ይዘንላችሁ ብቅ ብለናል።
👉 በቅርብ ደሞ ከሰዓት በፊት እና ቡኋላ የነበሩ ፈተናዎችልዩ ልዩ ተደርገዉ ይለቀቃሉ!

ለጓደኛዎ፣ ለልጆው እና ለወዳጅዎ ሼር አድርገው በትላልቆቹ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲማሩ እድሉን ያመቻቹ!

https://uatprep.com/
❤ 24 🔥 6
ኪ
15:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ክርስቲያን ወንድም እህቶችን እናበረታታ።
❤ 44
ኪ
22:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
"የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል" ማር 13፡14
❤ 41
6 September 2026
ኪ
18:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓመቱ የመጨረሻ እሑድ እነሆ ተፈጸመ

በዓመት ውስጥ 52 እሑዶች ነበሩን ፣ ከ365 ቀናት 52ኡ የጌታ ናቸው እና ለጌታ ስንቱን ሰጠን?
እንዲህ ስል የእሑድ ክርስቲያኖች ብቻ ሆነን እንድንቀር አይደለም በእኛ ዘንድ ካሉ ብዙህ ችግሮች አንደኛውን አንስቼ እንጂ ክርስትና በየዕለቱ በየደቂቃው የሚኖር ነው። ክርስቲያን ተብለን የተጠራነው በእውነትም ክርስቶስ በእኛ ስላለ ነው ስለዚህም እንደ ተጠራንበት ስም ልንኖር ግድ ነው ያለበዚያ ክርስቲያን ተብሎ መጠራቱ አይጠቅመንም ይልቅስ የክርስቶስን ስም በዓለም እናሰድባለን እንጂ።

እውነተኛ ክርስቲያን የምንሆነው እንዴት ነው? ማኅተብ ስላሰርን? ነጠላ ስለለበስን? በክብረ በዓላት ቀን ቤተክርስቲያን ስለምንሔድ? ነጭ ልብስ ተጎናጽፈን ጧፍ አብርተን "አቤት የኦርቶዶክስ ውበቷ" ስላልን? የቤተክርስቲያን ሕንፃ ስላሠራን? ስለምንጾም? በመስቀል ምልክት ስለምናማትብ? ቅዱሳንን ስለምንዘክር? ይህ ሁሉ ከልብ ፍቅር ካልተደረገ ከንቱ ነው! እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ ነጠላ ለብሰን አደባባዩን ስለሞላነው በዚህ አይታለልልም! ይልቅስ እንደ እሥራኤል ይህ ህዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው ብሎ ይከሰናል እንጂ። ትላልቅ ሕንፃዎች ስላለን ፣ አደባባዩን በነጭ ልብስ ስለሞላነው ፣ ደመራችን በዩኔስኮ ስለተመዘገበ ፣ በጥምቀት ጎርፍ ሆነን ስለወጣን በቃ ክርስቲያን ሆነን እግዚአብሔርን ያስደሰትን ይመስለናል አይደል? ነገር ግን እግዚአብሔርን የእያንዳንዱን ልብ እና ኩላሊት ይመረምራል ፣ ከነጩ ልብስ ኋላ ያለውን የክፋት ልብ ያያል ፣ ከበዛው ሕዝብ መሃልም ለእርሱ የተመረጡትን በቁጥር ያውቃቸዋል ፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየኖሩ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሌሉ ሰዎች ወዮላቸው በፍርድ ቀን ክርስቶስ ሁሉን ይገልጣልና ፣ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ አይቀርም ፣ ነጭ ልብስም ሳያረጅ አይቀርም እግዚአብሔርን የሚፈራ ልብ ግን ለዘለዓለም ይኖራል።

እውነተኛ ክርስትና የሚጀምረው ከውስጥ ነው ፣ ክርስቶስን በእርግጥ ልባችን ውስጥ አለ? ከክርስቶስ ጋርስ ጥብቅ የሆነ ግኑኝነት አለን? እግዚአብሔርን በሚፈራ ሕሊናስ ምሥጢራትን እንቀበላለን? ሰው ከልብ በሌለው እምነት እና በእምነት በሚፈጸሙ ምሥጢራት በኩል ካልሆነ በቀር ሊድን አይችልም። ስለዚህ ለተጠራንበት ስም የታመንን እንሁን ክርስቲያን ተብሎ መጠራት ማንም በየመንገዱ እንደሚያንቋሽሸው ቀልድ አይደለም ፣ ስሙ የከበረ ነው እኛማ አቀለልነው ነገር ግን እውነተኛ ክርስቲያንስ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰለጠኑ እና የተመረጡ ናቸው ፣ እነርሱ ናቸው ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ላይ የተጻፈው ፤ ለዛ ስሙ ክርስቲያን ተብሎ ለሚጠራ ነገር ግን በሕይወት መጽሐፍ ላይ ላልተጻፈ ሰው ወዮለት!

እስቲ እውነተኛ ክርስቲያኖች እንሁን ፣ ከልባችን ንስሐ እንግባ ፣ እግዚአብሔርን በቅዳሴ እናምልከው ፣ ክርስቶስንም ከመሠዊያው እንቀበለው ፤ በየቀኑ ይህን ማድረግ ቢያስፈልገንም ቢያንስ ግን ዕለተ እሑድ የጌታ ትንሣኤ ናትና እስቲ የቀጣዩን ዓመት 52 እሑዶች ሁሉ ለጌታ እንስጥ ፣ በቅዳሴው እንገኝ ፣ የእግዚአብሔርን ቃል እንካፈል ፣ እግዚአብሔርን እናምልክ ፣ በእውነተኛ ንስሐ በገባ ልብ ቅዱስ ቁርባንን እንቀበል። የቻልን ከእሑድ በመቀጠል የጌታ በዓላትን እንዲሁ ለጌታ እንስጥ የሚችል ከዚህ በላይም ይጨምር ጊዜ ያለው ጊዜውን በሙሉ ለጌታ ቢሰጥ መልካም ነውና። ነገር ግን በሌሎች ጊዜ የሌለውም ቢሆን ባለበት ሥራም ሆነ ትምህርት እንዲሁም ማኅበራዊ ሕይወት ሁሉንም ቀናት እንደክርስቲያን ይኑር የመዳን ቀን አሁን ነውና! አዎ የክርስትና ሕይወትም ሆነ ዓለማዊ ሕይወት ከባድ ነው ነገር ግን በራሳችን ሳይሆን ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ሁሉን እንችላለን ፤ በእኛ ውስጥ በሚሠራ መንፈስ ቅዱስ ፍሬን እናፈራለን። ነገር ግን ሰው ነንና ብንወድቅም በሰማያት ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት አለልን ስለዚህም በእውነተኛ ልብ ንስሐ ብንገባ በደሙ እንነጻለን ዳግመኛም ክርስትናን የመኖርን ኃይል እናገኛለን ፣ ብናረጅ እንታደሳለን። ብቻ ሕይወታችን ከመሠዊያው ስር አይራቅ የዓመቱን ፍጻሜ በመሠዊያው እንደፈጸምን የዓመቱንም ጅማሬ መሠዊያው ስር እንጀምር በጌታ ቀናትም ሁሉ ወደ እርሱ እንቅረብ ለክርስቲያን ከክርስቶስ መሠዊያ ስር በቀር ሌላ መኖሪያ ቦታ የለውምና!

ማንነታችሁን ሁል ጊዜ አስታውሱ ክርስቲያን ናችሁ ፣ ክርስቲያን ናችሁ ፣ ክርስቲያን ናችሁ!
❤ 73 😢 4 👍 1
ኪ
19:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
አዲሱ ዓመት ለሐገራችንም ለቤተክርስቲያንም መልካም እንዲሆን ጸልዩ የሚታየው እና የሚሰማው ነገር ሁሉ መልካም አይደለም እኔ በውስጤ ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ታላቅ ጥፋትም እየመጣብን ነው የሚል ድምጽ ያቃጭልብኛል ስለዚህ ሁላችንም እስቲ እንጸልይ በእውነተኛ ንስሐ እንመለስ "ነነዌ ትገለበጣለች" እንደተባለው ኢትዮጵያ ትገለበጣለች ሳንባል እንመለስ በተለይ ደግሞ ለክርስቲያን ጥሩ ጊዜ የሚሆን አይመስልም እና ሐገራችን እንድ ሶማልያ የሙስሊም ሐገር እና የጦርነት ስፍራ ከመሆኗ በፊት እንንቃ!
🥰 37 ❤ 25 💯 9 🕊 6 🙏 2 🍓 1
ኪ
20:02
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዓመቱ መጨረሻ ላይ ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ የክርስቶስን ዳግመኛ መምጣት እና የዓለምን ፍጻሜ ታስባለችና ይሄን መዝሙር ተጋበዙልኝ የሁላችንም የልብ ናፍቆት ጌታ ነው ማራን አታ!

ማራንኣታ ኢየሱስ
ማራንኣታ ንጉሰይ ❤️

https://www.youtube.com/watch?v=3LljM8Vprs0
❤ 44 🕊 4
8 September 2026
ኪ
11:26
ኪዳን ዘኢየሱስ
On this day, the church celebrates the commemoration of the honorable Angel Raphael, the third of the Archangels, and the dedication of his church outside the city of Alexandria. During the time of Pope Theophilus, the twenty-third Patriarch, a faithful woman came from Rome, with her children and had with her a picture of the honorable Archangel Raphael. She had inherited much money from her husband. She revealed to the Pope her desire to build many churches. He showed her a large heap, which was in front of the patriarchate, which she removed and built a church in its place. Then she built another church in the name of the Angel Raphael, which was consecrated on this day.

May the intercession of this honorable angel be with us and Glory be to our God forever. Amen.
❤ 73 🥰 5 🙏 5
ኪ
15:19
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ
ቀሲስ መዝገቡ ካሳ
ቀሲስ ግርማ ባቱ
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
❤ 72 🔥 8 👏 3
ኪ
19:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://youtu.be/3aeVw-D3hWw?si=-f2Q8TClAXkZu3Ai

Zemari Bereket Tkue fever 🥶

Where have you been all my life ❤️
❤ 18 😁 4 ❤‍🔥 2 👍 1
9 September 2026
ኪ
17:27
ኪዳን ዘኢየሱስ
This is Confession Planner App.

ይህን አፕ አውርዱና ንስሐ ከመግባታችሁ በፊት ራሳችሁን መርምሩበት ይጠቅማችኋል በጣም። እናንተ ያላያችሁትን ሳይድ ሁሉ ያሳያችኋል። የሰሩትም ኮፕቲኮች ስለሆኑ የኛው የኦርቶዶክስ ነው።

ለአንድሮይድ ኮመንት ስር ሊንክ አስቀምጥላችኋለሁ ለአይፎን ደግሞ አፕስቶር ላይ ስለምታገኙት “confession planner” ብላችሁ ሰርች አድርጉ።
❤ 43
10 September 2026
ኪ
09:15
ኪዳን ዘኢየሱስ
❤ 26
ኪ
20:52
ኪዳን ዘኢየሱስ
2018 እነሆ አበቃ ይህ ዓመት እናንተ ጋር እንዴት ነበር?

እውነት ለመናገር ለእኔ የሕይወቴ ከባዱ ዓመት ነበር ይህ ዓመት ጌታ ኢየሱስ ባይኖር በቃ አልኖርም ነበር። እንዲሁም በቤተክርስቲያን በኩል ያገኘኋቸው ጓደኞቼ ብቻ ሳይሆኑ በቃ ቤተሰቦቼ የምላቸው እውነትም የክርስቶስ ልብ ያላቸው ናቸው ጌታ እነርሱን ባይሰጠኝ እኔ ዓመቱን አልጨርስም ነበር ብቻ ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።

ሕይወት ባዶ ሲመስል ፣ የመኖር ተስፋን ስናጣ የማይተወን ተስፋችን ግን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አለ። በራሳችን ለመቆም ስንሞክር ብንወድቅም እርሱ ግን እያነሳን አለ ፤ በፈተና ውስጥ እያለፍን ብንሰበርም እርሱ ግን እየጠገነን አለ ፤ አቅም አጥተን ወደፊት መራመድ ቢያቅተንም እርሱ ግን ኃይል እየሆነን እየመራን አለ። የእውነት ጌታ ኢየሱስ በሕይወታችን ውስጥ አለ! በዚህ ዓመት የችግርን ሁሉ መጨረሻ ባይም የጌታዬን የመጨረሻ እርዳታም አይቼበታለሁ ፤ 2018ን የጀመረው ኪዳን እና 2019ን የሚጀምረው ኪዳን አንድ አይደሉም ጌታ በእሳት ውስጥም ቢሆን ሠርቶኛል ፤ ጌታ ሆይ ስለ እሳቱ ባማርርም ስለ አንተ ግን አመሰግናለሁ!

አዲሱን ዓመት በክርስቶስ እንቀበል ፤ ዓመታት ያልቃሉ ፣ ዓለምም ትጠቀለላለች ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ትናንትም ዛሬም ለዘለዓለሙም ያው ነው ፣ ዓመታቱ ከቶ አያልቁም ፣ ቃል ኪዳኑንም አያጥፍም ሁላችንን ወደ እርሱ እስኪስበን ድረስ ስለእኛ ቆሟልና በተስፋ እርሱ ላይ እንጣበቅ እርሱ ተስፋችን ነውና። እውነት ለመናገር ይህንን ስል እውነት ላይመስላችሁ ይችላል ነገር ግን ይህን ዓመት በሕይወት ተስፋ የቆረጥኩባት ዓመት ነበረች በጣም በብዙህ ነገር ተፈትኛለሁ በተለይ ከጥር ጀምሮ እያንዳንዱ ቀን ስቃይ ነበር ለመኖር ምንም ጉጉት እና ተስፋ አልነበረኝም ፣ እምነቴንም ፣ ሕይወቴንም እስካጣ ደርሼ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬም አለሁ ዓመቱንም አልፌ ቀጣዩን ልጀምር ነው እምነቴም እንዳውም ከመጀመሪያው ይበልጥ ጠንክሯል። ይህ ሁሉ የሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ፣ ሁሉም ነገር በጨለመ ተስፋ አጥቼ ሞትን በተመኘሁ ጊዜ ብቸኛ ተስፋዬ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ከሞት አድኖኛል አሁንም እያኖረኝ ነው ፣ እውነት ለመናገር በኢየሱስ ላይ ያለኝ እምነት ባይኖር ኖሮ በሕይወት አልኖርም ነበር ስለ ቸርነቱ ጌታ ይመስገን!

ብቻ እንኳን ጌታ በሰላም ዓመቱን አስፈጸመን።
❤ 143 🔥 6 🥰 2
11 September 2026
ኪ
21:01
ኪዳን ዘኢየሱስ
አዲሱን ዓመት በክርስቶስ ምሕረት ጀምረናል ካለፈው ይልቅ ጥሩ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን።
❤ 161 🙏 24 💯 8
13 September 2026
ኪ
20:17
ኪዳን ዘኢየሱስ
ἐν Χριστῷ ❤️
❤ 37 ☃ 2
ኪ
20:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
"በክርስቶስ"

ህልውና ያገኘነው በክርስቶስ ነው ፤ ሕይወት ያገኘነው በክርስቶስ ነው ፣ ሞተን ሳለን የተነሣነው በክርስቶስ ነው ፣ ጠፍተን ሳለን የተገኘነው በክርስቶስ ነው ፣ ወደ ሲኦል ወርደን ሳለን ከፍ ከፍ ያልነው በክርስቶስ ነው ፣ አሁንም በኃጢአት ስንወድቅ የምንነጻው በክርስቶስ ነው ፣ በመጨረሻው ዘመንም መንግሥቱን የምንወርሰው በክርስቶስ ነው ፣ ዓለም ሳይፈጠር የተመረጥነው በክርስቶስ ነው ፣ ለእግዚአብሔር የሆነው በክርስቶስ ነው ፣ እግዚአብሔርን የምናመልከው በክርስቶስ ነው ፣ ለእግዚአብሔር የተዋጀነው በክርስቶስ ነው ፣ በሰማያዊ ስፍራ የተቀመጥነው ስለ እኛ ተቀዳሚ ሆኖ በገባው በክርስቶስ ነው ፣ የሕይወታችን ምሥጢር ሁሉ ያለው በክርስቶስ ነው ፣ ሁሉ በእርሱ ፣ ለእርሱ እና ስለእርሱ ተፈጥሯልና።

በክርስቶስ ❤️
❤ 131 ❤‍🔥 4 🔥 3 🥰 2 👍 1 👏 1 🤔 1
14 September 2026
ኪ
14:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

እኛ በክርስቶስ መሢሐዊ መንግሥት የተሰበሰብን መሢሐውያን ክርስቲያኖች የመንግሥቱ የመጀመሪያ አባል የሆነችውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናከብራለን ጉልበታችን ሁሉ የሚንበረከክለት መሢሐችን ከእርሷ ተገኝቷልና። በእርግጥም አምላክ ሰው የሆነባት እና የእግዚአብሔር ድኅነትም ወደ ሰው ልጆች እንዲመጣ የተመረጠች ምርጥ ዕቃ ለማሕየዊ የእግዚአብሔር ቃል መጻፊያ ሰሌዳ የሆነች የሐዲስ ኪዳን ጽላት እመቤታችን ናትና እናከብራታለን ከፍ ከፍም እናደርጋታለን። እመቤታችን በቅድስናዋና በትሕትናዋ እና በፍጹም መታዘዟ የእግዚአብሔር ልጅ ማደርያ በመሆን ለራሷም ሆነ ለዓለም ሁሉ የድኅነት ምክንያት ሆናለችና እናመሰግናታለን እርሷንም እንደ ትውልድነታችን ብጽዕት ናት እያልን እያመሰገንን ከእርሷ ጋር መድኃኒቴ ላለችው መድኃኔ ዓለም እንገዛለን ለመንግሥቱ በገዛ ደሙ ዋጅቶናልና።

ከዚህም የተነሣ "ወላዲተ አምላክ" በሚል ቃል ልትጠራ የተገባች ሆናለች። ይህ ቃል ምን ያህል የከበረ መሆኑን አስቡት ከፍጡራን ወገን አምላክን የወለደ አካል ማንም የለም ነገር ግን እርሱ እግዚአብሔር አብ ብቻ ቅድመ ዓለም አምላክን የወለደ ከእውነተኛ አምላክነቱ የተነሣ እውነተኛ አምላክን ያስገኘ ብቸኛ አካል ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አብ ቅድመ ዓለም ወልዶ "አንተ ልጄ ነህ" ብሎ ለጠራው አካል እንዲሁ በሥጋ "ልጄ" ብላዋለችና በምሳሌ መነጽር እግዚአብሔር አብን መስላለች ፤ ግብሯም እንዲሁ እንደ አብ ግብር "ልጄ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" የሚል ነውና በግብሯም መስላዋለች ፤ ለክርስቶስስ ክብሩ የእግዚአብሔር አብን ፈቃድ እስከ መስቀል ድረስ በመፈጸም ላመኑበት ሁሉ ድኅነት ይሆን ዘንድ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም "እነሆኝ የጌታ ባርያ" በማለት ለዚሁ ለእግዚአብሔር አብ ፈቃድ ተገዝታለችና "ያመነች ብጽዕት ናት" እንላታለን። በእርግጥም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያመነች ብጽዕት ናት ፣ በእምነትም ከክርስቲያን ወገኖች ተቀዳሚ ናት ፣ መድኃ ኔዓለምንም ከሁሉ በፊት "መድኃኒቴ" ብላዋለች ከሁሉም አስቀድማ እርሷ ድናለች እና ብጽዕት ናት። ይህ ክብር ከፍጡራን ወገን ለማን ተሰጠ? ለማንም ስለዚህም ነው እመቤታችን ክብሯ ከፍጡራን ሁሉ ይበልጣል ከሱራፌል እና ኪሩቤልም ትልቃለች በጌታ ዘንድም የከበረች ናት የምንለው።

በከበረች በአምላክ እናት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይማረን።
❤‍🔥 79 ❤ 21 🥰 15 👍 1 🤔 1
ኪ
19:00
ኪዳን ዘኢየሱስ
ሰሞኑን ከእኛ ቤተክርስቲያን በኩል ካህናት እና ዲያቆናት የሆኑ ሰዎች ፌሚኒስቶች "የሴቶች ጥቃት ይቁም" ብለው የትሰማ challenge በማስጀመራቸው በጣም ብዙህ ያልተገባ ንግግር ሲናገሩ እያየሁ ነው። ፌሚኒዝምን መቃወማቸው እሺ እሱ ችግር የለውም ነገር ግን ፌሚኒዝም ላይ ያሳዩትን ይህን ኃይል ለምን የሴቶች ጥቃት መከላከል ላይ አያውሉትም? መጀመሪያውኑ ቤተክርስቲያን ጥሩ ሰርታ ጥሩ ክርስቲያኖችን ብታፈራ ኖሮ እኮ የሴቶች ጥቃት ጥያቄ ራሱ ባልተነሣ ነበር። ከሁለት መጥፎ አንድ መጥፎ መምረጥ ነው ይሄ ብለው የሚያስቡ ካሉም ለምን ሁለቱንም ሲቃወሙ አንመለከትም ሁሌ ግን የሚታየው trend የሴቶች ጥቃት ይነሳል ፣ ፌሚኒስቶች ለምን ተጠቃች ብለው ይነሳሉ ከዛ ከዚህ ደግሞ የሴቶችን ጥቃት ብንቃወምም ፌሚኒዝምን እንቃወማለን በማለት ፌሚኒዝም ላይ ይነሳሉ። ለምን ግን ገና የሴቶች ጥቃት ጉዳይ ሲነሳ ጥቃትን እንቃወማለን ብለው አይወጡም መጀመሪያ? ለምን ሁሌ በፌሚኒስቶች ይቀደማሉ?

ከዚህ ባለፈ ደግሞ በጣም ኋላ ቀር የሆኑ አነጋገሮችም ከዲያቆናት እና ካህናት ሰምቻለሁ። አንደኛው ዲያቆን "ሴቶች እኮ በዚህ ጊዜ ፈተና ሆነዋል ይኸው አንድ ወንድም በሴቶች ሽቶ ህልመ ሌሊት ድረስ ሲፈተን አያለሁ ኧረ ፈተና አንሁን" ሲል ተመለከትኩ። እዚህ ጋር ግን የበሽታውን ባለቤት ለምን በትክክል ማየት አቃተው? የሴት ሽቶ ስለሸተተው ብቻ ራሱን መቆጣጠር ማይችል ወንድ ካለ ችግሩ የእርሱ እንጂ የሴቷ አይደለም ፤ ያን ወንድምህን መገሰጽ ሲገባህ ግን ሴቶች በሽቶ ፈተና ሆናችሁ ብለህ ትናገራለህ ይህን ያህል እንዳታስተውል ያደረገህ ነገር ግን ምንድነው?

ሌላኛው ካህን ደግሞ "የሴት ልጅ ግርዛት መጥፎ side effect እንዳለው ሁሉ አለመገረዝም side effect አለው ቅንዝራም ያስደርጋል" ሲል ሰማሁ። እዚህ ጋር መናገር የምፈልገው ነገር ሁለቱን ነገሮች እንደ real life scenario አነሳው እንጂ ትክረቴ እነዚህ caseኦች ላይ ብቻ አይደለም ምናልባት የቆዩ ይሆናሉ። ነገር ግን እንደዚህ አይነት የወረደ አስተሳሰብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መያዝ ማለት በእውነት በጣም የሚያሸማቅቅ ነው። ጭራሽ ባለፈው ጊዜ የ15 ዓመት ሴት ልጅን ጋብቻ በ13ተኛ ክፍለ ዘመን document justify ሲያደርጉ ተመልክተናል። ይሄ ደሞ የሆነው በግለሰቦች ደረጃ ብቻ ሳይሆን በብዙዎች "መምህራን" በተባሉ አካላት ስለሆኑ ጉዳዩ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ፣ የቤተክርስቲያናችንን ስም የሚያጠፋ እና የሴቶችንም ጥቃት የሚያበረታታ ነው።

በዚህ ሁሉ "philosophical debates" ውስጥ ግን ምስኪኗ እኅታችን በጥቃት ድምጽ አልባ ሆና አለች ፤ እርስ በእርስ መሟገቱ ይደርሳል መጀመሪያ ግን እስቲ ለምስኪኗ እኅታችን እንድረስ።
❤ 69 👏 11 👍 3 👎 1
ኪ
20:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
አንድ በራሴ ያስተዋልኩትን ነገር ልንገራችሁ ብዙህ ጊዜ በ confidence የሚናገር ሰው ሁሉ የሆነ የያዘው እውነትማ ቢኖር ነው እንዲህ confidence የሞላው ብላችሁ assume አታድርጉ። ብዙህ ጊዜ በአንድ ጉዳይ ላይ ገና ማወቅ የጀመረ ሰው በጣም በ over confidence ሊያወራ ይችላል ምክንያቱም እርሱ የጉዳዩን ጥልቀት አይረዳም የእንደማያውቅ የማያውቀው ብዙህ ነገር እንዳለ ራሱ አይረዳም ስለዚህ ጉዳዩን በሙሉ አጥንቶ የጨረሰ ስለሚመስለው ድፍረታዊ ንግግሮችን ይናገራል በቃ ለእርሱ ሁሉ ነገር ጥቁር እና ነጭ ነው።

ለዚህ ምርጡ ማሳያ ለምሳሌ የቤተክርስቲያን አባቶች እና የቤተክርስቲያን ታሪክ ጥናት ነው። ገና የጀመርን ሰሞን በቃ አባቶች ሁሉ የእኛ የኦርቶዶክስ ናቸው ፣ ከዛ ውጪ ያለው ሁሉ በአባቶች ተመዝኖ ይወድቃል ፣ በታሪክ ውስጥ ጠልቆ የገባ ሰው ኦርቶዶክስ አለመሆን አይችልም ምናምን እንላለን። (ደሞኮ የሚያስቀው ይህን ሁሉ እንል የነበረው አንድም የአባቶች ጽሑፍ ሳናነብ ነው ብቻ ይሄ አባት እንዲህ ብሏል ፣ ይሄ አባት እንዲህ ብሏል ብለን በሰማነው ብቻ ነው 😁)። ነገር ግን የቤተክርስቲያን ታሪክም ሆነ አባቶች ጥናት እንደምናስበው ወጥ እና በቃ ጥቁር እና ነጭነቱ ግልጽ ብሎ የሚታይ ነገር አይደለም ፣ ስለዚህም ነው እኔ ከሆነ ጊዜ በኋላ "ከአባቶች እንዲህ ያለ አንድ አይገኝም" "አባቶች ሁሉ ይህን ብለዋል" የሚል absolute ንግግሮችን ያቆምኩት ፤ ምንም ያህል ያነበባችሁ ቢመስላችሁ እናንተ ካላችሁት ተቃራኒ አንድ አባት ወይም አንድ እንኳን ታሪካዊ ክስተት ሊመጣ ይችላል። እንዲሁም የቤተክርስቲያን ታሪክ በጣም ውስብስብ እና messy ስለሆነ የሆነ አንድ ትውፊት ብቻ ሙሉ አባቶችን ምንም ሳይለወጡ በምልዓት ይዤያለሁ ብሎ claim ሊያደርግ አይችልም። ብዙህ ጊዜ በኦርቶዶክሳውያን በኩል ለዚህ መልስ "አንድ አባት ሳይሆን የአባቶች ስምምነት ፣ እኛ የአባቶች ስምምነት ነው የምንቀበለው" ሲባል ይታያል ነገር ግን የአባቶች ስምምነት ሲባል ምን ማለት ነው? አንድ ነገር ላይ አባቶች ተስማምተዋል የምንለው ምን ምን መሥፈርት ሲያሟላ ነው? የአባቶች ቁጥር ነው? የሚታመንበት አከባቢ መብዛት ነው? በታዋቂ አባቶች ዘንድ በአብዛኛው አንድ ቋሚ ትምህርት መኖሩ ነው? በግልጽ የተቀመጠ መስፈርት የለም ስለዚህ "የአባቶች ስምምነት" ለምንለውም ሆነ "ለዓለም አቀፍ ጉባኤ" አንድ ወጥ የሆነ ምሥፈርትን የያዘ epistemological model ያስፈልገናል እንጂ አባቶችን እንዲሁ በአንድ ጎራ ከተን ከኛ ጋር ናቸው ብንል በጣም ጥልቅ ጥናት ያደረገ ሰው አንድ አንድ ምሳሌዎችን ብቻ በመጥቀስ ሊያፈራርስብን ይችላል።

በዚህ ላይ ለመጨመር ደግሞ ለዚህ epistemological certainty በፊት Papacy መልስ ይመስለኝ ነበር በቃ የካቶሊክ ነገረ መለኮት በብዙህ ነገር የተዋቀረ ፣ የተደራጀ እና የሆነ ጥያቄ ቢነሳም በዓለም አቀፍ ደረጃ መልስ ሊሰጥበት በመቻሉ ጥሩ የሆነ epistemological model ይመስላል ለዚህ በፊት ላይ ኦሬንታል ኦርቶዶክስ ባልሆን ካቶሊክ እሆናለሁ እል ነበር ፣ ነገር ግን አባቶችን more ባየሁ ቁጥር እንዳውም Papacy ሐሰት መሆኑን እና epistemological modelኡም አንድ ደረጃ ከእኛ ወደ ኋላ ገፋው እንጂ መልሶ እኛን በሚጠይቁን ጥያቄ እንደሚወድቅ ተረዳው (ለምሳሌ Papacy እውነት መሆኑን በምን አወክ ሲባል ራሱ Papacy መልስ ሊሆን አይችልም circular ይሆናል ያለበለዚያ so መልሰን ወደ ታሪክ ጥናት ልንመጣ ነው ፤ ያኔ ደግሞ መልሰን ስንት አባቶች ተስማሙ ፣ በምን ያህል ቦታ ያሉ? የሚሉት ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም ምክንያቱም Papacyን ከሚደግፉትም ከሚቃወሙትም side ሁለቱም ከአባቶች ማስረጃ ማምጣት ይችላሉና።)

ብቻ እንደ ቤተክርስቲያን ታሪክ ጥናት the most humbling experience የለም ፤ አሁን ላይ እኔም በጣም ብዙህ እልፍ ይቀረኛል ነገር ግን እንደ በፊቴ የማላውቀውን የማላውቅ አይደለም ቢያንስ የማላውቀው ብዛት ስለማውቅ የድፍረት ንግግር ተናግሬ አፌን አላበላሽም 😄
❤ 90 ✍ 2 👎 1
15 September 2026
ኪ
21:03
ኪዳን ዘኢየሱስ
የዚህ ቻናል ተከታታዮች የእድሜ ክልላችሁ የትኛው ነው?
Anonymous poll
- ከ18 በታች 22 votes
- ከ18-24 412 votes, chosen vote
- ከ25-30 181 votes
- ከ30-40 53 votes
- ከ40 በላይ 15 votes
683 votes
እንደ እድሜያችሁ ልክ እንዲጻፍ ተፈልጎ ነው 😅
😁 26 👍 5 ❤ 4
ኪ
23:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://www.youtube.com/watch?v=UAIbYQSJ184

ይሄን ቪዲዮ ያየ አንድ ሰው ሊይዘው የሚችለው ድምዳሜ ሁለት ብቻ ነው፡ ንስጥሮስ ኬልቄዶናዊ ነው ፣ ወይም ደግሞ ኬልቄዶን ንስጥሮሳዊ ነው።

እስቲ ኬልቄዶናውያን እዩትና እኛ "ንስጥሮሳዊ" አይደለንም በሉ ያኔ ንስጥሮስን ኬልቄዶናዊ ነው እያላችሁት ነው የሚሆነው።

Great job by Agen 🙌
❤ 44 ⚡ 5 🤣 3 👍 1
16 September 2026
ኪ
14:46
ኪዳን ዘኢየሱስ
በቤተክርስቲያናችን ዲያቆን ተደርገው መሾም ያለባቸው ያገቡ ምዕመናን ብቻ መሆን እንዳለባቸው አሁን ያለንበት ጊዜ ከምንም በላይ ማሳያ ነው። እንደሚታወቀው አገልጋይ ሲሆን አንድ ሰው ልታይ ልታይ በሚል የተርእዮ ፈተና መፈተኑ አይቀርም ስለዚህም አገልግሎቱ ለእግዚአብሔር መሆኑን ይረሳና እርሱ ጎልቶ የሚታይበት ወደ ማድረግ ሊሔድ ይችላል። ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ አብዛኞቹ በተለይ የአዲስ አበባ አድባራት ላይ ቅዳሴ ሲቀደስ ዜማው በምልክቱ መሆኑ ቀርቶ "ቀሸረው" ለመባል ዜማውን ለማሳመር የሚሽረቀረቁት ፤ በተለይ የክብረ በዓል ቀን ቅዳሴ ከሆነማ አይጣል ነው ዲያቆናቱ እኔ ልቀድስ ፣ እኔ ልቀድስ በሚለው ይጣላሉ እንዲሁም በሰው ፊት ድምጹ ያምራል እንዲባሉ አላግባብ ዜማውን ማስረዘም እና ማሽቀርቀር ውስጥ ይገባሉ ፤ እንዲሁም ሶሻል ሚዲያ ላይ በልብሰ ተክህኖ "ጎምለል ጎምለል" እያሉ መውጣትን ተያይዘውታል። መቼስ የእኛ ምዕመን ምስኪን ነው አገልጋዮችን "ቅዱሳን" አድርጎ እስከ መሳል በተለየ ዓይን ስለሚያይ ገና ጉርምስናውን ያልጨረሰ አንድ teenagerን የተለየ አድርጎ በማየት በትዕቢት ያሳብጡታል።

እንዲሁም ሴቶች ብዙህ ጊዜ በእውቅና እና በዝና እንደ ሚፈተኑ ግልጽ ነው። በማኅበረሰብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ለሚሰጠው ወንድ ልባቸው ይሳሳል ምክንያቱም status ይማርካቸዋል pre-approved መሆኑን ያሳያልና። በዚህ ምክንያት ብዙህ ሴቶች እነዚህን ጎረምሳ ዲያቆናት idolize ወደ ማድረግ ይሔዳሉ ፤ Social media ላይ እያየን ያለነው trend አሰቃቂ ነው ሴቶች ዲያቆን ካልሆነ አላገባም ፣ ዲያቆኔ ሲቀድስ ሳየው ፣ የዲያቆን ፍቅረኛዬን ድምጽ ቅዳሴ ላይ ስሰማ ፣ እኔ ሰንበት ተማሪ እርሱ ዲያቆን ወዘተ የመሰሉ አሰቃቂ ዝናን ፍለጋ trend ተመልክተናል። Please ድቁና በራሱ መንፈሳዊነት አይደለም ፣ ዜማ መቀሸር በራሱ አያጸድቅም ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ አገልጋይ መሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ቀረቤታ አይሰጥም ፤ እኅቶች ሆይ አትሸወዱ መንፈሳዊነት ማለት ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ጎምለል ጎምለል ማለት ፣ ጥቁር ቀሚስ ከትልቅ መስቀል ጋር ማድረግ ፣ ነጭ የምርግትና ካባ ማድረግ ፣ ዜማን ማሽቀርቀር አይደለም እውነተኛ መንፈሳዊ ሰው ከልቡ ከቅዱሰ ቅዱሳን ክርስቶስ ጋር እውነተኛ ግኑኝነት ያለው ፣ ክርስቶስን በንጹሕ ልብ የሚወድ ፣ በኃጢአት ቢወድቅም በንስሐ እየተነሳ በቁርባናዊ ሕይወት የሚኖር ፣ በትሕትና ዝቅ ዝቅ የሚል እንጂ ልታይ ልታይ የማይል ሰው ነው። ስለዚህ ዲያቆን ወይም የቤተክርስቲያን የትኛውም አገልጋይ ስለሆነ ብቻ "ያፈሳችሁ" አይምሰላችሁ አሁን ላይ ብዙህ የተርእዮ አገልጋዮች ነው ያለን።

እናንተ ዲያቆናትም እራሳችሁን የተለየ አድርጋችሁ ማሰቡን ማቆም አለባችሁ ዲያቆን ማለት አገልጋይ የካህን ተላላኪ ማለት ነው በቃ ሌላ አይደለም ፣ በትዕቢት እና ተርእዮ ያበጠ ልባችሁን ስበሩትና ንስሐ ግቡ ፤ ያለ ንስሐ ሥራችሁ ስለሆነ ብቻ የምትቆርቡት ሥጋ እና ደም ለመፈራረጃ ይሆንባችኋልና። ካህኑ "ንጹሕ ያልሆነ አይቀበል ኃጢአታችሁ ወደ ራሳችሁ ይመለሳል" በማለት የሚወቅሰው ወቀሳ እናንተን ነው እስከመቼ ንስሐ በማይገባ ልባችሁ የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ላይ እንዲህ ታፌዛላችሁ? ቅዳሴ ላይ ራሳችሁ ሳታስተውሉ የምትሏት ቃል ልበላችሁ "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ"።
❤ 163 💯 21 👍 5 ❤‍🔥 2 👏 1
19 September 2026
ኪ
13:08
ኪዳን ዘኢየሱስ
ቡድሒዝም በክርስትና

ሰሞኑን የምሥራቅ ሃይማኖቶችን ላጥና ብዬ ጀምሬ ከቡድሂዝም ጀመርኩ ነገር ግን እዚህ ጥናት ላይ ያገኘሁት ነገር ጉድ አስባለኝ።

እንደሚታወቀው በቡድሂዝም እምነት መሥራችነት የሚታወቀው ቡድሃ (የበራለት እንደማለት ነው።) ሲዳርታ ጓውታማ ሲሆን የኖረው በ5ኛው ክፍለ ዘመን ቅ.ል.ክ እንደሆነ ይታመናል። ስለታሪካዊው ቡድሃ ብዙህ ነገር ባይታወቅም በቡድሂዝም አማኞች መጻሕፍት ውስጥ ታሪኩ ተዘጎ ይገኛል እርሱም እንዲህ ነው። አንድ ሃብታም ንጉሥ እና ንግሥት ነበሩ ልጅ አልነበራቸውም አንድ ቀን ንግሥቲቱ በህልልሟ ሆዷ ውስጥ ከሰማይ ነጭ ዝሆን ሲገባ ታያለች ነገር ግን ህመም አልተሰማትም። በኋላም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደች ፤ ልጁ ከተወለደ በኋላ አንድ ሰው "ይህ ልጅ ሲያድግ ታላቅ ይሆናል" ሲል ትንቢት ተናገረለት። ንጉሡ ይህን ፈርቶ ልጁን ከሰዎች አኗኗር እንዳለ ይደብቀዋል ልጁ ምንም አይነት ሕመም ፣ በሽታ ፣ ሞት እና ማርጀት እንዳያውቅ ተደርጎ ያድጋል። ይህ ልጅ በዚህ ሁኔታ ካደገ በኋላ ከአንድ ሰው ጋር ወደ ውጪ ይወጣና በተከታታይ አራት ምልክቶችን ያያል (የታመመ ሰው ፣ ያረጀ ሰው ፣ የሞተ ሰው እና በመጨረሻም meditate የሚያረግ ሰው።) እርሱም ሕመምን ስለማያውቅ በጣም ይፈራል ፤ ከሕመም ማምለጫ መንገዱም በ meditation መሆኑን ይረዳል በመጨረሻም ከብዙ የምንኩስና ጊዜ በኋላ የበራለት (ቦዲሳትቫ) በመሆኑ ቡድሃ ተብሎ ብዙዎች ደቀ መዛሙርትን ሰብስቦ አይተምሯል።

ታሪኩ ከዚህ በላይ ሰፊ ነው እኔ ዋና ይህን የመጻፌ ምክንያት ይህ ስላልሆነ እንዲሁ ታሪኩን ለማሳየት ያክል ነው። የገረመኝ ነገር ግን ምን መሰላችሁ? የቡድሃ ታሪክ እና አስተምህሮ ቡድሂዝም ጋር ብቻ የቀረ አይደለም ይልቅስ ታሪኩ በእስልምናም በክርስትናም adapt ተደርጎ ይገኛል።

በመጀመርያ ታሪኩ ከሳንስክሪት ወደ ፋርስቋንቋ ይተረጎማል ፤ በዚህ ቋንቋ እንዳለም ታሪኩ ትንሽ ይለወጣል። በቡድሂዝም መጻሕፍት ቡድሃ ብቻውን አብርሆት ላይ የደረሰ ሲሆን በፋርስ ቋንቋ ላይ ቡድሃ ገና የአባቱ ቤት እያለ ወደ እርሱ መጥቶ የሚያስተምረው ባርላም የሚባል ሰው ይመጣል (መጨረሻ ላይ meditate የሚያደርገው 4ተኛው ምልክት adaptation እንደሆነ ይታመናል)። ይህ መጽሐፍም ከፋርስ ወደ አረብኛ በእስልማዊ adaptation "ኪታብ ባላዋር ወቡዳሳፍ" (የባላዋር እና የቡዳሳፍ መጽሐፍ) ተብሎ ይተረጎማል። በአንዳንድ manuscriptኦች ግን "ቡድሃሳፍ" የሚለው ስም "ዩዳሃሳፍ" በመባል ይገባል። ይህ የሆነበት ሁኔታ የአረብኛው "በ" ፊደል እና "የ" ፊደል የሚለዩት በአንድ ነጥብ ብቻ ስለሆነ በስህተት ነው። ከዚህ አረብኛ መጽሐፍም ክርስቲያናዊ ተደርጎ ወደ ጆርጅያ ቋንቋ ይተረጎማል ፤ በመጨረሻም በጆርጂያ ወደ ግሪክ ቋንቋ በ10ው ክፍለ ዘመን አከባቢ ይተረጎማል። ይህ የግሪክ መጽሐፍ የትርጉም ሥራ ብቻ ሳይሆን በጣም ብዙህ ክርስቲያናዊ element እንዲኖረው ተደርጎ ነው የተተረጎመው ፣ ብዙህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ ፣ ባርላም መነኩሴ ይሆናል ፤ ወደ ቡድሃ (ከአረብኛው ዩዳሳፍ ፤ ዮሳፍ ሆኗል) በመምጣት ክርስቲያን ለማድረግ ይሞክራል አባቱ ግን ክርስቲያኖችን ሚያሳድድ ንጉሥ ነበር በኋላም ዮሳፍ አባቱን በክርስትና ያሳምነውና ይነግሣል። ዮሳፍ ግን ንግሥናውን ትቶ ይወጣል ልክ የቡድሒዝም ታሪክ ላይ እንዳለው 3ቱን ሕማማት ያያል (በሽታ ፣ ማርጀት ፣ ሞት) ከእነዚህም ለማምለጥ ከባርላም ጋር በምንኩስና ሕይወት ወደ አብርሆት ይሔዳል። ይህ የግሪክ ትርጉም መጽሐፍ በኢስተርን ኦርቶዶክሶች ዘንድ ዮሐንስ ዘደማስቆ የጻፈው እንደሆነ ቢነገርም ምሑራን ግን በ10ኛው ክፍለ ዘመን በአቶስ ገዳም የነበረው አውጣሚዮስ (Euthymius the Athonite) ከጎርጂያ ወደ ግሪክ እንደተተሮገመ ይታመናል። የሚገርመው ደግሞ ባርላም እና ዮሳፍ (Barlaam and Josaphat) በኢስተርን ኦርቶዶክስ ካላንደር ውስጥ ገብተው እንደ ቅዱሳን ይከበራሉ። (ከቡድሂዝም መሥራችነት ወደ ክርቲያን ቅዱስነት ትላለህ 😂)

የገረመኝ ነገር እዚህ ጋር ቢያበቃ ጥሩ አልነበረም? ነገር ግን አያበቃም ፤ ይህ የባርላም እና ዮሳፍ መጽሐፍ ከአረብኛ ወደ ግዕዝ በ16 ክፍለ ዘመን በደብረ ሊባኖሱ እጨጌ እንባቆም ተተርጉሟል። እጨጌ እንባቆም ከየመን የመጡ አረብኛ ተናጋሪ በመሆናቸው በአጼ ገላውዴዎስ ዘመን ወደ ግዕዝ ተርጉመውታል። የትርጉም ሥራውም ከእስልማማዊው የአረብኛ ምንጭ ይመስላል ምክንያቱም መጽሐፉ ሲጀምር ግዕዙ "በስመ እግዚአብሔር መሐሪ ወመስተሳሕል" ብሎ ነው ይህ ማለት የአረብኛው የሱረቱ አልፈቲሃ መግቢያ "ቢስሚ ኢላሂ ራህማን አረሂም" ለሚለው ቃል በቃል ትርጉም ነው በአማርኛ ስንመልሰው "መሐሪና ሩኅሩኅ በሆነው እግዚአብሔር ስም" ማለት ነው።

ይህ መጽሐፍ በግዕዙ "ገድሎሙ ለቅዱሳን ባርላም ወይዋስፍ" የሚል ርእስ ሲሰጠው (የቅዱሳን የባርላም እና የይዋስፍ ገድላቸው) አመዳደቡም ልክ እንደ ራዕየ ሳቤላ ፣ ፍካሬ ኢየሱስ ፣ ዜና እስክንድር እንደሚሉት አይነት መጻሕፍተ ጥበብ ውስጥ ነው። (ባዕድ ፍልስፍና መሆኑን አንርሳ)። አንድ ደስ የሚለው ነገር ግን ምንም እንኳን መጽሐፍ ገድላቸው በግዕዝ ቢኖርም የትኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ጥቅም ላይ አይውልም ፣ አይነበብም ፣ ቤተክርስቲያንም ሆነ ታቦት በስማቸው የለም፣ ሥንክሳር ውስጥም ቅዱሳን ተብለው አልገቡም እንዲሁ መጽሐፉ ብቻ በብራና በተለያዩ ገዳማት አለ እንጂ (በኢስተርኖች ግን ቅዱሳን ተብለው መታሰቢያ ቀን አላቸው።) ይህ የሚያስተምረን አንድ ትምህርት በግዕዝ ብራና ላይ የተገኘ መጽሐፍ ሁሉ የክርስቲያን መጽሐፍ እንዳልሆነ ነው ፤ እንኳንም ጌታ "ቅዱስ ቡድሃ አማልደን" ከማለት ተረፍን ብቻ።

ኮመንት ላይ በአዲስ አበባ ዩነቨርሲቲ reconstruct የተደረገውን ገድል ጥናት ተሠርቶበት ግዕዙ ስላለ ልቅላችኋለሁ ፤ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጅ የመጽሐፉን ወደ ግሪክ ፣ አርብኛ ፣ ፋርስ ፣ ላቲን ፣ እና ግዕዝ መምጣት የሚናገር articleም አስቀምጣለሁ።
❤ 26 😱 18 😁 9 👏 4 🔥 3 👍 1
ኪ
18:53
ኪዳን ዘኢየሱስ
"15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥"
😢 41 ❤ 12 🤔 3 👍 1
21 September 2026
ኪ
16:34
ኪዳን ዘኢየሱስ
ታላቅ ዲቤት

(ኦርቶዶክስ vs Anglican)

Timeless Truth vs David Yeshua

Moderator: ኪዳን ዘኢየሱስ
Jo_El
😁 63 🤣 46 🔥 8 ❤ 1
22 September 2026
ኪ
09:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
K
Kingdom Diaries 22.09.2026 08:49:20
It depends on what we mean by feminism. If by feminism we mean that women have equal dignity and worth, should have equal opportunities and should be protected from abuse, exploitation and discrimination, then of course I agree. Not only does that not contradict my Christian convictions but I believe that my Christian convictions actually require me to affirm those things. But there are also aspects of modern feminism I strongly disagree with like empowerment being synonymous with sexual liberation, motherhood or traditional marriage being treated as oppressive, men and women being treated as though they are completely interchangeable or when individual autonomy becomes the highest good. So there are things feminism has gotten very right and things it has gotten very wrong. So yeah, I’d rather discuss the actual ideas than accept or reject everything under one label.

More in the comment section…
❤ 31 🥱 4 👌 2 💯 2 👎 1
ኪ
12:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
My favorite verse ❤️

Customized T-shirts እንዲሁም ሥዕሎችንም ሆነ፣ ስቲከሮች እኅታችን አርሰማን እዘዟት @aesthetica_merch
❤ 91 🥰 4
26 September 2026
ኪ
18:50
ኪዳን ዘኢየሱስ
በአዳም ወደቅን በሁለተኛው አዳም ተነሣን
በሔዋን በኩል ሞት ነገሠ ፣ በሁለተኛዋ ሔዋን በኩል ሕይወት ክርስቶስ መጣ
በእንጨት ላይ ከፍ ባለው ፍሬ ሞትን ፣ በእንጨት ላይ ከፍ ብሎ በተሰቀለው ዳንን!

መስቀሉ የድኅነታችን አርማ ነው ፣ የተሰቀለው መድኃኒታችን ነው።
መስቀሉ የቤዛነታችን ምልክት ነው ፣ የተሰቀለው ቤዛችን ነው።
መስቀሉ የሕይወታችን ሰንደቅ ዓላማ ነው ፣ የተሰቀለው ሕይወታችን ነው።
በመስቀሉ የተቸነከረው የኃጢአት እዳ ደብዳቤያችን ነው ፣ በተሰቀለውም ያገኘነው የኃጢአታችንን ማስተሠርያ ነው።

መስቀሉን ስናይ የተሰቀለውን እናያለን ስለዚህም ነው "የመስቀሉ ቃል ለእኛ ለምንድን የእግዚአብሔር ኃይል ነው" የምንለው የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለንና!

እንኳን አደረሳችሁ
🥰 90 ❤ 43 🔥 3 👏 2 🙏 1
28 September 2026
ኪ
12:57
ኪዳን ዘኢየሱስ
The biggest one was I doubted the existence of God himself for a period of 4 years (from 14-18) I was essentially a nihilist at that stage. ወደ ቤተክርስቲያን በጥሩ እምነት ተመልሻለሁ ብዬ ማስበው ከ19 ዓመቴ ጀምሮ ነው። እውነት ለመናገር ክርስትናን ከስም መጠሪያነት አልፎ መኖር የጀመርኩትም ክርስቶስንም ማወቅ የጀመርኩት በደምብ በዛ እድሜ ነው። Before my 4 years of agnosticism ያው የትኛውም ኦርቶዶክስ ልጅ እንደሚያሳልፈው ቁርባን አቁሜ ቆይቻለሁ I like science and knowledge in general ትምህርት ቤት biology ስንማር evolution made sense to me ከዛ ግን ሰዉ እሱ ዝም ብሎ ነው ይላል ፤ ማስረጃ ጠይቃለሁ ዝም ብለህ እመን ነበር ምባለው ብቻ ሌላ አማራጭ ያለ ስለማይመስለኝም ዝም ብዬ አምናለሁ። ነገር ግን Internet መጠቀም ከጀመርኩ በኋላ I met with atheists ምናምን እና በጣም ፈራቸው ነበር ምክንያቱም እነርሱ እስቲ አለ ለምትለው አምላክህ ማስረጃ ምንድነው እያሉ በ confidence ይጠይቃሉ እኔ ደሞ ምንም ማስረጃ የለኝም even በዛ ጊዜ God wasn't even a big part of my life ቤተክርስቲያን ለመሳለም ከወራት አንዴ ብሔድ ነው እና ልቤ ወደነሱ ተሳበ ነው ፤ ነገር ግን በልጅነቴ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የብሉይ ኪዳንን ታሪኮች ገና በልጅነት እድሜ ተረት እንደማነብ አይነት ነበር ሳነባቸው የነበሩት እና ብቻ እነዛ ታሪኮች foundational ስለነበሩኝ ማስረጃ ባላገኝም ግን ሙሉ በሙሉ የለም ብዬ መደምደም አልፈለኩም። but then I discovered agnosticism እና middle ground ያዝኩ ነገር ነበር።
❤ 38 🔥 2
ኪ
13:39
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ከቤተክርስቲያን አልወጣሁም ነበር እንዲሁም ማንም አያውቅም ነበር ለራሴ በውስጤ የያዝኩት እንጂ። ደግሞ እንደሚታወቀው በዛ እድሜ Nominal Christianity በቃ የተለመደ ነው ሲጀመር ቁርባኑንም ያስቆሙናል ፤ እኔ መጀመሪያ ማቆም አልፈለኩም ነበር እንዳውም ለረጅም ጊዜ ወስድ ነበር ነገር ግን እንደ taboo እየታየሁ መጣሁ ማለትም በእኔ እድሜ ማንም ሚቆርብ የለም ከሕፃናት ጋር ተሰልፌ ነበር የምቆርበው ነገር ግን አከባቢዬ ያለው ሰው ሲታዘበኝ ማስተዋል አየሁ ፣ እንዲሁም peer pressure ሚባል ነገር ነበር ሁሉም ጓደኞቼ አይቆርቡም ከዛ ቆርባለሁ ብዬ ብናገር ልክ ጡጦ አልተውክም እስካሁን አይነት ሙድ መያዝ ነበር።

ነገር ግን ከዚህ በኋላ ነበር ነገሮች downhill የሔዱት ለቁርባኑ ነበር ቅዳሴ እየሮጥኩ የምሔደው ፤ አሁን አድገሃል ቁርባኑ አያስፈልግህም የሚለው ሲመጣ እንዲሁ ቅዳሴው ላይ ያለኝ ተሳትፎም እየቀነሰ መጣና completely ቅዳሴ መሔድ አቆምኩ ከዛ ከስንት አንዴ የሰርክ ጉባኤ ለመሳለም ነው የምሔደው ጓደኞችም እንደዛ ናቸው። በቃ ያው በስም ክርስቲያን ነኝ እላለሁ እንጂ የክርስትና ሕይወት የለኝም ማለት ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር ከኤቲስቶች ሚመጡት ጥያቄዎችም ማጠራጠር የጀመሩት። አምላክ ሊኖር አይችልም ብሎ ማሰቡ ራሱ በጣም taboo ስለነበር ዝም ፣ ጭጭ ነበር በቃ ይዤ በተቃራኒው ደግሞ facebook ላይ Ethiopian Atheists የሚል ግሩፕ ላይ ነበርኩ ፤ እነርሱ በቃ ልክ እንደ ቻርለስ ዳውኪንስ "ሃይማኖት ኋላ ቀርነት ነው ፣ ድንቁርና ነው ፣ your sky daddy" የሚባሉት የተለመዱት ስላቆች ነበሩ። ነገር ግን እኔ መልስ መስጠት ስለማልችል silent አባል ነበርኩ ፣ የእነርሱን ጥያቄ ለሌላ ባነሳ ዝም ብለህ እመን ነው የሚባለው። እና ብቻ ለአእምሮዬ ራሱ መልሼ መንገር አልፈልግም ነበር። ከዚህ ጋር ተጨምሮ የሕይወት ትርጉሙ ምንድነው? ለምን ተፈጠርኩ? አይነት existential ጥያቄዎችም ይመጡብኝ ነበር ለዛ መልስ ያደረኩት መጨረሻ ላይ Nihilism ነበር ምንም ጥቅም የለውም ሰው በቃ ይወለዳል ያድጋል ይሞታል እላለሁ (አሁንም ለራሴ ብቻ)።

ብቻ እንዲህ ረዘም አድርጌ የጻፍኩት አሁን ልጆች ያሏችሁ ወላጆችም ካላችሁ ፣ እንዲሁም ወደፊት ወላጆች የምትሆኑ ወጣቶች መቼም ቢሆን የልጆችን ጥያቄ dismiss አታድርጉ ቢያንስ መልሱን ካላወቃችሁ አላውቅም በሏቸውና አንብባችሁበት መልሱላቸው they are persons, they deserve their autonomy to be respected. እንጂ ዝም ብለህ እመን ወይ ደግሞ ጥያቄ ሲጠይቁ ማሸማቀቅ ወይም ጥያቄውን ስለጠየቁ ብቻ መጥፎ የሆኑ እንዲሰማቸው አታድርጉ እናንተ dismiss ብታደርጉባቸው ከእነርሱ አእምሮ ግን አይወጣም (እኔ ላይ ያጋጠመው ይህ ነው) ይልቅስ ከአሁኑ የልጆቻችሁን ጥያቄዎች ልትመልሱ የምትችሉበትን የእምነት እውቀት ታጠቁ እንዲሁም ገና ጥያቄ ሳይፈጠር ራሱ ከልጅነት ክርስትናን አስተምሯቸው (እኔ ለምሳሌ በልጅነቴ ሳነባቸው የነበሩት የብሉይ ኪዳን ታሪኮች foundation ስለሆኑኝ እንጂ ምናልባት ላልመለስ እችል ነበር) ገና ከልጅነታቸው ስለ ብሉይ ኪዳን አባቶች ፣ ስለ ነቢያት ፣ ስለእስራኤል ፣ እንዲሁም በሐዲስ ኪዳን ወንጌላትን internalize አስደርጓቸው ከክርስቶስ ጋር ገና በልጅነታቸው በፍቅር ይክነፉ ፣ ከዛም የሐዋርያት ሥራም ለእኔ ጥሩ ነበር ታሪክ ስለሆነ። ብቻ በየቀኑ የእግዚአብሔርን ቃል ንገሯቸው ፣ አንብቡላቸው ፣ እንዲያነቡ አበረቷታቸው ፣ አብራችሁ አንብቡ ፣ እንደ ቤተሰብ በሳምንት አንድ ቀን ይዛችሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንብባችሁ ተወያዩበት። በቃ well versed in God breathed scriptures አድርጓቸው ከልጅነት ጀምሮ እውነት ለመናገር መንፈስ ቅዱስ በዛ ውስጥ ይሠራል ፤ እኔ በልጅነቴ የእግዚአብሔርን ቃል ላንብብ ብዬ ራሱ አልነበረም ሳነብ የነበረው እንዲሁ ማንበብ እወድ ነበር ፊት ለፊት የማገኘው ደሞ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር ከዛ በቃ ታሪኮቹ ደስ ስለሚሉኝ እንዲሁ አነባቸዋለሁ ፣ ያኔ ለታሪኩ ደስታ ባነብም በዛ ግርሙስና እድሜዬ ግን እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዳልቆርጥ ያደረገኝ እነዛ ታሪኮች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከልጅነታቸው ጤነኛ doctrine እንዲያውቁ ጤነኛውን doctrine መግቧቸው።

አውቃለሁ ረዝሟል ግን please ታግሳችሁ አንብቡ ምናልባት ለሰው ይጠቅማል ብዬ ነው እንዲህ በሰፊው የጻፍኩት።
❤ 89 ❤‍🔥 9 👍 6 🔥 5 🥰 1 🙏 1 🤝 1
ኪ
15:43
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሄ ጥያቄ ስለተደጋገመ ለምን consider እንደማላደርግ በየተለየ መንገድ መጥቻለሁ፣ የመጀምሪያው ትልቁ Point consider ለማድረግ ራሱ ምንም ማስረጃ ያለው truth value የለውም የሚል ነው።

ስለዚህ ሙስሊሞቹን Challenge የማደርገው Consider የማደርግበት ምክንያት እንኳን እንዲሰጡኝ ነው ፤ Challengኡን ቀጣይ በምለቀው pdf አስቀምጫለሁ።
🔥 19 ❤ 7 ⚡ 2 💯 1
ኪ
20:40
ኪዳን ዘኢየሱስ
በጣም vulnerable ነው እንጂ ፤ ምክንያቶቹን በዚህ ጠቅሻለሁ ከፍታችሁ አንብቡት። ነገር ግን intellectually honest ያልሆነና አሁን ቤተክርስቲያን ያለችበት ሁኔታ crisis ላይ መሆኗን የማያምን ሰው ባያነበው ይመከራል ከእንግዲህ ዝም ማለት ቤተክርስቲያንን ስለሚጎዳ በግልጽ ነው ማውራት ያለብን። የቤተክርስቲያን ጥላቻ ምናምን እያለ የሚነጫነጭም አያንብበው።

https://telegra.ph/ኤቲዝም-ቀጣይ-ስጋት-09-28
❤ 39 👏 1
29 September 2026
ኪ
11:16
ኪዳን ዘኢየሱስ
I think Divine hiddenness is harder to answer than Problem of Evil.
❤ 22
30 September 2026
ኪ
14:49
ኪዳን ዘኢየሱስ
Of course atheism is worse are we even seriously asking the question? How can you compare someone who believes in “one God, the Father; one Lord Jesus Christ, incarnate of the Holy Spirit and the Virgin Mary, crucified under Pontius Pilate, who rose on the third day and will come again to judge at the end of the age and reign forever,” and who also believes in the Holy Spirit and the Catholic Church, with someone who completely disbelieves in God?
❤ 43 🤷 5 👏 1
ኪ
16:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጽዋዔ

መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2

ጽንሐ ተዋሕዶ

የልቦና ችሎት

አኮቴተ ቁርባን
❤ 66 🔥 2 🌚 2
1 October 2026
ኪ
14:05
ኪዳን ዘኢየሱስ
ጤናችሁን ከቲክቶክ ጠብቁ 🙌
❤ 44 👍 9 😱 3 💯 1
ኪ
17:32
ኪዳን ዘኢየሱስ
የሶሻል ሚዲያ ሱስ ምንነት

እንዴት እንደሚመጣ

ምልክቶች

መፍትሔዎች

እስቲ እነዚህን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ አንብባችሁ አስተያየት ስጡበት ይረዳል ብላችሁም ካሰባችሁ ለብዙህ ሰዎች share አድርጉ።

@KidanZeIyesus
@KidanZeIyesus
❤ 39 🥰 1 😱 1
ኪ
18:47
ኪዳን ዘኢየሱስ
1. The case for Resurrection of Jesus. By Michael Licona and Gary Habermas
2. On the Incarnation by St. Athanasius
3. Confessions by St. Augustine
4. The Crucifixion of the King of Glory by Eugenia Constantino
5. Council of Chalcedon Re-examined by Fr. VC Samuel
6. Christology and Council of Chalcedon by Fr. Shenouda Mar Yishak
7. God, Freedom and Evil by Alvin Plantiga
Bonus: Atonement by Eleneore Stump

I am not saying these are necessarily the best books. But these books had a huge impact on me.
❤ 36
ኪ
19:14
ኪዳን ዘኢየሱስ
https://ngl.link/kidel1917151

ሰሞኑን እስቲ ጥሩ ጥያቄዎችም እያመጣችሁ ነው እኔም በጣም የመጻፍ energy መጣልኝ መሰለኝ ብዙህ articles አጻፋችሁኝ። አሁን ጥያቄ ካላችሁ ጠይቁ ፤ ነገር የእኛ አልተመለስም የምትሉ I can't guarantee to answer all.
ኪ
20:21
ኪዳን ዘኢየሱስ
20:21
1. የምንቀበለው የክርስቶስ ሥጋና ደም የሞተው ፣ የተነሣው ወደ ሰማያት ያረገው ፣ አሁንም በአን ዘንድ ሊቀ ካህናታችን የሆነውን ፍጹመ መለኮት ፣ ፍጹመ ትስዕብት እንጂ ከትስብዕቱ ለይተን ነፍሱን አንቀበልም አንልም ፣ ክርስቶስ ነፍሱ የተለየው በሞተ ጊዜ ነው ስለዚህ ነፍስ የተለየውን እንቀበላለን ማለት የሞተ ምሥዋዕት እንቀበላለን ማለት ነው። ነገር ግን ክርስቶስ በሐዲስ ኪዳን እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት የሞተ እንስሳ ደም ሳይሆን ይልቅስ ሞቶ በተነሣ እና ሕያው በሆነ ደም ነው ወደ ቅድስት የገባው። አባታችን ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያም ክርስቶስ እስከ ትንሣኤ ድረስ ማሳኒ (ጓስቃላ) ሥጋ ነው የያዘው ስለሚል ዮልያኖስ ስለዚህ በቁርባንም ጎስቋላ ሥጋን ነው ምትቀበለው ሲለው የመለሰው የምንቀበለው የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ከትንሣኤ በፊት ያለውን ቢሆን ኖሮ ጓስቃላ ሥጋን በተቀበልን ነበር ጉስቁልና ግን ከቅዱስ ቁርባን ይራቅ የምንቀበለው በትንሣኤ የከበረውን የክርስቶስን ሥጋ ነው ይላል። እንዲሁም ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ግኖስቲኮችን ሲተች እነርሱ ቀርባን እውነተኛ አይደለም ይላሉ እኛ ግን በእርግጥም የሞተው የተነሣው ሥጋው ነው እንላለን እያለ ያስረዳል። እንዲሁም ሥጋውን እና መለኮቱን ተቀብለን ነፍሱን አንቀበለውም ማለት መለኮትን መክፈል ነው ፣ ምክንያቱም ነፍስ ከሥጋ ቢለይም መለኮት ከሥጋም ከነፍስም አልተየለም ፣ ስለዚህ መለኮቱን የምንቀበል ከሆነ ነፍሱ መለኮቱ ጋር የተዋሐደ ስለሆነ በመለኮት አንጻር እንቀበለዋለን ያለበለዚያ ከነፍስ ጋር የተዋሐደ መለኮት እና ከሥጋ ጋር የተዋሐደ መለኮት ብለን መለኮትን መክፈላችን ነው። እንዲሁም ቅዱስ ቁርባን "ለሥጋችን ፣ ለነፍሳችን ፣ ለመንፈሳችን ንጽሕና ቅድስና" ነው የሚለው ቅዳሴያችን ክርስቶስ ደግሞ ሁለንተናችንን ለማዳን ሁለንተናችንን ሆኗል "ያልተዋደውን አላዳነም" እንዲል ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ይህን ክርስቶስ የፈጸመውን ድኅነት በምሥጢራት በኩል ነው ምንቀበለውና ነፍስ የተለየው ክርስቶስን እንቀበላለን ማለት ነፍሳችን አይቀደስም ማለት ነው። ነፍስ ባይኖርም እኮ መለኮት አለ በመለኮት ነፍሳችን ይቀደሳል የሚል ሰው ካለ ደግሞ ታድያ ክርስቶስ መጀመሪያውኑ የሰውን ነፍስ መዋሐድ ለምን አስፈለገው? በመለኮቱ ብቻ አይቀድሰንም ነበር ያስብላል። ነገር ግን ይህን የምንዘጋው ምን ብለን ነው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተ መሥዋዕት ብቻ አይደለም ፣ እግዚአንሔር አብም የሞተ መሥዋዕት ብቻ አልተቀበለም ይልቅስ ክርስቶስ በትንሣኤው ሕያው መሥዋዕትን ነው ያቀረበው ፤ እኛም በቅዳሴ ጊዜ ከሰማያዊው የክርስቶስ አገልግሎት ስለምንሳተፍ የተነሣውንም ፣ የከበረውን ፍጹመ መለኮት ፣ ፍጹመ ትስብዕት ሥጋ እና ደም እንቀበላለን።

2. እኛ ሕጻናትን የምናጠምቀው ከአዳም የወረሱት ኃጢአት እና ፍዳ ተሽሮ በክርስቶስ ቅዱሳን እና ጻድቃን እንዲሆኑ ነው ፤ እንዲሁም ለአዲስ ልደት እና ለዘለዓለም ሕይወት ነው። ዓለም አቀፍ ጉባኤ የሆነው የኤፊሶን ጉባኤ ፣ በቅርጣግና የተደረገውን ጉባኤ ይቀበላል ቅርጣግና ጉባኤ ደግሞ ""የሕፃናትን ጥምቀት የሚክድ ወይም ደግሞ ጥምቀት ለኃጢአት ሥርየት ነው ብሎ ሕፃናት ግን ዳግመኛ በሚወልደው ውኃ መወገድ የሚያስፈልገውን ጥንተ አብሶ ከአዳም አይወርሱም ቢል ፤ ለኃጢአት ሥርየት ነው ማለቱ ሃሰት ነውና የተወገዘ ይኹን" ሲል ያስተምራል።
❤ 43 👎 5 👏 2
ኪ
21:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
እሺ ወንድሜ እሑድ ይድረስና በቁርባኑ እቀበላለሁ ፤ thanks for reminding tho 🫡
❤ 78 😁 22 🔥 6 😎 4 🥰 3 🫡 1
ኪ
22:11
ኪዳን ዘኢየሱስ
Waaqayyo isa abbootiin keenya osoo hin beekin waaqeffachaa turan, bara dhumaa kana keessa Ilma isaa isa dubara irraa dhalateen of nuuf mul'iseera. Erga mul'anni kun nuuf dhufee booda, Waaqayyo Abbaa Gooftaa fi Fayyisaa keenya Yesuus Kristos ni waaqeffanna malee, gara wallaalummaa kaleessaatti of duuba hin deebinu.
❤ 24 😨 1
ኪ
22:54
ኪዳን ዘኢየሱስ
1. ዳንኤል እውነት ለሁሉ- I don't have to explain this.

2. David Yeshua - Divinity of Christ ላይ መጻሕፍቶችን እንዳለ ጠጥቷል

3, መልሕቅ - እውነት ለመናገር logical and systematic way በሆነ መልኩ ስለሚያብራራ ለመሞገት ይመቻል

4. ቃሌ- ያው የነገረ መለኮት እውቀቱ የሚታወቅ ነው ያው አለቅ ያለችው ጴንጤነት አለች እንጂ 😁

5. Jonathan Lutheran - የአባቶች ትምህርት እና የሉተራን አስተምሮዎች ላይ ያለው እውቀት ጥልቅ ነው
👍 28 👏 5 🔥 2 ❤ 1 🌚 1
2 October 2026
ኪ
10:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
O
Orthodoxy eLibrary 01.10.2026 22:07:25
Please share this and do whatever you can to help.
❤ 29
ኪ
12:28
ኪዳን ዘኢየሱስ
12:28
In reply to this message
Manni Kiristaanaa keenya dogoggora kan hojjatte yeroo jalqabaa irrattidha. Yeroo ummata Waaqeffannaa keessa ture bishaan cuuphaatii fi humna Hafuura Qulqulluutiin ijoollummaa hafuuraa kennituufitti, aadaa ummatichaas cuuphdee (kiristiyaaneessitee) itti fufsiisuu qabdi turte malee, aadaa ummata kaabaa qofaan akka deeman dirqisiisuu hin qabne.

Mee yaadaa; Irreechi hundee isaa irratti galata Waaqayyoo ture mitii? Waaqayyo dhugaa kan ta'e, Abbaa Gooftaa fi Fayyisaa keenya Yesuus Kiristoosiif walitti qabamnee, aadaa keenyaan galata yoo dhiyeessine; akkasumas haroo irratti kadhannee, cuuphamnee, Qiddaasee qaddasiinee foonii fi dhiiga Gooftaa keenya Yesuusiin yoo fudhanne hammam bareeda? Galanni kana caalu hin jiru! Galanni kunis, jilbi hundi maqaa isaatiif akka jilbeenfatu fi afaan hundis 'Yesuus Gooftaadha' jedhee ragaa akka ba'uuf, Waaqayyo Abbaaf kan dhiyaatudha.

Garuu amma siyaasni waan keessa seeneef kana gochuun ulfaataadha. Gama biraatiin immoo, akka Abbootiin Niqiyaa nu barsiisanitti, amantaa biraa wajjin walitti makamnee kadhachuu, galateeffachuu fi waaqeffachuu hin qabnu. 'Yesuus Bi'eelzebul wajjin, ifni immoo dukkana wajjin tokkummaa maalii qaba?
❤ 8 👏 1
ኪ
12:48
ኪዳን ዘኢየሱስ
12:48
In reply to this message
🤣 44 😭 2
ኪ
14:42
ኪዳን ዘኢየሱስ
አሁን ደግሞ ሌላ መክሰሻ አገኛችሁ ስም ከመስጠት ውጪ ምንም ነገር አታውቁም አይደል? ለሀበሻ ምንም ነው የማይሆነው የምር ፤ እኔ እኮ በሰላም ለራሴ እያመለኩ መኖር እችላለሁ ፤ እነዚህ ነገሮች ላይ የምለፋው ተከፍሎኝ ይመስላችኋል እንዴ?

ኧረ ወዲያ እኔ ከአሁን በኋላ አርፌ ራሴን heal ማድረግ እና መንፈሳዊ ሕይወቴን ማሳደግ ላይ እሠራለሁ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ።
😭 17 😁 10 😢 4 💔 3
ኪ
15:09
ኪዳን ዘኢየሱስ
ይሄን ብቻ ተናግሬ ልፈጽም ከላይ ያስቀመጥኩት በቃ የመጨረሻ ሆነኝ እንጂ እነዚህ ክሶች የሚመጡት ከአንድ ሰው ብቻ አይደለም እዚሁ ጋር ራሱ ይሄ ያሳያል። Almost half comments እንደዛ ናቸው። ይሄ ደግሞ ያጋጠመው በሚዲያው ብቻ ቢሆን ምንም አይሆንም ነበር ነገር ግን በአካል ጓደኛ የምለው ሰው ራሱ በቅርቡ ብዙህ ክሶችን ተናግሮኛል። ሌሎችም ጓደኞች ብዬ ያሰብኳቸው እዚሁ ሚዲያ ላይ የምታውቋቸው ከጀርባዬ ብዙህ ክስ ሰምቻለሁ። (ጓደኛ ነው ብለህ ያሰብከው ሁሉ ጓደኛ አለመሆኑን ያስረዳሉ።)

እኔ እዚህ ላይ ያለሁት ተመችቶኝ ወይ ጊዜ ተርፎኝ አይደለም ይልቅስ ለዓመታት በmental health condition struggle እያደረኩ እንጂ። በmental healthኤ ምክንያት አይደለም አፖሎጄቲክስ ማቆም ብቻ ፣ ሕይወቴን ራሱ ላጣ ደርሼ ነበር። ከዚህ በፊትም የማቆሙን ሃሳብ ያመጣሁት ከዚሁ የተነሣ ነበር። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ አቆማለሁ እያልኩ እየተመለስኩ ብመጣም ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን መሳተፌን ይዘው የቅርብ ጓደኞች እስክላቸው የነበሩ ሰዎች በቤተክርስቲያን ጥላቻ ሲከሱኝ የነበረው። ማንም ግን ያለሁበትን ሁኔታ ራሱ ለመጠየቅ አልሞከረም እንኳን ለመረዳት።

ብቻ እንደ ተረዳሁት ከሆነ ለአእምሮ ጤናዬ ጥሩ አይደለም ይሄ environment በሙሉ ስለዚህ ጤናዬን ለመጠበቅ ስል ራሴን አገላለሁ።
😢 14 🥱 3 😨 3 💔 2 ❤ 1 ❤‍🔥 1
15:09
15:09
ኪ
15:35
ኪዳን ዘኢየሱስ
In reply to this message
Please አሁንም ሰው ስለተናገረህ ፣ ትችት ስለገጠመህ ምናምን እያላችሁ በውስጥ አትምጡብኝ እኔ ዋናው ምክንያቴ ጤናዬ ነው this toxic environment is negatively affecting my mental health which I was already struggling with these past 2 years. I won't go into details but I barely survived until now. ስለዚህ ራሴን heal ለማድረግ ከ toxic environment መራቅ አለብኝ። ስለዚህ ሰው ስላለህ ምናምን አትበሉኝ ሰው ሳይልም በፊት ለማቆም እያሰብኩ ነበር (ከዚህ በፊትም አቁሚያለሁ ብዬ የነበረው በዚሁ ነው ፣ ቲክቶክም ያቆምኩት በዚሁ ነው) ነገር ግን ይሄ toxic environment ይበልጥ መኖር እንደሌለብኝ ነው እና ብቻ ጌታ ኢየሱስ ይሁነን።
👍 8 ❤ 6 🔥 1 🤗 1
15:47
እና የቻናሉን files እና ጽሑፎች export እያደረኩት ነው ልክ export አድርጎ እንደጨረሰ አጠፋዋለሁ እና ቻናሉን ብቻ ጌታ ኢየሱስ ሁላችሁንም ይጠብቃችሁ
😭 12 💔 2 😢 1